ጌታዬ ሁለመናዬ!
2.71K subscribers
1.63K photos
193 videos
48 files
3.57K links
ስለ አንዲት፡ ቅድስት፡ ሐዋርያዊትና ኩላዊት ቤተ-ክርስቲያን ምንነትና ምን እንደምታስተምር ለማወቅ፣ ስለ ቤተክርስቲያን ታሪክ፤ ስለመላእክት፣ ስለቅዱሳን-ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ፣ ተዓምራት፤ የር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስን ወቅታዊ ትምህርቶች፤ መንፈሳዊ ፊልሞችን በቀላሉ ያገኙበታል፡፡ #ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)
Download Telegram
በተረጋጋ መንፈሳዊ ስሜት ሆነው ያንብቡት ስንል በጌታ ፍቅር ጋብዘንዎታል፡፡

🕊🌹🌹🌹🎂🎂🎂🕊🌷🌹💐🎂🍌❤️❤️

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 08/2014 ዓ.ም 85ኛ አመት ልደታቸውን አከበሩ።

🕊🌹🌹🌹🎂🎂🎂🕊🌷🌹💐🎂🍌❤️❤️


(1) ፓፓ ፍራንችስኮስ በየት በመቼ ዓ.ም ተወለዱ?

(2) የቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ስንተኛ ጳጳስ ናቸው?

(3) ማዕረገ ክህነትእና የጵጵስና ማዕረግ በመቼ ተቀበሉ?

(4) በቤተ-ክርስቲያናችን ር.ሊ.ጳ የተሸሙት በመቼ ነው?

(5) የምን ማህበር አባቶች ኣባል ናቸው?

(6) ማእረገ ክህነት ከተቀበሉ 52 ዓመት እንዳስቆጠሩ ያዉቁ ኖሯል?

(7) ቅዱስነታቸው አሁን ባሉበት የዓገልግሎት ሕይወት ከጀመሩ ጀምሮ ስንት ጳጳሳዊ መልእክቶችን ጽፈዋል ስማቸዉን ያሰታውሳሉ?

(8) በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ግላዊ ተነሳሽነት 23 መልእክቶች በላቲን ቋንቋ መጻፋቸው ያውቃሉ?

(9) ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ at pontefix በተሰኘው የቲውተር ገጻቸው በእየ ዕለቱ በሚያስተላልፉት መልዕክት በዓለም ዙሪያ 46 ሚልዮን ተከታይ እንዳላቸው ያዉቃሉ?

(10) ርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ማዕረጋቸውን ከመቀበላቸው በፊት የነበራቸውን ካርዲናል በርጎሊዮ የሚለውን የመጠሪያ ስማቸውን ለምን ቀየሩት?
እነዚህን እና የመሳሰሉ ሰፊ ማብራሪያዎችን ይዘን ቀርበናልና በትዕግስት በመንፈሳዊ ስሜት ያንብቡት፡፡

🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 08/2014 ዓ.ም 85ኛ አመት ልደታቸውን ማክበራቸው ተገለጸ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በታኅሳስ 17/1936 ዓ.ም የአርጄንቲና ዋና ከተማ በሆነችው በቦይነስ አይረስ መወለዳቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን 266ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመሆን በማገልገል ላይ እንደ ሚገኙ ይታወቃል።

👑👑👑👑👑👑👑👑


🎄 እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1969 ዓ.ም ማዕረገ ክህነት እንደ ተቀበሉ ከታሪካቸው ለመረዳት የተቻለ ሲሆን አሁንም እ.አ.አ በ1973 ዓ.ም በአርጄንቲና #የኢየሱሳዊያን_ማኅበር_አለቃ በመሆን መመረጣቸው ይታወሳል። እ.አ.አ በ1992 ዓ.ም የጵጵስና ማዕረግ መቀበላቸው የሚታወስ ሲሆን እ.አ.አ 1998 ዓ.ም የቦነስ አይረስ ሊቀ ጳጳስ በመሆን መሾማቸው ይታወሳል። እ.አ.አ በ2001 ዓ.ም በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከነበሩት ከዮሐንስ ሁለተኛ እጅ የካርዲናልነትን ማዕረግ መቀበላቸው የሚታወስ ሲሆን እ.አ.አ በመጋቢት 13/2013 ዓ.ም ደግም 266ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመሆን መሾማቸው ይታወሳል።

🌱 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እ.አ.አ በመጋቢት 04/2013 ዓ.ም. የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው የተመረጡበትን 8ኛውን ዓመት ማክበራቸው የሚታወስ ሲሆን ባለፈው ሰኞ በታኅሳስ 04/2014 ዓ.ም ደግሞ ማዕረገ ክህነት የተቀበሉበትን 52ኛ ዓመት ማክበራቸው ይታወሳል።

🌱 #ቅዱስነታቸው በእነዚህ ስምንት ዓመታት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው በተለየ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያን #ሚስዮናዊ የሆነ ተግባሯን አጠናክራ እንድትቀጥል እና ለሁሉም የሰው ልጆች በቅዱስ ወንጌል የሚገኘውን ደስታ እንድትመሰክር፣ በማንኛውም የቅዱስ ወንጌል የማብሰር ሂደት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በቀጥታ ተሳታፊ ይሆን ዘንድ በመፍቀድ ማከናውን እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው አበክረው መናገራቸው እና አሁንም ቤተ ክርስቲያን በእዚሁ መንገድ እንድትቀጥል ማሳሰባቸውን በፍጹም አላቋረጡም።

🌱 #ቅዱስነታቸው በእነዚህ ስምንት ዓመታት ውስጥ #በላቲን_ቋንቋ Lumen fidei በአማርኛው “የእመነት ብርሃን” የተሰኘ እና በእምነት ዙሪያ ላይ ያጠነጠን ጳጳሳዊ መልዕክት እና Laudato si በአማርኛው “ውዳሴ ለአንተ ይሁን”” በሚል አርእስት የጋራ የመኖሪያ ቤታችንን ስለ መንከባከብ (የአየር ንብረት ለውጥ) በማስመልከት የጻፉት ደግሞ ሁለተኛው ጳጳሳዊ መልእክት ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል።

🌱 #ቅዱስነታቸው በእነዚህ ስምንት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው #ሶስት_ጳጳሳዊ_መልእክቶችን ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወቅ ሲሆን እነዚህም Evangelii gaudium በአማርኛ ሲተረጎም “በወንጌል የሚገኝ ደስታ” የሚለው በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በእዚህም ቃለ ምዕዳን ቤተ ክርስቲያን በጉዞ ላይ መሆን እንዳለባት እና ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን ለማከናውን እና ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ሕዝቡ መሄድ እንዳለባት የሚያሳስብ ቃለ ምዕዳን ሲሆን በሁለተኛነት ደግሞ amoris laetitia በአማርኛው “የፍቅር ሐሴት” በሚል አርእስት ይፋ ያደረጉት ጳጳሳዊ መልዕክት በቤተሰብ ውስጥ ሊኖር ስለሚገባው ፍቅር፣ በቤተሰብ ውስጥ ስለሚታዩ ተግዳሮቶች፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለቤተሰብ ማድረግ ሰለሚጠበቅባቸው ሐዋርያዊ እንክብካቤ የሚያወሳ ድህረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል። በእዚህ ቃለ ምዕዳን በተለይም የኃይማኖት አባቶች በቤተሰብ ውስጥ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች በጥንቃቄ እና ብስለት በተሞላበት መልኩ፣ በጥንቃቄ በመመርመር በቤተሰብ ውስጥ የሚያግጥሙ ችግሮችን በችኮላ ከማውገዝ ይልቅ በእግዚአብሔር ምሕረታዊ ጸጋ በመታገዝ የመፍትሄ ሐሳቦችን መጠቆም እንደ ሚገባቸው እና ይህንንም ክህሎት ቀሳውስት ማዳበር እንዲችሉ ቤተሰብን የተመለከተ ትምሕርቶች ከዘረዓ ክህነት ጀምሮ መስጠት አስፍላጊ መሆኑን የሚገልጽ ጳጳሳዊ መልእክት ሲሆን በቅርቡ በመስከረም 24/2013 ዓ.ም ደግሞ በጣሊያነኛ ቋንቋ “fratelli tutti” ሁላችንም ወንድማማቾች ነን በሚል አርእስት ይፋ በአደርጉት ጳጳሳዊ መልእክት ወንድማማችነት እና ማኅበራዊ ወዳጅነትን በተመለከተ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን እያሳሰባቸው የመጡትን ጥያቄዎች እና በተጨማሪም ጳጳሳዊ መልእክቱ እ.ኤ.አ. በየካቲት ወር 2019 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ እና ታላቁ ኢማም አህመድ አል-ታይብ ‘ሰብዓዊ ወንድማማችነት ለዓለም ሰላም እና አብሮ ለመኖር’ በሚል አርእስት በጋራ በተፈራረሙት ሰነድ ላይ ያጠነጠነ ጳጳሳዊ መልእክት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።


