የዛሬው ጥያቄና መልስ ውድድር አሸናፊ DAEL ናት CONGRA 🏆🏆🏆🏅 ሽልማትሽን በውስጥ መውሰድ ትችያለሽ
በርቺ እሺ❤️❤️❤️😍
በርቺ እሺ❤️❤️❤️😍
=======ከንቱ ፍለጋ=======
የት ትገኝ ... የት ትሁን ሠላም
ልፈልጋት፣
ህዝቤ እኮ ተንከራተተ ሠላም
በሌለበት።
ገንዘቡን ይዞ ወጣ.. .. .. የለም እርካታ፣
ገንዘብ ቁስን"ጂ መች ይሰጣል እፎይታ።
ተጻፈ በሶለን
መስከረም 12/2015 e.c
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
የት ትገኝ ... የት ትሁን ሠላም
ልፈልጋት፣
ህዝቤ እኮ ተንከራተተ ሠላም
በሌለበት።
ገንዘቡን ይዞ ወጣ.. .. .. የለም እርካታ፣
ገንዘብ ቁስን"ጂ መች ይሰጣል እፎይታ።
ተጻፈ በሶለን
መስከረም 12/2015 e.c
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
🕒እስክመጣ ዋናው
ንጉስ እየሾመ የሰው ልጅ ተስማምቶ፣ ተሻሜውም ደግሞ ዙፋኑ ላይ ወጥቶ ፣ ሁሉም ይራሮጣል ይህን ክብር አይቶ፣ ጥላትም ይበዛል ለዚህ ክብር ቀንቶ ፣ ጊዜም ይጨክናል የሰጠውን ነስቶ ፣ ይሻራል ንግስናም ሌላው ተተክቶ ፣
አድሱም ይነግሳል አሮጌው ተትቶ ፣ በዚህ ሁሉ ግን እስክመጣ ዋናው፣
ሹመቱም ተሻሚም ሁሉም ጊዜዊ ነው፣
ቋሚንጉስ የለም ሁሉም ተለዋጭነው፣ እስክመጣ ዋናው ንግስና ፈራሽ ነው ፣
መንግሥቱምዙፋኑም ነበር የሚባልነው
እስክመጣ ዋናው ደግሞየተባለው ፣ ያለና የሚኖር እሱ ክርስቶስ ነው ፣
ዙፋኑም መንግሥቱም ካለበት መጣና፣
በሰማይ በምድር መንግሥቱን አፀና ፣ ድንበር የለሽ ዙፋን ንግስና ተሰጥቶት ፣
ጥላት በዚ ቀንቶ ልገለውም አምሮት ፣
በሙታንም ሰፈር ሊያኖረው ቢመኝም፣
ሞት እንደማይገድለው ምስጢሩን አይውቅም
የሚከተሉትም መስሏቸው ነበረ፣
መሰቀል ላይ ሲሰቀል ሞቶ እንዲሁ የቀረ
ሽቶውን ገዛዝተው ሊቀቡት ሲመጡ ፣
እጅግ ፈርተው ነበር የሞተው ኢየሱስ ሥጋውን ስያጡ፣
በሙታንም ሰፈር ፍለጋ እያሉ ፣
መልዕክት ተገልጠው እንድህም አሉ፣
ኅያውን ከሙታን መከከል ለምን ፈለጋቹ፣
ተነስቷል እዚህ የለም አትፍሩ ስላጣቹ ፣
ለ የምስራቹ እናንተም ምስክሮች ናቹ ፣
በየ ስፍራው ወተው እየተበታተኑ ፣
እውነቱን መስክረው በእምነታቸው ጸኑ፣
እስክመጣ ዋናው ሞት ያሸነፋቸው ፣
ነገስታት የሆኑ አረ ብዙ ናቸው ፣
የት እንደ ነበር መቃብሮቻቸው ፣
ተረሱ የሉም ጊዜ አልፈባቸው ፣
ጊዜ የማይሽረው ተተኪ ተገኝቶ ፣
እንከን የሌለበት ፈፀመኑ ከቶ ፣
ያልተቀበለ ከሰው ልጅ ላይ ሹመት፣
ያልፀደቀ ንግስናው በማንም ዳኝነት፣
ከላይ ከሰማያት ዋና ሆኖ መጣ ፣
ሞትን አሸንፎ ወደ ላይም ወጣ ፣
እሱ ነው ንግሱ ዳግም የሚመጣ ።
ፋሲካ ታከለ
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
ንጉስ እየሾመ የሰው ልጅ ተስማምቶ፣ ተሻሜውም ደግሞ ዙፋኑ ላይ ወጥቶ ፣ ሁሉም ይራሮጣል ይህን ክብር አይቶ፣ ጥላትም ይበዛል ለዚህ ክብር ቀንቶ ፣ ጊዜም ይጨክናል የሰጠውን ነስቶ ፣ ይሻራል ንግስናም ሌላው ተተክቶ ፣
