የአብስራ
505 subscribers
223 photos
782 videos
183 files
1.21K links
ሰሚት ከንዶሚንየም ሆነው አስጠኚ ከፈለጉ እና የአንድ ሳምንት ነፃ ሙከራን ጨምሮ ለማግኘት በስልክ ቁጥር:- 09-38-58-75-08 ላይ በመደወል ወይም በቴሌግራም @committed12 በመጫን ያገኙኛል።

ለተማሪዎች ተጨማሪ ድጋፍ የሚሆን
ነፃ የተንቀሳቃሽ ምሰል ማብራሪያዎች እዚህ ተጭናችሁ ታገኛላሁ:- https://youtube.com/@yabserawondewosen?si=M3rU1wnXO8__6RBx
Download Telegram
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
Pronouns ምን ይሰራሉ?

Pronouns: ተውላጠ ስም የምንላቸው ሲሆኑ፤ ስራቸው በስም ቦታ ተተክተው በመግባት እንደ መጠሪያ ወይም መለያ ማገልገል ነው።

Subject Pronouns: የምንላቸው በአረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ላይ ብቻ ተተክተው መግባት የሚችሉ ናቸው።

ምሳሌዎች:

- Abebe is playing football. 
  He is playing football.

- Kebedech is studying math. 
  She is studying math.

- My father & I are playing video games. 
  We are playing video games.

- My mother & my two sisters have gone shopping. 
  They have gone shopping.

- You are a pilot, right?

- I am studying math.
👍1
ተዉላጠ ስሞች እና ትርጉማቸዉ (ክፍል-1)

Subject pronouns - ባለቤትን ወካይ ቃላቶች(ተዉላጠ ስሞች)

Singular - ነጠላ
(1)
He - እሱ፣
She - እሷ፣
It - ነገርየዉ(ለእንስሳ/ለእቃ)፣
You - አንተ/ አንቺ፣
I - እኔ፤

Plural -  ብዙ (ከአንድ በላይ)
We - እኛ፣
They - እነሱ፣
You - እናንተ፤

ማስታወሻ፦ ባለቤት ማለት በአረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ላይ የሚገባ እና የድርጊቱ ፈፃሚ ነዉ፤ በተጨማሪም ተዉላጠ ስሞች ስራቸዉ በስም ቦታ ተክተዉ መግባት ነዉ።

ምሳሌ; He studies math everyday.

ማስታወሻ፦ "Subject pronouns" የተባሉት የአረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ላይ ብቻ ስለሚገቡ ነዉ።
ተዉላጠ ስሞች እና ትርጉማቸዉ (ክፍል-2)

object pronouns - ድርጊት የተፈፀመበትን ለመወከል

singular -ነጠላ(1)
    Him- እሱ፣   
    Her - እሷ፣ 
    It  - ነገርየዉ(ለእቃ/ለእንስሳ)፣   
    You - አንተ /  አንቺ ፣
    Me- እኔ፤


plural- ብዙ (ከአንድ በላይ)
   Them - እነሱ፣
   You -  እናንተ፣
   Us - እኛ፤

ማስታወሻ፦ "It" እና "You" "subject" እና  "object"ቱ አልያም ደግሞ የድርጊት ፈፃሚዉ እና ድርጊት የሚፈፀምበት የቃላቶቹ  አፃፃፍ አንድ አይነት ነዉ።

ምሳሌ፦The Doctor treated him verry well.

ማስታወሻ፦ "object pronouns" የተባሉበት ምክንያት ከድርጊት ቃሉ/"Verb" ከምንለዉ (እዚህ ጋር ከ"treated" ) ቀጥሎ ስለሚገቡ ነዉ።
👎1
ተዉላጠ ስሞች እና ትርጉማቸዉ (ክፍል-3)

posssesive pronouns - ባለቤትነትን ተናገሪ ተዉላጠ ስሞች

singular -ነጠላ(1)
  his - የርሱ
hers - የርሷ
its -  የነገርየዉ
mine - የኔ
yours :- የአንተ/ የአንቺ

  plural- ብዙ (ከአንድ በላይ)
yours - የእናንተ
ours  - የኛ
Theirs - የነሱ

ማስታወሻ፦ "possessive pronouns" ከጎናቸዉ የሚያብራሩት ስም አያስፈልጋቸዉም ግን "possessive adjective"ኦች ቀጥሎ የሚገልፁት ስም ያስፈልጋቸዋል።

ምሳሌ፦
That book is mine. <= possessive pronoun(ከ"mine" ቀጥሎ ስም የለም።)
That is my book.<= possessive adjective(ከ"my" ቀጥሎ ስም አለ።)
👍2
ያለእኩልነቶች ላይ የማይታወቁትን ዋጋዎች እንዴት መስራት ይቻላል-2(how to solve inequalities wit...
https://youtube.com/watch?v=DLlCYTkA4HA&feature=shared
አንዴ እድል ነዉ ሁለቴ ግን ብቃት፤

ለኔ ተማሪ ይስሃቅ ከዘጠና በላይ ማምጣት የሚከብደዉ ባለመሆኑ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል!

