ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ
30.6K subscribers
122 photos
3 videos
61 files
4 links
Philosophy For Higher Consciousness
Download Telegram
ከልዩነት ባሻገር!

ልዩነቱ የዘር፣ የቋንቋ፣ የመልክ፣ የቁመናም ሆነ የእምነት . . . ከእናንተ ለየት የሚለው ሰው በአካባቢያችሁ ሲሰራም ሆነ ሲኖር፣ ለየት ያለ ሰው በመሆኑ ምክንያት ከእናንተ ምንም አይነት ጥቃት፣ በደልና መገለል እንደማይደርስበት እንዲሰማው የማድረግ ሃላፊነት እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ፡፡ ይህንን ሃላፊነት መወጣት የትክክለኛ ስብእና ምልክቱ ነው፡፡

የእኛ ዘር፣ ቋንቋ፣ መልክ፣ ቁመና እና እምነት ያለው እኛን መሰል ሰው የሚጠቃበት፣ የሚበደልበትና የሚገለልበት አካባቢ እንዳለ አትዘንጉ፡፡ እኛ እዚህ በሌላው ላይ የምናደርገውን ሌሎች እዚያ በእኛ እና እኛን በመሰሉት ላይ ያደርጉታል፡፡ ዑደቱ ይኸው ነው፡፡

የጨዋነት ሁሉ ጨዋነት ከእኛ ለየት ያሉትን የመቻልና የመቀበል ጨዋነት ነው!

ዶ/ር እዮብ ማሞ
@zephilosophy
👍85
"I am the Now. I Am’

Eckhart Tolle

🌘On the surface it seems that the present moment is only one of many, many moments. Each day of your life appears to consist of thousands of moments where different things happen. Yet if you look more deeply, is there not only one moment, ever? Is life ever not this moment? This one moment, now, is the only thing you can never escape from. The one constant factor in your life. No matter what happens. No matter how much your life changes. One thing is certain. Its always now. Since there is no escape from the now, why not welcome it, become friendly with it.

💫When you make friends with the present moment, you feel at home no matter where you are. When you don't feel at home in the now, no matter where you go, you will carry unease with you. The present moment is as it is, always. Can you let it be?

🌓The division of life into past, present and future is mind made, and, ultimately, illusory. The past and future are thought forms, mental abstractions. The past can only be remembered Now. What you remember is an event that took place in the Now and you remember it Now. The future, when it comes, is the Now. So the only thing that is real, the only thing that ever is, is the Now.

💫To have your attention in the Now is not a denial of what is needed in your life. It is recognizing what is primary. Then you can deal with what is secondary with great ease. It is not saying, “I’m not dealing with things anymore because there is only the Now.” No. Find what is primary first, and make the Now into your friend, not your enemy. Acknowledge it, honor it. When the Now is the foundation and primary focus of your life, then your life unfolds with ease.

💫Almost everyone lives like this most of the time. Since the future never arrives, except as the present, it is a dysfunctional way to live. It generates a constant undercurrent of unease, tension, and discontent. It does not honor life, which is Now and never not Now. When your attention moves into the Now, there is an alertness. It is as if you were waking up from a dream, the dream of thought, the dream of past and future. Such clarity, such simplicity. No room for problem making. Just this moment as it is.

🌘When you step into the Now, you step out of the content of your mind. The incessant stream of thinking slows down. Thoughts don’t absorb all your attention anymore, don’t draw you in totally. Gaps arise in between thoughts–spaciousness, stillness. You begin to realize how much vaster and deeper you are than your thoughts. Thoughts, emotions, sense perceptions, and whatever you experience make up the content of your life. “My life” is what you derive your sense of self from, and “my life” is content, or so you believe.

💫You continuously overlook the most obvious fact: your innermost sense of I Am has nothing to do with what happens in your life, nothing to do with content. That sense of I Am is one with the Now. It always remains the same. In childhood and old age, in health or sickness, in success or failure, the I Am–the space of Now– remains unchanged at its deepest level. It usually gets confused with content, and so you experience I Am or the Now only faintly and indirectly, through the content of your life. In other words: your sense of Being becomes obscured by circumstances, your stream of thinking, and the many things of this world. The Now becomes obscured by time.

🌘And so you forget your rootedness in Being, your divine reality, and lose yourself in the world. Confusion, anger, depression, violence, and conflict arise when humans forget who they are. Yet how easy it is to remember the truth and thus return home: I am not my thoughts, emotions, sense perceptions, and experiences. I am not the content of my life. I am Life. I am the space in which all things happen. I am consciousness. I am the Now. I Am.
🌔💫🌔💫🌔💫🌔💫🌔💫

@zephilosophy
👍6🔥5👏1
Harmony & Order
(ስምምነትና ስርዓት)

በሶክራተስም ሆነ በፕላቶ ዕምነት የሰው ልጅ ሁሉ ችግር የማሰብ ኃይል ችግር ወይም የዕውቀት ችግር ነው። ዕውነተኛ ዕውቀት በሶክራተስም ሆነ በፕላቶ ዕምነት ትምህርት ቤት የምንማረው ወይም ሸምድደን እንደ ዳዊት የምንደግመው አይደለም። በሁለቱም ዕምነት ሆነ ኋላ ብቅ ባሉት የአውሮፓ ፈላስፋዎችና ተመራማሪዎች፣ ዕውነተኛ ዕውቀት ማለት ራሳችንን እንድናውቅ የሚያደርገንና፣ ወደ ውስጥ ራሳችንን ለመመልከት እንድንችል የሚያደርገን፣ የበለጠ ራሳችንን እንድንጠይቅ የሚያስችለን፣ የተፈጥሮን ህግጋት ጠለቅ ብለን እንድንረዳ የሚያስችለንና፣ በጥንቃቄም በተፈጥሮ ውስጥ ያሉትን ነገሮች በማውጣትና ቅርጻቸውን በመለወጥ እንድንጠቀምባቸው የሚያግዘን፣  ህብረተሰብን በስነ-ስርዓትና መልክ ባለው ሁኔታ እንድናደራጅ የሚረዳን፣ ከሰውነታችን ፍላጎት ይልቅ የመንፈስን የበላይነት በማረጋገጥ በመንፈስ ኃይል በመመራት ከሌላው ተመሳሳይ ሰው ጋር ተሳስቦ መኖር መቻል፣ በፍጹም የራስን ጥቅም በማስቀደም ዓላማ አለመመራት…ወዘተ. ናቸው።

የማንኛውም የሰው ልጅ ፍጡር ጥረት አርቆ በማሰብ ኃይል በመመራት ወደ እግዚአብሄር ለመጠጋት መጣር ነው። በፕላቶ ዕምነት ሌላው ለአንድ ህብረተሰብ ምስቅልቅል ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ ወይም ለጦርነት ምክንያት የሚሆኑ ከሰብአዊነትና ከወንድማማችነት ይልቅ የብሄረ-ሰብ/ጎሳነት(Ethnic Solidarity) ምልክት የሆኑ ቅስቀሳዎች ቦታ ከተሰጣቸው ነው። በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ለሚከሰት ችግር ዋናው ምክንያት የተለያዩ ብሄረሰቦች በመኖራቸው ወይም አንደኛው ብሄረሰብ በሌላው ላይ ጫና ስለሚያደርግ ሳይሆን፣ በስልጣን ላይ ያሉ ኃይሎች ራሳቸው በሚፈጥሩት ልዩነትና ስልጣን ላይ ለመቆየትና ህዝቡን አደንቁረው ለዘለዓለም ለመግዛት እንዲችሉ የብሄረሰብን ጥያቄ እንደ ፖለቲካ መሳሪያ አድርገው  ሳይንሳዊውንና የስልጣኔውን ፈለግ ያሳስታሉ። ስለዚህም ለአንድ ህብረተሰብ ችግር ዋናው መፍትሄ እያንዳንዱ ግለሰብ ከሌላው የማይበልጥ መሆኑን ሲረዳና፣ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የተለያዩ ብሄረሰቦች መኖር የታሪካዊ ግዴታ እንጂ እንደክፋት መታየት የሌለባቸው መሆኑን ሲገነዘብ ነው። በተጨማሪም ተፈጥሮ ውስጥ የተለያዩ ነገሮች፣ ለምሳሌ የተለያዩ አበባዎች፣ የተለያዩ ዛፎችና የተለያዩ አራዊቶች መኖር የተፈጥሮን ውበት እንደሚያመለክቱና የተፈጥሮም ግዴታ የሆኑትን ያህል ሁሉ፣ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥም የተለያዩ ብሄረሰቦች፣ ጥቁርና ቀይ መልክ  ያለው ሰው፣ ረዥምና አጭር ሰው… ወዘተ. መኖር እንደ ውበት መታየት ያለባቸው ነገሮች ናቸው። ስለዚህም በአንድ ህብረተስብ ውስጥ የሚከሰቱ ብጥብጦች የተፈጥሮን ውስብስብነትና ውበት ለመረዳት ካለመቻልና ጠለቅ ብሎ ለማየት ካለመፈለግ የተነሳ ወይም በተሳሳተ ዕውቀት በመመራት አንድን ህብረተሰብ ለመግዛት መቻኮል ነው። ለዚሁ ሁሉ መፍትሄው ይላል ፕሌቶ፣ ማንኛውም ግለሰብ አርቆ አሳቢነትን በማስቀደም በመፈቃቀር ላይ የተመሰረተ ህብረተሰብ ለመግንባት መጣር ነው። ማንኛውም ግለሰብ ይህንን የዩኒቨርስ ህግ ሲረዳና  ስምምነትንና ስርዓትን(Harmony and Order) በጭንቅላቱ ውስጥ ሲቀርጽ በምድር ላይ ዕውነተኛውን ገነት ይመሰርታል።

ዶ/ር ፍቃዱ በቀለ

@zephilosophy
👍16🔥21
የበታችነት ስሜት አይሰማችሁ

በአንዲት ጠብታ ውስጥ ያለው፣ በውቅያኖስ ውስጥም አለ፡ ዮጋ ይህንን ሱትራ ሁልጊዜም የሚናገር ቢሆንም ሳይንስ የደገፈው ግን በቅርቡ ነው፡፡ አንድ አተም በውስጡ ይህን ሃይል ይይዛል ብሎ ማንም አስቦ አያውቅም፡፡ በዚህ እጅግ በጣም ትንሹ በሆነው የቁስ ክፍል ውስጥ ይህ ሁሉ ሃይል ተደብቆ እንደሚገኝ ማንም አስቦ አያውቅም።

ይህ የዮጋ እይታ ሳይንሳዊ መሆኑ የተረጋገጠው አተምን ወደ ንዑስ አተምነት በመከፋፈል በተደረገው ጥናት ነው፡፡ አንድ አተም በአይን አንኳን ሊታይ አይችልም፤ ይሁን እንጂ በዚህ በአይን በማይታይ አተም ውስጥ ግዙፍ ሃይል አለ፡፡

በሰው ውስጥም የነፍስ አተም በአይን አይታይም። ሆኖም ግን እጅግ በጣም ግዙፍ ሃይል በውስጡ ተደብቆ ይገኛል። ይህ ሃይል፤ ሊገልፅ ሊወጣም ይችላል። ዮጋ እጅግ በጣም በትንሹ ውስጥ እጅግ በጣም ትልቁ እንደሚገኝ ሲናገር በእያንዳንዱ ቅንጣት (particle) ውስጥ የአምላክን መኖር እየገለፀ ነው፡፡

ዮጋ ለዚህ ሱትራ አፅንዖት የሰጠው ለምንድን ነው?