አድሱም ይነግሳል አሮጌው ተትቶ ፣ በዚህ ሁሉ ግን እስክመጣ ዋናው፣
ሹመቱም ተሻሚም ሁሉም ጊዜዊ ነው፣
ቋሚንጉስ የለም ሁሉም ተለዋጭነው፣ እስክመጣ ዋናው ንግስና ፈራሽ ነው ፣
መንግሥቱምዙፋኑም ነበር የሚባልነው
እስክመጣ ዋናው ደግሞየተባለው ፣ ያለና የሚኖር እሱ ክርስቶስ ነው ፣
ዙፋኑም መንግሥቱም ካለበት መጣና፣
በሰማይ በምድር መንግሥቱን አፀና ፣ ድንበር የለሽ ዙፋን ንግስና ተሰጥቶት ፣
ጥላት በዚ ቀንቶ ልገለውም አምሮት ፣
በሙታንም ሰፈር ሊያኖረው ቢመኝም፣
ሞት እንደማይገድለው ምስጢሩን አይውቅም
የሚከተሉትም መስሏቸው ነበረ፣
መሰቀል ላይ ሲሰቀል ሞቶ እንዲሁ የቀረ
ሽቶውን ገዛዝተው ሊቀቡት ሲመጡ ፣
እጅግ ፈርተው ነበር የሞተው ኢየሱስ ሥጋውን ስያጡ፣
በሙታንም ሰፈር ፍለጋ እያሉ ፣
መልዕክት ተገልጠው እንድህም አሉ፣
ኅያውን ከሙታን መከከል ለምን ፈለጋቹ፣
ተነስቷል እዚህ የለም አትፍሩ ስላጣቹ ፣
ለ የምስራቹ እናንተም ምስክሮች ናቹ ፣
በየ ስፍራው ወተው እየተበታተኑ ፣
እውነቱን መስክረው በእምነታቸው ጸኑ፣
እስክመጣ ዋናው ሞት ያሸነፋቸው ፣
ነገስታት የሆኑ አረ ብዙ ናቸው ፣
የት እንደ ነበር መቃብሮቻቸው ፣
ተረሱ የሉም ጊዜ አልፈባቸው ፣
ጊዜ የማይሽረው ተተኪ ተገኝቶ ፣
እንከን የሌለበት ፈፀመኑ ከቶ ፣
ያልተቀበለ ከሰው ልጅ ላይ ሹመት፣
ያልፀደቀ ንግስናው በማንም ዳኝነት፣
ከላይ ከሰማያት ዋና ሆኖ መጣ ፣
ሞትን አሸንፎ ወደ ላይም ወጣ ፣
እሱ ነው ንግሱ ዳግም የሚመጣ ።
ፋሲካ ታከለ
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
የሰነፎች ቁጣ አያስፈራኝ፣
ሁሉን ያሸነፈ ቃል አለኝ፣
የልቡን ስርዓት ተምሬ፣
አልሞትም ለጌታ ዘምሬ።
✍ዝማሪ አስፋው
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
ሁሉን ያሸነፈ ቃል አለኝ፣
የልቡን ስርዓት ተምሬ፣
አልሞትም ለጌታ ዘምሬ።
✍ዝማሪ አስፋው
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
መቆየት
ተወስጄ በሚታየው
"አገልግሎት" በተባለው
መርጋት ተስኖኝ
መቆም አድክሞኝ
ማድመጥ አልቆብኝ
መጠበቅ ጠፍቶኝ
ተራገብኩኝ..
በቻዬን አውርቼ
አንተንም ዘንግቼ
መማር አቁሜ
ተረጋግቼ
አደግሁ ተጣምሜ
ከእውነት ጠፍቼ
የሚያስፈልገውን ሳላስቀድም
አቅቶኝ ማለት "ዝም"
ባከንኩኝ ....
ጥቂቷን አጣሁ
ከእግርህ ስር ጠፋሁ
በልጦብኝ መታየት
አልቻልኩም መቆየት።
#በእምኒ
ጥቅምት 2013
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
ተወስጄ በሚታየው
"አገልግሎት" በተባለው
መርጋት ተስኖኝ
መቆም አድክሞኝ
ማድመጥ አልቆብኝ
መጠበቅ ጠፍቶኝ
ተራገብኩኝ..
በቻዬን አውርቼ
አንተንም ዘንግቼ
መማር አቁሜ
ተረጋግቼ
አደግሁ ተጣምሜ
ከእውነት ጠፍቼ
የሚያስፈልገውን ሳላስቀድም
አቅቶኝ ማለት "ዝም"
ባከንኩኝ ....
