(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ግሪል ቢዝነስ ውስጥ የገባው፣ የከባድ ሚዛን ቦክስ ሻምፒዮኑ ጆርጅ ፎርማን (Big George) በ76 አመቱ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን ቤተሰብ አስታወቀ:: ቤተሰቦቹ በኢንስታግራም አካውንታቸው ሞቱን ይግለፁ እንጂ ምክንያቱን እና የት እንደሞተ አልተናገሩም::
'ቢግ ጆርጅ' የሁለት ጊዜ የለም የከባድ ሚዛን ሻምፒዮን እና የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ነበር።
ታዋቂው ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን በX ገጹ ላይ በፃፈው የሃዘን መግለጫ "ለጆርጅ ፎርማን ቤተሰብ ሀዘናችንን እንገልፃለን። ለቦክስ እና ለቦክስ ያበረከተው አስተዋፅኦ መቼም አይረሳም" ብሏል።

ውድ ወገኖቼ! በጸሎታችሁ አግዙኝ። ከቻላችሁ መረጃው እንዲዳርስ በምትችሉት መንገድ ሼር በማድረግም፣ በምንም መልኩ አሰራጩልኝ። የምወደው ባለቤቴ ደረጄ ታደሰ ተሾመ ይባላል:: የከባድ መኪና ሹፌር ነው:: የፖሊስ ልብስና ሲቪል የለበሱ ኃይሎች የዛሬ ወር የወሰዱት አዲስ አበባ ካዛንቺስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታችን ነው፣ ለሌሊቱ 6፡00 ላይ።
አሁን ላይ የህግ አካል ይሁኑ አይሁኑ አላውቅም። የወሰዱት ግን በወቅቱ የፌዴራል ፖሊስ ደንብ ልብስ ነው የለበሱት። ሌሎቹ ደግሞ ሲቪል ለብሰዋል። በማግስቱ በሄደን ፖሊስ ጋር ስንጠይቅ "እኛ ጋር የለም" ብለውናል። ያልሄድንበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ፣ ያልሄድንበት የደህንነት መስሪያ ቤት የለም። ሁሉም "እዚህ የለም ነው" ያሉን። የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ጋርም ሄደን አመልክተናል፣ ግን "ይሄ ከእኛ አቅም በላይ ነው" ብለውናል።
42 ዓመት ዕድሜ ያለው ባለቤቴን ማግኘት አልቻልንም። ቤተሰብ ሁሉ ተጨንቀናል። ከቤት ከተወሰደ አንድ ወር የሞላውን ባለቤቴን ያለበትን የምታውቁ ወይም ስለጉዳዩ መረጃ ያላችሁ እባካችሁ በስልክ ቁጥር 0943069799 ደውሉልን። ሰላማዊት ጥላሁን እባላለሁ፤ ባለቤቱ ነኝ።
ጸሎታችሁ እጅግ በጣም ያስፈልገናል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) አባልና ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ሙሼ ሰሙ ስለ ብርቱካን እንዲህ ብለዋል፡-
"የወጣትነት ተስፋሽን ለጊዜውም ቢሆን አጨልመውታል። በበደል ላይ በደል እንዲሉ ያለ አቅምሽ የተሸከምሽውን መከራና ፍዳም ተክደሻል። ይህም ሆኖ ግፈኞችንና ሞትን አሸንፈሽ ዛሬ በሕይወት ብቅ ብለሻል። ለዚህ ላበቁሽ ጋዜጠኞች ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
"በወቅቱ ጩኽትሽን ለመጮኽ ብሞክርም በበደልሽ ልክ እንዳልነበር ዛሬ ይበልጥ ተሰምቶኛል። ትናንት የግፈኞችን ጨካኝ ክንዶች እንደተቋቋምሽ ሁላ ወደፊትም በስኬት ጎዳና እንደምናይሽ ጽናትሽ ከበቂ በላይ ምስክር ነውና በርቺ !!
ወገን፣ ግፍና መከራዋን መቀልበስ ባንችል እንኳ እህታችንን አለሁልሽ እንበላት፣ ወደ ሕይወት ጎዳናም እንመልሳት፣ እናቋቁማት!"