🌱 #ቅዱስነታቸው በእነዚህ ስምንት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው 23 የሚሆኑ በላቲን ቋንቋ motu proprio በአማርኛው በግርድፉ ሲተረጎም (አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ እንደራሴ በመሆኑ፣ በእዚህ በተሰጠው መንፈሳዊ ስልጣን በራሱ ተነሳሽነት ወቅታዊ ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባ መልኩ የሚጽፏቸው ሰነዶች፣ የሚያደርጋቸው ሹመቶች፣ ውሳኔዎች የተመለከቱ ጉዳዮችን ያመለክታል) በእዚህም መሠረት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ግላዊ ተነሳሽነት 23 መልእክቶች መጻፋቸው ይታወቃል። እነዚህም በእርሳቸው የግል ተነሳሽነት የተጻፉ 23 መልእክቶች ወይም ባላቲን “motu proprio” ሞቱ ፕሮፕሪዮ መልእክታቸው “የቅድስት መንበር የበላይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች መማክርት ጥልቅ የሆነ ታድሶ እንዲያደርጉ የሚያሳስቡ መልእክቶች፣ በቅድስት መንበር ውስጥ በተለይም ደግሞ በፋይናንስ እና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ ግልጽነት እና ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያሳስቡ መልእክቶች፣
በአንድ ባል እና በአንድ ሚስት መካከል የሚፈጠሩ ችግሮችን እንዴት ለመፍታት እንደ ሚቻል ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ማስቀመጥን የተመለከተ መልእክት፣ ለስርዓተ አምልኮ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ መጽሐፍት በእየአንዳንዱ ሀገር ብጹዐን ጳጳሳት እውቅና አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በሚመጣጠን መልኩ ውጤታማ እንዲሆኑ ክለሳ እንዲደረግባቸው የሚጠይቅ መልእክት እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉ አርእስቶችን ያቀፉ 23 ሞቱ ፕሮፕሪዮ በራሳቸው ተነሳሽነት በጣም ተጨባጭ እና ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ገንቢ የሆኑ ሐሳቦችን በማንሳት ለምፍቴ ማቅረባቸው ያታወቃል።

🌱 #ቅዱስነታቸው በእነዚህ ስምንት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ጊዜያቸው #ቤተሰብን በተመለከት ሁለት ጳጳሳዊ ሲኖዶሶች እንዲደረጉ ማድረጋቸው የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም ወቅታዊ በሆነ መልኩ በቤተሰብ መካከል አሁን ስለሚታዩ ተግዳሮቶች በማንሳት እና ትኩረት በመስጠት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት በቤተሰብ ጉዳይ እንዲመክሩ በማድረግ ወቅታዊ ለሆኑ ችግሮች ወቅታዊ የሆነ ምላሽ በሀገረ ስብከት ደረጃ የሚሰጥበትን የመፍትሄ አቅጣጫ እንዲቀይስ በር መክፈታቸው ይታወሳል።

🌹 #ከታኅሳስ 01/2008 ዓ.ም. እስከ ኅዳር 11/2009 ዓ.ም. ደርስ #ለ349_ቀናት ያህል የቆዬ ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት ኢዩቤልዩ ማወጃቸው የሚታወስ ሲሆን ይህንን ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት በወቅቱ በክርስቲያኖች እና በሙስሊም እምነት ተከታዮች መካከል በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ በተነሳው እርስ በእርስ ግጭት ተጎሳቁላ በነበረች ሀገር በመገኘት የሁለቱንም የኃይማኖት ተወካዮች በአንድነት ፊት ለፊት አቀራርበው በማናጋገር እርቅ እንዲፈጥሩ መነገዱን በመክፈት በእዚያው በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብልክ በባንጉዊ ከተማ በሚገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካቴድራል ተገኝተው ልዩ ቅዱስ የምሕረት አመት ኢዩቤሊዪን ማስጀመራቸው የሚታወስ ሲሆን በእነዚህም 349 ቀናት ውስጥ ምዕመናን መንፈሳዊ እና አካላዊ የምሕረት ተግባራት የሚፈጸሙበት ወቅት መሆኑን ገልጸው፣ በእዚህ ልዩ ቅዱስ የምሕረት አመት ክርስቲያኖች እርቅን እና ሰላምን ይፈጥሩ ዘንድ ማሳሰባቸው ይታወቃል።


🌾💐🌾 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ስምንት ዓመት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው ከጣሊያን ውጭ 22 ሐዋሪያዊ ጉብኝቶችን ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በእነዚህም ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በአፍሪካ አህጉር የሚገኙትን ኬኒያን፣ ዑጋንዳን እና የመካከለኛው አፍሪካ ሪፖብሊክ አንስቶ በኩባ በአሜሪካ፣ በላቲን አሜሪካ በምስራቅ አውሮፓ እና በኤሺያ አህጉር በመጓዝ የሰላም እና የአንድነት መልዕክት ማስተላለፋቸው የሚታወቅ ሲሆን 900 የካቶሊክ ምዕመናን የሚገኙባትን አዛርበጃንን ጨምሮ አብዛኛው የማኅበረሰብ ክፍል የሙስሊም ተከታይ ወደ ሆኑባቸው ባንግላዲሽ እና የቡዳ እምነት ተከታይ ወደ ሚበዛባት ማያን ማር (የቀድሞ ስሟ በርማ) ድረስ በመሄድ የሰላም እና የአንድነት መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

