YeneTube
79.1K members
10.2K photos
93 videos
59 files
365 links
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር


መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
to view and join the conversation
“እኔ ያደግሁባት ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሲሰቀልም ሆነ ሲወርድ እንኳን እግረኛ ቀርቶ መኪኖች ቆመው፣ ተሳፋሪዎች ወርደው ከበሬታቸውን የሚገልጹበት ጊዜ ነበር፡፡ይህ በየዓመቱ የምናከብረው በዓል ለሰንደቅ ዓላማችን ክብሩን የሚመልስ በመሆን ደረጃ መተግበር አለበት፡፡ ከበሬታችንን ደግሞ በሁሉም ቦታዎች እንግለጽ፡፡”

(ክብርት ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በ12ኛው የሰንደቅ ዐላማ ቀን ካደረጉት ንግግር የተወሰደ)፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በድጋሚ የወጣ የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎች ምልመላ ማስታወቂያ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ህዳር 2012 ዓ.ም ለሚያካሂደው የሲዳማ የክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ 5500 ( አምስት ሺህ አምስት መቶ) የሚሆኑ የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎችን በበጎ ፍቃድ አበል ክፍያ ከአንድ ወር ላልበለጠ ጊዜ ለማሰራት ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ነገር ግን በቂ የሆኑ አመልካቾች ስላልተገኙ ይህንን ማስታወቂያ በድጋሚ ለማውጣት ተገዷል፡፡

የስራው ሁኔታ- የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚ
የሚፈለገው ሰው ብዛት - 5500 (አምስት ሺህ አምስት መቶ)

የማመልከቻ ጊዜ- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተፈላጊው ቁጥር እስከሚሟላ ድረስ

የማመልከቻ ቦታ- ንፋስ ስልክ ቡና ቦርድ ፊትለፊት በሚገኘው የምርጫ ቦርድ ማሰልጠኛ ማእከል

አመልካቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
📌 የማንኛውም የፓለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ያልሆነች
📌 በትምህርት ዝግጅታቸው በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት/ ያለው
📌 እድሜ ከ20- 45 አመት የሆነች/የሆነ
📌 በገጠር ቀበሌዎች ተንቀሳቅሰው መስራት የሚችሉ
📌 የስራ ልምድ አይጠይቅም- ሆኖም በምርጫ አፈጻጸም ዙሪያ ወይም በተለያየ ማህበራዊ አገልግሎቶች የተሳተፉ አመልካቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ቦርዱ በስራ የሚሳልፉትን ጊዜ የቀን አበል የሚከፍል እና ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን በተጨማሪም በህዝበ ውሳኔው ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ለተሳተፉ አስፈጻሚዎች የተሳትፎና የእውቅና ምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@YeneTube @FikerAssefa
የገቢዎች ሚኒስቴር ከእቅድ በላይ ገቢ ሰበሰበ!

ሚኒስቴር መ/ቤቱ በ2012 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 56 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 57.3 ቢሊዮን ብር ወይም የእቅዱን 102 በመቶ መሰብሰቡን በዛሬው እለት የሩብ ዓመት እቅዱን በገመገመበት ወቅት ገልፃል፡፡ይህ አፈፃፀም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ12.9 ቢሊዮን ብር ወይም የ29 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ይህ አፈፃፀም በየወሩ ሲተነተንም በሀምሌ ወር 18 ቢሊዮን ብር ፤በነሀሴ ወር 20.2 ቢሊዮን ብር እና በመስከረም ወር ደግሞ 19.1 ቢሊዮን ብር በአጠቃላይ በሩብ ዓመቱ 57.3 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል፡፡

