Addis Ababa City Manager Office
1.47K subscribers
20K photos
570 videos
49 files
1.19K links
Download Telegram
በታላቁ ሩጫ ፤ታላቅ የህዝብ ስሜት
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በደማቅ ሁኔታ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በተሳተፉበት በተካሄደው "ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ" ላይ በደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ዑደት ስራ ላይ የተሰማሩ ማህበራት ቆሻሻን በመሰብሰብ ባሳዩት ትጋት ከፍተኛ ገቢ ማግኘት ችለዋል።
የማህበራቱ ጥረት ለከተማው ጽዳት ጥረት ትልቅ ድጋፍ ሲሆን፣ የስፖርቱን ደስታ ከአካባቢ ንጽህና እና ከገቢ ማስገኛነት ጋር ባገናኘ መልኩ ትልቅ ትምህርት ሰጥቷል።
"ብዙ የሰበሰበ ብዙ አገኝ" የሚለው መርህ በደማቅ ሁኔታ ሩጫው በተካሄደበት ወቅት ታዳሚዎች የተጠቀሙባቸውን ያገለገሉ የፕላስቲክ ጠርሙሶች ወዲያውኑ በመሰብሰብ ረገድ የማህበራቱ ሚና እጅግ የጎላ ነበር።
በተለይም የ'ሀይላንድ' ውሃ ጠርሙሶችን ለመሰብሰብ ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ቆሻሻ ወደ መልሶ ማምረቻ ግብዓትነት እንዲለወጥ አድርገዋል።
ህጋዊ ባጆችን በመጠቀም በስርዓት ሲሰሩ የዋሉት እነዚህ ማህበራት፤ ከፍተኛ ገቢ በማስገኘት ለራሳቸው ብልጽግና መሰረት ከመጣልም በተጨማሪ የከተማዋ ጽዳት እንዳይጓደል እና የአካባቢ ብክለት እንዳይፈጠር በመከላከል ለአካባቢ ፅዳት ትልቅ ድርሻ ተወጥተዋል።
ይህ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ትልቅ የኢኮኖሚ ዕድል መፍጠሩ ብቻ ሳይሆን፣ የደረቅ ቆሻሻን ችግር ወደ "ብልፅግና ዕድል" መቀየር እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ስኬታማ ምሳሌ ሆኗል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በአንድ ላይ የሚያሰባስብበት መድረክ መሆኑ ለፕላስቲክ መልሶ መጠቀም ስራውም ታላቅ ሽፋን በመስጠት፣ የአካባቢ ንቃተ-ህሊናን ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ እገዛ አድርጓል።
ህዳር 4/2018 አ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ዛሬ ህዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ስራ ለማከናወን በአዲስ አበባ እና ሸገር አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ኃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች :-
👉ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 8፡30 በመርካቶ፣ አብነት ሆቴል፣ ሞላ ማሩ፣ ተ/ኃይማኖት ፔፕሲ ፋበሪካ ፣ሰባተኛ በከፊል፣አማኑኤል ሆስፒታል፣ ሻወል ደማ ት/ቤት፣ በመሳለሚያ፣ አማኑኤል ቤተክርስትያን እስከ ኮካ፣
👉 2፡30 እስከ 10፡00 በሰበታ ከተማ ፣ አቀበና ውሃ ማምረቻ ፣ ዲማ ሆስፒታል፣አኔ ዲማ፣ ወጣቢቻ፣ ጉዱ፣ ሙሎ፣ ከሚሴ፣ድሬ ከአስፋልት በላይ፣ ገፈርሳ ውሀ ግድብ እና አካባቢው፣ ሲሊ፣ ከረላ፣ መናገሻ ፣ከሰብስቴሽን ፣ ባቡር ሐዲድ፣ ሲዳሞ አዋሽ፣ ገንደ ቆሬ፣ ገላን መኖሪያ ቤቶች፣ ገመዳ ማህበር፣በላይነህ ክንዴ፣ በስተቀኝ ያሉ ኢንዱስትሪዎች በሙሉ፣ ካፍ ማደያ አካባቢ፣ ብርጭቆ፣ አስኮ 40/60 ኮንዶሚኒየም፣ ዓለም ባንክ
👉ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 9፡30 በሰሜን ማዘጋጃ፣ ሸገር መናፈሻ፣ መስቀሉ ሥጋ ቤት፣ ዳዊት ፋርማሲ፣ ዕንቁላል ፋብሪካ አካባቢ፣ አባዲና ፣ ሩፋኤል ቤ/ክ አካባቢ እና አካባቢው ላይ የኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ Ethiopian Electric Utility -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
ስለሆነም አገልግሎቱ በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን ብሏል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ሳምንታችንን አጨልመን አንጀምርም!
የሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ ለእኛ ፍካትና ተስፋ የሚሰጠን ቀን ነው!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
‘ወርቃማ ሰኞ’ የሚል መጠሪያ የተሰጠውና በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ዘወትር ማለዳ የሚካሄደው የመማማሪያ መርሃ-ግብር ሁለተኛ ዓመት ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተከብሯል። ይህ ከሁለት ዓመት በፊት በክብርት ከንቲባ ሃሳብ አመንጭነትና መሪነት የተጀመረው መርሃ-ግብር ‘ጥቁር ሰኞ’ን ወደ ‘ወርቃማ ሰኞ’ የቀየረ ሆኗል። የከንቲባ ጽ/ቤት፣ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ የሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤትና የኮሙኒኬሽን ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የሚሳተፉበት ‘ወርቃማ ሰኞ’ ሦስት ግቦችን (ከተማችንን የብልጽግና ተምሳሌት እናደርጋለን፣ ስንተባበር ለውጥ እናመጣለን እና እዚህ ያለነው ለማገልገል ነው) በማነገብ የተጀመረ ነው።
በሁለተኛ ዓመት ክብረ በዓል አከባበር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሳምንቱን መጀመሪያ ሰኞን በፍካትና በተስፋ እንጂ አጨልመን አንጀምረውም ብለዋል። ይህ ለራስ እድገት አስፈላጊ የሆነው መርሃ-ግብር በአሁኑ ሰዓት ወደ ሁሉም የከተማዋ መዋቅሮች እንደተስፋፋ እና እየተተገበረ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
በዕለቱ ከክብርት ከንቲባ መልዕክት ባሻገር ‘ወርቃማ ሰኞ’ በሚል ርዕስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቲያትርና ባህል አዳራሽ ተውኔት ያቀረበ ሲሆን የሁለተኛ ዓመት የመርሀ-ግብሩ ጉዞም ለታዳሚው በገለጻ መልክ ቀርቧል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረው የፀረ-ሙስና ቀን "ትዉልድን በስነ ምግባር ተቋምን በአሰራር ‶ በሚል መሪ ቃል ተከበረ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት የፀረ ሙስና ቀንን አስመልክት በአለም ለ22ኛ ጊዜ በሀገራችንን ለ21ኛ ጊዜ አስመልክቶ ከፅ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር በዛሬዉ እለት ተከብሮ ዉሏል።
በዚሁ መድረክ የሰነ-ምግባር እና የፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክተር አቶ ምህረቴ ሙሉሰዉ በዚሁ መድረክ እንደተናገሩት ሙስና ደረጃው ይለያይ እንጂ በሁሉም የዓለማችን ሀገራት የሚገኝና የሁሉም ሀገራት ተግዳሮት መሆኑ ገልፀው እንደ ሀገር የሙስና ሂደቱን ለመቀነስ በጋራ እንዲሁም የተጠናከረ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ተናግረው እንደ ከተማ ትውልድን በፀረ ሙስና ትግል ግንባታና በስነ ምግባር የታነፀ እና ሙስናናን የሚፀየፍ ትዉልድ ለመፍጠር እንደ ተቋም ሰፊ ሰራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃና በከተማችን የፀረ ሙስና ትግል የእስካሁን እንቅስቃሴ ጥሩ የሚባል ጅማሮ ሲሆን በተለይም አዲስ አበባ ከተማ የሙስና ወንጀልን ለመከላከል በልዮ ትኩረት የሰነ-ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ተቋማት፣የሲቪክ ማህበራት፣የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል እና መዋቅሮችን በመዘርጋት ሙስናን መከላከያ ይገባል ሲሉም አመልክተዋል።
አክለዉም በተቋማት የስነ-ምግባር እና የፀረ ሙስና ትግል ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ ሰራዎች ወደ ተግባር በመቀየርና ተቋማትም የሚሰጡ አገልግሎቶች ከብልሹ አሰራር የፀዳ ለማድረግ ሁሉም አካላት በሙስናን በመታገልና በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በዚሁ መድረክ የስነምግባር ምንነት፣ብልሹ አሰራርን የመቀነስ መንገድ፣የስነምግባር መርሆች፣የስነምግባር ምንጮች፣ሙስና የሚያስከትለው ጉዳት፣የሙስና የመከላከያ ስልቶች፣የፀረ ሙስና ትግል ሁኔታዎች በእነዚህና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች የፅ/ቤት የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት በአቶ አለማየሁ ሙላት ሰነድ ቀርቦ ዉይይት ተካሂዶበት መድረኩ ተጠናቋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager