Yalcodes
210 subscribers
21 photos
7 videos
1 file
27 links
Walking in insight to the tech world.
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Part 3 : While loop
❤1
Yalcodes
1. Guys ጠዋት አነሳስ ላይ እንዴት ናቹ ።
ከ 14 ሰው 7 የለሊት ሰው አግኝተናል🫡
7ታቹ ግን ተመለሱ።😁
Anyways በለሊት መነሳት ጥሩ ነው።
Video ተመችቶኛል 👍

አይ እንደድሮው ይሻላል 👎
👍4
Yalcodes
Part 3 : While loop
ሁሉም ጨረሰ ?
ደቡብ ኮሪያ ውስጥ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ወጥተው ወደ ቤታቸው የሚሄዱት ከምሽቱ 4 ሰዓት  በኋላ ነው ብትባሉ ታምናላችሁ? 🌙

እኛ ፈተና ሲቃረብ "እስከ 4 ሰዓት አነበብን" ብለን ልንፎክር እንችላለን፤ ለእነሱ ግን ይሄ መደበኛ ከት/ቤት የመውጫ ሰዓታቸው ነው! የደቡብ ኮሪያ ተማሪዎች በቀን እስከ 16 ሰዓት ድረስ የት/ት እና ጥናት ሰአት አላቸው። ከጠዋቱ 2 ሰዓት ትምህርት ቤት ገብተው መደበኛ ክፍለ ጊዜያቸውን ሲጨርሱ፣ በቀጥታ "ሀጓን" (Hagwon) ወደሚባሉ የግል አካዳሚዎች ይተማሉ።

የሚገርመው ነገር፣ እኩለ ሌሊት ላይ አውቶቡሶች በእነዚህ ተማሪዎች ተጨናንቀው ይታያሉ፤ ሁሉም ወደ ቤታቸው የሚሄዱት በዚያ ሰዓት ነው። እኛ የከሰዓት ትምህርት ኖሮን እንኳን 8 ሰዓት ሲሆን "መቼ ነው የምንወጣው?" ብለን ለምንቸኩል ተማሪዎች ይህ ነገር እንደ ቅዠት ሊመስለን ይችላል። ለኮሪያውያን ግን የዕለት ተዕለት ኑሯቸው ነው!

From Lenege hub.
❤4😁2
ሚስጥራዊ መረጃዎን ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ከማጋራትዎ በፊት ሊያውቁት የሚገባ ጉዳይ

የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የዕለት ተዕለት ሥራችንን እጅግ እያቀለለልን ቢሆንም፣ ከእድገቱ ጋር ተያይዘው የሚመጡ የሳይበር ጥቃቶች ግን አልቆሙም።

በቅርቡ በChatGPT የሶፍትዌር ሥርዓት ላይ በተገኘ ከፍተኛ የደህንነት ክፍተት፣ ጥቃት አድራሾች በአንድ "አደገኛና አጥፊ ትእዛዝ" (Malicious Prompt) ብቻ የግልና የተቋማትን መረጃዎች መዝረፍ የሚያስችል አጋጣሚ ተፈጥሮ እንደነበር የቼክ ፖይንት (Check Point) ተመራማሪዎች ይፋ አድርገዋል።

ይህ የደህንነት ስጋት፣ አጥፊ የሆኑ የጽሁፍ ትእዛዞችን በመጠቀም የChatGPTን የመከላከያ አጥር በመጣስ፣ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በቀጥታ ወደ ጥቃት ፈጻሚዎች ሰርቨር (Server) ማስተላለፍ ያስችላል።

ይህም ተጠቃሚዎች ወደ AIው የሚጭኗቸውን ልዩ ልዩ ፋይሎች፣ የግል መልእክቶች እና ሚስጥራዊ የድርጅት ሰነዶች ለከፍተኛ አደጋ አጋልጦ ቆይቷል።

ራስዎን እንዴት ይጠብቁ?

👉 ትእዛዞችን (Prompts) ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ፦ በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በተለያዩ ድረ-ገጾች ላይ "ምርጥ ውጤት ያስገኛሉ" ተብለው የሚሰራጩ የትእዛዝ አይነቶችን ሳያረጋግጡ አይጠቀሙ። እነዚህ ትእዛዞች መረጃዎን በድብቅ ወደ ጥቃት ፈጻሚዎች የሚልኩ ድብቅ መመሪያዎችን ሊይዙ ይችላሉ።

👉ሚስጥራዊ ፋይሎችን ከመጫን ይቆጠቡ፦ የባንክ መረጃዎችን፣ የጤና ሰነዶችን ወይም የተቋማትን ሚስጥራዊ ፋይሎች ወደ AI ሲስተሞች ከመጫንዎ በፊት በደንብ ያስቡ። AIው መረጃውን ለሌላ ወገን እያጋራ መሆኑን ራሱ እንኳ ላያውቀው እንደሚችል ልብ ሊባል ይገባል።
❤3
🔅 Deep Learning with Python: Optimizing Deep Learning Models

📝 Leverage techniques for optimizing deep learning models and implementing them using Python.

🌐 Author: Frederick Nwanganga
🔰 Level: Intermediate
⏰ Duration: 2h 1m

📋 Topics: Deep Learning, Python

🔗 Join Artificial intelligence for more courses
❤5
የዓለማችን የመጀመሪያው በሮቦት ቴክኖሎጂ የታገዘ ስልክ (Robot Phone) ይፋ ሆነ

ስማርት ስልኮች ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገሩ መሆኑን የሚያሳይ አስገራሚ ዜና ወጥቷል። HONOR የተባለው ኩባንያ የዓለማችንን የመጀመሪያውን በሮቦት ቴክኖሎጂ የታገዘ ስልክ (Robot Phone) ለገበያ አቅርቧል። ይህ ስልክ ከወትሮው በተለየ መልኩ ራሱን ማንቀሳቀስ የሚችል እና ለተጠቃሚው ምላሽ የሚሰጥ ነው።

ስልኩ በውስጡ እጅግ ጥቃቅን የሞተር ሲስተም (Gimbal system) የያዘ ሲሆን፣ ይህም ካሜራው ሰዎችን ተከትሎ እንዲዞር እና በቪዲዮ ጥሪ ወቅት ተጠቃሚው ቢንቀሳቀስ እንኳ ሳይቋረጥ እንዲከታተል ያስችለዋል። በተጨማሪም AI Object-tracking የተባለ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የሚንቀሳቀሱ ምስሎችን በከፍተኛ ጥራት መቅረጽ ይችላል።

ከቴክኒካዊ ብቃቱ በተጨማሪ፣ ስልኩ እንደ ሰው ስሜቱን በእንቅስቃሴ መግለጽ ይችላል። ለምሳሌ በአንድ ነገር ሲስማማ ራሱን በአዎንታ መነቅነቅ (Nodding )፣ ካልተስማማ ደግሞ ራሱን መነቅነቅ (Shaking) ይችላል። እንዲሁም ሙዚቃ ሲከፈት ከዜማው ጋር አብሮ የመንቀሳቀስ ብቃት አለው። ይህ ግኝት ስልኮች ከመሣሪያነት አልፈው የሰዎች የቅርብ ረዳትና አጋር የሚሆኑበትን ጊዜ አቅርቦታል።

ምንጭ፦ HONOR News

From balageru tech
❤3
How can i say አንድ ቀን ይሂ Ai ይበልጠናል after watching this 🤔🤔
❤4
Do u know ለምን እንደዚ እንደሚፈጠር????
❤3
Local decoding inconsistency ይባላል Ai chatbot ያጋጥመዋል ይህ ችግር።
Ai chatbot ብቻም አይደለም ችግሩ ዘርፈ ብዙ ነው in the field.
I will explain it. ግን
React አርጉ👍
👍2❤1
ከይለፍ-ቃል (Password) ወደ ማለፊያ-ቁልፍ (Passkey)፡ የዲጂታል ደህንነታችንን እናሳድግ!

