ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ
30.7K subscribers
123 photos
3 videos
61 files
4 links
Philosophy For Higher Consciousness
Download Telegram
እንዴት ናችሁ፤ እናንተ ስግብግቦች!!

“እሱ ሸንቋጫችን ነው፣ እኛ ደግሞ እረፍት የለሽ አውሬዎች ይነካካን እንዲቆሰቁሰን እንፍቀድለትና ሰላማችንን እንጣ!”

እሱም አለ...
“እንዴት ናችሁ፤ እናንተ ስግብግቦች፣ ጥላቻን አነፍናፊ፣ ትርፍ አጋባሽ የአብርሀም ልጆች... እናንተ ለፍላፊዎች አሻማጆች፣... እናንተ አስመሳዮች አትገድሉም፣ አትሰርቁም፣ አትዘሙቱም ምክንያቱም ፈሪ ናችኋ። መልካም ምግባራችሁ፣የፍርሀት ውላጆች በመሆናችሁ የመጣ ነው።... እናንተ አህዮች! ረሀብ፣ ጥም፣ ብርድ እና ግርፊያው ቢፀናባችሁም ትጠገረራላችሁ። ትለፋላችሁ። ለራሳችሁ አንዳችም ክብር የላችሁም።

መልካምነታችሁም የጉስቁልና ውላጆች በመሆናችሁ የመጣ ነው:: እናንተ የቀበሮ ባህታዊያን ከአንበሳው ጉድጓድ ውጪ ትቆማላችሁ። ከፈጣሪም መኖሪያ ውስጥ አትገቡም.. እናንተ የሌዊ ልጆች አምላካችሁን በገንዘብ የምትለውጡ፡፡

...... እናንተ አክራሪ፣ ራስ ወዳዶች፣ የራሳችሁን ፊት ትመለከቱና እንደናንተው ፅንፈኛና ራስ ወዳድ ዓይነት አምላክ ትፈጥራላችሁ፡፡ ከዛም ራሳችሁን ዝቅ አድርጋችሁ በመስገድ ታመልካላችሁ። ስለምን? እናንተኑ ይመስላላ!!
....እናንተ የማትሞት ነፍሳችሁ ሸቃጭ የሆነችው በራፋችሁ ላይ ተቀምጣችሁ ለደሃ ሳንቲም በመመፅወት ለእግዜር ታበድራላችሁ᎓᎓ በመዝገብም ታሰፍራላችሁ:: ይህንንም  በአፀደ ነፍስ ፈጣሪ ፊት ታቀርባላችሁ። በምትኩም ከማይጠፋው፣ ከማያልቀው ሚሊዮኖች ለመሰብሰብ።
... እናንተ፣ ዋሾዎች የጌታን ትዕዛዝ የናቃችሁ የምትገድሉ፣ የምትሰርቁ፣ የምትዘሙቱና በኋላ የምታለቅሱ ፣ ደረታችሁን የምትደቁ ፡ - መሰሪ ሰይጣኖች...."

የመጨረሻው ፈተና
ኒኮስ ካዛንታኪስ

@Zephilosophy
👍62
ፍቅር መራር ትዝታዎቹን አስታቅፎህ እብስ ብሎ ይጠፋል…

በፍቅር ዘንድ … ትላንት ወይም ዛሬ፣

ዛሬ ወይም ነገ…

እዚህ ወይም እዚያ ብሎ ነገር የለም፡፡

ሁሉም ወቅቶች የፍቅር ወቅቶች ናቸው፡፡ የትኛውም ቦታ ቢሆን ለፍቅር ቤተ መቅደስነት የተገባ ክቡር ነው፡፡

ፍቅርን … ወሰንም ሆነ ዳር ድንበር

ካቴናም ሆነ የተዘጋ በር አይገድበውም፡፡

የትኛውም መሰናክል ጉዞውን ያሰናከለው ፍቅርም በተቀደሰው የፍቅር ስም ለመጠራት ባልተገባው፡፡

ዘወትር፣ ፍቅር ዕውር ነው ብላችሁ ስታወሩ እሰማለሁ፡፡ … አዎን … አፍቃሪ በተፈቃሪው ላይ አንዳችም እንከን አያይም ማለታችሁ ነው፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ … ይሄ ዓይነት አለማየት የማየት ከፍታ ጫፍ ነው፡፡

በምንም ነገር ላይ እንከን አታዩ ዘንድ ምነው ሁሌ በታወራችሁ፡፡

አይይ … የፍቅር ዓይኖችማ … ንፁህ፣ የጠሩና ሰርስረው የሚያዩ ብሌኖች ናቸው፡፡ ስለዚህም ምንም እንከን አያዩም፡፡

አዎን … ፍቅር ዓይናችሁን ሲያበራው … ያኔ … ለፍቅራችሁ ያልተገባ የቱንም እክል አታዩም፡፡ በዕርግጥም፣ ፍቅር አልባ ሸውራራ ዓይን ብቻ ነው በሌሎች ላይ እንከን ፍለጋ የሚተጋ፡፡ የትኛውም የሚያያቸው እንከኖችም … የሌላም ሳይሆን የራሱ ናቸው፡፡


The book of midrad
በሚካዔል ኔይማ
ትርጉም -ግሩም ተበጀ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍54
እውነትን ፍለጋ

ምንጭ ፦ከፈላስፎች አለም

የሰው ልጅ እውነትን በመሻት ሂደቱ ውስጥ በተለያየ አቅጣጫ ሲያካሄድ የቆየው ውስጣዊና ውጫዊ ጉዞ የታሪኩን እኩሌታ አስቆጥሯል ለማለት ይቻላል። አንዳንዱ ሀይማኖትንና መንፈሳዊነትን መሰረት በማድረግ፣ ገሚሱ ፍልስፍናን በመንተራስ የተቀረውም ሳይንስን በመሞርኮዝ ሁሉም በየፊናው የህይወትን ትርጓሜ ለመረዳትና በዙሪያው ያለውን እውነታ ለመገንዘብ፣ ግንዛቤውንም በመሰሎቹ ዘንድ ለማስረጽ ታትሯል። ይህም ሆኖ ሁሉንም ከሚያስማማ፣ በሁሉም ሰው ዘንድ ተቀባይነት ካለው የጋራ ድምዳሜ መድረስ የተሳነው ይመስላል።

በመሆኑም በዚህ የረዥም ዘመን ሂደት እውነት በሶስት መልክ ተተርጉሞ ከሶስት የተለያዩ ድምዳሜዎች ተደርሷል። አንዳንዶች እውነት ከሁኔቶችና ከሰዎች አመለካከት ጋር የማይለዋወጥ ፍጹም ሀቅ ነው ሲሉ ሌሎች በበኩላቸው እውነት እንደየሰዉ አመለካከትና ግላዊ ስሚት የሚለያይ አንጻራዊ ክስተት መሆኑን ይጠቁማሉ። በሶስተኛው ጎራ የሚፈረጁት ደግሞ እውነት ከቶውኑ ሊታወቅ የሚችል አይደለም ከሚል ድምዳሜ ደርሰዋል።

ከዚህ አኳያ የእውነትን አንጻራዊነትና ፍጹማዊነት በተመለከተ ከሶቅራጥስ ጊዜ ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የማያባራ ሙግት አሁንም መቋጫ ያልተገኘለት ነው። በርግጥ ብዙዎች ነባር እንጂ አዲስ እውነት የለም እንደሚሉት በዚህ ዘመን ስለ እውነት አንጻራዊነት የሚካሄዱ ሰጣ ገባዎች የጥንቱን መሰረት ያደረጉ ቅጥያዎች ናቸው።

እውነት ከሰው ሰው የሚለያይ አንጻራዊ ክስተት ነው ብለው ከሚያምኑ ጥንታዊ ፈላስፎች ውስጥ በግምባር ቀደምትነት የሚነሳው የአፕዴራው ሱፊስት ፕሮታጎረስ ነው። የፕሮታጎረስ የአንጻራዊነት ድምዳሜ መሰረት ያደረገው የሰው ልጅ ስለ ገሀዱ አለም ያለው እውቀት በህጸጽ የተሞላ መሆኑ ላይ ነው።

ሰው የገሀዱን አለም እውነታዎች መገንዘብ የሚችለው በስሜት ህዋሳቱ አማካኝነት ነው። ሆኖም የሰው የስሜት ህዋሳት ከሰብአዊ የአፈጣጠር ገደብ አኳያ ነገራትን ሙሉ ለሙሉ መመልከት አይችልም። ቀጥ ያለ ብረት ውሀ ውስጥ ሆኖ ሲታይ የተጣመመ መስሎ ይገኛል። የብረቱን መጣመም የሚፈጥረው የሰዎች የእይታ ግድፈት ነው። ስለሆነም
የስሜት ህዋሶቻችን አቅምና ሀያል ነገራትን በትክክል ለመመልከትና ለመገንዘብ የሚያስችል አይደለም።

ነገራትን በትክክል ለመገንዘብ በሚል እሳቤ በሰው ልጅ የተፈበረኩ የተለያዩ ማሽኖች ቢኖሩም የነገራትን ትክክለኛ ህልውና ለማሳየት ብቁ አይደሉም። በርግጥ ማይክሮስኮፕና ቴሌስኮፕን የመሳሰሉ በሰው ልጅ የተፈበረኩ የማጉያ መነጽሮች ያለጥርጥር የእይታ አድማሳችንና አቅማችንን ያሰፋሉ። ድምጽን የሚያጎሉ ድምጽ ማጉያዎች የሰው ልጅ ከመስማት ችሎታው በላቀ እንዲያደምጥ ያስችሉታል። ይህም ሆኖ እነዚህ ሰው የፈበረካቸው መሳሪያዎች ፍጹምና እንከን የለሽ ባለመሆናቸው የነገራትን እውነተኛ ህልውና በትክክል የሚያመላክቱ አይደሉም።

በመሆኑም የሰው ልጅ በጎዶሎ ሀይሉ ማግኘት የሚችለው እውቀት ጎዶሎ ይሆናል" የሚያገኘውም እውቀት ሌሎች ከሚያገኙት የተለየ ነው ሁለት ሰዎች አንድን እውነት ፍጹም ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ሊመለከቱ አይችሉም። በዚህ የተነሳ እውቀት እንደየሰዉ አተያይና ግላዊ ስሜት የሚለያይ ይሆናል" ለእኔ እውነት የሆነው እውነትነቱ ለእኔ ብቻ ሲሆን ለአንተ እውነት የሆነው እውነትነቱ ላንተ ብቻ ይሆናል።

