Zehabesha
61.5K subscribers
4.84K photos
476 videos
14 files
6.36K links
Ethiopian News
Download Telegram
ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜናዎች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ነው የምናስተላልፍላችሁ። የዘገየነው በአካባቢው ባለው ኢንተርኔት ችግር ነው። ይቅርታ።
https://www.youtube.com/watch?v=CLrD4b-grps
የአማራ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ወጣቶች ባህርዳር ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
****
ወጣቶቹ በአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በመንቀሳቀስ የአማራ ህዝብ የነበረውን የታሪክ ፣የስነ ልቦናና የባህል ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ጉዞ መጀመራቸውንና ዛሬ ባህርዳር ሲገቡ የከተማዋ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶ/ር ድረስን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የከተማ አመራሮች በተገኙበት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ዝግጅቱ ላይ ተገኝተው የትግራይ ወራሪና አሸባሪ ኃይል የአማራን ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ ላለፉት 27 ዓመታት እያደረሰ ያለው ግፍ የወልቃይት ህዝብ ተቀዳሚ ገፈት ቀማሽ በመሆኑ እጅግ ብዙ መከራን አስተናግዷል ብለዋል።

በዚህም ወጣቱ ከሌላው ማህበረሰብ ጋር በመሰለፍ ሲያደርግ የቆየው ትግል የሚመሰገን ያም ተጋድሏቸው ፍሬ እያፈራ ፣ተደራራቢ ድል እያስመዘገበ መሆኑንና በዚህ ረገድ የባህርዳር ከተማ ወጣት ከጎናቸው ሆኖ ከፍተኛ መስዋዕትነትን በመክፈሉ የዝክረ ሰማዕታት መታሰቢያ እየደረገለት መሆኑንም ገልፀዋል።

በመሆኑም መላው የአማራ ህዝብ በአንድነት በመቆም የተጀመረውን ድል በስኬታማነት አጠናቆ ለልማትና ዲሞክራሲ ግንባታ ዘብ መቆም እንደሚገባም ይህ ጉዞ ዓይነተኛ ሚና ያለው መሆኑንም ተናግረዋል።

በአማራ ክልል ብልፅግና ፖርቲ የወጣቶች ሊግ ጽ/ት ኃላፊ አቶ ጋሻው ተቀባ በበኩላቸው በግፈኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል በርካታ ግፍ ከተቀበሉ የአማራ ህዝቦች መካከል የወልቃይት ህዝብ ቀዳሚ ገፈት ቀማሽ በመሆኑ ዘግናኝ ድርጊቶች የተፈፀሙበት መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም ባህሉን ፣ቋንቋውን ፣አንድነቱን ከነ የቀደመ ስነልቦናው ተነጥቆ ከወገኑ የአማራ ህዝብ ጋር እንዲገነጠል ይደረግ በነበረው ሴራ ከፍተኛ ትግልና መስዋዕትነት ያሳለፈ ህዝብ መሆኑንም አንስተዋል።

ስለሆነም በዚህ ወቅት የተጀመረውን ትግል ዳር ለማድረስ ከመላው የአማራ ህዝብ ጋር ከፍተኛ መስተጋብር መፍጠር የሚያስችል የእርስ በርስ ግንኙነት ለማዳበር ያለመ ጉዞ እያደረጉ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አሸተ ደምለው እንዲሁ የትግራይ ወንበዴ ቡድን አማራን በመዋቅር ተደራጅቶ በማፍረስ የራሱን ሀገር ለመገንባት ሲል በአማራ ህዝብ ላይ በተለይም በላ ለምለም መሬትና እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት የሆነችውን የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞንን ከአማራ ዘርፎ ለራሱ ለማድረግ ሲል እጅግ ዘግናኝ ግፍ መፈፀሙን ገልፀዋል።

ይህ የመጨረሻ የክፋት ጥግ የተፈፀመበት ህዝብ የቀደመ የአማራ ማንነቱን ለማስከበር እያደረገ ያለው እልህ አስጨራሽ ትግል ወደኋላ እንዳይቀለበስ ወጣቱ ሀገር ተረካቢ እንደመሆኑ መጠን ከሌሎች የአማራ ህዝቦች ጋር የእርስ በርስ ግንኙነትን ሊያዳበር የሚችል ይፍዊ ጉብኝት ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውንና ዛሬም በባህርዳር ከተማ አስተዳደር በተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል የተሰማቸውን ኩራት ገልፀዋል።

በዕለቱም በባህርዳር ከተማ ባህል በቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ በሆኑት አቶ አብርሃም አሰፋ የባህርዳር ከተማ ሁለንተናዊ ዳራን የተመለከተ እንዱሁም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስለ ኢትዮዽያ ጥንት የአገዛዝና የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት እና በዚህም የአማራ ህዝብ ሚናና ውቅር የስነ ልቦና አንድነትን አስመልክቶ የመነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

ተጓዦቹ በባህርዳር ከተማ ቆይታቸውም በጣና ኃይቅ የሚገኙ ገዳማትንና አድባራትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መዳረሻዎችን የሚጎበኙ መሆኑ ተገልጿል።