.
.
"በዚህ አለም መኖር በሁሉም የማይገኝ ነገር ነው። አብዛኛዉን ሰው ህያው ብቻ ነው። በቃ።"
✍️Oscar Wild
join and share
@Yelbedrset
@Yelbedrset
👤👤👤👤👤👤
inbox me @amanYTZ23
👤👤👤👤👤👤
.
"በዚህ አለም መኖር በሁሉም የማይገኝ ነገር ነው። አብዛኛዉን ሰው ህያው ብቻ ነው። በቃ።"
✍️Oscar Wild
join and share
@Yelbedrset
@Yelbedrset
👤👤👤👤👤👤
inbox me @amanYTZ23
👤👤👤👤👤👤
.
.
"ሁሉም ሰው የሌለው እናንተ ብቻ ያላቹህ ነገር እራሳቹህ ነው። ድምፃቹህ ፣ ጭንቅላታቹህ፣ ታሪካቹህ፣ ራዕያቹህ። ስለዚህ ፃፉ እና ሳሉ እና ገንቡ እና ተጫዎቱ እና ዳንሱ እናም እንደምትችሉት ሁናቹህ ኑሩ።"
✍NEIL GAIMAN
join and share
@Yelbedrset
@Yelbedrset
✍✍✍✍✍✍
inbox me @aman116

#ዘወረደ_አራት_ነገሮች_ይነገሩበታል 👇
1.የአዳም ከገነት ወደ ምድረ ፋይድ መውረድ
2.የወረደውን ለመመለስ የአካላዊ ቃል ከሰማይ መውረድ
3.ከሰማይ የወረደው ጌታ የተሰቀለበት የዕፀ መስቀል ከኢየሩሳሌም ወደ ፋርስ መውረድ
4.ክርስቶስ የወሰደለት የእኛ ሰውነት ከጽድቅ ከቅድስና ወደ ኃጢአት መውረድ ይነገርበታል!
ለአራቱም ከፍታ/መመለስ/ዕርገት አላቸው 👇
1.አዳም ወደ ገነት ተመልሷል
2.ክርስቶስም ወደ ሰማይ ዐርጓል
3.ዕፀ መስቀሉም በንጉሠ ሮም ኅርቃል አማካይነት በምእመናነ ኢየሩሳሌም ጾምና ጸሎት በ 614 ዓ.ም ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሷል
4.እኛም በንስሐ እናርጋለን (ወደ ጽድቅ ወደ ቅድስና እንመለሳለን)
አጠቃላይ የጾሙ ምሥጢርም ይኸው ነው
ከፍታ የሚነገርበት በይቅርታ እግዚአብሔርን የምንመስልበት የሥጋ ሳይሆን የመንፈስ ለውጥ የምናሳይበት ነው!
ጾሙን ለምሕረትና ለበረከት ድል ለመንሣት ያድርግልን🙏
ሠናይ ዐቢይ ጾም!
መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው ዘመካኒሳ ሚካኤል
From ✍ፉኖተ ጽድቅ
@alphatourmedia
@YelbeDrset

እንቅስቃሴዋ ሁሉ ክብርዋን የጠበቀ ይሁን
የትም መቸም ቢገኙ እራሱዋን እንደ የክብር እንግዳ ይቁጠሩ ። ሌሎች ሰወች በዙሪያቸው በሚካሂደው ነገር ሲረበሹ እርስዋ ከክብርዋ አይውረዱ ። ጭፍን ፈጥዝያና ዝላይ የበዛባቸውን ድግሶች አይታደሙ ። ህዝባዊይ በሆኑ ስብሰባወች በዓላት ላይ ቢታደሙ ከህይወት አላማወት አቁሞት ላይ ዝንፍ አይበሉ።
✍Roha(@alphatourmedia)

#ፈራሁ
.
.
ደመናት በሰማይ ቅርፅ እየፈጠሩ _ አይስሉም ትተዋል፣
የጓሮ ሰበዞች_ አበቦች ረግፈዋል።
ወንዞችም ጠፍተዋል_እንደ ዱሮ አይመጡም፣
ሽማግሌዎች ዛፍ ስር_ሸንጎ አይቀመጡም፣
ያልጠኑ ጥጃዎች እየፈነጠዙ_መስክ ላይ አይሮጡም፣
ልጆች ሲቆጧቸው_ቶሎ አይደነግጡም፣
ህፃናት አውቀዋል_እንደ ልጅ አይፈሩም፣
በእሳት ዙሪያ ከበው_ተረት አያወሩም፣
ከእለታት አንድ ቀን_አይባልም ቀረ፣
ያልኖርነውን እድሜ_ልጅም እየኖረ፣
ወንዞችም ደርቀዋል_እያሉ አይፈሱም፣
ወጣቶች ደክመዋል_ለሽበት አይደርሱም፣
ክረምትና በጋም_ተናፍቀው አይመጡም፣
ቀኖቹ እሮጠዋል_ምንም ጊዜ አይሰጡም፣
እየገሰገሰ እንዲ እየጋለበ_ጊዜ በቀን ፈረስ ዘመንን ቢያስስም፣
በአመት በአል ቀን እንኳን_አመት በአል አይደርስም፣
አሁን እንደ ዱሮ_አሁን ያለ አይመስልም፣
ቀብር ይፋጠናል_ለቅሶ አይደረስም፣
መርዶ አይተረክም_ሞትም አይፈራ፣
በሰርግ ቤት እንኳን_አይሞቅም ጭፈራ።
ለአደራ የሚበቃ_ሰው አንሷል በአገሩ፣
ጎረቤት አይመጣም_ጠንክሯል አጥሩ፣
እናቶች በፍቅር_ቡና አይጠጣጡም፣
ምን አገባኝ እያሉ_የሰው ልጅ አይቀጡም፣
ሁሉም ነገር ቢኖር_በቃ!ምንም የለም፣
ጥም አይቆርጥም ውሀ_አይማርክም ቀለም፣
ገበታ ላይ ያለም እህል ቆርሶ ይዞ_መተከዝ አያጣም፣
ይሰከራል ቶሎ_በወግ አይጠጣም፣
በቃ!! በቃ!!_ደስታ የለም።
ምኞትም ተመኘ_የድሮውን ነገር፣
ጠቅሎ ሄደና_ሀገር ከራሱ ሀገር፣
አብሮ መብላት ጠፍቶ_ፍቅር የጠፋ ዕለት፣
ደስታም ይጨክናል_ተስፋም ይጨልማል፣
የፊቱ አይታይም_አሁን ይደፈናል፣
መልኩ አይናገርም_ተፈጥሮም ዝም ይላል፣
ሙሉ ሕይወት የለም ሁሉም ባዶ_ባዶ ባዶ ይላል፣
አሁን የኛም ነገር_ይህንን ይመስላል፣
ግና ተስፋ አለ_ሁሉም ጥሩ ይሆናል።
ፍቅር ያሸንፋል!