የመጀመሪያው ምክንያት እውነታው እሱ ስለሆነ ነው። ሁለተኛው ምክንያት በትንሹ ውስጥ ትልቁ ተደብቆ እንደሚገኝ ከታወቀ ሰው የራሱን ውስጣዊ አቅም እንዲያስታውስ ስለሚረዳው ነው፡፡ ሰው ትንሽ መሆኑ ሊሰማው የሚችልበት ምክንያት የለም። እጅግ በጣም ትንሹ እንኳ ትንሽነት ሊሰማው የሚችልበት ምክንያት የለም፡፡

ከዚህ በተቃራኒም እጅግ በጣም ሰፊውና ትልቁ እንኳ በኢጐ ስሜት ሊሞላ አይገባውም፤ ምክንያቱም እሱ ውስጥ ያለው እጅግ በጣም ትንሹ ውስጥም አለ፡፡ አንድ ውቅያኖስ በኢጐ ስሜት ከተሞላ እብደት ነው፤ ምክንያቱም እሱ ያለውን ጠብታውም አለው፡፡ ትንሹ የበታችነት፣ ትልቁ ደግሞ የበላይነት ሊሰማቸው የሚችልበት ምክንያት የለም፡፡ የበታችነትም ሆነ የበላይነት ትርጉም የላቸውም፡፡ ሁለቱም ትርጉም አልባ ናቸው፡፡

ሰው በሁለት ነገሮች ተጠምዶ ህይወቱን ያባክናል። ወይ በበታችነት ስሜት ወይ ደግሞ በበላይነት ስሜት ይሰቃያል፡፡

አንድ ሰው በበታችነት ስሜት ከተያዘ ውስጡ በጥልቀት ይታመማል፡፡ ከንቱ እንደሆነ እያሰበ ከኖረ በህይወት የመቆየቱ ጉዳይ አስቸጋሪ ይሆናል። በህይወት እየኖረ ቢሆንም ሙት ነው። እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ በህይወት የሚቆዩ በጣም ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡ አብዛኞቹ ግን ከመሞታቸው በፊት የሚሞቱ ናቸው፡፡ በሰባ አመታቸው ቢቀበሩም የሞቱት ግን ቀደም ብለው ነው፡፡ በሞታቸውና በቀብራቸው መሀል የሰላሳ፣ የአርባ ወይም የሃምሳ ዓመታት ክፍተት ሊኖር ይችላል፡፡

በዙሪያችሁ የተንሰራፋውን ግዝፈተ ተፈጥሮ ስትመለከቱ የበታችነት ሊሰማችሁ ይችላል። ከዚህ አንፃር ሲታይ ሰው ምንም ነው፡፡ በውቅያኖስ ሞገዶች ላይ እንደተንሳፈፈ ገለባ ነው፡፡ ምንም አይነት ሃይልም ሆነ አቅጣጫ የለውም፡፡ እንደዚህ አይነት የበታችነት ስሜት አይምሮን ጨምድዶ ከያዘ የሰው ህይወት በመከፋት የተሞላ ይሆናል፡፡ በህይወት የሚኖር ሙት ይሆናል። ህይወቱ አመድና ትቢያ ይሆናል። የህይወታችሁ ነበልባል ከውስጣችሁ ከጠፋ፣ የፋኖሳችሁ ነበልባል ከጠፋ፣ በፀሃይ ብርሃንም ምንም ማድረግ አትችሉም፡፡ ለናንተ ፀሃይ ምንም ጥቅም አይኖራትም፡፡

በሰው ውስጥ መላው ግዝፈተ ተፈጥሮ እንደሚገኝ ማስታወስ ያስፈልጋል። በሰው ውስጥ መለኮት እንደሚገኝ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም ሰው የበታች አይሆንም፡፡ በጣም የሚገርመው ሰው የበታችነት ስሜቱን ለማውደም አስቦ በየበላይነት ስሜት መጃጃሉ ነው፡፡ የበታችነት ስሜቱን ለማፈን የተለያዩ መንገዶችን መፈለግ ይጀምራል። ውስጡን የበታችነት ስሜት ሲሰማው ሃብት በማከማቸት ለአለም ህዝብ ከንቱ አለመሆኑን ሊያሳይና ከሌላው የበላይ የመሆን ስሜት ሊሰማው ይችላል። ከየበታችነት ስሜቱ የተነሳ ጭንቅላቱ ላይ ዘውድ ደፍቶ ከንቱ አለመሆኑን ለማሳየት ይሞክራል። የበላይነት ፉክክር ውስጥ የሚከተው የበታችነት ስሜት ነው፡፡ እናም የበላይ ለመሆን በሚደረግ የእብዶች እሽቅድምድም ውስጥ ያሉ ሰዎች ያለጥርጥር ውስጣቸው በየበታችነት ስሜት እየተሰቃየ ነው።

ምንጭ ፦ የንቃት ፀሀይ (ኦሾ)
ትርጉም ፦ መርሻ በነበሩ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍142
"እንደ ሰው ከመቆጠር ስናልፍና አንፋሽ አናፋሻችን ሲበዛ የሰልፍ መሪ የሆንን እየመሰለን እንደገና ያገኘንበት እንረግጣለን። መልካም መካሪ ካገኘን ወደ ሰልፋችን የመመለሳችን ነገር ያውም በጭብጨባ ታጅቦ ይደገማል። ካልሆነ ግን ማንነት ፣አላማ ፣ስብዕና እብድ የበላው በሶ ሆኖ ይቀራል። የታዋቂና እውቅና መንኮታኮቱ፤ የአገር ፖለቲካ ፣ኢኮኖሚ በልክ እንዳልተሰፋ ቀሚስ መንዘላዘሉ ፤ የትውልድ ሽሽት ከመጥበሻው ወደ እሳቱ የመሆኑም ነገር ሁሉ የማንነትን ሰልፍ እንደመሳት ነው። አጉል ወደድኩ ባይ ሰልፍ ስትጥስ የሚያጨበጭብልህ ፤ ደግሞም ጠላሁ ብሎ ከሰልፍህ ጎትቶ የሚያስወጣህ በሞላበት አገር ጥላቻና ፍቅርን እኩል የጥፋት መንገድ መሆናቸው የሚገባህ እንዲህ ከራስህ ጋር ሀቅ ሀቁን ስትነጋገር ነው።"

ዶ/ር አሸብር
አሌክስ አብርሃም
@zephilosophy
👍8🔥41👏1
🔆Noble Truth [የከበሩ እውነታዎች]

by DEMIS SEIFU 

🌪በመኖር ወዲያ ወዲህ… በመክረም ገበታ… በመውጣት መግባት መስተጋብር… በፍለጋ ላይና ታች ፍኖት… መሆናቸው እርግጥ ከሚባልላቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው…#ድቁሳት… Dukkha ይሉታል ምስራቃውያኑ… Suffering የሚለውን ቃል ፈተና ወይም ድቁሳት እያልኩ ልረዳው ወደድኩ… ስቃይ የዘለለት ቅኝት.. ፈተና የጊዜያዊነት ስሜት አለውና…

🌪ቡድሃ “The Four Noble Truths” በተባለው የመጀመሪያ ትምህርቱ ላይ ስለ ድቁሳት /ፈተና/ አራት ቁምነገሮችን አስተምሯል…

        ፩. There is suffering…

💧የመጀመሪያው ንዑድ እውነት “ድቁሳት አለ” ይላል… በቃ መደቆስ አለ… ይህንን እውነት መካድ አይቻልም… ከኑረት ገጾች በአንደኛው ላይ መታተሙ … ካለፍ አገደም ሁሉንም ቤት መጎብኘቱ ሳይታለም የተፈታ ነው… ስለዚህም እውቅና ከመስጠት እንጀምር ይላል ቡድሃ… አይቀሬነቱን ከመቀበል… ይህም ሁኔታውን ‘ለምን እኔ ላይ ብቻ…’ ከሚል ተጨማሪ ህመም ነፃ ያደርገዋል… መደቆስ ስላለ ተደቆስን እንጂ ‘እኛ’ ስለሆንን ሆነብን አንልም ማለት ነው… ሁሉም እንደየብጤቱ ይደቆሳል… እንደ ትከሻው… What do we have in common is suffering…

   ፪. There is an origin of suffering…

💦“እያንዳንዱ ድቁሳት የራሱ ሰበበ ኑረት አለው”… እርሱም የፍላጎት እስረኝነት ነው… ልክ ያልተበጀለት ፍላጎት የስቃይ ምንጭ ይሆናል… ስለዚህም የማይረካን ፍላጎት ወግድ ማለት ደግ ነገር ነው… እርግጥ ‘ፍላጎት’ እንዲጠፋ መፈለግም ያው ‘ፍለጋ’ ነው… ቁምነገሩ ፍላጎትን የመግራት ጥበብ ካለመፈለግ አይከሰትም… ፍላጎትህ የህመም ሰበብ መሆኑን ከመረዳት እንጂ… ደግሞም መፈለግህ ብቻ አይደለም ችግር… የሚያስፈልግህን አለማወቅም እንጂ…