Passkey (የማለፊያ-ቁልፍ) ምንድን ነው?
ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ በስልካችን ወይም በኮምፒውተራችን ላይ የሚቀመጡ ክሪፕቶግራፊክ (Cryptographic) ቁልፎችን የሚጠቀም ሲሆን፤ የጣት አሻራን (Fingerprint) ወይም የፊት ገጽታን (Facial recognition) በመጠቀም በቀላሉ ወደ አካውንታችን እንድንገባ ያስችለናል። ይህ ማለት ከዚህ በኋላ ረጅም እና ውስብስብ የይለፍ-ቃላትን ማስታወስ ላያስፈልገን ይችላል። በአሁኑ ወቅት እንደ አፕል (Apple)፣ ጉግል (Google)፣ ማይክሮሶፍት (Microsoft) እና ኤክስ (X) የመሳሰሉ ታላላቅ የቴክኖሎጂ ተቋማት ይህንን አሰራር በስፋት እየደገፉት ይገኛሉ።

በሀገራችን ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ እና አገልግሎቶች በፍጥነት እያደጉ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ የሳይበር ጥቃቶች እና የመረጃ ስርቆቶችም በተመሳሳይ እየጨመሩ ይገኛሉ። በመሆኑም የማለፊያ-ቁልፎች (Passkeys) አጠቃቀም ከማጭበርበር (Phishing) እና ከመለያ ስርቆት የላቀ ጥበቃን ይሰጡናል።
ይሁን እንጂ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች እንደሚያስጠነቅቁት፤ ይህ ቴክኖሎጂ ገና በሁሉም ድረ-ገጾች እና መተግበሪያዎች ላይ ሙሉ ለሙሉ ስላልተተገበረ ብቻውን የመጨረሻ መፍትሄ ሊሆን አይችልም።


እንዴት ልንጠቀመው እንችላለን?
አብዛኛዎቻችን በስማርት ስልኮቻችን ላይ የምንጠቀማቸው የጉግል እና አፕል አካውንቶች የ Passkey አገልግሎትን ጀምረዋል። በስልካችሁ “Security Settings” ውስጥ በመግባት "Passkeys" የሚለውን በመምረጥ ማስተካከል ትችላላችሁ።
❤2
Forwarded from INSA Cyber Talent Center
የ2018 ኢመደአ ሰመር ካምፕ የምዝገባ መስፈርቶች – INSA Cyber Talent Challenge 2026
• ምዝገባ በብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ይደረጋል (ከውጪ ዜጎች በስተቀር)
• በብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ከተመዘገቡ/ማራጋገጫ ከጨረሱ ቡሀላ ወደዋናዉ የምዝገባ ፖርታል ገብተዉ ፎርሙን መሙላት እንዳይረሱ

