YG Tech
3.69K subscribers
27 photos
12 links
Accurate crypto news, trading guidance, and digital income ideas
Download Telegram
አዲሶቹ IPHONE.... የባትሪ ቆይታ 🙌

የቱ ተመቻችሁ ከ አቅማችሁ ጋር

IPHONE 17♥️
17 👍
17 pro🙏
17 air 🔥
16 pro max 👌
ሰበር ዜና!!

በአሁኑ ሰአት በተወሰነ የአለም ክፍል ባጋጠመ የኢንተርኔት መቋረጥ ብዙ ድረገፆችና ፕላትፎርሞች እየሰሩ አይደለም።

የAmazon web service የVirginia server ለመቋረጡ ምክንያት ነው ተብሏል።

አማዞን ዌብ ሰርቪስ ለብዙ ድርጅቶች የserver፣ የdatabase እንዲሁም የstorage አገልግሎት ይሰጣል።

በዚህ ምክንያትም ብዙ ባንኮች፣ ድረገፆች፣ የጌሚንግ ፕላትፎርሞች፣ የማህበራዊ ድረገፆች የመሳሰሉት እየሰሩ አይደለም።

በግልፅ የታወቁት እነዚህ ናቸው።
Amazon, Amazon Alexa, Amazon Music, Amazon Prime Video, Amazon Web Services, Ancestry, Asana, Atlassian, Bank Of Scotland, Blink Security, BT, Canva, Clash Of Clans, Clash Royale, Coinbase, Dead By Daylight, Duolingo, EE, Epic Games Store, Eventbrite, Flickr, Fortnite, Government Gateway services (including HMRC), Halifax, Hargreaves Lansdown, Hay Day, Hinge, HMRC, IMDB, Jira Software, Just Eat, Life360, Lloyds Bank, Microsoft 365, My Fitness Pal, Ocado, Peloton, Perplexity AI, Playstation Network, Pokemon Go, Rainbow Six, Reddit, Ring, Roblox, Rocket League, Signal, Sky Mobile, Slack, Smartsheet, Snapchat, Strava, Square, Tidal, WhatsApp, Wordle, Xero, Zoom
ይህ መቋረጥ ኢትዮጵያ ላይ አይከሰትም ምክንያቱም ኢትዮጵያ የምታገኘው AWS ሰርቨር ምንም ችግር ስላልደረሰበት።

የተወሰኑት የAWS ሰርቨሮች መገኛ
፨ US-East-1 → Virginia (currently having issues)
፨ US-West-2 → Oregon
፨ EU-West-1 → Ireland
፨ ME-South-1 → Bahrain (serves much of the Middle East & Africa)
፨ AF-South-1 → Cape Town, South Africa
New android features

Google Android ስልኮች ላይ በAI የታገዘ notification summarization ሊጀምር ነው።

ይህ feature በlatest Android 16 ላይ ተካቶ በGoogle pixel ስልኮች ላይ እየሰራ ያለ ሲሆን በቅርቡም ለSamsung ስልኮች ይለቀቃል ተብሏል። ስልካችሁ ላይ የሚገቡ ረጅም notifications summerize ተደርገው በ1 ቅፅበት የሚታዩ ይሆናሉ።

ከዚህ በተጨማሪ Google አዲስ የnotification organizer launch ያደረገ ሲሆን በዚህ ፊቸር ኖቲፊኬሽኖች እንደ ጠቃሚና አስፈላጊነታቸው low priorityና high priority ተብለው የሚመደቡ ይሆናል።

በመጨረሻው የAndroid 16 version ጠበቅ ያለ parental control የሚካተት ሲሆን ወላጆች የልጆቻቸውን ስልክ screen time መመጠን፣ የእንቅልፍ ሰዓታቸው ሲደርስ automatically እንዲዘጋ ማድረግ፣ በእያንዳንዱ app ላይ ምን ያክል ጊዜ ማጥፋት እንዳለባቸው መወሰን ይችላሉ ተብሏል።
Meta ማክሰኞ ዕለት በአይን መነፅር ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ይፋ አድርጓል፣ ይህም ሰዎች ጫጫታ ባለበት አካባቢ ሲሆኑ በተሻለ ሁኔታ እንዲሰሙ ያስችልዎታል። ይህ ባህሪ መጀመሪያ ላይ በአሜሪካ እና ካናዳ ውስጥ በሬይ-ባን ሜታ እና በኦክሌይ ሜታ HSTN ስማርት መነፅሮች ላይ ይገኛል ሲል ኩባንያው ተናግሯል። በተጨማሪም መነፅሮቹ Spotifyን በመጠቀም አሁን ባለው እይታዎ ውስጥ ካለው ጋር የሚዛመድ ዘፈን እንዲጫወቱ የሚያስችልዎ ሌላ ማዘመኛ እያገኙ ነው።
chatGPT, X, Telegram Wallet እየሰሩላችሁ ነው? አሳዉቁኝ
የአዲስ አበባ ፖሊስ የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ሙያዊ ክብርን የሚያዋርዱ፣ ከህብረተሰቡ ባህል፣ እምነትና ሞራል ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን የሚያስተላልፋ" የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪዎችን" (Social Media Influencers and Content Creators) መያዝ እንደጀመረ አስታውቋል።

