የአብስራ
503 subscribers
223 photos
782 videos
183 files
1.21K links
ሰሚት ከንዶሚንየም ሆነው አስጠኚ ከፈለጉ እና የአንድ ሳምንት ነፃ ሙከራን ጨምሮ ለማግኘት በስልክ ቁጥር:- 09-38-58-75-08 ላይ በመደወል ወይም በቴሌግራም @committed12 በመጫን ያገኙኛል።

ለተማሪዎች ተጨማሪ ድጋፍ የሚሆን
ነፃ የተንቀሳቃሽ ምሰል ማብራሪያዎች እዚህ ተጭናችሁ ታገኛላሁ:- https://youtube.com/@yabserawondewosen?si=M3rU1wnXO8__6RBx
Download Telegram
Tense በእውነት ከባድ ነው? 🤔

ማስታወሻ፦https://t.me/YWTutorial/2111
🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Tense በእውነት ከባድ ነው? 🤔

በ Youtube ለመመልከት፦https://youtu.be/uQmGIPtrAvE?si=RvZv7mOsP_xUxswN
Conditional ከባድ ነዉ?

አዋ! ያለ ማን ነዉ?
አይታችሁ ለምን አትፈርዱም፦

0 Conditional- እዉነታ(if v1,v1)
1st Conditional- የሚሆን(if v1,will v1)
2nd Conditional- የማይሆን(if v2, would v1)
3rd Conditional- ፀፀት(if had v3, would have v3)

ምኑ ነዉ ከባድ?
#commingsoon@YWTutorial
👏1
Conditional በእውነት ከባድ ነው? 🤔

"ይህ ቢሆን ኖሮ ያ ይሆን ነበር" ብሎ ማሰብ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ነው። በእንግሊዝኛ ቋንቋም Conditional የምንለው አንድ ነገር ለመከሰት ሌላ ነገር "ቅድመ ሁኔታ" ሆኖ ሲገኝ ነው።

ለምን ስለ Conditional ማወቅ አስፈለገን?

ኮንዲሽናልን ማወቅ ማለት የንግግራችሁን "ጥራት" እና "ግልጽነት" በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ማለት ነው። ለምሳሌ፦

* ምኞትንና እቅድን ለመግለጽ፦ የነገ እቅዳችሁን ወይም የትላንት ፀፀታችሁን በትክክል ለሰው ለማስረዳት።
     * በእቅድ ጊዜ፦ "ዝናብ ከዘነበ፣ ጉዟችንን እንሰርዛለን" (1st Conditional) በማለት ለሌሎች ግልጽ መረጃ ትሰጣላችሁ።
   * ከስህተት ለመማር፦ "ያን ጊዜ ተጠንቅቄ ቢሆን ኖሮ፣ ይሄ አይፈጠርም ነበር" (3rd Conditional) ብላችሁ ባለፈው ስህተት ላይ ትክክለኛውን ፀፀት ትገልጻላችሁ።

* ​ምክንያትና ውጤትን ለማሳየት፦ ሳይንሳዊ እውነታዎችን ወይም ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ለመተንበይ።

* ​ውሳኔ ለመስጠት፦ አማራጮችን አመዛዝኖ ለመናገር መሠረቱ ይሄው (Conditional) ነው።

የ Conditional (ሁኔታዊ ዓረፍተ ነገሮች) ዝርዝር አንድ ዓይነት ምሳሌ (ማጥናትና ማለፍን) በመጠቀም፣ አራቱንም አይነቶች እንደ የመሆን እድላቸው (Probability) እንያቸው፦

0. Zero Conditional (እውነታ)

ሁልጊዜ እውነት ለሆኑ ነገሮች ወይም ለሳይንሳዊ እውነታዎች።
* ምሳሌ፦ If you study, you pass.
* ትርጉም፦ ካጠናህ፣ ታልፋለህ። (ይህ አጠቃላይ እውነት ነው፤ ጥናት ሁሌም ወደ ማለፍ ይመራል)።
* ማስታወሻ፦ Structure: If + V1, V1

1st. First Conditional (የሚሆን - እድል ያለው)

ወደፊት ሊከሰት የሚችልን እውነተኛ እድል ወይም እቅድን ለማሳየት ነው።
* ምሳሌ፦ If you study, you will pass.
* ትርጉም፦ አሁን ካጠናህ፣ ወደፊት (በፈተናው) ታልፋለህ / የማለፍ እድል ይኖርሃል።
* ማስታወሻ፦ ድርጊቱ ገና ስላልተከናወነ Will እንጨምራለን።
   * Structure: If + V1, will + V1