✍️ቴዲ አፍሮ
@Yelbedrset
@aman116
@alphatourmedia
.
#ፈራሁ
.
.
ደመናት በሰማይ ቅርፅ እየፈጠሩ _ አይስሉም ትተዋል፣
የጓሮ ሰበዞች_ አበቦች ረግፈዋል።
ወንዞችም ጠፍተዋል_እንደ ዱሮ አይመጡም፣
ሽማግሌዎች ዛፍ ስር_ሸንጎ አይቀመጡም፣
ያልጠኑ ጥጃዎች እየፈነጠዙ_መስክ ላይ አይሮጡም፣
ልጆች ሲቆጧቸው_ቶሎ አይደነግጡም፣
ህፃናት አውቀዋል_እንደ ልጅ አይፈሩም፣
በእሳት ዙሪያ ከበው_ተረት አያወሩም፣
ከእለታት አንድ ቀን_አይባልም ቀረ፣
ያልኖርነውን እድሜ_ልጅም እየኖረ፣
ወንዞችም ደርቀዋል_እያሉ አይፈሱም፣
ወጣቶች ደክመዋል_ለሽበት አይደርሱም፣
ክረምትና በጋም_ተናፍቀው አይመጡም፣
ቀኖቹ እሮጠዋል_ምንም ጊዜ አይሰጡም፣
እየገሰገሰ እንዲ እየጋለበ_ጊዜ በቀን ፈረስ ዘመንን ቢያስስም፣
በአመት በአል ቀን እንኳን_አመት በአል አይደርስም፣
አሁን እንደ ዱሮ_አሁን ያለ አይመስልም፣
ቀብር ይፋጠናል_ለቅሶ አይደረስም፣
መርዶ አይተረክም_ሞትም አይፈራ፣
በሰርግ ቤት እንኳን_አይሞቅም ጭፈራ።
ለአደራ የሚበቃ_ሰው አንሷል በአገሩ፣
ጎረቤት አይመጣም_ጠንክሯል አጥሩ፣
እናቶች በፍቅር_ቡና አይጠጣጡም፣
ምን አገባኝ እያሉ_የሰው ልጅ አይቀጡም፣
ሁሉም ነገር ቢኖር_በቃ!ምንም የለም፣
ጥም አይቆርጥም ውሀ_አይማርክም ቀለም፣
ገበታ ላይ ያለም እህል ቆርሶ ይዞ_መተከዝ አያጣም፣
ይሰከራል ቶሎ_በወግ አይጠጣም፣
በቃ!! በቃ!!_ደስታ የለም።
ምኞትም ተመኘ_የድሮውን ነገር፣
ጠቅሎ ሄደና_ሀገር ከራሱ ሀገር፣
አብሮ መብላት ጠፍቶ_ፍቅር የጠፋ ዕለት፣
ደስታም ይጨክናል_ተስፋም ይጨልማል፣
የፊቱ አይታይም_አሁን ይደፈናል፣
መልኩ አይናገርም_ተፈጥሮም ዝም ይላል፣
ሙሉ ሕይወት የለም ሁሉም ባዶ_ባዶ ባዶ ይላል፣
አሁን የኛም ነገር_ይህንን ይመስላል፣
ግና ተስፋ አለ_ሁሉም ጥሩ ይሆናል።
ፍቅር ያሸንፋል!
✍️ቴዲ አፍሮ
@Yelbedrset
@aman116
@alphatourmedia
(የማርች 8 እና የእኩልነት ሀሳብን ወደ ቤትሽ ይዘሽ አትግቢ )
አላገባሁም ግን ስለትዳር ለማወቅ ለመረዳት እና መልካም ሚስት ለመሆን እማራለሁ አነባለሁ እጠይቃለሁ።
እነሆ ለብዙዎች የሚመር ግን ለተረዳው ሰው የሚጣፍጥ እውነታ ሆኖ ያገኘሁት እና የግል አቋሜን ላካፍላችሁ
ማርች 8 ሲመጣ የእኩልነት ሀሳብ በየቦታው ይጮሀል እኔም በውስጤ ይሄ ሀሳብ ይጮሀል በአደባባይ ድምጹ ብዙ የማይሰማ ቢሆንም እኔ ግን በእኔ ዘመን ላሉ ወጣት ሴቶች ይሄንን በድፍረት እናገራለሁ!