ጥቂቷን አጣሁ
ከእግርህ ስር ጠፋሁ
በልጦብኝ መታየት
አልቻልኩም መቆየት።
#በእምኒ
ጥቅምት 2013
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
አፈ ታሪክ......
የ93 አመት አዛውንት ናቸው. ድንገት አሟቸው ይወርቃሉ
Hospital ተወስዶ 24 ስአት oxygen ይሰጠዋል
ተሽሎት ወደ ቤት እንድሄድና የህክምናው ወጪ 5000 dollar መሆኑን ዶክተሩ ይነግራቸዋል
አዛውንቱም ስቅስቅ ብሎ እንባውን ጠብ ጠብ ስያረግ ፣ ዶክተሩ ለብር ከሆነ አታልቅስ ሌላ ግዜ ብሆንም ይከፍላሉ አላቸው
ሽማግለውም : ልጄ እኔ የህክምናው ወጪ መክፈል እችላለሁ ግን ልጄ ሆይ ፣ እናንተ ለ24 ስአት አየር 5000 dollar ከጠየቃችሁኝ 93 አመት ሙሉ በነፃ ለተነፈስኩ አየር ፈጣር ክፈል ብለኝ ስንት የፈጠረው እዳ አለብኝ ?
ዛሬ የእግዚአብሔር እዳውን ብጠይቀን መልሳችን ምን ይሁን ???
እንዲሁ ለሰጠን አየር እንኳን ተመስገን እንበለው😓😥😭
✍source : unknown
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
የ93 አመት አዛውንት ናቸው. ድንገት አሟቸው ይወርቃሉ
Hospital ተወስዶ 24 ስአት oxygen ይሰጠዋል
ተሽሎት ወደ ቤት እንድሄድና የህክምናው ወጪ 5000 dollar መሆኑን ዶክተሩ ይነግራቸዋል
አዛውንቱም ስቅስቅ ብሎ እንባውን ጠብ ጠብ ስያረግ ፣ ዶክተሩ ለብር ከሆነ አታልቅስ ሌላ ግዜ ብሆንም ይከፍላሉ አላቸው
ሽማግለውም : ልጄ እኔ የህክምናው ወጪ መክፈል እችላለሁ ግን ልጄ ሆይ ፣ እናንተ ለ24 ስአት አየር 5000 dollar ከጠየቃችሁኝ 93 አመት ሙሉ በነፃ ለተነፈስኩ አየር ፈጣር ክፈል ብለኝ ስንት የፈጠረው እዳ አለብኝ ?
ዛሬ የእግዚአብሔር እዳውን ብጠይቀን መልሳችን ምን ይሁን ???
እንዲሁ ለሰጠን አየር እንኳን ተመስገን እንበለው😓😥😭
✍source : unknown
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
#በቆሎና_ስንዴ..
ነጋሪ ብታጣ ማየትም ቢሳንህ፤
ቢመስልህ ትክክል ባይፈጥን ቅጣትህ፤
ቢስማማ ለጊዜው ቀኑ ቢታገስህ፤
አይቀርም በእርሻህ ማፍራቱ የዘርህ፤
ተነቅንቆ በዝቶ ሞልቶ በመስፈሪያህ።
ምህረት ሌላ ነገር ህግን አይፃረን፤
ሽፋን እንዳይመስልህ የ'ሱ ታጋሽ መሆን፤
አትሞኝ..ገምግም ተክልህን፤
አጥራ አስተካክል መሄጃ መንገድህን፤
ቀን ቆጥሮ ሲመጣ የለህም መሸሻ
ስንዴ አይታጨድም ከበቆሎ እርሻ።
#በእምኒ
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
ነጋሪ ብታጣ ማየትም ቢሳንህ፤
ቢመስልህ ትክክል ባይፈጥን ቅጣትህ፤
ቢስማማ ለጊዜው ቀኑ ቢታገስህ፤
አይቀርም በእርሻህ ማፍራቱ የዘርህ፤
ተነቅንቆ በዝቶ ሞልቶ በመስፈሪያህ።
ምህረት ሌላ ነገር ህግን አይፃረን፤
ሽፋን እንዳይመስልህ የ'ሱ ታጋሽ መሆን፤
አትሞኝ..ገምግም ተክልህን፤
አጥራ አስተካክል መሄጃ መንገድህን፤
ቀን ቆጥሮ ሲመጣ የለህም መሸሻ
ስንዴ አይታጨድም ከበቆሎ እርሻ።
#በእምኒ
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
ፍልስፍና