ተማሪ ይስሃቅ በመጀመሪያዉ ሩብ አመት እና ሁለተኛዉ ሩብ አመት ከዘጠና በላይ በማስመዝገቡ የመጀመሪያዉን ግማሽ አመት 92.96% አማካይ እና ድምር 743.75/800 በማምጣት ወደሁለተኛዉ የአመት ግማሽ በታላቅ ድል አልፏል።

በመሆኑም የእርሱን ስኬት በሌሎቹ ተማሪዎቼ የመድገም ጉጉት እንዲኖረኝ እና ከእስከ አሁኑ በይበልጥ ተግቼ እንድሰራም ያደረገ ነዉ።

የደስታዬ ተካፋዮች እንደምትሆኑ እምነቴ ነዉ።

- የአብስራ
ስኬታማ ድርጊቶችን እንደግማለን፤

ወይም ለመድገም እንሞክራለን ኢስኬታማ የሆኑትን ደግሞ በፍጥነት ለማቆም እንጥራለን በዚህም የወደፊት ጉዞዋችንን እናቀላጥፋን።

የኔ ተማሪ ማርያማዊት ደግሞ ስኬቷን ደግማለች ማለትም በአንደኛ እና በሁለተኛ ሩብ አመት ከዘጠና በላይ በማስመዝገብ የመጀመሪያ ግማሽ አመት 93.53% አማካይ እና ድምር 654.75/700 በማምጣት በአሸናፊነት ወደሁለተኛዉ አመት ተላልፋለች።

ልክ እንደ እኛ ስህተትን ከመደጋገም ለመላቀቅ እና ትክክል መሆንን ለመደጋገም ለምትጥሩ ከጎናችሁ ነን እያልኩ መልካም ምኞቴን እገልፃለዉ።

መልካም እድል!

- የአብስራ
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቀላል የድርጊት እና የባለቤት ስምምነት ማበራሪያ። "subject verb agreement simplified"


በቀላሉ ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦ https://youtu.be/dZ2juDQA2LQ?si=KoJO_d4aHQ9MyhG2
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
'Pronoun'ኦችን እንዴት ልትጠቀሟቸዉ ትችላላችሁ?
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
"Adverbs" ምን ያደርጋሉ?

Adverbs: የግስ ገላጭ ቃላቶች ናቸው፤ ስራቸው የድርጊት ቃሉን የተፈፀመበትን ሁኔታ፣ ቦታ፣ ድግግሞሽ፣ መጠን እና ጊዜ ማሳየት ነው።

"Adverbs" አይነት እና ጠቀሜታ አላቸው፤ እነሱም እንደሚከተለው ይቀርባሉ፦

- Adverbs of manner: ድርጊቱ የተፈፀመበትን ሁኔታ ለመግለጽ እንጠቀማቸዋለን። 
  ምሳሌዎች:
  - He ran quickly
  - She sings loudly.

- Adverbs of frequency: ድርጊቱ የተፈፀመበትን ድግግሞሽ ለመግለጽ እንጠቀማቸዋለን። 
  ምሳሌዎች:
  - He often runs. 
  - She frequently practices singing.

- Adverbs of degree: ድርጊቱ የተፈፀመበትን መጠን ለመግለጽ እንጠቀማቸዋለን። 
  ምሳሌ:
  - She loves her mom very much.

- Adverbs of place: ድርጊቱ የተፈፀመበትን ቦታ ለመግለጽ እንጠቀማቸዋለን። 
  ምሳሌዎች:
  - He plays outside
  - She studies inside.

- Adverbs of time: ድርጊቱ የተፈፀመበትን ጊዜ ለመግለጽ እንጠቀማቸዋለን። 
  ምሳሌዎች:
  - She will arrive tomorrow
  - They left early.
👍3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
'Tense'ሶች ምንድን ናቸዉ ? ቀላል የጥያቄ አሰራርስ አላቸዉ ወይ?(አዎ)