Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
338K subscribers
20.9K photos
3.1K videos
10 files
1.38K links
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Download Telegram
“ …እንደምን ዋላችሁ? …

… ከፖለቲካው… ከቧልቱ… ከቀልድ ከሳቁ… ከግርግር ከመፈክሩ… ከቡረቃው… ከኮንሰርቱ ስንመለስ ይሄን አስከፊ የራብ ጉዳይም በደንብ እናስብበት። … አጥብቀን እንጸልይበትም። ራቡ በትግራይና በዐማራው ክፍል ብቻ ተወስኖም አይቀርም። ይታሰብበት…

… ይቅርታ እንዲህ ዓይነት ዜና ማየትም ሆነ መስማት የማትፈልጉ ወንድም እህቶች እንዳላችሁ አውቃለሁ። ሙዳችሁ እንደሚሰረቅ ቀናችሁ እንደሚበላሽም ይገባኛል፤ የሆነው ሆኖ ግን የግድ ማየት መስማት አለብን። የግድ ነው።
ቀጠሮ…

… በዚህ በጥሞና ጊዜ በእነ ቀሲስ ሳሙኤል ግዛው ቤት እኔና ወንድሜ ሀብታሙ አያሌው በለሆሳስ እናወጋ ዘንድ በኢትዮ ቤተሰብ ሚድያ ላይ ተጋብዘናል። ግርር ብላችሁ ሳትበዙ ጥቂት ሆናችሁ በስፍራው በመገኘት ነጭ ነጯን የሆነውን ወጋችንን ታደምጡ ዘንድ ተጋብዛችኋል።

… ሼር አድርጉት እና እዚያው እንገናኝ !!

https://youtu.be/utzN-OdGYL8
… መጪውን ጊዜ የበለጠ ተግተን ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ድምጽ እንሆን ዘንድ ከዚህ በታች በተከፈተው የጎፈንድሚ አካውንት የመረጃ ቴሌቭዥንን አቅማችሁ የፈቀደውን ትረዱ ትለግሱ ዘንድ በትህትና እንማጸናችኋለን።

https://gofund.me/2f3fef2c
11,000  ሺ ዶላር ደርሰናል።

… መጪውን ጊዜ የበለጠ ተግተን ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ድምጽ እንሆን ዘንድ ከዚህ በታች በተከፈተው የጎፈንድሚ አካውንት የመረጃ ቴሌቭዥንን አቅማችሁ የፈቀደውን ትረዱ ትለግሱ ዘንድ በትህትና እንማጸናችኋለን።

https://gofund.me/2f3fef2c
14,440  ሺ ዶላር ደርሰናል።

… መጪውን ጊዜ የበለጠ ተግተን ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ድምጽ እንሆን ዘንድ ከዚህ በታች በተከፈተው የጎፈንድሚ አካውንት የመረጃ ቴሌቭዥንን አቅማችሁ የፈቀደውን ትረዱ ትለግሱ ዘንድ በትህትና እንማጸናችኋለን።

https://gofund.me/2f3fef2c
ለዛሬ ያቀድነውን 15000  ሺ ዶላር አሳክተናል። እንዲያውም ከእቅዳችን በላይ 110 ዶላር አስገብተናል። የመረጃ ቲቪ የአንድ ወር የሳታላይት ወጪ ተችሏል ማለት ነው።

… መጪውን ጊዜ የበለጠ ተግተን ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ድምጽ እንሆን ዘንድ ከዚህ በታች በተከፈተው የጎፈንድሚ አካውንት የመረጃ ቴሌቭዥንን አቅማችሁ የፈቀደውን ትረዱ ትለግሱ ዘንድ በትህትና እንማጸናችኋለን።

https://gofund.me/2f3fef2c
" ስጋት አይግባችሁ… በኦሮሚያ የምርጫ ጣቢያዎች በእዚህ መልኩ በደንብ እና በጥንቃቄ በሚገባም እየተጠበቁ ናቸው ተብሏል።" ሂኢ… ደግሞ ተብሏል ነው ያልኩት። ፎቶ ሾፕ በሆነ በል
" ይሄም ነገር ይጣራልን የሚሉ አሉ… ከወዲሁ ራይት በራይት ተደርጎ ከሆነ አደጋ አለው…
ምጥንቀቓቅ

" በጎጃምም ከወዲሁ እንዲህም እየተደረገ ነው ተብሏል። ነገርየው አሉ ቢሆንም ወ/ሮ ብርቱካን ግን ይሄን ነገር ቸል ባይሉት መልካም ነው።

… ሰከላ ዓባይን ወለደ… ብልጼም ይሄን…
ምርጫውን በተመለከተም የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይህን ብሏል። ይነበብ…

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=4129340113823363&id=123960474361367
"… ደህና እደሩልኝ …
"… እንደምን አደራችሁልኝ? …
ዑስታዞቻችን ምነው ዝም አሉ?
የት ጠፉ?
ይሄም ጥያቄ ነው?