#በጣሊያን ውስጥ ብቻ 17 የጣሊያን ከተሞችን በተለይም ደግሞ በተፈጥሮ አደጋ ለምሳሌም በርዕደ መሬት አደጋ ጉዳት የደረሱባቸውን እና ከአፍሪካ እና ከተለያዩ ሀገራት የተውጣቱ ስደተኞ ወደ አውሮጳ አህጉር መግቢያ በር አድርገው የሚጠቀሙበትን የላፓዱዛ ደሴትን ጭምር በመጎብኘት ለስደተኞች ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጥ ሰብዐዊ መብታቸው እንዲከበር ለዓለም ድምጻቸውን ማሰማታቸው እና ዓለም ለስደተኞች ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጥ ማሳሰባቸው የሚታወስ ሲሆን ስደተኞችም በበኩላቸው በእንግድነት የሚቀበሉዋቸውን ሀገሮች ማሕበራዊ ሕግጋቶችን በማክበር እንዲኖሩ፣ በእንግድነት የተቀበላቸውን ማኅበረሰብ ወግ እና ባሕል እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ መስጠታቸውም ይታወሳል።

🌹 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእነዚህ ስምንት የጵጵስና ዓመታት ዘወትር ረቡዕ ዕለት ባደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ 10 ልዩ ልዩ አርዕስቶችን መዳሰሳቸው የሚታወቅ ሲሆን በእነዚህ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምሕሮ “የእመታችን መገለጫ ከሆነው የጸሎተ ኃይማኖት አንስተው ሰባቱን ምስጢራት፣ የመነፍስ ቅዱስ ስጦታዎችን የተመለከቱ፣ ቤተ ክርስቲያንን፣ ቤተሰብን፣ ምሕረትን፣ የክርስቲያን ተስፋን፣ በመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ዙሪያ፣ አባታችን ሆይ በሚለው ጸሎት ዙሪያ፣ ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ በሕይወቱ ያደረጋቸውን ጉዞዎች በተመለከተ፣ በቅዱስ ዮሴፍ ሕይወት ዙሪያ እና በመሳሰሉት በርካታ አርዕስቶች ላይ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ማደረጋቸው ይታወሳል።

🌷🌹🌷 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በስምንት ዓመታት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤተ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ እስከ 600 ያህል ስብከቶችን ማደርጋቸው የሚታወስ ነው፣ አጠቃላይ የስብከታቸው ይዘት “ክርስትያኖች በሕይወት ጉዞዋቸው የሚያጋጥማቸውን ችግሮች መጋፈጥ እንጂ መሸሽ የለባቸውም” ማለታቸው ይታወሳል።

🌱ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ at pontefix በተሰኘው የቲውተር ገጻቸው በእየ ዕለቱ በሚያስተላልፉት መልዕክት በዓለም ዙሪያ 46 ሚልዮን ተከታይ እንዳላቸው የሚታወቅ ሲሆን በተጨማሪም Instagram በተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ #5_ሚልዮን_ተከታዮች እንዳልቸው ይታወቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ተተኪ በመሆን ከስምንት ዓመት በፊት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን 266ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው መመረጣቸው የሚታወቅ ሲሆን በትውልድ አርጀንቲናዊ የሆኑ የ85 ዓመት እድሜ ባለጸጋ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ምዕረጋቸውን ከመቀበላቸው በፊት የነበራቸውን ካርዲናል በርጎሊዮ የሚለውን የመጠሪያ ስማቸውን በመቀየር በ13ኛ ክፍለ ዘመን የኖረውን እና የድኾች አባት በመባል የሚታወቀውን የአዚዚውን የቅዱስ ፍራንቸስኮ ፈለግ ለመከተል በማሰብ የእርሱ የመጠሪያ ስም የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ዘመን መጠሪያ እንዲሆን መምረጣቸው የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም መሠረት ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም በሯን ክፍት ያደርገች፣ ለሁሉም የሰው ልጆች በቅዱስ ወንጌል የሚገኘውን ደስታ ማወጅ እና ማብሰር እንደ ሚገባት ምኞታቸው መሆኑን በተለያዩ አጋጣሚዎች መግለጻቸው ይታወቃል።

☔️#ቤተ_ክርስቲያን_ሁሉንም_የሰው_ልጆች ማስተናገድ የምትችል የሰው ልጆችን እንደ ሕይወታቸው ፈተና እና ድካም ቦታ ልትሰጣቸው የምትችል ቤተ ክርስቲያንን እንደ ሚመኙ መግለጻቸው የሚታወቅ ሲሆን በጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም የሰው ልጆች ተደራሽ መሆን ይገባታል፣ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ የሕይወት ጫናዎች ምክንያት ከቆሰሉ ሰዎች ጋር በመሆን የፈውስ ሂደት አካል ልትሆን ይገባታል የሚል ጽኑ አቋም እንደ ሚያንጸባርቁ ያታወቃል።

