ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለመናፍቃንና ለአህዛብ መልስ አላት!
1.98K subscribers
328 photos
21 videos
6 files
109 links
እዚህ ቻናል ውስጥ አህዛብ እና መናፍቃን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች በክርስቶስ አምላካችን ፣ በቅዱሳኑ ትሩፍት እና በስርዓተ ቤተ ክርስትያን ላይ ስለ ሚነሱ የስህተት ና የቅሰጣ ትምህርቶች ሙሉ መልስ የሚሰጥበት ቻናል ነው። በተመሳሳይ፦
* የቤተ ክርስትያን ቀኖና፣ዶግማ፣ትውፊት፣ታሪክ
* ነገረ ቅዱሳን
ይዳስሳሉ ይነገራሉ።

ለማንኛውም አስተያየት በዚህ ታገኙናላችሁ
@Selamawitttttttt
Download Telegram
እንኳን ለሊቀ መላእክት፡ አኃዜ መንጦላዕት፣
መልአከ ኃይል ፡ ሰዳዴ ሳጥናኤል ፣
መዝገበ ርህራሄ ወሳህል ፡ መልአከ ምክሩ ለልዑል…

ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ።

🍁 ሚካኤል ፩ እምነ መላእክት ቅዱሳን እስመ በዲበ ሠናይቱ ለሰብእ ተአዛዚ ዲበ ሕዝብ ።

⇨ ለሰው ባደረገው በጎነት ላይ ለሕዝቡ ታዛኝ ነውና ከነበሩ ከመላእክት አንዱ ሚካኤል ነው።

⇨ Michael, one of the Holy Angels, namely the one put in charge of the best part of humankind, in charge of the nation.

. 🌴 [ሔኖ ፮፥፭]

🍁 ወውእቱ ቀዳማዊ ርኁቀ መዓት ወብዙኀ ምሕረት ሚካኤል ውእቱ

⇨ እሱም የመጀመርያው ይቅር የሚል ከመዓትም የራቀ ቅዱስ ሚካኤል ነው"

⇨ This first is Michael, the merciful and long-suffering without an urge to harm.

. 🌴 [ሔኖ ፲፥፲፪]

“ለእውነት ነገር የሚላክ ሚካኤልም በውነት አመስጋኝ ነው እውቀቱን የሚገልጥልኝ ጻድቃን እስከ ገቡባቸው ድረስ የእውነት በሮቹን የሚከፍትልኝ እሱ ነው።” [ተረፈ ባሮክ ፭፥፴፭]
"ሰኔ ፳ ሕንጸታ ቤተክርስቲያን "
በዚሕች ቀን በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በአምላክ እናት ስም ታንጻለች።
ከመጀመርያው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን "ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕዛበ" (አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ) ማቴ. 28:19 ባላቸው ቃል መሠረት ዓለምን በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል::

የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና (ዮሐ. 6:56) አበው ሐዋርያት ቁርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር::

በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲሕ ይከናወን ነበር:: ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኩራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቁጥር እጅጉን በዛ::

በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ:: በዚሕ ምክንያት መምሕራን ሕዝቡን "ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?" ቢሏቸው "እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት እንደሆን የለን" ሲሉ መለሱላቸው::

ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ጳውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች "ለምን አናንጽም" ብለው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ግን "ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም" አለ:: (ለዚሕ ነው ዛሬም ሊቀ ጳጳስ ካልፈቀደ ቤተ ክርስቲያን የማይታነጸው::)

ከዚያ ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ጴጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱም "የጌታችን ፈቃዱ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ" ብሎ አዋጅ ነገረ::

በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ። በሱባዔአቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ::

ሁሉንም ሐዋርያት በደመና ጭኖ ፊልጵስዩስ አደረሳቸው:: ከከተማ ወጣ ብሎ ባለ መሬት ላይም "ቤተ ክርስቲያንን በእናቴ ስም አንጹ" ብሎ አዘዛቸው:: ለቅዱስ ጴጥሮስም ሦስት ዓለቶችን ሰጠው::

እነዚያን መሬት ላይ ተክሎ ጌታችን ቆሞለት ሐዋርያቱ እየተራዱት ግርምት የምትሆን ሦስት ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን በ52 ዓ/ም በዚህች ቀን አንጿል::

