የአብስራ
506 subscribers
223 photos
782 videos
183 files
1.21K links
ሰሚት ከንዶሚንየም ሆነው አስጠኚ ከፈለጉ እና የአንድ ሳምንት ነፃ ሙከራን ጨምሮ ለማግኘት በስልክ ቁጥር:- 09-38-58-75-08 ላይ በመደወል ወይም በቴሌግራም @committed12 በመጫን ያገኙኛል።

ለተማሪዎች ተጨማሪ ድጋፍ የሚሆን
ነፃ የተንቀሳቃሽ ምሰል ማብራሪያዎች እዚህ ተጭናችሁ ታገኛላሁ:- https://youtube.com/@yabserawondewosen?si=M3rU1wnXO8__6RBx
Download Telegram
"Tense"ሶችን እንዴት ትለዩዋቸዋላችሁ?

Tense: ማለት ጊዜን ገላጭ የድርጊት ቃል ሆኖ ሳለ፤
ሶስቱ ዋና ማለትም "past, present,& future"
እና ሁለቱ ተጨማሪዎች "Continuous" እና "perfect" ሆነዉ 12 የ"Tense"ሶች አይነቶችን ይሰራሉ ብሎም አንዱን ከሌላዉ በቀላሉ እንዴት መለየት እንደምትችሉ  አቅጣጫዉን ላሳያችሁ፤

ሶስቱ ዋናዎቹ
- present:V1(ምንም ለዉጥ ሳይኖረዉ ቅጥያ በስተመጨረሻዉ ካለዉ ደግሞ-s/-es   ያለዉ ነዉ።)
- past: V2(ብዙውን ጊዜ-ed/-d  በስተመጨረሻዉ ያለዉ ነዉ።)
- future: will/shall/can + V1(ምንም ለዉጥም ሆነ ቅጥያ ሳይኖረዉ፤)

ሁለቱ ተጨማሪዎች
- Continuous: V1+ing
- perfect:V3( ብዙዉን ጊዜ -ed/-en/-t/-d መጨረሻዉ ላይ ያለ)

እነዚህ ዋናዎቹን ከተጨማሪዎቹ ጋራ አንድ በአንድ አልያም ሁለቱንም አንድ ላይ በመቀላቀል 12  የተለያዩ ጠቀሜታ ያላቸዉን "Tense"ሶች መስራት ይቻላል፤

በተጨማሪም ማስተዋል ሚኖርባችሁ ነገር አንድ "Tense" አለ ማለት ያንን ሚለየዉ ግስ ከላይ እንደተጠቀሰዉ በዉስጡ (በ"Tense"ሱ) አለ ማለት ነዉ።
👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አረፍተነገር ስንት ክፍሎች አሉት?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/5grVQAvnR1A?si=VGVOGZxykcokEC6W
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"Verb" ምን ማለት ነዉ? አይነቱስ?
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"Auxiliary Verbs" ምንድን ናቸዉ?
"Can" ምን ማለት ነው?

Can: ማለት ብቃትን አልያም ችሎታን ለማሳየት የምንጠቀመዉ፤ ብቃትን አልያም ችሎታን ለመናገር ወይም ለመጠየቅ የምንጠቀመዉ የ"Modal verb" አይነት ነዉ።

ምሳሌዎች:

1. He can play football. (Positive sentence)
2. Can she do her homework on her own? (Question)
3. Can't they play with us? (Negative question)
4. We can't let that happen. (Negative sentence)
"Will"ምን ማለት ነው?

  Will: እቅድን እና የወደፊት ሃሳብን በ"future tense" ላይ ለማሳየት፤ ለመናገር እንዲሁም ለመጠየቅ ልንጠቀመዉ እንችላለን።

ምሳሌዎች:

- He will study later. 
    እሱ  በሇላ ያጠናል።

- She won't be cleaning later. 
    እሷ በሇላ አታፀዳም።

- Will they be here on time? 
    እነሱ በጊዜ ይደርሱ ይሆን?