• ከ11 ዓመት ጀምሮ ያለ ማንኛውም ታለንት ያለው ኢትዮጵያዊ መሳተፍ ይችላል
- ምዝገባው የሚቆየው እስከ ግንቦት 8
• ሰመር ካምፑ በ6 ዩኒቨርሲቲዎች ይካሄዳል፡
1) አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
2) ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ
3) ሀረሚያ ዩኒቨርሲቲ
4) ጅማ ዩኒቨርሲቲ
5) ደብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ
6) ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
• በሳይበር ደህንነት፣ ዴቨሎፕመንት፣ ኢምቤድድ ሲስተም፣ ኤሮስፔስ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ላይ ፍላጎት እና ተሰጥኦ (Talent with passion) ያላቸው
• የተቋሙን ፈተና/ቻሌንጅ ማለፍ የሚችሉ
• አዲስ ነገር የመማር ፍላጎት እና ተግባራዊ ስራ ላይ የመሳተፍ ፈቃደኝነት/ዝግጁነት
• ችግር ፈቺ እና በራስ የመስራት/የመማር ማይንድሴት ያላቸው
• የስነ-ምግባር ችግር የሌለባቸዉ
የስልጠና ዘርፎች
• ሳይበር ደህንነት
• ሶፍትዌር ልማት
• Embedded Systems
• Aerospace
• Emerging Technologies
በምዝገባዉ መሳተፍ የማይችሉ/የማይመለከታቸዉ
1. በሳይበር ደህንነት እና ተዛማጅ ዘርፎች ላይ ፍላጎት እና ታለንት የሌላቸዉ
2. በኢመደአ የ4ዙር የሰመር ካምፕ/ፕሮግራም የተሳተፉ ድጋሜ መመዝገብ አይቻልም
⚠️ ማሳሰቢያ፡
ፎርሙ ስትሞሉ ሙሉ በሙሉ በAI የተፃፈ ይዘት መጠቀም አይፈቀድም። ከአንድ ጊዜ በላይ መሞከር ከምዝገባዉ ሊታገዱ ስለሚችሉ።
🎯 ተሳታፊዎች በINSA የመስራት እድል ፣ የስታርታፕ እድል እና ሌሎች ተጨማሪ እድሎች ተጠቃሚ ይሆናሉ
👉 ተጨማሪ መረጃ: https://t.me/insactc
👉 ለመመዝገብ: https://ctc.insa.gov.et/registration
❤1
Forwarded from INSA Cyber Talent Center
📌 Registration Requirements – INSA Cyber Talent Challenge 2026
• Registration must be completed using a National ID (except for foreign nationals).
• After completing National ID verification/registration, applicants must proceed to the main portal and complete the application form.
• Any Ethiopian citizen aged 11 years and above with talent and passion is eligible to apply.
. Registration Deadline ⏰ May 17
• The summer camp will be hosted at the following universities:
1. Addis Ababa Science and Technology University
2. Bahir Dar University
3. Haramaya University 
4. Jimma University
5. Debre Berhan University
6. Wolaita Sodo University
Preferred Fields/Streams
Applicants should demonstrate interest, talent, and passion in areas such as:
• Cybersecurity
• Software Development
• Embedded Systems
• Aerospace
• Emerging Technologies
Selection Criteria
Applicants should:
• Successfully pass the INSA’s selection test/challenge
• Be willing and ready to learn new skills and participate in practical activities
• Have strong problem-solving ability and self-learning discipline
• Maintain good ethical behavior and discipline
❌ Individuals Not Eligible for Registration
1. Applicants who do not have genuine interest, passion, and talent in Cybersecurity and related technology fields.
2. Individuals who previously participated in the 4-round INSA summer camp/program are not eligible to register again.
⚠️ Important Notice: Submitting fully AI-generated responses in the application form is strictly prohibited. The system only provides a one-time warning and will not tolerate repeated attempts. Continued violations may result in automatic disqualification from the registration process.
🎯 Benefits for Participants
Selected participants may gain access to:
• Employment opportunities at INSA
• Startup and innovation opportunities
• Additional training and career development benefits
👉 More information: https://t.me/insactc
👉 Registration Portal: https://ctc.insa.gov.et/registration
❤2
ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሆኑ ተማሪዎች የክረምት ስልጠና ተዘጋጅቷል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች የክረምት ስልጠና ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ተማሪዎች በቴክኖሎጂው ዘርፍ ራሳቸውን እንዲያንጹ ታስቦ በተዘጋጀው በዚህ መርሃ ግብር ላይ ፦
🤖 በፈንዳሜንታል ኦፍ ኤ.አይ፣
💻 ፕሮግራሚንግ፣
🧠 ማሽን ለርኒንግ፣
⚙️ በሮቦቲክስ እና IOT፣
📊 ዳታ ሳይንስ እና በሌሎችም የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ስልጠናል ይሰጣል።

ተማሪዎች ተቋሙ ባዘጋጀውን ይፋዊ ድረ-ገጽ https://aii.et/summercamp በመጠቀም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም

@tikvahethiopia
❤2