የገጣሚያን ማኅበር
19.1K subscribers
244 photos
13 videos
11 files
512 links
እዚህ ማኅበር ውስጥ የሚካተቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች፦
👉መንፈሳዊ ግጥም
፦ስለ ሀገር ፦ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ፦ስለ ወንጌል ፦ስለቤተክርስቲያን👉መነባነብ
👉ግጥማዊ ትረካ
ይቀላቀሉን
Channel👉 @Ye_Getamian_Mahiber
Group👉 @yegetamianmahiber
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA
Download Telegram
በእግዚአብሔር ታምናላችሁ?
ሁሉም ነገር ለበጎ ነው

ያልፋል እሺ🥹
አዉጣለት አላወጣሁለትም

መኖር በተለምዶ ምህረት ተለማምዶ
አንተዉ በፈጠርከዉ ሰዉ እራሱን ወዶ
ጌትነትህ ክዶ አዳኝ እንደሆንከዉ
ሌላዉ ፍለጋ ይባዝናል ይህ ሰዉ


አንተ በሰራኸዉ ሌላዉን ያልቃል
አንተ እደፈጠርከዉ ፍፁም እረስቶታል
የሰጠኸዉ ሳለህ አንተ ፍፁም ሰላም
አንተኑ እረስቶ ስንቱስ ይባዝናል።

እየሡስ ጌታ ነዉ ብለን ስንነግረዉ
እና እኔ ምን አልኩ ይለኛል ይሔ ሰዉ
አንተ በፈጠርከዉ ፍጡር እየሾመ
በቀንና ጊዜ እያሽሞነሞነ
ዛሬ እንትናነዉ ይለኛል በድፍረት
ቀኑ እንደዚነዉ እሡም ማነግስበት
ይለኛል ይሔ ሰዉ እንደዚ ነዉ ቀኑ
ሠዉ እየሡስ ከሌለዉ አወይ መባዘኑ።

         እኔ ግን የሱሴ አንተኑ አለኘኝ
ቀን የማይለውጥህ መታመኛ የሆንከኝ
በእረፍት በሰላምህ ህይወቴን የሞላህ
   እርካታ የሆንከኝ የህወቴ ከለላ።

ዮናስ እድሉ
“እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።”
  — ሮሜ 8፥28
😊😊አጭር ታሪክ

ከብዙ ረጅም ጊዜ ብኃላ ዛሬ ከምወዳት
እናቴ ጋር ሰፊ ጊዜ አሳልፌያለሁ።አጅግ
በጣም ደስ የሚልና የምማርክ ጊዜ
ነበረኝ እናቶች ፍቅር ናቸው የቤተሰብ
ድምቀትና የማጣፈጫ ቅመም ናቸው
በሚገባ ታውቁታላችሁ።እናት ምስጢር
ትሰማለች፤ትደብቃለች።በወድቀታችን
ራሱ ትኮራብናለች።ልጅ እያለሁ ብዙ
ነገር አብረን ሰርተናል።የኔ ጀግና ነች።
ሁሉም ነገራችን በእሷ ይሸፈናል።
ያጠፋነው ጥፋታችን፤የልጅነታችን ቆሻሻ
አለማወቅ ያመጣው ቅዤታችን ሁሉ
በእርሷ ይደበቅና መልካምነታችን
ያልሰራነው ጽድቃችን ሁሉ ወደ አባታችን
ያልፊና ሞገስ እናገኛለን።ልጆች እንባላለን።#አስታውሱ....

የማወራው ነገር ስለ እናት ብቻ አይደለም..ወደ ሰማዩ አባታችን በልጅነት
ስልጣን መግባት የቻልነው ያሰራነው ኃጢአት፣በደል፣ቆሻሻ፣ዕድፍ... ሀሉ በልጁ በክርስቶስ ተሸፍኖ ነው።ክርስቶስ ሁሉንም በራሱ ከጨረሰ በኃላ ነው
ወደ ሰማዩ አባታችን የገባነው። ክርስቶስ በመካከላችን ባይኖር ኖሮ ከአባታችን ጋር ባልተገናኘን ነበረ።ኃጢአት ሸፍኖ ለፍርድ የተሰያዳን ነበረ.. አያችሁ... እናት ጥፋታችንን በራሷ ጥበብ ባታሸፍን ኖሮ
የሚመጣብን የአባታችን ቁጣና ግርፋት?
ይሄ ነው የሆነው በእኛ በእግዚአብሔር
መካከል ልጁ ክርሰቶስ ሁሉንም በደሙ
ሸፍኖ መካከላችን ሆኖ ነው ከቁጣው
ያመለጥነው።