ከዓለም እወቀት የረቀቀ
ከአህምሮአችን የጠለቀ
ሌላ ኑሮ ሌላ እውቀት
የዘለለ ከወረቀት
ሚተገበር ከቃል አልፎ
ማይታለፍ ጥቅስ ቀጥፎ
ለካ አለ ጥበብ አምላካዊ
መልኩ ሁሉ ሰማያዊ
ለካ አለ ሌላ መረብ
ሚዘረጋ ሁሉ ለዓለም
ለካ አለ ሌላ ኑሮ
የዘለለ ከእንጀራ
ያለፈ ከጉሮሮ
የትዉልድን እንባ ሚያብስ
የሚያሳርፍ ከእሮሮ
የሊቅ ጆሮ ያልሰማው
የነገስታት ዓይን ያላየው
ሚቀዳ ከማይታየው
የሚፈስ ለሚታየው
ከስሌት ቀመር የወጣ
ከካልኩሌሽን ያለፈ
ካምላክ የተጠለፈ
መንፈሱ አንድ የሆነ
ሲወርድ የተከፋፈለ
ከምንም ጋር ያልተዳበለ
ያልቀየጠ ያልቀላቀለ
እግዚአብሔራዊ ፍልስፍና
ከብዶ የሚያልፍ ያልቀለለ
✍ሳምራዊት ታለግን
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
ከዓለም እወቀት የረቀቀ
ከአህምሮአችን የጠለቀ
ሌላ ኑሮ ሌላ እውቀት
የዘለለ ከወረቀት
ሚተገበር ከቃል አልፎ
ማይታለፍ ጥቅስ ቀጥፎ
ለካ አለ ጥበብ አምላካዊ
መልኩ ሁሉ ሰማያዊ
ለካ አለ ሌላ መረብ
ሚዘረጋ ሁሉ ለዓለም
ለካ አለ ሌላ ኑሮ
የዘለለ ከእንጀራ
ያለፈ ከጉሮሮ
የትዉልድን እንባ ሚያብስ
የሚያሳርፍ ከእሮሮ
የሊቅ ጆሮ ያልሰማው
የነገስታት ዓይን ያላየው
ሚቀዳ ከማይታየው
የሚፈስ ለሚታየው
ከስሌት ቀመር የወጣ
ከካልኩሌሽን ያለፈ
ካምላክ የተጠለፈ
መንፈሱ አንድ የሆነ
ሲወርድ የተከፋፈለ
ከምንም ጋር ያልተዳበለ
ያልቀየጠ ያልቀላቀለ
እግዚአብሔራዊ ፍልስፍና
ከብዶ የሚያልፍ ያልቀለለ
✍ሳምራዊት ታለግን
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
#ሰው_ጠፍቶ_ከመንገድ
ከመንደር የሰፈር:አንድነት ማህበር
አንተ ትብስ ተብሎ:ወገን ሲተባበር
ሲፈጥር አንድ ክንድ:አንድ ሆኖ በአንድ ላይ
የአንድነት መንፈስ:ገኖ ገዝፎ ሲታይ
ሁሉን ሰው ለውጦ:በልብ አስተሳስሮ
ጠላትን ደምስሶ:የቀረውን አስሮ
በዚህ ቅን ምልልስ:ከፊት እየሄደ
ባላሰበው መንገድ:ጠላቱ ባሰረው:ገመድ ተገመደ
ያከማቸውን ሀብት:የዘራውን ፍሬ
ተበዝብዞ አልቆ:ተሟጦ ተወስዶ:በጠላቱ ወሬ
የነበረው ውበት:ሀይል ደም ግባቱ
ክፉ ዘር ወድቆበት:እነደ ጢስ በነነ:አለቀ በፊቱ
ያሻውን ወሰደ:የቀረውን ትቶ:ያ ክፉ ጠላቱ
አሁንማ ወድቆ:መስል የቆመ ሠው
የገዛ ራሱ:ማንነቱ ጠፍቶት:ሀገሩን የሸጠው
ጠመንጃውን ታጥቆ:ቀዬ መንደሬውን የሚያተራምሰው
የሰው ደም ጠጥቶ:አካሉን ቆራርጦ:ጥሙን እያረካ
በጎሳ በሀይማኖት:ወገኑን ከፋፍሎ:በዘር ፓለቲካ
ወደ ማንነቱ:ሰውን የሚመልስ:ሰው ጠፍቶ በሀገሩ
ህሊና ተጨንቆ:ተናጋሪው ቆሞ:በየጉራንጉሩ
ፈልጉት ይህን ሰው:ብዙ ርቆ ጠፍቷል
ወደ ራሱ ይምጣ:በፀሎት አስቡት:ከሞቱ ይነቃል
ሴት እህቴን ወስዶ: አበባዋን ቀጥፎ
ሳንጃ ስለት ወስዶ:ማንነቷን ገፎ
ለጊዜያዊ ስሜት:ነገዋን ቀሞቶ
ጠቅሞ እንኳን ላይጠቅም :በቁሙ ሞት ሞቶ
ጠፍቶ እያጠፋ:ወድቆ እየቆመ
እንደ ክረምቱ ውርጭ:በሰውነት ገብቶ ልብ እያሳመመ
እረ የሰው ያለህ:ሰው ጠፍቶ በሀገሩ
በየአደባባዩ:ጩከትሚሰማ:ፍለጋ ቢዞሩ
ሰው ጠፍቷል: ሙሉ ሰው:ሰውን አትፈልጉ
ሁሉም ተበታትኗል:ጥሎ ርቆ ሄዳል:ለራሳቹ ስጉ
ሀሳብን ሰብስበህ:ፍሬውን ስታገኝ
አንዴ ቆይ እዚህ ጋር:ሀሳቤን ያዝልኝ
👇👇👇👇👇👇👇👇
.