እኔ ባል እና ሚስት እኩል ናቸው ብዬ አላምንም ግን ደግሞ ሚስት ለባሏ ዘውድ ናት የሚለው ምሳሌ ይማርከኛል
ዘውድ የሚለው ቃል ኃይልን፣ክብርን፣ ዘላለማዊነትን፣ንጉሣዊነትን እና ሉዓላዊነትን ይወክላል።ብዙውን ጊዜ ከከበሩ ማዕድናት የተሠራ የተዋበ ነው!
ልባም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት መባሉ? በእግሯ አትረግጣትም በንቀት የምትታይ አይደለችም የበታች አይደለችም ዘውድ ነች!
አንቺ ዘውድ እንድትሆኚ የባልሽን ንግስና መቀበል አለብሽ ወንድ ልጅ በተፈጥሮ ያገኘውን የመሪነት እና የመግዛት ማንነት ከተጋፋሽ ዘውድ የመሆን እድልሽን እየገፋሽ ነው ማለት ነው!
ጨዋ ሴት ለባልዋ ልዩነትንና ክብርን ትጨምራለች እሷን በመልበሱ ኩራት ይሰማዋል እሷን ሊያሳያት ይፈልጋል በሌሎች ፊት ያመሰግናታል ባሏ በአደባባይ ሲያመሰግናት ካያችሁ ብዙ ጊዜ ይሄ አስተሳሰብ አላት ማለት ነው በትዳራቸው ውስጥ የእኩልነት ሀሳብ የሚያራምዱ ሴቶች ትዳር ምሳሌ ሆኖ አላገኘሁትም!
ከሱ በብዙ መንገድ ልትበልጪ ትችያለሽ በገንዘብ ፣በእውቀት ነገር ግን በቤት ውስጥ እሱ መሪሽ ነው ለመብለጥ ለመፎካከር አትሞክሪ
ስለዚህ መሪነቱን በመቀበል ፣በመገዛት፣በማክበር አላማውን ግቡን እንዲያሳካ እርጂው ወንድነቱን አክብሪ።
From ©hana hailu
@isetmind

"በምትሞትበት ጊዜ በመጀመሪያ ስምህ ይቀየራል ስምህም ሬሳ ትባላለች" እከሌ/እከሊት ሳይሆን ሬሳዉ አልወጣም ወይ ትባላለህ። የቅርብ ሰዉ እንኳን ቢሆን ከጎንህ ሊሆን ይፈራል"
ወደ መቃብር ስፍራ ወስደዉ አጣድፈዉ ከቀበሩህ በሗላ ብቻህን ጥለዉህ ለመሔድ ይቻኮላሉ።
ላይጠቅምህ አብሬህ ካልሔድኩ እያለ የሚያለቅሱልህ እንኳን ቢኖር ቀብሮህ ተሎ ይሸሻል።ቀብረዉህ እደተመለሱ ንብረት ካለህ ለመከፋፈል ይጣደፋሉ ። ከሳምንት በሗላ ጭራሹኑ ከምድር ያልኖርክ እስኪመስል ድረስ በአብዛኞቹ ትረሳለህ ።
የቅርብ ወዳጆችህ እንኳን ቢሆኑ ሀዘኑ በልባቸዉ ጥቂት ወራት ያክል ቢቆይ ነዉ ።በቃ ምድር ላይ የነበረህ ቆይታ በዚህ መልኩ ይጠናቀቃል ።ፍራሽህ አፈር ትራስህ ደሞ ድንጋይ ይሆናል😌 ይሔዉ ነዉ ።
ያኔ ማንም ምንም አይጠቅምህም መልካም ስራህ ብቻ🙌
በዚች አለም ላይ እድለኛ ሠዉ ማለት በህይወት እያለ ወደ ፈጣሪዉ የተመለሠ ሰዉ ነዉ 🙌"👏
From Alpha

#ጥላ
ጠዋት
ፀሐይ ፍልቅ ብላ ጎህ እንደቀደደ
ከምስራቅ ተነስቶ ምዕራብ ወደቀ
ቀትር
ሰሜን አልዘመተ ደቡብም አልሄደ
ከምዕራብ ተነስቶ እግሬ ስር ሰገደ
ማታ
ከምዕራብ እግሬ ስር ትሁት የነበረ
ከእግሬ ስር ተነስቶ ወደ ምስራቅ ዞረ
ሌሊት
ጨለማ ጎልብቶ ብርሀኑ ሲገፋ
አቻውን አግንቶ እኔን ክዶኝ ጠፋ
ቀኑን ከኔ ውሎ ሌቱን ካላደረ
ፀሐይ ወይስ ጥላ ከእኔ ጋር የዞረ ??
@Yelbedrset
@Yelbedrset
@Jona20t የጥበብ
ጠዋት
ፀሐይ ፍልቅ ብላ ጎህ እንደቀደደ
ከምስራቅ ተነስቶ ምዕራብ ወደቀ
ቀትር
ሰሜን አልዘመተ ደቡብም አልሄደ
ከምዕራብ ተነስቶ እግሬ ስር ሰገደ
ማታ
ከምዕራብ እግሬ ስር ትሁት የነበረ
ከእግሬ ስር ተነስቶ ወደ ምስራቅ ዞረ
ሌሊት
ጨለማ ጎልብቶ ብርሀኑ ሲገፋ
አቻውን አግንቶ እኔን ክዶኝ ጠፋ
ቀኑን ከኔ ውሎ ሌቱን ካላደረ
ፀሐይ ወይስ ጥላ ከእኔ ጋር የዞረ ??
