«አንድ ክርስቲያን ነበር፤ እሱም በመስቀል ላይ ሞቷል»
ፍሬደሪክ ኒቼ
«በዚህ በማይታወቀው ድብቅና ውስብስብ አለም ውስጥ የምንኖር ነጻ ነፍሶች፣ በሴራው፣ በተንኮሉ፣ በሰላ ብልጠቱ አዝዞ አናዝዞ በሚገዛው ስርአት ውስጥ የምንኖር እምቢ ባዮች፤ አንዳንዴ ስርአቱን ለመውደድ አንዳንዴም ለመፍራት እንገደዳለን፡፡ ይህን ከእይታ ውጪ የሆነ ስልና ውስብስብ ስርአት አሻፈረኝ የማለት አቅም እንኳ እንዳይኖረን የፊጥኝ ታስረናል፡፡ ሁላችን ከተጣለብን ሀላፊነትና ግዴታ እንዳናፈገፍግ ተደርገን ተጠፍረናል፡፡ በርግጥ አንዳንዴ እጅና እግራችንን የጠፈረንን ካቴና፣ የአንገታችንን ካራ ተሸክመን ብንቦርቅም ብዙውን ጊዜ በዚህ የእጣ-ፈንታችን አምባገነን ስርአት ላይ ጥርሳችንን እንነክሳለን፣ ግንባራችንን እንቋጥራለን፡፡ እናም ያሻንን አድርገን ያሻንን እንሆናለን፡፡ ተርታውም ተመልካች ሀላፊነት ከማይሰማቸው ስርአት አልበኞት ይመድበናል፡፡ በርግጥ ሁሌም ቢሆን የተቺዎች ውግዘት ድርሻችን ነው፡፡
«እናንተ ነጻ ነፍሶች ምናልባት ለስርአቱ ያለን ታማኝነት፣ የከንቱነታችን ስር እንዳይሆን?! ምናልባት ስርአቱ የጣለብን የስነ ምግባር ቀምበር የደካማ ጎናችን፣ የድድብናችን ምንጭ እንዳይሆን?! ምናልባት ለስርአቱ ባለን ታማኝነት ለዛ ቢስ፣ ደባሪ ፍጡራን እየሆንን እንዳይሆን - በዚህች አጭር ህይወት፣ እፍኝ ለማትሞላ እድሜ ደባሪ ሆኖ መገኘት አያሳስብምን?»
እ.ኤ.አ ከ844 - 1900ዓ.ም የኖረው አወዛጋቢው ፈላስፋ ፍሬደሪክ ኒቼ የዘመኑ የግብረ ገብ አስተምህሮ ከእውነተኛው ግብረ ገብነት ፍጹም ተቃራኒ እንደሆነ ይገልጻል፡፡
ምክንያቱም ማንኛውም አይነት የስነ ምግባር አስተምህሮ ከሰው ልጅ ተፈጥሮ ጋር የሚጣጣም እንጂ በፍጹም የሚቃረን መሆን የለበትም፡፡ ኒቼ የሰው ልጅ ተፈጥሮውን፣ ደመ ነፍሱንና ውስጣዊ ፍላጎቱን መሰረት እድርጎ ፍላጎቱን ለማሟላት የሚዋትት ፍጡር ነው በሚለው የአርተር ሾፐንሀወር አስተሳሰብ ይስማማል፡፡ ይሁን እንጂ ከሾፐንሀወር የጸለምተኝነት ፍልስፍና በተቃራኒ ኒቼ ውስጣዊ ፍላጎታችንን ከማጥፋት ወይም አንዳንድ የዘመኑ አስተምህሮቶች እንደሚሰብኩት ከማፈን ይልቅ ሙሉ በሙሉ በማሟላት ስኬትና እርካታ መጎናጸፍ ይቻላል ብሎ ያምናል፡፡
የኒቼ ልእለ ሰብ (Super human) የአስተሳሰብ ምጥቀትን ከአካላዊ ልእልና ጋር አቀናጅቶ የተላበሰ ሰው ነው፡፡ እስካሁን ከዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው ባይኖርም ኒቼ ከመጪው ትውልድ ይከሰታል ብሎ ያምናል፡፡ እስካሁን በእጅጉ ሀያል የሆኑ ታላላቅ ሰዎች ቢከሰቱም ልእለ ሰብ ከመባል የሚያጎሏቸው ባህሪያት ነበሩ፡፡ የኒቼ የልእለ ስብ እሳቤ የቄሳርን ታላቅነትና ግርማዊነት ከእየሱስ የሞራል ምጥቀት ጋር አቀናጅቶ መላበስ ነው፡፡
ሰው ከዝንጀሮዎች ሁሉ የላቀ እንደመሆኑ የኒቼ ልእለ ሰብም ከሰዎች ሁሉ በደረጃ የላቀ ልዩ ፍጡር ነው፡፡ በአስተሳሰብ ከሁሉ የላቀ በመሆኑ ይቅርታና ምህረት አይፈልግም፤ ማንኛውንም ስህተት መተውና መርሳት ይችላል፡፡ በመንፈስ እንደ እየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ ለጠላቶቹ ምህረት እየጠየቀ ነው፡፡
ፍሬደሪክ ኒቼ እየሱስ ክርስቶስ ፍጹም የሆነ የክርስትና ተምሳሌት እንደነበር አበክሮ ይገልጻል፡፡ ሆኖም ክርስቲያኖች ይህን ፍጹም ተምሳሌት መከተል ተስኗቸዋል፡፡ በመሆኑም በኒቼ አባባል «አንድ ክርስቲያን ነበር፤ እሱም በመስቀል ላይ ሞቷል» ይላል።
ኒቼ በአምላክ መኖር ባያምንም በአምላክ እናምናለን እያሉ በሀጢያት በሚጎድፉት ላይ የሚያወርደው ትችት በእጅጉ ስልና ገደበ ሰፊ ነበር፡፡
@Zephilosophy

❤58👍4😡3🥰1👏1😁1
ከማበዴ በፊት
ከማበዴ በፊት ያው እንደ እናንተ ነበርኩ፡፡ እኔም እናንተም እኮ እብዶች ነን፡፡ ልዩነቱ እብደታችንን በቅጡ አውቀን መተወኑ ላይ ብቻ ነው፡ ፡ ከማበዴ በፊት እንደ እናንተ እንደ እያንዳንዳችሁ ነበርኩ፡፡ መንጋ ሂድ ሲሉኝ የምሄድ ቁም ሲሉኝ የምቆም፡፡ ሰው የመሆንን ድሪቶ የምጥፍ አንድ ደቃቅ ፍጡር የልማድ እስረኛ፡፡ ሰው ወደዚህ ምድር በተፈጥሮ ይሁንታ ሲመጣ ሌጣው ነበር፡፡ እናንተ ግን አባቶቻችሁ ያወረሷችሁን ዘመን የተጫነው ደበሎ ድሪታችሁን ያለ ውዴታው ታሸክሙታላችሁ፡፡ ከዚያ ወዲያ ሰው እንደ ሰው ሳይሆን እንደ እናንተ ይሆናል፡፡ እንደ እናንተ ሙስሊም፣ ወይም እንደ እናንተ ክርስቲያን ከምንም ውጪ እንዲሆን አትፈቅዱለትማ፡፡ እንደ እናንተ ኢትዮጵያዊ ወይም እንደ እናንተ አሜሪካዊ፤ እንደ እናንተ ሀብታም ወይም እንደ እናንተ መናጢ ድሃ.... ኤዲያ ሰው ከዚህ ውጪ የሕይወት ቅኝት የለውም ማለት ነው?