..
...
ወዳጄ ይህን ስማኝ:በቃ አንዴ ስማኝ
ልብህን አዘጋች:ሀሳቤን ደግፈኝ
ሰው ጠፋ በሀገሩ:እያልክ ከቶ አትስጋ
አንተው#ሰው_ሁንና:የጠፋውን እንቁ:ለመፈለግ ትጋ
👉ክብር_ሰፈር
ታሜ 🔥🔥
#ሀዋሳ
01/11/2014
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
ከመንደር የሰፈር:አንድነት ማህበር
አንተ ትብስ ተብሎ:ወገን ሲተባበር
ሲፈጥር አንድ ክንድ:አንድ ሆኖ በአንድ ላይ
የአንድነት መንፈስ:ገኖ ገዝፎ ሲታይ
ሁሉን ሰው ለውጦ:በልብ አስተሳስሮ
ጠላትን ደምስሶ:የቀረውን አስሮ
በዚህ ቅን ምልልስ:ከፊት እየሄደ
ባላሰበው መንገድ:ጠላቱ ባሰረው:ገመድ ተገመደ
ያከማቸውን ሀብት:የዘራውን ፍሬ
ተበዝብዞ አልቆ:ተሟጦ ተወስዶ:በጠላቱ ወሬ
የነበረው ውበት:ሀይል ደም ግባቱ
ክፉ ዘር ወድቆበት:እነደ ጢስ በነነ:አለቀ በፊቱ
ያሻውን ወሰደ:የቀረውን ትቶ:ያ ክፉ ጠላቱ
አሁንማ ወድቆ:መስል የቆመ ሠው
የገዛ ራሱ:ማንነቱ ጠፍቶት:ሀገሩን የሸጠው
ጠመንጃውን ታጥቆ:ቀዬ መንደሬውን የሚያተራምሰው
የሰው ደም ጠጥቶ:አካሉን ቆራርጦ:ጥሙን እያረካ
በጎሳ በሀይማኖት:ወገኑን ከፋፍሎ:በዘር ፓለቲካ
ወደ ማንነቱ:ሰውን የሚመልስ:ሰው ጠፍቶ በሀገሩ
ህሊና ተጨንቆ:ተናጋሪው ቆሞ:በየጉራንጉሩ
ፈልጉት ይህን ሰው:ብዙ ርቆ ጠፍቷል
ወደ ራሱ ይምጣ:በፀሎት አስቡት:ከሞቱ ይነቃል
ሴት እህቴን ወስዶ: አበባዋን ቀጥፎ
ሳንጃ ስለት ወስዶ:ማንነቷን ገፎ
ለጊዜያዊ ስሜት:ነገዋን ቀሞቶ
ጠቅሞ እንኳን ላይጠቅም :በቁሙ ሞት ሞቶ
ጠፍቶ እያጠፋ:ወድቆ እየቆመ
እንደ ክረምቱ ውርጭ:በሰውነት ገብቶ ልብ እያሳመመ
እረ የሰው ያለህ:ሰው ጠፍቶ በሀገሩ
በየአደባባዩ:ጩከትሚሰማ:ፍለጋ ቢዞሩ
ሰው ጠፍቷል: ሙሉ ሰው:ሰውን አትፈልጉ
ሁሉም ተበታትኗል:ጥሎ ርቆ ሄዳል:ለራሳቹ ስጉ
ሀሳብን ሰብስበህ:ፍሬውን ስታገኝ
አንዴ ቆይ እዚህ ጋር:ሀሳቤን ያዝልኝ
👇👇👇👇👇👇👇👇
.
..
...
