የአብስራ
506 subscribers
223 photos
782 videos
183 files
1.21K links
ሰሚት ከንዶሚንየም ሆነው አስጠኚ ከፈለጉ እና የአንድ ሳምንት ነፃ ሙከራን ጨምሮ ለማግኘት በስልክ ቁጥር:- 09-38-58-75-08 ላይ በመደወል ወይም በቴሌግራም @committed12 በመጫን ያገኙኛል።

ለተማሪዎች ተጨማሪ ድጋፍ የሚሆን
ነፃ የተንቀሳቃሽ ምሰል ማብራሪያዎች እዚህ ተጭናችሁ ታገኛላሁ:- https://youtube.com/@yabserawondewosen?si=M3rU1wnXO8__6RBx
Download Telegram
"Future continuous tense" ምንድን ይሰራል?

ጥቅም: ወደፊት ላይ ረዘም ያለ ጊዜን ወስደው የሚደረጉ/የማይደረጉ ነገሮችን ለመናገር ወይም ለመጠየቅ እንጠቀማለን።

ቀመር: subject + will + be + V1+ing + object

ምሳሌዎች:

1. He will be playing football tomorrow.
2. She will be planning for the project.
3. Will they be studying for the exam?
4. Won't we be preparing for the emergency?
"Future perfect continuous tense" ምንድን ይሰራል?

ጥቅም: በፊት ላይ ተጀምረዉ ወደፊት ላይም የሚቀጥሉ/የማይቀጥሉ ነገሮችን ለመናገር ወይም ለመጠየቅ እንጠቀመዋለን፤

ቀመር: subject + will +have+ been + V1+ing + object

ምሳሌዎች:
1. He will have been playing football for two hours by the time you arrive.

2. She will not have been planning the project for a week by next week.

3. Will they have been studying for the exam for a month by next month?

4. Will we not have been preparing for the emergency for several days by tomorrow?
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አረፍተ ነገር ምንድን ነዉ?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/oH9ytlqcpGA?si=GSLHiUoOMZCNMRRM
"Active” እና “passive” ልዩነታቸዉ ምንድን ነዉ?

Active voice: ማለት ስለ ድርጊት ፈፃሚዉ ለማጉላት የምንጠቀመዉ አረፍተ ነገር ነዉ።

ምሳሌ: She had been studying math.

አዚህ ጋር ስለአጥኚዋ ማለትም ስለ እሷ(She) ነዉ ለማጉላተ የተፈለገዉ።

Passive voice: ማለት ስለ ድርጊት የተፈፀመበት አካል ለማጉላት የምንጠቀመዉ አረፍተ ነገር ነዉ።

ምሳሌ: Math had been being studied by her.

አዚህ ጋር ስለተጠናዉ ማለትም ስለ "Math" ነዉ ለማጉላተ የተፈለገዉ።
Verb" ምን ማለት ነዉ?

Verb: ማለት ግስ ማለት ሲሆን ጠቀሜታዉ ድርጊትን በተለያዩ ጊዜዎች ዉስጥ ማሳየት ነዉ።

"Verbs" የተለያየ ጊዜን ሲገልፁ፤

Verb1    Verb2    Verb3
play/s   played   played
eat         ate         eaten
study     studied studied

በመጨረሻ
Verb 1: ድግግሞሽን ለመናገር፣
Verb 2: ያለፈ ጊዜ ላይ የተደረገ ነገርን ፣ እና
Verb 3: ከድርጊት በፊት የተደረገ ድርጊትን ለመናገር  እንጠቀማቸዋለን።
"Nouns" ምንድን ናቸው?

Noun: ማለት ስሞች የምንላቸው ሲሆኑ ስራቸው የሰዎችን, የቦታ, የነገሮች, የእንስሶች እና የሃሳቦች መጠሪያ እና መለያ ማሳየት ነው።

የሰዎች፦ Abebe, Father, Mother, Doctor...

የቦታዎች፦ Hospital, School, Addis Ababa...

የነገሮች፦ Chair, Table, Money...

የእንስሳት፦ Elephant, Lion, Cat, Hippopotamus...

የሃሳቦች፦ Stoicism, Confucianism, Taoism...
"Verb" ምን ማለት ነዉ? አይነቱስ?