እንዳልኳችሁ ነው፡፡ ከማበዴ በፊት እኔ እንደ እናንተ እንደ እያንዳንዳችሁ ነበርኩ፡፡ በሚያዳልጠው ህዋ ላይ ሞትን ዘወትር የምሸሽ ፈሪ ፍጥረት፤ ለእናንተ ጣዖታት ሱባኤ የምይዝ፣ ለእናንተ አማልክት መስዋዕት የማቀርብ ድንጉጥ... እንደ እናንተ ህሊናን የሚያክል ትልቅ እግዚአብሔርን እያታለልኩ ከደመና በላይ በምናብ ለሰቀልኩት እግዜር የለበጣዬን የማጎበድድ፣ የሞራል ዝቅጠቴን እንደ ሥልጣኔ የምቆጥር ግልብ ነበርኩ፡፡ ነገርኳችሁ በቃ ከማበዴ በፊት እንደ እናንተ እንደ እያንዳንዳችሁ ነበርኩ፡፡ በተዘፈነበት የምጨፍር፣ በተለቀሰበት የማለቅስ፣ ጮኽ ብዬ የምስቅ ተራ ሰው... ለነገሩ ከእናንተ የወጣ ሰው እንደ እናንተ ከመሆን ውጪ ሌላ ምን ዕጣ አለው? አትፈቅዱለትማ!
ዕብደቱ ሲጀማምረኝስ ምን ሆንኩ? ለእናንተ እንዲገባችሁ እንጂ ዕብደት ማለቴ ነገርዬው ያው ተምሰልስሎት ቢጤ ነው፡፡ መጀመሪያ ቤተሰቦቼን ተውኩ፡፡ በመቀጠል የእናንተን የእያንዳንዳችሁን አስተሳሰብ ናቅኩ፡፡ እግዜራችሁም አላስፈለገኝም፡፡ በመጨረሻስ? በመጨረሻማ የማይቀረው ዕጣዬን ራሴን መካድ ሆነ፡፡ በፍለጋ ሕይወት ትልቁ መገለጥ እኮ ይሄ ነው፡፡ እንዳልኳችሁ ከማበዴ በፊት እንደ እናንተ እንደ እያንዳንዳችሁ ለማዳ እንስሳ ሆኜ ከቤት ወደ ሥራ ከሥራ ወደ ቤት መመላለስ የማይሰለቸኝ፣ መንጋዬን የምከተል ነበርኩ፡፡ አሁን ይሄ ታሪክ
ተቀየረ፡፡
እንዲያውም የአበድኩ ሰሞን እግዚአብሔርን መንገድ ላይ አግኝቼው ነበር መሰለኝ፡፡ ላናግረው ስል ተሰወረብኝ፡፡ እብዶችን ይፈራል ልበል? ወይስ እሱም በራሱ መንገድ አብዷል? መቼም ያላበደ አምላክ ይህችን የተቀዣበረች ዓለም ሊፈጥር አይችልም፡፡
ያበድኩ ሰሞን መጀመሪያ የተገለፀልኝ እውነት ግን የእናንተ የእያንዳንዳችሁ ሕይወት ጥቂትም ለዛ ያገኘው ስለ አምላክ ባላችሁ ቀቢጸ ተስፋ ላይ መሆኑ ነው፡፡ እውነትስ ይህ ምስኪን ጉስቁል ሕዝብ ድንገት እግዚአብሔር የለም ሲሉት በቀፅበት ገበያ መሀል የጣሏት ጥንቸል ሆኖ መጠለያ ሊያጣ አይደለምን? ለነገሩ እኔም እናንተም እንሸሻለን፡፡ ልዩነቱ የመሸሻ መጠሊያችን ብቻ ነው፡፡ እኔ ወደ ምንምነት አዘቅት. እናንተ ደግሞ ወደ እምነት ቀቢፀ ተስፋ .. እኔ ስነቃ እናንተ ባንቀላፋ ደመነፍስ
ካበድኩ በኋላ በዓለም መሀል እያለሁ ከዓለም ተነጥያለሁ፡፡ ግን የቱንም ያህል ብሸሽ ላመልጣችሁ አልቻልኩም፡፡ እንደ ጥላዬ በየሄድኩበት ትከተሉኛላችሁ፡፡ ለነገሩ ታስፈልጉኛላችሁ፡፡ ሀኪሞች መድሀኒቶቻቸውን በአይጦች እንደሚሞክሩ እንደዚያ እኔም በእናንተ ጎስቋላ ሕይወት መመራመሩን ወድጀዋለሁ፡፡
በነገራችን ላይ በዓለም ላይ እንደ ሁሉም እንድሆን ቢፈቀድልኝ የእናንተን እግዜር ግን መሆን አልፈልግም፡፡ ውዳሴና ምስጋናን አምርሬ እጠላቸዋለሁ፡፡ አስቡት እስቲ ወፈ ሰማይ መላእክት እግሬ ስር ጠብ እርግፍ ፍርጥ እያሉ ሲሰግዱልኝ ማየት እንዴት ያስጠላል? ለነገሩ የእናንተ እግዜር እና የምድር ነገሥታት አንድ ናቸው፡፡ የሚገዙላቸውን ይወዳሉ፡፡ የሚያሙፁትን በሰይፍ ይቀጣሉ፡፡ አለቀ፡፡ ትናንት ጣዖታቱ ሀውልቶች ነበሩ፡፡ ዛሬ ጣዖታቱ ከደመና በላይ ናቸው፡፡
እኔ ለእናንተ አብጃለሁ፡፡ እናንተ ለእኔ ሙልጭ ያላችሁ እብዶች ናችሁ፡፡ በዚህ መሀል እውነት የለም፡፡ ይሄ የምርምሬ ግኝት ነው፡፡ ተብሰልሳይ ሰው ወታደር ቢሆን ጥይቱ ጥያቄው ነው፡፡ በተምሰልስሎት ውስጥ ጥያቄዎች አያልቁም መልሶችም አይነጥፉም፡፡ ሆኖም ሁሉም መረዳት፣ ሁሉም አስተውሎት የጥርጣሬ፣ የምናልባት ብቻ ነው፡፡
አሁን ሙሉ ለሙሉ አብጃለሁ፡፡ በምንም ለምንም የማልጓጓ፣ በምንም ለምንም የማልፈራ፣ በምንም ለምንም የማልደነግጥ... ሆኛለሁ፡፡ እንደ እናንተ የጊዜ ቅጣት እና በረከት ለእኔም ይደርሰኛል፡፡ ውርጩ ያወረዛኛል፡፡ ዝናቡ ያበሰብሰኛል፡፡ ፀሐዩ ያቃጥለኛል፡፡ አሁን ረሃብን ረስቸዋለሁ፣ ማፍቀር ተዘንግቶኛል፣ መጥላትም ተረስቶኛል፡፡ እናስ ዓለምን አላሸነፍኳትም ትላላችሁ? በምን ታታልለኛለች?