@Yelbedrset
@Yelbedrset
@Jona20t የጥበብ
አንቺ
በአንቺ ሰፈር ሹሞች
ድንቁርና ገዝፎ ደልቶት ሲደላደል
ፅድቅ ነው ይሉታል የሚሰሩትን በደል
የሐቂቃን ክብደት ሲመዝኑት በውሸት
ቆሮቆንዳን ሁላ ይሉታል ለጋ እሸት
@Yelbedrset @Yelbedrset
Yebekal Godan ✍️
@Jona20t
በአንቺ ሰፈር ሹሞች
ድንቁርና ገዝፎ ደልቶት ሲደላደል
ፅድቅ ነው ይሉታል የሚሰሩትን በደል
የሐቂቃን ክብደት ሲመዝኑት በውሸት
ቆሮቆንዳን ሁላ ይሉታል ለጋ እሸት
@Yelbedrset @Yelbedrset
Yebekal Godan ✍️
@Jona20t
☦☦☦☦☦☦☦☦☦☦☦☦☦
"ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እም ንዋም
ወከመ ኃይል ወኅዳገ ወይን" መዝ 77፥65
☦እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤዉ
በሰላም አደረሳችሁ!☦
በዓሉ የሰላም ፣የፍቅር ፣የደስታ ይሁንልን።
☦መልካም በዓል☦
@YelbeDrset @YelbeDrset
inbox @amanYTZ23
"ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እም ንዋም
ወከመ ኃይል ወኅዳገ ወይን" መዝ 77፥65
☦እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤዉ
በሰላም አደረሳችሁ!☦
በዓሉ የሰላም ፣የፍቅር ፣የደስታ ይሁንልን።
☦መልካም በዓል☦
@YelbeDrset @YelbeDrset
inbox @amanYTZ23
እንኳን አደረሳችሁ🙏
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 1,444ኛው የዒድ አልፈጥር (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!👳♂️👳♂️👳♂️
ዒድ ሙባረክ!
عيد الأضحى!
Eid Mubarek
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset
@YelbeDrset
👳♂👳♂👳♂👳♂👳♂
inbox @aman116
🧕🧕🧕🧕🧕

# የጓደኛዬ ኑዛዜ
ክፍል 1
ቅዱሳን መካናትን በኢየሩሳሌምና አካባቢው ለመሳለም ከባለቤቱ ጋር እስራኤል ሄዶ እንደተመለሰ ጓደኛዬ ደወለልኝና፦
“ ደኅና መጣችሁ ? እንዴት ነበር ጉዟችሁ? ስለው
“አየኋት እኮ! ገሊላ ባሕር ዳር ቆማ አየኋት !”አለኝ በደስታ ሲቃ። ቀጠለና
“ሀገረ ሕይወት ፣ ብሔረ ቅዱሳን ለመግባቷ ጥርጥር የለኝም፤ የጌታዬ ምህረት በዛልኝ!” አለኝ።
“ምንድን ነው የምታወራው ? ማንን ነው ገሊላ ባሕር ዳር ቆማ ያየሃት ?” አልኩት ነገሩ ግራ አጋብቶኝ።
ይልቅስ “ አሁን ተሎ ላግኝህ ”አለኝና ቤቴ መሆኔን ስነግረው “መጣሁ መጣሁ ” አለና ስልኩን ዘጋው።
የቤቴ በረንዳ ላይ ወንበር አውጥቼ እንደተቀመጥን፦
“መጀመሪያ እንዴት እንዳየኋት ልንገርህና ማን መሆኗን ኃላ እነግርሀለሁ ። ለብዙ ጊዜ ልነግርህ እየፈለኩ ያልነገርኩህ የኑዛዜ ታሪክ አለኝ” አለ።
የሄደበትን የጉብኝት ዝርዝር ከመንገር ይልቅ ሌላ ግራ የሚያገባ ጉዳይ ቢመዝም ጉጉት የሚጭር ስለሆነ፦
“በል እሽ በመሰለህ መልኩ ተርክልኝ ” አልኩት በትኩረት ለማዳመጥ መዘጋጀቴን በሚያሳይ መልክ ሁለመናዬን ወደ እርሱ አዙሬ።
“እንዴት መሰለህ !ሌሊቱንና ረፋዱን የትንሳኤን በዓል በኢየሩሳሌም ካከበርን በኋላ ከሠዓት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዶ ወደ አደረገበትና የማስተማር ሥራውን ወደ ጀመረበት ወደ ገሊላ አውራጃ ተጓዝን።
ገሊላ ጥብርያዶስ ደርሰን ሆቴል ገብተን አረፍ አልን። ወደ 12 ስዓት አየሩ ቀዝቀዝ ሲል ከባለቤቴ ጋር ተያይዘን ወደ ጥብርያዶስ ዳርቻ ሄድን።
