የአብስራ
506 subscribers
223 photos
782 videos
183 files
1.21K links
ሰሚት ከንዶሚንየም ሆነው አስጠኚ ከፈለጉ እና የአንድ ሳምንት ነፃ ሙከራን ጨምሮ ለማግኘት በስልክ ቁጥር:- 09-38-58-75-08 ላይ በመደወል ወይም በቴሌግራም @committed12 በመጫን ያገኙኛል።

ለተማሪዎች ተጨማሪ ድጋፍ የሚሆን
ነፃ የተንቀሳቃሽ ምሰል ማብራሪያዎች እዚህ ተጭናችሁ ታገኛላሁ:- https://youtube.com/@yabserawondewosen?si=M3rU1wnXO8__6RBx
Download Telegram
አጭሩ ከ"Active=> passive" መቀየሪያዉ  ቀመር።

ብዙዎች "Active voice" ወደ "passive voice" መቀየር ድርጊቱ የተፈፀመበትን ጊዜ/"Tense" መቀየር መስሎ ይታያቸዋል እዉነታዉ ግን "Active Voice" የምንለዉ ስለ ደርጊት ፈፃሚው አጉልቶ ለማዉራት የምንጠቀመዉ ሲሆን "passive voice" የምንለዉ ደግሞ ድርጊቱ ስለተፈፀመበት አካል በዋነኛነት አተኩሮ የሚያወራ ነዉ፤

ለምሳሌ፦
Active - we love icecream.
እዚህ ጋረ "we" የድርጊት ፈፃሚዉ ነዉ፤ ስለሱም ነዉ አጉልቶ አረፍተ ነገሩ ማሳየት የፈለገዉ ለዛ ነዉም "Active voice" ላይ ያለ አረፍተ ነገር የተባለዉ።

passive - Icecream is loved by us.
እዚህ ጋር ደግሞ "Icecream" ድርጊቱ የተፈፀመበት ነዉ ፤ ስለሱም ነዉ አጉልቶ አረፍተ ነገሩ ማሳየት የፈለገዉ ለዛ ነዉም "passive voice" ላይ ያለ አረፍተ ነገር የተባለዉ።

ከ"Active => passive" በምትቀይሩ ጊዜ የምትጠቀሙት "Verb to be" ከአንዱ
"Tense" ወደ "Tense" የተለያየ ነዉ፤ ቢሆንም ግን በቀላሉ ወደ "passive" ለመቀየር እናንተ መመልከት የሚኖርባችሁን አና እነዛን ስትመለከቱ ምን አይነት "verb to be" እንደምትጠቀሙ የምናወራ ይሆናል፤

በመጀመሪያ ዋነኛዎቹን ከ"Active => passive" መቀየሪያ ቀመሮችን እንመልከት፤

Active - subject + verb +
object.

passive - object + verb to be + verb3 + subject

ቀደም ብሎ እንደተመለከታችሁት ከ"Active => passive" በምትቀይሩ ጊዜ ሁልጊዜም ልትከተሉት የሚገባዉ ቀምር ሲሆን "object" እና "subject" ቦታ ይቀያየራሉ፤ እንዲሁም አሁን የምናወራዉን "Verb to be"  ትጨምራላችሁ ከዛም ዋነኛዉን ግስ ወደ "Verb3" ትቀይሩታላችሁ።


በአረፍተ ነገራችሁ ዉስጥ "Verb 1" ካለ የምትጠቀሙት "Verb to be"=> "is/am/are" ነዉ።

ምሳሌ፦ he plays football.
football is played by him.

በአረፍተ ነገራችሁ ዉስጥ "Verb 2" ካለ የምትጠቀሙት "Verb to be"=> "was/were" ነዉ።

ምሳሌ -
Active - They studied verry hard for the exam.
passive - The exam was studied hard for by them.

