የአብስራ
506 subscribers
223 photos
782 videos
183 files
1.21K links
ሰሚት ከንዶሚንየም ሆነው አስጠኚ ከፈለጉ እና የአንድ ሳምንት ነፃ ሙከራን ጨምሮ ለማግኘት በስልክ ቁጥር:- 09-38-58-75-08 ላይ በመደወል ወይም በቴሌግራም @committed12 በመጫን ያገኙኛል።

ለተማሪዎች ተጨማሪ ድጋፍ የሚሆን
ነፃ የተንቀሳቃሽ ምሰል ማብራሪያዎች እዚህ ተጭናችሁ ታገኛላሁ:- https://youtube.com/@yabserawondewosen?si=M3rU1wnXO8__6RBx
Download Telegram
'Infinitives' ምንድን ናቸው?

Infinitives-  ግሶች ናቸው፤ የሚከተሉት የ'infinitives' ዋና ዓይነቶች ናቸው፦

Bare - ከተጨማሪ አጋዥ ግሶች ጋር (modal verbs) ጋር ጥቅም ላይ ይዉላሉ (can go, will run, shall eat, would sing)
- ምሳሌ: "she can sing. / እሷ መዝፈን ትችላለች።"

To-Infinitive - ተግባርን ያመለክታል (to go, to run, to eat)
- ምሳሌ: "I want to learn. / እኔ መማር እፈልጋለሁ።"

Object - ግስን ይከተላል (ask to go, love to sing)
- ምሳሌ: "She loves to dance / እሷ መደነስ ትወዳለች"

ማስታወሻ፦ 'Infinitives' መሰረታዊ ግሶች፤ ምንም ቅጥያም ሆነ ለዉጥ ሳይኖራቸዉ ያሉ ግሶች ናቸዉ፤ ስራቸዉ ብዙ ነዉ።

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ስለነሱ እና 'gerunds' ለመማር: https://youtu.be/RSLeFfBkOq4?si=3nMxPgPYtVRo5ST0 እዚህ ተጫኑ።
'Quantity adjectives' ምንድን ናቸዉ?

Quantity adjectives- የምንላቸዉ ቁጥርን የሚያሳዩ የስም ገላጭ አይነቶች ናቸዉ።

Many-ለሚቆጠሩ እና ብዙ ለሆኑ ነገሮች
- ምሳሌ፦ He has many cars./ብዙ መኪናዎች አሉት።

Few-ለሚቆጠሩ እና ጥቂት ለሆኑ ነገሮች
- ምሳሌ፦ we have a few books you could borrow./የተወሰኑ መፅሃፍት አሉ ልትዋስ የምትችላቸዉ።

Little- ለማይቆጠሩ እና ጥቂት ለሆኑ ነገሮች
- ምሳሌ፦ what a little time I have./ጥቂት ጊዜ ነዉ ያለኝ።

Much-ለማይቆጠሩ እና  ብዙ ለሆኑ ነገሮች
- ምሳሌ፦ the tea has too much sugar in it./ሻዩ ብዙ ስኳር በውስጡ አለዉ።

Some-ለሁለቱም ለሚቆጠሩ እና ለማይቆጠሩ በተናጋሪ አረፍተነገር ውስጥ መጠቀም እንችላለን፤
- ምሳሌ፦ she has some cars parked outside/የተወሰኑ ዉጪ የቆሙ መኪናዎች አሏት።

Any-ጥያቄ ለመጠየቅ እና አለመሆንን ለመናገር መጠቀም እንችላለን፤
- ምሳሌ፦I don't have any pens left to give./ምንም የቀረኝ የምሰጠዉ እስክሪቢቶ የለኝም።

ማስታወሻ፦ 'many/much' የተለያዩ ነገሮችን ቁጥር ቢገልፁም 'a lot' ሁለቱንም መተካት ይችላል።

የማይቆጠሩ(uncountable nouns)-እነዚህ  የበዛ ስም የሌላቸዉ ናቸዉ፤ ማለትም ውሃዎች(waters) አይባልም።
- ምሳሌ፦water,sugar,oil, powder...