ወዳጄ ይህን ስማኝ:በቃ አንዴ ስማኝ
ልብህን አዘጋች:ሀሳቤን ደግፈኝ
ሰው ጠፋ በሀገሩ:እያልክ ከቶ አትስጋ
አንተው#ሰው_ሁንና:የጠፋውን እንቁ:ለመፈለግ ትጋ
👉ክብር_ሰፈር
ታሜ 🔥🔥
#ሀዋሳ
01/11/2014
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
Forwarded from Tsedenia
YouTube
ተፈጸመ
መንፈሳዊ ግጥሞች
ነገ በሕይወትህ ድንቅ አደርጋለሁ
ብቻ አንተ ተቀደስ እኔ ሰራለሁ
ብሎ ጌታ አሰበኝ ቃሉን አክብሮ
ምርኮዬን መልሷል ስሜን ቀይሮ
አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም
በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል
ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል
ጌታውን ተማምኖ የሚጠባበቅ
ኃይሉ ታደሰ እንጂ ዘላለም አይወድቅ
እግዚአብሔር ይሄ ነው ተስፋ ያረኩት
ጸሎቴን መልሷል ኑ ስሙን ባርኩት
አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም
በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል
ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል
በለስን ጠብቆ ፍሬን የበላ
ከጌታው ጋር ሆኖ ያልቀረ ኋላ
አከናውኖልኛል ምኔን ልክፈለው
የሚል በዕልልታ ጌታን ያክብረው
አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም
በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል
ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል
ሥጋዬን በጥርሴ እነክሳለሁኝ
ቢገድለኝም እርሱን እጠብቃለሁኝ
ብሎ ለጠበቀው ጌታን በእምነት
ሁለት እጥፍ መጣ የኢዮብ በረከት
አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም
በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል
ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል
እረድኤቴና መድሃኒቴ
አከናውኖልኛል ኢየሱስ አባቴ
በፊቱ ዘላለሁ እንደ እንቦሳ
ስላራቀው ከእኔ ያንን አበሳ
አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም
በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል
ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል
ልጄ ልብህን ስጠኝ ወደ እኔ ና
እሰራለሁ ብሎ አባበለና
እኔም ከአምላኬ ጋር ወዲያው ስታረቅ
ጸሎቴን መለሰው ሥሙ ይባረክ
አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም
በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል
ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል (2x)
ገራም መዝሙር ነው 🥰
ዘማሪ ቃልአብ ተክለ። አሁን
ከተለቀቀው መዝሙር የተወሰደ።
ቃልአብ ጌታ ይባርክህ
ጸጋው ይደግፍህ።
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
ብቻ አንተ ተቀደስ እኔ ሰራለሁ
ብሎ ጌታ አሰበኝ ቃሉን አክብሮ
ምርኮዬን መልሷል ስሜን ቀይሮ
አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም
በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል
ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል
ጌታውን ተማምኖ የሚጠባበቅ
ኃይሉ ታደሰ እንጂ ዘላለም አይወድቅ
እግዚአብሔር ይሄ ነው ተስፋ ያረኩት
ጸሎቴን መልሷል ኑ ስሙን ባርኩት
አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም
በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል
ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል
በለስን ጠብቆ ፍሬን የበላ
ከጌታው ጋር ሆኖ ያልቀረ ኋላ
አከናውኖልኛል ምኔን ልክፈለው
የሚል በዕልልታ ጌታን ያክብረው
አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም
በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል
ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል
ሥጋዬን በጥርሴ እነክሳለሁኝ
ቢገድለኝም እርሱን እጠብቃለሁኝ
ብሎ ለጠበቀው ጌታን በእምነት
ሁለት እጥፍ መጣ የኢዮብ በረከት
አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም
በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል
ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል
እረድኤቴና መድሃኒቴ
አከናውኖልኛል ኢየሱስ አባቴ
በፊቱ ዘላለሁ እንደ እንቦሳ
ስላራቀው ከእኔ ያንን አበሳ
አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም
በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል
ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል
ልጄ ልብህን ስጠኝ ወደ እኔ ና
እሰራለሁ ብሎ አባበለና
እኔም ከአምላኬ ጋር ወዲያው ስታረቅ
ጸሎቴን መለሰው ሥሙ ይባረክ
አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም
በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል
ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል (2x)
ገራም መዝሙር ነው 🥰
ዘማሪ ቃልአብ ተክለ። አሁን
ከተለቀቀው መዝሙር የተወሰደ።
ቃልአብ ጌታ ይባርክህ
ጸጋው ይደግፍህ።
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
ወደህ ተጨነቅህ
ያኔበጎልጎታ.....