እንደምታውቀው የጥብርያዶስ (የገሊላ ) ባሕር ክርስቶስ በጀልባ እየተመላለሰ ፣ ደቀመዛሙርቱን ያስጨነቀውን የባሕሩን ሞገድ የገሰፀበት ፣ ጴጥሮስ ተጠራጥሮ ሊሰጥም ሲል ያወጣበት ፣ በቃሉ ብዙ ዓሣ የተጠመደበት ፣ አብዛኞቹ ሐዋርያት የተጠሩበት ባሕር መሆኑን ማሰብ ልዩ መንፈሣዊ ሀሴት ያጎናፅፋል ። ይህንን እየተነጋገርን በባሕሩ ዳር ትንሽ እንደተጓዝን አንዲት እስራዔላዊት ወጣት ፊቷን ወደ ሀይቁ አዙራ በእጆቿ የጸሎት መጽሐፏን ይዛ ከፊት ወደኋላ ጎንበስ ቀና እያለች እንደ አይሁድ ልማድና ፀሎት ታደርሳለች። ወጣትነቷ ፣ ዘመናዊ አለባበሷ ፣ በባዶ እግሯ ቆማ መጸለይዋ ተዳምሮ ልዩ ትንግርት ነበር። ከእኔ ይልቅ ባለቤቴ በተመስጦ ታያት ነበር።
"አየህ ይህች ልጅ ወጣት ናት፣ ዘመናዊ ናት። በዚህ በሠለጠነ ዓለም የተገኘች ባትሆንም ሃይማኖት አልረሳችም አለች በአድናቆት ።
"እውነት አልሽ። እስራኤል ሃይማኖትን ከሥልጣኔ ጋር በአግባቡ ያጋባች ሀገር ናት። የጥንካሬዋም ምንጭም ማንነቷን ማክበሯ ነው። ይሁዲነት የትም አገር ይኖራል ። እስራኤል ግን ያለይሁዲነት የለችም። ይህ በወጉ ተረድተዋል' አልኳት።
ባለቤቴ ቀጠለችና በስሜት ሆና፦
'በሚቀጥለው ጊዜ ልጆቼን አምጥቼ ይህን ምሥጢር እንዲረዱ ማድረግ አለብኝ። ሃይማኖትን ጠብቆ፣ ማንነትን አክብሮ መሰልጠንና መዘመን እንደሚቻል መረዳት አለባቸው ። ያለችንን ትንሽ ገንዘብ ከማውረስ ይልቅ ይህን ባሳያቸው ለራሳቸውም ለሀገርም ኃላፊነቴን ተወጣሁ ማለት ነው' አለች።
ግሩም ሀሳብ ነው!' ብያት በባሕሩ አቅራቢያ እየተዘዋወርን ውሃውን እየቀዳን ራሣችን ላይ እያፈሰስን በሀሴት አምሽተን ወደ ሆቴላችን ተመለስን።
“እሺ ከዚያስ?” አልኩት ታሪኩ አልያዝልህ ቢለኝ።
"ከሌሎች ተጓዦች ጋር ራታችን ተመግበን ፈጣሪን አመስግነን ወደ የክፍላችን ሄደን ተኛን። ብዙም ሳልቆይ ደስ ብሎኝ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ።
ከባለቤቴ ጋር በአድናቆት ጎንበስ ቀና እያለች ጸሎት ስታደርስ ያየናት ወጣት ትመስለኛለች ። ልክ ምሽት ላይ እንዳየናት ጸሎቷን ቀጥላለች ።ቆይታ በትከሻዋ በኩል ወደኋላ የወረደው ወርቃማ ፀጉሯ ተቀይሮ አጠር ያለ የሀበሻ ፀጉር መሰለ። ቀጥ ብለው የቆሙት የእግሮቿ ባት የቆዳ ቀለም ከፈረንጅ ሊጥ መሰል ቆዳ ወደ ጠይም የሀበሻ ቆዳ ቀለም ሲቀየር ታየኝ። ድንገት ዞር ስትል በዚያች በአንዲት በጭቃና እንጨት በተሠራች ክፍል ተጥላ የነበረችው <ሰናይት> ናት።
ይቀጥላል...
ደራሲ ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ
#ችቦ

#ለእግዜር_የተላከ_ደብዳቤ!
.
.
እንደምነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው?
እኛማ...
ለእልፍ አዕላፍ አለቃ
ማመልከቻ ፅፈን፣
ለወፈ ሰማይ ህዝብ
መድረክ ላይ ለፍፈን፣
ፆለት ቤታችንን
እኛው ላይ ቆልፈን፣
የምድር አተካራ
ህግጋቱን አልፈን
ደብዳቤ ላክንልህ፤
አይንህን ካየነው
ሁለት ሺህ ዘመን
እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ መቅረትህ ገዘፈ...
እንደውም እንደውም...
"በእመጣለሁ ተስፋ
ሁለት ሺህ ዘመን
ገትሮን ከጠፋ፣
በቀጠሮው ሰአት
መምጣት ከተሳነው፣
እግዜር አበሻ ነው"
እያሉ ያሙሃል...
እኔ ምን አውቃለሁ...
አመስግነው ሲሉ እልልታ የማቀልጥ፣
ቃሉን ስማ ሲሉኝ...ሰባኪው እግር ስር በደስታ እምቀመጥ፣
'እግዚኦ! በሉ' ሲባል...እንባዬን የማፈስ፣
ሃሌ ሉያ ሲሉኝ...በሳቅ ልቤ 'ሚፈርስ፣
ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ፣
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ፣
እኔ ምን አውቃለሁ...
ግን አንተ ደህና ነህ?
ከምር እንደሚያሙት ምፅአት ቀረ እንዴ?
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አትከፋም አንዳንዴ!
የሆነስ ሆነና ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
አብረሃም ሰላም ነው...?
እዛስ ቤት ገነባ ዛሬም በድንኳን ነው?
እኛማ ይሄውልህ...
በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን፣
"ኤሎሄ" እንላለን ጎጆ እንድትጥልልን....
ወደላይ ገነባን ወደጎን አሰፋን፣
ወደላይም ከላይ ወደጎንም ከጎን
እንደጉድ ተገፋን...
ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን!!
አባታችን ሙሴ እንዴት ነው ለክብሩ፣
ውቂያኖስ መክፈያው ደህና ናት በትሩ?
እኛማ ይሄውልህ...
እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋርጥ፣
የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ፣
የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን፣
ንገርልንና በትሩን ያውሰን...
እናልህ እግዜር ሆይ...
ከተስፋዋ ምድር ወደሌላ ተስፋ አለን እየኳተን
መሄጃው ሲገርመን መመለሻ መንገድ መቆሚያ ቦታ አጥተን...!
ላባታችን ሙሴ እንደምትልልን..
"የመሄድ ዘመን ነው ባህር የመሻገር
ዱላህን ላክልን" ብሎሃል በልልኝ...
"ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
ዳዊትስ ደህና ነው?
ዛሬም ይዘምራል?
ዛሬም ይፎክራል?
ሰላም ነው ጠጠሩ?
ሰላም ናት ወንጭፉ?
እዛስ አቅል ገዛ ጎሊያድ ተራራው ጎሊያድ ግዙፉ?
እልፍ አዕላፍ ጎሊያድ ከቦን ሲደነፋ፣
ወንጭፉን ጠቅልሎ ምነው ዳዊት ጠፋ?
ብሎሃል በልልኝ!!
ለረከሰ ጠጠር ለሞላ ወርዋሪ፣
"ወንጭፍህን ስጠው ለዚህ ታሪክ አውሪ"
ብለህ እዘዝልን...!!
እንዴት ነህ ጌታ ሆይ? ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
የሙሴ አልጋ ወራሽ እያሱ ሰላም ነው?
ያቆማትን ፀሃይ ግቢ ቢላት ምነው?
ያው እንደምታውቀው፣
አስራ ሶስት ወራት ነው ፀሃይ የምንሞቀው
ኧረ ፀሀይ በዛ፣ኧረ ፀሀይ በዛ
የመጣው ወር ሀሉ ፀሀይ እያዘለ፣
የተሾመው ሁሉ "ፀሀይ ነኝ" እያለ
የአስራ ሶስት ወር የግዜር ፀሃይ፣
የአስራ ሶስት ወር የሰው ጀምበር፣
ባቃጠላት ምድጃ አገር፣
ምን ታምር ሊኖር ይችላል ፀሀይ ሁኖ እንደመፈጠር
ኧረ እግዜር በናትህ በጭንቅ አማላጇ፣
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ፣
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና፣
ሙቀት ገደለና!
እናልህ እግዜር ሆይ ማጣፊያው አጥሮናል፣
ስም ያለው ሞኝ ነው ሁሉም ይጠራናል
ጳውሎስ ሲሉን...አቤት
ጴጥሮስ ሲሉን...ወይዬ
ይሁዳ ሲሉንም አቤት እንላለን፣
ስማችንን ሸጠን...ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን
ተወው የኛን ነገር...ሰማይ ቤት እንዴት ነው....
ሄዋንስ ደህና ናት?
ያው የልጅ ልጆቿ በእግሯ ተተክተው
የፍሬው ሲገርምህ ግንዱንም አንክተው
ለፍጥረተ አዳም ባይኑ ያገምጡታል፣
ሰይጣንም ደህና ነው ኑሮ ተስማምቶታል...
ሰውን ለማሳሳት ላይ ታች ማለት ትቷል፣
ሳይጠራው የሚጎርፍ ህዝብ በዝቶለታል...!!
ኧረ እግዜር በናትህ በጭንቅ አማላጇ፣
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ፣
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና፣
ሙቀት ገደለና!!!
✍️አሌክስ አብርሃም
join and share
@Yelbedrset
@Yelbedrset
✍✍✍✍✍✍
inbox me @aman116
✍✍✍✍✍✍
.
#ለእግዜር_የተላከ_ደብዳቤ!
.
.
እንደምነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው?
እኛማ...
ለእልፍ አዕላፍ አለቃ
ማመልከቻ ፅፈን፣
ለወፈ ሰማይ ህዝብ
መድረክ ላይ ለፍፈን፣
ፆለት ቤታችንን
እኛው ላይ ቆልፈን፣
የምድር አተካራ
ህግጋቱን አልፈን
ደብዳቤ ላክንልህ፤
አይንህን ካየነው
ሁለት ሺህ ዘመን
እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ መቅረትህ ገዘፈ...
እንደውም እንደውም...
"በእመጣለሁ ተስፋ
ሁለት ሺህ ዘመን
ገትሮን ከጠፋ፣
በቀጠሮው ሰአት
መምጣት ከተሳነው፣
እግዜር አበሻ ነው"
እያሉ ያሙሃል...
እኔ ምን አውቃለሁ...
አመስግነው ሲሉ እልልታ የማቀልጥ፣
ቃሉን ስማ ሲሉኝ...ሰባኪው እግር ስር በደስታ እምቀመጥ፣
'እግዚኦ! በሉ' ሲባል...እንባዬን የማፈስ፣
ሃሌ ሉያ ሲሉኝ...በሳቅ ልቤ 'ሚፈርስ፣
ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ፣
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ፣
እኔ ምን አውቃለሁ...
ግን አንተ ደህና ነህ?
ከምር እንደሚያሙት ምፅአት ቀረ እንዴ?
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አትከፋም አንዳንዴ!