ከዚህም ባሻገር የሊዮንቲየሙ ጆርጂየስ የፕሮታጎረስን የአንጻራዊነት አስተሳሰብ ይበልጥ በማስፋት ለኒሊዝምና ስኬፕቲዝም አመለካከት መሰረት ጥሏል። በኒሊዝም አራማጆች ዘንድ እውነት የሚባል ነገር ከነአካቴው የለም። እውነት የሚለው አስተሳሰብ በራሱ ውሽት ነው። ፈይራቤንድ እንዳስቀመጠው ‹‹ፍጹም የሆነው እውነት ፍጹም የሆነ እውነት አለመኖሩ ብቻ ነው›

ከስኬፕቲክስ ጎራ የሚፈረጁት ደግሞ እውነት የሚባል ነገር ቢኖር እንኳ ማወቅ አይቻልም ባይ ናቸው። እውነት የሚባል ነገር የለም ቢኖርም እውነትን ማወቅ አይቻልም የሚለው የነጆርጂየስ አመለካከት ፍሬድሪክ ኒቼንም የሚያስማማ ይመስላል። ኒቼ እውነተኛውን መንገድ አስመልክቶ እንዳስቀመጠው ‹‹እኔ የራሴ የሆነ መንገድ አለኝ፤ አንተም የራስህ መንገድ ይኖርሀል። ብቸኛውን፣ ትክክለኛውንና እውነተኛውን መንገድ በተመለከተ - የለም››

ከዚህ አመለካከት በመነሳት ጆርጂየስ ሶስት መሰረታዊ መርሆዎችን አስቀምጧል። አንድ - እውነተኛ ህልውና የለም። ሁለት - ሊኖር ቢችል እንኳ ሰው እውነታውን ማወቅ አይችልም። ሶስት በሆነ አጋጣሚ እውነትን ማወቅ ቢችል እንኳ ያወቀውን ለሌሎች ማሳመን አይችልም።

እነዚህን የኒሊዝምና ስኬፕቲዝም አመለካከቶች አጥብቀው የሚቃረኑ ፈላስፎች በበኩላቸው አመለካከቶቹ በራሳቸው መስፈርት ውድቅ የሚሆኑ፣ እርስ በርሳቸው የሚጻረሩ አመለካከቶች መሆናቸውን ይገልጻሉ። ምክንያቱም እውነት የሚባል ነገር ከሌለ የኒሊዝም እውነቶችም እውነት አይደለም ማለት ነው" ማንኛውንም ነገር ማወቅ አይቻልም ብለን ካሰብን ደግሞ ቢያንስ ማወቅ እንደማይቻል ማወቃችን በራሱ ምን ሊባል ነው?

@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍84
"መምህር ሆይ ስለጋብቻ ምን ትላለህ?"

እሱም አለ፦

"የተወለዳችሁት አብራችሁ ነው ። አብራችሁም ለዘለአለም ትኖራላችሁ ። የሞት ነጫጭ ክንፎች ቀናችሁን ባጨለሙባችሁ ጊዜም አብራችሁ ትሆናላችሁ።
አዎን ሌላው ቀርቶ በፀጥተኛው የእግዚአብሄር ዝክር ውስጥ እንኳ አብራችሁ ትኖራላችሁ…

"ነገር ግን በአብሮነታችሁ ውስጥ ክፍት ስፍራወች ይኑሩ ።
እርስ በእርስ ተፋቀሩ እንጂ የፍቅር ሰንሰለት አታብጁ። ይልቅስ በነፍሶቻችሁ ዳርቻዎች መካከል የሚንቀሳቀስ ባህር ይኑር…

"እርስ በእርሳችሁ ፅዋችሁን ተሞላሉ እንጂ ከአንድ ፅዋ አትጠጡ ።
ከዳቦወቻችሁ አንዳችሁ ለሌላችሁ ስጡ እንጂ ከአንድ ቁራሽ ዳቦ አትብሉ ። በአንድነት ዘምሩ፣ በአንድነት ጨፍሩ ።
ደስም ይበላችሁ ። ነገር ግን እያንዳንዱ ለብቻው ይሁን። የክራር ክሮች እንኳን በአንድ ሙዚቃ አብረው ቢርገበገቡም የታሰሩት ለየብቻ አይደለምን?…

"ልቦቻችሁን ስጡ እንጂ አንዳችሁ የሌላችሁን ልብ አትያዙ።
ልቦቻችሁን ሊይዝ የሚችለዉስ የህይወት እጅ ብቻ አይደለምን?…

"ደግሞም አብራችሁ ቁሙ እንጂ በጣም ተቀራርባችሁ አትቁሙ ። የቤተ መቅደስ ምሰሶዎችም ተራርቀው ነውና የሚቆሙት ።
ደግሞስ የባሉጥ ዛፍና ጥድ አንዳቸው በሌላኛው ጥላ ስር ተሸፍነው ያድጋሉን?"

ምንጭ ፦ The prophet(ነብዩ)
ደራሲ ፦ ካህሊል ጂብራን

@Zephilosophy
@Zephilosophy
10👍72🥰2
የአእምሮ ሰርከስ

ከእብደት ነፃ የምትሆነው መቶ በመቶ ከአእምሮህ ሰርከስ ከወጣህ ብቻ ነው።

ምንጭ ፦ የህይወት ኬሚስትሪ (ሳድጉሩ)
ተርጓሚ ፦ ሀኒም ኤልያስ

አእምሮን ሰርከስ ብለን የምንጠራው ለምንድነው? ሰርከስ ትርምስ ሳይሆን ሆን ተብሎ የተመሰቃቀለ እንዲመስል የተደረገ በጣም የተቀናጀ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ሰርከስ በአንድ ደረጃ የተመሰቃቀለ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ግን በጣም የተቀናጀ ተግባር ነው፡፡ በአንጎል ውስጥ የነርቭ ሴሎች እንዳለ የሚቀጣጠሉበትን እየተፈጠረ መንገድና ምን ብትመለከት ትደነቃለህ፤ በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ የአብሮነት ስሜት አለ፡፡ ወደ የሰውነት አሠራር ስርኣት እየተተረጎመ ያለውም ይህ አብሮነት ነው፡፡ በአንጎል ውስጥ እጅግ በጣም የተቀናጀ ጨዋታና እንቅስቃሴ ስላለ ብቻ በዚህ አካል ውስጥ አንድ ቢሊዮን ነገሮች እየተከሰቱ ነው። ግን እንደ አለመታደል ሆኖ የብዙ ሰዎችን ተሞክሮ ስንመለከት አእምሮ የተመሰቃቀለ ሆኗል፡፡ አእምሯቸው ልክ እንደ ሰርከስ ቢሆንም፣ ሁለቱም የሰርከስ ገጽታዎች ቢኖሩትም፣ ወደ አእምሯዊ እንቅስቃሴያቸው ስንመጣ ተሞክሯቸው ያመጣላቸው የተመሰቃቀለ አእምሮ ሆኖ እናገኘዋለን።

ታዲያ የዚህ ሰርከስ አማራጭ ምንድነው? ይህ ሰርከስ ወደ ታላቅ ከፍታ ሊወስድህ ወይም ደግሞ በራስህ ውስጥ ወዳለ የገሃነም ጥልቀት ሊወረውርህ ይችላል፡፡ እነዚህ ሁለት አማራጮች በእያንዳንዳችን ውስጥ ያሉ ሲሆን፣ ዋናው ነገር ይህንን ሰርከስ እንዴት እየመራነው ነው፣ ለምን ያህሉስ ሀላፊነት ወስደናል? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ነው። አእምሮ ለአንድ ሰው ደስ የሚያሰኝ፣ ለሌላው ሰው ደግሞ የማሰቃያ መሳሪያ የሚመስለው ለምንድነው? በሕይወታችን ውስጥ አእምሮ እጅግ ተአምረኛ የስኬት መሣሪያና በተነፃፃሪ ደግሞ የመከራ ማምረቻ ማሽን የሆነው ለምንድነው? የሰው ልጅ እየደረሰበት ያለው መከራ ሁሉ በአእምሮው ውስጥ የተመረተ ነው። በዚህች ፕላኔት ላይ የሚኖሩ ሰዎች የአእምሮ ስቃይን መሸከም ባለመቻላቸው፣ የአእምሯቸውን ምስቅልቅል ለመቅረፍ ሲሉ ከትክክለኛው መንገድ የተለዩና ጤናማ ያልሆኑ ነገሮችን ፈጥረዋል፡፡ እነዚህ ጤናማ ያልሆኑ ነገሮች ጊዜያዊ እፎይታ ሊሰጡዋቸው ቢችሉም፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን ምስቅልቅሉ እንዲጨምር ያደርጋሉ እንጂ አያጠፉትም፡፡

ከዚያም አእምሮህ በብዙ ማንነቶች ተለይቶ የሚታወቅ ስለሚሆን የመለኮት መሰላል  ‌ መሆን ሲገባው ወደ ገሃነም የሚወስድ ደረጃ ይሆናል፡፡ አእምሮ አንድ ጊዜ በሆነ ማንነት ተለይቶ ከታወቀ፣ ግንዛቤህ የተዛባ ይሆናል፤ ይህ መዛባት ደግሞ በሁሉም የሕይወትህ ገፅታዎች ውስጥ ይንሰራፋል። ማንኛውም ሰው ራሱን በፆታው፣ በቤተሰቡ፣ በብቃቶቹ፣ በማህበረሰቡ፣ በዘሩ፣ በእምነቱ፣ በሀገሩ ወይም በሕይወቱ ውስጥ በሚወስዳቸው ሌሎች ሚሊየን መለያዎች ውስጥ የሚያስቀምጥ ከሆነ፤ ራሱን ወደ ራሱ የመጨረሻ ተፈጥሮ ይመራል።

የአእምሮ ሰርከስን እንደ ተዘበራረቀ ሳይሆን በተአምራዊ ሁኔታ እንደተቀናጀ ተግባር አድርገህ የምታይ ከሆነ፣ አእምሮህ በምንም አይነት መለያ የሚታወቅ አይሆንም፤ ይህ ደግሞ በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነገር ነው፡፡ አእምሮ ሁሉንም ነገር ያለማቋረጥ እንደሚቆርጥ ስለት ነው፡፡ በአንድ ነገርና በሌላ ነገር መካከል የመለየት ችሎታህ የመጣው በአእምሮህ ምክንያት ብቻ ነው፡፡ በመሬትና በወንበር መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ የቻልከው አእምሮህ እየሰራ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ በግድግዳው በኩል ሳይሆን በበሩ መግባት እንዳለብህ ያወቅከው አእምሮህ ስለሚሰራ ብቻ ነው፡፡ የአእምሮ እንቅስቃሴ ከሌለ ምንም ነገር መለየት አትችልም፡፡

