የአብስራ
506 subscribers
223 photos
782 videos
183 files
1.21K links
ሰሚት ከንዶሚንየም ሆነው አስጠኚ ከፈለጉ እና የአንድ ሳምንት ነፃ ሙከራን ጨምሮ ለማግኘት በስልክ ቁጥር:- 09-38-58-75-08 ላይ በመደወል ወይም በቴሌግራም @committed12 በመጫን ያገኙኛል።

ለተማሪዎች ተጨማሪ ድጋፍ የሚሆን
ነፃ የተንቀሳቃሽ ምሰል ማብራሪያዎች እዚህ ተጭናችሁ ታገኛላሁ:- https://youtube.com/@yabserawondewosen?si=M3rU1wnXO8__6RBx
Download Telegram
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
በአንድ_ቀመር_ሁሉንም_Active_Voice_ሶች_ወደ_Passive_Voice_ሶች_መቀየር.pdf
200.6 KB
በአንድ ቀመር ሁሉንም "Active Voice"ሶች ወደ "Passive Voice"ሶች መቀየር ይቻላል? አዎን።(መፀሃፉ በፅሁፍ መልክ)

በቀላሉ መፅሃፋን በቪድዮ መልክ ለማግኘት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/T-WqtAcc2PM?si=uVeRow9OF_EyP23T
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
የ_Conditional_አረፍተ_ነገሮች_ቀላል_ጥያቄ_አሰራር_ቀመር_አላቸዉ_1.pdf
251 KB
የ"Conditional" አረፍተ ነገሮች
ቀላል ጥያቄ አሰራር ቀመር
አላቸዉ? አዎን።

በቀላሉ የምስል ማብራሪያዉን እና ንባቡን ለማግኘት፦https://youtu.be/JFglsCpfj_k?si=44WwNZVjXwS2L-w0
👍2
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የ"if conditional" ጥያቄዎችን በቀላሉ መስራት ይቻላል?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/SrpUfz-2vGk?si=-vO-p1Br9Mj4o-bd
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የነዚህን ጥቅም አለማወቅ ኢንግሊዘኛችሁን እያዳከመዉ ያለዉ አንዱ ሚስጥር ነዉ።
አዲስ አመት አዲስ ዉጤት ቻሌንጅ።

በ1 ወር ኢንግሊዘኛን የመልመድ ቻሌንጅ አዘጋጅቻለሁ።

ይህ ለ3 ቀናት ብቻ  የሚቆይ ቻሌንጅ የሚጀመረዉ መጪዉ እሁድ ሲሆን ከምንም በፊት ሞክራችሁ ልታቆሙበት የምትችሉበት የ3 ሰአት ነፃ ሙከራን ጨምሮ የያዘ ነዉ፤

እጅጉን ቀላል የሆኑ የጥያቄ አለያየት ብሎም የጥያቄዎች ቀላል መስሪያ ቀመሮችን ከመፅሃፍት እና ቪድዮዎች ጋር ታገኛላችሁ፤

በመሆኑም እነዚህን ይዛችሁ በ1ወር ወይም ከዛ ባነሰ ጊዜ ዉስጥ የትኛዉም የኢንግሊዘኛ ፈተና ላይ አመርቂ ዉጤትን ማስመዝገብ ትችላላችሁ።

ለተጨማሪ መረጃ ባዩዉ ላይ ያለዉን ስልክ በመጫን ታገኙኛላችሁ፤

ከዚህ ቀደም የፃፍኳቸዉን መፅሃፍት በነፃ ለማግኘት ባዩዉ ላይ ሊንኮች አሉ የመጀመሪያዉን በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ።
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"CVC" ምን ማለት ነዉ?
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
ቦታ እና ጊዜን ገላጭ ቃላቶች እነማን ናቸዉ?