በሩብ አመቱ ከተሰበሰበው ገቢ 54 በመቶ ያህሉ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰበሰበ ሲሆን ቀሪው 46 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከጉምሩክ ገቢ የተሰበሰበ ነው፡፡ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከማስተማር ጀምሮ ጠንካራ የህግ ማስከበር ስራዎችን የሰራ ሲሆን በዚህ ሩብ ዓመትም ከድርጊታቸው ያልተቆጠቡና ሀሰተኛ ደረሰኝ በመጠቀም ግብይት የፈፀሙ 16 ድርጅቶች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲዉሉ አድርጓል፡፡በተመሳሳይ በግብይት ወቅት ደረሰኝ የማይቆርጡ ድርጅቶች ላይ የኢንተለጀንስ ስራ በመስራት 50 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲዉሉና 2.6 ሚሊዮን ብር አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲቀጡ አድርጓል፡፡

Via የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
የሰኔ 15 ክስተት ተጠርጣሪዎች ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያስገቡት አቤቱታ!

እኛ በሰኔ 15/2011ቱ ክስተት ተጠርጥረን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት የምንገኝ ተጠርጣሪዎች የሚከተሉት ችግሮች እንዲፈቱልን እንጠይቃለን:

1. ያለብንን የህይወት የደህንነት አደጋ: በተደጋጋሚ በፖሊሶች የሚፈፀሙ ትንኮሳዎች፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ፣ በፍ/ቤት ችሎት (ሳይቀር የጠመንጃ ቃታ ተከፍቶ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሮ የነበረ መሆኑ)
2. በግልፅ ከፖሊሶች እንገድላችኋለን፣ እንዘረጋችኋለን የሚል ማስጠንቀቂያ እየተሰጠን ስለሆነ
3. በእጀባ ጊዜ የስነ ልቦና ጫና የሚፈጥር የአንድ ወገን አድሎ ከፖሊስ ይታያል
4. እንደ እስረኛ የምንጠይቃቸው መብቶች በማስፈራራት ማፈን( ለምሳሌ ከጨለማ ቤት ለመውጣትና ነፃና ገለልተኛ ፍትህ ለመጠየቅ የርሃብ አድማ ስናደርግ ችግሩን ለመፍታት ከመቅረብ ይልቅ ርምጃ እንወስዳለን የሚል ማሸማቀቂያ በመነጋገር ችግሩን ከመቅረብ ይልቅ ያልተገባ አካሄዶች አሉ)

ስለሆነም ከላይ የተገለፀው ችግር እንዲስተካከል

1. አጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች እንዲስተካከሉ
2. በህግ ጥበቃ ስር ሰለሆን የህይወት ዋስትናችን እንዲጠበቅ
3. የሚመለከተው የፖለቲካ ሺመኛ ቀርቦ እንዲያነጋግረን
4. ያለነውና የተጠረጠርነው በሰኔ 15ቱ ቢሆንም ተያያዥ ያልሆኑ ብሔር ተኮር ጥያቄዎች እና መገለሎች እንዲቆሙ
5. ፖሊስ እና የፍትህ ተቋማት ከወገንተኝነት የፀዳ አገልግሎት እንዲሰጡ
6. በፖለቲካ አመለካከታችን ብቻ ታስረን እየተሰቃየን ስለሆነ የፖለቲካ ውሳኔ እንዲሰጠን እንጠይቃለን

ከሰላምታ ጋር
ከሰኔ 15 የህሊና እስረኞች

ግልባጭ
- ለሰባዊ መብት ኮሚሽን
- ለሁሉም ብዙሃን መገናኛ ዘዴዎች
-ለኢትዮጵያ ሰባዊ መብቶች ጉባኤ
-ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ
Forwarded from ZenachBrands😎 (Kal)
Red frames😍 are ready for computer 😎⭕️💻 and sun light we also work 🙁 prescribed lenses call now @+251912894364 or inbox🏃‍♂ via @ZenachBrands1
Forwarded from YeneTube
Buy and Order Quality clothes we will bring any orders from USA 🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 in 8 to 15 days
for more info: @order_us1_inbox
0911073577 (abrsh)
👉tops 👚
👉Demin👖
👉Dress 👗
👉underwear 👙
👉T- shirt 👕
For more 👇🏾👇🏾👇🏾join the chanal
👉🏻 https://t.me/joinchat/AAAAAFeEeXHsZxR6KmWVxA

