የአብስራ
506 subscribers
223 photos
782 videos
183 files
1.21K links
ሰሚት ከንዶሚንየም ሆነው አስጠኚ ከፈለጉ እና የአንድ ሳምንት ነፃ ሙከራን ጨምሮ ለማግኘት በስልክ ቁጥር:- 09-38-58-75-08 ላይ በመደወል ወይም በቴሌግራም @committed12 በመጫን ያገኙኛል።

ለተማሪዎች ተጨማሪ ድጋፍ የሚሆን
ነፃ የተንቀሳቃሽ ምሰል ማብራሪያዎች እዚህ ተጭናችሁ ታገኛላሁ:- https://youtube.com/@yabserawondewosen?si=M3rU1wnXO8__6RBx
Download Telegram
'Interjections' ምንድን ናቸው?

Interjections- አጭር ቃላት ስሜትን ወይም ሃሳብን ይገልጻሉ፤ የሚከተሉት የ'interjections' ቃላት ዓይነቶች ናቸው፦

Excitement - ደስታን ይገልፃል (great, cool, awesome, hooray) - ምሳሌ: "Great job  /  ጥሩ/ጎበዝ "

Disappointment - መበሳጨት ያሳያል (oh, alas, darn, ugh) - ምሳሌ: "Oh we lost / ኦህ ተሸንፈናል"

Attention - ትኩረትን ይጠይቃል (hey, listen, look, wait) - ምሳሌ: "Hey come here / ሄይ ወደዚህ ና"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ስለ 'parts of speech' ለመማር: https://youtu.be/6KAxql0zNxk?si=q-wYbj54zOqXppdZ እዚህ ተጫኑ።
👍1🏆1
'Conjunctions' ምንድን ናቸው?

Conjunctions - አገናኝ ቃላት፤ ቃላትን ወይም አረፍተ ነገሮችን ያገናኛሉ፤ የሚከተሉት የ'conjunctions' ቃላት ዓይነቶች ናቸው፦

Coordinating - እኩል ጠቀሜታ ያላቸዉን ክፍሎች ያገናኛል (for, and, nor, but)
- ምሳሌ: "She always sings and dances. / እሷ ሁሌም ትዘፍናለች እና ትጨፍራለችም።"

Subordinating - ዋና እና ጥገኛ ሃረጋትን ያገናኛሉ (since, if, while, though)
- ምሳሌ: "He left since he was tired. / እሱ ስለደከመ ሄደ።"

Correlative - ጥንድ በመሆን ይሰራሉ (neither…nor, either…or, both…and)
- ምሳሌ: "Neither she nor I run. / እሷም እኔም አንሮጥም።"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ለመማር: https://youtu.be/Y8zRuS-qkXQ?si=jxeAvrjrw7NL4Q9C እዚህ ተጫኑ።
🙏1
'Phrases' ምንድን ናቸው?

Phrases-ሃረግ የምንላቸዉ ሃሳብን ይጨምራሉ፤ የሚከተሉት የ'phrases'  ዓይነቶች ናቸው፦

Noun - ስምን ያገልፃል (big house, fast car) - ምሳሌ: "Tall man  / ረጅም ሰው "

Verb - ድርጊትን ያብራራል (run fast, sleep well)
- ምሳሌ: "She sings beautifully / እሷ በደምብ ትዘምራለች"

Prepositional - የመገኛን እና የነገሩን ግንኙነት ያሳያል (on table, in room)
- ምሳሌ: "Book on shelf / መጽሐፍ መደርደሪያ ላይ"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ስለ'Verbs' ለመማር: https://youtu.be/lxu_g4MkTTc?feature=shared እዚህ ተጫኑ።
'Conditionals' ምንድን ናቸው?

Conditionals-ሁኔታዎች የሚከሰቱበትን(ምክንያት እና ዉጤትን) ያሳያሉ፤ የሚከተሉት የ'conditionals'  ዓይነቶች ናቸው፦

Zero - እውነታዎችን ለማሳያት ይጠቅማል
(if +V1, V1)
- ምሳሌ: "If you heat water to 100°C, it boils. / ውሃ በ100°C ሙቀት ላይ ቢጣድ፤ ይፈላል።"

First - ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ያመለክታል
(if + V1,will+V1)
- ምሳሌ: "If I study hard,I will pass the exam./  ተግቼ ካነበብኩ፤ፈተናዉን አልፋለዉ።"