ቢላዋ ማንኛውንም ነገር ያለምንም እንከን በጥሩ ሁኔታ መቁረጥ ካለበት፣ የሚቆርጠው ነገር በእሱ ላይ እንዳይጣበቅ መጠንቀቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የሚቆርጣቸው ቁርጥራጭ ነገሮች ቢላዋው ላይ የሚጣበቁ ከሆነ፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይህ ቢላዋ የማይረባ ይሆናል። ሽንኩርት በከተፍክበት ቢላዋ ማንጎ ወይም ፖም ብትቆርጥ፣ የቆረጥከው ማንጎ ወይም ፖም የሽንኩርት ጣዕም ይኖረዋል፡፡ በሌላ አነጋገር አእምሮህ በአንድ ወይም በሌላ ማንነት ከታወቀ፣ በዚያ በታወቀበት ሰንሰለት ‌ ይታሰራል፡፡ ይህ ነገር አንድ ጊዜ ከተከሰተ ደግሞ፣ ሙሉ በሙሉ የተዛባ የአእምሮ ልምድ ይኖርሀል።

አእምሮህ አንድ ጊዜ በሆነ ነገር ተለይቶ የታወቀ ከሆነ፣ ይህ ተለይቶ የታወቀበት ማንነት በአንድ ደረጃ ላይ ብቻ የሚቀር ሳይሆን በብዙ ደረጃዎች ላይ የሚኖር በመሆኑ፣ ሁሉም ነገር የተመሰቃቀለ ይሆናል፡፡ አንድ ጊዜ በሆነ ነገር ተለይተህ የታወቅክ ከሆነ፣ የአእምሮህ ሰርከስ ወደ የትኛውም ትልቅ ጫፍ በፍጹም መውጣት የማይችል ትርምስ ብቻ ይሆናል፡፡ መጠጦችን፣ አደንዛዥ እጾችን እና ሁሉንም ዓይነት ነገሮችን የሚሞክሩ ሰዎች፣ ይህንን ልምዳቸውን ማቆም የሚችሉት በዚያ ማንነት መለየታቸውን ሲያቆሙ ብቻ ነው፡፡

@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍151
ግብ-ተኮር አእምሮ

ምንጭ ፦ ሁለንተና (ኦሾ)
ትርጉም ፦ አባድር

አእምሮ ውጤት ተኮር ነው:: ሁሌም ለውጤት ዋታች ነው፡፡ አእምሮ ለውጤት እንጂ ለድርጊት ደንታ ቢስ ነው፡፡ «ይህን ካደረግኩ ምን አገኛለሁ?» በሚል አስተሳሰብ የሚመራ አካል ነው፡፡ አእምሮ ያለ ብዙ ድርጊት ውጤት ማግኘት የሚችል ከሆነ ሁሌም አቋራጮችን ይመርጣል፡፡ የተማሩ ሰዎች ብልጥ የሆኑት አቋራጭ መንገዶችን ማግኘት ስለሚችሉ ነው፡፡

በትክክለኛው መንገድ ገንዘብ ለማግኘት መላው የህይወታችሁን ጊዜ ሊወስድባችሁ ይችላል፡፡ ካጭበረበራችሁ ግን ገንዘብን በአጭር ጊዜ ማግኘት ይቻላል፡፡ በቁማር፣ የፖለቲካ መሪ በመሆንና... በመሳሰሉት አማራጮች በአጭር ጊዜ ሀብታም መሆን ይቻላል፡፡ የተማሩ ሰዎች ብልጥ እንጂ አስተዋይ አይደሉም፡፡ ምንም ነገር ሳያደርጉ ሁሉንም ነገር ማግኘት የሚሹ ይሆናሉ፡፡

አእምሮአችን ሁሌም ውጤት ተኮር ነው፡፡ ህልውናችሁ ግን ከዚህ የተለየ አካል ነው፡፡ ተመስጥኦ ሊከሰት የሚችለው ውጤት ተኮር ላልሆኑ ህሊናዎች ነው፡፡

አንድ የቆየ ታሪክ አለ፡፡ አንድ ራስን በማወቅና በተገልጾ ዙሪያ ከፍተኛ ፍላጎት የነበረው ሰው ነበር፡፡ ሰውዬው መላው ፍላጎቱ ተመስጥኦን የሚያስተምረው መምህር ማግኘት ነበር፡፡ ከአንድ መምህር ወደ ሌላ እየተዘዋወረ ቢሞክርም ምንም የተከሰተለት ነገር አልነበረም፡፡ አመታት በሄዱ ቁጥር ሰውየው እየተዳከመና ሀይሉን እየጨረሰ መጣ፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ከሆነ ሰው ጥቆማ ደረሰው፡፡

«የሚያስተምርህ መምህር የምትፈልገው ከልብህ ከሆነ ወደ ሂማሊያ መጓዝ ይኖርብሀል፡፡ እዚያ ጥሩ መምህር አለ፡፡ መምህሩ በሂማሊያ ውስጥ በሆነ በማይታወቅ መገኛ ላይ ስለሚኖር ፈልገህ ማግኘት አለብህ፡፡ የስውየውን ትክክለኛ መገኛ የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ ምክንያቱም ሰውየው የሚፈልጉት ሰዎች እንዳሉ ሲሰማ ይበልጥ ጥልቅ ወደሆኑት የሂማልያ ሰንሰላታማ ተራራዎች ውስጥ ይሰርጋል፡፡ አንድ ነገር ግን እርግጥ ነው- ሰውየው በሂማሊያ ውስጥ አለ፡፡»

መረጃው የደረሰው ፈላጊ እያረጀ ቢሆንም ያለውን ሀይልና ድፍረት ሰብስቦ ለፍለጋ ተነሳ፡፡ ለሁለት ዓመት ያህል ለጉዞው የሚያስፈልገውን ያህል ገንዘብ ለማግኘት ከሰራ በኋላ ጉዞውን ጀመረ:: አንዳንድ ጊዜ በግመል ሌላ ጊዜ በፈረስ እንዲሁም በእግር ረዥሙንና አድካሚውን ጉዞ ካደረገ በኋላ ከሂማሊያ ደረሰ፡፡ ከቦታው ደርሶ አለ ስለተባለው መምህር የተለያዩ ሰዎችን ሲጠይቅ «አዎ ስለ አንድ አዛውንት ሰምተናል፡፡ ሰውየው ግን የጥንት ነው፡፡ እድሜውን መገመት አይቻልም፡፡ ሶስት መቶ ወይንም አምስት መቶ ሊሆነው ይችላል። ትክክለኛ እድሜውን የሚያውቅ የለም፡፡ ሰውየው የሚኖረው በዚህ አካባቢ ቢሆንም ትክክለኛ መገኛውን የሚጠቁምህ አታገኝም፡፡ በጽናት ከፈለግከው ግን እንደምታገኘው እርግጥ ነው» አሉት፡፡

ይህን የሰማው ፈላጊው እንጥፍጣፊ ሀይሉ እስክታልቅ ድረስ ፈለገ፡፡ ለሁለት ዓመታት ያህል በሂማልያ ውስጥ እየተዘዋወረ አሰሰ። ለሁለት አመታት ያህል ሰው ሊኖርባቸው ይችላል ብሎ ያሰባቸውን ቦታዎች ሁሉ ሲበረብር ቆየ። በመጨረሻ ግን እጅግ ተደከመ። ሀይሉን ጨረሰ፡፡ ለሁለት ዓመታት ያህል በጫካ ውስጥ ፍራፍሬና ቅጠላ ቅጠሎችን ብቻ እየተመገበ ስለቆየ ለሞት ምንም ያልቀረው ድካም ተሰማው፡፡ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰውነቱን ክብደት አጥቷል። ይሄ ሁሉ ቢሆንም ሰውየው ፍለጋውን አላቆመም፡፡ ፍለጋ ህይወቱን ሊያሳጣው ቢችልም እንኳን ሰውየውን ለማግኘት ቆርጧል ደግሞም ይገባዋል።

ፍለጋውን ቀጥሎ ሳለ አንድ ቀን ትንሽዬ የሳር ጎጆ ተመለከተ፡፡ ሰውየው አለ የተባለውን መምህር የማግኘት ተስፋው ጎጆዋ ውስጥ ብቻ ነበር፡፡ በጣም ከመዳከሙ የተነሳ መራመድ እንኳ አቅቶት በጉልበት እየዳኸ ከጎጆዎ ደረሰ፡፡ ጎጆዋ በር አልነበራትም፡፡ ቀረብ ብሎ ወደ ውስጥ ሲመለከትም አንድ እንኳን ነፍስ ያለው ፍጡር ከጎጆው ውስጥ አጣ፡፡ በጎጆዋ ውስጥ ሰው አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን ለብዙ ዓመታት ያህል በጎጆዋ ውስጥ ሰው እንዳልነበር የሚያመለክቱ ግልጽ ምልክቶችን ሳይቀር አገኘ፡፡

በምስኪኑ ሰው ላይ ምን እንደተከሰተ አስቡት፡፡

ፍጹም በሆነ ድካም ከመሬቱ ላይ ተዘረጋ፡፡ ቢሂማልያ ቀዝቃዛ የንፋስ ሽውታ ከተንዠረገገው ጸሐይ ስር ፍጹም በሆነ ድካም  «በቃኝ» ብሉ በጀርባው ተንጋለለ፡፡ በድንገት ግን በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የቡራኬ ስሜት ይሰማው ጀመር፡፡ ቀስ በቀስ ውስጡ በብርሀን ሲሞላ ተሰማው፡፡ ከመቅጽበት ሀሳቦቹ ሁሉ ጠፍተው በእድሜ ዘመኑ ሙሉ አይቶት የማያውቀው አይነት ሰላም ከውስጡ ሲሰፍን አደመጠ።

በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ የሆነ ሰው ከአጠገቡ እንዳለ ተገነዘበ፡፡ አይኖቹን ሲከፍት እጅግ ጥንታዊ የሆነ ሰው ከአጠገቡ ቆሞ ተመለከተ፡፡

አዛውንቱ ፈገግ አሉና «በስተመጨረሻ ደርሰሀል። የምትጠይቀኝ ነገር አለህ?» ሲሉ ጠየቁት። ፈላጊውም «አይ የለኝም» ሲል መለሰላቸው፡፡ አዛውንቱ ከልባቸው ሳቁ፡፡ ሳቃቸው በሸለቆው ዙሪያ ተስተጋባ፡፡

«ስለዚህ አሁን ተመስጥኦ ምን ማለት እንደሆነ ተረዳህ?» ብለው ጠየቁት

ሰውየውም «አዎ» ሲል መለሰ፡፡

የተከሰተው ነገር ምን ነበር?