የሆነስ ሆነና ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
አብረሃም ሰላም ነው...?
እዛስ ቤት ገነባ ዛሬም በድንኳን ነው?
እኛማ ይሄውልህ...
በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን፣
"ኤሎሄ" እንላለን ጎጆ እንድትጥልልን....
ወደላይ ገነባን ወደጎን አሰፋን፣
ወደላይም ከላይ ወደጎንም ከጎን
እንደጉድ ተገፋን...
ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን!!
አባታችን ሙሴ እንዴት ነው ለክብሩ፣
ውቂያኖስ መክፈያው ደህና ናት በትሩ?
እኛማ ይሄውልህ...
እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋርጥ፣
የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ፣
የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን፣
ንገርልንና በትሩን ያውሰን...
እናልህ እግዜር ሆይ...
ከተስፋዋ ምድር ወደሌላ ተስፋ አለን እየኳተን
መሄጃው ሲገርመን መመለሻ መንገድ መቆሚያ ቦታ አጥተን...!
ላባታችን ሙሴ እንደምትልልን..
"የመሄድ ዘመን ነው ባህር የመሻገር
ዱላህን ላክልን" ብሎሃል በልልኝ...
"ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
ዳዊትስ ደህና ነው?
ዛሬም ይዘምራል?
ዛሬም ይፎክራል?
ሰላም ነው ጠጠሩ?
ሰላም ናት ወንጭፉ?
እዛስ አቅል ገዛ ጎሊያድ ተራራው ጎሊያድ ግዙፉ?
እልፍ አዕላፍ ጎሊያድ ከቦን ሲደነፋ፣
ወንጭፉን ጠቅልሎ ምነው ዳዊት ጠፋ?
ብሎሃል በልልኝ!!
ለረከሰ ጠጠር ለሞላ ወርዋሪ፣
"ወንጭፍህን ስጠው ለዚህ ታሪክ አውሪ"
ብለህ እዘዝልን...!!
እንዴት ነህ ጌታ ሆይ? ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
የሙሴ አልጋ ወራሽ እያሱ ሰላም ነው?
ያቆማትን ፀሃይ ግቢ ቢላት ምነው?
ያው እንደምታውቀው፣
አስራ ሶስት ወራት ነው ፀሃይ የምንሞቀው
ኧረ ፀሀይ በዛ፣ኧረ ፀሀይ በዛ
የመጣው ወር ሀሉ ፀሀይ እያዘለ፣
የተሾመው ሁሉ "ፀሀይ ነኝ" እያለ
የአስራ ሶስት ወር የግዜር ፀሃይ፣
የአስራ ሶስት ወር የሰው ጀምበር፣
ባቃጠላት ምድጃ አገር፣
ምን ታምር ሊኖር ይችላል ፀሀይ ሁኖ እንደመፈጠር
ኧረ እግዜር በናትህ በጭንቅ አማላጇ፣
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ፣
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና፣
ሙቀት ገደለና!
እናልህ እግዜር ሆይ ማጣፊያው አጥሮናል፣
ስም ያለው ሞኝ ነው ሁሉም ይጠራናል
ጳውሎስ ሲሉን...አቤት
ጴጥሮስ ሲሉን...ወይዬ
ይሁዳ ሲሉንም አቤት እንላለን፣
ስማችንን ሸጠን...ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን
ተወው የኛን ነገር...ሰማይ ቤት እንዴት ነው....
ሄዋንስ ደህና ናት?
ያው የልጅ ልጆቿ በእግሯ ተተክተው
የፍሬው ሲገርምህ ግንዱንም አንክተው
ለፍጥረተ አዳም ባይኑ ያገምጡታል፣
ሰይጣንም ደህና ነው ኑሮ ተስማምቶታል...
ሰውን ለማሳሳት ላይ ታች ማለት ትቷል፣
ሳይጠራው የሚጎርፍ ህዝብ በዝቶለታል...!!
ኧረ እግዜር በናትህ በጭንቅ አማላጇ፣
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ፣
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና፣
ሙቀት ገደለና!!!