📖ከባዶ ላይ መዝገን
ያዕቆብ ብርሀኑ
@zephilosophy

❤56🔥8👍5
ከፈሪሳ የመፅሀፍ ገፆች የተቆነጠሩ መስመሮች
“ እነሆ የምስክርነቴን ሽንቁር እደፍን ዘንድ ጀርባዬን ለሰጠሁት መልክአምድር ደረቴን አቀበልኩ። ወገኖቼ እንደገቦ ፍሬ በያሉበት ተንጠባጥበው ዐየሁ። ሕብረት አጥተዋልና በጥንቱ ኩራት ፈንታ ከፊታቸው ፍርሐትና ድንጋጼ ወሯቸው ዐየሁ። በምድራቸው ሁሉ ፈጣሪያቸው ጆሮውን አላዘነበለም። በፊታቸውም መልካም ሆኖ የታያቻውን ኹሉ ሳይመረምሩ ያደርጋሉ። "
“ ወገኖቼ ከማነሳቸው የተነሳ ዕውነትና ትዕምርት ቀርቶ ውሸትና ቅዥት እንኳ መለየት የማይችሉ ኾነዋል፣ ሲገድሉም ኾነ ሲሞቱ አለማወቅ ውስጥ ኾነው በኩራት ተንጠርብበው ነው።"
"አባቶቻችን ብቻ ሳይሆን ወንድሞቻችንንም አጥብቀን የምንጠላ ኾንን። ይኸው እዚህ ደረስን። ከእዚህ ማን ያውጣን? ጌትነታችን አባቶቻችን በገነቡት ቤት ውስጥ ቀርታለች። “ዓመቶች እየቀጠሉ በኼዱ ቁጥር ባልደረሱ የተሻለ ነበር የሚያሰኙ የሚታዩና የሚያሰቃዩ ብዙ ነገሮች አሉ” እንደተባለ ፣ እንዲሁ ሆነ።"
"ሀገር የማይተማመኑበት ሽሽት ኾኗል። ህዝቡ ወዴት? እንዴት? እንደምን? ለምን? እንደሚኼድ የማያውቅ ደራሽ ኾኗል። ”
“ እንደመስቀል ደመራ ከየቤቱ የተውጣጣ የክፋት ችቦ ለኩሰናል። እኛኑ መልሶ እስኪያቃጥለን ድረስ በደስታ ሞቀነዋል። ”

❤49🔥4👏1
"ነጻ መውጣት የሚችለው ለመጠራጠር የደፈረ አእምሮ ብቻ ነው።"
ፍልስፍና የመልሶች ስብስብ አይደለም። ገና ከመነሻው የሚጀምረው በሌሎች የቀረበልንን እውነት በመጠራጠር ድፍረት ነው። እውነተኛ ፍልስፍና የመጻሕፍት ስብስብ ሳይሆን የነፍስ ዓመፅ ነው፤ በሕይወት እያሉ እንደ ሙት የመቆጠር፣ በድን ሆኖ የመኖር እምቢተኝነት ነው።
ፍልስፍና የሚኖረው በሰፋፊ የመጽሃፍት መደርደሪያዎች ሳይሆን በቀጭኑ የደም ሥራችን ውስጥ ነው። የሚጀምረው በታላላቅ ስሞች ጥቅስ ሳይሆን በልባችን ውስጥ በምታስተጋባው "ለምን?" የምትል ጥያቄ ነው። ይህች ጥያቄ አንዴ ከተጠየቀች የያዝነው ሁሉ ይናወጣል።
ፍልስፍናን መረዳት ማለት የጥንት ጠቢባንን ሐሳብ መሸምደድ አይደለም። ይልቁንም እነሱ ያኔ የተሰማቸውን የእውነት ረሐብ እና የገጠማቸውን የጥርጣሬ ስቃይ በራሳችን ሕይወት ውስጥ ዳግም ማግኘት ነው። መጻሕፍት ካርታ ናቸው፤ ነገር ግን ጉዞውን መጓዝ ያለብን እኛው ነን። ፍልስፍና የምንማረው ነገር ሳይሆን ሕይወትን እንደ ተራ ነገር መቁጠር ስናቆም በነፍሳችን ውስጥ የሚቀጣጠል እሳት ነው።
እውነተኛ ራስን ፈልጎ ማግኘትና ራስን ሆኖ መኖር ትልቁ ተጋድሎ ነው። ባህል፣ ማኅበረሰብ፣ ቤተሰብ፣ ወይም ምቾት የለጠፉብንን እልፍ ጭምብሎች አንድ በአንድ መግፈፍን ይጠይቃል። እና ይህ ሂደት በጣም ያማል፤ ቅዠትን ከእውነት ነቅሎ ማውጣት ሁሌም ዋጋ ያስከፍላል። ነገር ግን ከዚህ ስቃይ በቀር ወደ እውነተኛ ማንነት የሚያደርስ ሌላ መንገድ የለም።
ይህ ውስጣዊ ቁፋሮ ጸጥ ያለ ተግባር ነው። ታላቅ መድረክ አይሻም። አንድ የጋለ አመለካከት ሲሰማችሁ፣ ቆም ብላችሁ "ይህ ሐሳብ የእኔ ነው? ወይስ የባህሌ፣ የቤተሰቤ፣ የአስተዳደጌ ማሚቶ?" ብላችሁ መጠየቅ ነው። አንድ ውሳኔ ስትወስኑ፣ "የምጓዘው ዋጋ ወደምሰጠው ነገር ነው? ወይስ ከምፈራው ስሜት እየሸሸሁ ነው?" ብላችሁ ራሳችሁን መመርመር ነው።
እነዚህ ትናንሽ ግን ሃቀኛ ጥያቄዎች የሐሰት ሰንሰለቶችን የሚበጥሱ የመጀመሪያ መሣሪያዎች ናቸው።
ፍልስፍናን መኖር ማለት እነዚህ ጥያቄዎች እንዲለውጡን መፍቀድ ማለት ነው። ዋናው ነገር እውነትን መያዝ ሳይሆን ለእውነት በቅንነት መገዛት ነው። ዓለም የአእምሮ ሰላም የሚገኘው እርግጠኛ በመሆን እንደሆነ ይሰብከናል። ፍልስፍና ግን በሹክሹክታ "ሰላም የሚገኘው ከእውነት ጋር በመታረቅ ብቻ ነው፣ እውነት ደግሞ መጀመሪያ ላይ ሁሌም ነውጠኛ ናት" ይለናል።
የመንጋው ሙቀት፣ የብዙኃኑ ጭብጨባ፣ እንደ ሰው የመኖር ምቾት ሁሌም አማላይ ነው። ከእውነት ብቸኝነት ይልቅ የተለመደውን የጋራ ውሸት መምረጥ ይቀላል። ማኅበረሰቡ ለዚህ ምቾት የሚጠይቀው አንድ ነገር ብቻ ነው፦ ልዩነትታችንን እና እውነተኛነታችንን አሳልፈን እንድንሰጥ። ግን ለዚህ ምቾት ብሎ ነፍስን አሳልፎ መስጠት ትልቅ ኪሳራ ነው።
ይህን ግብይት አለመቀበል፣ ከብዙሃኑ ተለይቶ የራስን እውነት መፈለ ትዕቢት ሳይሆን ለራስ መታመን ነው። እውነተኛ ዓመጽ ጩኸት ሳይሆን በማስመሰል የመኖር ጸጥ ያለ እምቢተኝነት ነው።
