የልቤ ድርሰት የብዕር ጠብታ
1.67K subscribers
183 photos
1 video
1 file
9 links
Well come😊
ትኩረት ነጥቦች
፩ ፦ግጥም ፪፦ድርሰት ፫፦ፍልስፍና
፬፦ስዕል ፭፦ሙዚቃ ፮፦ስሜት ፯፦ፎቶ
አላማ
~> በዚህ ቻናል አዳማጭ ያጡ ልቦችን እናንኳኳለን ከዝምታው አለም እንዲወጡ ፣ የልባቸውን ድርሰት የብዕራቸዉን ጠብታ እንዲያጋሩ ፣ የዉስጥ እረፍት እንዲያገኙ እና ወደ ወደፊት ህልማቸው አንድ እርምጃ እንዲጠጉ ማድረግ ነው። inbox @amanytz

የሁሉም ሰው ልብ ደራሲ ነው!!
Download Telegram
.
.
.
.
☁️ ሌሎቹን እሚዎቅስ=
እረጅም ጉዞ አለበት።

🌤 እራሱን እሚዎቅስ=
ግማሹን ተጉዟል።

☀️ ማንንም እማይዎቅስ=
ደርሷል!

✍️
Chinese Proverb

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
.
.
.
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳቹህ!

#ጥምቀትን_በጎንደር
የዘንድሮ እጅግ ልዩ ነበር! ለቀጣይ ዓመት ለ2016 ዓ.ም ከአሁኑ ጎንደር ጥሪዋን ታስተላልፋለች።🙏

#መልካም_ጥምቀት!

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
inbox me @amanYTZ23
😍😍😍😍😍😍
.
.
.
በዓለም ላይ..
1% ሰዎች ዓለምን ይቆጣጠራሉ። 4% ሰዎች አሻንጉሊቶች ናቸው። 90% ሰዎች ተኝተዋል። 5% ሰዎች የሚሆነውን ያውቃሉ እና 90% ለማንቃት እየሞከሩ ነው። የ1% ሰዎች 5%ሰዎች 90% ሰዎችን እንዲቀሰቅሷቸው አይፈልጉም።

Connecting Consciousness

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23
🌍🌍🌍🌍🌍🌍
.
.
.
አንድ ቀን ነው ያየኋት..
የጥምቀትን በዓል ላከብር ወደ መናገሻዋ ከተማ የታሪክ ደብር ወደ ጎንደር ተጉዤ በዕለተ ጥምቀቱ ማልጄ በጥምቀተ ባህሩ ተሰልፌ ጸበል ለመረጨት ስጋፋ.. 'ዘንድሮ ሴቱም ጉልበተኛ ሁኗል እቴ' ብየ በቀኘ በኩል ስመለከት ጸበሉን እሚረጩት አባትም ወደዚያው አቅጣጫ ጸበሉን ሲያዘንቡት የረፋዷ ፀሐይ መልኳን በእጆቿ ስትዳብሰው እርሷም አይኗን ጨፍና ስትረጭ.. አ የ ኋ ት .. ጸበሉ ፀጉሯን ከተከናነበችው ነጠላ እስከ ደረቷ ሲፈስ በይኔ መዝገብ ሰፈረ.. ጸበሉ ነው ወይስ ፀሐዩዋ ናት ወይንስ እርሷ ናት እምታበራ ያለች.. ለኔ ብቻ እየታየችኝ መሰለኝ.. አንድ አባት ሲያስተምሩ "አዳምና ሄዋን ከገነት ከተባረሩ በኋላ አዳም ሄዋንን እንዳይጠላት 'ታይታ እንድትወደድ!' እሚያደርጋትን ፀጋ ፈጣሪ ሰቷታል እና ሁሉም ሴቶች ታይተው እሚወደዱት ለዚያ ነው!" ያሉት ትዝ አለኝ..ግን እንዲያ ባይሆንም እንኳ ታይታ እምትወደድ ሁና ተቀረፀችብኝ..
'ሰው ጸበል ብሎ ሄዶ መቼም መጋኛ አይመታም! ይቺማ በቀኘ ያገኘኋት ላይኔ የቀናችኝ ሄዋኔ መሆን አለባት!' ስል አሰብኩ.. ጸበሉ በግምባሯ አድርጉ ሲፈስ ፊቷ ላይ እምነቷ ይነበባል..አይኖቿን ገልጣ ፈገግ ስትል ልቤ ወደ እሳት እንዳስጠጉት ቅቤ ቅልጥ አለ..!! በሁሉም አቅጣጫ የሚገፉኝን ተቋቁሜ በላየ ላይ እሚወርደዉን ጸበል ችላ ብየ እሷን እያየሁ የአይን ጥምቀቴን ወሰድኩ.. ጸበል ያልተረጨ ሰው ለመረጨት..የተረጨው ደግሞ እንዳይበሰብስ ተሎ አካባቢዉን ለመልቀቅ በሚደረገው ፍትጊያ መሐል ተራራቅን.. በፀጉር ልክ በሆነው ህዝብ መሃል ገብታ ጠፋችኝ.. በቻልኩት መጠን ፈለኳት ግን ላገኛት አልቻልኩም.. ወይ ጉድ.. ጓደኞቼን ሰባስቤ የሆነዉን ነገርኳቸው..እንደማላገኛት ነገሩኝ! ይባስ አንዱማ "ሜኳፗ ለቆባት ይሆናል ባንዴ የጠፋች!" ብሎ ተሳለቀብኝ!! እኔ ግን ያየሁትን አዉቃለሁ.. ከዛን ቀን በኋላ ጥምቀትን እንደኔ እሚጠብቀው እና እሚናፍቀው ሰው አልነበረም.. በየአመቱ እዛው ቦታ እጠብቃት ጀመር ግን ድጋሚ አላየኋትም.. በቃ ያኔ አንድ ቀን አንዴ ነው ያየኋት ግን በአይኔ ቆቦች ላይ ተስላ ቀረች..አይኔን ስጨፍን አያታለሁ..አይኔን ስገልጥ ግን ከጎኔ የለችም..።
.
.
.
.
✍️Aman😑 YTZ
@amanYTZ23

