በደብረብርሃን ከሃያ ሺህ በላይ፣ በዋግ ሕምራ ሰቆጣ ከ65 ሺህ በላይ፣ በቆቦና አካቢው ከ60 ሺህ በላይ በዳባት እንዲሁ በሺዎች የሚቆግጠሩ፣ በደቡብ ክልል የተለያዩ ከተሞች እንዲሁ በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ይገኛሉ። አነሰም በዛም እነዚህ ተፈናቃዮች ቢያንስ ትንሽም ነገር አግኝተዋል፤ በሚዲያም ተዘግቦላቸዋል። በቂ ባይሆንም። ሆኖም በጎጃም ፍኖተ ሰላም የሚገኙ ከመቶ ሺህ በላይ የሚሆኑት ተፈናቃዮች ግን የሚጮህካቸው አክቲቪስትም፣ የሚያስታውሳቸው ወገንም፣ ዞር ብሎ የሚያያቸው ባለስልጣን የለም። ከዚህ ቀደም ተማረው ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ከጎጃም ፍኖተሰላም እና ቡሬ ተነስተው ወደ ባህርዳር የ እግር ጉዞ ቢጀምሩም በጥብቃ ኃይሎች እንዲመለሱ ተደርገዋል። ድምጻቸውም አልተሰማም። የዘ-ሐበሻ ባልደረባ ተዋቸው ደርሶ ለነዚህ ወገኖች ድምጽ ከመሆን ፍኖተ ሰላም በመሄድ ተፈናቃዮቹን እነጋግሯቸዋል፤ አብዛኛዎቹ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ከወለጋ የተፈናቀሉ ናቸው፤ ድምጻቸውን እንስማ። ቪድዮውን በየቦታው በማጋራት ትኩርት እንዲያገኙ እናድርግ።
https://www.youtube.com/watch?v=k2RN9TPWKKA
https://www.youtube.com/watch?v=k2RN9TPWKKA