ከሰውየው ጥልቅ ህልውና መንጭቶ ‹‹በቃኝ›› ካስባለው እርግጠኝነት ጋር መላው ግብ-ተኮር የሆነው የአእምሮ መውተርተርና መጣጣር ጠፋ፡፡ ‹‹በቃኝ›› ብሎ ከገባበት የምስጠት ህይወት በኋላ ሰውዬው የበፊቱ አይነት ሰው አልነበረም፡፡ ‹‹በቃኝ ›› ካለ በኋላ ወደ ማንምነት ተቀይሮ ነበር። ይህን ጊዜ ነበር በቡራኬ ሙላት የተጥለቀለቀው፡፡ ይህን ጊዜ ነበር የተመስጥኦን ትርጉም የተረዳው፡፡

ተመስጥኦ ከግብ ተኮርነት ነጻ የሆነ የአእምሮ ሁኔታ ማለት ነው።

በሌላችም መንፈሳዊ ከፍታዎች ፍቅር መልካምነት እና ርህራሄ ላይ የምትደርሱት ግብ ተኮር እና ምክንያታዊ ከሆነው የአእምሮ ሁኔታ ልቃቹ ስትገኙ ብቻ ነው።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍151
ሶስቱ የነፃነት መንገዶች
(ግመል፣አንበሳ፣ህፃን)
ኒቼ

አንተ ታላቅ ነህ ራስህንስ ስለምን ከመንጋዎች መሃል ትፈልገዋለህ? ሰዎች ባሰመሩልህ መስመር ላይስ ስለምን ትኖራለህ? ከልጅነትህ እስካሁን የተነገሩህ እና የተጻፉልህን ትርጓሜዎችን መርመራቸው ፤  አውላላ ሜዳ ላይ የታሰሩ መስሏቸው ከቆሙ በጎች ጋርስ ምን ታደርጋለህ?
መንጋዎች መነጠልን አይፈልጉም፤ በራሳቸውም የሚወስኑት ውሳኔ የለም - እንዲሁ ከመንጋው ጋር በመጓዝ ደህንነታቸውን (ምቾታቸውን)ማስጠበቅ ብቻ ይፈልጋሉ፡፡

መንጋዎች አብረው አንድ ላይ ይሰበሰባሉ፤ ለእነሱ መልካም የሆነውን እንዲያሳያቸውም እረኛውን ይከተሉታል፡ ከመንጋው ተነጥለህ ነጻነትህን ማወጅ ከፈለግኽ መንገድህ ይህ ነው - ግመል - አንበሳ - ህጻን


ግመል - (እውቀትን፣ እውነት እና ጥበብን ፍለጋ)

አንዳንድ ሰዎች እንደ በግ መንጋው ውስጥ አይወሸቁም፤ ሃላፊነትንም ከመሸከም አይሸሹም፤ በሃሩር በረሃ ውስጥ ከባድ ሸክምን ተሸክመው ያልፋሉ፡፡ በመንጋ ቢጓዙም፣ ሸክሙ የየግላቸው ነው፡፡ ማንም ግመል የሌላኛውን ሃላፊነት ሸክም አይጋራም፡፡ የመጀመሪያው የነጻነት መንገድ “ግመል" መሆን ነው፡፡
ግመል መሆን የምንጀምረው እውነታውን ከመጋፈጥ ነው። እውቀትን እና ጥበብን ከእያንዳንዱ ጥጋት መለቃቀም  ጀምር፤ እውነታውንም እወቅ፡፡ ግመል እንዲህ ይጠይቃል፡-

“ምን ያህል ይከብዳል፣ ከባዱና ሊያስደስተኝ የሚችለው ሸክምስ የትኛው ነው?

ታላቁን ሸክም መሸከም ይኖርብናል፤ የግመል መንፈስ ደስታውን የሚያገኘው በጥንካሬው ውስጥ ነው፡፡ ከባዱን ሸክም እንደተሸከመ ወደ በረሃው ይጣደፋል፡፡ ከባድ ሃላፊነቶች ታላቅ እና መልካም ናቸው። ሸክማችን በበዛ ቁጥር ማወቃችን ይጨምራል ግመል- ሕይወት ከእርሱ ላይ የምትወረውራቸውን ነገሮች (ፍርሃት፤ አስፈሪ እውነት፤ ፍቅር ወዘተ) መቻል ይኖርበታል።


አንበሳ - (ማድረግ እችላለሁ)

አዲሱ ማንነት በረሃውን መቆጣጠር እና መምራት ይኖርበታል፤ ነገር ግን ይህን ለማድረግ ከግዙፍ እና አስፈሪ ድራጎን ጋር መጋፈጥ አለበት፡፡ የድራገኑም ስም “ይህን አድርግ/አታድርግ” ይባላል። ድራገኑ እውነተኛ ነጻነትን እንዳታገኝ ይጋርድሃል።

“ይህን አድርግ/አታድርግ” ማህበረሰቡ ያስቀመጠልህ መስመሮች ናቸው፡፡ እንዴትም መሆን እና ምን ማድረግ እንዳለብህም ይነግሩሃል። ይህ ዋናው ጠላትህ ነው፤ ድራጎኑንም ልትገድለውም ይገባሃል።

አንበሳው በድራገኑ ፊት በቀረበ ጊዜ “እችላለሁ፤ አደርገዋለሁም” አለው። ድራገኑም መልሶ “ማንም እንደዚህ አድርጎ አያውቅም፤ አንተ ማነህና ነው?
አንበሳው ነጻነቱን ለማግኘት የበረሃውን ድራጎን ማሸነፍ ይኖርበታል።
አጓራ “እኔ ማንም አይደለሁም፤ እንዲሁ ያለፍቃዴ የተጫነብኝን ስርዓት አልቀበልም”

ኒቼ ይህንን The Sacred No' (ቅዱስ አይ) ይለዋል፡፡ አይነኬ ተብለው በማህበረሰቡ ውስጥ የተቀመጡ ህግ፣ ደንብ ወግ እና ባህሎችን ይቃወማል።ማንም ቢሆን የሚመሩትን የራሱን ስርዓት እና ደንቦች ለራሱ ማውጣት ይኖርበታል፡፡ አይሆንም እያሉ ድራጎኑን በመፋለም ሂደት ውስጥ ደስታ
የለም፤ ሆኖም ነጻነትን የፈለገ የግድ ይህን ማድረግ ይኖርበታል::

ህጻን - (አዲስ ጅማሮ)

አሁን ፍቃድህ ባንተ እጅ ነው᎓᎓ ድራጎኑ ሞቷል፡፡
አንዲት ከተማን አስብ - በዚህች ከተማ ውስጥ ህግ፣ ስርዓት፣ ደንብ እና ወግ የሚባሉ ማሰሪያዎች የሉም፡፡ ሁሉም እንደየራሱ ይኖራል:: ይህቺ ከተማ ማንን ትወክላለች? ምንስ የሚሆንባት ይመስልሃል?
ከተማዋ የህጻናት ከተማ ናት፤ ህግን የማያውቁ ህጻናት እንዲሁ ተፈጥሮ እንዳዘዘቻቸው የሚኖሩ ህጻናት ሞልተውባታል፡፡

ኒቼ ይህንን The Sacred Yes” (ቅዱስ አዎ) ይለዋል፡፡
“ህጻናት ንጹህ እና ዝንጉ ናቸው፡፡ አዲስ ጅማሮ፣ አዲስ ጨዋታ በራሱ የሚሽከረከር ጎማ፣ የተቀደሰ አዎ”

እውነተኛ ነጻነት ያለው በጫወታ ውስጥ ባሉ ህጻናት ላይ ነው ይለናል ኒቼ። ህጻናት ዓለምን ከማንም አልተረከቧትም፡፡ በአግራሞት እና አዲስ ነገርን በመፈለግ ውስጥም ይኖራሉ፡፡ ህጻን በሚያደርጋቸው ተግባራት ውስጥ ትርጉሞችን በራሳቸው ፍቃድ ይፈልጋሉ፡፡ ማንም ሕይወት እንዲህ ናት፣ ዓለም ይህቺ ናት ብሎም የተረጎመላቸው የለም፡፡
ሰው-ማህበረሰቡ የሰጠውን ሁሉንም
ትርጓሜዎች አልቀበልም (The
Sacred No) ካለ በኋላ፣ ሕይወት የምትሰጠውን ትርጉም ይቀበላል (The Sacred Yes) የራሱን ህግ እና ደንቦች ያረቃል፤ የራሱን እሴቶች ይገነባል᎓᎓ ተፈጥሯዊ የሆነውን ማንነቱንም ይኖራል፡፡

በኒቼ ፍልስፍና ሰው ነፃነቱን ከፈለገ ከግመልነት ጀምሮ ህፃን እስኪሆን ድረስ መጓዝ ይኖርበታል።


መፅሀፍ-የፍልስፍና ማዕድ
ደራሲ -ጥበበኛው ሰለሞን

@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍172
Audio
ፈጣሪ ርቦት

ከገጣሚ ኤፍሬም ስዩም
የአዋጁ ጊዜ መፅሀፍ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
🔥3👍1
ከልዩነት ባሻገር!

ልዩነቱ የዘር፣ የቋንቋ፣ የመልክ፣ የቁመናም ሆነ የእምነት . . . ከእናንተ ለየት የሚለው ሰው በአካባቢያችሁ ሲሰራም ሆነ ሲኖር፣ ለየት ያለ ሰው በመሆኑ ምክንያት ከእናንተ ምንም አይነት ጥቃት፣ በደልና መገለል እንደማይደርስበት እንዲሰማው የማድረግ ሃላፊነት እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ፡፡ ይህንን ሃላፊነት መወጣት የትክክለኛ ስብእና ምልክቱ ነው፡፡

የእኛ ዘር፣ ቋንቋ፣ መልክ፣ ቁመና እና እምነት ያለው እኛን መሰል ሰው የሚጠቃበት፣ የሚበደልበትና የሚገለልበት አካባቢ እንዳለ አትዘንጉ፡፡ እኛ እዚህ በሌላው ላይ የምናደርገውን ሌሎች እዚያ በእኛ እና እኛን በመሰሉት ላይ ያደርጉታል፡፡ ዑደቱ ይኸው ነው፡፡

የጨዋነት ሁሉ ጨዋነት ከእኛ ለየት ያሉትን የመቻልና የመቀበል ጨዋነት ነው!

ዶ/ር እዮብ ማሞ
@zephilosophy
👍85
"I am the Now. I Am’

Eckhart Tolle

🌘On the surface it seems that the present moment is only one of many, many moments. Each day of your life appears to consist of thousands of moments where different things happen. Yet if you look more deeply, is there not only one moment, ever? Is life ever not this moment? This one moment, now, is the only thing you can never escape from. The one constant factor in your life. No matter what happens. No matter how much your life changes. One thing is certain. Its always now. Since there is no escape from the now, why not welcome it, become friendly with it.

💫When you make friends with the present moment, you feel at home no matter where you are. When you don't feel at home in the now, no matter where you go, you will carry unease with you. The present moment is as it is, always. Can you let it be?