Second - ሊሆኑ የማይችሉ ነገሮችን ያሳያል
(if+V2,would+V1)
- ምሳሌ: "If I were rich,I would buy a car./ ሀብታም ብሆን ኖሮ፤ ቤት ገዛ ነበር።"

Third-በፊት ላይ ያልሆነን እና መፀፀትን/ወቀሳን ያሳያል
(if+had+V3,would+have+V3)
-ምሳሌ:If I had time,I would have studied.(ጊዜ ቢኖረኝ ኖሮ፤ አጠንቼ ነበረ።)

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ለመማር: https://youtu.be/PRa34Rr80Ss?feature=shared እዚህ ተጫኑ።
'Voice'ኦች ምንድን ናቸው?

Voice-  ስለ ድርጊት ፈፃሚዉ/ድርጊቱ ስለተፈፀመበት (የድርጊት ቃሉን እና የአረፍተነገሩን ቅርፅ በመቀየር) ያወራል፤ የሚከተሉት የ'voice'  ዓይነቶች ናቸው፦

Active - ስለአድራጊዉ በዋነኝነት አተኩሮ ያወራል (I hit, she writes)
- ቀመር፦ Subject + Verb +Object.
- ምሳሌ: "He kicks the ball / እሱ ኳሱን ይመታል"

Passive - ድርጊቱ ስለተፈፀመበት አካል በዋነኛነት አተኩሮ ያወራል (is hit, was written)
- ቀመር፦ Object +  Verb to be + Verb3 + by +Subject
- ምሳሌ: "The Ball is kicked / ኳሱ ተመታ"

ማስታወሻ፦ 'Verb to be' የምንላቸዉ 'is,am,are,was,were,be & been' ናቸዉ፤  Verb3 የምንላቸዉ ደግሞ ብዙዉን ጊዜ በስተመጨረሻቸዉ'-ed,-d.-en,-ne,-t' ሊያልቁ የሚችሉ ናቸዉ።

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ለመማር: https://youtu.be/Wi2k3PIL1gw?feature=shared እዚህ ተጫኑ
'Clauses' ምንድን ናቸው?

Clauses - ሃረግ የምንለዉ ብዙዉን ጊዜ ያልተሟላ ሃሳብን ይይዛሉ፤ የሚከተሉት የ'clauses' ቃላት ዓይነቶች ናቸው፦

Independent - ተነጥሎ ለብቻዉ መቆም የሚችል እና በራሱ ትርጉም ሊሰጥ ይችላል (I run, she sings, he eats)
- ምሳሌ: "He plays well./ እሱ ጥሩ ይጫወታል።"

Dependent - ጥገኛ ስለሆነ ሌላ ሚያሟላዉ ይፈልጋል (because I run, if she sings)
- ምሳሌ: "Because she is tired / ስለደከመች"

Relative - ስምን ያብራራል (who, which, that, whom) - ምሳሌ: "the Boy who runs / የሚሮጠዉ ልጅ"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ስለ 'conjunctions' ለመማር: https://youtu.be/Y8zRuS-qkXQ?si=jxeAvrjrw7NL4Q9C እዚህ ተጫኑ።
'Punctuation' ምንድን ናቸው?

Punctuation-ሥርዓተ ነጥብ የምንለዉ ንግግርን ያደራጃል፤ የሚከተሉት የ'punctuation'  ዓይነቶች ናቸው፦

Period - አረፍተ ነገርን ያጠናቅቃል (.)
- ምሳሌ: "I sleep early./ እኔ በጊዜ እተኛለሁ።"

Comma - ዝርዝርን  ያሳያል (,)
- ምሳሌ: "She runs, jumps.../ እሷ ትሮጣለች፣ ትዘልላለች..."

Question - ጥያቄን ያመለክታል (?,) - ምሳሌ: "Why are you late? / ለምን አረፈድክ?"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ለመማር: https://youtube.com/playlist?list=PLSx8HfSguTqXZ2HqIly4pdO0nm3bXBmsu&si=O69Sg97ONM7L-gMd እዚህ ተጫኑ።
'Tenses' ምንድን ናቸው?