2nd. Second Conditional (የማይሆን - ምናባዊ)

አሁን ባለንበት ሁኔታ የማይሆንን ወይም በምኞት ብቻ ያለን ነገር ለመግለጽ ነው።
* ምሳሌ፦ If you studied, you would pass.
* ትርጉም፦ ብታጠና ኖሮ፣ ታልፍ ነበር። (ግን አሁን እያጠናህ አይደለም፤ የማለፍ እድሉም የለም)።
* ማስታወሻ፦ የማይሆንን ነገር ስለሆነ ግሱን ወደ V2 (Past) እንቀይረዋለን።
   * Structure: If + V2, would + V1

3rd. Third Conditional (ፀፀት - ያለፈ ታሪክ)

ባለፈ ጊዜ ውስጥ ያልተደረገን ነገር እና የነበረውን ውጤት ለመግለጽ።
* ምሳሌ፦ If you had studied, you would have passed.
* ትርጉም፦ አጥንተህ በነበረ ኖሮ፣ አልፈህ ነበር፤ ግን ስላላጠናህ አላለፍክም። (ሙሉ በሙሉ ያለፈና የማይቀየር ፀፀት)።
* ማስታወሻ፦ Structure: If + had V3, would have V3

💡 የአረፍተ ነገር መዋቅር (Structure)
​በእነዚህ አረፍተ ነገሮች ውስጥ የምንከተለው መሠረታዊ መዋቅር፦

If + Condition (ሁኔታው) + Result (ውጤቱ)

Condition: ድርጊቱ እንዲፈጸም መሟላት ያለበት ነገር።
Result: ሁኔታው ከተሟላ የሚመጣው ውጤት።

>  * Subject + Verb + Object መዋቅሩን እዚህም አንረሳውም!
* ምሳሌ፦ If you (S) + study (V) + the book (O), you (S) + will pass (V) + the exam (O).

ማሳሰቢያ፦ የዓረፍተ ነገሩን ቅደም ተከተል መቀየር ይቻላል። ለምሳሌ፡ You will pass if you study. (መሃል ላይ "if" ሲገባ ኮማ አያስፈልግም)።

​ታዲያ ምኑ ላይ ነው ከባዱ?

​አንዱን ቅርፅ (Structure) ከሌላው ጋር እንዳታቀላቅሉ "ሎጂኩን" መረዳት ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ።
0 = 100% እውነታ
1st = ሊሆን የሚችል (50/50)
2nd = ህልም/ምኞት (0%)
3rd = ያለፈ ታሪክ/ፀፀት

@YWTutorial
👏1
Conditional በእውነት ከባድ ነው? 🤔

ማስታወሻ፦https://t.me/YWTutorial/2116
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Conditional በእውነት ከባድ ነው? 🤔

ቪድዮ፦https://youtu.be/iHDhvkZmc1s?si=1-Yzyd3lxe3BTUzN
Active to Passive በጣም ከባድ ነዉ!😱

የሚሉ ብዙዎች ናቸዉ🙅‍♂፤ እኔ ግን አለመረዳት ነዉ ብዬ አስባለዉ፤ ምክንያቱም፦ ልዩነቱ ያለው ትኩረታቸዉ እና አቀማመጣቸዉ ላይ በመሆኑ ነዉ።

መሠረታዊ ቀመራቸዉ
Active: Subject + Verb + Object
Passive: Object + Be (Verb) + Verb 3 (Past Participle)

​በጥቅም ላይ ሲዉሉ፦
Active: He eats lunch. (እሱ ምሳ ይበላል።)
Passive: Lunch is eaten. (ምሳዉ ይበላል።)

አቀማመጥ እና ትኩረታቸዉ!👆
ታዲያ ምኑ ነው ከባድ?

#commingsoon@YWTutorial
Active to Passive ከባድ ነዉ?

ብዙ ሰዎች "Active እና Passive voice ግራ ያጋባል" ይላሉ። እኔ ግን ችግሩ ያለው ከባድነቱ ላይ ሳይሆን፣ ጥቅሙንና አጠቃቀሙን በሚገባ አለመረዳት ነው ብዬ አስባለሁ። እስቲ ሰፋ አድርጋችሁ እዩት፦

ለምን ስለ Passive Voice ማወቅ አስፈለጋችሁ?

የቋንቋውን ትኩረት የመቀየር ጥበብ 🎯
Active Voice ስትጠቀሙ ትኩረታችሁ ድርጊቱን አድራጊው ላይ ነው። Passive Voice ስትጠቀሙ ግን ትኩረታችሁ ድርጊቱ የተፈጸመበት ነገር ላይ ይሆናል። ይህ ለምን ይጠቅማችኋል?