Verb: ማለት ግስ ማለት ሲሆን ጠቀሜታዉ ድርጊትን በተለያዩ ጊዜዎች ዉስጥ ማሳየት ነዉ።

"Verbs" አይነት እና ጠቀሜታ አላቸዉ እነሱም፦

Auxiliar Verbs: አጋዥ ግሶች የምንላቸዉ ናቸዉ ዋነኞቹ፤

   Have=> have,has & had
   Be=>is, am, are ,was, were, be, been, & being
   Do=> do,does, & did

Modal Verbs: ፈቃድ፣ የመሆን እድልን፣ አስፈላጊነትን፣ እና ብቃትን  ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን፤

እነሱም ፦ can, could, shall, should, will, would, have to, ought to, & need to...

Transitive verbs: ካለ ድርጊት የተፈፀመበት አካል መቅረብ የማይችሉ ግሶች ናቸዉ፤

ምሳሌ፦ He plays football.

እዚህ ጋር "plays"=>"Transitive verb" ነዉ ምክንያቱም ደግሞ የተሻገረበት ድርጊት የተፈፀመበተ አካል ቀጥሎ ስለኖረዉ ነዉ።

Intransitive verbs: ካለ ድርጊት የሚፈፀምበት አካል መቅረብ የሚችሉ የግስ አይነቶች ናቸዉ፤

ምሳሌ፦The water boils.

እዚህ ጋር "boils" =>"Intransitive Verb" ነዉ ምክንያቱም ደግሞ የተሻገረበተ ድርጊት የተፈፀመበት አካል ባለመኖሩ ነዉ።
👍1
"Auxiliar Verbs" ምንድን ናቸዉ?

Auxiliar Verbs: አጋዥ ግሶች የምንላቸዉ ናቸዉ ዋነኞቹ፤

   Have=> have,has & had.
   Be=>is, am, are ,was, were, be, been, & being.
   Do=> do,does, & did.

Have: እና አይነቶቹን ብዙዉን ጊዜ ከ "Verb3" ጋር የ"Perfect Tense" መሆኑን ለማሳየት ትጠቀሙታለቸሁ፤

ምሳሌ፦ Have you finished yet.

Is: እና አይነቶቹን ብዙዉን ጊዜ ከ "Verb+ing" ጋር የ "Continuous Tense" መሆኑን ለማሳየት ትጠቀሙታለቸሁ፤

ምሳሌ፦ he is studying Math.

Do: እና አይነቶቹን ብዙዉን ጊዜ ከ "Verb1" ጋር የ "Simple Tense" መሆኑን ለማሳየት ትጠቀሙታለቸሁ፤

ምሳሌ፦ Do you like to play?
👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"Modal Verbs" ምንድን ናቸዉ?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/OCcK16neW7k?si=zaa3U4XsTSQ1i8id
"Modal verbs" ምንድን ናቸዉ?

Modal verbs: አማራጭ ፣ የመሆን እድልን፣ አስፈላጊነትን፣ እና ብቃትን ሌሎችንም ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን።

እነሱም ፦
- can - ፈቃድን ለመጠየቅ/ለመናገር
- could - ይቻላልን ለመጠየቅ/ለማሳየት
- shall - ወደፊት ላይ ያለ አማራጭን ለመጠየቅ/ለመጠቆም
- should - ምክር ለመስጠት
- will - የወደፊት እቅድን ለማሳየት
- would - ፍላጎትን ለመጠየቅ
- have to - ግዴታን ለማሳየት
- ought to - ምክር ለመስጠት
- need to - አስፈላጊነትን ለማሳየት
- must - ግዴታን ለማሳየት

እነዚህ ከብዙ ጠቀሜታቸዉ ጥቂቶቹ ናቸዉ።
"Sentence" ምንድን ነዉ?

Senence: የምንለዉ ትርጉም የሚሰጥ የቃላት ስብስብ ሆኖ ሳለ ቃላቱ በትክክለኛዉ ቅደም ተከተል መቀመጥ ይኖርባቸዋል አረፍተነገር የሚለዉን ስያሜ ለማግኘት።

አረፍተነገሮች አራት ዋና ዋና አይነቶች አሏቸዉ እነሱም፦

Declarative: እዉነታን እና መረጃን ለማሳየት፤
ምሳሌ፦ water boils at 100°C.

Imperative: ትእዛዛዊ፤
ምሳሌ፦ Do your homework.

Interrogative : ጥያቄያዊ፤
ምሳሌ፦ What is your name?

Exclamatory: ጠንካራ ስሜትን ለመግለፅ፤
WOW! what a beautiful house!
👍2
"Tense"ሶችን እንዴት ትለዩዋቸዋላችሁ?