🌱🌱 አንድ በምቾት ውስጥ ያለች ቤተ ክርስቲያን በራሷ ምቾት ብቻ ራሱና ቆልፋ የምትኖር ከሆነ ያቺ ቤተ ክርስቲያን ጤናማ ቤተ ክርስቲያን ልትባል አትችልም በማለት በተደጋጋሚ መናገራቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህንን የመሰለ አሉታዊ ባሕርይ ያላቸው አብያተ ክርስቲያናት ይህንን አፍራሽ የሆነ ባሕርይ በማስወገድ ሰውን ከእግዚኣብሔር ለማገናኘት የተሰጣትን ተልዕኮ በመወጣት በእምነት የሚገኘውን ውበት እና ደስታ ለሰው ዘር በሙሉ ማሳየት እንደ ሚኖርባት ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።
🌹🌾🌹 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ Evangelii gaudium በአማርኛ ሲተረጎም “በወንጌል የሚገኝ ደስታ”በሚል አርእስት በጻፉት ቃለ ምዕዳን በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በእዚህም ቃለ ምዕዳን ቤተ ክርስቲያን በጉዞ ላይ መሆን እንዳለባት እና ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን ለማከናወን እና ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ሕዝቡ መሄድ እንዳለባት የሚያሳስብ ቃለ ምዕዳን ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህ ቃለ ምዕዳን ቤተ ክርስቲያንን መንፈስ ቅዱስ እንዲያስገርማት መፈቅድ ይገባታል የሚል ጭብጥ ያዘለ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በቀጣይንት ድምጹዋን እንድታሰማ እና አዳዲስ ነገር በቤተ ክርስቲያን እንዲከሰት የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ስለ ሆነ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንን እንዲያንቀሳቅስ ልንፈቅድለት ይገባል የሚል አጠቃላይ የሆነ መልዕክት የያዘ ቃለ ምዕዳን ነው።


🧚🧚🧚 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእዚህ ስምንት ዓመት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዓመታት በዋነኛነት እና በማዕከላዊነት “ምሕረት” የሚለውን ቃል በተደጋጋሚ መጥቀማቸው የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም መሠረት “የሰማይ አባታችሁ መሐሪ እንደ ሆነ እናንተም ምሕረት አድራጊዎች ሁኑ” የሚለው የክርስቲያኖች የዕለት ተዕለት መፈክር ሊሆን ይገባል በማለት በተደጋጋሚ ማስታወሳቸው ይታወሳል። ሁላችንም የመጨረሻ ቀን ፍርድ እንደ ሚጠብቀን በመጨረሻው ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከማልአክቱ ጋር በዙፋኑ ላይ ቁጭ ብሎ በጎቹን ከፊየሎቹ በመለየት በማቴዎስ ወንጌል 25 እንደ ተጠቀሰው ተርቤ አብልታችሁኛል፣ ተጠምቼ አጠጥታችኃኛል፣ ታርዤ አልብሳችሁኛል፣ እንግዳ ሆኜ መጥቼ ተቀብላችሁኛል. . .ወዘተ በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያቀርብልን ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ከአሁኑ መዘጋጀት ይኖርብናል በማለት በተደጋጋሚ የተናግሩ ሲሆን በመጨረሻው ሰዓተ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰጥን ፍርድ አሁን በሕይወት እያለን በምናከናውነው የምሕረት ወይም የበጎ አድርጎት ተግባር ላይ በተመሠረተ መልኩ በመሆኑ ከአሁኑ በጎ ተግባራርትን ማከናወን ይኖርብናል ብለዋል።


🌱 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእዚሁ በስምንት ዓመት የጵጵስናቸው ዓመታት በቤተ ክርስቲያን የቄስውስት ብቻ ሳትሆን መላው ምዕመን በተገቢው መልኩ ይሳተፉ ዘንድ መፈቀድ እንደ ሚገባ በተደጋጋሚ ማሳሰባቸው የሚታወቅ ሲሆን ምዕመናን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያልቸውን ሚና በሚገባ እንዲወጡ ማስቻል ያስፈልጋል በማንኛውም የቤተ ክርስቲያን ውሳኔዎች ውስጥ ምዕመናን በትኩረርት እንዲሳተፉ ማድረግ ይገባል የሚል ጽኑ አቋም እንዳላቸው የታወቃል። በተለይም ደግሞ ሴቶች በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ አስተዋጾ ስላላቸው ይህንን አውንታዊ የሆነ ሚና እንዲጫወቱ መፍቀድ ያስፈልጋል በማለት በተደጋጋሚ የተናገሩት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ ማሪያም ከኢየሱስ ደቀ-መዛሙርት በላይ እንደ ነበረች በማንሳት ሴቶች ለቤተ ክርስቲያን ሊያበረክቱት የሚችሉትን ከፍተኛ አስተዋጾ ቅዱስነታቸው በተደጋጋሚ አመላክተዋል።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእዚሁ ስምንት ዓመታት የጵጵስናቸው ዘመን ክርስቲያኖች ሁሉ ቅዱስ ወንጌልን በማብሰር ሂደት ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋጾ መጫወት እንደ ሚገባቸው በመገለጽ ክርስቲያኖች በመነፍስ ቅዱስ በመሞላት ቅዱስ ወንጌልን “በድፍረት፣ ጮክ ብሎ እና በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ ለማወጅ መዘጋጀት ይገባቸዋል ማለታቸውም የሚታወስ ሲሆን “በተለይም ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች በስቃይ ላይ የሚገኙትን ሰዎች ተጨባጭ በሆነ መልኩ በማገዝ፣ ተስፋ እንዳይቆርጡ በማድረግ ተፋቸው እንዲለመልም የሚያደርጉ የምሕረት ተግባራርትን ማከናወን ይገባል በማለት በተደጋጋሚ መናገራቸው ይታወቃል።