ፍልስፍና ምቾት ሳይሆን ግልጽነት ነው። ቅዠቶችን ያቃጥላል እና ከቃጠሎው የሚተርፈው ብቸኛው ነገር እውን ነው። ይህ እውነታ ከባድ ነው ምክንያቱም ትርጉም ያለው ነገር ሁሉ ክብደት አለው። ነገር ግን ከዚህ ክብደት ጋር ያልተጠበቀ ቅለትም ይመጣል። የማስመሰልን ከባድ ሸክም ማውረድ፣ ለሌሎች ጭብጨባ መኖር ማቆም፣ በመጨረሻም በራስህ መሬት ላይ ቀጥ ብሎ መቆም... ይህ ቅለት የነጻነት ደስታና እርካታ ነው።
ስለዚህ ፍልስፍና እንዲያናውጣችሁ፣ እንዲያቃጥላችሁ፣ ልማዳችሁንና እምነቶቻችሁን ሁሉ እንዲፈታተን ፍቀዱለት። ምክንያቱም ነጻ መውጣት የሚችለው ለመጠራጠር የደፈረ አእምሮ ብቻ ነው። ፍልስፍና እሳት ነው፤ ቃጠሎውን መቋቋም ከቻልክ ነፍስህን ለኩሶ ያበራታል።
ዮናታን በጋሻው

❤73👏13👍8🔥7🥰4😁3💯3👎2
"እውነት ከሰው ልጅ ፍላጎት ውጭ ነው በስምምነት አይፈጠርም፡፡ እውነት ከሰው ልጅ ፖለቲካዊ ስልጣንና ሀይል ጋርም ግንኙነት የለውም፤ የኃይል ብዛት እውነትን ማጥፋትም ሆነ መፍጠር አይችልም፡፡ በርግጥ እውነትን የኃይለኞች ፍላጎት አድርገው የሚተረጉሙ አሉ፡፡ የራሳቸውን ፍላጎት ህዝቡ ሁሉ የሚገዛበት እውነት አድርገው ለማቅረብ ቄሱ መፅሐፍ ቅዱስን፣ ሼሁ ቁርዓንን፣ ሀብታም ገንዘቡን፣ ባለስልጣን ደግሞ ህግንና ሚዲያን ይጠቀማሉ፡፡ በዚህም የተነሳ ሀይማኖት፣ ገንዘብ፣ ስልጣንና ሚዲያ እውነትን የመፈብረኪያ ማሽኖች እየሆኑ በዘመናት ሁሉ ታይተዋል፡፡’’
ኢትዮጲያዊው ፈላስፋ ዘርዓያዕቆብ
@zephilosophy
ኢትዮጲያዊው ፈላስፋ ዘርዓያዕቆብ
@zephilosophy
👍53❤25
በአንድነት ሁኑ
"በጥልቁ ተፈጥሯችን ውስጥ አክራሪነት ሳይሆን ሰብአዊነትና ሁለንተናዊነት ነው ያለው፡፡ ፍቅርንና ጋብቻን የፈጠረ አምላክ በእናንተ ፍቅር ይነግሳልና ክርስቲያኑ ከሙስሊሙ እየተፋቀራችሁ ተጋቡ፤ ሃይሞኖታችሁን አልፋችሁ ፍቅርም ሆነ ጋብቻ እንዳትመሰርቱ የሚል ትዕዛዝ ፍቅርን ከፈጠረ አምላክ የተሰጠ ሊሆን አይችልም፡፡ እግዚአብሔር በፍቅር ገደብ የለሽነት ይደሰታል እንጂ እናንተ እንደምታስቡት ፍቅርን በመገደብ አይከብርም፡፡
መመገብን የተገባ አድርጎ በምግብ የሚኮንን አምላክ የለንምና የክርስትያን፣ የሙስሊም ሳትሉ ለጤናችሁ የሚስማማውን ምግብ ሁሉ በአንድነት ሆናችሁ ተመገቡ፡፡”
ብሩህ አለምነህ
📖ፍልስፍና

❤40👎24👍10🙈8😡4😁3🤔3😭2🤣1👀1
"ሙዚቃን ኃጢያት አታድርጉት"
ሙዚቃንና ዳንስን ተፈጥሯዊ ባህሪያችን አድርጎ፣ በሙዚቃና በዳንስ የሚኮንን አምላክ የለንምና ዝፈኑ፣ ደንሱ፡፡ ስትደንሱ ሀሴት ታደርጋለችሁ፣ ስትዘፍኑም ጥልቁ ተፈጥሯችሁ ውስጥ ትገባላችሁ፡፡ ሙዚቃ እና ዳንስ አካልና እአምሮ ፍፁም የሚዋሃዱበትና ከመላው ዩኒቨርስ ጋርም ኀብረት የሚፈጠርበት
ክስተት ነው፡፡ እግዚአብሔር ምን አይነት ጥልቅ ተፈጥሮ ውስጣችን እንዳስቀመጠ ማወቅ የምትችሉት በመመሰጥ አሊያም በሙዚቃ መሪነት ነው፡፡
ስለዚህ ሙዚቃን ኃጢያት አታድርጉት፡፡ ወደ ኃጢያት የማይመራችሁን ውብ ሙዚቃዎች ሁሉ ያለጥርጣሬ በደስታ አዳምጧቸው፤ አብራችሁም አንጎራጉሩ፡፡
የሙዚቃን ውበት፣ የሙዚቃን ሃይል አድንቁ እንጂ የሃይማኖት አባቶቻችሁ እንደነገሯችሁ ሙዚቃን አታውግዙ፡፡ ፍቅርን በስዕል መግለፅ ኃጢአት አይደለም ፍቅርን በስጦታ፣ በግጥም በቃላትና በመሳም መግለፅ አልተከለከለም፤ ታዲያ ፍቅርን በሙዚቃ መግለፅ ስለምን እንደ ኃጢያት ይቆጠራል።
ሙዚቃ ወደ ጥልቁ ተፈጥሮአችሁ የምትሄዱበት መንገድ ነው።መልካም ግጥሞችንና ሀሳቦችን መርጣችሁ እንደምትሰሙት ሁሉ መልካም ሙዚቃዎችን መርጣችሁ አጣጥሙ።

👎58👍49❤9🔥4👏4😁3🤔3🥰1
"ተገኘ የተባለው ድፍድፍ የጠላ ነው እንዴ"
(በእውቀቱ ስዩም)
በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሳቢያ ወትሮም በጫፍ ላይ ያለው ኑሩዋችን የቁልቁሊት እየነካው ነው፤ ድሮ “ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ “ ይባል ነበር ፤ የሚገርመው እኛ ከኑጉ አርባ ሚሊዮን ክንድ ርቀን ፥ ዘነዘናው አላስተረፈንም፤
በቀደም የኢንትርኔቱን ኬብል ከቀይባህር ላይ ሊበጥሱት እየተሰናዱ ነው ፤ የሚል ወሬ ስለሰማሁ ለምንም ለምንም ብየ ባለሀያ አንድ ኢንች ቲቪና ዴክ ገዛሁ፤ ከዚያ ቪድዮ ማከራያ ቤት ፍለጋ አዲስአበባን ሙሉ ዞሬ ስላጣሁ ፥ ከሳይንስ ሙዝየም ፥ “ማዘር ኢንዲያ እና “ፋዘር ፓኪስታን “የተባሉ ፊልሞችን በVHS ተከራየሁ፤
ኑሮ ሁሉም የሚወድቅበት ፈተና እየሆነ ነው ጎበዝ!
