ጫማ ተበድሮ ሮጦ ያሸነፈው 60,000.00 ዶላር ያሸነፈው ኢትዮጵያዊው አትሌት
.
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዛሬ በተከናወነው የህንዱ ታታ ሙምባይ ማራቶን ውድድር በወንዶችም በሴቶችም ኢትዮጵያዊያን ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በወንዶች ምድብ አትሌት ደራራ ሁሬሳ አንደኛ ሆኖ ሲገባ፣ አትሌት አየለ አብሽሮና አትሌት ብርሀኑ ተሾመ ተከትለውት ገብተዋል፡፡ አትሌት ደራራ የቦታውን ሪከርድ በመስበር ጭምር ነው ያሸነፈው፡፡
በመሆኑም በማሸነፉ 45 ሺህ ዶላር እንዲሁም ሪከርድ በመስበሩ ተጨማሪ 15 ሺህ ዶላር በጠቅላላው 60 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ሁለተኛና ሶስተኛ የወጡት አትሌት አየለና አትሌት ብርሀኑም የቦታውን ሪከርድ በመስበራቸው ለሪከርዱ በተመሳሳይ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
በሴቶች ምድብ ደግሞ አስገራሚ ውጤት ኢትዮጵያዊያኑ አግኝተዋል፡፡ ውድድሩን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አማኒ በሪሶ ሁለት ሰአት ከሀያ አራት ደቂቃ ከሀምሳ አንድ ሰከንድ ውድድሩን በማጠናቀቅ አንደኛ የወጣች ሲሆን ሁለተኛ የገባችው ኬንያዊቷ ሮዳ ጃኮሪ ናት፡፡ ከሶስተኛ እስከ ዘጠነኛ ደረጃ ያለውን ቦታ ይቀው የጨረሱት በሚሉ ኢተዮጵያዊያን ናቸው፡፡ አትሌት አማኒ ምንም እንኳ የቦታውን ሪከርድ ለመስበር ጥቂት እየቀራት ውድድሩን ብታጠናቅቅም በአሸናፊነቷ ግን የ45 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሆናለች፡፡
በወንዶች አሸናፊ የሆነው አትሌት ደራራ ሁሬሳ ከውድድሩ በኋላ ሲናገር ‹‹በዚህ ርቀት ከእኔ ይልቅ ልምድ ያለው አየለ አብሽሮ ነበር፡፡ ውድድሩን እንዲያሸንፍም ነግሬው ነበር፡፡
ይሁንና ዞር ብዬ ስመለከተው ወደኋላ ስለቀረ በአንደኝነት ለመጨረስ ወሰንኩ›› ብሏል፡፡ የሚያስገርመው ደግሞ የተወዳደረው አብርሀም ግርማ ከተባለ ሯጭ በተበደረው ጫማ ነበር፡፡ ሲናገርም ‹‹የእኔን ጫማ አውሮፕላን ውስጥ ረስቼው ነበር›› ካለ በኋላ ጫማውን ባለማግኘቱ አጓደኛው ለመበደር እንደተገደደ አስረድቷል፡፡ ያ የብድር ጫማም ለስልሳ ሺህ ዶላር ሽልማት አብቅቶታል፡፡ ዘገባው የስፖርት ስታር ነው፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=v8TEAuBuoPc

YouTube
Ethiopia: ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና | Zehabesha Daily News January 19, 2020
Zehabesha Daily Ethiopian News January 19, 2020 | Eritrean News | Eritrea News Timket Celebration
We’re here for one reason to provide fair and unbiased information to the community and is committed to separating news and views, while covering broad areas…

ቤተክርስቲያኗ ለጥምቀትና ደመራ በዓል ማክበሪያ ቦታ እንዲሰጣት ለሀዲያ ዞን አስተዳደር ያቀረበችው ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል!
በሐዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የከተራ በአል ትናንት እንደተከበረ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት አስታውቋል። በዛሬው ዕለትም የጥምቀት በዓል እንደሚከበር ገልጿል።
የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ ቢንያም መንቸሮ እንደገለጹት ቤተክርስቲያኗ በከተማው ለጥምቀትና ደመራ በዓል ማክበሪያ ቦታ እንዲሰጣት ለሀዲያ ዞን አስተዳደር ያቀረበችው ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል። ቤተ ክርስቲያኗ ትናንት የከተራ በዓልን እንዳከበረች አስታውቀዋል። ዛሬም የጥምቀት በዓልን ለማክበር ዝግጅት እያደረገች መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
ኢዜአ

"ከ50 ዓመታት በኋላ ጥምቀትን በጎንደር ማክበር በመቻሌ ደስተኛ ነኝ"--- በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም
የኤርትራ ልዑክ ጥምቀትን በጎንደር እየታደመ ነው። በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም የተመራ የኤርትራ ልዑክ ትናንት ጠዋት ነው የጥምቀት በዓልን ለመታደም ጎንደር የገባው።
አምባሳደሩ ከዛሬ 50 ዓመታት በፊት በወቅቱ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ተብሎ ይጠራ በነበረው በዛሬው ፋሲለደስ የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ ሆነው ይሰሩ እንደነበርም አስታውሰዋል።
በወጣትነት እድሜያቸው ጥምቀትን ከጎንደር ሕዝብ ጋር ያከብሩ እንደነበር አስታውሰው ከበርካታ ዓመታት በኋላ የዘንድሮውን ጥምቀት በመታደማቸው ደስተኛ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።
AMMA አማራ ማስ ሚዲያ

አማራ ብዙሃን መገናኛ ጋዜጠኞች ለዘሃበሻ ያደረሱት ልዩ የባህረ ጥምቀት በአል በጎንደር፣ባህርዳር (ጣና) እናሌሎችም አካባቢ ምስሎች ። እንኳን አደረሳችሁ። ከእኛ ጋር በመሆን የመረጃችን አሌኝታ ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።