🏠location: medihanialem mall, 3rd floor , 306
Forwarded from YeneTube
የማስታወቂያ ሰዓት!!!
ጤና ይስጥልኝ! ክብራት እና ክቡራን የYeneTube ቤተሠቦች፡፡ ጥራታቸውን የጠበቁ የተለያዩ የሴት እና የወንድ አልባሳትን ከቱርክ በማስመጣት ለእርሶ እናቀርባለን፡፡ በአሁን ሰዓት ትዕዛዝ እየተቀበልን ስለሆነ ከታች ባለው ሊንክ ቻናላችንን በመቀላቀል እርሶ ያሻዎትን ይዘዙን በ 1 ሳምንት ውስጥ እናደርስሎታለን፡፡
እናመሠግናለን፡፡

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/joinchat/AAAAAEa9jhKpu8JbbDsYLQ

☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

ትዕዛዝ ለመስጠት በዚህ ያዋሩን @Hode40

ወይም ይደውሉ +251940407900
አየር ኃይል ያሰለጠናቸዉን ተማሪዎች ነገ ያስመርቃል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ያሰለጠናቸዉን አብራሪዎች፣ ቴክኒሻኖችንና የኤር ፖሊስ አባላትን ነገ ጥቅምት 4 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡አየር ኃይሉ “የዘመናዊ ሰረዊት ግንባታ ጉዞኣችን በተቋማዊ ሪፎርሙ ይሳካል” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደዉ የምርቃት ፕሮግራም ከፍተኛ የመንግስትና የመከላከያ ባለስልጣናት በተገኙበት በደማቅ ስነ-ስርዓት ይከናወናል ተብሏል፡፡

ምንጭ: ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የዐለም ግዙፉ የቴሌኮም ኩባንያ ቮዳኮም በኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት እያሟሟቀ እንደሆነ ካፒታል አስነብቧል፡፡ የኩባንያው የአፍሪካ መካከለኛው መስራቅና እስያቀ ቀጠና ሃላፊ የመሩት ልዑክ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ቴሌኮም ሃላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡ የቴሌኮም ገበያ ፍላጎት ዳሰሳም አድርጓል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from Fiker Assefa
የክልሉ ምክር ቤት ጉባዔ ከነገ ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባዔ ከጥቅምት 4 እስከ 7 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በክልሉ ምክር ቤት የጉባዔ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

በእነዚህ ቀናትም የክልሉ ምክር ቤት፣ የክልሉ መንግስት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2011 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል፡፡ በተጨማሪም ልዩ ልዩ ረቂቅ አዋጆችና ደንቦች የሚቀርቡ ሲሆን ሹመትና የዳኞች ስንብትም እንደሚኖር ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
በኮንታ ልዩ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 18 ደረሰ!

በደቡብ ክልል ኮንታ ልዩ ወረዳ ትናንት ማታ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት መንሸራተት ምክንያት እስካሁን የ18 ሰዎች አስከሬን ተቆፍሮ መውጣቱን የወረዳው ኮሙኒኬሽን አስታውቋል፡፡የሰዎችን ህይወት ለማዳን በኤክስካቫተር በመታገዝ ርብርብ መደረጉን እና አሁንም አራት ሰዎች እንዳልተገኙ፤ በህይወት ይተርፋሉ የሚለው ተስፋም እንደተመናመነ የወረዳው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ፋሲካ ሙሉጌታ በተለይ ለኢቢሲ አስታውቀዋል፡፡ከአፈር በታች በሆኑት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በግምት 22 የሚሆኑ ሰዎች ሊኖሩ ስልሚችል የሟቾች ቁጥር ሊጨር እንደሚችል ነው ኢቢሲ የዘገበው።