ዝርዝር መረጃ Tikvah_ethiopia
ChatGPT ላይ መጠቀም ያሉባችሁ ወሳኝ ፊቸሮች
🔴Codex
🔴Project
🔴Canvas
🔴Study and learn
🔴GPTs
🔴Quizzes
የኢትዮዽያን የቴሌኮም ኢንዱስትሪ ሁለተኛ አቅራቢ ሆኖ የተቀላቀለው ሳፋሪኮም ኢትዮዽያ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉ ተሰማ።

ሳፊሪኮም ኢትዮዽያ ለደንበኞቹ የዋጋ ማሻሻያ ወይም የአገልግሎት ጭማሪ ማድረጉንም ከኦፕሬተሩ ሰምተናል።

ጭማሪ ተደርጎበታል የተባለው የዳታ ጥቅል አገልግሎት ላይ ነው።

ሳፋሪኮም ኢትዮዽያ ይህንን ጭማሪ ያደረገው የኢንቨስትመንት እና የኦፕሬሽናል ወጪዎች ከፍ ማለታቸውን ተከትሎ እንደሆነ ሰምተናል።

ኩባንያው ለጊዜው ጭማሪ ያደረገበት የዳታ ጥቅል አገልግሎት ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ አልጠቀሰም።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ኢንተርኔት እያቀረበ ያለው ካወጣው ዋጋ ከእጥፍ በላይ እየቀነሰ ወይም እየከሰረ መሆኑንን መናገሩ ይታወሳል፡፡

ኩባንያው ስራውን እያስፋፋ፣ አገልግሎቱን እያቀረበ ያለውም በባለ አክሲዮኖቼ ድጋፍ ነው ብሎ ነበር፡፡

የኮሙኒኬሽን ባለስልጣን የሞባይል ኢንተርኔት ዋጋን ተመልክቶ አዲስ ተመን እንደሚያወጣ እንጠብቃለን ፣ ያ ካልሆነ ግን የቴሌኮም ዘርፍ ባለበት ይቆማል የሚል ስጋት አንዳለሁ ኩባንያው ከወራት በፊት መናገሩ ይታወሳል፡፡

ጭማሪው ስንት ነው? በComment አሳውቁን።

Via shegerfm.com
👍1
በኦንላይን ይዘት ገቢ ላይ ግብር ሊጣል ነው

ታኅሣሥ 17፣ 2018
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ቲክቶክና ዩቲዩብን ጨምሮ ከሌሎች የዲጂታል ገጾች ገቢ የሚያገኙ አካላት ግብር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አሰራር እየዘረጋ መሆኑን አስታውቋል።

ባለፈው ዓመት በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት፥ በኦንላይን ይዘቶች ገቢ የሚያገኙ አካላት በሙሉ በገቢዎች ቢሮ ተመዝግበው የግብር መለያ ቁጥር የማውጣት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

ቢሮው ይህን ሥራ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከንግድ ቢሮ እና ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ነው የገለጸው።

የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ገቢያቸውን በፈቃደኝነት እንዲያሳውቁ ጥሪ ቀርቦላቸዋል መባሉን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

ቁጥጥሩ ከይዘት ፈጣሪዎች ባለፈም ምርትና አገልግሎት የሚያስተዋውቁ ነጋዴዎችንም ይመለከታል ነው የተባለው።

(አራዳ ኤፍ ኤም)
በVLC media player በሺ የሚቆጠሩ አለም አቀፍ የቴሌቭዥ ጣቢያዎችን ቀጥታ መከታተል እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?

ለምሳሌ
National Geography, BBC, MTV, Fox News, ABC, NBC እንዲሁም ሌሎች የስፖርትና የህፃናት ቻናሎችን ቀጥታ መከታተል ይችላል።

፨ ይህን ለማድረግ

🔴 VLC Media Player ከከፈታችሁ በኋላ ከላይ menu bar ላይ media የሚለውን click ታደርጋላችሁ።

🔴 ከሚዘረዘርላችሁ ውስጥ Stream የሚለውን ምረጡ።

🔴 ከዛ Network የሚለውን click ካደረጋችሁ በኋላ Please enter a network URL የሚለው ጋ ይህን ሊንክ paste ታደርጋላችሁ።



🔴 ከዛ stream, Next, Next, Stream ብላችሁ ትጨርሳላችሁ።

🔴 ይህን ካደረጋችሁ በኋላ ከታች ያለውን Toggle Playlist የሚለውን ስትመርጡ ሙሉ ቻናሎች ይዘረዘሩላችኋል። የተመቻችሁን እየመረጣችሁ መክፈት ትችላላችሁ።