በአረፍተ ነገራችሁ ዉስጥ "modal verb ፦ will, would, may, might, can, could, ought to, have to, need to, shall & should " ካለ የምትጠቀሙት "Verb to be"=>"be" ነዉ።

Active - he will play football every sunday.
passive -  football will be played every sunday by him.

በአረፍተ ነገራችሁ ዉስጥ "Verb1+ing " ካለ የምትጠቀሙት "Verb to be"=>"being" ነዉ።

ምሳሌ -
Active - he is playing football.
passive - football is being played by him.


በአረፍተ ነገራችሁ ዉስጥ "has/had/have " ካለ የምትጠቀሙት "Verb to be"=>"been" ነዉ።

ምሳሌ-
Active - he has played football.
passive - football has been played by him.

ስለ "Verb to be" በምናወራ ጊዜ አጋዥ ግስ ሆነዉ ሳለ ጠቀሜታቸዉ አረፍተ ነገሩ የሚነገርበትን ጊዜ ማሳየት ነዉ፤

በተጨማሪም  ተመሳሳይ ጊዜን የሚያሳዩ ግን የተለያየ የባለቤት ብዛትን የሚያሳዩም ናቸዉ ማለትም "was/were" ያለፈ ጊዜን ግን የተለያየ ቁጥርን፤

ምሳሌ፦
Active - They were studying verry hardfor the exam.
passive - The exam was being studied hard for by them.

እዚህ ጋራ እንደምትመለከቱት በ"Active" አረፍተ ነገሩ ላይ "were" የነበረዉን "passive" አረፍተ ነገሩ ላይ "was" ሆኗል ምክንያቱም ደግሞ ሁለቱም አንድ አይነት ጊዜን ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን(ከ"Active=> passive" ስትቀይሩ ጊዜዉን ስለማትቀይሩ) ግን የተለያየ የባለቤት ቁጥርን ለማሳየት ስላስፈለገ ማለት ነዉ።

"is/am/are" አሁን ላይ ያለ ጊዜን ግን የተለያየ የባለቤትን ብዛትን ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን፤

ምሳሌ፦
Active - They are playing football.
Passive - football is being played by them.

እዚህ ጋራ እንደምትመለከቱት በ"Active" አረፍተ ነገሩ ላይ "are" የነበረዉን "passive" አረፍተ ነገሩ ላይ "is" ሆኗል ምክንያቱም ደግሞ ሁለቱም አንድ አይነት ጊዜን ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን(ከ"Active=> passive" ስትቀይሩ ጊዜዉን ስለማትቀይሩ) ግን የተለያየ የባለቤት ቁጥርን ለማሳየት ስላስፈለገ ማለት ነዉ።

"has/have" ላይም አንድ አይነት ጊዜን ግን የተለያዩ የባለቤቶችን ቁጥርንም ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን፤ ስለዚህም ወደ "passive" ስትቀይሩ "active"ን ማለት ነዉ፤

ምሳሌ፦
Active - he has played with footballs already.
passive -  footballs have been played with by him.

እዚህ ጋራ እንደምትመለከቱት በ"Active" አረፍተ ነገሩ ላይ "has" የነበረዉን "passive" አረፍተ ነገሩ ላይ "have" ሆኗል ምክንያቱም ደግሞ ሁለቱም አንድ አይነት ጊዜን ለማሳየት እንጠቀማቸዋለን(ከ"Active=> passive" ስትቀይሩ ጊዜዉን ስለማትቀይሩ:) ግን የተለያየ የባለቤት ቁጥርን ለማሳየት ስላስፈለገ ማለት ነዉ፤