💦ቁጭ ብለህ በእግረ ሃሳብ የምትኳትነው… በውጣ ውረድ ድግግሞሽ ባትለህ የምትውለው ለኑረትህ ግድ የሆኑትን ለማግኘት አይሆን ይሆናል… በዙሪያህ ባሉ ሁኔታዎች በቀላሉ በሚቃኝ አዕምሮህ ግፊት የአግበስባሽነት ኢጎ ተጠናውቶህ ሊሆን ይችላል… ችግሩ የፈለግኸውን አግኝተህ እንኳ ባገኘኸው አትረካም… ቀዳዳ ኪስ አይሞላማ… ሌላ ጨምር ይልሃል… ቀዳዳውን ስትደፍን ግን ሙላትህን መገንዘብ ትጀምራለህ… ፍላጎትን ፈር ማስያዝ እንግዲህ ቀዳዳን መጥቀም ነው… እኔዬ በቂ ነው ማለት…

🌊ለኑረትህ ግድ የሚባሉ ነገሮችን ማወቅ የሰላምህ ምንጭ… የሚጎድልም የሚሞላም የሌለህ መሆንህን ማወቅ ደግሞ አብርሆት ነው… ከውጭ የምታሳድደው ሁሉ የውስጥህን አይተካም… በቅርፃዊዉ ዓለም የቁሳዊነትም ሆነ የፍለጋዎች ጡዘት ግቡ “ደስታ” ነው ቢባልም በውስጥ ውስጠኛው አንተ ውስጥ ያለውን የዘለለት ሐሴትን ግን አይተካም… ስትፈልግ የኖርከው ያለህን ግን ደግሞ ያላየኸውን ነው ማለት ነው…

🌊በአልማዝና በከበሩ እንቁዎች የተሞላ ሳጥን ላይ ቁጭ ብሎ እርጥባን እንደመልቀም መሆኑ ነው…

   ፫. There is the cessation of suffering…

🌊ድቁሳት ምን ቢከብድ… ፈተና ምን ቢረቅ… የሆነ ጊዜ ያበቃል… ይተናል… ይበናል… የ Impermanence ህግ እንዲህ ይላል… “All that is subject to arising is subject to ceasing.” ስለዚህ ድቁሳትን በመሸሽ አታመልጠውም… ለተፈጥሮአዊ ሞቱ ትተወዋለህ እንጂ…

🌊የድቁሳትህ ምንጮች ‘መጥፎ’ የምትላቸው ነገሮች ብቻ አይደሉም… ‘ጥሩ’ ነገሮችህም ሁነኛ ማደሪያ ናቸው… ድቁሳት ከነገሩ ተፈጥሮ ይልቅ ለጉዳዩ ካለን ጥልቅ ዝማሜ ግዘፍ ይነሳል…

🌊ሁሌም ቢሆን ከሁነቶች ጋር የመቋጠር ቅኝት አለን… ቅርፃውያን ስለሆንን ከደስታችን ቅዥትና ከሃዘናችን ጥላ ጋር ‘የዘላለሜነሽ’ ሕብረ ዜማ እናረግዳለን… Attachment (ከነገሮች ጋር መጣመር) ክፉ ነገር ነው… ከሚያልፍ ነገር መቋለፍ ደግሞ የበለጠ አደገኛ … በውድቀት ስኬት ከፍ ዝቅ መኳተንና በወዲያ ወዲህ ፔንዱለማዊ ስሌት መዋለል የመቋለፍ ውጤት ነው… ነገሮችን እንደአመጣጣቸው ተቀብሎ የሚሸኝ ግና በጊዜያዊ ደስታ ከመስከርና በሚያልፍ ሃዘን ከመሰበር ይድናል… የወንዙን አወራረድ ለማየት ሁነኛው ቦታ የወንዙ አፋፍ ነው… እዚያ ነው የ’ሁሉም ያልፋል’ ጥበብ የሚወለደው…

🌊ለስሜት ስብራት የሚገፉኝን ሁኔታዎች በትኩረት መመልከት ስጀምር የሚገባኝ አሃዱ የትስስሬ ጥልቀት ነው… ድብርት ውስጥ ስገኝ… ብቻነት ሲሰማኝ… እጦት ሲያንገበግበኝ… ዕድሜ ከሌላቸው ነገሮች ጋር አዕምሮዬ እንደታበተ አስተውላለሁ… ለጊዜው ካበረህ ጋር ለሁልጊዜ በፍቅር መውደቅ ክፉ እርግማን ነው… ሟችን ለሞቱ ተወው…

    ፬. The way out of Suffering

❄️በድቁሳት መኖር ላይ ተግባባን… ምንጭ እንዳለውም ገባን… ተፈጥሮአዊ ሞት እንደሚሞትም እንዲሁ… ከድቁሳት ነፃ መውጣትስ አይቻል ይሆን?… ይሄ የሰው ልጅ ሁሉ ጥያቄ ይመስለኛል… ቡድሐም አብርሆት ከተቀዳጀባት ዛፍ /Bodhi Tree/ የዚህን ጥያቄ መልስ ሳያገኝ አልተነሳም… አዎን ከድቁሳት ነፃ መውጣት ይቻላል… እንዴት?

❄️ቡድሐ ‘The eightfold path’ በማለት የሰየማቸው ስምንት ‘ቀኖናዎች’ አሉ… ለቀኖናዎቹ መቅናት ከድቁሳት ነፃ ያወጣል…

RightView,
Right Intention,
Right Speech,
Right Action,
Right Livelihood,
Right Effort,
Right Mindfulness and
Right Concentration ናቸው…

🌟ከዚህ በኋላ ደቆስቆስ የሚያደርጉህ ነገሮች ሲበረክቱ ከኒህ ስምንት ቀኖናዎች የትኛውን እንዳጎደልክ መርምር…

@zephilosophy
@zephilosophy
👍63🔥2😁1
እሱ፤ አንድ ሚልዮን ብር ብሰጥሽ ከኔ ጋር ትተኛለሽ?

እሷ፤ አንድ ሚልዮን ብር? ዋው! ይመስለኛል አዎ፡፡

እሱ፤ በመቶ ብርስ?

እሷ ፤ ጥፋ ከዚህ፡፡ ምን መስዬህ ነው? ሴተኛ አዳሪ?

እሱ፤ ሴት አዳሪነትሽን መጀመሪያውኑ ተስማምተናል፡፡ አሁን በገንዘቡ ላይ እንደራደር።

ልክነት መቼ እና እንዴት ነው
የሚኖረው? መቼ ነው ይህቺን ሴት ሴተኛ አዳሪ የምንላት? መቼ ነው ይህቺን ሴት ክብሯን የጠበቀችው? መቶ ብር ወይስ መቶ ሺ ብር ላይ? ወይስ አንድ ሚሊዮን ላይ? መቼ ነው ክብሯን ያጣችው?

የገነባነው ክብር እና ፅድቅ  በየትኛው የብር መጠን ላይ እንሽረዋለን? ከሻርነውስ የእውነት መልካም ሰው ነን ማለት እንችላለን?
ምናልባት ምግባራችን እንደ ሴቷ በገንዘብ ስላልተፈተነ ይሁን ጥሩ ሰው የመሰልነው ?

@zephilosophy
👍32💔64🎄1👾1
ካላመኑበት ቅድስና ያመኑበት ኩነኔ ይሻላል!
---**---

የሰው ልጅ እምቢም እሺም የማይልበት አካለ ቁመና (ተክለ ሰውነት) ተሰጥቶታል፡፡ ነገርግን ቀሪውን ማንነት እራሱ ይፈጥራል (የአእምሮ እና የስነልቦናዊ የአስተሳሰብ ምህዋር 30% ውርስ 70% አካባብያዊ ተፅእኖ):: በዚህ አካሄድም ውስጥ ከአካል ውጪ ባለው ራስን በመፍጠር ሂደት <እምነት> እና <ነፃነት> ወሳኙን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ በኛ ማህበረሰብ “በየ-አይነት መብላት” እንጂ “በየ-አይነት” ማሰብ አይፈቀድም፡፡ በምናድግበት አካባቢ ያለውን ልማድ እና ወግ ጎጂም ቢሆን ማክበራችን “ጨዋ” ያሰኘናል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ባደግኩበት ሰፈር… የአጥር ጥግ ይዞ የሚሸና ወንድ “ባለጌ” ብሎ ሚሰድበው የለም፡፡ ነገርግን እኔ ድንገት እርቦኝ ከመንገድ ዳቦ ገዝቼ እየገመጥኩ ስሄድ እንደ መብረቅ እየጮሁ “ባለጌ” የማለት ልማድ አለ፡፡ ታዲያ ደጋግሜ አሰላሰልኩኝና ከዚህ ድምዳሜ ደረስኩ በሀገራችን ‹የማህበረሰብ እንጂ የግለሰብ ነፃነት የለም!!›

አንፃራዊነቷ እንዳለ ሆኖ በየትኛውም ጉዳይ ላይ “እውነት ከወዴት ናት? የትኛው ጥሩ የትኛውስ ጎጂ ነው?” ብለን ስናብሰለስል በመጨረሻ ላይ የምንደርስበትን ድምዳሜን <እምነት> እለዋለሁ፤ ስምምነት እንጂ ማስረጃ ማቅረብ አይጠበቅም!