🌓The division of life into past, present and future is mind made, and, ultimately, illusory. The past and future are thought forms, mental abstractions. The past can only be remembered Now. What you remember is an event that took place in the Now and you remember it Now. The future, when it comes, is the Now. So the only thing that is real, the only thing that ever is, is the Now.

💫To have your attention in the Now is not a denial of what is needed in your life. It is recognizing what is primary. Then you can deal with what is secondary with great ease. It is not saying, “I’m not dealing with things anymore because there is only the Now.” No. Find what is primary first, and make the Now into your friend, not your enemy. Acknowledge it, honor it. When the Now is the foundation and primary focus of your life, then your life unfolds with ease.

💫Almost everyone lives like this most of the time. Since the future never arrives, except as the present, it is a dysfunctional way to live. It generates a constant undercurrent of unease, tension, and discontent. It does not honor life, which is Now and never not Now. When your attention moves into the Now, there is an alertness. It is as if you were waking up from a dream, the dream of thought, the dream of past and future. Such clarity, such simplicity. No room for problem making. Just this moment as it is.

🌘When you step into the Now, you step out of the content of your mind. The incessant stream of thinking slows down. Thoughts don’t absorb all your attention anymore, don’t draw you in totally. Gaps arise in between thoughts–spaciousness, stillness. You begin to realize how much vaster and deeper you are than your thoughts. Thoughts, emotions, sense perceptions, and whatever you experience make up the content of your life. “My life” is what you derive your sense of self from, and “my life” is content, or so you believe.

💫You continuously overlook the most obvious fact: your innermost sense of I Am has nothing to do with what happens in your life, nothing to do with content. That sense of I Am is one with the Now. It always remains the same. In childhood and old age, in health or sickness, in success or failure, the I Am–the space of Now– remains unchanged at its deepest level. It usually gets confused with content, and so you experience I Am or the Now only faintly and indirectly, through the content of your life. In other words: your sense of Being becomes obscured by circumstances, your stream of thinking, and the many things of this world. The Now becomes obscured by time.

🌘And so you forget your rootedness in Being, your divine reality, and lose yourself in the world. Confusion, anger, depression, violence, and conflict arise when humans forget who they are. Yet how easy it is to remember the truth and thus return home: I am not my thoughts, emotions, sense perceptions, and experiences. I am not the content of my life. I am Life. I am the space in which all things happen. I am consciousness. I am the Now. I Am.
🌔💫🌔💫🌔💫🌔💫🌔💫

@zephilosophy
👍6🔥5👏1
Harmony & Order
(ስምምነትና ስርዓት)

በሶክራተስም ሆነ በፕላቶ ዕምነት የሰው ልጅ ሁሉ ችግር የማሰብ ኃይል ችግር ወይም የዕውቀት ችግር ነው። ዕውነተኛ ዕውቀት በሶክራተስም ሆነ በፕላቶ ዕምነት ትምህርት ቤት የምንማረው ወይም ሸምድደን እንደ ዳዊት የምንደግመው አይደለም። በሁለቱም ዕምነት ሆነ ኋላ ብቅ ባሉት የአውሮፓ ፈላስፋዎችና ተመራማሪዎች፣ ዕውነተኛ ዕውቀት ማለት ራሳችንን እንድናውቅ የሚያደርገንና፣ ወደ ውስጥ ራሳችንን ለመመልከት እንድንችል የሚያደርገን፣ የበለጠ ራሳችንን እንድንጠይቅ የሚያስችለን፣ የተፈጥሮን ህግጋት ጠለቅ ብለን እንድንረዳ የሚያስችለንና፣ በጥንቃቄም በተፈጥሮ ውስጥ ያሉትን ነገሮች በማውጣትና ቅርጻቸውን በመለወጥ እንድንጠቀምባቸው የሚያግዘን፣  ህብረተሰብን በስነ-ስርዓትና መልክ ባለው ሁኔታ እንድናደራጅ የሚረዳን፣ ከሰውነታችን ፍላጎት ይልቅ የመንፈስን የበላይነት በማረጋገጥ በመንፈስ ኃይል በመመራት ከሌላው ተመሳሳይ ሰው ጋር ተሳስቦ መኖር መቻል፣ በፍጹም የራስን ጥቅም በማስቀደም ዓላማ አለመመራት…ወዘተ. ናቸው።

የማንኛውም የሰው ልጅ ፍጡር ጥረት አርቆ በማሰብ ኃይል በመመራት ወደ እግዚአብሄር ለመጠጋት መጣር ነው። በፕላቶ ዕምነት ሌላው ለአንድ ህብረተሰብ ምስቅልቅል ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ ወይም ለጦርነት ምክንያት የሚሆኑ ከሰብአዊነትና ከወንድማማችነት ይልቅ የብሄረ-ሰብ/ጎሳነት(Ethnic Solidarity) ምልክት የሆኑ ቅስቀሳዎች ቦታ ከተሰጣቸው ነው። በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ለሚከሰት ችግር ዋናው ምክንያት የተለያዩ ብሄረሰቦች በመኖራቸው ወይም አንደኛው ብሄረሰብ በሌላው ላይ ጫና ስለሚያደርግ ሳይሆን፣ በስልጣን ላይ ያሉ ኃይሎች ራሳቸው በሚፈጥሩት ልዩነትና ስልጣን ላይ ለመቆየትና ህዝቡን አደንቁረው ለዘለዓለም ለመግዛት እንዲችሉ የብሄረሰብን ጥያቄ እንደ ፖለቲካ መሳሪያ አድርገው  ሳይንሳዊውንና የስልጣኔውን ፈለግ ያሳስታሉ። ስለዚህም ለአንድ ህብረተሰብ ችግር ዋናው መፍትሄ እያንዳንዱ ግለሰብ ከሌላው የማይበልጥ መሆኑን ሲረዳና፣ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የተለያዩ ብሄረሰቦች መኖር የታሪካዊ ግዴታ እንጂ እንደክፋት መታየት የሌለባቸው መሆኑን ሲገነዘብ ነው። በተጨማሪም ተፈጥሮ ውስጥ የተለያዩ ነገሮች፣ ለምሳሌ የተለያዩ አበባዎች፣ የተለያዩ ዛፎችና የተለያዩ አራዊቶች መኖር የተፈጥሮን ውበት እንደሚያመለክቱና የተፈጥሮም ግዴታ የሆኑትን ያህል ሁሉ፣ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥም የተለያዩ ብሄረሰቦች፣ ጥቁርና ቀይ መልክ  ያለው ሰው፣ ረዥምና አጭር ሰው… ወዘተ. መኖር እንደ ውበት መታየት ያለባቸው ነገሮች ናቸው። ስለዚህም በአንድ ህብረተስብ ውስጥ የሚከሰቱ ብጥብጦች የተፈጥሮን ውስብስብነትና ውበት ለመረዳት ካለመቻልና ጠለቅ ብሎ ለማየት ካለመፈለግ የተነሳ ወይም በተሳሳተ ዕውቀት በመመራት አንድን ህብረተሰብ ለመግዛት መቻኮል ነው። ለዚሁ ሁሉ መፍትሄው ይላል ፕሌቶ፣ ማንኛውም ግለሰብ አርቆ አሳቢነትን በማስቀደም በመፈቃቀር ላይ የተመሰረተ ህብረተሰብ ለመግንባት መጣር ነው። ማንኛውም ግለሰብ ይህንን የዩኒቨርስ ህግ ሲረዳና  ስምምነትንና ስርዓትን(Harmony and Order) በጭንቅላቱ ውስጥ ሲቀርጽ በምድር ላይ ዕውነተኛውን ገነት ይመሰርታል።

ዶ/ር ፍቃዱ በቀለ

@zephilosophy
👍16🔥21
የበታችነት ስሜት አይሰማችሁ

በአንዲት ጠብታ ውስጥ ያለው፣ በውቅያኖስ ውስጥም አለ፡ ዮጋ ይህንን ሱትራ ሁልጊዜም የሚናገር ቢሆንም ሳይንስ የደገፈው ግን በቅርቡ ነው፡፡ አንድ አተም በውስጡ ይህን ሃይል ይይዛል ብሎ ማንም አስቦ አያውቅም፡፡ በዚህ እጅግ በጣም ትንሹ በሆነው የቁስ ክፍል ውስጥ ይህ ሁሉ ሃይል ተደብቆ እንደሚገኝ ማንም አስቦ አያውቅም።

ይህ የዮጋ እይታ ሳይንሳዊ መሆኑ የተረጋገጠው አተምን ወደ ንዑስ አተምነት በመከፋፈል በተደረገው ጥናት ነው፡፡ አንድ አተም በአይን አንኳን ሊታይ አይችልም፤ ይሁን እንጂ በዚህ በአይን በማይታይ አተም ውስጥ ግዙፍ ሃይል አለ፡፡

በሰው ውስጥም የነፍስ አተም በአይን አይታይም። ሆኖም ግን እጅግ በጣም ግዙፍ ሃይል በውስጡ ተደብቆ ይገኛል። ይህ ሃይል፤ ሊገልፅ ሊወጣም ይችላል። ዮጋ እጅግ በጣም በትንሹ ውስጥ እጅግ በጣም ትልቁ እንደሚገኝ ሲናገር በእያንዳንዱ ቅንጣት (particle) ውስጥ የአምላክን መኖር እየገለፀ ነው፡፡

ዮጋ ለዚህ ሱትራ አፅንዖት የሰጠው ለምንድን ነው?

