የአብስራ
505 subscribers
223 photos
782 videos
183 files
1.21K links
ሰሚት ከንዶሚንየም ሆነው አስጠኚ ከፈለጉ እና የአንድ ሳምንት ነፃ ሙከራን ጨምሮ ለማግኘት በስልክ ቁጥር:- 09-38-58-75-08 ላይ በመደወል ወይም በቴሌግራም @committed12 በመጫን ያገኙኛል።

ለተማሪዎች ተጨማሪ ድጋፍ የሚሆን
ነፃ የተንቀሳቃሽ ምሰል ማብራሪያዎች እዚህ ተጭናችሁ ታገኛላሁ:- https://youtube.com/@yabserawondewosen?si=M3rU1wnXO8__6RBx
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"pronouns" ምንድን ናቸዉ?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/4214FcR8uFA?si=ATyFPo1Apkv1ul34
👍4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"Adjectives" ምንድን ናቸዉ?


በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/rwEkdgdXb1E?si=KvyQc1g7LACObGsd
🔥2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"Adjectives" ምን ይሰራሉ?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/plHjvDyf-eQ?si=C_V0iJAWtpE-Qajf
👏2
"Tense" ምንድን ነዉ?

Tense: ማለት ጊዜን ገላጭ የድርጊት ቃል ማለት ነዉ፤ ይህ ማለት የድርጊት ቃሉን (ግሱን ) በመቀየር ብቻ አረፍተነገሩ አየተነገረ ያለበትን ጊዜ ወይም "Tense" መቀየር ይቻላል ማለት ነዉ፤

በድርጊት ቃላት(ግሶችን) በመጠቀም ጊዜዉን ለመቀየር ደግሞ የድርጊት ቃላቱ ምን ምን አይነት እንደሆኑ እና ምን ጠቀሜታ እንዳላቸዉ ማወቅ ተገቢ ነዉ፤

ስለሆነም ጠቀሜታቸዉን እና አይነታቸዉን አንመልከት፦

- Verb 1(ምንም ያልተቀየረዉ የግስ አይነት ማለት ነዉ)፦ ድርጊቱ የሚፈፀመዉ በተደጋጋሚ እንደሆነ ለማሳየት ይጠቅማል።
- Verb 2(ብዙ ጊዜ በስተመጨረሻዉ -d/-ed ያለዉ ነዉ)፦ድርጊቱ የተፈፀመዉ ያለፈ ጊዜ ላይ እንደሆነ ለማሳየት እንጠቀመዋለን።
- Verb 3(ብዙ ጊዜ በስተመጨረሻዉ -d/-ed/-en/-ne/-t ያለዉ ነዉ)፦እንደ አገባቡ ድርጊቱ ከሌላ ድርጊት በፊት ቀድሞ እንደሚደረግ ወይም አንደተደረገ ለማሳየት እንጠቀመዋለን።
- Verb + ing(ሁሉም ጊዜ በስተመጨረሻዉ -ing ያለዉ ነዉ)፦ ድርጊቱ ረዘም ያለ ጊዜ ወስዶ የሚደረግ ድርጊት መሆኑን ለማሳየት እንጠቀመዋለን።

ማስታወሻ፦ ብዙ ጊዜ ማለት ሁል ጊዜ ማለት አይደለም።
2👍1
"Verbs" አና "Tense" ምን ያገናኛቸዋል?

Verbs: የድርጊት ቃላት ሆነዉ ሳለ ስራቸዉ ድርጊትን ከማሳየት ባለፈ የአረፍተ-ነገሩን ጊዜ/"Tense" ማመላከት ነዉ።

Tense: ማለት ደግሞ ጊዜን ገላጭ የድርጊት ቃል/"Verb" ማለት ነዉ፤
ስለሆነም አረፍተ-ነገሩ ያለበትን ጊዜ ለመቀየር የድርጊት ቃሉን መቀየር ዋነኛዉ ስራ ነዉ።

ምሳሌ፦
present simple=>past simple

He plays football. => He played football.