ልዩና አዲስ የሆነ ሀሳብን እንደመብረቅ በመጮህ አልያም በጫና ከማስቀረት ይልቅ፤ መጥፎ ሀሳብን መልሶ በሀሳብ ማሸነፍ… አልያም መልካም ከሆነ ማፅደቅ ይገባናል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን የሆነ ሰው በሀሳብ ተሸንፎ የአቌም ለውጥ ካደረገ ‹አሽቃባጭ› የሚል ተውላጠ ስም እንሰጠዋለን፡፡

የሰው ልጅ ከእናቱ ሆድ ተጨርሶ እንደወጣ ልክ እንደ ግኡዝ አካል በሀሳብ ለውጥ አያድርግ ብለን ጫና እንፈጥራለን፡፡ ይሄ ተፈጥሮን መፃረር ይሆናል፡፡

መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ‹በሌላ ሀገር ትንሽ ወንዝ ካለ መዝናኛ አድርገው ይዝናኑባታል፡፡ እኛ ሀገር ትንሽ ወንዝ ካለ የመለያያ ድንበር አድርገን እንጋጭባታለን› ይሉናል:፡ ብዝሀነት/የሀሳብ ልዩነት ላይ ለመግባባት መድረክ የሌለው ማህበረሰብ በልዩነት ለመፍረስ የሰናፍጭ ፍሬን የምታህል ትንሽ ምክንያት ይበቃዋል፡፡

አበው ‘ገንፎ ለገንፎ ዘፍ ተደጋግፎ!’ እንደሚሉት፤ ግለሰቦችን ልክ እንደ እኛ  ካልሆንክ ብሎ ማስጨነቅ ደግ አይድለም!

በነፃነት የሚፈጠር ሰብአዊነት ውስጥ ልዩ ውበት አለ!!

ከመወለዳችን በፊት የተሰጡን አካላት በሙላ ቀን በቆጠረ ጊዜ ሁላ እያደጉ ይመጣሉ፡፡ የሰው ልጅ አእምሮ ግን በፈቃደኝነት ነው የሚያድገው፡፡ ጭንቅላትህ ፈቀድክለት አልፈቀድክለትም ማደጉን አያቁምም አእምሮህ ግን ካልፈቀድክለት አይበስልም!

ታዲያ አካለሰውነት በዘፈቀደ ሲያድግ እኛነታችንን ደግሞ በፈቃዳችን እናበጃለን፡፡ በዚህ የራሳችንን ስብዕና በመፍጠር ሂደት ውስጥ ነፃነት ከሌለን ከመብዛት ውጪ ምንም አናመጣም፡፡

--> ለምን ተፈጠርኩ? ለሚለው ጥያቄ ከመላምት ያለፈ ተጨባጭ ምክንያታዊ መልስ አናበጅለትም፡፡

--> ስብዕናዬን እንዴት ፈጠርኩ/ገነባሁ? ለሚለው ግን በማስረጃ የተደገፈ መልስ ከሁላችን ኪስ ይኖራል፡፡

ፈጣሪ ግማሹን ይፈጥራል እኛ የቀረውን ማንነታችንን እንፈጥራለን!

አንድ ግለሰብን ያለነፃነት ካመነበት ጉዳይ ውጪ ነገሮችን እንዲከውን ስናስገድደው በውስጡ ፍርሀት ይነግሳል፤ ፍርሀት ደግሞ ከእለት ወደ እለት ወደ ድብቅ ክፋት ያድጋል፡፡ “የክፋት ዘር ቀን ቆጥሮ ያመረቅዛል” በአፈና የተገነባ ማንነትን የያዘ ሠው፤ ራስን ለመከላከል ብሎም ለተፈጠረበት ድብቅ ውስጣዊና ሰንካላ ስሜት ሲል ማጥቃት ይጀምራል፡፡ ተንኮል፣ ክፋት፣ ሴሰኝነት፣ ጨቋኝነት፣ መስገብገብ ብዙ ብዙ፡፡
ያለነፃነት በተገነባ ማንነት ውስጥ በራስ መተማመን ስለሚጠፋ በድካም መሸፋፈን ይጀመራል፤ በገዛ ስራው ሀላፊነትን አይቀበልም፡፡ የሰብአዊነት ውበትም ያኔ ይጠፋል፡፡

አሁን የመረጃ ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ የሁሉ ነገር ፍጥነት አስገራሚ ሆኗል!

ከማስመሰል የነፃ ትውልድ ካልፈጠርን፤ በዚህ በመረጃ ዘመን ከማስመሰል ነፃ የሆነው የሌሎች ባይተዋር ባህል ስር ሰዶ ያፈርሰናል፡፡ የታፈነው ማንነት በአንዴ ፈንድቶ እንደጎርፍ ሊጠራርገን ይነሳል፡፡

የባህር ማዶ ሰዎች በብዙ ንፅፅር ከባህላችን ሲስተያዩ ባለጌ ቢሆኑም አለማስመሰላቸው፤ የውስጥ ስሜታቸውን አለመደበቃቸውከምንም በላይ  ጨዋነት ነው፡፡

አትታዘቡኝ “ነፃነትን እንደማክበር ያለ ወደር የሌለው ጨዋነት አላውቅም!”

ገናና በነበርንበት ዘመን እራስን መምሠል እንጂ ማስመሰል የማይበረታታ እንደነበረ አስባለሁ፡፡ ለዚያም ነው ከብዙዎች የተለየነው!

አካላዊ ቁመናችን ሲፈጠር እሺም እምቢም ማለት እንደማንችለው ሁሉ፤ ዛሬም በየ-ቤቱ በየ-ሰፈሩና በየ-ስራ ዘርፉ የገዛ ስብእናችንን ለመፍጠር ስንሞክር፤ ‘እንቢ’ም ‘እሺ’ም እንዳንል ሆነን ልንጠፈጠፍ አይገባም፡፡

አንድአይነት እንድንሆን መገደድ የለብንም!
ዜጎቻችን በነፃነት የፈጠሩት ስብዕና ካላቸው ለሚያሣርፉት በጎም ይሁን መጥፎ አሻራ ሀላፊነቱን ለመውሰድ ያመቻቸዋል፡፡

በዚህ የመረጃ ዘመን ግሩም የሆነ ኢትዮጵያዊ ስብዕናችንን ጠብቀን እናቆይ ዘንድ ከልጆቻችን ጋር በግልፅ የሀሳብ ትግል አድርገንና በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ተማምነን በነፃነት ስብዕናቸውን እንዲገነቡ ልናበረታታቸው ይገባል፡፡

“ካላመኑበት ቅድስና ያመኑበት ኩነኔ ይሻላል!’’

ራሳችሁን ለመፍጠር ትጉ! ፍቅር ደግሞ ከሁሉም ትበልጣለች፡፡ አደራ ታዲያ፤ ‹ስብእናችሁን ስትፈጥሩ ፍቅርን እግር አድርጓት፤ ጥናካሬዋ ድንቅና ውበቷም ልዩ ነው! እርሷ የትኛውንም ርቀት ትሄዳለች፤ ካሰበችበት ለመድረስ የሚያቆማት አይገኝም፡፡ እንደው ምን አልባት… ምን አልባት… ከጭቃ ውስጥ ያለ እሾህ ቢወጋት እንኳን፤ ይዛው እንጂ ሰብራው አትሄድም፡፡›


@Zephilosophy
👍318🎉1
የፍልስፍና ጥቅሞች

ፍልስፍና ሰፊ እውቀት በመለገስ የሰው ልጅ ስለራሱም ሆነ ስለሚኖርበት ዓለም ሰፊ ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረግ፣ ባገኘው ሰፊ ግንዛቤም ሰው ከችግሮቹና በህልውናው ላይ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ የተፈጥሮ ሥርዓቶች ላይ የበላይነት እንዲያገኝ ማድረግና በዚህም የራሱን ህልውና አስተማማኝ ማድረግ እርካታ የተሞላበት ኑሮ መምራት እንዲችል ማድረግ ነው፡፡

ከእነዚህ የፍልስፍና አጠቃላይ ግቦችና ጠቀሜታዎች ተነስተን የተለያዩ እጅግ ብዙ ግለሰባዊና ማኀበራዊ ጠቀሜታዎችን ከፍልስፍና ማግኘት እንችላለን፡፡

🔥ፍልስፍና ጠያቂዎችና ተመራማሪዎች እንድንሆን ያስችለናል፡፡ ነገሮችን የምንረዳበት የአስተሳሰብ አድማሳችን ያሠፋልናል፣ ሰዎች ነገሮችን ከሚመለከቱበትና ከሚረዱበት በተለዬ አመለካከት እንድንረዳቸው፤ ስህተት አስተሳሰቦች የደበቁትን እውነት ይፋ ማውጣት ያስችለናል፡፡

🔥የመኖር ትርጉምን እንድንረዳና አላማ ወይም ግብ ያለው ህይወት መምራት የሚያስችለን እውቀት ይሰጠናል፡፡

🔥ችግሮቻችን በጥልቀት መረዳት ያስችለናል፣ ለችግሮቻችን መፍትሔ የማፈላለግ አቅማችንን ያሣድግልናል፡፡ በህልውናችን ላይ አዳጋ የሚያደርሱ ሁኔታዎችን አስቀድመን መረዳት እንድንችልና መቋቋም የሚያስችል ብልሃት እንዲኖረንና ከተወሳሰቡ ግዙፍ ችግሮች መውጣት የምንችልበት የሰብዕና ጥንካሬ እንዲኖረን ይረዳናል፡፡

🔥ውሳኔዎቻችን የሚያስከትሉትን ውጤት አስቀድመን ማወቅ እንድንችልና የነገን ህይወታችን በእውቀትና በማስተዋል መምራት እንድንችል ያደርገናል፤ የምናደርጋቸውን ነገሮች በምክንያታዊና ሚዛናዊ አስተሳሰብ እንዲመሩና ከስሜታዊነት፣ ወገንተኛነት፣ አድሎ ፈፃሚነት፣ አግላይነት፣ አካባቢያዊነት እና ከዘረኛነት ተላቀን ህይወታችን በህሊናዊነት እንዲመራ ያስችለናል፡፡


🔥የራሳችንን ማንነት መረዳት እንድንችል፣ በህብረሰተብ ውስጥ ሊኖረን የሚችለው ሚና ከአቅማችን ጋር የተገናዘበ እንዲሆን፣ ባለን አቅምና ችሎታ የራስ መተማመን እንዲኖረንና የሚጠበቅብንን ሁሉ በድፍረት ማድረግ እንድንችል ይጠቅመናል፡፡

🔥የምንኖርበትን ህብረተሰብና የዓለምን ሁኔታ እንቅስቃሴ በጥልቀት ለመከታተልና ማድረግ የምንችለውን በህሊናዊ ውሳኔ መፈጸም እንድንችል ያደርገናል፡፡