- Won't we be there on time?
   እኛ  በጊዜ አንደርስም ይሆን?
"Shall" ምን ይሰራል?

Shall: ፈቃደኝነትን ለመጠየቅ፣ ምክር ለመለገስ እና ስነስርአት ባለዉ መልኩ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ልንጠቀመዉ እንችላለን።

ምሳሌዎች፦

You shall do your homework.
የቤት ስራህን ብትሰራ ጥሩ ይመስለኛል።

They shalln't play with fire.
በእሳት ባይጫወቱ ጥሩ ነዉ።

Shall we study math?
ሂሳብ እናጥና ይሆን?

Shalln't they swim in the sea?
ባህሩ ዉሰጥ መዋኘት የለባቸዉም ይሆን?
👍1
"Is" ምን ይሰራል?

Is: ጠቀሜታዉ( ነዉ የሚለዉን ትርጉም ይሰጣል) አንድ ተናጋሪ አልያም ጠያቂ አረፍተ ነገር  የ"Continuous tense" መሆኑን ማለትም ቀጣይኀት ያለዉ ወይም ረዘም ያለ ጊዜን እንደሚወስድ ለማሳየት ነዉ።

ምሳሌዎች፦

He is playing football now.
እሱ አሁን ኳስ እየተጫወተ ነዉ።

She is not studying math at this moment.
እሷ አሁን ሂሳብ እያጠናች አይደለም።

Is she not working right now?
አሁን እሷ አየሰራች አይደለም ወይ?

Is he washig his cloth currently?
አሁን እሱ  ልብሱን እያጠበ ነዉ ወይ?
"are" ምን ጠቀሜታ አለዉ?

are: ጠቀሜታዉ(ናቸዉ ማለት ሆኖ ሳለ) ተናጋሪዉ አልያም ጠያቂዉ አረፍተነገር   ባለቤቱ ብዙ እንደሆነ እና አረፍተነገሩ ያለበት "Tense" የ"Continuous tense" መሆኑን ማለትም ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስድ ድርጊትን ለማሳየት ነዉ።

ምሳሌዎች፦

They are studying math.
እነሱ ሂሳብ እያጠኑ ነዉ።

we aren't playing football.
አኛ ኳስ እየተጫወትን አይደለም።

are they cleaning the house?
እነሱ ቤቱን እያፀዱት ነዉ ወይ?

aren't we researching the project?
እኛ ፕሮጀክቱን እየተመራመርን አይደለም ወይ?
"am" ምን ጠቀሜታ አለዉ?

am: ጠቀሜታዉ(ነኝ ማለት ነዉ።) በተናጋሪ አልያም በጠያቂ አረፍተነገር ላይ የ"Continuous tense" አረፍተነገር መሆኑን ማለትም ድርጊቱ ረዘም ያለ ጊዜ ወስዶ እንደሚፈፀም ለማሳየት እንጠቀመዋለን።

ምሳሌዎች፦

I am playing football.
እኔ ኳስ እየተጫወትኩ ነዉ።

I'm not reading the book.
እኔ መፅሃፉን አያነበብኩት አይደለም።

am I the one to play the game?
እኔ ነኝ ጨዋታወን መጫወት ያለብኝ?

am I not the person you are searching for?
እኔ አይደለሁም በአንተ/በአንቺ የተፈለኩት?
"Adjectives" ምን ያደርጋሉ?

Adjectives: የስም ገላጭ ቃላት ናቸው፤ ስራቸው ስምን መግለፅ እና አንዱን ከሌላው ማወዳደር ነው።

"Adjectives" አይነት አላቸው፤ እነሱም:

- "Positive": ነገሮችን ለመግለፅ እንጠቀማቸዋለን። 
  - *Example:* The house is beautiful.