እናም ከእናቴ ጋር አንዳንድ ነገሮችን ስናወጋ ነበረ የልጅነት ታሪኬን። በጣም
ሞኝ እንደነበርኩና አስቸጋሪ ባህሪ
እንዳለኝ።ከዛም አባቴ ሁለም እንደሚመታኝና ሁለም እንደምቀጣኝ...
አንዳንዴ እኮ ደካሞች ነን ኃጢአት ይፈትነናል ቅጣት ይበዛብናል ነገር ግን ወድቀን እንዳንጠፋ ልጁ ክርስቶስ
በአብና በእኛ መካከል ያለ አስታራቂያችን
ነው ክብር ለኢየሱስ ይሁን❤️❤️


Solen
ነሀሴ 2/2016 E.C
ወ.ሶ


Please subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA
አንቃኝ

በስተ መጨረሻዉ በአለቀዉ ሰአት
ሙሽራዉ ሊመጣ በተቃረበበት
በባከነዉ ሰአት  በሚጠፋዉ አለም
ለሀሳብህ ሚኖር ከቶ አንድም የለም

ሁሉም እራስ ወዳድ አንተን የማይፈራ
ቃልህንም አዉቆ ለሰዉ የማይራራ  
ይሮጣል ለማግኘት  የአለሙን ነገር
በስምህ ነግዶ እራሱን ሊያከብር

ይባዝናል ይሕ ሰዉ እርካታን ፍለጋ
በገንዘቡ ብዛት ልቡን ሊያረጋጋ
ይሮጣል ይሔ ሰዉ ይዞራል ሁሉምጋ 
ገንዘብ ቢሰበሰብ ላያደርስ አንተጋ
ይባዝናል ይህ ሰዉ እረፍትን ፍለጋ ።

ታድያ አምላኬ ሆይ እንድነቃ እርዳኝ
በሰተ መጨረሻ ዘይቴ እንዳያልቅብኝ
በቆሸሸ አለም ነዉር በሞላባት
ተቀድሼ ልኑር ጌታ ሆይ ባንተ ፊት ።

ቃሌና ተግባሬ እንዲሆን ሚያከብርህ
የአንደበቴ ቃል አንተን እንዲገልጥህ
በያንዳኑዱ መንገድ በሕይወት ጎዳና
አንተን ብቻ ይበል ልቦናኤን አቅና።

መንገዴን እንዳልስ እንዳልፈልግ ሌላ
አማራጭ ፍለጋ ልቤ እንዳይላላ
እንዳልደክም እኔስ ተቅበዥብዤ ባለም
ጌታ ሆይ እንዳይህ አበርታኝ ዘላለም ።



              ✍️✍️ ተፃፈ በዮናስ እድሉ ✍️

Please subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA
አዲስ ድንቅ ግጥም በዩቲዩብ ቻኔላችን
ተለቋል ❤️
🥰🥰

ገብታችሁ ተባረኩበት ለጓደኞቻችሁ ሼር
አድርጉ ሀሳብ አስተያየት በComment ያስቀምጡ። አገልግሎቱን ለመደገፍ
#Subscribe ማድረጉ አትርሱ።