* ድርጊቱ ከአድራጊው በላይ ሲያመዝን፦ ለምሳሌ "አዲሱ ድልድይ ተመረቀ" ለማለት ብትፈልጉ፣ የመረቀው ሰው ስም ባይታወቅም የምረቃው ዜና ራሱ ትርጉም አለው።

* አድራጊው ሳይታወቅ ሲቀር ወይም ግልጽ ካልሆነ፦ ለምሳሌ "መንገዱ ተጠርጓል" ስትሉ፣ መንገዱ መጽዳቱ እንጂ ማን እንደጠረገው መግለጽ ላያስፈልጋችሁ ይችላል።

* ለፕሮፌሽናል አጻጻፍ፦ በቢዝነስ ሪፖርቶች፣ በዜናዎችና በሳይንሳዊ ምርምሮች ላይ Passive Voice ንግግራችሁን የሰለጠነና ሚዛናዊ (Objective) ያደርገዋል።

መሠረታዊ መዋቅሮቹ (General Formulas)

ወደ ዝርዝሩ ከመግባታችን በፊት ሁለቱን የዓረፍተ ነገር ግንባታዎች እናወዳድር፦
* Active Formula: Subject + Verb + Object
   (አድራጊ + ድርጊት + ተሳቢ)

* Passive Formula: Object + Be Verb (am/is/are/was/were...) + Verb 3 (Past Participle)
   (ተሳቢ + ረዳት ግስ + ድርጊቱ በ 3ኛው ቅርጽ)

የለውጥ ሂደቱ በዝርዝር (Step-by-Step)

አንድን ዓረፍተ ነገር ወደ Passive ለመቀየር እነዚህን 3 ደረጃዎች መከተል ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ፦
* ተሳቢውን (Object) ወደ ፊት ማምጣት፦ በአረፍተ ነገሩ መጨረሻ የነበረውን ነገር መጀመሪያ ላይ አድርጉት።
* ተገቢውን "Be" ግስ መጠቀም፦ እንደ ቴንሱ ዓይነት (am, is, are, was, were, been, being) መርጣችሁ አስገቡ።
* ዋናውን ግስ ወደ V3 መቀየር፦ ግሱ ምንም ይሁን ምን ወደ 3ኛው ቅርጽ (Past Participle) ቀይሩት።

በስምንቱም ቴንሶች የተሰሩ ምሳሌዎች
አንድ ወጥ ምሳሌ (The house) በመጠቀም ልዩነቱን በእያንዳንዱ ቴንስ ውስጥ ተመልከቱ፦


1. Present Simple
* Active: He builds the house.
* Passive: The house is built. (ቤቱ ይገነባል።)

2. Present Continuous
* Active: He is building the house.
* Passive: The house is being built. (ቤቱ እየተገነባ ነው።)

3. Present Perfect
* Active: He has built the house.
* Passive: The house has been built. (ቤቱ ተገንብቶ አልቋል።)

4. Past Simple
* Active: He built the house.
* Passive: The house was built. (ቤቱ ተገነባ።)

5. Past Continuous
* Active: He was building the house.
* Passive: The house was being built. (ቤቱ እየተገነባ ነበር።)

6. Past Perfect
* Active: He had built the house.
* Passive: The house had been built. (ቤቱ ተገንብቶ ነበር።)

7. Future Simple
* Active: He will build the house.
* Passive: The house will be built. (ቤቱ ይገነባል።)

8. Future Perfect
* Active: He will have built the house.
* Passive: The house will have been built. (ቤቱ ተገንብቶ ያልቃል።)

ታዲያ ይሄ ምኑ ነው ከባድ?!

ልዩነቱ ያለው ትኩረታችሁ ላይ ብቻ ነው።
"ማን አደረገው?" ከሚለው ወጥታችሁ "ምን ተደረገ?" ወደሚለው ስትመጡ ዓረፍተ ነገሩ በራሱ ጊዜ Passive ይሆናል። ይህንን መለማመድ ንግግራችሁን ይበልጥ ግልጽና ፕሮፌሽናል ያደርገዋል።

ማሳሰቢያ፦ አድራጊውን መጥቀስ ከፈለጋችሁ መጨረሻ ላይ "by + Subject" መጨመር ትችላላችሁ። (ለምሳሌ፦ The house was built by him.)

@YWTutorial
👏2
Forwarded from የአብስራ
Active to Passive ከባድ ነዉ?

ማሶታወሻ፦https://t.me/YWTutorial/2120
ሰሚት አካባቢ ሆነው አስጠኚ ከፈለጉ እና የአንድ ሳምንት ነፃ ሙከራን ጨምሮ ለማግኘት  በስልክ ቁጥር፦ +2519-38-58-75-08 ተጭነው በመደወል ወይም በቴሌግራም @committed12 ላይ የፅሁፍ መልክት በመፃፍ ያገኙኛል።
Direct to Indirect በጣም ከባድ ነዉ!

የሚሉ ብዙዎች ናቸዉ፤ እኔ ግን አለመረዳት ነዉ ብዬ አስባለዉ፤ ምክንያቱም ልዩነቱ ያለው የጊዜ (Tense) አንድ እርምጃ ወደ ኋላ መመለስ ላይ ብቻ ነው።

መሠረታዊ ቀመሮቹ (General Formulas):
Direct: Subject + says, "I + Verb 1 + Object"
Indirect: Subject + said (that) + He/She + Verb 2 + Object

ታዲያ ምኑ ነው ከባድ?

Direct: He said, "I eat lunch."
Indirect: He said that he ate lunch.
ምስጢሩ፦
አንድ ሰው የተናገረው ነገር አሁን "ያለፈ ታሪክ" ስለሆነ፣ ግሱን አንድ እርምጃ ወደ ኋላ (ወደ Past) መውሰድ ብቻ ነው!
​ታድያ ይሄ ምኑ ነዉ ከባድ?!
#ComingSoon @YWTutorial
Direct to Indirect Speech ከባድ ናቸዉ?!

ክፍል አንድ (Part 1)፦ የቴንስ ለውጦች

Direct to Indirect Speech: በሌላኛዉ ስሙ የሰሙትን የማስተላለፍ ጥበብ 🗣️ ምንለዉ ማለት ነዉ፤ እንደምታስቡት ከባድ አይደለም፤ ምክንያቱም ልዩነቱ ያለው ጊዜውን አንድ እርምጃ ወደ ኋላ መቀየር ላይ ብቻ ስለሆነ ነው። ይህንን ማወቃችሁ የሰማችሁትን መረጃ ሳታዛቡ ለሌላ ሰው በልበ ሙሉነት እንድታስተላልፉ ይረዳችኋል።

በመቀጠል... ይህንን እናስተውል (Structure)
አንድ ሰው የተናገረውን ንግግር ለሌላ ሰው ስታስተላልፉ የምትከተሉት መሠረታዊ ቀመር ይህ ነው፦
* Direct: Subject + said, "I + Verb (Present) + Object"
* Indirect: Subject + said (that) + He/She + Verb (Past) + Object

በሁሉም 12 ቴንሶች የተሰሩ ምሳሌዎች
አንድ ወጥ ምሳሌ ("I work") በመጠቀም ቴንሱ እንዴት ወደ ኋላ እንደሚመለስ በዝርዝር እንመልከት፦


1. Present Simple → Past Simple
* Direct: "I work hard."
* Indirect: He said that he worked hard.

ማስታወሻ፦ሁሉም እና ሁሌም ከ direct ወደ Indirect ስንቀይር የመልእክት አስተላላፊዉ ስለሚቀየር ዋና ተናጋሪዉን እሱ/እሷ አያልን መጠሪያቸዉን እንቀይራለን፤ በተጨማሪም አንድ ወደኋላ ጊዜዉን በድርጊት ቃሉ(ግሱ) እንቀይራለን እዚህ ጋር work ወደ worked እንደተቀየረዉ ማለት ነዉ።

2. Present Continuous → Past Continuous
* Direct: "I am working hard."
* Indirect: He said that he was working hard.

ማስታወሻ፦ Verb to be ከ present  ወደ past ስትቀይሩ አንድ ለሆነ ባለቤት is  ትጠቀሙ ከነበረ ወደ was ትቀይሩታላቸሁ ብዙ ከሆኑ ደግሞ are ወደ were ይቀየራል፤

3. Present Perfect → Past Perfect
* Direct: "I have worked hard."
* Indirect: He said that he had worked hard.

ማስታወሻ፦present perfect ላይ have/has የነበረዉ ደግሞ Indirect ላይ ወደ had ይቀየራል(ለሁለቱም አንድ አይነት ነዉ)።

4. Present Perfect Continuous → Past Perfect Continuous
* Direct: "I have been working hard."
* Indirect: He said that he had been working hard.