"prepositions" - ቦታ እና ጊዜን ገላጭ ቃላቶች የምንላቸዉ ስማቸዉ እንደሚያሳየዉ እንደ አገባባቸዉ ቦታን አልያም ጊዜን ይገልፃሉ ከሁለት አንዱን በአንድ ጊዜ ማለት ሆኖ ሳለ የሚገልፁት፤

በመቀጠል ሶስቱን ዋነኞቹን ተለዋዋጭ ትርጉም ያላቸዉ የቦታ እና የጊዜ ገላጭ ቃላቶች ትርጉማቸዉ እና አጠቃቀማቸዉ እንደ አገባባቸዉ እንዴት ሊለያይ ይችላል የመለዉን  አንይ፤

ጊዜን ሲገልፁ፦
1. In:  ረዘም ያሉ ጊዜያትን ለማሳየት ትጠቀሙታላችሁ (ክፍለ ዘመናትን፣ አመትን እና ወራትን)  
   - ምሳሌ ፦ in June, in 2021, in the 21st century.
2. On: ልዩ ቀናትን እና የካላንደር ቀናትን ለማሳየት  ትጠቀሙታላችሁ፤ 
   - ምሳሌ፦ on Monday, on July 4th, on my birthday.
3. At: ትክክለኛዉን የቀኑን ጊዜ ለማሳየት እንጠቀመዋለን፤
   - ምሳሌ፦at 3 PM, at midnight, at noon.

ቦታን ተናጋሪ ሲሆኑ፦
1. In: ሰፊ ቦታዎችን ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን፤
  (ሃገር፣ ከተማ፣ ሰፊ ቦታ እና ቤት...)
   - ምሳሌ፦ in France, in New York, in the room.
2. On: መገኛዉ ከላይ እንዳለ ለማሳየት ወይም የአንድ ነገርን መገኛ በሌላ ቦታ ላይ መሆኑን ለማሳየት ትጠቀሙታላችሁ፤

   - ምሳሌ፦ on the table, on Main Street, on the bus.
3. At: ልዩ ቦታን ለማሳየት ትጠቀሙታላችሁ፤
   - ምሳሌ፦at the corner, at the bus stop, at the entrance.
1
ቦታ እና ጊዜን ገላጭ ቃላቶች እነማን ናቸዉ?

"prepositions" - ቦታ እና ጊዜን ገላጭ ቃላቶች የምንላቸዉ ስማቸዉ እንደሚያሳየዉ እንደ አገባባቸዉ ቦታን አልያም ጊዜን ይገልፃሉ ከሁለት አንዱን በአንድ ጊዜ ማለት ሆኖ ሳለ የሚገልፁት፤

በመቀጠል ሶስቱን ዋነኞቹን ተለዋዋጭ ትርጉም ያላቸዉ የቦታ እና የጊዜ ገላጭ ቃላቶች ትርጉማቸዉ እና አጠቃቀማቸዉ እንደ አገባባቸዉ እንዴት ሊለያይ ይችላል የመለዉን  አንይ፤

ጊዜን ሲገልፁ፦
1. In:  ረዘም ያሉ ጊዜያትን ለማሳየት ትጠቀሙታላችሁ (ክፍለ ዘመናትን፣ አመትን እና ወራትን)  
   - ምሳሌ ፦ in June, in 2021, in the 21st century.
2. On: ልዩ ቀናትን እና የካላንደር ቀናትን ለማሳየት  ትጠቀሙታላችሁ፤ 
   - ምሳሌ፦ on Monday, on July 4th, on my birthday.
3. At: ትክክለኛዉን የቀኑን ጊዜ ለማሳየት እንጠቀመዋለን፤
   - ምሳሌ፦at 3 PM, at midnight, at noon.

ቦታን ተናጋሪ ሲሆኑ፦
1. In: ሰፊ ቦታዎችን ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን፤
  (ሃገር፣ ከተማ፣ ሰፊ ቦታ እና ቤት...)
   - ምሳሌ፦ in France, in New York, in the room.
2. On: መገኛዉ ከላይ እንዳለ ለማሳየት ወይም የአንድ ነገርን መገኛ በሌላ ቦታ ላይ መሆኑን ለማሳየት ትጠቀሙታላችሁ፤

   - ምሳሌ፦ on the table, on Main Street, on the bus.
3. At: ልዩ ቦታን ለማሳየት ትጠቀሙታላችሁ፤
   - ምሳሌ፦at the corner, at the bus stop, at the entrance.
1
በአዲስ አመት የነፃ መአት።

ከኔ ጋር ለነበራችሁ ደንበኞቼ በሙሉ
አዲሱን አመት በማስመልከት መልካም ምኞቴን እየገለፅኩ መልካም ዜናን ይዤ መጥቻለዉ።

በ2018 የትምህርት ዘመን ላይ ትምህርት ከተጀመረ ቀን እስከ አንድ ሳምንት ድረስ  የጥናት አገልግሎትን ለምትጀምሩ  ነባር ደንበኞች በሙሉ የመጀመሪያዉን ሳምንት ነፃ መሆንን ሳሳዉቃችሁ ይህ ጅማሬዉ እንጂ ፍፃሜዉ እንዳልሆነ እንድታዉቁ እፈልጋለዉ።

