Maleda Sport ማለዳ ስፖርት
1.53K subscribers
3.69K photos
8 videos
149 files
336 links
ዓለም ዓቀፍ የእግር ኳስ ክስተቶችን በተለየ መልኩ ወደ እርስዎ የምናደርስበት ለእግር ኳስ መረጃዎች ትክክለኛው ቻናል👍👌

ጥልቅ እይታና ሚዛናዊ አቀራረብ መለያችን ነው!


Amazing channel on telegram 👏🙌


👇Admin👇
👉 @alrightmama 👉
Download Telegram
Maleda Sport ማለዳ ስፖርት
Photo
🔴 በኤምሬትስ የተከናወነው የአርሰናል እና ሊቨርፑል ተጠባቂ ጨዋታ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

በፕሪሚየር ሊጉ ተጠባቂ ጨዋታ አርሰናል ከሊቨርፑል 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀው ነጥብ ተጋርተዋል።

ቡካዮ ሳካ እና ሚኬል ሜሪኖ ለመድፈኞቹ ጎሎችን ሲያስቆጥሩ ቨርጅል ቫን ዳይክ እና ሞ ሳላ ለቀዮቹ ኳስና መረብን አገናኝተዋል።

ሊቨርፑል ከማንቸስተር ሲቲ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ የተገደደ ሲሆን አርሰናል ሶስተኛ ደረጃውን ይዟል።
🔴 ማንቸስተር ዩናይትድ ኤሪክ ቴን ሀግን ከሀላፊነት አንስቷል።

በውድድር አመቱ እጅግ ደካማ እንቅስቃሴ ያደረጉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ከማንቸስተር ዩናይትድ የአሰልጣኝ ሀላፊነት ተሰናብተዋል።
🔴 ሩድ ቫኒስትሩይ በማንቸስተር ዩናይትድ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግን ከሀላፊነት ያነሳው ማንቸስተር ዩናይትድ የቀድሞው ኮከቡን ሩድ ቫንስትሩይ ጊዜያዊ አሰልጣኝ አድርጎ ሹሟል።
🔵 ለታላቁ ሽልማት ቅድመ አሸናፊነት ያገኘው ቪኒሲዬስ ጁኒዬር በፍቅር ከተማዋ ፓሪስ በትልቁ የእግር ኳስ የኮከቦች ሽልማት ድግስ ላይ እንደማይገኝ ዘገባዎች አመላክተዋል።

የሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬስ አሰልጣኙን ጨምሮ አንድም የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ወደ ፓሪስ እንዳይሄድ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

አሁን በሚወጡ ሪፖርቶች መሰረት የባሎን ዶሩ አሸናፊ ቅድመ ግምት ያገኘው ቪኒሲዬስ ጁኒዬር ሳይሆን ሮድሪ እንደሚሆን ነው።
🔴 አዲሱ የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ለመሆን ?

ሩበን አሞሪም በስፖርቲንግ ሊዝበን በውድድር አመቱ አስደናቂ ጅማሮ አድርገዋል።

9 ጨዋታዎች
9 ድሎች
30 ጎሎች አስቆጠረ
2 ጎሎች ብቻ ተቆጠሩበት
🔵 ወጣቱ ኮከብ ላሚን ያማል የኮፓ ትሮፊ ክብርን በልቀት አሸንፏል።

ሶስት የባርሰሎና ተጫዋቾች በአለፉት አራት አመታት የኮፓ ትሮፊ አሸናፊ መሆን ችለዋል።

ፔድሪ በ 2021
ጋቪ በ 2022
ያማል በ 2024
🔴 የ 2024 ኮፓ ትሮፊ ክብር አሸናፊ ላሚን ያማል
🔴 ይሄንን ትልቅ ክብር በማሸነፌ የድል ኩራት ተሰምቶኛል።

ሽልማቱ ለእናቴ ፣ ለአያቴ ፣ ለቡድን ተጫዋቾቼ ፣ ለአሰልጣኙ እና እኔን ለደገፉኝ በሙሉ ይሁንልኝ።

ላሚን ያማል
⚪️ አንድም ተወካይ በፓሪስ ያላከው ሪያል ማድሪድ የአመቱ ምርጥ ቡድን ሽልማትን አሸንፏል።
🔴 ቶኒ ክሩስ በኢንስትግራም ገጹ ቪኒ ጁኒዬርን ምርጥ ሲል አሞካሽቶታል።
🔴 ሀሪ ኬን እና ኪሊያን ኧምባፔ በ 2024 ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን የገርድ ሙለር ክብር አሸናፊዎች ሆነዋል።

በሽልማቱ ላይ ሀሪ ኬን ብቻ ነው የተገኘው።
🔴 ቀጣይ ባሎን ዶር 👑
🔵 ኤሚ ማርትኔዝ በባሎን ዶር ሽልማት የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል።

የአለም ሻምፒዮኑ በሁለት ተከታታይ አመት ውስጥ የላቀውን ሽልማት የግሉ አድርጓል።
⚪️ ስኬታማው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የባሎን ዶር የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ክብር አሸናፊ ሆነዋል።
ባሎን ዶር ሪያል ማድሪድ የአመቱ ምርጥ ቡድን መሰኘቱን ተከትሎ ቪኒሲዬስ ጁኒዬር በሌለበት የሪያል ማድሪድ ተጫዋቾች ምስል አድርጎ ለማድሪዱ ክለብ እንኳን ደስ አለህ ብሏል።
ስፔናዊቷ የባርሰሎና ኮከብ አይታና ቦንማቲ በተከታታይ አመት ለሁለተኛ ጊዜ የባሎን ዶር ክብርን በማሸነፍ በእግር ኳሱ የንግስት ዙፋን ደፋታለች።
🔵 ከሌላኛዋ ንግስት አሌክሲያ ፑቴያስ በኋላ በአለም እግር ኳስ እስከወዲያኛው የነገሰች ድንቅ ኮከብ አይታና ቦንማቲ።
🔵 ሮድሪ የ 2024 የባሎን ዶር አሸናፊ መሆኑ ተረጋግጧል።

ታላቁ የእግር ኳስ የኮከቦች ሽልማት በፓሪስ ይፋ ሲሆን ስፔናዊው የማንቸስተር ሲቲ ተከላካይ አማካኝ ትልቁን ክብር በልቀት አሸንፏል።

የዩሮ ዋንጫ እና የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ከሌሎች ክብሮች ጋር ያሳካው ሮድሪ ባሎን ዶርን ያሸነፈ የመጀመሪያው የተከላካይ አማካኝ ተጫዋች በመሆን አዲስ ክብር አስመዝግቧል።
ዣቪ ፣ ኢኔስታ ፣ ቡስኬት ፣ ቪያ ያላሳኩትን የባሎን ዶር ሽልማት ሮድሪ በማሳካት ስፔን ከ 64 አመታት በኋላ በትልቁ ሽልማት ልጅ አግኝታለች።

ሮድሪ ባሎን ዶርን ያሸነፈ የመጀመሪያው የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋች ሲሆን ከ 64 አመታት በኋላ ደግሞ የመጀመሪያው ስፔናዊ ተጫዋች ሆኗል።
በባሎንዶር ሽልማት ከ 1-3 የወጡ ኮከቦች

ሮድሪ
ቪኒሲዬስ
ቤሊንግሃም