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset
❤️❤️❤️❤️❤️
inbox me @amanYTZ23
🍋🍋🍋🍋🍋
.
.
.
"ነይ ፥ ጣፋጭዬ እኔና አንቺ ከማለፋችን በፊት እርስ በርሳችን እንዋደድ።"


✍️Rumi
(fb page = Films & Art)

join and share
@Yelbedrset
@Yelbedrset

inbox me @aman116
እንኳን ደህና መጣቹህ!🙏

በአልፋ መንገድ ሲጓዙ
፩፦ ትምህርታዊ ፁሑፎች
፪፦ በልብ የተቃኙ ግጥሞች
፫፦ አጫጭር መጣጥፎች
፬፦ የመጽሐፍት ዳሰሳ
፭፦ እንደማር ጠብታ ያሉ ጥቅሶች
፮፦ በካሜራ አይኖች የተመዘገቡ ፎቶዎች
፯፦ ፍልስፍናዎችን
ወደ አልፋ በምናደርገው ጉዟችን እንቃኛለን።
"መልካም ጉዞ!"

inbox = 251974759617

"ወደ የት እንደምትሄድ እማታዉቅ መርከብ ንፋስ እራሱ አያግዛትም!"

join join join
👇👇👇👇👇👇
@alphatourmedia
@alphatourmedia
@alphatourmedia

@YelbeDrset
.
.
.
የደመቁ ገፆች . .

መፈለግ ደስ ይላል።  ...   ድሮ ፍቅርን በተመለከተ  እኔ  ፈላጊ ነበርኩ፤  ከመፈለጌና  የሚፈልገኝን ከማጣቴ የተነሳ  ...   ሴቶችን ከሆኑት በላይ  ብርቅ አድርጌ ነበር ከፍ ከፍ የማደርጋቸው።  በዓለሙ ላይ ከወንድ እኩሌታ ሴቶች በብዛት እንዳሉ በማያውቅ ካብ ነበር የማስቀምጣቸው። "ምነው ባደረገኝ የደጅሽን አፈር ፣  አንቺ ስትረግጪኝ እኔ እንድንፈራፈር "  የሚለው ዘፈን ፣ ትርጉን የሚሰጠው ለኔ ብቻ ነበር።

በጣም ብርቅ መሆንን ቢሹም  ...  ከሚገባው በላይ ብርቅ ስታደርጋቸው  ግን ሴቶች ይደነግጣሉ።     ...   ይደነግጡና ያስደነገጣቸውን ይሸሻሉ።  ...  " ፈጽሞ ሴት የማያውቅን ወንድ እንወዳለን "  ቢሉም ፣በጣም አጋኖ የሚያመልካቸው ግን ምቾት ይነሳቸዋል።
-------------

ሌሊሳ ግርማ
(ይመስላል ዘላለም)
በጣም ውብ መፅሀፍ ነው ። እውነትም ሌሊሳ አጭር ልብወለድ ግዛቱ ነው ። አንብቡት !!