ቤተ ክርስቲያኗን ነገ ጌታችን ቀደሳት የምንል ነንና ይቆየን::
አምላካችን የድንግል እናቱን ፍቅር : የተቀደሰች ቤቱን ጸጋ : የቡሩካን ሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን::

ሰኔ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
2.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
3.ቅዱሳን ሐዋርያት
4.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ዕረፍቱ)

ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
4.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
5.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
6.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት

"በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::"
(፪ቆሮ. ፲፩፥፳፫-፳፰)

ዜና ቅዱሳን (ታሪክ)
"ሰኔ ፳ እና ፳፩"
ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።

ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ።

ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር።

ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።

የእምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን!
ክፉን በመልካም እንዴት መቃወም ይቻላል?

የምታስፈራዋን የፍርድ ቀን እንባህን በማፍሰስ አስብ። ተስፋህ በእርሱ ዘንድ የቀና የጸና ይሆን ዘንድ የፈጣሪህን መልካም ተስፋውን ስበክና መስክር።
መቀባጠር የሚያበዙትን በአርምሞ ጸጥ አርጋቸው።ሐሜተኞችን በትዕግሥትህ ገሥጻቸው እንቅልፋሞችን በትጋትህ አንቃቸው ኃጥኣንን አጽናናቸው የተዋረዱትን ራስህን በማዋረድ በትህትና አረጋጋቸው ገንዘብ በማጠራቀም የበለጸጉትን ናቃቸው። ከዓለም የተለየህ ሁን የዓለም ፍቅሯና ትርፏ ፍርድን እንዲያመጣ እወቅ። ከዚህች ዓለም ትሸሽ ዘንድ ፍጠን ተሽቀዳድም። ነፍስህንም ከመቀባጠር ጥቅም ከሌለው ከንቱ ጨዋታና ዋዛ ፈዛዛ አሳርፋት። ይልቁንም የተሰወረውን ለሚያውቅ እግዚአብሔር ምስጋና አቅርብ እንጅ ድኽነትን እንደ ወርቅ ውደዳት።
(መጽሐፈ ወግሪስ ገጽ 34)
ዝክረ ሰማዕታት በሻሸመኔ ፩ኛ ዓመት

"አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዛ ዓለም።
ወከዓው ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር
ወተዐገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግሥተ ሰማያት።
ተሣሃለነ በከመ ዕበየ ሳህልከ።
ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ፤
ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ።
ስለ መንግስተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሱ።
እንደ ይቅርታህ ብዛት ይቅር በለን።"
(የሐሙስ ውዳሴ ማርያም)

በኦሮሚያ የተጨፈጨፉ ሰማዕታት አንደኛ ዓመት ሲታሰብ

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል፡
“ተወዳጆች ሆይ!
ስለ ሰማዕታቱ ብቻ የምትሰሙ አትሁኑ፡፡ እነርሱን ለመምሰልም ተጣጣሩ እንጂ፡፡ ለጊዜው ብቻ የምታደንቋቸው አትሁኑ፡፡ ወደ ቤታችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ልቡናችሁ ውሳጤም ዘልቀው እንዲገቡ አድርጉ፡፡ ዘወትር አስቧቸው፡፡ በልቡናችኁ ጓዳ እንዲገቡ አድርጓቸው፡፡ እናንተን ትተው ይሔዱ ዘንድ አትፍቀዱላቸው፡፡ ይኽን ያደረጋችሁ እንደሆነ ዘወትር እያያችኋቸው ትበረታላችሁ፡፡ በእምነት ትጸናላችሁ፡፡ የለበሱትን የጽድቅ ጥሩር፣ የያዙትን ምግባረ ወንጌል፣ የእምነት ጋሻ፣ የመዳን ራስ ቁር፣ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ እየተመለከታችሁ ትበረታላችሁ፡፡”

በረከታቸው ይድረሰን!
ደብተራነት ለዘልአለም ይኑር!
እያነበባችሁ ሼር በሀይለኛው ሼር አድርጉት

የተሰማኝ ደስታ እጥፍ ድርብ ነው “ለምን?” ካላችሁ ኦርቶዶክሳዊነት ረቀቅ ነው።ፍቅሩ ሲገባህ የቅዱሳኑ ተጋድሎ ሲማርክ የእመ አምላክ እናትነት፣ደግነት፣ምልጃና በረከት ሲፀናብህ የቅድስት ሥላሴ አምላክነት ምስጢሩ ሲሰርፅብህ የቅድስት ቤክ እውነተኛነት ቀጥተኝነት ሲገባህ በፈቃድህ ትማረካለህ ወደህ እጅ ትሰጣለህ።