የመጀመሪያው ምክንያት እውነታው እሱ ስለሆነ ነው። ሁለተኛው ምክንያት በትንሹ ውስጥ ትልቁ ተደብቆ እንደሚገኝ ከታወቀ ሰው የራሱን ውስጣዊ አቅም እንዲያስታውስ ስለሚረዳው ነው፡፡ ሰው ትንሽ መሆኑ ሊሰማው የሚችልበት ምክንያት የለም። እጅግ በጣም ትንሹ እንኳ ትንሽነት ሊሰማው የሚችልበት ምክንያት የለም፡፡

ከዚህ በተቃራኒም እጅግ በጣም ሰፊውና ትልቁ እንኳ በኢጐ ስሜት ሊሞላ አይገባውም፤ ምክንያቱም እሱ ውስጥ ያለው እጅግ በጣም ትንሹ ውስጥም አለ፡፡ አንድ ውቅያኖስ በኢጐ ስሜት ከተሞላ እብደት ነው፤ ምክንያቱም እሱ ያለውን ጠብታውም አለው፡፡ ትንሹ የበታችነት፣ ትልቁ ደግሞ የበላይነት ሊሰማቸው የሚችልበት ምክንያት የለም፡፡ የበታችነትም ሆነ የበላይነት ትርጉም የላቸውም፡፡ ሁለቱም ትርጉም አልባ ናቸው፡፡

ሰው በሁለት ነገሮች ተጠምዶ ህይወቱን ያባክናል። ወይ በበታችነት ስሜት ወይ ደግሞ በበላይነት ስሜት ይሰቃያል፡፡

አንድ ሰው በበታችነት ስሜት ከተያዘ ውስጡ በጥልቀት ይታመማል፡፡ ከንቱ እንደሆነ እያሰበ ከኖረ በህይወት የመቆየቱ ጉዳይ አስቸጋሪ ይሆናል። በህይወት እየኖረ ቢሆንም ሙት ነው። እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ በህይወት የሚቆዩ በጣም ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡ አብዛኞቹ ግን ከመሞታቸው በፊት የሚሞቱ ናቸው፡፡ በሰባ አመታቸው ቢቀበሩም የሞቱት ግን ቀደም ብለው ነው፡፡ በሞታቸውና በቀብራቸው መሀል የሰላሳ፣ የአርባ ወይም የሃምሳ ዓመታት ክፍተት ሊኖር ይችላል፡፡

በዙሪያችሁ የተንሰራፋውን ግዝፈተ ተፈጥሮ ስትመለከቱ የበታችነት ሊሰማችሁ ይችላል። ከዚህ አንፃር ሲታይ ሰው ምንም ነው፡፡ በውቅያኖስ ሞገዶች ላይ እንደተንሳፈፈ ገለባ ነው፡፡ ምንም አይነት ሃይልም ሆነ አቅጣጫ የለውም፡፡ እንደዚህ አይነት የበታችነት ስሜት አይምሮን ጨምድዶ ከያዘ የሰው ህይወት በመከፋት የተሞላ ይሆናል፡፡ በህይወት የሚኖር ሙት ይሆናል። ህይወቱ አመድና ትቢያ ይሆናል። የህይወታችሁ ነበልባል ከውስጣችሁ ከጠፋ፣ የፋኖሳችሁ ነበልባል ከጠፋ፣ በፀሃይ ብርሃንም ምንም ማድረግ አትችሉም፡፡ ለናንተ ፀሃይ ምንም ጥቅም አይኖራትም፡፡

በሰው ውስጥ መላው ግዝፈተ ተፈጥሮ እንደሚገኝ ማስታወስ ያስፈልጋል። በሰው ውስጥ መለኮት እንደሚገኝ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም ሰው የበታች አይሆንም፡፡ በጣም የሚገርመው ሰው የበታችነት ስሜቱን ለማውደም አስቦ በየበላይነት ስሜት መጃጃሉ ነው፡፡ የበታችነት ስሜቱን ለማፈን የተለያዩ መንገዶችን መፈለግ ይጀምራል። ውስጡን የበታችነት ስሜት ሲሰማው ሃብት በማከማቸት ለአለም ህዝብ ከንቱ አለመሆኑን ሊያሳይና ከሌላው የበላይ የመሆን ስሜት ሊሰማው ይችላል። ከየበታችነት ስሜቱ የተነሳ ጭንቅላቱ ላይ ዘውድ ደፍቶ ከንቱ አለመሆኑን ለማሳየት ይሞክራል። የበላይነት ፉክክር ውስጥ የሚከተው የበታችነት ስሜት ነው፡፡ እናም የበላይ ለመሆን በሚደረግ የእብዶች እሽቅድምድም ውስጥ ያሉ ሰዎች ያለጥርጥር ውስጣቸው በየበታችነት ስሜት እየተሰቃየ ነው።

ምንጭ ፦ የንቃት ፀሀይ (ኦሾ)
ትርጉም ፦ መርሻ በነበሩ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍142
"እንደ ሰው ከመቆጠር ስናልፍና አንፋሽ አናፋሻችን ሲበዛ የሰልፍ መሪ የሆንን እየመሰለን እንደገና ያገኘንበት እንረግጣለን። መልካም መካሪ ካገኘን ወደ ሰልፋችን የመመለሳችን ነገር ያውም በጭብጨባ ታጅቦ ይደገማል። ካልሆነ ግን ማንነት ፣አላማ ፣ስብዕና እብድ የበላው በሶ ሆኖ ይቀራል። የታዋቂና እውቅና መንኮታኮቱ፤ የአገር ፖለቲካ ፣ኢኮኖሚ በልክ እንዳልተሰፋ ቀሚስ መንዘላዘሉ ፤ የትውልድ ሽሽት ከመጥበሻው ወደ እሳቱ የመሆኑም ነገር ሁሉ የማንነትን ሰልፍ እንደመሳት ነው። አጉል ወደድኩ ባይ ሰልፍ ስትጥስ የሚያጨበጭብልህ ፤ ደግሞም ጠላሁ ብሎ ከሰልፍህ ጎትቶ የሚያስወጣህ በሞላበት አገር ጥላቻና ፍቅርን እኩል የጥፋት መንገድ መሆናቸው የሚገባህ እንዲህ ከራስህ ጋር ሀቅ ሀቁን ስትነጋገር ነው።"

ዶ/ር አሸብር
አሌክስ አብርሃም
@zephilosophy
👍8🔥41👏1
🔆Noble Truth [የከበሩ እውነታዎች]

by DEMIS SEIFU 

🌪በመኖር ወዲያ ወዲህ… በመክረም ገበታ… በመውጣት መግባት መስተጋብር… በፍለጋ ላይና ታች ፍኖት… መሆናቸው እርግጥ ከሚባልላቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው…#ድቁሳት… Dukkha ይሉታል ምስራቃውያኑ… Suffering የሚለውን ቃል ፈተና ወይም ድቁሳት እያልኩ ልረዳው ወደድኩ… ስቃይ የዘለለት ቅኝት.. ፈተና የጊዜያዊነት ስሜት አለውና…

🌪ቡድሃ “The Four Noble Truths” በተባለው የመጀመሪያ ትምህርቱ ላይ ስለ ድቁሳት /ፈተና/ አራት ቁምነገሮችን አስተምሯል…

        ፩. There is suffering…

💧የመጀመሪያው ንዑድ እውነት “ድቁሳት አለ” ይላል… በቃ መደቆስ አለ… ይህንን እውነት መካድ አይቻልም… ከኑረት ገጾች በአንደኛው ላይ መታተሙ … ካለፍ አገደም ሁሉንም ቤት መጎብኘቱ ሳይታለም የተፈታ ነው… ስለዚህም እውቅና ከመስጠት እንጀምር ይላል ቡድሃ… አይቀሬነቱን ከመቀበል… ይህም ሁኔታውን ‘ለምን እኔ ላይ ብቻ…’ ከሚል ተጨማሪ ህመም ነፃ ያደርገዋል… መደቆስ ስላለ ተደቆስን እንጂ ‘እኛ’ ስለሆንን ሆነብን አንልም ማለት ነው… ሁሉም እንደየብጤቱ ይደቆሳል… እንደ ትከሻው… What do we have in common is suffering…

   ፪. There is an origin of suffering…

💦“እያንዳንዱ ድቁሳት የራሱ ሰበበ ኑረት አለው”… እርሱም የፍላጎት እስረኝነት ነው… ልክ ያልተበጀለት ፍላጎት የስቃይ ምንጭ ይሆናል… ስለዚህም የማይረካን ፍላጎት ወግድ ማለት ደግ ነገር ነው… እርግጥ ‘ፍላጎት’ እንዲጠፋ መፈለግም ያው ‘ፍለጋ’ ነው… ቁምነገሩ ፍላጎትን የመግራት ጥበብ ካለመፈለግ አይከሰትም… ፍላጎትህ የህመም ሰበብ መሆኑን ከመረዳት እንጂ… ደግሞም መፈለግህ ብቻ አይደለም ችግር… የሚያስፈልግህን አለማወቅም እንጂ…

💦ቁጭ ብለህ በእግረ ሃሳብ የምትኳትነው… በውጣ ውረድ ድግግሞሽ ባትለህ የምትውለው ለኑረትህ ግድ የሆኑትን ለማግኘት አይሆን ይሆናል… በዙሪያህ ባሉ ሁኔታዎች በቀላሉ በሚቃኝ አዕምሮህ ግፊት የአግበስባሽነት ኢጎ ተጠናውቶህ ሊሆን ይችላል… ችግሩ የፈለግኸውን አግኝተህ እንኳ ባገኘኸው አትረካም… ቀዳዳ ኪስ አይሞላማ… ሌላ ጨምር ይልሃል… ቀዳዳውን ስትደፍን ግን ሙላትህን መገንዘብ ትጀምራለህ… ፍላጎትን ፈር ማስያዝ እንግዲህ ቀዳዳን መጥቀም ነው… እኔዬ በቂ ነው ማለት…

🌊ለኑረትህ ግድ የሚባሉ ነገሮችን ማወቅ የሰላምህ ምንጭ… የሚጎድልም የሚሞላም የሌለህ መሆንህን ማወቅ ደግሞ አብርሆት ነው… ከውጭ የምታሳድደው ሁሉ የውስጥህን አይተካም… በቅርፃዊዉ ዓለም የቁሳዊነትም ሆነ የፍለጋዎች ጡዘት ግቡ “ደስታ” ነው ቢባልም በውስጥ ውስጠኛው አንተ ውስጥ ያለውን የዘለለት ሐሴትን ግን አይተካም… ስትፈልግ የኖርከው ያለህን ግን ደግሞ ያላየኸውን ነው ማለት ነው…

🌊በአልማዝና በከበሩ እንቁዎች የተሞላ ሳጥን ላይ ቁጭ ብሎ እርጥባን እንደመልቀም መሆኑ ነው…

   ፫. There is the cessation of suffering…

🌊ድቁሳት ምን ቢከብድ… ፈተና ምን ቢረቅ… የሆነ ጊዜ ያበቃል… ይተናል… ይበናል… የ Impermanence ህግ እንዲህ ይላል… “All that is subject to arising is subject to ceasing.” ስለዚህ ድቁሳትን በመሸሽ አታመልጠውም… ለተፈጥሮአዊ ሞቱ ትተወዋለህ እንጂ…

🌊የድቁሳትህ ምንጮች ‘መጥፎ’ የምትላቸው ነገሮች ብቻ አይደሉም… ‘ጥሩ’ ነገሮችህም ሁነኛ ማደሪያ ናቸው… ድቁሳት ከነገሩ ተፈጥሮ ይልቅ ለጉዳዩ ካለን ጥልቅ ዝማሜ ግዘፍ ይነሳል…