በስተመጨረሻ ሁሉም "passive voice" የሚጠቀመዉ ግስ "Verb 3" ነዉ ይህ ማለትም ብዙዉን ጊዜ መጨረሻዉ ላይ "-ed/-en/-ne/-d/-t"  ያሉት ሲሆን ብዙዉን ጊዜ ማለት ግን ሁል ጊዜ ማለት አይደለም።
👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግሶቹን (የድርጊት ቃላቶቹን) ብቻ በመመልከት ከ"active" ወደ "passive" መቀየር ይቻላል?
የአብስራ pinned «አጭሩ ከ"Active=> passive" መቀየሪያዉ  ቀመር። ብዙዎች "Active voice" ወደ "passive voice" መቀየር ድርጊቱ የተፈፀመበትን ጊዜ/"Tense" መቀየር መስሎ ይታያቸዋል እዉነታዉ ግን "Active Voice" የምንለዉ ስለ ደርጊት ፈፃሚው አጉልቶ ለማዉራት የምንጠቀመዉ ሲሆን "passive voice" የምንለዉ ደግሞ ድርጊቱ ስለተፈፀመበት አካል በዋነኛነት አተኩሮ የሚያወራ ነዉ፤ …»
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከባድ የሆኑት በተመጣጣኝ የአልጀብራ እና ያልታወቁ የተለዋዋጭ ዋጋዎችን በቀላሉ፤

ወዲያዉ ለመመልከት እዚህ ተጫኑhttps://youtu.be/z1qltLMNURo?feature=shared
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግሶቹን (የድርጊት ቃላቶቹን) ብቻ በመመልከት ከ"active" ወደ "passive" መቀየር ይቻላል?
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግሶቹን (የድርጊት ቃላቶቹን) ብቻ በመመልከት ከ"active" ወደ "passive" መቀየር ይቻላል?
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከባዶቹ በጎነ ሶስቶች ተመሳሳይነት እና አንግላቸዉን ማግኘት ዙሪያ ልትጠየቋቸዉ የምትችሏቸዉን በቀላሉ፤

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/jnNUWa1B3Fk?si=R9jEg74HwTGsgx8n
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግሶቹን  (የድርጊት ቃላቶቹን) ብቻ በመመልከት ከ"active" ወደ "passive" መቀየር ይቻላል?(5 ጥያቄዎች በአንድ ላይ)

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/uc4uS4W4bw0?feature=shared
ዋናኞቹ አራቱ የአረፍተ ነገሮቹ አይነቶች እና አይነቶቻቸዉ

Declarative Sentences - እዉነታን ለመናገር የምንጠቀማቸዉ የአረፍተ ነገር አይነቶች ናቸዉ፤ እነሱም "Simple Declarative Sentences" እና "Complex Declarative Sentences" ተብለዉ ይከፈላሉ፤


     - Simple Declarative Sentences - አንድ በራሱ ሙሉ ትርጉም ሰጥቶ መቆም የሚችል አረፍተ ነገር ሲሆን፤
         - ምሳሌ፦"She loves to dance."

    - Complex Declarative Sentences - በውስጡ ሁለት እና ከዛ በላይ ሃረጎች ሊኖሩት ይችላሉ በተጨማሪም በራሳቸዉ ሙሉ ትርጉም መስጠት የሚችሉ እና  ጥገኛ ሃረጎችን ሊያካትቱ ይችላሉ፤
         - ምሳሌ፦"Although she was tired, she went to the party because she wanted to see her friends."

  Interrogative Sentences - ጥያቄያዊ አረፍተ ነገሮች፤ እነሱም "Yes/No Questions" እና "Wh-Questions" ተብለዉ ይከፈላሉ፤
    - Yes/No Questions -  አዎ ወይም አይ ጥያቄወችን ለመጠየቅ የምንጠቀማቸዉ አረፍተ ነገሮች ናቸዉ፤
       - ምስሌ፦ "Did you finish your homework?"
    - Wh-Questions - አንድን የቦታ፣ የጊዜ፣ የማንነት፣ የባለቤትነትን እና በአጠቃላይ ግልፅ  መረጃ ለመጠየቅ ምንጠቀማቸዉ ናቸዉ፤

       ምስሌ፦ "Where did you go last night?"