የሚቆጠሩ(countable nouns)- እነዚህ የበዛ ስም ያላቸዉ ናቸዉ፤ ማለትም መኪናዎች(cars) ማለት እንችላለን።  ምሳሌ፦car,cat,dog,pen,pencil...

ተጨማሪ ስለ'Adjectives' ለመማር እዚህ  https://youtu.be/lbsURYM2tSk?si=bRAV8832KW9s_4ZM ተጫኑ።
'Auxiliaries' ምንድን ናቸው?

Auxiliaries-ረዳት ግሶች ሆነዉ ሳለ ዋና ግስን ይደግፋሉ፤ የሚከተሉት የ'auxiliaries' ቃላት ዓይነቶች ናቸው፦

Primary - ዋና ግስን ይረዳል (be, have, do, is)
- ምሳሌ: "She is running / እሷ እየሮጠች ነዉ።"

Modal - የመሆን እድልን/ግዴታን/ችሎታን/ምክርን... ያሳያል (can, will, must, should)
- ምሳሌ: "He can swim / እሱ መዋኘት ይችላል"

Semi-Modal - ተጨማሪ መረጃን ይሰጣል (need to, dare, used to)
- ምሳሌ: "I need to study / ማጥናት  አለብኝ።"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ስለ'Verbs' ለመማር: https://youtu.be/lxu_g4MkTTc?feature=shared እዚህ ተጫኑ።
'Ellipsis' ምንድን ናቸው?

Ellipsis -  ቃላትን ከመደጋገም ማስወገጃ ሲሆኑ፤ የሚከተሉት የ'ellipsis'  ዓይነቶች ናቸው፦

Nominal - ስምን ያስወግዳል (John left, Mary too)
- ምሳሌ: "She sings, he too / እሷ ትዘምራለች፣ እሱም"

Verbal - ግስን ያስወግዳል (I can, you can’t)
- ምሳሌ: "I run, she doesn’t / እኔ እሮጣለሁ፣ እሷ አትሮጥም"

Clausal - የሃረግ ክፍልን ያስወግዳል (if possible, when ready)
- ምሳሌ: "If ready, go / ዝግጁ ከሆንክ፣ ሂድ"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ለመማር: https://www.youtube.com/@yabserawondewosen/ellipsis እዚህ ተጫኑ።
'Correlative Conjunctions' ምንድን ናቸው?

Correlative Conjunctions- ጥንድ በመሆን  ክፍሎችን ያገናኛል፤ የሚከተሉት የ'correlative conjunctions'  ዓይነቶች ናቸው፦

Either…Or - አማራጮችን ያሳያል (either…or, one…or)
- ምሳሌ: "Either run or walk./ ወይ ሩጥ ወይ ተራመድ።"

Neither…Nor - አሉታዎችን(አለመሆኖችን) ያገናኛል (neither…nor, not…nor)
- ምሳሌ: "Neither she nor I sing. / እሷም እኔም አንዘፍንም።"

Both…And - መጨመርን ያሳያል (both…and, as…as)
- ምሳሌ: "she can both sing and dance / እሷ ሁለቱንም መዝፈንም መጨፈርም ትችላለች።"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ስለ'Conjunctions' ለመማር: https://youtu.be/Y8zRuS-qkXQ?si=jxeAvrjrw7NL4Q9C እዚህ ተጫኑ።
'Participles' ምንድን ናቸው?