Tense: ማለት ጊዜን ገላጭ የድርጊት ቃል ሆኖ ሳለ፤
ሶስቱ ዋና ማለትም "past, present,& future"
እና ሁለቱ ተጨማሪዎች "Continuous" እና "perfect" ሆነዉ 12 የ"Tense"ሶች አይነቶችን ይሰራሉ ብሎም አንዱን ከሌላዉ በቀላሉ እንዴት መለየት እንደምትችሉ  አቅጣጫዉን ላሳያችሁ፤

ሶስቱ ዋናዎቹ
- present:V1(ምንም ለዉጥ ሳይኖረዉ ቅጥያ በስተመጨረሻዉ ካለዉ ደግሞ-s/-es   ያለዉ ነዉ።)
- past: V2(ብዙውን ጊዜ-ed/-d  በስተመጨረሻዉ ያለዉ ነዉ።)
- future: will/shall/can + V1(ምንም ለዉጥም ሆነ ቅጥያ ሳይኖረዉ፤)

ሁለቱ ተጨማሪዎች
- Continuous: V1+ing
- perfect:V3( ብዙዉን ጊዜ -ed/-en/-t/-d መጨረሻዉ ላይ ያለ)

እነዚህ ዋናዎቹን ከተጨማሪዎቹ ጋራ አንድ በአንድ አልያም ሁለቱንም አንድ ላይ በመቀላቀል 12  የተለያዩ ጠቀሜታ ያላቸዉን "Tense"ሶች መስራት ይቻላል፤

በተጨማሪም ማስተዋል ሚኖርባችሁ ነገር አንድ "Tense" አለ ማለት ያንን ሚለየዉ ግስ ከላይ እንደተጠቀሰዉ በዉስጡ (በ"Tense"ሱ) አለ ማለት ነዉ።
👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አረፍተነገር ስንት ክፍሎች አሉት?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/5grVQAvnR1A?si=VGVOGZxykcokEC6W
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"Verb" ምን ማለት ነዉ? አይነቱስ?
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"Auxiliary Verbs" ምንድን ናቸዉ?
"Can" ምን ማለት ነው?

Can: ማለት ብቃትን አልያም ችሎታን ለማሳየት የምንጠቀመዉ፤ ብቃትን አልያም ችሎታን ለመናገር ወይም ለመጠየቅ የምንጠቀመዉ የ"Modal verb" አይነት ነዉ።

ምሳሌዎች:

1. He can play football. (Positive sentence)
2. Can she do her homework on her own? (Question)
3. Can't they play with us? (Negative question)
4. We can't let that happen. (Negative sentence)
"Will"ምን ማለት ነው?

  Will: እቅድን እና የወደፊት ሃሳብን በ"future tense" ላይ ለማሳየት፤ ለመናገር እንዲሁም ለመጠየቅ ልንጠቀመዉ እንችላለን።

ምሳሌዎች:

- He will study later. 
    እሱ  በሇላ ያጠናል።

- She won't be cleaning later. 
    እሷ በሇላ አታፀዳም።

- Will they be here on time? 
    እነሱ በጊዜ ይደርሱ ይሆን?

- Won't we be there on time?
   እኛ  በጊዜ አንደርስም ይሆን?
"Shall" ምን ይሰራል?

Shall: ፈቃደኝነትን ለመጠየቅ፣ ምክር ለመለገስ እና ስነስርአት ባለዉ መልኩ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ልንጠቀመዉ እንችላለን።

ምሳሌዎች፦

You shall do your homework.
የቤት ስራህን ብትሰራ ጥሩ ይመስለኛል።

They shalln't play with fire.
በእሳት ባይጫወቱ ጥሩ ነዉ።

Shall we study math?
ሂሳብ እናጥና ይሆን?

Shalln't they swim in the sea?
ባህሩ ዉሰጥ መዋኘት የለባቸዉም ይሆን?
👍1
"Is" ምን ይሰራል?

Is: ጠቀሜታዉ( ነዉ የሚለዉን ትርጉም ይሰጣል) አንድ ተናጋሪ አልያም ጠያቂ አረፍተ ነገር  የ"Continuous tense" መሆኑን ማለትም ቀጣይኀት ያለዉ ወይም ረዘም ያለ ጊዜን እንደሚወስድ ለማሳየት ነዉ።

ምሳሌዎች፦

He is playing football now.
እሱ አሁን ኳስ እየተጫወተ ነዉ።

She is not studying math at this moment.
እሷ አሁን ሂሳብ እያጠናች አይደለም።

Is she not working right now?
አሁን እሷ አየሰራች አይደለም ወይ?

Is he washig his cloth currently?
አሁን እሱ  ልብሱን እያጠበ ነዉ ወይ?