ማስታወሻ፦ have ወደ had ከተቀየረ በኋላ been እንደነበረ ቀጥሏል V1+ing ያለዉ ግስም እንደነበረ ይቀጥላል።

5. Past Simple → Past Perfect
* Direct: "I worked hard."
* Indirect: He said that he had worked hard.

ማስታወሻ፦ worked የነበረዉ ወደ had worked ተቀይሯል፤ ከ had ቀጥሎ ሁሌም የሚገባዉ V3 ነዉ።

6. Past Continuous → Past Perfect Continuous
* Direct: "I was working hard."
* Indirect: He said that he had been working hard.

ማስታወሻ፦ was ወደ had been ከተቀየረ በኋላ V1+ing እንደነበረ ቀርቷል።

7. Past Perfect → Past Perfect (አይቀየርም)
* Direct: "I had worked hard."
* Indirect: He said that he had worked hard.

ማስታወሻ፦  የተቀየረዉ ነገር I ወደ he ብቻ ነዉ እሱም የተናገረዉ(አዲስ አስተላላፊ) ሰዉ ስለተቀየረ ነዉ።

8. Past Perfect Continuous → (አይቀየርም)
* Direct: "I had been working hard."
* Indirect: He said that he had been working hard.

ማስታወሻ፦had ብሎ V3  ካለ ከአስተላላፊዉ ዉጪ የሚቀየር ነገር የለም።

9. Future (Will) → Would
* Direct: "I will work hard."
* Indirect: He said that he would work hard.

ማስታወሻ፦will ወደ would ተቀየረ።

10. Future Continuous (Will be) → Would be
* Direct: "I will be working hard."
* Indirect: He said that he would be working hard.

ማስታወሻ፦ will ወደ would ከተቀየረ በኋላ be working ምንም ለዉጥ ሳይኖረዉ ቀጠለ።

11. Future Perfect (Will have) → Would have
* Direct: "I will have worked hard."
* Indirect: He said that he would have worked hard.

ማስታወሻ፦ will have ወደ would have ተቀየረ።

12. Future Perfect Continuous → Would have been
* Direct: "I will have been working hard."
* Indirect: He said that he would have been working hard.

ማስታወሻ፦ will have been ወደ would have been ይቀየራ፤ ቀጥሎ ያለዉ V1+ing እንደነበረ ይቀጥላል።

አጠቃላይ ማስታወሻ ፦ indirect ላይ አስተላላፊ እንጂ ተናጋሪ የለም፤ direct ላይ ነዉ የተናጋሪዉ የራሱ ንግግር የሚደገመዉ፤ ሁለቱም የተባለዉን አስተላላፊ ቢሆኑም።

ክፍል-2ን በቅርቡ ጠብቁ!

@YWTutorial
2
Direct to Indirect Speech ከባድ ናቸዉ?!

ማስታወሻ፦https://t.me/YWTutorial/2124

የኔ ስራዎች፦https://t.me/YWTutorial/2083?single
Much vs Many፡ ምኑ ነው ከባዱ? 🤔

ብዙዎቻችን እንሳሳታለን፤ ግን ምስጢሩ ያለው "s" ላይ ብቻ ነው!

1. የ "s" ደንብ (Countable)
ቃሉ መጨረሻ ላይ "s" ካለው የሚቆጠር ነው፤ ስለዚህ Many ወይም Few ተጠቀሙ።
* Many books, Many friends.
* ልዩ ሁኔታ፦ People, Men, Children (s ባይኖራቸውም ይቆጠራሉ!)።

2. የ "s " ደንብ (Uncountable)
ቃሉ መጨረሻ ላይ "s" ከሌለው (ፈሳሽ፣ ጊዜ፣ ገንዘብ) Much ወይም Little ተጠቀሙ።
* Much water, Much time, Much money.
* ልዩ ሁኔታ፦ Information, Advice, News (ፈሳሽ ባይሆኑም አይቆጠሩም!)።

3. የ "A" ምስጢር (Few vs A few)
* A few / A little = ጥቂት ግን በቂ (አዎንታዊ 👍)
* Few / Little = በጣም ጥቂት / አይበቃም (አሉታዊ 👎)

4. ለሁለቱም (Double Play)
A lot of እና Some ለሚቆጠርም ለማይቆጠርም ይሰራሉ!
* A lot of cars (s አለው - )
* A lot of water (s የለውም - )

ማጠቃለያ፦
* Any = ለጥያቄና ለ "Not"
* Too = ለ "Much/Many" (ከመጠን በላይ)
* Very = ለ "Few/Little" (በጣም ጥቂት)

ታዲያ ይሄ ምኑ ነው ከባድ?! ቃሉን አይታችሁ "s" ካለው Many፣ ከሌለው Much መምረጥ ብቻ ነው!

#commingsoon@YWTutorial
6
ለምንድን ነዉ እናንተ ስታዉቁ ለሌላዉ የማታጋሩት?

የመረዳዳት ባህላችን እዚህ ስንመጣ ከፍ ሊል እንጂ እኮ ሊያንስ አይገባዉም፤ እኛ ስናዉቅ ጓደኛችንም ቢያዉቅ ከእኛ ብቻ እዉቀት ወደ ሁለት ሰዎች እዉቀት... ይህ ሲኖር ተግባቦት ያድጋል፣ በማህላችን የመረዳዳት የባህል ያድጋል ይህም እናንተን እንደሰዉ ያበረታል እናም አንድ የአሸናፊ ቡድን አባል ያደርጋችኋል፤

አለበለዚያ አንዳችን አንዳችንን ለመርዳት መሰላል ካልሆንን ሌላ እንዲረዳን መጠበቅ ህልም ሳይሆን ቅዠት ነዉ፤ ጥሩነትን እናንተ መተግበር ካልጀመራችሁ ሌላ ሰዉ እንዲጀምረዉ መጠበቅ ሞኝነት ነዉ፤ ያላደረጋችሁትን ነገር እንዲደረግላችሁ አጠብቁ።

ሌላ እንዲጀምረዉ ለናንተ እንዲያደርገዉ አጠበቁ እናንተ ጀምሩት አሁን ወዲያዉ ባይመለስላችሁ ባይደረግላችሁ እንኳ ጠቃሚ ሰዎችን ሊረዱ የሚችሉ ነገሮችን የማጋራት ባህሉን  መጀመሩ ታላቆች ያደርገናል ብዬ አምናለዉ።

ስታዉቁ አሳዉቁ ይበልጥ እንድታዉቁ።

እወዳችኋለዉ የሃገሬ ሰዎች!

- የአብስራ
2
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
ታይተዉ የማይታወቁ ቀላሎቹ.pdf
246.6 KB
ታይተዉ የማይታወቁ ቀላሎቹ የ"Tense"ሶች አሰራር፤ ከነትገበራቸዉ። (መፅሃፍ በፅሁፍ መልክ)


በመጀመሪያ መፅሃፋን ይክፈቱ ፤

በመቀጠል የመፅሃፋን የድምፅ ንባብ በመክፈት ማድመጡን እና ንባቡን አንድ ላይ ያድርጉአቸዉ ፤

ማስተወሻ እያነበቡ ያሉትን ነገር ማድመጥ የማስታወስ ብቃትዎን ይጨመራል

በስተመጨረሻ ማንኛዉም አይነት ከመፅሃፉ ጋራ  የተያያዘ ችግር ከገጠማችሁ በ0938587508 በመደወል ታገኙኛላችሁ።

መልካም ጊዜ!

- የአብስራ
4👏1
ታይተዉ የማይታወቁ ቀላሎቹ የ"Tense"ሶች አሰራር፤ ከነትግበራዉ።
የግል የጥናት ማዕከል
ታይተዉ የማይታወቁ ቀላሎቹ የ"Tense"ሶች አሰራር፤ ከነትገበራቸዉ። (መፅሃፍ በንባብ መልክ)


በመጀመሪያ መፅሃፋን ይክፈቱ ፤

በመቀጠል የመፅሃፋን የድምፅ ንባብ በመክፈት ማድመጡን እና ንባቡን አንድ ላይ ያድርጉአቸዉ ፤

ማስተወሻ እያነበቡ ያሉትን ነገር ማድመጥ የማስታወስ ብቃትዎን ይጨመራል

በስተመጨረሻ ማንኛዉም አይነት ከመፅሃፉ ጋራ  የተያያዘ ችግር ከገጠማችሁ በ0938587508 በመደወል ታገኙኛላችሁ።

መልካም ጊዜ!

- የአብስራ
3
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
የ_Conditional_አረፍተ_ነገሮች_ቀላል_ጥያቄ_አሰራር_ቀመር_አላቸዉ_1.pdf
251 KB
የ"Conditional" አረፍተ ነገሮች
ቀላል ጥያቄ አሰራር ቀመር
አላቸዉ? አዎን።

በቀላሉ የምስል ማብራሪያዉን እና ንባቡን ለማግኘት፦https://youtu.be/JFglsCpfj_k?si=44WwNZVjXwS2L-w0
👏1
የMany እና Much ልዩነት ምንድን ነዉ?


ብዙዎች "Much" እና "Many" ይደባለቁባቸዋል። እኔ ግን ልዩነቱ ያለው ነገሩ ይቆጠራል ወይስ አይቆጠርም የሚለው ላይ ብቻ ስለሆነ ቀላል ነው ብዬ አስባለሁ፤

እነዚህ በአጠቃላይ ስማቸዉ "Quantifiers" የምንላቸዉ ሲሆኑ ለሚቆጠር እና ለማይቆጠርም ሳትለዩ ለሁለቱም አይነት ልትጠቀሟቸዉ የምትችሏቸዉም አይነቶች አሉ፤
እያንዳንዳቸዉን ከገለፃ፣ ምሳሌ እና ከጥያቄ አሰራራቸዉ ጋር የምናይ ይሆናል፤ አብራችሁኝ ቆዩ።

ለምን ይህን ማወቅ አስፈለጋችሁ?

ትክክለኛውን መጠን ለመግለጽ እና ንግግራችሁ ሰዋሰዋዊ ስህተት እንዳይኖረው ይረዳችኋል።

ለምሳሌ "ብዙ ገንዘብ" ለማለት "Many money" ካላችሁ ስህተት ነው።

Quantifiers: የሚቆጠሩ እና የማይቆጠሩ ስሞች ማጠቃለያ 📝

በእንግሊዝኛ ቋንቋ የነገሮችን መጠን ለመግለጽ የምንጠቀምባቸው ቃላት (Quantifiers) በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ። አንድ ስም መጨረሻው ላይ "s" ካለው የሚቆጠር መሆኑን በቀላሉ መለየት ትችላላችሁ።

1. ለሚቆጠሩ ስሞች ብቻ (Countable Only)
እነዚህ ቃላት የሚጠቅሙት መጨረሻቸው ላይ "s" ሊኖራቸው ለሚችሉ ቃላት ብቻ ነው (ለምሳሌ፦ Books, Pens, Friends)።
 * Many (ብዙ)፦ ለብዙ ቁጥር ያገለግላል።
 * Few (ትንሽ)፦ በጣም አነስተኛ ለሆነ ቁጥር ያገለግላል።
   * ምሳሌ፦ Many books, Few pens.

2. ለማይቆጠሩ ስሞች ብቻ (Uncountable Only)
እነዚህ ቃላት የሚጠቅሙት መጨረሻቸው ላይ "s" ለሌላቸው ድፍን ሃሳቦች፣ ፈሳሾች ወይም ስብስቦች ነው (ለምሳሌ፦ Water, Time, Money, Sugar)።
 * Much (ብዙ)፦ ለብዙ መጠን ያገለግላል።
 * Little (ትንሽ)፦ በጣም አነስተኛ ለሆነ መጠን ያገለግላል።
   * ምሳሌ፦ Much time, Little money.

3. ለሁለቱም የሚሆኑ (For Both)
እነዚህ ቃላት ለሚቆጠሩትም ለማይቆጠሩትም ያገለግላሉ።
 * A lot of (ብዙ)፦ ለሁለቱም አይነት ስሞች "ብዙ" ለማለት ያገለግላል።
 * Some (ጥቂት/የተወሰነ)፦ ለሁለቱም አይነት ስሞች "የተወሰነ" ለማለት ያገለግላል።
   * ምሳሌ፦ A lot of friends (Countable), A lot of water (Uncountable).
ዋና ዋና የአጠቃቀም ደንቦች (Important Rules)
 * Some እና A lot ofን ስትጠቀሙ Not/Too/Very የሚሉ ቃላትን አብራችሁ አትጠቀሙ።
 * Very የሚለውን ቃል መጠቀም የምትችሉት ከ Few እና Little ጋር ብቻ ነው (ለምሳሌ፦ Very few books, Very little water)።
 * Too የሚለውን ቃል መጠቀም የምትችሉት ከ Many እና Much ጋር ብቻ ነው (ለምሳሌ፦ Too many cars, Too much sugar)።
 * Any የሚለውን ቃል ለጥያቄ ወይም "Not" ላለባቸው አሉታዊ ዓረፍተ ነገሮች ብቻ ተጠቀሙ።


ምሳሌዎች (Examples)
 * Many books: መጽሐፍ ስለሚቆጠር "Many" እንጠቀማለን።
 * Few pens: እስክሪብቶ ስለሚቆጠር "Few" እንጠቀማለን።
 * Too much time: ጊዜ ስለማይቆጠር "Much" እንጠቀማለን።
 * Little money: ገንዘብ (እንደ ድፍን ሃሳብ) ስለማይቆጠር "Little" እንጠቀማለን።

ዋና ዋና ደንቦች (Key Rules)

 * Some እና A lot ofን ስትጠቀሙ Not/Too/Very የሚሉ ቃላትን አትጨምሩ።
 * Much እና Little የሚጠቅሙት ለማይቆጠሩ ነገሮች ብቻ ነው።
 * Many እና Few የሚጠቅሙት ለሚቆጠሩ ነገሮች ብቻ ነው።
 * Very የሚለውን ቃል ከ Few ወይም Little ጋር መጠቀም ትችላላችሁ (ለምሳሌ፦ Very few, Very little)።
 * Too የሚለውን ቃል ከ Much ወይም Many ጋር መጠቀም ትችላላችሁ (ለምሳሌ፦ Too much, Too many)።
 * Any የሚለውን ቃል ለጥያቄ ወይም "Not" ላለባቸው አሉታዊ ዓረፍተ ነገሮች ተጠቀሙ።

የልምምድ ጥያቄዎች (Practice)

 * The man has a lot of friends. (ጓደኛ ስለሚቆጠርና አዎንታዊ ስለሆነ)
 * He has little time left. (ጊዜ ስለማይቆጠርና መጠኑ በጣም አነስተኛ መሆኑን ለመግለጽ)

Countable vs Uncountable Nouns: የመጨረሻ ማስታወሻ 📝

አንድ ነገር እንደሚቆጠር (Countable) ለማወቅ ቀላሉ መንገድ ቃሉ መጨረሻ ላይ "s" መያዝ መቻሉን ማየት ነው። ለምሳሌ፦ Book (አንድ) → Books (ብዙ)። መጨረሻው ላይ "s" ካለው የሚቆጠር ነው ብላችሁ መያዝ ትችላላችሁ።

የራስ መመዘኛ ጥያቄዎች (Practice Quiz)
እስቲ ከታች ያሉትን ክፍት ቦታዎች ተገቢውን Quantifier በመምረጥ አሟሉ (እያንዳንዱ ጥያቄ አንድ ትክክለኛ መልስ ብቻ ነው ያለው)።

 1. There are too __ cars on the road today.
   A) much
   B) many
   C) little
 2. I don't have __ money in my pocket.
   A) many
   B) any
   C) few
 3. We have very __ milk left; we need to buy more.
   A) few
   ) little
   C) many
 4.  She has __ of friends from school.
   A) much
   B) a lot
   C) any
 5.  How __ water do you drink every day?
   A) many
   B) much
   C) few
 6.  There are only a __ students in the classroom.
   A) few
   B) little
   C) much
 7.  He spent too __ time playing video games.
   A) many
   B) few
   C) much
 8. Do you have __ questions about the lesson?
   A) much
   B) any
   C) little
 9. I have __ sugar, but I need more for the cake.
   A) some
   B) many
   C) few
 10. There isn't __ information about the meeting.
   A) many
   B) few
   C) much

💡 ለጥያቄዎቹ ፍንጭ (Clues)

 * ጥያቄ 1 እና 6፦ "Cars" እና "Students" መጨረሻቸው ላይ "s" ስላላቸው የሚቆጠሩ ናቸው።
 * ጥያቄ 5 እና 10፦ "Water" እና "Information" ፈሳሽ እና ድፍን ሃሳብ ስለሆኑ "s" አይቀበሉም (አይቆጠሩም)።
 * ጥያቄ 2 እና 8፦ ዓረፍተ ነገሮቹ አሉታዊ እና ጥያቄ ስለሆኑ ምን መጠቀም እንዳለባችሁ አስታውሱ።

ታዲያ ይሄ ምኑ ነው ከባድ?!
ቃሉ መጨረሻ ላይ "s" ካለውና ከሌለው በመነሳት ብቻ የትኛውን ቃል እንደምትጠቀሙ መወሰን ትችላላችሁ።

ቃሉ መጨረሻ ላይ "s" ካለው Many/Few፣ ከሌለው ደግሞ Much/Little መጠቀም ብቻ ነው።

ልዩነቱ ያለው ነገሩ መቆጠሩን እና አለመቆጠሩን ለይቶ ተገቢውን ቃል መምረጥ ላይ ብቻ ነው።


@YWTutorial
5
የMany እና Much ልዩነት ምንድን ነዉ?

ማስታወሻ፦https://t.me/YWTutorial/2131

የኔ ስራዎች፦https://t.me/YWTutorial/2083?single
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የMany እና Much ልዩነት ምንድን ነዉ?

በYoutube ለመመልከት፦https://youtu.be/PmVpLSzLXPg?si=lgLt9whwHszgTZFa