ቅድም ቤንዚን ፍለጋ ከጃንሜዳ እስከ ቀበና የተሰለፉትን መኪኖች አይቸ ሆዴ ባባ ! አንዳንዶች መኪናቸው ውስጥ ተኮራምተው እኔ በእግሬ አፈስ አፈስ ሳደርገው በከባድ ቅናት ይመለከቱኛል፤ አንዳንድ ባለመኪኖች ጥበቃው ረጅም ጊዜ እንደሚፈጅ ቀድመው ስለጠረጠሩ፤ ስንቅ መድሀኒት ትራስና ብርድልብስ ሳይቀር ይዘው መጥተዋል፤
እረ የነዳጅ ያለህ ! የሆነ ጊዜ ላይ ተገኘ የተባለው ድፍድፍ የጠላ ነው እንዴ ? ውሀውን ወደ ወይን የቀየርህ ጌታ ፤ከሀይቆች አንዱን መርጠህ ወደ ናፍጣ ቀይረህ አስደምመን እንጂ ! አሜን !
ድሮ የቸገረው ሰው በአለባበሱ ይታወቅ ነበር፤ አሁን ዘንጦ የሚቸገር ሰው እየበዛ ነው፤ አንድ ደህና የለበሰ ሰው መንገድ ዳር ቆሞ እጁን ከዘረጋልኝ ፥ ለምጽዋት ይሁን ለሰላምታ መለየት እየተቸገርኩ ነው፤
በቀደም የሆነ ካፌ ገብቼ ሳንዱቹ ስበላ ከፊት ለፊቴ የተቀመጠ ሰውየ ደጋግሞ ያፈጥብኛል፤ እኔም ባጻፋው አፈጠጥኩበት፤ ሰውየው የጣልያን ሱፍ ለብሶ ፥የኩባ ከራባት አስሯል፤ “ ወንድሜ!” አለኝ “ ወንድሜ! የሳንዱችህ መአዛ እየተፈታተነኝ ስለሆነ አንዴ አስነክስኝ “ አለኝ ፤
አዘንኩ፤ ተከዝኩ፤ ላለማልቀስ እየታገልኩ ብድግ ብየ፥ የሳንዱቹ መአዛ ወደ ሰውየው አፍንጫ የማይደርስበት ቦታ መርጨ ተቀመጥኩ፤

🤣135❤31😁21👍12😱3🔥2😢2🤔1
Manipulation
ብዙ ጊዜ በፍልስፍና እና የስነልቦና ውይይቶች ውስጥ በተለይም በሃይማኖት እና ፖለቲካ ርዕሶች ላይ Manipulation የሚል ቃል እንጠቀማለን። ይህ ግን ቃል ብቻ ሳይሆን ጥልቅ የሆነ ሃሳብም ጭምር ነው።
Manipulation ምንድን ነው? ማኒፒዩሌሽን የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ ማታለል ወይም ማጭበርበር ተብሎ የሚተረጎም ሲሆን ሃሳቡም:
የሰዎች ሃሳብ፣ ስሜት ወይም ድርጊት ላይ ከዕውቅናቸው ውጪ ወይም ሳያስተውሉት ተጽዕኖ ማድረስ ወይም መቆጣጠር የሚል ነው።
Manipulation ግልጽ የሆነ ስለት ያለው ዓይነት ብቻ ሳይሆን ፈገግታ የሚለብሰም ነው። ፍቅርን፣ ፍርሀትን እና ቋንቋን እንደ መሳሪያ የሚጠቀም አይነት ነው።
Manipulation ስለ ጥንካሬ አይደለም። ትክክለኛውን ስሜታዊ ጊዜ የመጠበቅ ችሎታ ነው። ስትደክሙ፣ አብሮነትን ስትራቡ ወይም ትርጉም ስፈልጉ ያውቃል። በሩን አይንኳኳም—በወረስናቸው ታሪኮች እና እኛ ለመፈተሽ በጣም በምንፈራቸው እምነቶች ውስጥ ይንሸራተታል።
ብዙውን ጊዜ የሚጀምረው በመተማመን ነው። አንድ ሰው የእናንተን እሴቶች ያንጸባርቃል፣ ቋንቋችሁን ይናገራል፣ ፍርሃታችሁን “ቅዱስ”፣ ህመማችሁን “የእቅዱ አካል” ብሎ ይጠራቸዋል። ድንገት ስትነቁ እሱን እየተከተላችሁ አይደለም—እሱ እንድትሆኑ የገነባላችሁን የእራሳችሁን ስሪት እየተከተላችሁ ነው።
Manipulation በሃይማኖታዊ አመራር ውስጥ እንደ መለኮታዊ ማስፈራሪያ ሆኖ ይመጣል።
“ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፣ አትጠይቁ” ተብላችኋል።
ግን የእግዚአብሔር ድምፅ ጭምብል ለብሶ ወግ ቢሆንስ የሚያስተጋባው?