በጅራፍ ግርፋት በደም ተጨማልቀህ
ስድብን ስትቀበል እየተተፋብህ
ንፁህ የሆንክ አንተ ስቃይህ ጨምሮ
በርባን ሲፈታብህ የነበረው ታስሮ
ሄሮድስ ከጲላጦስ እየተማከሩ
ለህዝቡ ጥያቄ ምላሽን ሊያኖሩ
አንዱ ንጉሥ ሲልህ ካባውን አልብሶ
ደግሞ ሲያስወግርህ ጭካኔን ተላብሶ
ሌላው ንፁህ እንደሆንክ በውል ተመልክቶ
እጁን በመታጠብ እራሱን አውጥቶ
ፍርዱን ለህዝብ ሲተው...
ህዝቡም በአንድ ድምፅ ይሰቀል እያለ
ልታድነው መጥተህ ሲፈርድብህ ሳለ
ጴጥሮስም ሲክድህ በገረድ ፊት ሳይቀር
ፍቅር የታመምከው ለብቻህን ነበር።
አንተ ስትሰቃይ መልክህ ተበላሽቶ
ፊትህም ገርጥቶ ደም ግባትህ ጠፍቶ
ደዌን ስትቀበል ፍቅር ስትታመም
ራስክን አድን እንጂ እኔን ያለህ የለም።
ወደህ ተጨነቅህ አፍህን ሳትከፍት
አፍቅረህ ተነዳህ በሸላቾችህ ፊት
ፍቅር ተሰቃየህ ፍቅር ሀጥያት ሆንህ
በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰድህ
ይሄ ሁሉ ሲሆን በመስቀሉ ሰፈር
ውዴ የታመምከው ለብቻህን ነበር።
አባትህ በደዌ ሊያደቅህ ፈቀደ
ብዙ ሊያተርፍብህ ሊዘራህ ወደደ
ፃድቅ ሆነህ ሳለ ሀጥያት ተሸክመህ
ስለታላቅ ፍቅርህ ነፍስህን አኖርህ
ከአመፀኛው ጋር አንተም ተቆጠርህ
ዳሩ ግን መልሰህ ስለእርሱ ማለድህ።
ውዴ ወዳጄ ሆይ
አንተ ስትሰቃይ መልክህ ተበላሽቶ
ፊትህም ገርጥቶ ደምግባትህ ጠፍቶ
ወደህ ስትጨነቅ አፍህን ሳትከፍት
አፍቅረህ ስትሄድ በሸላቾችህ ፊት
ሞቴን ስትሞተው በሞትህ ስትገለኝ
እንኳንም ተጨነክ ነው እንጂ ያስባለኝ
ለምንና እንዴት ፈፅሞ አላልኩም
ባትሞት ህይወትን ጨርሼ አላውቀውም።
📝by beti fares
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
ያኔበጎልጎታ.....
በጅራፍ ግርፋት በደም ተጨማልቀህ
ስድብን ስትቀበል እየተተፋብህ
ንፁህ የሆንክ አንተ ስቃይህ ጨምሮ
በርባን ሲፈታብህ የነበረው ታስሮ
ሄሮድስ ከጲላጦስ እየተማከሩ
ለህዝቡ ጥያቄ ምላሽን ሊያኖሩ
አንዱ ንጉሥ ሲልህ ካባውን አልብሶ
ደግሞ ሲያስወግርህ ጭካኔን ተላብሶ
ሌላው ንፁህ እንደሆንክ በውል ተመልክቶ
እጁን በመታጠብ እራሱን አውጥቶ
ፍርዱን ለህዝብ ሲተው...
ህዝቡም በአንድ ድምፅ ይሰቀል እያለ
ልታድነው መጥተህ ሲፈርድብህ ሳለ
ጴጥሮስም ሲክድህ በገረድ ፊት ሳይቀር
ፍቅር የታመምከው ለብቻህን ነበር።
አንተ ስትሰቃይ መልክህ ተበላሽቶ
ፊትህም ገርጥቶ ደም ግባትህ ጠፍቶ
ደዌን ስትቀበል ፍቅር ስትታመም
ራስክን አድን እንጂ እኔን ያለህ የለም።
ወደህ ተጨነቅህ አፍህን ሳትከፍት
አፍቅረህ ተነዳህ በሸላቾችህ ፊት
ፍቅር ተሰቃየህ ፍቅር ሀጥያት ሆንህ
በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰድህ
ይሄ ሁሉ ሲሆን በመስቀሉ ሰፈር
ውዴ የታመምከው ለብቻህን ነበር።
አባትህ በደዌ ሊያደቅህ ፈቀደ
ብዙ ሊያተርፍብህ ሊዘራህ ወደደ
ፃድቅ ሆነህ ሳለ ሀጥያት ተሸክመህ
ስለታላቅ ፍቅርህ ነፍስህን አኖርህ
ከአመፀኛው ጋር አንተም ተቆጠርህ
ዳሩ ግን መልሰህ ስለእርሱ ማለድህ።
ውዴ ወዳጄ ሆይ
አንተ ስትሰቃይ መልክህ ተበላሽቶ
ፊትህም ገርጥቶ ደምግባትህ ጠፍቶ
ወደህ ስትጨነቅ አፍህን ሳትከፍት
አፍቅረህ ስትሄድ በሸላቾችህ ፊት
ሞቴን ስትሞተው በሞትህ ስትገለኝ
እንኳንም ተጨነክ ነው እንጂ ያስባለኝ