በተጨማሪም በየወሩ ከተለመዱት የጥናት ቀናት ዉጪ በፈቀዳችሁት የእረፍት ቀን ላይ ተጨማሪ 2 ነፃ ቀናትን ይዤላችሁ መጥቻለዉ፤

ይህ ሁሉ ደግሞ ከዚህ ቀደም ታገኙት ከነበረዉ ወርክሽት ጋር እና ተማሪዉ ምንም ቀሪ ሳይኖርበት በሴሚስተር የሰርተፊኬት ዉጤቱ ከነበረዉ መሻሻልን ካላሳየ የ1 ወር ነፃ አገልግሎትን(የዉጤታማነት ጋራንቲ) ጨምሮ እና ሌሎችንም ነፃዎች የምታገኙበት መሆኑን ሳሳዉቃችሁ ከታላቅ ደስታ ጋር ነዉ።

ማሳሰቢያ፦ እነዚህ ጋራንቲዎች የሚሰሩት በተባለዉ የጊዜ ገደብ ማለትም ትምህርት በተጀመረ በአንድ በሳምንት ፖኬጁን ለሚገዙ ደንበኞች ነዉ፤ ከዛ ጊዜ በኋላ ፓኬጆቹ ኤክስፓየር ያደርጋሉ።

በመጨረሻ አዲሱ አመት የሰላም፣ የጤና፣ የእድገት፣ የመትረፍረፍ ደግሞም ከሁሉም በላይ የዉጤታማነት እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለዉ።

መልካም አዲስ አመት እና በአል!

- የአብስራ
1
ሌሎችንም ነፃዎች...
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
ጠቋሚ ቃላት ምንድን ናቸዉ?

"articles"/ጠቋሚ ቃላት የምንላቸዉ፤
ስራቸዉ ቁጥርን፣ መታወቅን እና አለመታወቅን ለመናገር ልንጠቀማቸዉ እንችላለን፤

ጠቋሚ ቃላት ለሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ እነሱም የሚታወቅን አሳዪ /"definite articles"እና የማይታወቅን አሳዪ /"indefinite articles"ናቸዉ፤

የሚታወቅን አሳዪ /"definite articles" -  እነዚህ የሚታወቅ/ቁ ነገሮችን ለማሳየት ልንጠቀማቸዉ እንችላለን፤
ለምሳሌ፦ The table - ጠረጴዛዉ

እዚህ ጋር እንደምትመለከቱት ጠረጴዛ(የትኛዉም ጠረፔዛ ሊሆን ይችላል) የሚለዉን ወደ ጠረፔዛዉ ማለትም ከዚህ በፊት ወደምናዉቀዉ ጠረፔዛ ትርጉሙን ለወጠዉ ማለት ነዉ።

የማይታወቅን አሳዪ /"indefinite articles" - እነዚህ በተለምዶ ለማይቆጠሩ ማንጠቀማቸዉ ሲሆኑ፤ ቁጥሩ 1 እንደሆነ እንዲሁም ያልተለመደ እና አዲስ  ለሆነ ነገር ነዉ የምንጠቀማቸዉ፤

ምሳሌ፦ an apple -  1 እና አዲስ ፖም
a boy - 1 እና አዲስ የሆነብን ወንድ ልጅ እንደማለት ናቸዉ፤

በተጨማሪም እነዚህን (የማይታወቅን አሳዪ /"indefinite articles") ከመጠቀማችሁ በፊት ማስተዋል ያለባችሁ የመጀመሪያዉ ፊደል የሚያወጣዉ ድምፅ "Vowel sound" ወይም "consonant sound" መሆኑን ነዉ፤

ማለትም "a,e,i,o & u"=> "Vowel"ድምፅ ነዉ ለዛም የምትጠቀሙት "indefinite article" => "an" ነዉ፤ ምሳሌ  "apple" የሚለዉ ቃል ላይ የመጀመሪያዉ ድምፅ የ"Vowel sound" በመሆኑ ወደ "an apple" ይቀየራል ወይም "an" መጨመር ያስችለናል ማለት ነዉ፤በተጨማሪም 1 እና አዲስ  መሆኑን  ለማሳየት ማለት ነዉ።