Tenses- ድርጊትን መቼ እንደተደረገ ያሳያሉ፤ የሚከተሉት የ'tenses' ቃላት ዓይነቶች ናቸው፦

Present - አሁን ያለን ይገልፃል (walk, eats, is, am)
- ምሳሌ: "He walks fast / እሱ በፍጥነት ይራመዳል።"

Past - ያለፈውን ያመለክታል (walked, ate, was, were)
- ምሳሌ: "She ate bread yesterday. / እሷ ትላንት ዳቦ በልታለች።"

Future - ወደፊትን ያሳያል (will walk, will eat, shall be)
- ምሳሌ: "They will sing / እነሱ ወደፊት ይዘምራሉ/ይዘፍናሉ።"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ለመማር: https://youtu.be/cvleos5h9_E?feature=shared እዚህ ተጫኑ።
'Sentences' ምንድን ናቸው?

Sentences - አረፍተ ነገሮች ሙሉ ሃሳብን ያስተላልፋሉ፤ የሚከተሉት የ'sentences' ቃላት ዓይነቶች ናቸው፦

Simple - አንድ ዋና ሃሳብን ያሳያል (subject, verb, object, modifier)
- ምሳሌ: "She reads books / እሷ መጽሐፍትን ታነባለች"

Compound - ሁለት እኩል ክፍሎች አሉት (and, but, or, so)
- ምሳሌ: "He runs but stops after awhile / እሱ ይሮጣል ግን ቶሎ ይቆማል"

Complex - ዋና እና ጥገኛ ክፍል አላቸው (because, if, although, when)
- ምሳሌ: "She sleeps because she is tired / እሷ ትተኛለች ምክንያቱም ስለደከመች "

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤  ስለ ሌሎች የ'sentence'ሶች አይነት ለመማር: https://youtu.be/Xv2U4QPg69U?feature=shared እዚህ ተጫኑ።
'Agreement' ምንድን ናቸው?

Agreement-ማለት የቃላት መስማማት ነዉ፤ የሚከተሉት የ'agreement'  ዓይነቶች ናቸው፦

Subject-Verb - የባለቤት እና የድርጊት ቃል በቁጥር መስማማት (he runs, they run)
- ምሳሌ: "She walks fast / እሷ በፍጥነት ትራመዳለች"

Pronoun-Antecedent -  ስም እና ተዉላጠ ስሙ በቁጥር እና በፆታ መስማማት (he-his, she-her)
- ምሳሌ: "John lost his book / ጆን መጽሐፉን አጣ"

Number - የብዛት መስማማት (one is, two are)
- ምሳሌ: "Two dogs bark / ሁለት ውሾች ይጮኻሉ"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ስለ'Subject-Verb Agreement ' ለመማር: https://youtu.be/dZ2juDQA2LQ?si=KoJO_d4aHQ9MyhG2 እዚህ ተጫኑ።
'Gerunds' ምንድን ናቸው?

Gerunds - በግስ የሚሰሩ ስሞች ናቸዉ ፤ የሚከተሉት የ'gerunds'  ዓይነቶች ናቸው፦

Subject - የአረፍተነገሩ ርዕሰ ነገር ይሆናል (running, swimming, reading, writing)
- ምሳሌ: "Running is fun / መሮጥ አዝናኝ ነው"

Object - በአረፍተ ነገሩ ውስጥ ድርጊት ሚፈፀምበት ይሆናል (love running, enjoy swimming)
- ምሳሌ: "I love reading / እኔ ማንበብ እወዳለሁ"

Complement - ለግሱ መረጃ ማሟያ ይሆናል (is running, about swimming)
- ምሳሌ: "Her hobby is dancing / የእሷ ተወዳጅ መዝናኛ መደነስ ነው"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ
ለመማር: https://youtu.be/RSLeFfBkOq4?si=3nMxPgPYtVRo5ST0 እዚህ ተጫኑ።
'Parallelism' ምንድን ናቸው?

Parallelism-ተመሳሳይነት ያለዉ አወቃቀርን ይጠብቃል፤ የሚከተሉት የ'parallelism'  ዓይነቶች ናቸው፦

Verbs - ግሶችን በተመሳሳይ መልኩ በመደጋገም መግለፅ(run-jump, eat-drink)
- ምሳሌ: "She runs and jumps / እሷ ትሮጣለች እና ትዘልላለች"

Nouns - ስሞች በተመሳሳይ መልኩ መደጋገም (cats-dogs, books-pens)
- ምሳሌ: "Cats and dogs sleep / ድመቶችና ውሾች ይተኛሉ"

Adjectives - ገላጭ ቃላትን በተመሳሳይ መልኩ በመደጋገም መግለፅ (tall-strong, fast-smart)
- ምሳሌ: "He’s tall and strong / እሱ ረጅምና ጠንካራ ነው"

ማስታወሻ፦ ይህን ሃሳብ በቀላሉ ስናየዉ የምትዘረዝሩት ነገር ድርጊት/ስም/የስምገላጭ... ቢሆን በአንድ አይነት አፃፃፍ/አባባል መቀመጥ እንዳለበት ነዉ።

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ በተጨማሪ ስለ 'Verbs' ለመማር: https://youtu.be/lxu_g4MkTTc?feature=shared እዚህ ተጫኑ።
1
'Questions' ምንድን ናቸው?