#ምንጭ፦ ቫቲካን ዜና
#አቅራቢ፦ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ
#አዘጋጅ፡ ያሬድ ደሳለ

ስለ አንዲት፡ ቅድስት፡ ሐዋርያዊትና ኩላዊት ቤተ-ክርስቲያን ምንነትና ምን እንደምታስተምር ለማወቅ፣ ስለ ቤተክርስቲያን ታሪክ፤ ስለመላዕክት፣ ስለቅዱሳን-ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ፣ ተዓምራት፤ የር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስን ወቅታዊ ትምህርቶች፤ መንፈሳዊ ፊልሞችን ሁሉ በቀላሉ ያገኙበታል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ቤተሠብ ይሁኑን፡፡ #ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33) #አሜን አሜን!!

👇👇👇👇👇👇👇



http://t.me/YariedDessale



👆👆👆👆👆👆👆

The Universal Catholic Church Teaching Channel.
" ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤
የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።" (1 ዮሐ 2: 17)
" ሕዝብህን አድን፥ ርስትህንም ባርክ ጠብቃቸው፥ ለዘላለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው።"
(መዝ 28: 9)
" የልመናዬን ቃል ሰምቶኛልና እግዚአብሔር ይመስገን።"
(መዝ 28: 6)
"ስፍራ እስከማይቀር ድረስ እናንተም በምድር ላይ ብቻችሁን እስክትቀመጡ ድረስ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ እርሻንም ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!"

(ኢሳ 5: 8)
" በላይ ያለውን አስቡ እንጂ
በምድር ያለውን አይደለም።"
(ቆላ 3: 2)
" ሕግህ ለእግሬ መብራት፥
ለመንገዴ ብርሃን ነው።"
(መዝ 119: 105)
ዳግም ቡራኬያችን እነሆ!!

#ፓሩሺያ ፪!

" እንደቀድሞው አስተምሕሯችን እንደጥንቱ ዛሬም መልሰን ደጋግመን ስለኢየሱስ የማያቋርጥ ጉብኝት በምስጢራቱ በኩል ስለሚያደርግልን ቃሉን ፓሩሲያ ብለን እየጠራን ልናወራ ይገባል"

(የነገረ መለኮት ሊቅመጋቢ ስኮት ሀን)


በወጣት ሴሚናሪና ዘማሪ ራዕይ ሳሙኤል (ጆሲ ደብረሰላም) የተዘጋጀ ድንቅ ዝማሬ በቅርቡ ይጠብቁን!!

ክብር ምስጋና ሁሉም በእሱ ከእሱ ለሆነው ለአምላካችን!! አሜን አሜን!!

#ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33) #አሜን አሜን!!

👇👇👇👇👇👇👇



http://t.me/YariedDessale



👆👆👆👆👆👆👆

The Universal Catholic Church Teaching Channel.
"#አምናለሁ!"
(ብጹዕ አቡነ ልሳነ-ክርስቶስ ማቴዎስ)

1) እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለምን የሰማዕት ንግስት ብለን እንጠራታለን?

2) በዚህ ትምህርት በእምነት መታዘዝ ውስጥ በዋናነት፡ ያመነች ብጽዕት የሆነችዋን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እና የእምነት አባት የሆነውን አብርሃምን የሁለቱን ምሳሌ እንመለከታለን፡፡

"#እምነት_ማለት፡ ተስፋ ስለምናደርገው ነገር እርግጠኛ የምንሆንበትን የማናየውን ነግር የሚያስረዳ ነው፡፡"

ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ቃሉን ይካፈሉ!!
👇👇👇👇👇👇


https://www.youtube.com/watch?v=Hd8HuddlIh4&list=PLigVl6KfrsvmGtfK5LqdU3YetEnaHRijj&index=8
" ስለ ምን፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ ትሉኛላችሁ፥
የምለውንም አታደርጉም?"