የ"Consonant sound" በሚሆን ጊዜ ደግሞ "a" ትጠቀማላችሁ ማለት ነዉ፤
ምሳሌ፦ a pen (የመጀመሪያዉ ድምፅ "p" በመሆኑና ከ"Vowel sound" ዉጪ ማለትም
ከ"a,e,i,o & u" ዉጪ በመሆኑ ማለትም "Consonant sound" በመሆኑ "a" መጠቀም ያስችለናል ማለት ነዉ ፤ በተጨማሪም 1 እና አዲስ  መሆኑን  ለማሳየት ማለት ነዉ።)

  ተጨማሪ ምሳሌዎች በ "Vowel Sounds" ላይ አልያም "an" በመጠቀም ዙሪያ፤
1. An apple - "She ate an apple."
2. An elephant - "They saw an elephant at the zoo."
3. An hour - "It took an hour to finish."(ማስታወሻ: "hour" የሚጀምርበት ድምፅ"vowel sound"/"o" ስለሆነ ነዉ "An" መጠቀም ያስቻለዉ።)
4. An ice cream - "He wants an ice cream."
5. An orange - "Would you like an orange?"


  ተጨማሪ ምሳሌዎች በ "Consonant Sounds" ላይ አልያም "a" በመጠቀም ዙሪያ፤
1. A car - "She bought a car."
2. A dog - "They have a dog."
3. A university - "He studies at a university." (ማስታወሻ: "university" የሚጀምርበት ድምፅ"consonant sound"/"y" ስለሆነ ነዉ "A" መጠቀም ያስቻለዉ።)
4. A book - "She is reading a book."
5. A house - "They live in a house."
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
ግሶች ምንድን ናቸዉ? ጠቀሜታቸዉስ?
-ግሶች/"Verbs" የምንላቸዉ የድርጊት ቃላት ሲሆኑ ያዉ ጠቀሜታቸዉ ድርጊትን ማመላከት ነዉ፤
ምሳሌ፦

play - መጫወት
eat - መመገብ
read - ማንበብ
study - ማጥናት የመሳሰሉት ምሳሌዎች መሆን ይችላሉ፤

በተጨማሪም በሚጠቀሙት የግስ አይነት ጊዜንም ሊያመላክቱ ይችላሉ ስለሀሸነም በመቀጠል በተለያዩ ጊዜዎች ላይ የአጠቃቀም ልዩነታቸዉን እናያለን፤

የ"verb1"፣ የ"verb 2" እና የ"verb 3" ልዩነቶች

Verb 1- ማለት ግሱ ምንም አይነት ለዉጥም ሆነ ቅጥያ ሳይኖረዉ(ባለቤቱ 1 ሲሆን -s/-es ከመጠቀሙ ዉጪ)ማለት ሲሆን፤ የምንጠቀመዉ አሁን/"present"ላይ ያለ ጊዜን ለማሳየት ነዉ ፤
ምሳሌ፦
Verb1
play/plays
eat/eats
read/reads
drink/drinks
study/studies
watch/watches

Verb2 - ማለት ግሱ እየገለፀ ያለዉ ጊዜ ያለፈ "past" መሆኑን ሲሆን ብዙውን ጊዜ በ"-ed/-d/-t" የሚያልቁ ናቸዉ፤ ብዙ ጊዜ ማለት ግን ሁልጊዜ ማለት አይደለም ፤ ምሳሌዎችን እንይ፦
Verb1 => Verb2

- drink => drank
- play=> played
- teach => taught
- eat => ate
- think => thought

Verb3 - የምንላቸዉ ደግሞ ከአንድ ድርጊት በፊት የተፈፀመ ድርጊትን(ሁሉንም የ"perfect tense"ሶች) ለማሳየት ሲሆን ጠቀሜታቸዉ ብዙዉን ጊዜ በስተመጨረሻቸዉ "-ed/-en/-ne/-d/-t"፤ ምሳሌ፦

Verb1 => Verb2 => Verb 3
- drink => drank => drunk
- play=> played => played
- teach => taught => taught
- eat => ate => eaten
- think => thought => thought

Verb1+ing - የምንላቸዉ ደግሞ ጊዜ ወስዶ የተፈፀመ ነገር (continuous) መሆኑን ለማሳየት ነዉ ምንጠቀመዉ፤

Verb1 => Verb1+ing
- drink => drinking
- play=> playing
- teach => teaching
- eat => eating
- think => thinking

ማስታወሻ እነዚህ የግስ አይነቶች የተለያየ ጊዜ ላይ ልትጠቀሟቸዉ የምትችሏቸዉ ናቸዉ፤ ማለትም "Verb1"=> "present"=>አሁንን
"Verb2"=> "past"=>ያለፈ
"Verb3"=> "perfect"=>ከድርጊት በፊት የተደረገ ድርጊትን
"Verb1+ing"=> "continuous"=>ጊዜ ወስዶ የተፈፀመ ድርጊትን
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
ከ"Direct speech" ወደ "Reported speech" ስትቀይሩ ምን ታደርጋላችሁ?