  Imperative Sentences - ትዕዛዛዊ አረፍተ ነገሮች የምንላቸዉ ሲሆኑ ፤ እነሱም "Direct Commands" እና "Polite Requests" ብለን እንከፍላቸዋለን፤

   Direct Commands - ግልፅ የሆነ መደረግ ያለበትን ነገር ለመናገር እንጠቀማቸዋለን ፤
     - ምሳሌ፦ "Close the window."

    - Polite Requests - ጥያቄያዊ በሆነ መንገድ ትዕዛዝን ያስተላልፋሉ፤

     - ምሳሌ፦ "Could you please pass the salt?"

  Exclamatory Sentences
- አጋናኝ አረፍተ ነገሮች ናቸዉ ፤ እነሱም "Expressive Exclamations" እና "Interjections" ናቸዉ፤

    - Expressive Exclamations - ስማቸዉ እንደሚያሳየዉ የተለያዩ ልክ እንደ ደስታ፣ ፈንጠዝያ ፣ ድንጋጤ ... ያሉ ጠንካራ ስሜቶችን ለመግለፅ ነዉ ጠቀሜታቸዉ፤

      - ምሳሌ፦ "What a beautiful day!"

  - Interjections - ስሜትን ገላጭ ባለአንድ  ቃላቶች ናቸዉ፤
ምሳሌ፦ "Wow! That was amazing!"
ሰሚት ከንዶሚንየም ሆነው አስጠኚ ከፈለጉ እና የአንድ ሳምንት ነፃ ሙከራን ጨምሮ ለማግኘት በስልክ ቁጥር:- +2519-38-58-75-08 ተጭነው በመደወል ወይም በቴሌግራም @committed12 በመጫን ያገኙናል።

ለተማሪዎች ተጨማሪ ድጋፍ የሚሆን
ነፃ የተንቀሳቃሽ ምሰል ማብራሪያዎች እዚህ ያገኛሉ:- (https://youtube.com/@yabserawondewosen?si=M3rU1wnXO8__6RBx)
የአብስራ pinned «ዋናኞቹ አራቱ የአረፍተ ነገሮቹ አይነቶች እና አይነቶቻቸዉ፤ Declarative Sentences - እዉነታን ለመናገር የምንጠቀማቸዉ የአረፍተ ነገር አይነቶች ናቸዉ፤ እነሱም "Simple Declarative Sentences" እና "Complex Declarative Sentences" ተብለዉ ይከፈላሉ፤      - Simple Declarative Sentences - አንድ በራሱ ሙሉ ትርጉም ሰጥቶ መቆም የሚችል…»
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መቼ ነዉ "Verb3"ዎችን የምትጠቀሙት?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/iiX5CMgmu10?si=LirTXZHotagfkgqc
ግሶች ምንድን ናቸዉ? ጠቀሜታቸዉስ?
-ግሶች/"Verbs" የምንላቸዉ የድርጊት ቃላት ሲሆኑ ያዉ ጠቀሜታቸዉ ድርጊትን ማመላከት ነዉ፤
ምሳሌ፦

play - መጫወት
eat - መመገብ
read - ማንበብ
study - ማጥናት የመሳሰሉት ምሳሌዎች መሆን ይችላሉ፤

በተጨማሪም በሚጠቀሙት የግስ አይነት ጊዜንም ሊያመላክቱ ይችላሉ ስለሀሸነም በመቀጠል በተለያዩ ጊዜዎች ላይ የአጠቃቀም ልዩነታቸዉን እናያለን፤

የ"verb1"፣ የ"verb 2" እና የ"verb 3" ልዩነቶች

Verb 1- ማለት ግሱ ምንም አይነት ለዉጥም ሆነ ቅጥያ ሳይኖረዉ(ባለቤቱ 1 ሲሆን -s/-es ከመጠቀሙ ዉጪ)ማለት ሲሆን፤ የምንጠቀመዉ አሁን/"present"ላይ ያለ ጊዜን ለማሳየት ነዉ ፤
ምሳሌ፦
Verb1
play/plays
eat/eats
read/reads
drink/drinks
study/studies
watch/watches