Link https://youtu.be/QUaYduEDlA0
https://youtu.be/QUaYduEDlA0
አንቺ አለም ልንገርሽ

ሃሴት መሳይ ሃሰት
እንደጋለ ስሜት
በውስጥሽ አጭቀሽ፣ ከቶ አትቦርቂ
ላይ ላዩን አግጦ
ተሙነሽንሾ አጊጦ
ፍንትው ባለው ሁሉ አትንቦራጨቂ።
አየሽ...
ምን ቢስብ ውቅያኖስ፣ ላዩ ተንዠርግጎ
ሃሴት ቢጭርብሽ፣ ከውስጠትሽ ሰርጎ
የሚታይ ነው ስሚኝ፣ የማይበላ ፍሬ
በውበት ደልሎ፣ የሚባላ አውሬ።
ከከፍታ ማማም፣
ሽቅብ ለመገስገስ አትሽቀዳደሚ
ምናልባትም እያልሽ፣ ለወጉ አቅማሚ
በስልጣኔውም በቅጡ ስትረቂ
እንደባቢሎኑ ግብን አትሰንቂ
አፅምሽ እንዲተርፍ ምናልባት ብትወድቂ።

እንግዳዬሁ ዘሪቱ



Please subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA
ዛሬ በዩቲዩብ ቻኔላችን ሁለት ቪድዎች ተለቀዋል🥰😊

አንደኛ
ገጣሚ፦ነጻነት አናቶ
ርዕስ፦ ለገባው
ደቂቃ፦3.13sec


ገብታችሁ #Like #Share #Subscribe and #Comment
ማድረጉ አትርሱ

ሊንክ👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/QUaYduEDlA0
ሁለተኛ ግጥም

ገጣሚ፦ነጻነት አናቶ
ርዕስ፦ሸክላ ሰሪው
ደቂቃ፦1.25sec

ገብታችሁ #Like #Share #Subscribe and #Comment
ማድረጉ አትርሱ

ሊንክ👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/-TgqN0SidtI
ልብ ስጠኝ!

ፀሎት መጣሁ ..፡..በጭንቅ ነፍስ
ሜዳ ልቤ ..፡..ምኞት ሲያነፍስ
ከይሁዳ ልብ... አስመልጠኝ
ገንዘብ ስልህ .. ልብ ስጠኝ።

አንተ ጨንቆክ ደም እንደላብ ስታፈስስ
እኔ ጭንቄ.... ጫማስ .....ልብስስ
ስጠይቀኝ   " ያን አበባ ማን አስጌጠው"?
የ'ኔ ትጋት  ፡ እንዴት ወንድሜን ልብለጠው።
ያንተ ፍቃድ ፡ እንካኝ እኔን እንዳይጨንቅህ
እኔ   ከንቱ  ፡ ፍቃዴን ነው  ምጠይቅህ።

'ባክህ አድነኝ........ ከፍቃዴ
    ልማድ ሆኗል ....እንግድግዴ
             እግሬም መቆም እያቃተው
              እንዴት ብዬ ምርኩዝ ልተው።

ገንዘብ ምርኩዝ.... መኖር ምርኩዝ
አዘናግቶ ሚያደርግ .... እርኩስ
የሚያስጥል ያ'ንተን በረከት...
.....................እየመራ ገደል ሚከት ።
የሚገድል እያሳቀ...ገንዘብ ሰይጣን የረቀቀ
እውነትህን እያስካደ...
       ፍቅርህን እያስካደ...
                              ስንቱን ካንተ አራራቀ።

ፀሎት መጣሁ ፡ በጭንቅ ነፍስ
ሜዳ  ልቤ ፡  ምኞት ሲያነፍስ።
ከይሁዳ እግር አስመልጠኝ
ገንዘብ ስልህ ልብ ስጠኝ።

ቆራጥ አርገኝ........አንተን ስማር
ቃልህ ይጣፍጠኝ...ከምድር ማር።

ሌላ አይኑረኝ......የማወራው
ስም ሲሉኝ ስምህን ልጥራው።

ማን ነህ ሲሉኝ .....ማንም ልበል
እያረኩት ፡አንተን ቀና እኔን ዘንበል።
ታሪክ ካሉኝ.......... የ'ኔ ይጠር
ሐብት ካሉኝ..........አንተን ልቁጠር።