@alphatourmdia

@Yelbedrset
@YelbeDrset
✍️✍️✍️✍️✍️✍️
inbox me @aman116
✍️✍️✍️✍️✍️✍️
ከአካልዋ ይልቅ ለ አምርዋ ይጠንቀቁ

በሞራል የላሽቁ ሰወች አብዛኛውን ጊዜአቸውን ስለ አካላዊ ቁመናቸው በመጨነቅ ያሳልፍሉ ። እንስሳዊይ ማንነቶዋን ያሽቀንጥሩት ።ዋነኛው ሰው የመሆን አላማዎ ሰው የመሆን ምክንያታዊነትዎን በጽኑ መሰረት ላይ መገንባቱ ላይ ነው። በዚህ ምክንያታዊይነት በመመራት የተፈጥሮን ምንነት መረዳት፤ መገንዘብ ይችላሉ ።

@alphatourmdia

@YelbeDrset
ራስህን ተቀበል!

"በአዕምሮም በአካልም ራስን መሆን ሲችል ሌሎችን ለመምሰል እንደሚመኝ ሰው ጭንቀት የሚበዛበት የለም" ይላሉ አንጄሎ ፖተር የተባሉ ሊቅ ። ሌሎች ሰዎችን ለመምሰል የሚሞክር ሰው ራሱን ያልተቀበለ ሰው ነው። ለውጡ ላይ ፅናት ኑሮት የሚሰራ ሰው ደሞ ራሱን የተቀበለ ሰው ነው። ወዳጄ አንተም ራስህን መቀበል መቻል አለብህ ራስህን ስትቀበል ነው ከራስህ ጋር ሰላም የምትሆነው የውሸት እኔ እኮ እንዲህ ነኝ እንዲያ ነኝ ብትል ከላይ ከላይ ፈገግ አስብሎ ውስጥህን ይበላሀል ከሰዎች ጋር ስትሆን ደስተኛ ብትመስልም ከራስህ ጋር ስትሆን ግን ሀዘንተኛ ነው ምትሆነው። እንዲህ የይምሰል ህይወት ላለመኖር መፍትሔው ራስህን መቀበል ነው መጀመሪያ ራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደርህን አቁም ከዛም መለወጥ የምትችላቸው እና የማትችላቸው ነገሮች ካሉ ለይ እናም መለወጥ የምትችላቸውን ነገሮች ለመለወጥ ስራ የማትችላቸውን ነገሮች ደሞ ሙሉ ለሙሉ ተቀበላቸው።

"እራስህን ስታውቅ ሃይል ታገኛለህ እራስህን ስትቀበል የማትበገር ትሆናለህ" ትለናለች ቲና ሊፍፎርድ

እናምእልሀለው ወዳጄ ሌሎችን በመምሰል ውስጥ ራስህን አትጣ ራስህን ተቀብለህ ራስህን አሻሽል።
@alphatourmedia

@YelbeDrset
.
.
"በዚህ አለም መኖር በሁሉም የማይገኝ ነገር ነው። አብዛኛዉን ሰው ህያው ብቻ ነው። በቃ።"

✍️Oscar Wild

join and share
@Yelbedrset
@Yelbedrset
👤👤👤👤👤👤
inbox me @amanYTZ23
👤👤👤👤👤👤
.
.
"ሁሉም ሰው የሌለው እናንተ ብቻ ያላቹህ ነገር እራሳቹህ ነው። ድምፃቹህ ፣ ጭንቅላታቹህ፣ ታሪካቹህ፣ ራዕያቹህ። ስለዚህ ፃፉ እና ሳሉ እና ገንቡ እና ተጫዎቱ እና ዳንሱ እናም እንደምትችሉት ሁናቹህ ኑሩ።"

NEIL GAIMAN

join and share
@Yelbedrset
@Yelbedrset

inbox me @aman116
#ዘወረደ_አራት_ነገሮች_ይነገሩበታል 👇
1.የአዳም ከገነት ወደ ምድረ ፋይድ መውረድ
2.የወረደውን ለመመለስ የአካላዊ ቃል ከሰማይ መውረድ
3.ከሰማይ የወረደው ጌታ የተሰቀለበት የዕፀ መስቀል ከኢየሩሳሌም ወደ ፋርስ መውረድ
4.ክርስቶስ የወሰደለት የእኛ ሰውነት ከጽድቅ ከቅድስና ወደ ኃጢአት መውረድ ይነገርበታል!