  "says" የሚል ከሌለ በስተቀረ ሁልጊዜም "Backshift"ወይም ጊዜዉን ወደሇላ ትመልሱታላችሁ ማለት ነዉ፤

በመቀጠል  እንዴት የተለያዩ "Tense"ሶችን ወደሇላ እንደምትመልሱ እናወራ፤

1.የጊዜ ለዉጥ Simple present => Simple past ትለዉጡታላችሁ፤

DIRECT: He said"I play music."
INDIRECT:He said that he played music.

እዚህ ጋር እንደምትመለከቱት "Direct speech" ላይ "V1" የነበረዉን "Indirect speech"ወደ "V2" ቀየርነዉ፤

2.የጊዜ ለዉጥ "present continuous" =>   "past continuous" ትለዉጡታላችሁ፤

DIRECT: He said"I am playing music right now."
INDIRECT:He said that he was playing music at that moment.

እዚህ ጋር እንደምትመለከቱት "Direct speech" ላይ "Verb to be(am)" የነበረዉን "Indirect speech"ወደ "Verb to be(was)" ቀየርነዉ፤

3.የጊዜ ለዉጥ "present perfect" =>   "past perfect" ትለዉጡታላችሁ፤

DIRECT: He said"I have already played music."
INDIRECT:He said that he had played music already .

እዚህ ጋር እንደምትመለከቱት "Direct speech" ላይ "have" የነበረዉን "Indirect speech"ወደ "had" ቀየርነዉ፤

4.የጊዜ ለዉጥ "past continuous" => "past perfect continuous"  ትለዉጡታላችሁ፤

DIRECT: He said " I was playing football last night"
INDIRECT: He said that he had been playing football the night before.

እዚህ ጋር እንደምትመለከቱት "Direct speech" ላይ "was" የነበረዉን "Indirect speech"ወደ "had been" ቀየርነዉ፤
🏆2
የ"Direct speech" እና የ"Reported speech"  ልዩነት ምንድን ነዉ?

Direct speech፦ የምንለዉ  የተናጋሪዉ ንግግር ምንም የጊዜ ለዉጥ ሳይደረግበት በ"quotation"/"" መሃከል የሚቀርብ አረፍተ ነገር ነዉ፤

ምሳሌ፦ He said "I am studying right now"

Reported speech ፦ የምንለዉ ደግሞ ተናጋሪዉ የተናገረዉን ነገር ወደሇላ በመመለስ  ለመናገር የምንጠቀመዉ አረፍተ ነገር ሲሆን፤

ምሳሌ፦ He said that he was studying at that time.


በመቀጠል እንዴት ከ"Direct speech" ወደ "Reported speech" እንደምንቀይር እናወራለን፤


ጊዜዉን ማትቀይሩበትን እናዉራ፤

ሁልጊዜ የሚደረግ (ድግግሞሽ) ከሆነ  ፤

ምሳሌ፦
DIRECT: He said "I play music everyday."
REPORTED: He said that he plays music every day.

እዚህ ጋር እንደምትመለከቱት ሁለቱም ያሉበት "Tense" ማለትም የሚጠቀሙት ግስ "V1" ነዉ፤

እዉነታም ከሆነ ወደ"Reported speech" ስትቀይሩት ጊዜዉን አትቀይሩትም፤

ምሳሌ፦
DIRECT: He said"The sun rises in the east."
INDIRECT:He said that the sun rises in the east.