እዘህ ጋር እንደምትመለከቱት ከ"present simple"=>"past simple" ለመቀየር የለወጥኩት Verb 1(plays) የነበረዉን ወደ Verb 2 (played) በመቀየር በተደጋጋሚ ከሚደረግ ድርጊት ወደ ያለፈ ጊዜ ላይ ወደተደረገ ድርጊት ነዉ።
2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"Verb" እና "Tense" ምን ያገናኛቸዋል?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/Nw634a5O9_w?si=rMoZQO9yp7DDqiBS
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"Adjectives" ምን ይሰራሉ?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/lbsURYM2tSk?si=bRAV8832KW9s_4ZM
🔥2👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"Conjunctions" ምን ይሰራሉ?


በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/Y8zRuS-qkXQ?si=jxeAvrjrw7NL4Q9C
2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአንድ ቀመር ሁሉንም "Active Voice"ሶች ወደ "Passive Voice"ሶች  መቀየር ይቻላል? አዎን፤ ከነትግበራዉ(መፀሃፉ በቪድዮ መልክ)

በፍጥነት መፅሃፋን በቪድዮ መልክ ለማግኘት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/Wi2k3PIL1gw?si=rRbw5I90vWPoRDO9
🙏2
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ታይተዉ የማይታወቁ ቀላሎቹ የ"Tense"ሶች አሰራር፤ ከነትግበራቸዉ። (መፅሃፋ በቪድዮ መልክ)

በቀላሉ ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/0nZaBirXayY?si=HjVHr0fsht9jYxxP
🙏2
ታይተዉ የማይታወቁ ቀላሎቹ የ"Tense"ሶች አሰራር፤ ከነትግበራቸዉ። (መፅሃፋ በቪድዮ መልክ)


በፍጥነት ለመመልከት ይህንን ሊንክ ተጫኑ፦https://youtu.be/0NC06EZx8j8?si=YVuXr8Goh7yQ-chV
ቀጥታ ወደመፅሃፋ ይወስዳችሗል።

መልካም ጊዜ!

-የአብስራ
2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የ"Conditional" አረፍተ ነገሮች
ቀላል ጥያቄ አሰራር ቀመር
አላቸዉ? አዎን።


በቀላሉ የምስል ማብራሪያዉን እና ንባቡን ለማግኘት፦ https://youtu.be/PRa34Rr80Ss?si=4qkpMVFmOh8IJzGD
🔥2
"Adjectives" ምን ይጠቅማሉ?

Adjectives: በሌላኛው መጠሪያቸው የስም ገላጭ በመባል የሚታወቁ ሲሆን፤ የተለያዩ አይነቶች እና ጠቀሜታዎች አላቸው።

1. Demonstrative Adjectives: ጠቋሚ (this, that, these, those)

ምሳሌ፦
This book is interesting. / ይህ መፅሐፍ አስገራሚ ነው።

Those cars are expensive. / እነዛ መኪናዎች ውድ ናቸው።


2. Quality Adjectives: ጥራትን ተናጋሪ (big, small, beautiful, round, tall, smart)

ምሳሌ፦
A big house / ትልቅ ቤት

A smart student / ጎበዝ ተማሪ


3. Quantity Adjectives: ቁጥርን ተናጋሪ (many, few, several, some, all, enough)

ምሳሌ፦
Many people attended. / ብዙ ሰዎች ተገኝተዋል።

Some water is left. / ዉስን ውሃ ቀርቷል።


4. Interrogative Adjectives: ጥያቄያዊ (which, whose, what)

ምሳሌ፦
Which car do you like? / የትኛውን መኪና ወደድከዉ/ወደድሽዉ/ወደዳችሁት?

Whose book is this? / የማን መፅሐፍ ነው?


5. Possessive Adjectives: ባለቤትነትን ተናጋሪ (my, your, his, her, its, our, their)

ምሳሌ፦
Her bag is here. / የእሷ ቦርሳ እዚህ ነው።

Our house is big. / ቤታችን ትልቅ ነው።


6. Comparative Adjectives: ሁለት ነገሮችን ለማነፃፀር (bigger, smaller, more beautiful, taller, smarter)

ምሳሌ፦
This box is bigger than that one. / ይህ ሳጥን ከዛኛዉ አንፃር ትልቅ ነው።

She is smarter than her friend. / እሷ ከጓደኛዋ አንፃር ጎበዝ ናት።


7. Superlative Adjectives: አንድን ነገር ከሁለት እና ከዛ በላይ ከሆኑ ነገሮች ጋር ለማነፃፀረ (biggest, smallest, most beautiful, tallest, smartest)