የገሃነም ፍርሃት፣ የመዳን ተስፋ—እነዚህ ሁልጊዜ መንፈሳዊ እውነቶች አይደሉም። ስሜታዊ መልህቆች ናቸው። እምነትን እየመረጣችሁ አይደለም። ከእሳት እየሸሻችሁ ነው።
በፖለቲካውም ውስጥ ተመሳሳይ ቲያትር ነው።
መሪዎች “እኛ የህዝብ ነን እነሱ ጠላት ናቸው” ይላሉ።
እና ልክ እንደዚህ ውስብስብነት አፈር ይበላዋል።
Manipulation ሐሰተኛ ግልጽነትን ይፈጥራል። እንድታስቡ አይፈልጉም—ቶሎ ምላሽ እንድትሰጡ ይፈልጋሉ፣ እንድታስተጋቡ።
ቁጣ ምንዛሬ ይሆናል። ታዛዥነት መልካም ባህርይ ይሆናል። ጥርጣሬ ክህደት ይሆናል።
ይህ ሁሉ የሚሆነው ደግሞ እውነተኛ ችግሮች— ድህነት፣ ኢፍትሃዊነት፣ ድንቁርና—ዝምታን ለብሰው ባሉበት ነው።
አንዳንዶች "ሁሉም Manipulation ክፉ አይደለም
አንዳንድ ጊዜ እናት ለልጇ ስለ ከባድ እውነት ለስላሳ ታሪክ ትናገራለች።
አንዳንድ ጊዜ አስተማሪ የተኛ አእምሮን ለመቀስቀስ ምቾት መንሳት ያመጣል።
ያ ጭካኔ አይደለም—ስልታዊ እንክብካቤ ነው።" ሲሉ ይሞግታሉ።
ስለዚህ ጥያቄው የሚሆነው: የማንቂያ Manipulation ስህተት ነው?
ወይስ አሳሪ ሰንሰለት ሲሆን ብቻ ነው ስህተት የሚሆነው?
እና ከዚያ Self-manipulation አለ—በጣም ቅርብ የሆነ አይነት—ራስን ማጭበርበር።
መታዘዝ ጥበብ እንደሆነ እራሳችንን እናሳምነዋለን።
የተወረሱ እሴቶችን እንደ ግላዊ እውነቶች እንቆጥራለን።
ጥርጣሬን ባላየ ፈገግ እንላለን።
ሥነ ምግባር ብለን እንጠራዋለን፤ ግን ምናልባት የተለባበሰ ፍርሃት ብቻ ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ Manipulationን እንዴት እንዋጋለን?
በንዴት አይደለም። በኩራት አይደለም። በግልጽነት ብቻ።
እንጠይቃለን፡ ይህ እምነት ከየት ነው የመጣው?
የማንን ድምጽ ነው የምታዘዘው?
እያሰብኩ ነው—ወይስ ሀሳብን እየተወንኩ?
ማጭበርበር አንዴ ከተሰየመ ኃይሉን ያጣል።
እና ፍርሃት አንዴ ከተጠየቀ፣ መንገዳችንን ሊመራ አይችልም።
ቀዳማዊ ፍልስፍና
(ዮናታን በጋሻው)

❤43🔥7👎4👍1
አንድ ጊዜ አንድ ሰው ትልቅ ኩሬን የግሉ ያደርጋል፡፡ ትንሽ ሊሊ አበባም በኩሬው ላይ ትበቅልበታለች፡፡ ሰውዬውም በሆነው በጣም ደስተኛ ይሆናል፡፡ እሱ ሁሌም ቢሆን ሊሊ አበባን እንደወደደ ነበር፡፡ ግን ከዚያ በኋላ ሊሊ አበባዋ በየቀኑ ራሷን በእጥፍ ማባዛቷን ትቀጥላለች፡፡ ውሎ አድሮም ኩሬውን በሙሉ ልትሸፍነው ስለሆነ ሰውዬው በዚህ መጨነቅ ይጀምራል፡፡ እናም ሰውዬው ከኩሬው ውስጥ ዓሳዎች ነበሩት ዓሳዎቹን ደግሞ ለምግብነት ይጠቀምባቸው ሥለነበር ጭንቀቱ ጨመረበት፡፡ አንድ ጊዜ ኩሬው በእፅዋት ከተሞላ በኩሬው ውስጥ ያሉት ዓሣዎች ይሞታሉ፡፡ ሰውዬው ደግሞ ሊሊ አበባዎቹን መቁረጥ አልፈለገም ፤ ዓሣዎቹም እንዲጠፉ አልፈለገም በግራ መጋባትም ውስጥ ሆነ ፡፡ ወደ አንድ ባለሙያ ዘንድም ጋር ሄደ፡፡ ባለሙያውም ቀኑን ካሰላ በኋላ "አትጨነቅ ሊሊው ሁሉንም የኩሬውን አካል ለመሸፈን አንድ ሺህ ቀናት ይወስድበታል፡፡ አበባው ትንሽ ሲሆን ኩሬው ደግሞ በጣም ትልቅ ነው፡፡ ስለዚህ ምንም መጨነቅ አያስፈልግህም" አለው::
ከዚያም ባለሙያው ፍፁም ትክክል የሆነ መፍትሄን ነገረው፡፡ እሱም "ኩሬው በሊሊ አበባዎች ግማሽ በግማሽ እስኪሸፈን ድረስ ጠብቅ ከዚያም አበባዎች ከግማሽ በላይ እንዳይሄዱ ቁረጣቸው፡፡ ሁሌም ቢሆን ነጮቹን አባባዎች እና ዓሣዎቹን አደጋ ውስጥ ሳይገቡ ግማሹን የኩሬ አካል ለአበባዎቹ ግማሹን ደግሞ ለዓሳዎቹ በማድረግ በሁለቱም ዘና ማለት ትችላለህ" ይለዋል፡፡ መፍትሄው ፍፁም ይመስላል፡፡ እናም አንድ ሺህ ቀናት - በቂ ጊዜ ነበር፡፡ ስለዚህ እዚያ ምንም ጭንቀት የለም፡፡ ሰውዬውም ዘና አለ፡፡ እሱም "የኩሬው ግማሽ ሲሸፈን ሊሊዎቹን እቆርጣቸዋለሁኝ" አለ፡፡
ኩሬውም በግማሽ ተሸፈነ ግን ኩሬው ግማሽ በግማሽ የተሸፈነው በዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠነኛው ቀን ነበር፡፡ በተራው እሳቤ "ሌላው ግማሹ የኩሬው አካል ከአምስት መቶ ቀናት በኋላ ይሸፈናል" ብላችሁ ታስባላችሁ--- አይ! እንደዚያ አይደለም! እፅዋቱ ራሱን ሲያባዛ ቆይቶ ግማሹን ኩሬ ለመሸፈን ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ቀን ፈጅቶበት ሙሉ በሙሉ ኩሬውን ለመሸፈን አንድ ቀን ብቻ ነበር የቀረው፡፡ ግን ያ...ጊዜ አበባውን ለመቁረጥ እና ግማሹ ላይ እንዲቆይ ለማድረግ በቂ ጊዜ አልነበረም፡፡