ለምንና እንዴት ፈፅሞ አላልኩም
ባትሞት ህይወትን ጨርሼ አላውቀውም።
📝by beti fares
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
የክርስቲያን ግጭት
የክርስቲያን ግጭት ፥ሊሆን የሚገባው
ብዬ ሳሰላስል ፥በሃሳብ የከተመው
የግጭት መንስኤ፥
ምክንያት ይሄ ነው ፦
የወንድሜን እግር ላጥበው ፥
ላብሰው ልጠርገው
ዝቅ ስል ፥ ወንድሜ እንዲሁ እንደኔ
ስያጎነብስ ልያነሳ ፥ከእግሬ ኩነኔ
ጭንቅላቴ ከግንባሩ
እጄም ከእግሩ
ስጋጭ ብቻ ነው
መውደድ ገላጭ ግጭት
በፍቅር የሚሠራ እምነት
የፈጣሪም ደስታ ሙላት
እውን የሚሆነው
ትእዛዝም ሁሉ የሚጠቀለለው።
✍ፈቃዱ ተመስገን
ከአርባምንጭ
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
የክርስቲያን ግጭት ፥ሊሆን የሚገባው
ብዬ ሳሰላስል ፥በሃሳብ የከተመው
የግጭት መንስኤ፥
ምክንያት ይሄ ነው ፦
የወንድሜን እግር ላጥበው ፥
ላብሰው ልጠርገው
ዝቅ ስል ፥ ወንድሜ እንዲሁ እንደኔ
ስያጎነብስ ልያነሳ ፥ከእግሬ ኩነኔ
ጭንቅላቴ ከግንባሩ
እጄም ከእግሩ
ስጋጭ ብቻ ነው
መውደድ ገላጭ ግጭት
በፍቅር የሚሠራ እምነት
የፈጣሪም ደስታ ሙላት
እውን የሚሆነው
ትእዛዝም ሁሉ የሚጠቀለለው።
✍ፈቃዱ ተመስገን
ከአርባምንጭ
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
👉 መቃብር ቆፈሩ
በሸለቆው መኃል የተቀረጹ ፣
በሙያተኞች እጅ ደግሞ የተነጹ፣
በጥበብ ተክነው የተለሰኑትን ፣
ልጎበኙ ሄደው መቃብሮችን ፣
መቆፈር ጀመሩ ባዶ ድንጋዮችን፣
ድካማቸው ሁሉ ቀረ በመና ፣
ውስጡ ስከፍት ሆኖባቸው ኦና፣
ሚዛን ከደፋ ውጫዊው ውበት፣
ካሸነፈውማ ውስጣዊን ማንነት፣
አንድ ቀን ስመጣ አደጋው ይከፋል ፣
አብረቅራቂ ሁሉ መቼ ወርቅ ይሆናል ።
👉".....በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ ወዮላችሁ ። " ማቴ 23 -27
✤ ፋሲካ ታከለ
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
በሸለቆው መኃል የተቀረጹ ፣
በሙያተኞች እጅ ደግሞ የተነጹ፣
በጥበብ ተክነው የተለሰኑትን ፣
ልጎበኙ ሄደው መቃብሮችን ፣
መቆፈር ጀመሩ ባዶ ድንጋዮችን፣
ድካማቸው ሁሉ ቀረ በመና ፣
ውስጡ ስከፍት ሆኖባቸው ኦና፣
ሚዛን ከደፋ ውጫዊው ውበት፣
ካሸነፈውማ ውስጣዊን ማንነት፣
አንድ ቀን ስመጣ አደጋው ይከፋል ፣
አብረቅራቂ ሁሉ መቼ ወርቅ ይሆናል ።
👉".....በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ ወዮላችሁ ። " ማቴ 23 -27
✤ ፋሲካ ታከለ
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber
ምንም ላድርግ ብቻ ግን ብቻዬን አልሁን
በስኬቴም ቢሆን በውድቀቴም እርሱ መኖሩን እርግጠኛ ልሁን እንጂ አይገደኝም🤷♀
ብ....ቻ እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ይሁን!
✍ቱሪስት
@Ye_Getamian_Mahiber
በስኬቴም ቢሆን በውድቀቴም እርሱ መኖሩን እርግጠኛ ልሁን እንጂ አይገደኝም🤷♀
ብ....ቻ እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ይሁን!
✍ቱሪስት
@Ye_Getamian_Mahiber