ለአራቱም ከፍታ/መመለስ/ዕርገት አላቸው 👇
1.አዳም ወደ ገነት ተመልሷል
2.ክርስቶስም ወደ ሰማይ ዐርጓል
3.ዕፀ መስቀሉም በንጉሠ ሮም ኅርቃል አማካይነት በምእመናነ ኢየሩሳሌም ጾምና ጸሎት በ 614 ዓ.ም ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሷል
4.እኛም በንስሐ እናርጋለን (ወደ ጽድቅ ወደ ቅድስና እንመለሳለን)

አጠቃላይ የጾሙ ምሥጢርም ይኸው ነው
ከፍታ የሚነገርበት በይቅርታ እግዚአብሔርን የምንመስልበት የሥጋ ሳይሆን የመንፈስ ለውጥ የምናሳይበት ነው!

ጾሙን ለምሕረትና ለበረከት ድል ለመንሣት ያድርግልን🙏

ሠናይ ዐቢይ ጾም!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው ዘመካኒሳ ሚካኤል

From ፉኖተ ጽድቅ
@alphatourmedia

@YelbeDrset
እንቅስቃሴዋ ሁሉ ክብርዋን የጠበቀ ይሁን
 
የትም መቸም ቢገኙ እራሱዋን እንደ የክብር እንግዳ ይቁጠሩ ። ሌሎች ሰወች በዙሪያቸው በሚካሂደው ነገር ሲረበሹ እርስዋ ከክብርዋ አይውረዱ ። ጭፍን ፈጥዝያና ዝላይ የበዛባቸውን ድግሶች አይታደሙ ። ህዝባዊይ በሆኑ ስብሰባወች በዓላት ላይ ቢታደሙ ከህይወት አላማወት አቁሞት ላይ ዝንፍ አይበሉ።
Roha(
@alphatourmedia)

@alphatourmedia

@YelbeDrset
.
.
#ፈራሁ
.
.
ደመናት በሰማይ ቅርፅ እየፈጠሩ _ አይስሉም ትተዋል፣
የጓሮ ሰበዞች_ አበቦች ረግፈዋል።
ወንዞችም ጠፍተዋል_እንደ ዱሮ አይመጡም፣
ሽማግሌዎች ዛፍ ስር_ሸንጎ አይቀመጡም፣
ያልጠኑ ጥጃዎች እየፈነጠዙ_መስክ ላይ አይሮጡም፣
ልጆች ሲቆጧቸው_ቶሎ አይደነግጡም፣
ህፃናት አውቀዋል_እንደ ልጅ አይፈሩም፣
በእሳት ዙሪያ ከበው_ተረት አያወሩም፣
ከእለታት አንድ ቀን_አይባልም ቀረ፣
ያልኖርነውን እድሜ_ልጅም እየኖረ፣
ወንዞችም ደርቀዋል_እያሉ አይፈሱም፣
ወጣቶች ደክመዋል_ለሽበት አይደርሱም፣
ክረምትና በጋም_ተናፍቀው አይመጡም፣
ቀኖቹ እሮጠዋል_ምንም ጊዜ አይሰጡም፣
እየገሰገሰ እንዲ እየጋለበ_ጊዜ በቀን ፈረስ ዘመንን ቢያስስም፣
በአመት በአል ቀን እንኳን_አመት በአል አይደርስም፣
አሁን እንደ ዱሮ_አሁን ያለ አይመስልም፣
ቀብር ይፋጠናል_ለቅሶ አይደረስም፣
መርዶ አይተረክም_ሞትም አይፈራ፣
በሰርግ ቤት እንኳን_አይሞቅም ጭፈራ።
ለአደራ የሚበቃ_ሰው አንሷል በአገሩ፣
ጎረቤት አይመጣም_ጠንክሯል አጥሩ፣
እናቶች በፍቅር_ቡና አይጠጣጡም፣
ምን አገባኝ እያሉ_የሰው ልጅ አይቀጡም፣
ሁሉም ነገር ቢኖር_በቃ!ምንም የለም፣
ጥም አይቆርጥም ውሀ_አይማርክም ቀለም፣
ገበታ ላይ ያለም እህል ቆርሶ ይዞ_መተከዝ አያጣም፣
ይሰከራል ቶሎ_በወግ አይጠጣም፣
በቃ!! በቃ!!_ደስታ የለም።
ምኞትም ተመኘ_የድሮውን ነገር፣
ጠቅሎ ሄደና_ሀገር ከራሱ ሀገር፣
አብሮ መብላት ጠፍቶ_ፍቅር የጠፋ ዕለት፣
ደስታም ይጨክናል_ተስፋም ይጨልማል፣
የፊቱ አይታይም_አሁን ይደፈናል፣
መልኩ አይናገርም_ተፈጥሮም ዝም ይላል፣
ሙሉ ሕይወት የለም ሁሉም ባዶ_ባዶ ባዶ ይላል፣
አሁን የኛም ነገር_ይህንን ይመስላል፣
ግና ተስፋ አለ_ሁሉም ጥሩ ይሆናል።
ፍቅር ያሸንፋል!