እና ይህ ተከሰተ፡፡ በዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠነኛው ቀን ኩሬው በግማሽ ተሞላ እናም ሰውዬው በዚያ ቀን ትንሽ የህመም ስሜት ተሰምቶት ስለነበር ' ምንም የሚያጣድፍ ነገር የለውም፡፡ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ቀን ጠብቄያለሁኝ፡ እናም ምንም ችግር የለውም፡፡ አሁን በቃ ጥያቄው የአንድ ቀን ጥያቄ ብቻ ነው፡ ፡ ከአንድ ቀን በኋላ አደርገዋለሁ" አለ፡፡ በሚቀጥለው ጧት ላይ መላው ኩሬ በሊሊዎቹ ተሞልቶ ዓሣዎቹ ሙተው አገኛቸው::
ይህ ነው የህይወት እንቆቅልሽ፡፡ ይህ ግራ የሚያጋባ ነበር፡፡ አንድ ሰው መምረጥ ይኖርበታል፡፡ ነገሮችን እና ንብረቶችን ማከማቸታችሁን ገፍታችሁበታል፡፡ እፅዋቱም በኩሬው ላይ ራሱን በእጥፍ እያባዛ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ቀን ነገሮች ማድረጋችሁን ቀጥለዋል፡፡ እናም ህይወታችሁም የተፋፈገች እና የታፈነች ሆናለች፡፡ ህይወት ረዥም መስላ ትታያለች...ሰባ ዓመታት ፣ ሰማኒያ ዓመታት፡፡ ምንም የሚያጣድፍ ነገር የለም፡፡ ሰዎች "መካከለኛው ነጥብ ለይ ስንደርስ እንቀየራለን" ብለው ያስባሉ፡፡
ሰዎች ለሃይማኖት እስከሚያረጁ ድረስ ይጠብቃሉ፡፡ ሰዎች ሃይማኖት በዕድሜ ጠና ላሉ ሰዎች እንደሆነ መናገራቸውን ገፍተውበታል፡፡ ወደ ቤተ- ክርስቲያኖች ሂዱ ፣ ወደ ቤተ - መቅደሶች ሂዱ በሞት አፋፍ ላይ ያሉ በዕድሜ ጠና ያሉ ሰዎችን የምታገኙ ትሆናላችሁ፡፡ የእነርሱ አንድ እግር ከመቃብር ላይ ሆኗል፡፡ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠነኛው ቀን ላይ ናቸው፡፡ በሚቀጥለው ጧት ላይ ህይወት የምትታፈን ትሆናለች፡፡ ከዚያም እነርሱ መፀለይ ፣ መመሰጥ ይጀምራሉ ፤ ህይወት ምን እንደሆነች ማሰብ ይጀምራሉ፡፡ የህልውና ትርጉም ምን እንደሆነ ይጠይቃሉ፡፡ ግን ከዚያ በኋላ ይህ የረፈደ ይሆናል፡፡
ኃይማኖት ጥልቅ ችኮላን ይፈልጋል፡፡ ለይደር የምትይዙት ከሆነ በፍፁም ሃይማኖተኞች አትሆኑም፡፡ ኃይማኖት አሁኑኑ ሊደረግ የሚገባው ነገር ነው፡፡ አሁን እንደሆናችሁት ቀድሞውኑም ተንቀራፋችኋል፡፡ እንደሆናችሁት ብዙ ጊዜን አባክናችኋል እናም ጊዜን ያባከናችሁት እርባና - ቢስ በሆኑ ነገሮች ላይ ነው፡፡ ጊዜያችሁን ያባከናችሁት ከእናንተ ሊወሰዱባችሁ በሚችሉ ነገሮች ውስጥ ነው፡፡
ለእነዚህ ሁሉ ነገሮች ህይወታችሁን መክፈል ግድ ይላችኋል፡፡ የትኛውም ነገር ንብረታችሁ ይሁን ለዚያ ነገር ህይወታችሁን ታጣላችሁ፡፡ ህይወት ደግሞ በጣም ውድ እንጂ ርካሽ ነገር አይደለችም፡፡ አንድ ቀን ብዙ ንብረቶች ይኖሯችኋል፡፡ ግን እናንተ እዚያ አይደላችሁም፡፡ ነገሮች እዚያ ይኖራሉ ባለቤቱ ግን ሞቷል፡፡ የነገሮች ታላቅ ክምችት--- ግን በእነዚህ ነገሮች ውስጥ መኖርን ይፈልግ የነበረው ሰው ትቢያ ሆኗል፡፡
ሰዎች ለህይወት መዘጋጀታቸውን ቀጥለዋል እናም ዝግጅቱ ለመገባደዱ በፊት ይሞታሉ፡፡ ሰዎች ይዘጋጃሉ፡፡ በጭራሽ አይኖሩም፡፡ ኃይማኖተኛ መሆን ማለት ህይወትን መኖር ማለት ነው፡፡ መዘጋጀት አይደለም፡፡ በጣም የማይመስል ነገር ነው እያደረጋችሁ ያላችሁት፡ ድራማዊ ድግግሞሻችሁ ይቀጥላል እናም እውነተኛው ህይወት በጭራሽ አይጀመርም፡፡
ኦሾ

❤84👍12🤔4👏3
"በእውነትና በስራ ብቻ እንጂ በአፍና በምላስ እንፋቀር ዘንድ አይገባንም፡፡በአፋቸው የክርስቶስን ፍቅር እያስተማሩ በልባቸው ግን ፍቅር የሌላቸው፤ሲሳደቡና ሲጋደሉ እርስበርሳቸውም ስለ ሀይማኖታቸው ሲወዛገቡ እንደሚኖሩት እንደ ሀገራችን ክርስትያኖች አንሁን፡፡ እንደዚህ ዓይነት ፍቅር ከእግዚአብሔር ዘንድ አይደለምና ምንም አይጠቅምም፡፡ ዳግመኛም ከምላሳቸው ስር እባብ መርዝ እያለ፣ በአፋቸው የእውነትና የፍቅር ቃል አስመስለው እንደሚናገሩ ግብዞች አንሁን፡፡ እነሱ ልባቸው ሁልጊዜ መጣላትንና መከራከርን ያስባል፡፡ ፍቅራቸው ፍጹም አይደለምና የሀይማኖት ወገኖቻቸውን እየወደዱና በሀይማኖት የማይመስሏቸውን ሁሉ ግን እንደሚጠሉ ግብዞች አንሁን፡፡”
ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ወልደ ህይወት
@zephilosophy
ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ወልደ ህይወት
@zephilosophy
👍50❤37👏3🔥1
Forwarded from Tesfaab Teshome
ያለንበት አገራዊ ሁኔታ ብዙ ያሳስባል። የኑሮ ውድነቱ ያስጨንቃል፥ ተደጋጋሚ ግጭት ረፍት ይነሳል። ያለንበት አገራዊ ሁኔታ ብዙ ሰዎችንዠ ያሳስባል። ይህ ሁሉ ቢሆንም በርካታ ሰዎች ዝምታን መርጠዋል።
"እኔ ምንም ማምጣት አልችልም" ይላሉ። የዚህ ሰበቡ ሁለት ነው። ተስፋ መቁረጥ ወይንም ህዝባዊ አቅምን አለመገንዘብ!