✍️አሌክስ አብርሃም
join and share
@Yelbedrset
@Yelbedrset
✍✍✍✍✍✍
inbox me @aman116
✍✍✍✍✍✍
አባቴ ከማውቃቸው ሰዎች ሁሉ ምስኪኑ ሰው ነው።
አባቴ ዝምተኛ ነው። ዝምተኛ ነው ስል እነዚህ ማውራት እየቻሉ ምናባቱ ብለው እንደሚተውዉት ሰዎች አይደለም። እሱ የሚያወራው ነገር የለውም። ይኸው ነው።
አባቴ እወንድሜ ቤት ከተማ ይመጣና ብዙ ቀን መቆየት አይችልም። ከተማ ይጨንቀዋል። እሱ የሚወደው አፈር፤ ሳር፣ ቅጠል፣ ከብቶች፣ ሰማዩና መሬቱ የሚገናኙበትን አድማስ ማየት። በቃ።
አባኮ ጭምት ከመሆኑ የተነሳ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ልጆቹን በስማችን አይጠራንም ነበረ። ስሜን ስለማያውቀው ነው ወይስ መጥራት ያፍራል? እያልኩ የማስብበት ወቅት ነበረኝ። ከፈለገኝ ዝም ይልና “አቡሽ” ይለኛል😂 Not anymore tho. Now he calls me by my name, አዳም ይለኛል።
የኔ አባት ይሄ ሁላ ዘመን ሲፈራረቅበት እንዴት አድርጎ በዝምታ እንደሚያሳልፈው አላውቅም። ትንሽ አረቄ ከጠጣ ብቻ ይጫወታል። እንደኔ ጭንቅላቱ አልኮሆል አይችልለትም። ሁለት ከጠጣ በቃ። እናቴ ትናደዳለች ከዛ። ራስህ አይችልምኮ ለምን ትጠጣለህ ብላ ትቆጣዋለች። ገንዘብሽን ጨረስኩብሽ አይደለም? ይላል። አልነካብሽም ሁለተኛ ይላል። እኔ እስቃለሁ። ብቸኛው ድምጹን ከፍ አርጎ የሚያወራበት ሰዓት ያን ጊዜ ነው።
'አባ የምሥራቅ በር’* ሰዓት አያስርም። ስልክም አይጠቀምም። ምን ሊያደርግለት። ዝም ብሎ ማረስ፣ መዝራት፣ ማረም፣ መኮትኮት፣ ማጨድ፣ መውቃት.... ካመት እስካመት። በቃ።
ድንገት ትዝ ባለኝ ቀን ስለሱ አስብና ያሳዝነኛል። ከገበሬው ማህበረሰብ ውስጥ ስለሚገኝ መንግሥትና እግዜር እየተቀባበሉ ደባ ይሠሩበታል። ከገበሬም ዝምተኛ እና ጭምት ስለሆነ ዘመናይ ነን ባዮች፣ እንዳቅማቸው ዘምናኖች በየሄደበት ብልጫ ይወስዱበታል። ኧረ ምን ላድርግህ ጌትዬ!
አሁን አሁን ብዙ ጊዜ ስለማንገናኝ አልፎ አልፎ ስንገናኝ ያወራኛል። እንደሩቅ ሀገር ሰው ይጠይቀኛል ብዙ ነገር። የመጣልኝን መልስ እሰጠዋለሁ። ብዙ ጊዜ በሙሉ ዐይኑ አያየኝም። ካየኝ እፈራዋለሁ። “ይሄን ሁላ ፍቅር ተቀብዬ ምንድነው የማደርገው? ይ'ገባኛልን?” እላለሁ። አየው አየውና ለቅሶ ይከጅለኛል። ከግር እስከራሱ የሚዳሰስ ምንዱብ ነው።
ስለሱ ሳስብ ጎልቶ ትዝ የሚለኝ ነገር ኩታራ ሆኜ ለበዓላት ገንዘብ ካላመጣህ ብዬ ልቡን የምሰቅለው ነገር ነው። አምጣ እለዋለሁ። የለኝም ይለኛል። አለቅሳለሁ። ነገ እሰጥሃለሁ ይለኛል። አልሄድለትም ካጠገቡ። የማይቀር ሲሆንበት ከኪሱ በፌስታል የተቋጠሩ ሳንቲሞች ያወጣል። አሥር ሳንቲሞች፣ አምስት ሳንቲሞች፣ ስሙኔ ሳንቲሞች፣ ሽልንግ ሳንቲሞች... አሥር አሥር ሳንቲሞቹ ብዙ ጊዜ አዳዲስ ነበሩ ለምን እንደሆነ አላውቅም። ከአሥር ሳንቲሞቹ ውስጥ መርጬ እወስድበታለሁ። አባቴን እንዴት እንደምወደው አስብና መልሼ እወደዋለሁ በዛ ጊዜ።
ልጅ ሆኜ ካባቴ ጋር ነው የምተኛው። ለሊት ለሊት ሁሌ ሽንቴን እሸናበታለሁ። ለሊት ለሊት ሁሌ እየተነጫነጨ ይቀሰቅሰኛል። ስነቃ አልጋው ሽንት ብቻ ሆኖ አገኘዋለሁ። ቆይ ነገ ገና ሳልሸናው ነው የምነቃው እላለሁ። በሚቀጥለውም ቀን ከሸናሁት ወዲያ ነው የምነቃው። ያን ሳስታውሰው “እንዴት አይሰለቸውም?” እላለሁ። እሱ ቻይ ነው። ጭምት እዝጋቤል።
ይኸ ኃይሉ የተባለ Country man ከራሱ ጋር የሚኖር ሰው ነው። በዓለም ፊት የሞተ፤ ዓለምም በሱ ፊት የሞተች። አጠገቤ ሆኖ ሩቅ እንዳለ ይመስለኛል። ጋሼ ኃይሉን ትክ ብለው የተመለከቱት እንደሆነ፡ አምላክ እስቲ ጉዳችሁን ልይ ብሎ በአንድ ጥቁር ኮስማና ሰውዬ አቋም ሆኖ የሚያደርጉትን ሁላ በዝምታ እየታዘበ ያለ ይመስላል። አይ የሱ ሥራ...
*አባ የምሥራቅ በር - ከበውቀቱ ስዩም “ላባቴ” ግጥም ላይ የተወሰደ ሀረግ

እንደምን አላቹህ? ቤተሰቦች🤗
የሰሞኑን የስዕል ስራዎቼን ተጋበዙልኝ!😊🙏
ከዛሬ 14/10/2024 ዓ.ም እስከ 15/10/2024 ዓ.ም ምሽት 4 ሰዓት ደረስ እሚቆይ Free Package ስለምሰጥ ፎቶ በመላክ በነፃ ማሳል ትችላላቹህ!!
ፎቶ ለመላክ 👉@aman116
join and share
@YelbeDrset @YelbeDrset
👨🎨👨🎨👨🎨👨🎨👨🎨👨🎨👨🎨