✍️ቴዲ አፍሮ

@Yelbedrset
@aman116
@alphatourmedia
(የማርች 8 እና የእኩልነት ሀሳብን ወደ ቤትሽ ይዘሽ አትግቢ )
አላገባሁም ግን ስለትዳር ለማወቅ ለመረዳት እና መልካም ሚስት ለመሆን እማራለሁ አነባለሁ እጠይቃለሁ።
እነሆ ለብዙዎች የሚመር ግን ለተረዳው ሰው የሚጣፍጥ እውነታ ሆኖ ያገኘሁት እና የግል አቋሜን ላካፍላችሁ
ማርች 8 ሲመጣ የእኩልነት ሀሳብ በየቦታው ይጮሀል እኔም በውስጤ ይሄ ሀሳብ ይጮሀል በአደባባይ ድምጹ ብዙ የማይሰማ ቢሆንም እኔ ግን በእኔ ዘመን ላሉ ወጣት ሴቶች ይሄንን በድፍረት እናገራለሁ!
እኔ ባል እና ሚስት እኩል ናቸው ብዬ አላምንም ግን ደግሞ ሚስት ለባሏ ዘውድ ናት የሚለው ምሳሌ ይማርከኛል
ዘውድ የሚለው ቃል ኃይልን፣ክብርን፣ ዘላለማዊነትን፣ንጉሣዊነትን እና ሉዓላዊነትን ይወክላል።ብዙውን ጊዜ ከከበሩ ማዕድናት የተሠራ የተዋበ ነው!
ልባም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት መባሉ? በእግሯ አትረግጣትም በንቀት የምትታይ አይደለችም የበታች አይደለችም  ዘውድ ነች!
አንቺ ዘውድ እንድትሆኚ የባልሽን ንግስና መቀበል አለብሽ ወንድ ልጅ በተፈጥሮ ያገኘውን የመሪነት እና የመግዛት ማንነት ከተጋፋሽ ዘውድ የመሆን እድልሽን እየገፋሽ ነው ማለት ነው!
ጨዋ ሴት ለባልዋ ልዩነትንና ክብርን ትጨምራለች እሷን በመልበሱ ኩራት ይሰማዋል እሷን ሊያሳያት ይፈልጋል በሌሎች ፊት ያመሰግናታል ባሏ በአደባባይ ሲያመሰግናት ካያችሁ ብዙ ጊዜ ይሄ አስተሳሰብ አላት ማለት ነው በትዳራቸው ውስጥ የእኩልነት ሀሳብ የሚያራምዱ ሴቶች ትዳር ምሳሌ ሆኖ አላገኘሁትም!
ከሱ በብዙ መንገድ ልትበልጪ ትችያለሽ በገንዘብ ፣በእውቀት  ነገር ግን በቤት ውስጥ እሱ መሪሽ ነው  ለመብለጥ ለመፎካከር አትሞክሪ
ስለዚህ መሪነቱን በመቀበል ፣በመገዛት፣በማክበር አላማውን ግቡን እንዲያሳካ እርጂው ወንድነቱን አክብሪ።

From ©hana hailu
@isetmind

@alphatourmedia

@YelbeDrset
✍️#FB page
አለመኖር - አለማወቅ

join and share
@Yelbedrset
@Yelbedrset

inbox me @aman116