ሙሉጌታ ንጉሴ ታደሰ ጠበቃ ና የህግ አማካሪ
62 subscribers
60 photos
4 videos
48 files
202 links
በማንኛውም ፍ/ቤት ጠበቃ ና የህግ አማካሪ ስልክ 0936695274/0960024515
Download Telegram
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ፅ/ቤት የአሰራር ስርዓት መመሪያ ቁጥር 26/2017 ዓ.ም አውጥቷል።

ይህ መመሪያ በተለይም የፍርድ ቤት ክርክር ከተጠናቀቀ እና የፍርድ ባለዕዳ እና የፍርድ ባለመብት ከተለየ በኋላ በቀጣይ የሚከናወነውን የተሰጠውን ፍርድ የማስፈፀም ሂደትን በተመለከተ ለዚሁ ዓላማ የተቋቋመው እና በኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር ያለው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ፅ/ቤት ያለውን ሚና እና ፍርድን በማስፈፀም ሂደት ውስጥ ሊከተላቸው የሚገቡ የአሰራር ስርዓቶችን ያካተተ ነው።

መመሪያው በዋነኛነት የፍትሃብሄር አፈፃፀም ትዕዛዝ የተሰጠበትን ፍርድ ፍትሃዊ፣ግልፅ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ ማስፈፀም፤ የፍርድ ቤት ትዕዛዞች በአግባቡ መከበራቸውን ማረጋገጥ እና የተከራካሪ ወገኖችን መብት ማክበርና ማስከበር እንደዚሁም የፍርድ ቤት ትዕዛዞችን ተፈፃሚነት በማረጋገጥ ሕብረተሰቡ በፍርድ ቤት ላይ ያለውን አመኔታ ከፍ ማድረግ የሚሉትን ዓላማዎች ያነገበ ሲሆን መመሪያው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግልፅነት እና ተጠያቂነት የተላበሰ አሰራር ለመዘርጋት የሚያካሂዳቸው የለውጥ ስራዎች አንዱ አካል ነው።

ተገልጋዮችም ይህንን መመሪያ መሰረት በማድረግ ከመመሪያው ውጪ የሚያጋጥማቸውን እንቅፋትም ሆነ ያስተዋሉት ችግር ካለ በመመሪያው በተቀመጠው የቅሬታ ማስተናገጃ እና መፍቻ ስርዓት በመጠቀም መፍትሄ የሚያገኙ መሆኑን እና መመሪያው በክቡር የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ተፈርሞ ከፀደቀበት ከነሃሴ 30 ቀን 2017 ዓም ጀምሮ ተፈፃሚ መሆን የጀመረ መሆኑንን እየገለፅን የመመሪያውን ሙሉ ይዘት እነሆ እንላለን።

የመመሪያውን ሶፍት ኮፒ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/fscethiopiaPR በመግባት ማግኘት ይችላሉ።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት