የአብስራ
506 subscribers
223 photos
782 videos
183 files
1.21K links
ሰሚት ከንዶሚንየም ሆነው አስጠኚ ከፈለጉ እና የአንድ ሳምንት ነፃ ሙከራን ጨምሮ ለማግኘት በስልክ ቁጥር:- 09-38-58-75-08 ላይ በመደወል ወይም በቴሌግራም @committed12 በመጫን ያገኙኛል።

ለተማሪዎች ተጨማሪ ድጋፍ የሚሆን
ነፃ የተንቀሳቃሽ ምሰል ማብራሪያዎች እዚህ ተጭናችሁ ታገኛላሁ:- https://youtube.com/@yabserawondewosen?si=M3rU1wnXO8__6RBx
Download Telegram
የተማሪዬን የዉጤት ለዉጥ ተመልከቱ!

በሳፋሪ አካዳሚ ት/ት ቤት የምትማረዉ እና የኔ ተማሪ የሆነችዉን የማርያማዊት ሰለሞን የዉጤት መሻሻል፤ የአንደኛዉ ሩብ አመት አና የሶስተኛዉ ሩብ አመት ንፅፅር እነሆአችሁ፦

                 የአንደኛዉ    የሶስተኛዉ    ልዩነት
አማርኛ            89.2         91        + 1.8
ሂሳብ              88.5         88         - 0.5
ኢንግሊዘኛ       79.5        89         + 9.5
ሳይንስ           80.25      88.5      + 8.25
አማካይ         86.63      89.5       + 2.87
ድምር           606.45    625.5     +19.05

ብሎም ሰሚት ኮንዶሚንየም ሆነው ልክ እንደዚህ የልጆችዎ ዉጤት ወዳላይ እንዲጓዝ የምትፈልጉ ከሆነ እና የአንድ ሳምንት ነፃ ሙከራን ጨምሮ ለማግኘት በስልክ 📞09-38-58-75-08 ተጭነው በመደወል ያገኙናል።
👍2
የተማሪዬን የዉጤት ለዉጥ ተመልከቱ!

በሳፋሪ አካዳሚ ት/ት ቤት የምትማረዉ እና የኔ ተማሪ የሆነችዉን የማርያማዊት ሰለሞን የዉጤት መሻሻል፤ የአንደኛዉ ሩብ አመት አና የሶስተኛዉ ሩብ አመት ንፅፅር እነሆአችሁ፦

                 የአንደኛዉ    የሶስተኛዉ    ልዩነት
አማርኛ            89.2         91        + 1.8
ሂሳብ              88.5         88         - 0.5
ኢንግሊዘኛ       79.5        89         + 9.5
ሳይንስ           80.25      88.5      + 8.25
አማካይ         86.63      89.5       + 2.87
ድምር           606.45    625.5     +19.05

ብሎም ሰሚት ኮንዶሚንየም ሆነው ልክ እንደዚህ የልጆችዎ ዉጤት ወዳላይ እንዲጓዝ የምትፈልጉ ከሆነ እና የአንድ ሳምንት ነፃ ሙከራን ጨምሮ ለማግኘት ባዮዉ ላይ ያለዉን የስልክ ምልክቱን 📞ተጭነው በመደወል ያገኙናል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"Tense" ምን ማለት ነዉ?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ ፦https://youtu.be/kQP-NUideQE?si=fzNlz6ERuOaqQsUO
"Tense" ምን ማለት ነዉ?

Tense=> ጊዜን ገላጭ የድርጊት ቃል ነዉ፤ ማለትም በድርጊት ቃሉ ብቻ "Tense" መቀየር ትችላላችሁ ማለት ነዉ።

ምሳሌ፦

በልቻለዉ - V2=ate/ V3= eaten
እየበላዉ ነዉ - eating
ልበላ ነዉ - going to eat/will eat

አነዚህ የድርጊት ቃላት የተለያየ ጊዜን ገልፀዋሉ ለዚህም የተለያዩ "Tense"ሶችን አንድን የድርጊት ቃል በመቀያየር እና ከጎኑ አጋዥ ግሶችን በመጨመር መቀየር ትችላላችሁ ማለት ነዉ።
"present Tense"ሶች ስንት አይነት አላቸዉ? ልዩነታቸዉስ?

አራት አይነት አላቸዉ እነሱም እንደሚከተሉት ከቀመር ፣ ልዩነታቸዉ እና ከምሳሌያቸዉ ጋር ይቀርባሉ፤

present simple tense - ድግግሞሽ፤
subject + V1 + object
ምሳሌ፦he plays football.

present continuous tense- አሁን ላይ አየተደረገ ያለ፤
subject +is/am/are+ V1+ing + object
ምሳሌ፦he is playing football.

present perfect tense - ቀደም ብሎ የተጀመረ ግን ቅርብ ሰአት ያለቀ፤
subject + has/have+V3 + object
ምሳሌ፦he has played football.

present perfect continuous- ቆይቶ የጀምረ እና አሁንም እየቀጠለ ያለ፤
subject + has/have+ been+V1+ing + object
ምሳሌ፦ he has been playing football for a while.

በስተመጨረሻ ማስተዋል የሚኖርባችሁ ነገረ present= ከተባለ=> V1፣
Continuous= ከተባለ=> V1+ing ፣
perfect=ከተባለ=>V3 እንደሚኖራቸዉ ነዉ።
"Past Simple Tense" ምንድን ይጠቅማል?

ሚገልፀው - ያለፈ ጊዜን፤
ቀመር - subject + V2 (-ed) + object

ምሳሌ 1: He played football yesterday afternoon.
ምሳሌ 2: She ate her lunch just before.
ምሳሌ 3: They studied math last Monday.
👍3
"Past Continuous Tense" ምንድን ይሰራል?

ሚገልፀው: ያለፈ ጊዜ ላይ ረዘም ያለ ጊዜ ወስዶ የተደረገን ነገርን ለማሳየት ነዉ፤

ቀመር: subject + was/were + V1 + ing + object

ምሳሌ 1: He was playing football.

ምሳሌ 2: They weren't studying math.

ምሳሌ 3: Who was crying?

ምሳሌ 4: When wasn't she reading?
Past Perfect Tense: ምንድን ይሰራል?

ጥቅም: ያለፈ ጊዜ ላይ ተጀምሮ የተፈፀመ/ያልተፈፀመ ነገርን ለመናገር/ ለመጠየቅ ይጠቅማል፤

ቀመር: subject + had + V3 + object

ምሳሌ 1: He had played football.

ምሳሌ 2: Had she studied math already?

ምሳሌ 3: They hadn't read the book yet.

ምሳሌ 4: Hadn't the man done the work yet?
Past Perfect Continuous: ምንድን ይሰራል?

ጥቅም: ቆይቶ የጀምረ እና አሁን ያለቀን ነገር ለመናገር፤

ቀመር: subject + had + been + V1 + ing + object

ምሳሌዎች:

1. He had been playing football for a while.
2. She hadn't been planning for the project.
3. Had they been studying for the exam?
4. Hadn't we been ready for the emergency?
"Future simple tense" ምንድን ይሰራል?

ጥቅም: ወደፊት ላይ የሚሆንን ነገር ለመናገር፤

ቀመር: subject + will + V1 + object

ምሳሌዎች:

1. He will play football tomorrow.
2. She will plan for the project.
3. Will they study for the exam?
4. Won't we prepare for the emergency?
"Future continuous tense" ምንድን ይሰራል?

ጥቅም: ወደፊት ላይ ረዘም ያለ ጊዜን ወስደው የሚደረጉ/የማይደረጉ ነገሮችን ለመናገር ወይም ለመጠየቅ እንጠቀማለን።

ቀመር: subject + will + be + V1+ing + object

ምሳሌዎች:

1. He will be playing football tomorrow.
2. She will be planning for the project.
3. Will they be studying for the exam?
4. Won't we be preparing for the emergency?
"Future perfect continuous tense" ምንድን ይሰራል?

ጥቅም: በፊት ላይ ተጀምረዉ ወደፊት ላይም የሚቀጥሉ/የማይቀጥሉ ነገሮችን ለመናገር ወይም ለመጠየቅ እንጠቀመዋለን፤

ቀመር: subject + will +have+ been + V1+ing + object

ምሳሌዎች:
1. He will have been playing football for two hours by the time you arrive.

2. She will not have been planning the project for a week by next week.

3. Will they have been studying for the exam for a month by next month?

4. Will we not have been preparing for the emergency for several days by tomorrow?
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አረፍተ ነገር ምንድን ነዉ?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/oH9ytlqcpGA?si=GSLHiUoOMZCNMRRM
"Active” እና “passive” ልዩነታቸዉ ምንድን ነዉ?

Active voice: ማለት ስለ ድርጊት ፈፃሚዉ ለማጉላት የምንጠቀመዉ አረፍተ ነገር ነዉ።

ምሳሌ: She had been studying math.