(ሉቃ 6: 46)
🌾🕊🕊🥀🌷🌷🍌🍏🍌💐🥀🌾🌾🌷🌷🌷

1. እግዚአብሔር ለእናንተ ማን ነው??
2. ባናየው እንኳ እግዚአብሔር አለ ማለት እንዴት እንችላለን??

🌾🕊🕊🥀🌷🌷🍌🍏🍌💐🥀🌾🌾🌷🌷🌷


እግዚአብሔር ፍፁም መንፈስና የሰማይና የምድር ፈጣሪ ነው፡፡
በመላው የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የወንድና የሴት ዘር ወይም ብሔር ቁም ነገር ሆኖ አያውቅም፡፡
ሰዎች በጸሎት፣ በስርዓት አምልኮ ፣ በመባዕና በሌሎችም መንገዶች ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ሲፈልጉ ኖረዋል፡፡ እግዚአብሔር ግን አይታይም፡፡ እርሱን ማወቅ የምንችለው በስራዎቹና በእምነታችን አማካይነት ብቻ ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር ያለን እውቀት በጣም የተገደበ ስለሆነ፣ እርሱን የምንገልጽበትም ቋንቋ ውስን ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር መናገር የምንችለው በህያዋን ፍጥረታት (ሰዎች ፣ እንስሳት ፣ ዕጽዋት ፣ አሽዋ . . . ወዘተ) እንዲሁም ውስን በሆነው ሰብዓዊ የእውቀትና የአስተሳሰብ መንገዶች ብቻ ናቸው፡፡

እግዚአብሔር የሰማይና የምድር በእርሱም ላይ የሚኖሩ ፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱ ፍጹም ስለሆነ ሊፈጠር አይችልም፡፡ ሰው ድልድዮችን ፣ መኪኖችን ፣ ቤቶችን፣ የተለያዩ መሳሪያዎችን ወዘተ ይሰራል፡፡ ነገር ግን እርሱ የሚጠቀምባቸው አሁን ያሉ ነገሮችን ነው፡፡ ከእምነት አንድን ነገር መፍጠር የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡
እግዚአብሔር ዓለምን በጥበቡ ፈጠረ፡፡ ዓለም የተፈጠረው በእርሱ ፍቃድ ፣ ጥበብና ቸርነት ነው፡፡ እግዚአብሔር እንደምንተነፍሰው አየር ነው፡፡ በዓይናችን ልናየው ባንችልም በዙሪያችን ግን አለ፣ በሕይወት የሚያቆየንም እርሱ ነው፡፡
እግዚአብሔር በሁሉም ቦታ ፣ በሁሉም ዘመን ፣ አእምሮ ፣ ጥበብ ፣ ቸርነት ፣ ፍጽምና ውስጥ ይኖራል፡፡ እርሱ በጊዜ አይገደብም፡፡(የአብርሃም ዘመን ዛሬም ያው ነው፡፡ አላረጀም፡፡ የሌላ አገር አምላክ ከአገራችን አምላክ ጋር ያው ነው፡፡ የእገሌ አገር ፣ ቡድን ወይም ሃይማኖት የሚል አምላክ የለምና )፡፡ እግዚአብሔር የመጨረሻ ዐዋቂና የመጨረሻ ደግ ነው፡፡
እግዚአብሔር ነጻ አድርጎ ስለፈጠረን መልካም ወይም ክፉ ማድረግን የመምረጥ ነጻነት አለን፡፡ ነገር ግን ነጻ ከሆንን ምርጫችን ለሚያስከትለው ውጤትም ተጠያቂዎች ነን፡፡ (ለምሳሌ ፣ እኔ ሌባ መሆንን ብመርጥና የሌሎች ሰዎችን ንብረት እየዞርኩ ብሰርቅ ውጤቱ በማንኛውም ወቅት እስር ቤት መግባትና ቤተ ሰቦቼ ያለ እረዳት፣ እኔም ያለ ነጻነት መቅረት ይሆናል)፡፡

እግዚአብሔር በሁሉም ቦታ እንዳለ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ ሁልጊዜ በእርሱ ፊት ነን፣ እርሱ ሁልጊዜ ያየናል ፣ እንዲያውም ወደ ሃሳባችን ሰርጾ ይገባል፡፡(ለጓደኞቸ ወይም ለቤተሰቦቸ እዋሽ ይሆናል ፣ እግዚአብሔር ግን በአእምሮዬና በልቤ ያለውን እውነት ሁሌም ያውቃል)፡፡ ሆኖም እግዚአብሔር ስህተታችንን እግር በእግር የሚከታተል ዘበኛ አይደለም፡፡ እርሱ የሚጠብቀን ፣ የሚረዳን አፍቃሪ አባታችን ነው፡፡ የእርሱ መገኘት የፍቅር ነው፡፡ ከህያዋን ፍጥረታት ሁሉ ውብ ስጦታ የሰጠን ለእኛ ብቻ ነው፡፡ አዎን ነፍስን ሰጥቶናል፡፡ በዚህ ምክንያት በእርሱ መልክና አምሳል ተፈጥረናል፡፡