እዚህ ጋርም እንደምትመለከቱት ሁለቱም ያሉበት "Tense" ማለትም የሚጠቀሙት ግስ "V1" ነዉ፤


"says" የሚል ካልሆነ በስተቀረ ሁልጊዜም "Backshift"ወይም ጊዜዉን ወደሇላ ትመልሱታላችሁ ማለት ነዉ፤

አሁን ደግሞ እንዴት የተለያዩ "Tense"ሶችን ወደሇላ እንደምትመልሱ እናወራለን፤

የጊዜ ለዉጥ Simple present => Simple past ትለዉጡታላችሁ፤

DIRECT: He said"I play music."
INDIRECT:He said that he played music.

እዚህ ጋር እንደምትመለከቱት "Direct speech" ላይ "V1" የነበረዉን "Indirect speech"ወደ "V2" ቀየርነዉ፤

የጊዜ ለዉጥ "present continuous" =>   "past continuous" ትለዉጡታላችሁ፤

DIRECT: He said"I am playing music right now."
INDIRECT:He said that he was playing music at that moment.

እዚህ ጋር እንደምትመለከቱት "Direct speech" ላይ "Verb to be(am)" የነበረዉን "Indirect speech"ወደ "Verb to be(was)" ቀየርነዉ፤

የጊዜ ለዉጥ "present perfect" =>   "past perfect" ትለዉጡታላችሁ፤

DIRECT: He said"I have already played music."
INDIRECT:He said that he had played music already .

እዚህ ጋር እንደምትመለከቱት "Direct speech" ላይ "have" የነበረዉን "Indirect speech"ወደ "had" ቀየርነዉ፤

የጊዜ ለዉጥ "past continuous" => "past perfect continuous"  ትለዉጡታላችሁ፤

DIRECT: He said " I was playing football last night"
INDIRECT: He said that he had been playing football the night before.

እዚህ ጋር እንደምትመለከቱት "Direct speech" ላይ "was" የነበረዉን "Indirect speech"ወደ "had been" ቀየርነዉ፤

ምትለዉጧቸዉ "modal verb"ኦች፤

will => would

DIRECT: He said"I will play music tomorrow."
INDIRECT:He said that he would   play music the next day.

እዚህ ጋር እንደምትመለከቱት "Direct speech" ላይ "will" የነበረዉን "Indirect speech"ወደ "would" ቀየርነዉ፤

have to => had to

DIRECT: He said"I have to wear my seat belt"
INDIRECT:He said that he had to   wear his seat belts.

እዚህ ጋር እንደምትመለከቱት "Direct speech" ላይ "have to" የነበረዉን "Indirect speech"ወደ "had to" ቀየርነዉ፤

must=> had to

DIRECT: He said"I must wear my seat belt"
INDIRECT:He said that he had to   wear his seat belts.

እዚህ ጋር እንደምትመለከቱት "Direct speech" ላይ "must" የነበረዉን "Indirect speech"ወደ "had to" ቀየርነዉ፤
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
ግሶች ምንድን ናቸዉ? ጠቀሜታቸዉስ?
-ግሶች/"Verbs" የምንላቸዉ የድርጊት ቃላት ሲሆኑ ያዉ ጠቀሜታቸዉ ድርጊትን ማመላከት ነዉ፤
ምሳሌ፦

play - መጫወት
eat - መመገብ
read - ማንበብ
study - ማጥናት የመሳሰሉት ምሳሌዎች መሆን ይችላሉ፤

በተጨማሪም በሚጠቀሙት የግስ አይነት ጊዜንም ሊያመላክቱ ይችላሉ ስለሀሸነም በመቀጠል በተለያዩ ጊዜዎች ላይ የአጠቃቀም ልዩነታቸዉን እናያለን፤

የ"verb1"፣ የ"verb 2" እና የ"verb 3" ልዩነቶች

Verb 1- ማለት ግሱ ምንም አይነት ለዉጥም ሆነ ቅጥያ ሳይኖረዉ(ባለቤቱ 1 ሲሆን -s/-es ከመጠቀሙ ዉጪ)ማለት ሲሆን፤ የምንጠቀመዉ አሁን/"present"ላይ ያለ ጊዜን ለማሳየት ነዉ ፤
ምሳሌ፦
Verb1
play/plays
eat/eats
read/reads
drink/drinks
study/studies
watch/watches

Verb2 - ማለት ግሱ እየገለፀ ያለዉ ጊዜ ያለፈ "past" መሆኑን ሲሆን ብዙውን ጊዜ በ"-ed/-d/-t" የሚያልቁ ናቸዉ፤ ብዙ ጊዜ ማለት ግን ሁልጊዜ ማለት አይደለም ፤ ምሳሌዎችን እንይ፦
Verb1 => Verb2