- "Comparative": ሁለት ነገሮችን ለማነፃፀር እንጠቀማቸዋለን። 
  - *Example:* Our house is more beautiful than yours.

- "Superlative": አንድ ነገርን ከሁለት በላይ ከሆኑ ነገሮች ጋር ለማወዳደር እንጠቀማቸዋለን። 
  - *Example:* Their house is the most beautiful house I have ever seen.
👍1
Pronouns ምን ይሰራሉ?

Pronouns: ተውላጠ ስም የምንላቸው ሲሆኑ፤ ስራቸው በስም ቦታ ተተክተው በመግባት እንደ መጠሪያ ወይም መለያ ማገልገል ነው።

Subject Pronouns: የምንላቸው በአረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ላይ ብቻ ተተክተው መግባት የሚችሉ ናቸው።

ምሳሌዎች:

- Abebe is playing football. 
  He is playing football.

- Kebedech is studying math. 
  She is studying math.

- My father & I are playing video games. 
  We are playing video games.

- My mother & my two sisters have gone shopping. 
  They have gone shopping.

- You are a pilot, right?

- I am studying math.
👍3
"Adverbs" ምን ያደርጋሉ?

Adverbs: የግስ ገላጭ ቃላቶች ናቸው፤ ስራቸው የድርጊት ቃሉን የተፈፀመበትን ሁኔታ፣ ቦታ፣ ድግግሞሽ፣ መጠን እና ጊዜ ማሳየት ነው።

"Adverbs" አይነት እና ጠቀሜታ አላቸው፤ እነሱም እንደሚከተለው ይቀርባሉ፦

- Adverbs of manner: ድርጊቱ የተፈፀመበትን ሁኔታ ለመግለጽ እንጠቀማቸዋለን። 
  ምሳሌዎች:
  - He ran quickly
  - She sings loudly.

- Adverbs of frequency: ድርጊቱ የተፈፀመበትን ድግግሞሽ ለመግለጽ እንጠቀማቸዋለን። 
  ምሳሌዎች:
  - He often runs. 
  - She frequently practices singing.

- Adverbs of degree: ድርጊቱ የተፈፀመበትን መጠን ለመግለጽ እንጠቀማቸዋለን። 
  ምሳሌ:
  - She loves her mom very much.

- Adverbs of place: ድርጊቱ የተፈፀመበትን ቦታ ለመግለጽ እንጠቀማቸዋለን። 
  ምሳሌዎች:
  - He plays outside
  - She studies inside.

- Adverbs of time: ድርጊቱ የተፈፀመበትን ጊዜ ለመግለጽ እንጠቀማቸዋለን። 
  ምሳሌዎች:
  - She will arrive tomorrow
  - They left early.
🙏1
"Adjectives" ምን ያደርጋሉ?

Adjectives: የስም ገላጭ ቃላቶች ናቸው፤ ስራቸው ስምን መግለፅ እና አንዱን ከሌላው ማወዳደር ነው።

"Adjectives" አይነት አላቸው፦

- Positive: ሲሆኑ ስምን ለመግለፅ እንጠቀማቸዋለን። 
  ምሳሌዎች:
  - The house is beautiful
  - The cat is fast
  - The boy is tall.

- Comparative: ሲሆኑ ሁለት ነገሮችን ለማነፃፀር እንጠቀማቸዋለን። 
  ምሳሌዎች:
  - Our house is more beautiful than yours. 
  - The dog is faster than the cat. 
  - This tree is taller than that one.