እኔን ልሙት...አንተን ልኑር
ከፍ ብለሃል ከፍ ላርግህ ባንተው መዝሙር።
የሞትክልኝ አንተ ንገስ።
                 የሞትክልኝ አንተ ክበር
ቅዱስ ደምህ ማለፊያዬ በገነት በር።
ቅዱስ ስምህ ከለላዬ
ክቡር ደምህ ጠበቃዬ...
  በእግዚአብሔር ፊት ቆሞልኛል
ንፁህ ደምህ......... ህሊናዬን አጥቦልኛል።

  (ፀሎት መጣሁ በጭንቅ ነፍስ)
  (    >>            >>    ሲያነፍስ )
   .....................>>
     (ገንዘብ ስልህ ልብ ስጠኝ)

እንደ ባዛር
    ጨረታ አርጎት ማዳንህን
የእርግቦች መነገጃ
        ላደረገው መቅደስህን
የሰው ሸክም ተሸክሞ               
............ያለአጢሀቱ የወጉት ጎን
                      ስንት ዲናር ያወጣ ይሆን?


➫Ⓓ.....

Please subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 125)
----------
1፤ በእግዚአብሔር የታመኑ እንደማይታወክ ለዘላለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።

2፤ ተራሮች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ሆኑ፥ ከዛሬ ጀምሮ ለዘላለም፤ እግዚአብሔር በሕዝቡ ዙሪያ ነው።


Say Amen❤️
“በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ።”
— መዝሙር 119፥10

GOOD NIGHT🥰
“ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።”
— መዝሙር 119፥105

መንገዴ እንድበራ ሕግህን አስተምረኝ
HAVE Blessed SUNDAY❤️
Why Low Reaction 🥹🥰
አብራችሁን በግጥማችሁ
ለማገልገል የምትፈልጉ
ልጆች መድረክ ክፍት ነው
በውስጥ መስመር ማናገር
ትችላላችሁ።
👉 @S_o_L_e_N_y
ጸጋችሁን አካፍሉ
(ላውጋህ ቀራንዮን)

ወንበዴን ከፃዲቅ  ባንድ' ሲፈርጁ
ፍርድ አያውቁም አይደል ቅዱሱን ሲፈጁ

እኛ የሰው ልጆች፣ ፍርድ አናውቅም አይደል?
ስብጥር ነው ለኛ፣ መፅደቅና በደል።
እሳት አመድ ወለደ ፣ ሆነና ነገሩ
ፃዲቅ ሆነህ አንተ፣ በደል ከኛ' ስሩ።

ደሞ በተረቱ
ከመንግስቱ ደጃፍ
ከጲላጦስ በራፍ
በደባ ሰው ጅራፍ
ያ! ጀርባ ሲገረፍ
ባይኑ' እየቃኘ
ንጉስ አይከሰስም፣ ይላል ያ! ሞኝ ሰው
ክርስቶስ ንጉሱስ፣ ፍርድን የለበሰው?

ላውጋህ ቀራኒዮን
የሞትህ ደብዳቤ፣ እግርህ ስር ሲጣል
ጌታዬ ንገረኝ፣ ምን ስሜት ይሰጣል ?
ጉዞውስ እንዴት ነው? የጎልጎታው ዳገት
መሞት የጀመርከው
መስቀል ተሸክመህ ተራራውን ስትግት..
የተቸነከርከው የእጅህ፣  ውስጥ ሚስማር
በታሪክ ክታብ ላይ፣ የለው አንዳች ማማር።

ወጣህ ከመስቀሉ
ሽቅብ እየቃኙ፣ እርቃንህን አይተው
እሰይ አሉ አይሁድ፣ አቅላቸውን ስተው..
አንተስ ጌታዬ ሆይ፣ ከላይ ከመስቀሉ
እንዴት አየሃቸው፣ በፌዝ አጀብ ሲሉ?...
"
ቸር አይደለህ አንተ
የይቅርታህ ጥግህ፣ የመውደድህ ህብር
አልተበጀለትም.... የለውም ዳር ድንበር
ከሊቅ እስከደቂቅ፣ ሊያገዝፍ ቢመኝም
ከአንተ ልቆ ፍቅር፣ አጀብ አያሰኝም።

Subscribe our YouTube channel
https://youtu.be/QUaYduEDlA0

(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)