ምሳሌ፦
She is the smartest student in the class. / እሷ ከክፍሉ ዉስጥ እጅግ ጎበዟ ተማሪ ናት።

This is the tallest building in town. / ይህ በከተማው ካሉት በጣም ረጅሙ ሕንጻ ነው።


8. Numeral Adjectives: ቁጥርን የሚገልጹ (one, two, first, second, third)

ምሳሌ፦
Three cats are playing. / ሶስት ድመቶች እየተጫወቱ ነዉ።

The first place goes to him. / አንደኛ የወጣዉ እርሱ ነዉ።


9. Distributive Adjectives: እያንዳንዱን ሰውን የሚያመላክት (each, every, either, neither)

ምሳሌ፦
Each student has a book. / እያንዳንዱ ተማሪ መፅሐፍ አለው።

Every person must attend. / እያንዳንዱ ሰው መገኘት አለበት።


10. Proper Adjectives: የመለያ ስምን የሚያሳይ (American, Ethiopian, African)

ምሳሌ፦
An Ethiopian dish is tasty. /   የኢትዮጵያ ምግብ ጣፋጭ ነው።

African music is rich. / የአፍሪካ ሙዚቃ በጣም  ምሉዕ ነው።

11. Article Adjectives: አንድ መሆንን እና አለመታወቅን(a/an) ፤መታወቅን ለማሳየት (the)

ምሳሌ፦

A cat is sitting here. / አንድ ድመት እዚህ ተቀመጧል።

The apple is red. / ያ ፖም ቀይ ነው።
2👍1
"Demonstrative Adjectives" ምን ይጠቅማሉ?

Demonstrative Adjectives: ጠቋሚ ቃላት  (this-ይህ, that-ያ, these-እነዚህ, those-እነዚያ) ናቸዉ።

ምሳሌዎች፦

This pen is mine. / ይህ እስክሪፕቶ የእኔ ነው።

That house is big. / ያ ቤት ትልቅ ነው።

These shoes are comfortable. / እነዚህ ጫማዎች ምቹ ናቸው።

Those mountains are far away. / እነዚያ ተራሮች ሩቅ ናቸው።
🔥2
"Quality Adjectives" ምን ይጠቅማሉ?

Quality Adjectives: ሁኔታን ተናጋሪ ቃላት (big-ትልቅ, small - ትንሽ, beautiful-ቆንጆ, round-ክብ, tall-ረጅም, smart-ጎበዝ) ናቸዉ።

ምሳሌዎች፦

A big house / ትልቅ ቤት

A smart student / ጎበዝ ተማሪ

A small dog / ትንሽ ውሻ

A beautiful flower / ቆንጆ አበባ

A round table / ክብ ጠረጴዛ

A tall tree / ረጅም ዛፍ
👍2🙏2
"Quantity Adjectives" ምን ይሰራሉ?

Quantity Adjectives: ቁጥርን ተናጋሪ (many-ብዙ/ብዙዎቹ, few-ጥቂት, several-የተወሰኑ, some-ውስን/አንዳንድ, all-ሁሉም, enough-በቂ)

ምሳሌዎች፦

Many people attended. / ብዙ ሰዎች ተገኝተዋል።

Some water is left. / ውስን ውሃ ቀርቷል።

Few students passed the exam. / ጥቂት ተማሪዎች ፈተናውን አለፉ።

All the books are new. / ሁሉም መጽሐፍት አዲስ ናቸው።

Several cars are parked outside. / የተወሰኑ መኪናዎች በውጭ ቆመዋል።

Is there enough food? / በቂ ምግብ አለ ይሆን?
"Interrogative Adjectives" ምን ይሰራሉ?

Interrogative Adjectives: ጥያቄያዊ ቃላት (which-የትኛዉ, whose-የማን, what-ምን, where-የት, when-መቼ, who- ማን, whom-ማን, how-እንዴት) ሲሆኑ፤

ምሳሌዎች፦

Which car do you like? / የትኛውን መኪና ወደድከው/ወደድሽው/ወደዳችሁት?

Whose book is this? / የማን መፅሐፍ ነው?

What color is your shirt? / ቲሸርትህ/ቲሸርትሽ/ቲሸርታችሁ ምን ቀለም ው?

Where is the station? / ጣቢያው የት ነው?

When is the meeting? / ስብሰባው መቼ ነው?

Who is your teacher? / አስተማሪህ ማን ነው?