ውድ ወዳጆቼ ይህንን ስራ ማለት አልፈልግም ይህንን ታላቅ ሱታፌ በእኛ ደካማ እና ሀጥያተኞቹ ላይ አድሮ የስራው እግዚአብሔር ብቻ ነው።ወንድሞቼን እና እህቶቼን አባቶቼን እና እናቶቼን ከጠፉበት ሰብስቦ ወደ በረቱ ያስገባቸው መንፈስ ቅዱስ ነው።የልባቸው ጥያቄ እርሱ በሀይሉ ስላወቀ ነው።ከእኔም ከጓደኞቼም የሆነው እንደ አንድ ታናሽ መታዘዝ ብቻ ነው።ምስክርነታቸውን የሰጡ ብዙ ናቸው።እኔም ከፈቃዳቸው ነውና እንድንማርበት እነዚህን ለአብነት እንሆ • • •

ኑሐሜን ግዛው(መአዛ ማርያም)ከፕሮቴስታንት(ካናዳ)
ነፃነት ሻፊ(ወለተ መድህን)ከፕሮቴስታንት(ኖርዌይ)
ኤፍሬም አዱኛ (ወልደ ጊዮርጊስ)ከፕሮቴስታንት
ዮናስ ደሞዝ(ገብረ ሥላሴ)ከፕሮቴስታንት
ዳናዊት ዮሴፍ(እህተ ማርያም)ክፕሮቴስታንት(አውስትራሊያ)
ዳዊት ዳባ(ገብረ ሥላሴ)ከፕሮቴስታን
አቶ ጊድዮን ኤባ(ወልደ አብ)ከፕሮቴስታንት
ወ/ሮ መርከብ ሞሲሳ(ሥርጉተ ማርያም)ከፕሮቴስታንት
(ያልተጠቀሱ 4 ሴት እና 9 ወንድ)

ናኦድ ኢሳያስ(ገብረ ማርያም) ከኢቫንጀሊካን
ብሌን ዋለልኝ(ወለተ ገብርኤል)ከሞርሞን(ይህ ሀይማኖት እኔ አላውቀውም)

አሚን ዳውድ(ክንፈ ገብርኤል)እስልምና
ሙራድ ሲራጅ(ወልደ ማርያም)ከእስልምና
ቶፊቅ ኑሩ(አክሊለ ገብርኤል)ከእስልምና
ሒክመት ኑርሴን(ሥርጉተ ሥላሴ)ከእስልምና
ሙና ሙሐመድ(አስራተ ማርያም) ከእስልምና
ሙሐመድ ሷሊህ ሙሐመድ( ወልደ ሩፍኤል)ከእስልምና
(ያልተጠቀሱ 3 ሴት 3 ወንድ)

ጉቱ ገላና (ወልደ መስቀል)ከሀገር ባህል እምነት

እነዚህ የክርስቶስ ቤተሰቦች የቅድስት ቤተክርስትያን ልጆች ሆነዋል እግዚአብሔር የወደደውን ከወደደው ቦታ በፍቅሩ ይጠራል።ገና እርሱ በፈቀደው ግዜና ሰዓት ሌሎችንም ይጠራል።

እናንተ የክርስቶስ ሙሽሮች እንግዲህ የጠራችሁ በቤቱ ያፅናችሁ ለክብር እና ለፅድቅ ያድርግላችሁ።

ምስጋና ለክንቱ ውዳሴ ቢጥልም እኔ ግን ወንድምቼን እና እናቶቼን ከልቤ በእግዚአብሔር ሥም አመሰግናለሁ።
ቢኒ(ኃይለ ገብርኤል)
ትንሹ(ወልደ ኢየሰስ)
ወ/ሮ ንግስቲ(ሒሩተ ሥላሴ)
አይመን ጆርጅ(ገብረ ፃድቅ)
እግዚአብሔር ይስጣችሁ።ባደረጋችሀት ልክ ሳይሆን አብዝቶ ይስጣችሁ!