🔥በንግግር ወይም በጽሑፍ የሚገለጡ ሀሳቦችን አድማጭና አንባቢዎችን ግልጽ ሆኖላቸው እንዲረዱት የሚያስችል የሀሳብ ተዋረድ ያለው አስተሳሰብ ማቅረብ እንድንችል ይረዳናል፤ ብዥታ የሚፈጥሩ ዘርፈ-ብዙ ትርጉሞች ያሏቸውና ህፀፆችን ማስወገድ እንድንችል ያደርገናል፤ ትንተና የመስጠት፣ ሀሳባችን ግልጽ በሆነ ሁኔታ አጠቃለን ለመግለጽ የሚያስችል ችሎታ እንድናዳብር ይጠቅመናል፡፡ የሌሎች ሰዎችን የተሳሳቱ ግንዛቤዎች ለማጋለጥና ትክክለኛ የሆነውንና የተሻለውን ሀሳብ ለማቅረብ ይረዳናል፤ የመተቸት አቅማችን ከፍ ይላል፤ ትችቶችን ጠቀሜታ እንዲኖራቸው አድርገን መግለጽ የምንችልበት ክህሎት እናዳብርበታለን፡፡

🔥ብልህ አንባቢና አድማጭ እንድንሆን ይረዳናል፡፡ በብልጣብጥና ተንኮለኛ ተናጋሪና ሰዎች እንዳንሞኝና የተሳሳተ መንገድ እንዳንከተል፣ ምንጊዜም በምክንያትና በመረጃ የቀረቡ ሀሳቦችን ብቻ አምነን እንድንቀበል ይረዳናል፡፡

ረ/ፕሮፌሰር ዋለለኝ እምሩ
@zephilosophy
👍253
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍3
ከዛሬ አራት አመት በፊት ሁለት ሆነን ጀምረን ዛሬ ከሃያ አምስት ሺ በላይ ቤተሰቦች ሆነን በዝተናል።ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን!!
ፍልስፍናና አዲስ ሀሳብ በሚፈራበት ማህበረሰብ ውስጥ፤  የፍልስፍና ዲፓርትመንት ከመላው ዩንቨርሰቲ በተፋቀበት ዘመን  እንደዚህ መብዛታችን ቀላል ነገር አይደለም።

ፁሁፎቹ ብዙ ሰው ጋር ይደርሱ ዘንድ #ሼር ስለምታደርጉ እናመሰግናለን🙏
👍232
Leave a comment

ስለምናቀርባቸው ፁሁፎች ያላችሁን አስተያየት እንድትሰጡን እንፈልጋለን
ከቻናላችን ምን ተጠቀማችሁ? ምን እንዲጨመር እና እንዲታረም ትፈልጋላችሁ?
በዚሁ ይቀጥል?

ሁላችሁም ተሳተፉ ወደ ፊት የምናቀርባቸውን የሀሳብ ይዘቶች ይወስናል!!

👇👇👇👇👇
👍13🔥1
🙏ስለ መልካም አስተያየታችሁ ሁላችሁንም ከልብ እናመሰግናለን።ፍቅራችሁን ያለስስት ገልፃችሁልናልና እውነት ከልብ እንወዳችኋለን። ከዚህ በላይ እንድንሰራ ትልቅ ሀላፊነት ጥላችሁብናል።

ይህ የቻናል የተፈጠረው ምክንያታዊ ና ሚዛናዊ አስተሳሰብ እንዲኖረን የሚያስችሉ ፍልስፍናዎችን ና እውቀቶችን ለማጋራት ነው።በተጨማሪም አካልን፣ ስሜትን እና አእምሮን የማስገዛት ጥበብን በማስተማር  ንቁ፣ በሳል እና ብልህ ሰው እንድንሆን ማገዝ ነው። እስካሁን በዚህ ቻናል የህይወት ልማድችንንና እምነታችንን የሚጠይቁ፤  የንቃት ሀይል የሚጨምሩ ፤ ፍቅር እና መንፈሳዊነትን የሚሰብኩ  ሀሳቦችን አጋርተናል።

ሆናም ግን ካነበብናቸው እና ካወቅናቸው ብዙ መፅሀፍትና ልምምዶች ጥቂቱን ብቻ ነው የጋራናችሁ። ከዚህ በኋለ በብዛት እንድናጋራችሁ ዘንድ ፈጣሪ የማይዋዥቅ ሞራልና የማይደበዝዝ ትጋት  ይሰጠን ዘንድ እንመኛለን!!

ብዙ ሰው ጋር ተደራሽ በመሆን ትጋታችን ይጨመር ዘንድ እያንዳንዱን ፁሁፍ #ሼር ማድረግ እንዳትዘነጉ!!

@zephilosophy
👍392
👍Reaction released

የምንለቃቸውን ፁሁፎች በላይክ ብዛት እያወዳደራችሁ እንዳታነቡ በሚል ምክንያት reaction አናበራም ነበር።የቴሌግራም monitazation ለመጠቀም ስንል አብርተነዋል። የምናቀርባቸው ፁሁፎች በክብደትም ሆነ በጥልቀት እየጨመሩ ስለሚመጡ እያንዳንዱን ሀሳብ ሳትመርጡ ብታነቡ መልካም ነው። ምክንያቱም የምናቀርባቸው ሀሳቦች መጀመሪያውኑም ከተመረጡ መፅሀፎች የተመረጡ እና የተጨመቁ ሀሳባች ስለሆኑ ...
👍184👏6🔥21
💬ሰለ ጥያቆቻችሁ

🤝ግሩፕ ስለመክፈት
የቻናላችን ግሩፕ  ለማታውቁት 👇👇
https://t.me/+XgPfefgVVvRhZjk0
በዚህ ግሩፕ በምናነሳቸው ሀሳቦች ላይ መወያየት፤ ተጨማሪ ሀሳብ መስጠት፤ መሞገትና መተቸት ትችላላችሁ።ወደፊት ደግሞ ብዙዎቻችሁን የሚያሳትፍ የውይይት እና የክርክር መድረክ ይኖረናል!!


📚soft copy መፅሀፍ ስለማጋራት
⭐️ብዙ pdf መፅሀፎች ቢኖሩንም ገብያ ላይ ካልጠፉና ደግመው የማይታተሙ ካልሆኑ በስተቀር የደራሲዎችን ጥቅም ስለሚጎዳ ያለ ደራሲዎች ፍቃድ መለጠፍ አንችልም።ምን ቢወደድ መፅሀፍ ከምንበላው ምግብ አያንስምና እየገዛችሁ የማንበብ ልምድን ማዳበር አለባችሁ።
👏33👍114
ሰው ከህዋ አንፃር ያለው ቦታ እና ግንዛቤ

ከግዙፉ ህዋ አንፃር የሰው ማንነት እንዴት ሊገለጽ ይችላል?
ሰው - ራሱን ከግዙፉ ህዋ ጋር እያስተያዬ ስለራሱ ማንነት ያስባል፣ የህይወቱን ትርጉም ፍለጋ ይኳትናል፣ ይጨነቃል፣ ተስፋ የሚሆነው ነገር ይፈልጋል፡፡ እነዚህን ስሜቶቹ፣ ፍላጐቶቹ፣ ተስፋዎቹ፣ እምነቶቹ. .. ወዴት ያደርሱታል ?

ሰው ከህዋ አንፃር ያለው ግንዛቤን ከጥንታዊ ሰው ታሪክ፤ ከመፅሀፍ ቅዱስ ፤ከትላልቅ ፈላስፎች እይታ አንፃር እናየዋለን።

1.ጥንታዊው ሰው ስለ ህዋ ያለው ግንዛቤ

የሰውና የህዋን ግንኙነት ምን እንደሚመስል ለመረዳት ከጥንታዊ ሰው ኑሮና አስተሳሰብ እንጀምር ካልን በአንድ በኩል ከላይ እንደተገለፀው ሰው ከተፈጥሮ በላይ የመሆን ማንነት ሲታይበት በተቃራኒው ደግሞ በዛን ዘመን ይኖር የነበረው ስው ተፈጥሮን ሌትም ቀንም በመፍራት ራሱን ከተፈጥሮ በታች የጣለበት ጊዜ ሁኖ እናገኘዋለን፡፡ በዘመኑ ሰው ነገሮች ሁሉ ነፍስ አላቸው ብሎ ያምን ነበር፤ ይህ ማለት ሰው በዘመኑ ነፍሳዊ (animist) ነበር፡፡ በሰማይ በምድር ያሉትን ሁሉ ሰውአዊ (antoropomorphic) ማንነት የሰጠበት ጊዜ ነበር፤ ከፍ ሲልም መንፈሳዊ ትርጉም በመስጠት ተፈጥሮን ያመለከበት ጊዜ ነበር።

የጥንቱ ዘመን የሰው ልጅ ታሪክ በእንደዚህ አይነት ሁለት የተለያዩ ስሜቶችና እምነቶች (በፍርሃትና በድፍረት፣ በሽንፈትና አሸናፊነት፣ በበታችነትና የበላይነት) ውስጥ ሰው ግራ ተጋብቶ የሚንገዋለል ማንነት ይዞ ይኖር የነበረበት ዘመን እንደነበር ያሳየናል፡፡ የጥንት ግብፃዊያን የምድር ህይወታቸውን በአባይም በፀሐይም ይመስሉት ነበር፡፡ አባይ ይሞላል - ይጐድላልም፤ ፀሐይ ትወጣለች ትጠልቃለችም፡፡ የሰው ህይወትም እንደዚያው ነው፡- ይወለዳል - ያድጋል፤ ይሞታል-ከሞትም ይነሳል፡፡ የተፈጥሮን የድግግሞሽ ሥርዓት መሠረት አድርገው ጥንታዊ ግብፃዊያን ሞተው እንደማይቀሩ - ከሞት እንደሚነሱ ያምኑ ነበር፡፡ የፀሐይ የሰማይ ላይ ጉዞ በምድር ላይ የሰው ጉዞ ነው፡፡ፀሐይ ስትጠልቅ ጠፍታ አትቀርም፤ በክብር ደግሞ ትወለዳለች፡፡ ይህም የሰው እጣፈንታው አንደፀሐይ የሆነና የሚሞት ገላው እንደሚነሳ የተስፋ ቃል የሚሰጠው ሆነ፡፡ በዚህ ምክንያትም ፀሐይን አምላክ ነሽ አሏት፤ መሪዎቻቸውንም በፀሐይ መሠሏቸው፡፡

ሥልጣኔ የሰውን ልጅ መጐብኘት ሲጀምር ተፈጥሮን የሚመለከትበት አይኑ እየሰፋ መጣ፤ ራሱንም በሰማያት ካሉት ፍጥረታት ጋር ያስተያይ ጀመር፡፡ ተፈጥሮን በማሸነፍ ማንነቱን ለማሳየትም ልቡ የበለጠ ተነሳሳ፤ ድንጋይ በድንጋይ እየደራረበ ራሱን ወደሰማይ ከፍ ያደርግ ጀመር፡፡ ከፍ አድርጐ በሠራው የድንጋይ ማማ ቁሞ መሬትን ቁልቁል ሲመለከታት እያነሰችበት መጣች፤ የእርሱ የበላይነት ግን ከሁሉ በልጦ ታየው፡፡

ከዚህ በመቀጠል ደግሞ መፅሀፍ ቅዱስ የሰው ልጅ ከህዋ አንፃር ያለውን ሁለት ምልከታ እናያለን...