Participles- በተለያዩ ጊዜያት ላይ የሚገኙ ግሶች ሆነዉ የባለቤቱን ድርጊት ማሳየት ሲሆን ስራቸዉ፤ የሚከተሉት የ'participles'  ዓይነቶች ናቸው፦

Present - በመካሄድ ላይ ያለን ድርጊት ያሳያል (running, singing, writing, reading)
- ምሳሌ: " she is running a marathon right now.  / አሁን ላይ እሷ ማራቶን እየሮጠች ነዉ።"

Past - የተጠናቀቀን ድርጊት ያመለክታል (written, sung, broken, eaten)
- ምሳሌ: "Those windows were broken last night / እነዛ መስታዉቶች ማታ ነበር የተሰበሩት። "

Perfect - ከተግባር በፊት  የተጠናቀቀ ድርጊትን ያሳያል  (having run, having sung) - ምሳሌ: "Having eaten, she left / ከበላች በኋላ ሄደች"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ስለ' Tense'ሶች ለመማር: https://youtu.be/cvleos5h9_E?feature=shared እዚህ ተጫኑ።
'Tenses' እና 'Verbs' ምንድን ያገናኛቸዋል?

Tense -  ማለትጊዜን ገላጭ ግስ ሲሆን፤ ምሳሌ፦ He always plays football.(present simple tense)

Verb - ደግሞ የድርጊት ቃል/ ግስ የምንለዉ ነዉ፤ ምሳሌ፦ play/plays(Verb1)

ማስታወሻ፦ግሶች/የድርጊት ቃላት የምንላቸዉ ከጊዜ ገላጭ ቃላት ወይም ሃረጎች በተጨማሪ በዋነኛነት የአረፍተ ነገሩን ጊዜ/'Tense' የሚያመላክቱ ናቸዉ።
ምሳሌ፦ 1.He plays football.(present simple tense)
2.He played football.(past simple tense)
3. He will play football.(future simple tense)

ማሳሰቢያ፦እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸዉ፤ ተጨማሪ ለመማር; https://youtu.be/QsIPgfbRRCo?feature=shared ተጫኑ።
'Present Simple Tense' ምን ይጠቅማል?

Present Simple Tense- ድግግሞሽን እና እዉነታን ለመናነር እንጠቀመዋለን።

ምሳሌ1፦ He always plays football./ እሱ ሁሌም ኳስ ይጫወታል።
ምሳሌ2፦ The sun rises in the east./ፀሃይ በስተምስራቅ ትወጣለች።

ማስታወሻ፦ምሳሌ1 ሚያሳየዉ ድግግሞሽን ሲሆን፤ምሳሌ2 ደግሞ የሚያሳየዉ እዉነታን ነዉ።

ማሳሰቢያ፦ ይህ ከ12 የ'Tense' አይነቶች ስለ አንድ የ'Tense አይነት በጥቂቱ የሚያወራ ሲሆን ተጨማሪ ስለሁሉም ከነአጠቃቀማቸዉ ለመማር;https://youtu.be/QsIPgfbRRCo?feature=shared ተጫኑ።
'Past Simple Tense' ምን ይጠቅማል?

Past Simple Tense- ያለፈ ጊዜን ለማሳየት ይጠቅማል።

ምሳሌ1፦ He played foot ball yesterday./አሱ ትላንት ኳስ ተጫዉቷል።

ምሳሌ2፦ She ate banana last time./ እሷ ያለፈዉ ጊዜ ላይ ሙዝ በልታለች።

ምሳሌ3፦ They saw the movie on the previous day./ፊልሙን ትላንት አዩት።

ማስታወሻ፦ የአረፍተ ነገሩ ባለቤት ግሱ ላይ ተፅዕኖ የለዉም፤ ሁሌም 'Verb2' ነዉ።

Regular verbs' የድርጊት ቃላት ሆነዉ  ያለፈ ጊዜ ላይ'-ed' በመጨመር ወደ 'Verb2' ይቀየራሉ።
ምሳሌ፦play=>played, study=>studied ...

irregular verbs-የድርጊት ቃላት ሆነዉ  ያለፈ ጊዜ ላይ'-ed' በመጨመር ወደ 'Verb2' የማይቀየሩ ናቸዉ።
ምሳሌ፦ eat=>ate,see=>saw,read=>read....