አዚህ ጋር ስለአጥኚዋ ማለትም ስለ እሷ(She) ነዉ ለማጉላተ የተፈለገዉ።

Passive voice: ማለት ስለ ድርጊት የተፈፀመበት አካል ለማጉላት የምንጠቀመዉ አረፍተ ነገር ነዉ።

ምሳሌ: Math had been being studied by her.

አዚህ ጋር ስለተጠናዉ ማለትም ስለ "Math" ነዉ ለማጉላተ የተፈለገዉ።
Verb" ምን ማለት ነዉ?

Verb: ማለት ግስ ማለት ሲሆን ጠቀሜታዉ ድርጊትን በተለያዩ ጊዜዎች ዉስጥ ማሳየት ነዉ።

"Verbs" የተለያየ ጊዜን ሲገልፁ፤

Verb1    Verb2    Verb3
play/s   played   played
eat         ate         eaten
study     studied studied

በመጨረሻ
Verb 1: ድግግሞሽን ለመናገር፣
Verb 2: ያለፈ ጊዜ ላይ የተደረገ ነገርን ፣ እና
Verb 3: ከድርጊት በፊት የተደረገ ድርጊትን ለመናገር  እንጠቀማቸዋለን።
"Nouns" ምንድን ናቸው?

Noun: ማለት ስሞች የምንላቸው ሲሆኑ ስራቸው የሰዎችን, የቦታ, የነገሮች, የእንስሶች እና የሃሳቦች መጠሪያ እና መለያ ማሳየት ነው።

የሰዎች፦ Abebe, Father, Mother, Doctor...

የቦታዎች፦ Hospital, School, Addis Ababa...

የነገሮች፦ Chair, Table, Money...

የእንስሳት፦ Elephant, Lion, Cat, Hippopotamus...

የሃሳቦች፦ Stoicism, Confucianism, Taoism...
"Verb" ምን ማለት ነዉ? አይነቱስ?

Verb: ማለት ግስ ማለት ሲሆን ጠቀሜታዉ ድርጊትን በተለያዩ ጊዜዎች ዉስጥ ማሳየት ነዉ።

"Verbs" አይነት እና ጠቀሜታ አላቸዉ እነሱም፦

Auxiliar Verbs: አጋዥ ግሶች የምንላቸዉ ናቸዉ ዋነኞቹ፤

   Have=> have,has & had
   Be=>is, am, are ,was, were, be, been, & being
   Do=> do,does, & did

Modal Verbs: ፈቃድ፣ የመሆን እድልን፣ አስፈላጊነትን፣ እና ብቃትን  ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን፤

እነሱም ፦ can, could, shall, should, will, would, have to, ought to, & need to...

Transitive verbs: ካለ ድርጊት የተፈፀመበት አካል መቅረብ የማይችሉ ግሶች ናቸዉ፤

ምሳሌ፦ He plays football.

እዚህ ጋር "plays"=>"Transitive verb" ነዉ ምክንያቱም ደግሞ የተሻገረበት ድርጊት የተፈፀመበተ አካል ቀጥሎ ስለኖረዉ ነዉ።

Intransitive verbs: ካለ ድርጊት የሚፈፀምበት አካል መቅረብ የሚችሉ የግስ አይነቶች ናቸዉ፤

ምሳሌ፦The water boils.

እዚህ ጋር "boils" =>"Intransitive Verb" ነዉ ምክንያቱም ደግሞ የተሻገረበተ ድርጊት የተፈፀመበት አካል ባለመኖሩ ነዉ።
👍1
"Auxiliar Verbs" ምንድን ናቸዉ?

Auxiliar Verbs: አጋዥ ግሶች የምንላቸዉ ናቸዉ ዋነኞቹ፤

   Have=> have,has & had.
   Be=>is, am, are ,was, were, be, been, & being.
   Do=> do,does, & did.

Have: እና አይነቶቹን ብዙዉን ጊዜ ከ "Verb3" ጋር የ"Perfect Tense" መሆኑን ለማሳየት ትጠቀሙታለቸሁ፤

ምሳሌ፦ Have you finished yet.

Is: እና አይነቶቹን ብዙዉን ጊዜ ከ "Verb+ing" ጋር የ "Continuous Tense" መሆኑን ለማሳየት ትጠቀሙታለቸሁ፤

ምሳሌ፦ he is studying Math.

Do: እና አይነቶቹን ብዙዉን ጊዜ ከ "Verb1" ጋር የ "Simple Tense" መሆኑን ለማሳየት ትጠቀሙታለቸሁ፤

ምሳሌ፦ Do you like to play?
👍1