ረ/ፕርፌሰር ዋለልኝ እምሩ

@zephilosophy
🔥19👍187
2.መጽሐፍ ቅዱስ ከህዋ አንፃር የሰው ልጅ ምንድን ነው? በማለት ይጠይቃል?

“የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፣
ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፣
ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?
ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?”

በማለት መዝሙረኛው ንጉስ ዳዊት ይጠይቃል፡፡
መዝሙረኛው ያነሳው ጥያቄ የዚህ ምዕራፍ ርዕስ ጉዳይ ነው፡፡ ሰው ተፈጥሯዊ የሆነ የአጋጣሚ ክስተት ውጤት ነው ወይስ ታላቅ አላማ ለማሳካት የተፈጠረ ልዩ ፍጥረት? ሰው በተፈጥሮ ሂደት በአጋጣሚ የተገኘ ቢሆንና የፍጥረታት ሁሉ የበላይና የመጨረሻ ግብ ሁኖ ሊወሰድ ይችላልን? ከፀሐይና ከጨረቃ-ከህዋ-አንፃር ሲታይስ እዚህ ግባ የማይባል ተፈጥሯዊ ማንነት ያለው ከብናኝ አፈር፣ በእግራችን ረግጠን እንደምንገድላቸው ትናንሽ ነፍሳት አይነት የሆነ ተራ ፍጥረት ነውን ወይስ በህዋ ውስጥ ያሉትን ነገሮች እንደፍላጐቱ ማድረግ የሚችል ኃያል ፍጥረት? ህዋ ለሰው ጥቅምና መልካም ግልጋሎት ተብሎ የተፈጠረ ነገር ነውን ወይስ መጥፋያው? መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ አይነት ጥያቄዎች የሚሰጠው መልስ ሁለት አይነት ነው፡፡ በአንድ በኩል የሰውን ኃያልነት ሲያጐላ በሌላ በኩል ተራ ፍጥረት መሆኑን ይነግረናል፡፡ መለኮታዊ ማንነት ያለውና በፍጥረታት ሁሉ ላይ ገዥነቱን የሚነግረን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንዳለ ሁሉ በሌሎች ክፍሎች ደግሞ ሰውን አዋርዶና አቅልሎ ይነግረናል፡፡ የሰውን ልዩ ማንነትና ገዥነቱን መዝሙረኛው ዳዊት እንዲህ በማለት ይገልፀዋል፡፡

“ከመላዕክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው፣
በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው፣
በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው፣
ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፣.."

ከጥቅሱ መረዳት እንደሚቻለው ሰው ከመላዕክት አንሶ የማያንስ በፍጥረታት ሁሉ ላይ ተሹሞ ዘውድ የደፋ ታላቅ ፍጥረት ነው፡፡ የሰው ታላቅነት ከአፈጣጠሩ ልዩ መሆን ይጀምራል፤ በእግዚአብሔር መልክ (በልጁ መልክ) የተፈጠረና የመለኮት ባህሪ ተካፋይ የሆነ ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ለሰው ልጅ ሌላ ማንነት ይሰጠዋል፡፡ ከሌሎች ፍጥረታት የማይለይ ይባስ ብሎ ከሌሎች ፍጥረታት አሣንሶ ሰውን ይገልፀዋል፡፡ መጽሐፈ መክብብ እንዲህ ይላል፡፡

“እኔ በልቤ ስለሰው ልጆች እንደ እንስሳ መሆናቸውን እንዲያዩ እግዚአብሔር ይፈትናቸዋል አልሁ፡፡ የሰው ልጆችና የእንስሳ እድል ፈንታ አንድ ነው፣ ድርሻቸውም ትክክል ነው፡፡ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፣ የሁለም እስትንፋስ አንድ ነው፣ ሁሉም ከንቱ ነውና ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም፡፡”

መጽሐፈ ኢዮብ ደግሞ የሰውን ማንነት ከዚህ በባሰ መልኩ ይገልፀዋል፡፡

“እነሆ፣ ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደሉም፣
ክዋክብትም በፊቱ ንጹሀን አይደሉም፣
ይልቁንስ ብስብስ የሆነ ሰው
ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ፡፡”

ፍልስፍናስ ምን ይላል? ፍልስፍና ትኩረት ከሚሰጥባቸው ጉዳዮች አንዱና ዋናው የሰውና የህዋ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ፍልስፍና ሰፋፊ፣ ጥልቀትና ብዛት ያላቸው አስተሳሰቦችን አቅርቧል። በቀጣይ እናያለን....

@zephilosophy
👍40🤔74👏1
ሰው ከህዋ አንፃር ያለው ቦታ እና ግንዛቤ በጥንታዊ እና በመካከላኛ ዘመን የነበሩ ፈላስፋዎች እይታ

ራሳቸውን ጥበበኞች እያሉ የሚጠሩ አንደበተኛና ጠርጣሪ (Sophist) ፈላስፋዎች እስከመጡበት ጊዜ የነበሩ ከቴለስ ጀምሮ የነበሩ ፈላስፋዎች ሰውን የተፈጥሮ አካል አድርገው ነው የተመለከቱት፤ ለሰው የተለዬ ማንነት አልሰጡትም፡፡ እንዲያውም ሰው የተፈጥሮ ህግ ተገዥና የበታች እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የዚህ አይነት አመለካከት በግሪክ ፈላስፋዎች ዘንድ የዘለቀው ራሳቸውን ጥበበኞች እያሉ የሚጠሩ አንደበታዊያን (Sophist) ፈላስፋዎች እስከመጡበት ጊዜ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ከበፊተኞቹ ፈላስፋዎች በተቃራኒው አንደበታዊያን ፈላስፋዎች ሰው የተለዬ ማንነት ያለው መሆኑን በፍልስፍናቸው አበሠሩ፡፡ አንደበታዊያን ሰውን ከተፈጥሮ በመለየት የራሱን እጣፈንታ በራሱ መወሰን የሚችል ፍጥረት እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ሰው ምን ያህል የተፈጥሮን ሥርዓት ሊያወቅና ሊቆጣጠር እንደሚችል ባይረዱትም ሰው ለራሱ ጥቅም ማስገኘት እስኪችል ድረስ ተፈጥሮን መቅረጽ ወይም መለወጥ እንደሚችል ያምናሉ፡፡

ፕሮታጐራስ የተባለው ታዋቂው አንደበታዊ ፈላስፋ “ለሁሉም ነገር ወሳኙ (ዳኛው) ሰው ነው- Man is the measure of everything” የሚል አባባል አለው፡፡ ይህ አባባል ሁለት ትርጉሞች አሉት፡፡ የመጀመሪያው እውነት ወይም ሀሰት፣ ጥሩ ወይም መጥፎ  የምንላቸው ነገሮች እንደ ሰው እይታ ነው ማለት ነው፡፡ ሌላው ትርጉሙ በሁሉም ነገር ላይ መወሰን የሚችለው ሰው ነው፤ ከሰው በላይ የሆነ ምንም ነገር የለም ማለት ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ማለት ከተፈጥሮም እንዲሁም ከአማልክትም በላይ ማለት ነው፡፡ በዚህ መልኩ በፍልስፍና ታሪክ ውስጥ ሰው የፍጥረታት ሁሉ ማዕከልና የበላይ የሆነ ክብር ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘው በአንደበታዊያን ፈላስፋዎች ነው፡፡

ከአንደበታዊያን በኋላ የመጡ እንደ ፕሌቶና አሪስቶትል ያሉ ፈላስፋዎች ከቁስ አካላትና ከህያዊያን ፍጥረታት ሁሉ በላይ የሚያደርገው በሰው ውስጥ የተለዬ ነገር አለ ብለው ያምናሉ፡፡ ሰው ተፈጥሮን ብቻ አይደለም ፍጹም የሆኑ ሃሳባዊያን ነገሮችን ጨምሮ መረዳት ይችላል፡፡ ይህ በሰው ዘንድ ያለ የተለዬ ነገር ነው፤ በዚህ የተለዬ ማንነት ሰው ከተፈጥሮ በላይ መሆን ብቻ ሣይሆን ከመለኰት ጋር ተመሣሣይ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ሰው በግዙፉ ህሊና ቢስ ህዋ ውስጥ የሚሆነው ነገር ጠፍቶት የሚንገዋለል ፍጥረት ሣይሆን የተፈጥሮን ሥርዓት አሸንፎ ወደ መለኮት ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ፍጥረት መሆኑን ፕሌቶና አሪስቶትል ያምናሉ፡፡

ከፕሌቶና አሪስቶትል በኋላ የመጡ ስቶይክ (Stoic) ፈላስፋዎች ደግሞ የተለዬ አመለካከት ነው ያላቸው፡፡ ለስቶይኮች ሰው የግዙፉ ህዋ ቅጅ ነው፡፡ በሰው ውስጥ ያለው በህዋ ውስጥ አስቀድሞ ያለው ነው፡፡ ሰው በህሊናው እንደሚመራው ሁሉ ተፈጥሮ በአጠቃላይ የሚመራው በስቶይኮች ቃል (logos) ብለው በሚጠሩት ህዋዊ ህሊና ነው፡፡ ሰው የሚኖረው ተፈጥሮ በሰጠችው ልክ በመሆኑ ተፈጥሮ እንዳደረገችው ሁኖ መኖር አለበት፡፡