Whom did you call? / ማን ጋር ደውለህ ነበር?

How did you finish the work? / ስራውን እንዴት ጨረስክ?
"Possessive Adjectives" ምን ይሰራሉ?

Possessive Adjectives: ባለቤትነትን ተናጋሪ (my-የኔ, your-የአንተ/የአንቺ/የእናንተ, his-የእርሱ, her-የእርሷ, its-የነገርየዉ(የእቃዉ/የእንስሳዉ), our- የእኛ, their- የእነርሱ)

ምሳሌዎች፦

My book is on the table. / መፅሐፌ ጠረጴዛው ላይ ነው።

Your phone is ringing. / ስልክህ/ስልክሽ/ስልካችሁ እየጠራ ነው።

His car is fast. / መኪናው(የእርሱ መኪና) ፈጣን ነው።

Her bag is here. / የእርሷ ቦርሳ(ቦርሳዋ) እዚህ ነው።

Its color is beautiful. / ቀለሙ ቆንጆ ነው።

Our house is big. / ቤታችን ትልቅ ነው።

Their children are playing. / ልጆቻቸው እየተጫወቱ ነው።
2👍1
"Comparative Adjectives" ምን ይሰራሉ?

Comparative Adjectives: ሁለት ነገሮችን ለማነፃፀር (bigger-ይተልቃል, smaller-ያንሳል, more beautiful-በዉበት ይበልጣል/ትበልጣለች(ለሴቶች እና ለእቃ), taller-ይረዝማል/ትረዝማለች, smarter-ይጎብዛል/ትጎብዛለች) ይጠቅማሉ፤

ምሳሌዎች፦

This box is bigger than that one. / ይህ ሳጥን ከዛኛዉ አንፃር ትልቅ ነው።

She is smarter than her friend. / እሷ ከጓደኛዋ አንፃር ጎበዝ ናት።

My car is faster than yours. / መኪናዬ ከአንተ መኪና አንፃር ፈጣን ነው።

This dress is more beautiful than that one. / ይህ ቀሚስ ከዚያኛው ቀሚስ አንፃር በጣም ውብ ነው።

He is taller than his brother. / እሱ ከወንድሙ አንፃር ረጅም ነው።

This problem is easier than the last one. / ይህ ችግር ከቀድሞው አንፃር ቀላል ነው።

The weather today is better than yesterday. / የዛሬዉ የአየር ሁኔታ ከትላንቱ ይሻላል።

She runs faster than anyone else in the class. / እሷ በክፍሉ ውስጥ  ካለ የትኛዉም ግለሰብ አንፃር በሩጫ ትፈጥናች።
"Superlative Adjectives" ምን ይሰራለ?

Superlative Adjectives: አንድን ነገር ከሁለት እና ከዛ በላይ ከሆኑ ነገሮች ጋር ለማነፃፀረ (biggest-ከተጠቀሱት ሁሉ ትልቁ, smallest-ከተጠቀሱት ሁሉ የመጨረሻ ትንሹ, most beautiful- ከተጠቀሱት ሁሉ ዉቡ, tallest-ከተጠቀሱት ሁሉ ረጅሙ, smartest-ከተጠቀሱት ሁሉ ጎበዙ) ይጠቅማሉ፤

ምሳሌዎች፦

She is the smartest student in the class. / እሷ ከክፍሉ ውስጥ እጅግ ጎበዟ ተማሪ ናት።

This is the tallest building in town. / ይህ በከተማው ካሉት በጣም ረጅሙ ሕንጻ ነው።

He is the best player on the team. / እሱ ከቡድኑ ውስጥ ምርጡ ተጫዋች ነው።

This is the most beautiful park in the city. / ይህ በከተማው ውስጥ ዉቡ መናፈሻ ነዉ ።

She is the youngest in the family. / እሷ ከቤተሰቡ ውስጥ በእድሜ ትንሿ ናት።

This is the smallest room in the house. / ይህ ከቤቱ ውስጥ በጣም ትንሹ ክፍል ነው።

He is the tallest student in the school. / እሱ በትምህርት ቤቱ ውስጥ በጣም ረጅሙ ተማሪ ነው።

This is the most interesting book I have ever read. / ይህ እኔ እስካሁን ካነበብኳቸዉ በጣም አስገራሚዉ መፅሐፍ ነው።
🔥1