Verb2 - ማለት ግሱ እየገለፀ ያለዉ ጊዜ ያለፈ "past" መሆኑን ሲሆን ብዙውን ጊዜ በ"-ed/-d/-t" የሚያልቁ ናቸዉ፤ ብዙ ጊዜ ማለት ግን ሁልጊዜ ማለት አይደለም ፤ ምሳሌዎችን እንይ፦
Verb1 => Verb2

- drink => drank
- play=> played
- teach => taught
- eat => ate
- think => thought

Verb3 - የምንላቸዉ ደግሞ ከአንድ ድርጊት በፊት የተፈፀመ ድርጊትን(ሁሉንም የ"perfect tense"ሶች) ለማሳየት ሲሆን ጠቀሜታቸዉ ብዙዉን ጊዜ በስተመጨረሻቸዉ "-ed/-en/-ne/-d/-t"፤ ምሳሌ፦

Verb1 => Verb2 => Verb 3
- drink => drank => drunk
- play=> played => played
- teach => taught => taught
- eat => ate => eaten
- think => thought => thought

Verb1+ing - የምንላቸዉ ደግሞ ጊዜ ወስዶ የተፈፀመ ነገር (continuous) መሆኑን ለማሳየት ነዉ ምንጠቀመዉ፤

Verb1 => Verb1+ing
- drink => drinking
- play=> playing
- teach => teaching
- eat => eating
- think => thinking

ማስታወሻ እነዚህ የግስ አይነቶች የተለያየ ጊዜ ላይ ልትጠቀሟቸዉ የምትችሏቸዉ ናቸዉ፤ ማለትም "Verb1"=> "present"=>አሁንን
"Verb2"=> "past"=>ያለፈ
"Verb3"=> "perfect"=>ከድርጊት በፊት የተደረገ ድርጊትን
"Verb1+ing"=> "continuous"=>ጊዜ ወስዶ የተፈፀመ ድርጊትን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መቼ "Verb1" ልትጠቀሙ ትችላላችሁ?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/7dRzS2wVs0A?si=al_bj1QwrlQfJSEo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መቼ ነዉ "-ing"ያለዉን ግስ ምትጠቀሙት?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦ https://youtu.be/yVCVdaMhIgA?feature=shared
ይህ 2ተኛ የወጣዉ የኔ ተማሪ  የሆነዉ የተማሪ ኪሩብ ሃይሉ የአንደኛ ሴሚስተር  ዉጤት ሲሆን

ተማሪ ኪሩብ በኢንግሊዘኛ ትምህርት 100 ሲሆን ያመጣዉ፤ ከ 7 ትምህርቶች ማለትም  647 / 700  በአማካይ ዉጤት 92.428 % በማስመዝገብ ወደ ሁለተኛ ሴሚስተር ከክፍሉ 2ተኛ በመዉጣት በአሸናፊነት ወደሁለተኛ ሴሚስተር ገብቷል።

በመሆኑም ሰሚት ኮንዶሚንየም ሆናችሁ ልክ እንደዚሁ ልጆችዎ ልዩ እና አመርቂ ዉጤት እንዲያስመዘግቡ የምትፈልጉ ከሆነ በ+251938587508 በመጫን ታገኙኛላችሁ።


- የአብስራ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መቼ "Verb2" ልትጠቀሙ ትችላላችሁ?

በቀላሉ ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/UBgAA4AFyi4?si=AKxEy8iKiDc_-iDA
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ምን ሲያጋጥማችሁ ነዉ "Verb 1/Verb 2/Verb 3" ልትጠቀሙ የምትችሉት?

በፍጥነት ለመመልከት እዚህ ተጫኑ፦https://youtu.be/DuOX7oOLy9o?feature=shared