Questions - ጥያቄዎች ናቸዉ ፤ የሚከተሉት የ'questions' ዓይነቶች ናቸው፦

Yes/No - አዎ ወይም አይ መልስ የሚያስፈልጋቸዉ ጥያቄዎች ናቸዉ (is, are, do, can)
- ምሳሌ: "Are you ready? / ዝግጁ ነህ?"

Wh-Questions - ዝርዝር ይጠይቃሉ  (what ምን, where-ቦታ, when-መቼ, why-ለምን, how- እንዴት, which-የቱ)
- ምሳሌ: "Where is she? / እሷ የት ነች?"

Tag - ማረጋገጫ ጥያቄዎች ናቸዉ (isn’t it, does he)
- ምሳሌ: "You’re here, aren’t you? / እዚህ ነህ፣ አይደል?"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ስለ 'Sentence' አይነቶች ለመማር: https://youtu.be/Xv2U4QPg69U?feature=shared እዚህ ተጫኑ።
'Negation' ምንድን ናቸው?

Negation-አለመሆንን/አለመፈጠርን ያሳያሉ፤ የሚከተሉት የ'negation'  ዓይነቶች ናቸው፦

Simple - አለመሆን በአንድ ቃል ያሳያል (not, no, never, isn’t)
- ምሳሌ: "I’m not tired / እኔ አልደከምኩም"

Double - በሁለት ቃላት አለመሆንን/አለመፈጠርን ያሳያል (not nothing, never nowhere)
- ምሳሌ: "She never says nothing / እሷ መቼም ምንም አትልም"

Contraction - በአጭሩ አለመሆንን/አለመፈጠርን ያሳያል (don’t, can’t, won’t, aren’t)
- ምሳሌ: "He can’t run / እሱ መሮጥ አይችልም"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ስለኢንግሊዘኛ ሃሳቦች ለመማር: https://www.youtube.com/@yabserawondewosen/negation እዚህ ተጫኑ።
'Subjunctive Mood' ምንድን ናቸው?

Subjunctive Mood- የምኞት ሃሳብን ያሳያል፤ የሚከተሉት የ'subjunctive mood' ቃላት ዓይነቶች ናቸው፦

Present - ምኞት ይገልፃል (be, have, go, stay) - ምሳሌ: "I suggest he stay / እሱ እንዲቆይ እመክራለሁ"

Past - ያልሆነን ያመለክታል (were, had, went) - ምሳሌ: "If I were rich / እኔ ሀብታም ብሆን"

Future - ማይሆንን ያሳያል (should be, might go) - ምሳሌ: "Should he arrive / እሱ ቢደርስ"

ማስታወሻ፦ ምንም ለዉጥ የሌለዉን ግስ/የድርጊት ቃል ይጠቀማሉ፤ ብዙዉን ጊዜ ያልሆነ/የማይሆንን ነገርን ለመናገር ይጠቅማሉ።

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ስለ'Verbs' ለመማር: https://youtu.be/lxu_g4MkTTc?feature=shared እዚህ ተጫኑ።
'Relative Clauses' ምንድን ናቸው?

Relative Clauses- አገናኝ ሃረጎች ሆነዉ ስሞችን ያብራራሉ፤ የሚከተሉት የ'relative clauses'  ዓይነቶች ናቸው፦

Defining - ለመግለፅ እንጠቀማቸዋለን (who, which, that, whom)
- ምሳሌ: "Man who runs will reach the destination faster. / የሚሮጥ ሰው ቶሎ ይደርሳል።"

Non-Defining - ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል  (who, which, whose, whom)
- ምሳሌ: "Anna, who sings, is here. / አና ፤የምትዘምረዉ፤ እዚህ ናት።"

ማስታወሻ፦ 'Defining' ከጎደለ ትርጉም አይሰጥም፤'Non-Defining'ግን ግዴታ አይደለም፤ ሁለተኛዉ ምሳሌ ላይ ስናስወግደዉ ተመልከቱ
"Anna is here. / አና እዚህ ናት።"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ስለ'pronouns' ለመማር: https://youtu.be/OEFqTsuAlE8?feature=shared እዚህ ተጫኑ።
'Comparisons' ምንድን ናቸው?

