Zehabesha
61.1K subscribers
4.84K photos
478 videos
14 files
6.42K links
Ethiopian News
Download Telegram
በካሊፎርኒያ ሎሳንጀለስ የኢትዮጵያ ቆንስል ጀነራል ብርሃነመስቀል አበበ ሰኚ ከስልጣናቸው ተነስተዋል:: በአቶ ብርሃነ መስቀል አበበ ምትክም እዚያው ቆንስል ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ካውንስልነት ይሰሩ የነበሩት ሙክታር ዋሬ በጊዜያዊነት መሾማቸውን ሰምተናል:: ብርሃነመስቀል አበበ ሰኚ የተነሱት ከዜግነት ጋር በተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር የዘ-ሐበሻ ምንጮች ቢናገሩም እርሳቸውን አግኝተን ለማነጋገር ያደረገነው ጥረት አልተሳካም:: ሆኖም የዘ-ሐበሻ ምንጮች አቶ ብርሃነመስቀል ለረዥም ጊዜያት ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ሲጠየቁ እንደቆዩና ማቅረብም እንዳልቻሉ፤ ሆኖም የሌላ ሃገር ዜግነት እንዳላቸው በፊትም ካላረጋገጡ፤ መጀመሪያውኑ እንዴት እንደተሾሙ ራሱ አስገራሚ መሆኑን ይናገራሉ:: አቶ ብርሃነ መስቀል በጉዳዩ ላይ ምላሽ ከሰጡን የምናቀርብ ይሆናል::