ተፈጥሮ በህሊናዊ ኃይል ስለምትመራ ተፈጥሮን መቃወም ስህተት ነው፡፡ ይህ አመለካከት ሰውን ከተፈጥሮ በታች የሚያደርግ ብቻ ሣይሆን የሰው ህይወት አስቀድሞ የተወሰነና መቀየር የማይቻል መሆኑን ይሣየናል፡፡

የመካከለኛው ዘመን የነበሩ ክርስቲያን ፈላስፋዎች በመካከላቸው ልዩነት ይኑር እንጅ ዙሮ ዙሮ እግዚአብሔርን የህዋ ፈጣሪ መሆንና ሰውም የእግዚአብሔር ምርጡ የሥራ ውጤት መሆኑን ይስማሙበታል፡፡ ነገር ግን አካላዊ (ቁሳዊ) ማንነቱ ለሰው ጥቅም አልሰጠውም፤ ምኞትን፣ ሀጢዓትንና ሞትን አመጣበት፡፡ ሁለን ነገር በበላይነት ገዝቶ እንዲኖርበት የተሰጠው ዓለምም መከበሪያው ሣይሆን መቀበሪያው ሆነ፡፡ በመሆኑም አካላዊ (ቁሳዊ) ማንነቱና ምድራዊ ኑሮው አስፈላጊ አይደለም፤

ከሞት ነፃ ሁኖ የሚኖርበት ሌላ ማንነትና ሌላ ዓለም ያስፈልገዋል፡፡ ይህን ዓለም ሰው ንቆ መኖር አለበት፤ ይህ ዓለም ክብርና ዋጋ የሚሰጠው አይደለም፡፡ ጥቅም አለው ከተባለም ወደ ሌላኛው ዓለም ለመድረስ ለመሸጋገሪያነት ማገልገሉ ነው፡ ስለዚህ ሰው መሻት ያለበት እየኖረበት ያለውን ዓለም ሣይሆን ሌላኛውን (ከላይ) ያለውን ዓለም ነው፡፡

ዓለም ንቆ መኖር ካለበት በህዋ ላይ ሊጫወተው የሚችለው ሚናም ሆነ በህዋ የራሱን ቦታ ምን ሊሆን እንደሚችል ማወቅ አያስፈልገውም፡፡ ይህ አመለካከት ሰውንና ህዋን፣ ህሊና እና ቁስን መንፈስንና አካልን የሚለያይ ነው፡፡ ሰውን ከሚኖርበት ዓለም የሚለያይ አመለካከት ደግሞ ሰው በዚህ ዓለም ሊያደርግ የሚችለው ነገር ቢኖር እንኳ ጥቅም (ዋጋ) እንደሌለው ያመለክታል፡፡ ሰው ዓለምን ለመግዛት ቢፈጠርም የራሱን አካል እንኳ መግዛት ስለተሳነው በዚህ ዓለም ሊያገኝ የሚችለው ዘላለማዊ ክብርን አጥቶታል፡፡ ስለዚህ ሰው ማሰብ ያለበት ከሞት በኋላ ስለሚኖረው ህይወት እንጅ ከሞት በፊት ስላለው ሊሆን አይገባም፡፡

ዋናው ነገር ይህ ዓለም ለሰው መልካም እንዳይደለ መታመኑ ነው፡፡ ይህ ዓለም መጥፎና የሥቃይ ሁሉ ምክንያት ነው፡፡ የሐጢዓት ምክንያት በመሆኑ ይህ ዓለም ለሰው ልጅ ጠላቱ ነው፡፡ የላይኛው መንፈሳዊ ዓለም ግን የጽድቅና የዘላለም በረከት የሚገኝበት ነው፡፡ የመልካም ነገሮች ሁሉ መኖሪያ ቤትና የመለኮት ማረፊያ በመሆኑ የሰው ልጅ አላማ ሊሆን የሚገባው ቁሳዊ (ምድራዊ) ዓለምን መተውና መንፈሳዊ የሆነውን ዓለም ማግኘት ነው።

ዘመናዊ ፍልስፍና ስለ ህዋ ምን ይላል??

ረ/ፕርፌሰር ዋለልኝ እምሩ

@zephilosophy
@zephilosophy
👍492🔥1
5.የህዋ ግንዛቤ በዘመናዊ ፍልስፍና ታሪክ ውስጥ

የህዳሴውን ዘመንን ተከትሎ በሣይንሱም ሆነ በፍልስፍናው ብዙ አይነት አስተሳሰቦችና ትምህርቶች ይራመዱ ጀመር፡፡

ፍልስፍና “የሰውን ህይወት እጣፈንታ የሚወስን ኃይል አለ” ከሚል እምነት በመላቀቅ ሰው የራሱን ህይወት በራሱ ፈቃድና እውቀት መምራት ይችላል ወደሚል እምነት ተሸጋገረ፡፡

በመካከለኛው ዘመን ሰው ተስፋውን በአምላክ ጥሎ የራሱን ማንነት ረስቶ ነበር፡፡ በዚያ ዘመን ሰው ስለራሱ ማንነት ያንቀላፋበት ጊዜ ነበር፡፡ ከህዳሴው ዘመን ጀምሮ ግን ሰው ለረጅም ዘመን ከአንቀላፋበት ነቃ - ራሱን ማስተዋል ጀመረ፡፡ ወደራሱ በተመለከተ ቁጥር በሌላ ኃይል ከመተማመን ይልቅ የራሱ ኃይል ከምንም ነገር በላይ ሊያደርገው እንደሚችል አሰበ፡፡ በሳይንሳዊ እውቀት ምስጢሩን የተረዳውን ተፈጥሯዊ ሥርዓት በራሱ አቅም መግዛትና ለራሱ ጥቅም ማዋል እንደሚችል ድፍሩቱን ማሳየት ጀመረ፡፡

ይህ የህዳሴው ዘመን መንፈስ ነበር - በራሱ የመተማመን መንፈስ! የህዳሴው ዘመን ፍልስፍና የዘመናዊ ፍልስፍና መግቢያ በር ነው፡፡ ሙሉ ትኩረት የሰጠውም የሰው ልጅ ተፈጥሮን የመለወጥ አቅም ላይ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት የህዳሴው ዘመን ፍልስፍና ሰባዊነት - Humanism የሚል መጠሪያ አገኘ፡፡ እንደ ሉዶቪቾ ቫይቪስ (Ludovico Vives) ፣ ፔትሪስ ራመስ (Petrus Ramus) እና በርናርዲኖ ቴሎሶ (Bernardino Telesio) የመሳሰሉት ሰባዊ አስተሳሰብን በቀደምትነት ያራመዱ ፈላስፋዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ፈላስፋዎች የሰው ልጅ አጋዥ ሣያስፈልገው በራሱ አቅም የተፈጥሮን ኃይል ቀልብሶ ራሱን የበላይ አድርጐ መኖር ይችላል የሚል ከፍተኛ እምነት ነበራቸው፡፡ በዚህ አቋማቸው ሰውን አቅመ - ቢስ ያደረጉ እምነቶች ላይ አመጽ የጀመሩ ፈላስፋዎች ለመሆን ቻሉ፡፡ ሳይንስ ያመጣውን መነቃቃት ተከትሎ ሰባዊያን ያመጡት ፍልስፍና ለጨለማው ዘመን ማብቂያና የብርሃን ዘመን መምጣት የተበሠረበት ፍልስፍና ለመሆን ቻለ፡፡

ሳይንስ በፈጠረላቸው መደላድል ላይ ተመሥርተው ፍራንሲስ ቤከንና ቶማስ ሆብስ የተባሉ ፈላስፋዎች ሰው ከህዋ ጋር ያለውን ግንኙነት በእውቀት ላይ የተመሠረተ ሊሆን እንደሚገባው በማስገንዘብ የተፈጥሮን እንቅስቃሴና አጠቃላይ ሥርዐተ - ህጉን ማወቅ የሰው ልጅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡በተለይ ለሆብስ የተፈጥሮ ህግ መታወቅ ከተቻለ ሰው ህጉን እንደፈቃዱ እያስተካከለ መኖር እንደሚችል እምነቱን ገለፀ፡፡

እነ ቶማስ ሆብስ ሁሉን ነገር ቁሳዊ አደረጉት፡፡ ህሊና-ሀሳብ - በእንቅስቃሴ ላይ ያለ ቁስ ነው፤ እግዚአብሔርም ቢሆን ቁስአካላዊ ነው፤ መንፈሳዊ የሚባል ነገር የለም የሚል እምነት ማራመድ ጀመሩ፡፡

በእንደዚህ አይነት አመለካከቶች ተጋግሎ የነበረው የሰባዊነት ፍልስፍና ሳይታሰብ መቀዝቀዝ ጀመረ፡፡

ለምን ??? ይቀጥላል..