🌊ሁሌም ቢሆን ከሁነቶች ጋር የመቋጠር ቅኝት አለን… ቅርፃውያን ስለሆንን ከደስታችን ቅዥትና ከሃዘናችን ጥላ ጋር ‘የዘላለሜነሽ’ ሕብረ ዜማ እናረግዳለን… Attachment (ከነገሮች ጋር መጣመር) ክፉ ነገር ነው… ከሚያልፍ ነገር መቋለፍ ደግሞ የበለጠ አደገኛ … በውድቀት ስኬት ከፍ ዝቅ መኳተንና በወዲያ ወዲህ ፔንዱለማዊ ስሌት መዋለል የመቋለፍ ውጤት ነው… ነገሮችን እንደአመጣጣቸው ተቀብሎ የሚሸኝ ግና በጊዜያዊ ደስታ ከመስከርና በሚያልፍ ሃዘን ከመሰበር ይድናል… የወንዙን አወራረድ ለማየት ሁነኛው ቦታ የወንዙ አፋፍ ነው… እዚያ ነው የ’ሁሉም ያልፋል’ ጥበብ የሚወለደው…

🌊ለስሜት ስብራት የሚገፉኝን ሁኔታዎች በትኩረት መመልከት ስጀምር የሚገባኝ አሃዱ የትስስሬ ጥልቀት ነው… ድብርት ውስጥ ስገኝ… ብቻነት ሲሰማኝ… እጦት ሲያንገበግበኝ… ዕድሜ ከሌላቸው ነገሮች ጋር አዕምሮዬ እንደታበተ አስተውላለሁ… ለጊዜው ካበረህ ጋር ለሁልጊዜ በፍቅር መውደቅ ክፉ እርግማን ነው… ሟችን ለሞቱ ተወው…

    ፬. The way out of Suffering

❄️በድቁሳት መኖር ላይ ተግባባን… ምንጭ እንዳለውም ገባን… ተፈጥሮአዊ ሞት እንደሚሞትም እንዲሁ… ከድቁሳት ነፃ መውጣትስ አይቻል ይሆን?… ይሄ የሰው ልጅ ሁሉ ጥያቄ ይመስለኛል… ቡድሐም አብርሆት ከተቀዳጀባት ዛፍ /Bodhi Tree/ የዚህን ጥያቄ መልስ ሳያገኝ አልተነሳም… አዎን ከድቁሳት ነፃ መውጣት ይቻላል… እንዴት?

❄️ቡድሐ ‘The eightfold path’ በማለት የሰየማቸው ስምንት ‘ቀኖናዎች’ አሉ… ለቀኖናዎቹ መቅናት ከድቁሳት ነፃ ያወጣል…

RightView,
Right Intention,
Right Speech,
Right Action,
Right Livelihood,
Right Effort,
Right Mindfulness and
Right Concentration ናቸው…

🌟ከዚህ በኋላ ደቆስቆስ የሚያደርጉህ ነገሮች ሲበረክቱ ከኒህ ስምንት ቀኖናዎች የትኛውን እንዳጎደልክ መርምር…

@zephilosophy
@zephilosophy
👍63🔥2😁1
እሱ፤ አንድ ሚልዮን ብር ብሰጥሽ ከኔ ጋር ትተኛለሽ?

እሷ፤ አንድ ሚልዮን ብር? ዋው! ይመስለኛል አዎ፡፡

እሱ፤ በመቶ ብርስ?

እሷ ፤ ጥፋ ከዚህ፡፡ ምን መስዬህ ነው? ሴተኛ አዳሪ?

እሱ፤ ሴት አዳሪነትሽን መጀመሪያውኑ ተስማምተናል፡፡ አሁን በገንዘቡ ላይ እንደራደር።

ልክነት መቼ እና እንዴት ነው
የሚኖረው? መቼ ነው ይህቺን ሴት ሴተኛ አዳሪ የምንላት? መቼ ነው ይህቺን ሴት ክብሯን የጠበቀችው? መቶ ብር ወይስ መቶ ሺ ብር ላይ? ወይስ አንድ ሚሊዮን ላይ? መቼ ነው ክብሯን ያጣችው?

የገነባነው ክብር እና ፅድቅ  በየትኛው የብር መጠን ላይ እንሽረዋለን? ከሻርነውስ የእውነት መልካም ሰው ነን ማለት እንችላለን?
ምናልባት ምግባራችን እንደ ሴቷ በገንዘብ ስላልተፈተነ ይሁን ጥሩ ሰው የመሰልነው ?

@zephilosophy
👍32💔64🎄1👾1
ካላመኑበት ቅድስና ያመኑበት ኩነኔ ይሻላል!
---**---

የሰው ልጅ እምቢም እሺም የማይልበት አካለ ቁመና (ተክለ ሰውነት) ተሰጥቶታል፡፡ ነገርግን ቀሪውን ማንነት እራሱ ይፈጥራል (የአእምሮ እና የስነልቦናዊ የአስተሳሰብ ምህዋር 30% ውርስ 70% አካባብያዊ ተፅእኖ):: በዚህ አካሄድም ውስጥ ከአካል ውጪ ባለው ራስን በመፍጠር ሂደት <እምነት> እና <ነፃነት> ወሳኙን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ በኛ ማህበረሰብ “በየ-አይነት መብላት” እንጂ “በየ-አይነት” ማሰብ አይፈቀድም፡፡ በምናድግበት አካባቢ ያለውን ልማድ እና ወግ ጎጂም ቢሆን ማክበራችን “ጨዋ” ያሰኘናል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ባደግኩበት ሰፈር… የአጥር ጥግ ይዞ የሚሸና ወንድ “ባለጌ” ብሎ ሚሰድበው የለም፡፡ ነገርግን እኔ ድንገት እርቦኝ ከመንገድ ዳቦ ገዝቼ እየገመጥኩ ስሄድ እንደ መብረቅ እየጮሁ “ባለጌ” የማለት ልማድ አለ፡፡ ታዲያ ደጋግሜ አሰላሰልኩኝና ከዚህ ድምዳሜ ደረስኩ በሀገራችን ‹የማህበረሰብ እንጂ የግለሰብ ነፃነት የለም!!›

አንፃራዊነቷ እንዳለ ሆኖ በየትኛውም ጉዳይ ላይ “እውነት ከወዴት ናት? የትኛው ጥሩ የትኛውስ ጎጂ ነው?” ብለን ስናብሰለስል በመጨረሻ ላይ የምንደርስበትን ድምዳሜን <እምነት> እለዋለሁ፤ ስምምነት እንጂ ማስረጃ ማቅረብ አይጠበቅም!

ልዩና አዲስ የሆነ ሀሳብን እንደመብረቅ በመጮህ አልያም በጫና ከማስቀረት ይልቅ፤ መጥፎ ሀሳብን መልሶ በሀሳብ ማሸነፍ… አልያም መልካም ከሆነ ማፅደቅ ይገባናል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን የሆነ ሰው በሀሳብ ተሸንፎ የአቌም ለውጥ ካደረገ ‹አሽቃባጭ› የሚል ተውላጠ ስም እንሰጠዋለን፡፡

የሰው ልጅ ከእናቱ ሆድ ተጨርሶ እንደወጣ ልክ እንደ ግኡዝ አካል በሀሳብ ለውጥ አያድርግ ብለን ጫና እንፈጥራለን፡፡ ይሄ ተፈጥሮን መፃረር ይሆናል፡፡

መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ‹በሌላ ሀገር ትንሽ ወንዝ ካለ መዝናኛ አድርገው ይዝናኑባታል፡፡ እኛ ሀገር ትንሽ ወንዝ ካለ የመለያያ ድንበር አድርገን እንጋጭባታለን› ይሉናል:፡ ብዝሀነት/የሀሳብ ልዩነት ላይ ለመግባባት መድረክ የሌለው ማህበረሰብ በልዩነት ለመፍረስ የሰናፍጭ ፍሬን የምታህል ትንሽ ምክንያት ይበቃዋል፡፡

አበው ‘ገንፎ ለገንፎ ዘፍ ተደጋግፎ!’ እንደሚሉት፤ ግለሰቦችን ልክ እንደ እኛ  ካልሆንክ ብሎ ማስጨነቅ ደግ አይድለም!

በነፃነት የሚፈጠር ሰብአዊነት ውስጥ ልዩ ውበት አለ!!

ከመወለዳችን በፊት የተሰጡን አካላት በሙላ ቀን በቆጠረ ጊዜ ሁላ እያደጉ ይመጣሉ፡፡ የሰው ልጅ አእምሮ ግን በፈቃደኝነት ነው የሚያድገው፡፡ ጭንቅላትህ ፈቀድክለት አልፈቀድክለትም ማደጉን አያቁምም አእምሮህ ግን ካልፈቀድክለት አይበስልም!

ታዲያ አካለሰውነት በዘፈቀደ ሲያድግ እኛነታችንን ደግሞ በፈቃዳችን እናበጃለን፡፡ በዚህ የራሳችንን ስብዕና በመፍጠር ሂደት ውስጥ ነፃነት ከሌለን ከመብዛት ውጪ ምንም አናመጣም፡፡

--> ለምን ተፈጠርኩ? ለሚለው ጥያቄ ከመላምት ያለፈ ተጨባጭ ምክንያታዊ መልስ አናበጅለትም፡፡

--> ስብዕናዬን እንዴት ፈጠርኩ/ገነባሁ? ለሚለው ግን በማስረጃ የተደገፈ መልስ ከሁላችን ኪስ ይኖራል፡፡

ፈጣሪ ግማሹን ይፈጥራል እኛ የቀረውን ማንነታችንን እንፈጥራለን!

አንድ ግለሰብን ያለነፃነት ካመነበት ጉዳይ ውጪ ነገሮችን እንዲከውን ስናስገድደው በውስጡ ፍርሀት ይነግሳል፤ ፍርሀት ደግሞ ከእለት ወደ እለት ወደ ድብቅ ክፋት ያድጋል፡፡ “የክፋት ዘር ቀን ቆጥሮ ያመረቅዛል” በአፈና የተገነባ ማንነትን የያዘ ሠው፤ ራስን ለመከላከል ብሎም ለተፈጠረበት ድብቅ ውስጣዊና ሰንካላ ስሜት ሲል ማጥቃት ይጀምራል፡፡ ተንኮል፣ ክፋት፣ ሴሰኝነት፣ ጨቋኝነት፣ መስገብገብ ብዙ ብዙ፡፡
ያለነፃነት በተገነባ ማንነት ውስጥ በራስ መተማመን ስለሚጠፋ በድካም መሸፋፈን ይጀመራል፤ በገዛ ስራው ሀላፊነትን አይቀበልም፡፡ የሰብአዊነት ውበትም ያኔ ይጠፋል፡፡

አሁን የመረጃ ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ የሁሉ ነገር ፍጥነት አስገራሚ ሆኗል!