… ሰው ባልሞተበት… የእሳት አደጋው ንብረትና ቤተ እምነት ብቻ ባቃጠለበት በሞጣው አሳፋሪ ድርጊት ወቅት " እንደ ዓለም ዋንጫ " በጉጉት ይጠባበቁ ይመስል ሌሊት ጭምር ተነሥተው ድርጊቱን ያወገዙት ጠቅላያችንን ጨምሮ ኡስታዞቻችን በሙሉ አሁን በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እያዩ እየሰሙም ምነው ዝም ጭጭ አሉ?

… በእስልምና አማኞች ዘንድ ቅዱስ ሥፍራ የሆነችው ሳዑዲ አረቢያ በነቢያቸው " አትንኳቸው " የተባሉትን ሀበሾችን ከመንካት አልፈው እንዲህ የምድር ሲኦል ገሃነመ እሳት ሲሆኑባቸው እነዚያ ለዜጎች ሁሉ አዛኞቹ አንደበተ ርቱዑ የሆኑቱ የኦሮሞ፣ የአርጎባና የዐማራ ኢትዮጵያውያን ዑስታዞቻችን ግን ከምር የት ጠፉ? ምነው ጮጋ አሉ?

… ሳዑዲ ግን የምትዘርፈውን፣ የምትደበድበውን፣ የምትገድለውን አልመረጠችም። … ቀለም አልመረጠችም… ሃይማኖት አልመረጠችም… ጾታም አልለየችም። እንዲያውም በአብዛኛው ግፍ እየደረሰባቸው የሚገኙት የኦሮሞ ሙስሊሞች ናቸው። የዐማራ እና የትግሬ እስላሞች ቢሆኑ እንኳን እሺ አይመለከታቸውም ይባላል። እና ይሄ ሁሉ የኦሮሞ እስላም የሆነ ሙስሊም እንዲህ አሰቃቂ መከራውን እያየ ኡስታዞቻችን ምነው ባላየ፣ ባልሰማ ዝም አሉ?

… ቢያንስ ከእኛ ይልቅ ዐረብኛውን የሚቀሽሩት… በየ ንግግራቸው… ሰበካና ዲስኩራቸው መካከል የሚደነስሩት ዑስታዞቻችን ናቸው። እነ አል አሩሲን የመሰሉ የዓባይ ወንዝ ተሟጋቾች… እነ አህመዲን ጀበል፣ አቡኪ… ካሚሎ… ወዘተ የመሳሰሉ የግፍ ጠል የነፃነት ምነው ተሸበለሉ? የእስላም ሚድያዎቹ ጋዜጠኞች እነ ይስሃቅ ኢሸቱ… እነ አብዱሬ… እነ ጀግናው ሳዲቅ አህመድ ምነው ዝም አሉ? ኣ?

… የዓረብ ሃበሻ ደግሞ ለዑስታዞቹ ያለው ፍቅር እኮ "መጣም: መጣም "ልዩ ነው። ለትግሉ እንደጉድ በገፍ ገንዘብ የሚልከውም እኮ እሱ ነው። የእርዳታ እጁን የሚዘረጋውም እሱ ነው። ለቤንዚን፣ ለሰይፍና ለገጀራ መግዣም ሲያዋጣ የማያፍር… በፌስቡክ ቀጥታ ወጥቶ በድፍረት የሚናገርላቸውም እሱ ነው። እናም ኡስታዞቹ ምነው ዝም አሉ? ባላየ ባልሰማ ላሽ አሉሳ? ወይስ እኛ የማናውቀው እነሱ የሚያውቁት ነገር ቢኖር ነው ዝምታው። እስላማዊት ቅድስት ሃገራቸው እስላማዊ ሃበሾችን… ነፍሰ ጡሮች፣ አራሶች፣ ህጻናትና አቅመ ደካሞችን ሲያሰቃዩ ምነው ዝም አሉ?

… በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል ለተፈጠረው ሰሞነኛ ጦርነት ለፍልስጤም አግዘው፣ የፍልስጤም ባንዲራን ለብሰው በአዲስ አበባ ከፖሊስ ጋር ሲፋጠጡ የከረሙት አፍቃሬ ዓረቦቹ የእኛ ጉዶችስ አሁን የት ገቡ? ምነው ተደበቁ? ለማያውቀው ፍልስጤማዊ ሙስሊም ለሃጩንም ላቡንም ሲያዘረበርብ የከረመው እዩኝ ውደዱኝ ባይ እወደድ ባይ ሁላ አሁን የእናቱን ልጅ የወንዝ የሃገሩን ልጅ የሳዑዲ ፖሊስ እንዲህ ሲያሰቃየው እያየ ምነው ዝም አለ? ዑስታዞቻችን መልስ ስጡኝ እንጂ? ከእኛ ይልቅ እናንተ ቋንቋውንም ስለምትችሉት፣ ዘመዳማቾችም ስለሆናችሁ ብዬ ነው ኡስታዞቼ። አትቀየሙኝ። ዐማራ ክልል ብቻ የሆነ ነገር ኮሽ ሲል ነው እንዴ እናንተ ሃገር ምድሩን የምትደበላልቁት? ተዉ እንጂ ኡስታዞቻችን? ተዉ…