@zephilosophy
👍274🎄1
የዘመናዊ ፍልስፍና ሙግቶች

የቀጠለ
....የዳሳሽነት (empiricism) ፍልስፍናን ያራመዱ የብሪታንያ ፈላስፋዎች ሰውን የሁሉ ነገር ማዕከል አድርገው የተረዱ ቢሆንም ከሰው አሳቤ ውጭ ህዋ የራሱ የሆነ ህልውና የለውም በማለት ህዋንና ሰውን ያስተሳሰረውን ገመድ ቆርጠው ጣሉት፡፡ በርክሌይ የተባለው ፈላስፋ ቁሳዊ ነገሮች ከሰው ህሳቤ ውጭ ህልውና የላቸውም ማለቱና የስሜት ህዋሳቶች መረጃዎች መገኛቸው ቁሳዊ ነገሮች ሣይሆኑ እግዚአብሔር ነው ማለቱ የሳይንስን መሠረት የሆነውንና ሰው ማንነቱ ሊገለጽበት የሚችለው ቁስ አካል ከንቱ (ዋጋ የሌለው) ነገር ሁኖ እነዲታሰብ አደረገው፡፡ ይባስ ብሎ ዴቭድ ሂዩም የሰው ልጅ የስሜቶችና የሀሳቦች መንሸራሸሪያ መንገድ ከመሆን ውጭ ሌላ ማንነት የለውም፤ የህዋን (የቁስ አካላት) ህልውናንም ማረጋገጥ አይቻልም በማለቱ በፍልስፍና ተሟሙቆ የነበረው የሰውን ኃያልነት የማሳየት አስተሳሰብ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ቸለሰበት፡፡

ሌሎች ደግሞ የህዋን ህልውና ሙሉ በሙሉ ሀሳባዊ አደረጉት፡፡  እንጀ ሜልብራንች ያሉ ፈላስፋዎች (Malebranche) እኛ የምናውቀው እግዚአብሔር የገለፀልንን ነው፤ እርሱ ከሰጠን ሃሳብ ውጭ ምንም የምናውቀው ነገር የለም የሚል እምነት ያዙ፡፡  ሜልብራንች ሲናገር “እግዚአብሔር ዓለምን ቢያጠፋና አሁን እንዲሰማኝ እንዳዳረገኝ ወደፊትም እንዲሰማኝ ቢያደረገኝ ወደፊት የማየው አሁን የማየውን ነው፡፡” በሌላ አገላለጽ ይህ ማለት “እግዚአብሔር ዓለምን ቢያጠፋ ነገር ግን ልክ አሁን እንደሚሰማኝ (እንዳልጠፋች አድርጐ እንዳስብ ቢያደርገኝ) የማስበው ወይም የምረዳው መጥፋቷን ሣይሆን መኖሯን ነው፡፡የሚል ራሱን ሙሉ በሙሉ  የእግዚአብሔር ሀሳብ ብቻ እንደሆነ አድርጐ እንዲያስብ የሚያስችል አመለካከት ያራምድ ነበር።

በዘመናዊ ፍልስፍና የታዩ አንዳንድ ፈላስፋዎች ደግሞ ከጊዜው ነባራዊ ሁኔታ ውጭ ሆነውና የሣይንስን መንገድ ስተው የሰውን ልጅ ወደ ጥንታዊ ኑሮው ለመመለስ የሚከጅል ሀሳብ ማራመድ ጀመሩ፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆነው የዣን -ዣክ ሩሶ (Rousseau) ፍልስፍና ነው፡፡ ሩሶ እንደሚለው ሣይንስ የተፈጥሮ ህግ እውቀት ነው፤ ሳይንስ የሰውን ልጅ ኑሮ ይምራ ማለት ሰው በህግ ይመራ ማለት ነው፡፡ ሳይንስ ሰውን በህግ አስሮ መያዝ ይፈልጋል፡፡ ሰው ግን እንደፈቃዱና ስሜቱ መኖር የሚሻ ፍጥረት ነው፡፡ ሳይንስና ሳይንስ ያመጣቸው ስልጣኔዎች ግን የሰውን ልጅ ነፃነት የሚጋፉ በመሆናቸው አያስፈልጉም የሚል እምነት ማራመድ ጀመረ፡፡

ከላይ የተመለከትናቸውን ፍልስፍናዎች አጠቃለን ስናያቸው ዘመናዊ ፍልስፍና መስመር ይዞ መራመድና ወጥ የሆነ አቋም መያዝ እንደተሳነው መረዳት እንችላለን፡፡ በአንድ በኩል የሰውን ልጅ የበላይ አድርጐ ሲመለከት በሌላ በኩል ደግሞ እግዚአብሔርን በሰው ዘር ህሊና ላይ ይሾማል፤ አንዳንዴ ደግሞ ሰው ስለራሱም ሆነ ስለሚኖርበት ዓለም እንዲጠራጠር ሲያደርግ በሌላ በኩል ደግሞ ሰውን የራሱ የሥራ ውጤት ከሆነው ሥልጣኔ አርቆ ተፈጥሯዊ ኑሮ ብቻ መኖር ወደ ሚችልበት ወደ ተፈጥሮአዊነት ኑሮ መመለስ ይሻለዋል የሚል ሙግት ውስጥ ገባ፡፡

ኢማኑየል ካንት እንደብሪታንያ ፈላስፋዎች ሁሉ ሰው የሚረዳው የራሱን ሃሳብ ነው የሚል እምነት ቢኖረውም በምክንያታዊ አስተሳሰብ ሰው ከራሱ ውጭ የሆነ ቁሳዊ ዓለም መኖሩን፣ የእግዚአብሔርን ህልውናም ሆነ ዘላለማዊነት እና ነፃነት አለ ብሎ እንዲያምን አስችሎታል በማለት አሣወቀ፡፡ እነዚህ እምነቶች ደግሞ ተግባራዊ የሆነ ሥነ ምግባራዊ ኑሮና ሌላም አይነት ማኀበራዊ ህይወት እንዲኖርና ራሱንም ከተፈጥሮ በላይ አድርጐ እንዲያስብ አስችሎታል የሚል መደምደሚያ ሃሳብ ላይ ደረሰ፡፡ ይህን የመሰለው የካንት አስተሳሰብ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የሰውን በህዋ ላይ ያለውን የበላይነትና ክብር የመመለስ አስተሳሰብ ሁኖ ተወሰደ፡፡

በካንት መጫሚያ እግራቸውን ያስገቡ ሌሎች የጀርመን ፈላስፋዎች የሰውን ልጅ በህዋ ውስጥ ያለው መንፈሳዊና ህሊናዊ ኃይል ወራሽ በማድረግ ከቁስ አካላትና ከሌሎችም ፍጥረታት ሁሉ በላይ የሆነ ማንነት ያለው መሆኑን የሚያመለክት ጥልቅና ረቂቅ የሆነ ሀሳባዊ ፍልስፍና አቀረቡ፡፡ ካንትን ተከትለው የመጡ እንደ ሩዶልፍ ኸርማን ሎዝ፣ ሼልንግና ሄግል አይነት ፈላስፋዎች ህዋና ሰውን በአንድ አይናቸው የተመለከቱ ፈላስፋዎች ናቸው፡፡ ህዋ ለእነዚህ ፈላስፋዎች ህያው ነው፤ ህሊናዊ ነው፤ ሁልጊዜ ከፍ ወዳለ ደረጃ ለመሸጋገር የሚንቀሳቀስ ነገር ነው፡፡ በዚህ ህሊናዊ የለውጥ ሂደት ህዋ የራሱን የመጨረሻ የዕድገት ደረጃ የደረሰው በሰው ነው፡፡ ህዋ ሙሉ የሚሆነውና ራሱን የሚያውቀው በሰው ነው፡፡ ለእነዚህ ፈላስፋዎች ሰው ማለት ትንሽ ህዋ ነው፡፡


ከብዙ ፍልስፍና ሀሳቦች በጥቂቱ ስንቃኘው የህዋና የሰው ግንኙነት በፈላስፋዎች ዘንድ ይኼን የመሰለ አስተሳሰብ ፈጥሯል፡፡ በእኛም ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ቀላል አይሆንም፡፡ በህዋ ውስጥ ሰው ያለው ቦታ ለመወሰንና በሰውና በህዋ መካከል ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ከውዝግብ የፀዳና የማያሻማ መልስ  ማግኘት ባንችልም ርዕሰ ጉዳዩን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሰፋ አድርገን እንድንመለከተው የሚያስችል ሃሳቦችን አግኝተናል ።

ረ/ፕርፌሰር ዋለልኝ እምሩ

@zephilosophy
@zephilosophy
👍38👏106
ብቸኛው ባለቅኔ
ካህሊል ጂብራን

ለጋስነት በልቤ ውስጥ ተዘርታለች። ክምር ስንዴ አመረትኩ ፤ ለተራቡም አካፈልኩ። ነብሴ ለወይን ፍሬ ትሰጣለች፡፡ ወይኑን ጨምቄ ለተጠሙ አጠጣሁ። ፋኖሴን ዘይት ሞልቼ መስኮቴ ጋር አኖርኩኝ። በጭለማ ለሚጓዙ እንግዶች መንገዱን አበራሁ፡፡ ይህንን ሁሉ የማደርገው በእነዚህ ድርጊቶቼ ውስጥ ስለምኖር ነው። የሕይወት እጣ ለጋስ እጆቼን ብታስርበኝ ሞትን እመርጣለሁ። ገጣሚ ነኝና መለገስ ካልቻልኩ ፈፅሞ አልቀበልም። የሰው ልጅ ቁጣ እንደ አውሎ ነፋስ ያጓራል። እኔ ግን በዝምታ እተነፍሳለሁ፡፡ ምክንያቱም ትንፋሼ ፈጣሪ ጋር ሲደርስ ወጀቡ በሙሉ ይቆማልና። ሰዎች ምድራዊ ነገሮች ላይ ይንጠለጠላሉ፡፡ የኔ መሻት ግን የፍቅር ችቦ ናት። በብርሃኗ የልቤን ሰብአዊነት ታነፃልኛለች፡፡ ሰዎች በዘር ፣ በቀለም በሃይማኖት ተከፋፍለዋል። እኔ ደግሞ በሁሉም አገር እንግዳ ነኝ – የየትኛውም ወገን አይደለሁም፡፡ ሥነ-ፍጥረት (ዩኒቨርስ) አገሬ ስትሆን ጉሳዬ ደግሞ ሁሉም የሰው ልጅ ነው፡፡ የሰው ልጅ አቅመቢስ ሆነውም የተከፋፈሉ ናቸው። በየጊዜው የምትጠበውን ምድር በግዛትና አገራት መሰነጣጠቅ አላዋቂነት ነው። የሰው ልጆች እጅ ለእጅ የሚያያዙት የነፍስን ቤተ መቅደስ ለማፍረስና ምድራዊ ድልድይ ለመገንባት ብቻ ነው። ብቻየን ቆሜ እንዲህ የሚል የውስጥ ድምፄ ተሰማኝ ፡
#ፍቅር  ለሰው ልብ ሕይወት እንደምትሰጥ ሁሉ አለማወቅን ማወቅ ደግሞ የእውቀትን መንገድ ያሳየዋል። ፍቅርና አለማወቅን መረዳት ወደ ታላቅ ደስታ ይመራሉ– ምክንያቱም ፈጣሪ ከፀሀይ በታች ለሰው ልጅ መከራን አልፈጠረምና።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍6625🥰9👏4