የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የተፈጠረውን የድንበር ውዝግብ እንዲሸመግሉ አንድ ሞሪታኒያዊ ዲፕሎማትን ሰየመ፡፡
የተመደቡት ዲፕሎማት መሀመድ ኡሉድ ሊባት የሚባሉ ሲሆኑ ከሮብ አንስቶ በጉዳዮ ላይ ምክክር መጀመራቸውን አንድ የሞሪታኒያ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ኢሉድ ሊባት በሞሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የሰሩ ሲሆን በመቀጠል እ.ኤ.አ ከ2003 እስከ 2005 ባሉት አመታት በኢትዮጵያ የሞሪታኒያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን በአፍሪካ ህብረት የአገራቸው ተወካይም ነበሩ፡፡ በዚህ ወቅት የአፍሪካ ህብረት በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክና ሩዋንዳ መረጋጋትንና ሰላምን መልሶ ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ መድቧቸው ነበር፡፡
በተጨማሪም የአልበሽር መንግስት በመፈንቅለ መንግስት ከወደቀ በኋላ በሱዳን ብሄራዊ መግባት እንዲፈጠር የተሳካ ሚና ተጫውተዋል፡፡ (ዘሐበሻ የዕለቱ ዜና)

‹‹የሜኒሶታ ህግ አውጪዎች በኢትዮጵያ የታሰረው ሚኖሶታዊ እንዲፈታ ጥሪ አቀረቡ›› ሲል ኤም ፒ አር ኒውስ የዛሬ ዘገባውን ጀምሯል፡፡ ዘገባው ሲቀጥልም በትዊን ሲቲስ ነዋሪ የነበረው ጃዋር መሀመድ መታሰሩንና እስከ ትላንት አርብ ድረስ ለአስራ ዘጠኝ ቀናት በረሀብ አድማ ላይ እንደሚገኝ አውስቷል፡፡ የግዛቱ ሴናተር የሆኑት ጆን ሆፍማን ለዜና ምንጩ በሰጡት መግለጫ ጃዋር መሀመድ ከእስር ተለቆ ብሮክሊን ፓርክ ከሚገኙት ቤተሰቦቹ ጋር ሊቀላቀል እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹እነዚህ የፖለቲካ እስረኞች የረሀብ አድማ ላይ ናቸው፡፡ ስለዚህም ያሉበት ሁኔታ በህይወትና ሞት መሀከል ነው፡፡ የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ በማቅረብ ከዚያ ቦታ አስወጥቶ ወደአገራቸው ማምጣት ይገባል›› ብለዋል፡፡ ሆፍማን ሌሎች አምስት ሴናተሮች በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የጃዋር መሀመድን ጤንነት ቼክ እንዲያደርግ ያቀረቡትን ጥያቄ መቀላቀላቸውንም ገልፀዋል፡፡ ሴናተር ሆፍማን የጃዋር መሀመድ ጉዳይ በአግባቡ እንዳልተመረመረም አስታውቀዋል፡፡ አባባላቸውን ሲያስረዱም ‹‹ይህ ሰው የብሮክሊን ፓርክ ነሪ የነበረ ነው፡፡ ሚስቱና ልጁም እዚሁ ናቸው፡፡ ያለምንም የክስ ቀጠሮ ይህንን ሰው በእስር ቤት ማስቀመጥ ጥሩ አይደለም›› ማለታቸውን የዜና አውታሩ ዘግቦ አይተናል፡፡