ነፋስ ስላለንና በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ስለተፈጠርን ፣ እርሱ ከፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ ትልቅ ዋጋ አለን፡፡ እርሱ ስለሚወደን እኛም ለፍቅሩ ተመሳሳይ ምላሽ እንድንሰጥ ይመኛል፡፡

#ጥያቄዎች
1. እግዚአብሔር ለእናንተ ማን ነው??
2. ባናየው እንኳ እግዚአብሔር አለ ማለት እንዴት እንችላለን??

#መልስ፡-
እርሱ መኖሩን የምናውቀው በእርሱ ፍጥረት አማካይነትና በእርሱ ላይ ባለን እምነት ነው፡፡
እምነት ከሌለን በእግዚአብሔር አናምንም፡፡

#ምንጭ፡- ከሲስተር ክርስቲያን ኦሊቪራ ሊማ 3ኛ መጽሐፍ የተወሰደ 2008

#ጽሁፍ_ዝግጅት፡ ወጣት ሙሉዩ ወርቁ

#ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33) #አሜን አሜን!!

👇👇👇👇👇👇👇



http://t.me/YariedDessale



👆👆👆👆👆👆👆

The Universal Catholic Church Teaching Channel.
" የተዋረዱትን ወደ ላይ ያወጣል፥
ኀዘንተኞችንም ለደኅንነት ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል።"
(ኢዮብ 5: 11)
Forwarded from Yemi Assefa
ሰላም ለሁላችሁ!
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረበዓል አደረሰን/ አደረሳችሁ!
በኖቬና ጸሎት ዝግጅት ላይ አብራችሁን በተለይ ለሀገራችን ሰላም ስትጸልዩ የነበራችሁትን፣ ጸሎት ስታስተባብሩልን የነበራችሁ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ያካፈላችሁን ሁላችሁንም እያመሰገንንን ዛሬ በዋዜማ ጸሎት እና ዜማ ማህሌት እንዲሁም ደግሞ በነገው እለት መስዋዕተ ቅዳሴውንም በታላቅ መንፈሳዊነት አብረን እንድናከብር እንጋብዛችኋለን።
ዋዜማውን እና የበዓሉን መስዋዕተ ቅዳሴ በአካል በመገኘት መካፈል ለማትችሉ በ Youtube ቀጥታ ስለምናስተላልፍ የYoutube ቻናላችንን ስብስክራብ በማድረግ እንድትከታተሉን በታላቅ ፍቅር እንጋብዛችኋለን።
https://www.youtube.com/channel/UCwoHbF4QNqnhk-F3hgki3-Q
መልካም በዓል!
" ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።"

(ሮሜ 12: 21)
አብሳሪው መልዓክ ቅዱሰ ገብርኤል ሆይ የድል ብስራትህ አይለዬን!!

" ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው #ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ።"
(ዳን 9: 21)

" #መልአኩም መልሶ፦ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፤" (ሉቃ 1: 19)

" #መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ፦ ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።"
(ሉቃ 1: 28)



http://t.me/YariedDessale
" የማያስተውሉ፥
ውል የሚያፈርሱ፥
ፍቅር የሌላቸው፥ ምሕረት ያጡ ናቸው፤"
(ሮሜ 1: 31)
🌱🌱🌷🌾🕊🕊🌱🌱💐💐💐🌱🙏❤️🙏

የውድ አገልጋይ እናታችንን ነፍስ አምላክ በቤቱ ይቀበልልን!!
🌱🌱🌷🌾🕊🕊🌱🌱💐💐💐🌱🙏❤️🙏

"ሩጫዬን እስከመጨረሻው ሮጫለው፣ ሃይማኖቴን ጠብቄያለው።
ከእንግዲህ ወዲህ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀኛል።" (2ኛጢሞ.4፣7)

እግዚአብሔር አምላክ፥
የእናታችንን የክብርት ወርቄን ነፍስ ከአብርሃም ከይስሐቅና ከያዕቆብ አጠገብ ያኑርልን።
ለውድ ቤተሰቦችም ጌታ አምላክ መጽናናቱን አብዝቶ ይስጥልን፡፡ አሜን
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

"እንግዲህ በሠማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የ እግዚአብሔር ልጁ ኢየሱስ ስላለን÷
#ጸንተን_ሀይማኖታችንን_እንጠብቅ።" (ዕብ. 4:14)
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

"የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።
ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።
ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና። (ማቴ. 5: 4፣ 6፣8)

http://t.me/YariedDessale