- drink => drank
- play=> played
- teach => taught
- eat => ate
- think => thought

Verb3 - የምንላቸዉ ደግሞ ከአንድ ድርጊት በፊት የተፈፀመ ድርጊትን(ሁሉንም የ"perfect tense"ሶች) ለማሳየት ሲሆን ጠቀሜታቸዉ ብዙዉን ጊዜ በስተመጨረሻቸዉ "-ed/-en/-ne/-d/-t"፤ ምሳሌ፦

Verb1 => Verb2 => Verb 3
- drink => drank => drunk
- play=> played => played
- teach => taught => taught
- eat => ate => eaten
- think => thought => thought

Verb1+ing - የምንላቸዉ ደግሞ ጊዜ ወስዶ የተፈፀመ ነገር (continuous) መሆኑን ለማሳየት ነዉ ምንጠቀመዉ፤

Verb1 => Verb1+ing
- drink => drinking
- play=> playing
- teach => teaching
- eat => eating
- think => thinking

ማስታወሻ እነዚህ የግስ አይነቶች የተለያየ ጊዜ ላይ ልትጠቀሟቸዉ የምትችሏቸዉ ናቸዉ፤ ማለትም "Verb1"=> "present"=>አሁንን
"Verb2"=> "past"=>ያለፈ
"Verb3"=> "perfect"=>ከድርጊት በፊት የተደረገ ድርጊትን
"Verb1+ing"=> "continuous"=>ጊዜ ወስዶ የተፈፀመ ድርጊትን
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ምን ሲያጋጥማችሁ ነዉ "Verb 1/Verb 2/Verb 3" ልትጠቀሙ የምትችሉት?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/DuOX7oOLy9o?feature=shared
🔥1
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
አጭሩ ከ"Active=> passive" መቀየሪያዉ  ቀመር።

ብዙዎች "Active voice" ወደ "passive voice" መቀየር ድርጊቱ የተፈፀመበትን ጊዜ/"Tense" መቀየር መስሎ ይታያቸዋል እዉነታዉ ግን "Active Voice" የምንለዉ ስለ ደርጊት ፈፃሚው አጉልቶ ለማዉራት የምንጠቀመዉ ሲሆን "passive voice" የምንለዉ ደግሞ ድርጊቱ ስለተፈፀመበት አካል በዋነኛነት አተኩሮ የሚያወራ ነዉ፤

ለምሳሌ፦
Active - we love icecream.
እዚህ ጋረ "we" የድርጊት ፈፃሚዉ ነዉ፤ ስለሱም ነዉ አጉልቶ አረፍተ ነገሩ ማሳየት የፈለገዉ ለዛ ነዉም "Active voice" ላይ ያለ አረፍተ ነገር የተባለዉ።

passive - Icecream is loved by us.
እዚህ ጋር ደግሞ "Icecream" ድርጊቱ የተፈፀመበት ነዉ ፤ ስለሱም ነዉ አጉልቶ አረፍተ ነገሩ ማሳየት የፈለገዉ ለዛ ነዉም "passive voice" ላይ ያለ አረፍተ ነገር የተባለዉ።

ከ"Active => passive" በምትቀይሩ ጊዜ የምትጠቀሙት "Verb to be" ከአንዱ
"Tense" ወደ "Tense" የተለያየ ነዉ፤ ቢሆንም ግን በቀላሉ ወደ "passive" ለመቀየር እናንተ መመልከት የሚኖርባችሁን አና እነዛን ስትመለከቱ ምን አይነት "verb to be" እንደምትጠቀሙ የምናወራ ይሆናል፤

በመጀመሪያ ዋነኛዎቹን ከ"Active => passive" መቀየሪያ ቀመሮችን እንመልከት፤

Active - subject + verb +
object.

passive - object + verb to be + verb3 + subject

ቀደም ብሎ እንደተመለከታችሁት ከ"Active => passive" በምትቀይሩ ጊዜ ሁልጊዜም ልትከተሉት የሚገባዉ ቀምር ሲሆን "object" እና "subject" ቦታ ይቀያየራሉ፤ እንዲሁም አሁን የምናወራዉን "Verb to be"  ትጨምራላችሁ ከዛም ዋነኛዉን ግስ ወደ "Verb3" ትቀይሩታላችሁ።


በአረፍተ ነገራችሁ ዉስጥ "Verb 1" ካለ የምትጠቀሙት "Verb to be"=> "is/am/are" ነዉ።

ምሳሌ፦ he plays football.
football is played by him.