Comparisons-ንፅፅሮች እና ልዩነቶችን ያሳያሉ፤ የሚከተሉት የ'comparisons'  ዓይነቶች ናቸው፦

Comparative - ሁለት ነገሮችን ይነፃፀራል (taller, faster, more, less) - ምሳሌ: "He is taller / እሱ ይበልጥ ረጅም ነው"

Superlative - ከሁሉም ከፍ ያደርጋል (tallest, fastest, most, least) - ምሳሌ: "She’s the fastest / እሷ ፈጣኗ ነች"

Equal - እኩልነት ያሳያል (as tall, as fast) - ምሳሌ: "I’m as strong / እኔ እኩል ያህል ጠንካራ ነኝ"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ስለ 'Adjectives' ለመማር: https://youtu.be/lbsURYM2tSk?si=bRAV8832KW9s_4ZM እዚህ ተጫኑ።
👍1
'Word Order' ምንድን ናቸው?

Word Order- የቃላት አሰላለፍ አረፍተ ነገርን ያደራጃል፤ የሚከተሉት የ'word order'  ዓዯነቶች ናቸው፦

Declarative - መረጃ ይሰጣል (subject-verb-object, I eat bread) - ምሳሌ: "She reads books / እሷ መጽሐፍትን ታነባለች"

Interrogative - ጥያቄ ይጠይቃል (verb-subject, do you eat) - ምሳሌ: "Do you run? / አንተ ትሮጣለህ ወይ?"

Imperative - ትዕዛዝ ይሰጣል (verb-object, eat bread) - ምሳሌ: "Close the door / በሩን ዝጋ"

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ስለ'sentence' አይነቶች ለመማር: https://youtu.be/Xv2U4QPg69U?feature=shared እዚህ ተጫኑ።
👍1
'Articles Usage' ምንድን ናቸው?

Articles Usage - መለያ ሲሆኑ ስሞችን ይደግፋሉ፤ የሚከተሉት የ'articles usage'  ዓይነቶች ናቸው፦

Definite - ልዩነትን ያመለክታል (the)
- ምሳሌ: "The cat sleeps /  ድመቱ/ቷ ትተኛለች"

Indefinite - ያልተወሰነን (ያልተለየ) ያሳያል (a, an)
- ምሳሌ: "A dog barks / አንድ ውሻ ይጮኻል"

ማስታወሻ፦ 'Indefinite' አንድ እና በአጠቃላይ(በልዩነት ተነጥሎ ያልሆነ) ያለ ነገርን ለማሳየት ስንጠቀማቸዉ፤'Definite'ቶች ደግሞ ልዩ ሆነዉ ብዙ/አንድ የሆነ ነገርን ያሳያሉ። 


ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ለመማር: https://youtu.be/feeXX0rBD2k?si=bA0pFYSWbt4qQL7g እዚህ ተጫኑ።
'Infinitives' ምንድን ናቸው?

Infinitives-  ግሶች ናቸው፤ የሚከተሉት የ'infinitives' ዋና ዓይነቶች ናቸው፦

Bare - ከተጨማሪ አጋዥ ግሶች ጋር (modal verbs) ጋር ጥቅም ላይ ይዉላሉ (can go, will run, shall eat, would sing)
- ምሳሌ: "she can sing. / እሷ መዝፈን ትችላለች።"

To-Infinitive - ተግባርን ያመለክታል (to go, to run, to eat)
- ምሳሌ: "I want to learn. / እኔ መማር እፈልጋለሁ።"

Object - ግስን ይከተላል (ask to go, love to sing)
- ምሳሌ: "She loves to dance / እሷ መደነስ ትወዳለች"

ማስታወሻ፦ 'Infinitives' መሰረታዊ ግሶች፤ ምንም ቅጥያም ሆነ ለዉጥ ሳይኖራቸዉ ያሉ ግሶች ናቸዉ፤ ስራቸዉ ብዙ ነዉ።

ማሳሰቢያ: እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ተጨማሪ ስለነሱ እና 'gerunds' ለመማር: https://youtu.be/RSLeFfBkOq4?si=3nMxPgPYtVRo5ST0 እዚህ ተጫኑ።