Zehabesha
61.1K subscribers
4.84K photos
478 videos
14 files
6.42K links
Ethiopian News
Download Telegram
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባን ከየካቲት 08 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ዙሮች ሲያከናውን እንደነበር እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ተጨማሪ ቀናት በመጨመር እና የፓርቲዎችን አቤቱታዎች በመፍታት ሲያከናውን ቆይቷል።

በዚህም መሰረት የእጩዎች ምዝገባ ትላንትና የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በይፋ ተጠናቋል። በመሆኑም በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቢሮዎች ችግር የተነሳ በልዩ ሁኔታ የሚታይ ካልሆነ በስተቀር ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የእጩዎች ምዝገባ መዘጋቱን እየገለጸ አጠቃላይ የጸደቁ የእጩዎች ዝርዝርን በቅርቡ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
መጋቢት 01 ቀን 2013 ዓ.ም
የአስራ አንድ አመቷ ሀይራ በመንደራቸው ጥቃቱ ሲጀመር የነበረውን ሁኔታ ታስታውሳለች፡፡ ስትናገርም ‹‹መጀመሪያ የተኩስ ድምፅ ስሰማ ብዙም ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር፡፡ ነገር ግን ድምፁ እየቀረበ መጣ›› ብላለች፡፡ በዚህ ጊዜ ቤተሰቦቿ ለደህንነታቸው ስጋት ስላደረባቸው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ዳንጉር ወረዳ ከሚገኘው ቤታቸው ወጥተው ለሊቱን በሀይራ አያት ቤት አደሩ፡፡....
ዝርዝሩን የ ዕለቱ የዘ-ሐበሻ ዜና ላይ ይመልከቱ.. https://www.youtube.com/watch?v=5P2qp1e_Kik