@YeneTube @FikerAssefa
የፊንላንድ ፕሬዝዳንት ሶሊ ኒኒስቶ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ።

የፊንላንድ ፕሬዝዳንት ሶሊ ኒኒስቶ ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ እንደሚገቡ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።የሶሊ ኒኒስቶ ጉብኝት በሁለቱ አገራት መካከል በፕሬዝዳንት ደረጃ የሚካሄድ የመጀመሪያ ጉብኝት ነው ተብሏል።ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር ይወያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬው ዕለት የፌደራል ጤና ሚንስቴር አንድ አምቡላንስ በህዝብ መዋጮ ለገዛ አንድ ወረዳ/ከተማ አስተዳደር ሌላ ተጨማሪ አምቡላንስ ይጨመርላችኋል የሚለውን ቃሉን በመጠበቅ ወደ አገር ውሰጥ የገቡ 200 አምቡላንሶችን ለሁሉም ክልሎች ጤና ቢሮ ኃላፊዎች ደርሻቸውን አስረከበ።

በዚሁ ወቅት የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግሥት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ የክልሉን ደርሻ አምቡላንሶች ሲሰከቡ እንደተናገሩት አምቡላንሶችን ከመርከብ ባለፈ ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት በማኑዋሉ መሠረት መስጠትና ከታሰበለት ዓላማ ውጭ የሚጠቀሙ አካላትን ተጠያቂ ማድረግ እንደሚገባ አስታውቋል።

ምንጭ: የክልሉ ጤና ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ በዛሬው እለት በ1492 ጣሊያናዊው አሳሽ ክርስቶፈር ኮለምበስ ሀገሪቱን የረገጠበትና ለተቀረው አለም ያስተዋወቀበትን ቀን Columbus day ወይም Indigenous People day በሚል እያከበረች ትገኛለች። ይህ በዓል በየአመቱ October በገባ በሁለተኛው ሰኞ ይከበራል።

@YeneTube @FikerAssefa
<<መደመር>>የተሰኘው መፅሀፍ በዚህ ሳምንት በገበያ ላይ ይውላል
-
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የፃፉት ‹‹መደመር›› የተሰኘው መፅሀፍ በዚህ ሳምንት ለገበያ እንደሚቀርብ ተሰማ፡፡

ካፒታል የእንግሊዘኛ ጋዜጣ እንደዘገበው መፅሀፉ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀ ሲሆን 287 ገፆች ያሉት ነው፡፡ የመፅሀፉ አንድ ሚሊዮን ኮፒ በቻይና በነፃ እንደታተመም ጋዜጣው አስረድቷል፡፡

16 ምእራፎች ያሉት መፅሀፉ አገሪቱ መከተል በሚገባት የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ የውጭ ግንኙነትና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የፖሊሲ ጉዳዮችን የያዘ ነው ተብሏል፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ታዛቢዎች የዚህ መፅሀፍ ሀሳብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት ገዢው ፓርቲ ወደፊት የሚከተለው ርእዮተ አለም እንደሚሆን እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡

እስካሁን ድረስ ገዢው ፓርቲ ኢህአዲግ እየተመራ ያለው ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ባረቀቁትና አብዮታዊ ዲሞክራሲ በተሰኘው ርእዮተ አለም እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ይህ ‹‹መደመር›› የተሰኘው መፅሀፍ ለገበያ የሚቀርበው በ300 ብር እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ከሽያጩ የሚገኘው ገቢም በአገሪቱ ውስጥ ትምህርት ቤቶችን ለማሰሪያነት እንዲውል መታሰቡም ተሰምቷል፡፡ መፅሀፉ በእንግሊዘኛ የቀረበው ‹‹ሲነርጂ›› በሚል ርእስ ነው፡፡

ምንጭ: ዘ-ሐበሻ
@YeneTube @Fikerassefa