ከማስመሰል የነፃ ትውልድ ካልፈጠርን፤ በዚህ በመረጃ ዘመን ከማስመሰል ነፃ የሆነው የሌሎች ባይተዋር ባህል ስር ሰዶ ያፈርሰናል፡፡ የታፈነው ማንነት በአንዴ ፈንድቶ እንደጎርፍ ሊጠራርገን ይነሳል፡፡

የባህር ማዶ ሰዎች በብዙ ንፅፅር ከባህላችን ሲስተያዩ ባለጌ ቢሆኑም አለማስመሰላቸው፤ የውስጥ ስሜታቸውን አለመደበቃቸውከምንም በላይ  ጨዋነት ነው፡፡

አትታዘቡኝ “ነፃነትን እንደማክበር ያለ ወደር የሌለው ጨዋነት አላውቅም!”

ገናና በነበርንበት ዘመን እራስን መምሠል እንጂ ማስመሰል የማይበረታታ እንደነበረ አስባለሁ፡፡ ለዚያም ነው ከብዙዎች የተለየነው!

አካላዊ ቁመናችን ሲፈጠር እሺም እምቢም ማለት እንደማንችለው ሁሉ፤ ዛሬም በየ-ቤቱ በየ-ሰፈሩና በየ-ስራ ዘርፉ የገዛ ስብእናችንን ለመፍጠር ስንሞክር፤ ‘እንቢ’ም ‘እሺ’ም እንዳንል ሆነን ልንጠፈጠፍ አይገባም፡፡

አንድአይነት እንድንሆን መገደድ የለብንም!
ዜጎቻችን በነፃነት የፈጠሩት ስብዕና ካላቸው ለሚያሣርፉት በጎም ይሁን መጥፎ አሻራ ሀላፊነቱን ለመውሰድ ያመቻቸዋል፡፡

በዚህ የመረጃ ዘመን ግሩም የሆነ ኢትዮጵያዊ ስብዕናችንን ጠብቀን እናቆይ ዘንድ ከልጆቻችን ጋር በግልፅ የሀሳብ ትግል አድርገንና በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ተማምነን በነፃነት ስብዕናቸውን እንዲገነቡ ልናበረታታቸው ይገባል፡፡

“ካላመኑበት ቅድስና ያመኑበት ኩነኔ ይሻላል!’’

ራሳችሁን ለመፍጠር ትጉ! ፍቅር ደግሞ ከሁሉም ትበልጣለች፡፡ አደራ ታዲያ፤ ‹ስብእናችሁን ስትፈጥሩ ፍቅርን እግር አድርጓት፤ ጥናካሬዋ ድንቅና ውበቷም ልዩ ነው! እርሷ የትኛውንም ርቀት ትሄዳለች፤ ካሰበችበት ለመድረስ የሚያቆማት አይገኝም፡፡ እንደው ምን አልባት… ምን አልባት… ከጭቃ ውስጥ ያለ እሾህ ቢወጋት እንኳን፤ ይዛው እንጂ ሰብራው አትሄድም፡፡›


@Zephilosophy
👍318🎉1
የፍልስፍና ጥቅሞች

ፍልስፍና ሰፊ እውቀት በመለገስ የሰው ልጅ ስለራሱም ሆነ ስለሚኖርበት ዓለም ሰፊ ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረግ፣ ባገኘው ሰፊ ግንዛቤም ሰው ከችግሮቹና በህልውናው ላይ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ የተፈጥሮ ሥርዓቶች ላይ የበላይነት እንዲያገኝ ማድረግና በዚህም የራሱን ህልውና አስተማማኝ ማድረግ እርካታ የተሞላበት ኑሮ መምራት እንዲችል ማድረግ ነው፡፡

ከእነዚህ የፍልስፍና አጠቃላይ ግቦችና ጠቀሜታዎች ተነስተን የተለያዩ እጅግ ብዙ ግለሰባዊና ማኀበራዊ ጠቀሜታዎችን ከፍልስፍና ማግኘት እንችላለን፡፡

🔥ፍልስፍና ጠያቂዎችና ተመራማሪዎች እንድንሆን ያስችለናል፡፡ ነገሮችን የምንረዳበት የአስተሳሰብ አድማሳችን ያሠፋልናል፣ ሰዎች ነገሮችን ከሚመለከቱበትና ከሚረዱበት በተለዬ አመለካከት እንድንረዳቸው፤ ስህተት አስተሳሰቦች የደበቁትን እውነት ይፋ ማውጣት ያስችለናል፡፡

🔥የመኖር ትርጉምን እንድንረዳና አላማ ወይም ግብ ያለው ህይወት መምራት የሚያስችለን እውቀት ይሰጠናል፡፡

🔥ችግሮቻችን በጥልቀት መረዳት ያስችለናል፣ ለችግሮቻችን መፍትሔ የማፈላለግ አቅማችንን ያሣድግልናል፡፡ በህልውናችን ላይ አዳጋ የሚያደርሱ ሁኔታዎችን አስቀድመን መረዳት እንድንችልና መቋቋም የሚያስችል ብልሃት እንዲኖረንና ከተወሳሰቡ ግዙፍ ችግሮች መውጣት የምንችልበት የሰብዕና ጥንካሬ እንዲኖረን ይረዳናል፡፡

🔥ውሳኔዎቻችን የሚያስከትሉትን ውጤት አስቀድመን ማወቅ እንድንችልና የነገን ህይወታችን በእውቀትና በማስተዋል መምራት እንድንችል ያደርገናል፤ የምናደርጋቸውን ነገሮች በምክንያታዊና ሚዛናዊ አስተሳሰብ እንዲመሩና ከስሜታዊነት፣ ወገንተኛነት፣ አድሎ ፈፃሚነት፣ አግላይነት፣ አካባቢያዊነት እና ከዘረኛነት ተላቀን ህይወታችን በህሊናዊነት እንዲመራ ያስችለናል፡፡


🔥የራሳችንን ማንነት መረዳት እንድንችል፣ በህብረሰተብ ውስጥ ሊኖረን የሚችለው ሚና ከአቅማችን ጋር የተገናዘበ እንዲሆን፣ ባለን አቅምና ችሎታ የራስ መተማመን እንዲኖረንና የሚጠበቅብንን ሁሉ በድፍረት ማድረግ እንድንችል ይጠቅመናል፡፡

🔥የምንኖርበትን ህብረተሰብና የዓለምን ሁኔታ እንቅስቃሴ በጥልቀት ለመከታተልና ማድረግ የምንችለውን በህሊናዊ ውሳኔ መፈጸም እንድንችል ያደርገናል፡፡

🔥በንግግር ወይም በጽሑፍ የሚገለጡ ሀሳቦችን አድማጭና አንባቢዎችን ግልጽ ሆኖላቸው እንዲረዱት የሚያስችል የሀሳብ ተዋረድ ያለው አስተሳሰብ ማቅረብ እንድንችል ይረዳናል፤ ብዥታ የሚፈጥሩ ዘርፈ-ብዙ ትርጉሞች ያሏቸውና ህፀፆችን ማስወገድ እንድንችል ያደርገናል፤ ትንተና የመስጠት፣ ሀሳባችን ግልጽ በሆነ ሁኔታ አጠቃለን ለመግለጽ የሚያስችል ችሎታ እንድናዳብር ይጠቅመናል፡፡ የሌሎች ሰዎችን የተሳሳቱ ግንዛቤዎች ለማጋለጥና ትክክለኛ የሆነውንና የተሻለውን ሀሳብ ለማቅረብ ይረዳናል፤ የመተቸት አቅማችን ከፍ ይላል፤ ትችቶችን ጠቀሜታ እንዲኖራቸው አድርገን መግለጽ የምንችልበት ክህሎት እናዳብርበታለን፡፡

🔥ብልህ አንባቢና አድማጭ እንድንሆን ይረዳናል፡፡ በብልጣብጥና ተንኮለኛ ተናጋሪና ሰዎች እንዳንሞኝና የተሳሳተ መንገድ እንዳንከተል፣ ምንጊዜም በምክንያትና በመረጃ የቀረቡ ሀሳቦችን ብቻ አምነን እንድንቀበል ይረዳናል፡፡

ረ/ፕሮፌሰር ዋለለኝ እምሩ
@zephilosophy
👍253
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍3
ከዛሬ አራት አመት በፊት ሁለት ሆነን ጀምረን ዛሬ ከሃያ አምስት ሺ በላይ ቤተሰቦች ሆነን በዝተናል።ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን!!
ፍልስፍናና አዲስ ሀሳብ በሚፈራበት ማህበረሰብ ውስጥ፤  የፍልስፍና ዲፓርትመንት ከመላው ዩንቨርሰቲ በተፋቀበት ዘመን  እንደዚህ መብዛታችን ቀላል ነገር አይደለም።

ፁሁፎቹ ብዙ ሰው ጋር ይደርሱ ዘንድ #ሼር ስለምታደርጉ እናመሰግናለን🙏
👍232
Leave a comment

ስለምናቀርባቸው ፁሁፎች ያላችሁን አስተያየት እንድትሰጡን እንፈልጋለን
ከቻናላችን ምን ተጠቀማችሁ? ምን እንዲጨመር እና እንዲታረም ትፈልጋላችሁ?
በዚሁ ይቀጥል?

ሁላችሁም ተሳተፉ ወደ ፊት የምናቀርባቸውን የሀሳብ ይዘቶች ይወስናል!!

👇👇👇👇👇
👍13🔥1
🙏ስለ መልካም አስተያየታችሁ ሁላችሁንም ከልብ እናመሰግናለን።ፍቅራችሁን ያለስስት ገልፃችሁልናልና እውነት ከልብ እንወዳችኋለን። ከዚህ በላይ እንድንሰራ ትልቅ ሀላፊነት ጥላችሁብናል።

ይህ የቻናል የተፈጠረው ምክንያታዊ ና ሚዛናዊ አስተሳሰብ እንዲኖረን የሚያስችሉ ፍልስፍናዎችን ና እውቀቶችን ለማጋራት ነው።በተጨማሪም አካልን፣ ስሜትን እና አእምሮን የማስገዛት ጥበብን በማስተማር  ንቁ፣ በሳል እና ብልህ ሰው እንድንሆን ማገዝ ነው። እስካሁን በዚህ ቻናል የህይወት ልማድችንንና እምነታችንን የሚጠይቁ፤  የንቃት ሀይል የሚጨምሩ ፤ ፍቅር እና መንፈሳዊነትን የሚሰብኩ  ሀሳቦችን አጋርተናል።

ሆናም ግን ካነበብናቸው እና ካወቅናቸው ብዙ መፅሀፍትና ልምምዶች ጥቂቱን ብቻ ነው የጋራናችሁ። ከዚህ በኋለ በብዛት እንድናጋራችሁ ዘንድ ፈጣሪ የማይዋዥቅ ሞራልና የማይደበዝዝ ትጋት  ይሰጠን ዘንድ እንመኛለን!!

ብዙ ሰው ጋር ተደራሽ በመሆን ትጋታችን ይጨመር ዘንድ እያንዳንዱን ፁሁፍ #ሼር ማድረግ እንዳትዘነጉ!!

@zephilosophy
👍392