… ለማንኛውም እኔ በበኩሌ እንደ ዜጋ በሚለው መመሪያዬ መሰረት ዛሬ ማታ ከዚያው ከሳዑዲ አረቢያ በቀጥታ የሚተላለፍ የቴሌቭዥን መርሃ ግብር ይኖረኛል። ዘር አልመርጥም። ሃይማኖት አልመርጥም። በፖለቲካ አመለካከታቸው አልገፋቸውም። ሳይረዱኝ፣ ሳይገባቸው እየጠሉኝ፣ እየዛቱብኝ፣ እየገፉኝ እንኳ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ብቻ ድምጼን አሰማላቸዋለሁ። መከራ ስቃያቸውን ለዓለም ህዝብ አሳውቅላቸዋለሁ። ዛሬ ማታ ምሽት ሁለት ሰዓት ጠብቁኝ።

… ከምር አትስደቡኝና… አትቀየሙኝና ዑስታዞቻችን ግን የት ጠፉ? ጠቅላይ ሚንስትሬስ ምነው ዝም አሉ? ሁለት መስመር በቂ እኮ ነው። አይደለም እንዴ?
Zemedkun Bekele (ዘመዴ) pinned «የት ጠፉ? ይሄም ጥያቄ ነው? … ሰው ባልሞተበት… የእሳት አደጋው ንብረትና ቤተ እምነት ብቻ ባቃጠለበት በሞጣው አሳፋሪ ድርጊት ወቅት " እንደ ዓለም ዋንጫ " በጉጉት ይጠባበቁ ይመስል ሌሊት ጭምር ተነሥተው ድርጊቱን ያወገዙት ጠቅላያችንን ጨምሮ ኡስታዞቻችን በሙሉ አሁን በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እያዩ እየሰሙም ምነው ዝም ጭጭ አሉ? … በእስልምና…»
ማስታወቂያ… 

• ኦጎኖቼ እኔ ዘመዴ ሃሳቤን የምሸጠው ከዚህ በታች ባሉ የሃሳብ መሸጫ መደብሮች ውስጥ ብቻ ነው። ከእነዚህ ኪዮስኮቼ ውጪ በስሜ የተከፈቱ ሌሎች መደብሮች ውስጥ ገብታችሁ ፎርጅድ ሃሳብ ሸምታችሁ እንዳትከስሩ ከወዲሁ አሳስባለሁ። ተናግሬአለሁ። ላልሰማ አሰሙ። ላላየም አሳዩ። የመደብሬ ደምበኛ ይሆኑ ዘንድ ሌሎች ወዳጅ ዘመድዎትንም ወደ መደብሬ ጋብዙ። ኣ? 

👉🏿 https://www.facebook.com/Zemedemedia/  172 ሺ ደምበኞች አሉኝ።

👉🏿  http://t.me/ZemedkunBekeleZ
                250 ሺ 6 መቶ ደንበኞች

👉🏿  https://t.me/zemede_Discussion
የተወገደው ተወግዶ 197 ሺ 8 መቶ ደምበኞች አሉኝ። ተመስገን ነው። የሰው ሃብታም ነኝ።

… እናም እርስዎም ማስፈንጠሪያዎቹን ጠቅ… ጠንቆል… ጠቆም ያድርጓቸውና የመደብሬ ደምበኛ ይሁኑ… ሌሎችንም ጋብዙ  !!

… በዚህም ቅና አሉህሽ ደግሞ…  ሂኢ 
Zemedkun Bekele (ዘመዴ) pinned «ማስታወቂያ…  • ኦጎኖቼ እኔ ዘመዴ ሃሳቤን የምሸጠው ከዚህ በታች ባሉ የሃሳብ መሸጫ መደብሮች ውስጥ ብቻ ነው። ከእነዚህ ኪዮስኮቼ ውጪ በስሜ የተከፈቱ ሌሎች መደብሮች ውስጥ ገብታችሁ ፎርጅድ ሃሳብ ሸምታችሁ እንዳትከስሩ ከወዲሁ አሳስባለሁ። ተናግሬአለሁ። ላልሰማ አሰሙ። ላላየም አሳዩ። የመደብሬ ደምበኛ ይሆኑ ዘንድ ሌሎች ወዳጅ ዘመድዎትንም ወደ መደብሬ ጋብዙ። ኣ?  👉🏿 https://www.fac…»