ዝንቅ መዝናኛ
3.92K subscribers
827 photos
128 videos
14 files
32 links
«ኢትዮጵያችን እራሷ ዝንቅ ናት!»

Join via Link

https://t.me/+Q_0RbUjl6KtNPpK4
Download Telegram
Channel photo updated
ማስክ አድርጎ መተቃቀፍ?

ዋናዉ ምነ ሆነና?

አይ ደጉ ህዝቤ... 😭
ከታክሲ ረዳቶች ጋር ሳንቲም ስንቀባበል ያለዉ ነገር እራሱ ከመጨባበጥ አይተናነስም!!
"እሩቅ ምስራቅ ሳለሁ ጃፓንዋን ወድጄ." የሚለው ዘፈን ከድሮም አይመቸኝም ነበር..!😏😁


@ZiniQ for more
ይሄው ቢሮ በቫይረሱ ምክንያት ሁላችንም አረቄ ጠጥተን ገብተን እየተደባደብን ነው። .... አይ ለትንሽ አለቃዬን በስቴፕለር ሳትኩት! ቆይማ በፕሪንተር ደግሞ ልሞክረው ....

ትላንት ጤና ጥበቃ ባያሳዉቅ ኖሮ
አዳሜ ዛሬ ሰላምታሽ የጦፈ ነበር.....🤪
ቀን ጥሎ ቀን ቢጥላት!
የኛን ድመት አይጥ በላት!.....


@ZiniQ for more
አስባቹታል
እንዴት ሀብታም ሆንክ ሲባል?
ኮሮና የመጣ ወቅት ጭምብል እና ጓንት
በብዛት እና በአሪፍ ዋጋ ሼጬ.....🤪🤪🤣
ይሄ አሁን ኮሮና በመምጣቱ
ሳይደሰት ይቀራል...🤨

@ZiniQ for more
Tip for the rest of your life
በህይወትህ ብዙ ስህተት ልትሰራ ትችላለህ ግን አደራ በፍፁም ገላጋይ የሌለበት ቦታ እንዳትደባደብ

@ZiniQ for more
4 ደርሷል 😔😔😔
ሴት ልጅ ስትወድህ ባትወዳት እንኳን አክብራት... ይገባታል!!

ሴት ልጅ እየወደድካት ባትወድህ እንኳን አክብራት... ይገባታል።

ስታከብራት ግን ካልገባትና ፈረንጆቹ እንደሚሉት if she starts to take it for granted ይሄን ብይ 💪 ብለህ አስቀይማት 😂😁😁😂 የዛኔ ከተኛችበት ትነቃለች 😁😂😁 ማክበርህ ምርጫህ እንጂ ግዴታህ እንዳልነበረ ትረዳሃለች።

ብልህ ሴት ግን ከነዚህ ሁሉ በላይ ነች 😊 አፈጣጠሯም ከቃላት በላይ ነዉ፤ ላገኛትም ወንድ በረከት ናት። የምትሰጠዉም ከፈጣሪ ብቻ ነዉ።

ሰላም እደሩ!!
ኮሮናን በጋራ እንከላከል። ጥንቃቄ አይለየን!!

@ZiniQ ዝንቅ መዝናኛ
ብዙ ሰዉ በኮሮና በሽታ ዙሪያ "ኧረ ፀሎት እንደመፀለይ ሚም አትስሩ። ይህ የሚቀለድበት በሽታ አይደለም" እያለ ሲፖስት እያየዉ ነዉ። አንዳንዱ እንደዉም ለመሳደብ የተፈጠረ ስለሆነ ይቺንም ምክንያት አድርጎ አፉን ይካፈታል። እኔ ግን ስሩ ብዬ አበረታታለሁ። በ2 ምክንያቶች

1. ሰዉ ስለ ኮሮና ከበሽታዉ ይልቅ psychological ጉዳቱ እየገደለዉ ስለሆነ ፍርሃቱን በሳቅ ይቀንሳል ብዬ አስባለሁ።

2. ስለበሽታዉ እንደቀልድም ቢሆን የሚተላለፉት መልዕክቶች 2 ገፅ ስለ ኮሮና ከሚፃፈዉ ፅሑፍ በላይ ተደራሽነትና ተነባቢነት ስላለዉ awareness'ሱን ይጨምረዋል።

ስንቴ አይደል እንዴ የሰይፉ ሾዉ ላይ ምን እንደተባለ ማን እንደቀረበ ሚም ብቻ አይተን የምንረዳዉ? Meme is a tool for now.

ነገር ግን ከሚሙ በተጨማሪ እነዚያን ረጃጅም ፅሑፎች ታማኝ ሚድያዎች ላይ ስታገኙ ብታነቧቸዉ ታተርፋላችሁ እንጂ አትጎዱም። በተለይ ደግሞ family ዉስጥ አዛዉንቶች ያሏችሁና ከያዛቸዉ ብላችሁ በፍርሃት የምትጨናነቁ ወጣቶች!