ማሳሰቢያ፦ ይህ ከ12 የ'Tense' አይነቶች ስለ አንድ የ'Tense አይነት በጥቂቱ የሚያወራ ሲሆን ተጨማሪ ስለሁሉም ከነአጠቃቀማቸዉ ለመማር;https://youtu.be/QsIPgfbRRCo?feature=shared ተጫኑ።
1
'Future Simple Tense' ምን ይጨቅማል?

Future Simple Tense- የወደፊት ጊዜን ያሳያል።

ምሳሌ1፦ She will study later./እሷ በኋላ ታጠናለች።

ምሳሌ2፦He will read a book tommorrow./እሱ ነገ አንድ መፅሃፍ ያነባል።

ምሳሌ3፦ They will play football tommorrow./እነሱ ነገ ኳስ ይጫወታሉ።

ማስታወሻ፦ የግስ አቀማመጡ'Will+Verb1' ሲሆን 'Verb1' የምንለዉ የግስ/የድርጊት ቃሉ መሰረታዊዉ ቃል ምንም አይነት ለዉጥ ሳይኖረዉ ነዉ።

ማሳሰቢያ፦ ይህ ከ12 የ'Tense' አይነቶች ስለ አንድ የ'Tense አይነት በጥቂቱ የሚያወራ ሲሆን ተጨማሪ ስለሁሉም ከነአጠቃቀማቸዉ ለመማር;https://youtu.be/QsIPgfbRRCo?feature=shared ተጫኑ።
'Conditionals' ምን ይጠቅማሉ?

Conditionals- ምክንያት እና ዉጤትን ሚያሳዩ አረፍተ ነገሮች ናቸዉ፤ አይነት አላችሁ እነሱም፦

Conditional 0 - እዉነታ
ቀመር፦If +v1, v1
ምሳሌ፦if you heat water to 100°C, it boils.

Conditional 1 - የሚሆንን ነገር
ቀመር፦If +v1, will+v1
ምሳሌ፦ if you study hard, you will pass the exam.

Conditional 2 - የማይሆንን  ነገር
ቀመር፦If +v2, would+v1
ምሳሌ፦ If I were a bird, I would fly away.

Conditional 3 -ፀፀት/ወቀሳ
ቀመር፦If+had+v3, would + have +v3
ምሳሌ፦ If I had eaten food, I would haven't been hungry.

ማሳሰቢያ እነዚህ ከብዙ በጥቂቱ ሲሆኑ ተጨማሪ ለመማር፦https://youtu.be/PRa34Rr80Ss?feature=shared እዚህ ተጫኑ።
'Present Continuous Tense' ምን ይጠቅማል?

Present Continuous Tense - አሁን ላይ እየተደረገ ያለ ድርጊትን ያሳያል።

ምሳሌ1፦ He is playing football right now./እሱ አሁን ኳስ እየተጫወተ ነዉ።

ምሳሌ2፦She is cleaning the house at the moment./እሷ አሁን ላይ ቤት እያፀዳች ነዉ።

ምሳሌ3፦They are currently watching TV./እነሱ አሁን ላይ ቲቪ እያዩ ነዉ።

ማስታወሻ፦'is/am/are + Verb1+ing' ቀመሩ ነዉ።

ማሳሰቢያ፦ ይህ ከ12 የ'Tense' አይነቶች ስለ አንድ የ'Tense አይነት በጥቂቱ የሚያወራ ሲሆን ተጨማሪ ስለሁሉም ከነአጠቃቀማቸዉ ለመማር;https://youtu.be/QsIPgfbRRCo?feature=shared ተጫኑ።
'Present,past and future Tense' ልዩነታቸዉ ምንድን ነዉ?