በእርግጥ በተደጋጋሚ ድምፅ አሰምተን ጠብ ያለ ነገር አልታየን ይሆናል። እንደ ህዝብም መተባበር እንደማንችል ልናስብም እንችላለን።
እውነታው፥ ትንንሽ ነጠብጣቦች ተደማምረው ትልቁን ምስል ይፈጥሩታል። በግል የምንጠይቀው የመብት ጥያቄ አንዲት ነጥብ ናት። "ኑሮ ውድነቱ ይብቃ፥ ግጭት ይቁም፥ መብት ይከበር" ማለታችን አንዲት ትንሽ ነጥብ ናት። የእያንዳንዳችን ነጠብጣቦች ሲደመሩ ትልቁን ምስል ይሰራሉ!
አምባገነኖች አቅመ ቢስነት የሚሰማቸው ተስፋ ቢስ ዜጎችን ይፈልጋሉ። ደካማነት የሚሰማውን ህዝብ እንዳሻቸው ይነዱታልና!
አምባገነኖች እንዴት መተባበር እንዳለበት የማያውቅን ህዝብ ይመርጣሉ። የዜጎች አለመተባበር ለጭቆና ይረዳቸዋልና!
ተስፋ ቢሶች አንሁን፥ ጠጠር እናዋጣ። የእያንዳዳችን የመብት ጥያቄ እንደ ነጠላ ጡብ ተደማምሮ የነፃነትን ህንፃ ይገነባሉ።
'እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ' ከማለት ይልቅ 'መብቴ ይከበር' የማለትን ድፍረት እናዳብር !
Via ተስፋኣብ ተሾመ
https://t.me/Tfanos

👍30❤15👎2👏2
ኢቶሪካ እና የወፍ-በረር ትዝብቶቼ
ልደቱ አያሌው
ከአገራችን የኪነ-ጥበብ ሰዎች መካከል የግፍ አገዛዝን በመጋፈጥ እረገድ በዘመነ ኢህአዴግ አንደኛ፣ በዘመነ ዐቢይ ደግሞ አራተኛ ጀግናዬ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ነው። የተጽዕኖ ፈጣሪውን የቴዲን አልበም መለቀቅ ተከትሎ በተፈጠረው የሰሞኑ ከፍተኛ የህዝብ ስሜት ዙሪያ የሚከተሉትን ስምንት ቁም-ነገሮች ታዝቤአለሁ። ትዝብቶቹ የድርሻ ኃላፊነቱን የተዎጣውን ቴዲ አፍሮን ሳይሆን የሱን አልበም መለቀቅ ተከትሎ የተፈጠረውን የህዝብ ስሜት የሚመለከቱ ናቸው።
1ኛ. ማናችንም ከምንገምተው በላይ የኢትዮዽያ ህዝብ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ብሶት፣ ምሬት፣ ስጋት፣
የተቃውሞ ስሜትና የለውጥ ጥማት ውስጥ ነው።
2ኛ. በአገራችን ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ በቋሚነት ከምንደክመው ፖለቲከኞችና ማህበራዊ አንቂዎች በላይ ኪነ-ጥበብ በብዙ እጥፍ የህዝብን ስሜት የማነሳሳት ትልቅ አቅምና ሚና ዓላት።
3ኛ. የወቅቱ የአገራችን የብሄር ብሄርተኞች “አልቆለታል” ወይም “ተሸንፏል” ከሚሉት በተቃራኒ የኢትዮዽያ ብሄርተኝነት ፖለቲካ ዛሬም በህዝቡ ውስጥ “የተዳፈነ ረመጥ” ሆኖ ቀጥሏል።
4ኛ. የህዝበኝነት /Populism/፣ የስሜታዊነት፣ የጽንፈኝነት፣ የብሄርተኝነት እና የመርህ የለሽነት የፖለቲካ ባህል በህዝባችን ውስጥ አስፈሪ በሆነ መጠን ተጠናክሮ ቀጥሏል።
5ኛ. አብዛኛው የአገራችን የፖለቲካ ማህበረሰብ ተደራጅተው ከሚታገሉለት፣ ከታሰሩለት እና መተኪያ የሌለው ውድ ህይዎታቸውን ጭምር በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል አሳልፈው ከሰጡለት ጀግኖቹ በላይ በዘፈንና በቅኔ ስሜቱን ለሚገልጹለት አርቲስቶች የበለጠ ፍቅርና አድናቆት አለው።
6ኛ. ዘላቂ ሰላም እና ፍቅር፣ እኩልነት እና አንድነት በባዶ ቃላት የምንመኛቸው ባዶ ተስፋዎች ከመሆን አልፈው መሳኪያ መንገዳቸው የገባን ዓላማዎቻችን አልሆኑም።
7ኛ. አሸናፊነትና ዘላቂ ለውጥ በስሜትና በምኞት ሳይሆን በተደራጀ ትግልና መስዋዕትነት ብቻ የሚገኝ
ውጤት መሆኑ ገና አልገባንም።
8ኛ. ከቴዲ አፍሮ ዜማና ቅኔ በላይ የኢትዮዽያ የፖለቲካ ማህበረሰብ ፍች የጠፋለት ቅኔ ሆኗል።
ፖለቲከኞች እና ማህበራዊ አንቂዎች ስምንት ዓመት ታግለን ማነሳሳት ያልቻልነውን ሕዝብ ቴዲ አፍሮ በስምንት ደቂቃ የ“ዳስ ጣል” ዜማና ቅኔው አነሳስቶታል። ይህን ሳይ ፖለቲከኛ ከመሆን ይልቅ ቅኔ ዘራፊ በሆንኩ የሚል መንፈሳዊ ቅናት አድሮብኛል። ቴዲ አፍሮ “ስማ እራሴ” እንዳለው የስምንቱን ትዝብቶቸን ዝርዝር ትንታኔ ቅኔ ወዳጅ የሆናችሁት እናንተ፣ ለእናንተው እንድትነግሩት ትቸዋለሁ። ተወያዩበት። አሁን፣ በኢትዮዽያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 11 ሰዓት ነው።
ሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ/ም
ከልደቱ አያሌው facebook ገፅ
የተወሰደ

❤35👎3👏2😁1