- Superlative: ሲሆኑ አንድ ነገርን ከሁለት በላይ ነገሮች ጋር ለማወዳደር እንጠቀማቸዋለን። 
  ምሳሌዎች:
  - Their house is the most beautiful house I have ever seen. 
  - The horse is the fastest animal on the farm. 
  - He is the tallest student in the class.
1
5ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች፤

በሚል መሪ ቃል በ"Udacity.com" የተዘጋጀዉን የመሰረታዊ የዳታ ምርምር ስልጠና ሰሞኑን የወሰድኩ ሲሆን፤

ስልጠናዉ በዋናኝነት አንድን ችግር ለመፍታት የትኛዉ መረጃ መታየት እና መሰላት እነዳለበት እንደገናም ይህን ሁሉ በ"Excel" እንዴት መስራት እንደሚያስችል የሚያስተመር  ነዉ፤

በአሁኑ የመረጃ አስፈላጊነት በላቀበት አለም እንዴት ቢዝነሶች በመረጃ ላይ ተመስርተዉ ለችግሮች  መፍትሄ መስጠት እንደሚችሉ በጥልቀት ያስተምራል።

ብሎም እንደኔ የ"Nanodegree" ሰርተፊኬት ለማግኘት እና እኔ የተማርኩበትን ድህረ-ገፅ  ለመጎብኘት እዚህ ይጫኑ፦ Udacity.com

በተጨማሪም የኔ ሰርተፊኬት እዉነተኛ እና ከ"Udacity" የተበረከተ መሆኑን ለማረጋገጥ ይህንን ይጫኑ ፦ confirm.udacity.com/DUQ2PTUS

መልካም ትምህርት!

-የአብስራ
🔥4👍2
እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ!

አዲሱ አመት የሰላም፣ የጤና ፣ የብርታት ፣ የስኬት እና የመትረፍረፍ እንዲሁም ያሰባችሁት ሁሉ የሚሳካበት አመት ከነቤተሰባችሁ እንዲሆን ከልብ እመኛለዉ፤ ቸር ያሰማን!

መልካም አዲስ አመት!

- የአብስራ
🙏3🔥2
ሶስቱም መፅሃፍቶቼ እነሆአችሁ፤ መልካም ንባብ።
Forwarded from የአብስራ (የአብ ስራ)
በአንድ_ቀመር_ሁሉንም_Active_Voice_ሶች_ወደ_Passive_Voice_ሶች_መቀየር.pdf
200.6 KB
በአንድ ቀመር ሁሉንም "Active Voice"ሶች ወደ "Passive Voice"ሶች መቀየር ይቻላል? አዎን።(መፀሃፉ በፅሁፍ መልክ)

በቀላሉ መፅሃፋን በቪድዮ መልክ ለማግኘት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/T-WqtAcc2PM?si=uVeRow9OF_EyP23T
ታይተዉ የማይታወቁ ቀላሎቹ.pdf
246.6 KB
ታይተዉ የማይታወቁ ቀላሎቹ የ"Tense"ሶች አሰራር፤ ከነትገበራቸዉ። (መፅሃፍ በፅሁፍ መልክ)


በመጀመሪያ መፅሃፋን ይክፈቱ ፤

በመቀጠል የመፅሃፋን የድምፅ ንባብ በመክፈት ማድመጡን እና ንባቡን አንድ ላይ ያድርጉአቸዉ ፤

ማስተወሻ እያነበቡ ያሉትን ነገር ማድመጥ የማስታወስ ብቃትዎን ይጨመራል

በስተመጨረሻ ማንኛዉም አይነት ከመፅሃፉ ጋራ  የተያያዘ ችግር ከገጠማችሁ በ0938587508 በመደወል ታገኙኛላችሁ።

መልካም ጊዜ!

- የአብስራ
የ_Conditional_አረፍተ_ነገሮች_ቀላል_ጥያቄ_አሰራር_ቀመር_አላቸዉ_1.pdf
251 KB
የ"Conditional" አረፍተ ነገሮች
ቀላል ጥያቄ አሰራር ቀመር
አላቸዉ? አዎን።

በቀላሉ የምስል ማብራሪያዉን እና ንባቡን ለማግኘት፦https://youtu.be/JFglsCpfj_k?si=44WwNZVjXwS2L-w0
💯2👍1