በመጀመሪያ 'Tense'- ማለት የጊዜን ገላጭ የድርጊት ቃል ማለት ነዉ።

በመቀጠል
Present simple tense- አሁን(Verb1/Verb1+s/es) ፤
ምሳሌ፦ He always plays football./እሱ ሁሌም ኳስ ይጫወታል።

Past simple tense- ያለፈ(Verb2;በ-ed/-d/-t የሚያልቅ)፤
ምሳሌ፦He  played football yesterday./እሱ ትላንት ኳስ ተጫዉቷል።

Future Simple Tense-ወደፊት(Will+Verb1)፤ ምሳሌ፦ He will play football tomorrow./እሱ ነገ ኳስ ይጫወታል።

'Tenses' ሊያሳዩ የሚችሉ ጊዜያት፦
Present simple tense(ድግግሞሽ)- always- ሁሌም,seldom-አንዳንዴ,sometimes-አንዳንዴ, never- መቼም, everyday-ሁል ቀን...

Past simple tense(ያለፈ)-yesterday-ትላንት ,previously-ባለፈዉ ,last time-ያለፈዉ ጊዜ,last week-ያለፈዉ ጊዜ...

Future Simple Tense(ወደፊት)- tomorrow-ነገ, next time-በሚቀጥለዉ ጊዜ, next week-በሚቀጥለዉ ሳምንት, later በኋላ, soon- በቅርቡ...

ማሳሰቢያ፦ ይህ ከ12 የ'Tense' አይነቶች ስለ ሶስቱ የ'Tense አይነት በጥቂቱ የሚያወራ ሲሆን ተጨማሪ ስለሁሉም ከነአጠቃቀማቸዉ ለመማር;https://youtu.be/QsIPgfbRRCo?feature=shared ተጫኑ።
2
'Past continuous tense' ምን ይጠቅማል?

Past continuous tense- ያለፈ ጊዜ ላይ ረጅም ጊዜ ወስዶ የተደረገ ድርጊትን ወይም ያለፈ ጊዜ ላይ ረጅም ጊዜ ወስዶ እየተደረገ የነበረ ድርጊት በአጭር ድርጊት ሲቋረጥን ያሳያል።

ምሳሌ1፦ He was playing football.

ምሳሌ2፦ She was washing her clothes when she got a call on the phone.

ማስታወሻ፦ ምሳሌዎቹ በገለፃዉ ቅደም ተከተል ናቸዉ።

ማሳሰቢያ፦ ይህ ከ12 የ'Tense' አይነቶች ስለ አንድ የ'Tense አይነት በጥቂቱ የሚያወራ ሲሆን ተጨማሪ ስለሁሉም ከነአጠቃቀማቸዉ ለመማር;https://youtu.be/QsIPgfbRRCo?feature=shared ተጫኑ።
1
'Future continuous tense' ምን ይጠቅማል?

Future continuous tense- ወደፊት ላይ ረጅም ጊዜ ወስደዉ የሚደረጉ ድርጊቶችን ያሳያል እንዲሁም ወደፊት ላይ ረጅም ጊዜ ወስዶ የሚደረግ ድርጊት በአጭር ድርጊት እንደሚቋረጥ ያሳያል።

ምሳሌ1፦ He will be going to Paris next week.

ምሳሌ2፦I will be waiting until you arrive.

ማስታወሻ፦ ምሳሌዎቹ በገለፃዉ ቅደም ተከተል ናቸዉ።

ማሳሰቢያ፦ ይህ ከ12 የ'Tense' አይነቶች ስለ አንድ የ'Tense አይነት በጥቂቱ የሚያወራ ሲሆን ተጨማሪ ስለሁሉም ከነአጠቃቀማቸዉ ለመማር;https://youtu.be/QsIPgfbRRCo?feature=shared ተጫኑ።
1
'Present perfect tense' ምን ይጠቅማል?

Present perfect tense-
1.በያለፈዉ እና በአሁን መሃከል ያለን ግንኙነት ያሳያል፤ያለፈ ጊዜ ላይ ተፈፅሞ አሁን ላይ ተፅዕኖ ያለዉን ድርጊት ያሳያል፤

ምሳሌ፦ He has lost his keys./እሱ ቁልፎቹ ጠፍተዉበታል።

2.ያለፈ ጊዜ ላይ ተጀምሮ አሁንም እየቀጠለ ያለ ድርጊትን ያሳያል፤

ምሳሌ፦ She has taught here since 1989./እሷ ከ1989 ጀምሮ እዚህ አስተምራለች።

3.ጊዜው በግልፅ ያልተቀመጠ ድርጊትን ያሳያል።

ምሳሌ፦ They have visited London./
እነሱ ለንደንን ጎብኝተዋል።

4. አሁን በቅርቡ የተጠናቀቀ ድርጊትን ያሳያል።

ምሳሌ፦ He has just finished reading./አሁን ገና ማንበብ ጨረሰ።

ማሳሰቢያ፦ ይህ ከ12 የ'Tense' አይነቶች ስለ አንድ የ'Tense አይነት በጥቂቱ የሚያወራ ሲሆን ተጨማሪ ስለሁሉም ከነአጠቃቀማቸዉ ለመማር;https://youtu.be/QsIPgfbRRCo?feature=shared ተጫኑ።
1
'Past perfect tense' ምን ይሰራል?

Past perfect tense-ያለፈ ጊዜ ላይ ከድርጊት በፊት የተፈጠረ ድርጊትን ያሳያል።

ምሳሌ፦ He had studied math before he played chess./እሱ ሂሳብ አጥንቶ ጨርሶ ነበር ቼዝ ከመጫወቱ በፊት።

ምሳሌ፦He played chess after he  had already studied math./እሱ ቼዝ ተጫወተ ቀድሞ አጥንቶ ከጨርሰ በኋላ።

ማሳሰቢያ፦ ይህ ከ12 የ'Tense' አይነቶች ስለ አንድ የ'Tense አይነት በጥቂቱ የሚያወራ ሲሆን ተጨማሪ ስለሁሉም ከነአጠቃቀማቸዉ ለመማር;https://youtu.be/QsIPgfbRRCo?feature=shared ተጫኑ።
1
'Future perfect tense' ምን ይጠቅማል?

Future perfect tense- ወደፊት ላይ ከድርጊት በፊት የሚፈፀምን ድርጊትን ያሳያል።

ምሳሌ1፦ I will have completed the project before the presentation.

ምሳሌ2፦ They will have planned the trip before they go.

ማሳሰቢያ፦ ይህ ከ12 የ'Tense' አይነቶች ስለ አንድ የ'Tense አይነት በጥቂቱ የሚያወራ ሲሆን ተጨማሪ ስለሁሉም ከነአጠቃቀማቸዉ ለመማር;https://youtu.be/QsIPgfbRRCo?feature=shared ተጫኑ።
1
'Present perfect continuous tense' ምን ይጠቅማል?

Present perfect continuous tense- ያለፈ ጊዜ ላይ ተጀምሮ አሁንም ተፅዕኖ ያለዉ ወይንም ያለፈ ጊዜ ላይ ተጀምሮ  አሁንም እየተደረገ ያለ ነገርን ለመናገር እንጠቀመዋለን።

ምሳሌ1፦ He has been playing football for the last two years.

ምሳሌ2፦ She has been studying for the last two hours.

ምሳሌ3፦ Has it been raining outside for the last few days?

ማሳሰቢያ፦ ይህ ከ12 የ'Tense' አይነቶች ስለ አንድ የ'Tense አይነት በጥቂቱ የሚያወራ ሲሆን ተጨማሪ ስለሁሉም ከነአጠቃቀማቸዉ ለመማር;https://youtu.be/QsIPgfbRRCo?feature=shared ተጫኑ።
1