በሉ በጥንቃቄ ዋሉ!! ፀሎትም አትርሱ!!
ፈጣሪ በምህረቱ ስለሀገራችንም ስለአለማችንም መልካም ዜና ያሰማን።
አሜን!! 🙏

@ZiniQ ዝንቅ መዝናኛ
ታክሲ ዉስጥ ከተዋወኳት ጡታም ቺክ ጋር ሁለት ፌርማታ ያህል "ስለ ኮሮና ቫይረስ ታሪካዊ አመጣጥና አሁን ስለደረሰበት ደረጃ" በሰፊዉ ካወራን በኃላ ልትወርድ ስትል በማኪያቶ ዙሪያ ዉይይቱን ለመቀጠል ተስማምተን ስልኳን ጠይቄያት እየነገረችኝ ሳትጨርስ ከታክሲዉ ወረደች። አንገቴን በመስኮት አዉጥቼ "ኧረ ቁጥሩን አልጨረሽም ኪያዬ" ከማለቴ ታክሲዉ ጉዞ ጀመረ። እሷም አላሳፈረችኝም እየጮኸች "ሁለት አንድ ሁለት ሰባት" ስትል ሰሟኃት። ግን ልፅፈዉ ወደ ስልኬ ሳጎነብስ ግራ ገባኝ

ሁለት አንድ ሁለት ሰባት ማለት 😏🤔

2127 ነዉ ወይስ
1127 ወይስ
1177 ወይስ
2177? የቱን ብዬ ልፃፈዉ? 🤷‍♂
🤔🤔😡🤕

@ZiniQ ዝንቅ መዝናኛ
አብዛኛዉን ፐርሰንቶች አሟላለዉ ብዬ ነዉ ማስበዉ። በጣም እጄን እታጠባለሁ። ሳሙና አለኝ። የደረቴንም አጥንት በአልኮል አጥባለሁ። ቆዳዬ በጣም ንፁህ ነዉ። አይኔን በጣም አልነካካም። ስለዚህ ቢያንስ 70% የአለም አቀፍ ጤና ድርጅት መስፈርት አሟላለሁ።
😂😁😂😁

#CoronaVersion

@ZiniQ ዝንቅ መዝናኛ
መገናኛ አከባቢና ኢንስታግራም ላይ የሚዉሉ ሰዎች ግን ስለ ኮሮና መግባት እስካሁን የሰሙ አይመስለኝም። የመገናኛ አከባቢ ሰዎች እስካሁን ዕለታዊ ሩጫ ላይ ናቸዉ። የኢንስታግራሞቹ ደግም ከቫኬሽን ገና አልተመለሱም። ለሁለቱም እንዴት አድርጌ በኢትዮጵያዊ ባህል ሳላስደነግጣቸዉ እንደምነግራቸዉ ቀኑን ሙሉ ሳሰላስል ነዉ የዋልኩት።
😠🙁😕😟

@ZiniQ ዝንቅ መዝናኛ
ሰሞኑን በሶሻል ሚድያ ለሚመላለሰዉ የፌጦ ጉዳይ የተሰጠ መልስ

እኔም ደግሞ እንደሁልጊዜዉ ዛሬም ልበላችሁ

"ኧረ በፈጠራችሁ ኧረ እንደዉ በመፅሐፉ በኃይማኖት ስም ማንም የሚነዳን አህዮች አንሁን!! ግድ የላችሁም ጭንቅላታችንን እንጠቀም፤ ኃጢአት አይሆንብንም።"
አቦ ጭንቅላትህ አይጣላህ ብቻ ወንድሜ 😁

የእሁዷ አርቲስት የሰኞዋ መልዕክተኛ የፖሰተቺዉ ነዉ
ዝንቅ መዝናኛ
አቦ ጭንቅላትህ አይጣላህ ብቻ ወንድሜ 😁 የእሁዷ አርቲስት የሰኞዋ መልዕክተኛ የፖሰተቺዉ ነዉ
ለማንኛዉም እንዲህ አይነት ዜና ዉሸትና ክብረ ቢስ ከመሆኑም ባሻገር የማይታወቅ combination ስለሆነ ለጤናችን ያላሰብነዉን ጉዳትም ሊያስከትል ስለሚችል እባካችሁ ጥንቃቄ እናድርግ!! በተለይ አዛዉንቶች ቤቶቻችን የሚገኙ ወጣቶች ተሳስተን እነሱንም ወደ ጉዳት እንዳንከታቸዉ እንጠንቀቅ። ሶሻል ሚድያዉ ላይ ያለዉን ያልተረጋገጠዉን ሁሉ እንደወረደ ከማቅረብና apply ከማድረግ እንቆጠብ።

ፈጣሪ በምህረቱ ይጠብቀን! ፀሎትም አንርሳ!
በተረፈዉ ንፅህናችንና ቅርርባችን በማስተካከል በሽታዉን እንከላከል።

@ZiniQ ዝንቅ መዝናኛ
ዝንቅ መዝናኛ
Photo
#ጠቃሚ_መረጃ
#ለአዲስ_አበባ_ነዋሪዎች

በሀገር ውስጥ የተመረተ የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በከተማዋ ወደሚገኙ የከነማ ፋርማሲዎች እና ጤና ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡
በከተማዋ እየተሰራጨ ያለው የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር 200ሺህ ሊትር የሚሆን ሲሆን በከነማ ፋርማሲዎች ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ ይሆናል፡፡

ከነገ ጀምሮ ህብረተሰቡ ከከነማ ፋርማሲዎች የንጽህና መጠበቂያውን ማግኘት እንደሚችል ማሳወቅ እንወዳለን፡፡

© የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ዝንቅ መዝናኛ pinned «#ጠቃሚ_መረጃ #ለአዲስ_አበባ_ነዋሪዎች በሀገር ውስጥ የተመረተ የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በከተማዋ ወደሚገኙ የከነማ ፋርማሲዎች እና ጤና ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡ በከተማዋ እየተሰራጨ ያለው የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር 200ሺህ ሊትር የሚሆን ሲሆን በከነማ ፋርማሲዎች ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ ይሆናል፡፡ ከነገ ጀምሮ ህብረተሰቡ ከከነማ ፋርማሲዎች የንጽህና መጠበቂያውን ማግኘት…»