በአረፍተ ነገራችሁ ዉስጥ "Verb 2" ካለ የምትጠቀሙት "Verb to be"=> "was/were" ነዉ።

ምሳሌ -
Active - They studied verry hard for the exam.
passive - The exam was studied hard for by them.

በአረፍተ ነገራችሁ ዉስጥ "modal verb ፦ will, would, may, might, can, could, ought to, have to, need to, shall & should " ካለ የምትጠቀሙት "Verb to be"=>"be" ነዉ።

Active - he will play football every sunday.
passive -  football will be played every sunday by him.

በአረፍተ ነገራችሁ ዉስጥ "Verb1+ing " ካለ የምትጠቀሙት "Verb to be"=>"being" ነዉ።

ምሳሌ -
Active - he is playing football.
passive - football is being played by him.


በአረፍተ ነገራችሁ ዉስጥ "has/had/have " ካለ የምትጠቀሙት "Verb to be"=>"been" ነዉ።

ምሳሌ-
Active - he has played football.
passive - football has been played by him.

ስለ "Verb to be" በምናወራ ጊዜ አጋዥ ግስ ሆነዉ ሳለ ጠቀሜታቸዉ አረፍተ ነገሩ የሚነገርበትን ጊዜ ማሳየት ነዉ፤

በተጨማሪም  ተመሳሳይ ጊዜን የሚያሳዩ ግን የተለያየ የባለቤት ብዛትን የሚያሳዩም ናቸዉ ማለትም "was/were" ያለፈ ጊዜን ግን የተለያየ ቁጥርን፤

ምሳሌ፦
Active - They were studying verry hardfor the exam.
passive - The exam was being studied hard for by them.

እዚህ ጋራ እንደምትመለከቱት በ"Active" አረፍተ ነገሩ ላይ "were" የነበረዉን "passive" አረፍተ ነገሩ ላይ "was" ሆኗል ምክንያቱም ደግሞ ሁለቱም አንድ አይነት ጊዜን ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን(ከ"Active=> passive" ስትቀይሩ ጊዜዉን ስለማትቀይሩ) ግን የተለያየ የባለቤት ቁጥርን ለማሳየት ስላስፈለገ ማለት ነዉ።

"is/am/are" አሁን ላይ ያለ ጊዜን ግን የተለያየ የባለቤትን ብዛትን ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን፤

ምሳሌ፦
Active - They are playing football.
Passive - football is being played by them.

እዚህ ጋራ እንደምትመለከቱት በ"Active" አረፍተ ነገሩ ላይ "are" የነበረዉን "passive" አረፍተ ነገሩ ላይ "is" ሆኗል ምክንያቱም ደግሞ ሁለቱም አንድ አይነት ጊዜን ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን(ከ"Active=> passive" ስትቀይሩ ጊዜዉን ስለማትቀይሩ) ግን የተለያየ የባለቤት ቁጥርን ለማሳየት ስላስፈለገ ማለት ነዉ።

"has/have" ላይም አንድ አይነት ጊዜን ግን የተለያዩ የባለቤቶችን ቁጥርንም ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን፤ ስለዚህም ወደ "passive" ስትቀይሩ "active"ን ማለት ነዉ፤

ምሳሌ፦
Active - he has played with footballs already.
passive -  footballs have been played with by him.

እዚህ ጋራ እንደምትመለከቱት በ"Active" አረፍተ ነገሩ ላይ "has" የነበረዉን "passive" አረፍተ ነገሩ ላይ "have" ሆኗል ምክንያቱም ደግሞ ሁለቱም አንድ አይነት ጊዜን ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን(ከ"Active=> passive" ስትቀይሩ ጊዜዉን ስለማትቀይሩ:) ግን የተለያየ የባለቤት ቁጥርን ለማሳየት ስላስፈለገ ማለት ነዉ፤

በስተመጨረሻ ሁሉም "passive voice" የሚጠቀመዉ ግስ "Verb 3" ነዉ ይህ ማለትም ብዙዉን ጊዜ መጨረሻዉ ላይ "-ed/-en/-ne/-d/-t"  ያሉት ሲሆን ብዙዉን ጊዜ ማለት ግን ሁል ጊዜ ማለት አይደለም።
4
Live stream started
Live stream finished (11 seconds)
Forwarded from የአብስራ