Woldia University®🕎
2.75K subscribers
42 photos
4 videos
4 links
WHAT IS NEW!!
Info about Woldia University,📝
Talk about most burning issues of the student🗣
🔱Motivations
Funny GIFs😂
⚜️Great restaurants in the city and their foods🍔
for any comments and ads
@VJ_Sura
Download Telegram
ስማኝ ታናሼ....
በመጀመሪያ ዩንቨርስቲ ገባን፡፡ ያስገረመንን ትልቅ በር እያለፍን፡፡
ገና በመጀመሪያዎቹ ቀናት ምድብ ድልድል ወጣልን፡፡ ልዩ የቅበላ ፕሮግራም ከአማራ ክልል ለመጣችሁ፣ ለኦሮሚያ ተወላጆች፣ ለተጋሩ፣ በጌታ ለሆናችሁ፣ ለኦርቶዶክሳዊያን፣ ለሙስሊም ወንድሞቻችን ወ.ዘ.ተ አይነት ማስታወቂያዎች ግድግዳዎቻችንን እያጨናነቁት፡፡ “እየመደቡን ይሁን እየሰደቡን ማርያም ትወቅ፡፡” ነቄ ያልነው ሰኞ የአማራ ክልል የስነፅሁፍ ፕሮግራም፣ ማክሰኞ የተጋሩ የጥበብ ምሽት፣ እሮብ የኦሮሚያ የባህል ምሽት፣ ሃሙስ ግቢጉባዔ፣ አርብ ፌሎውሺፕ.....እያልን ሰባቱንም ቀናት መታደም ጀመርን፡፡ ምንያቱም ፍሬሽ ነበርን፡፡በዚያውም ዶርም ሲደለደል የአገር ልጅ የሚለው ሃሳብ የጎጥ ልጅ የሚለውን እንደሚወክል ተማርን፡፡

በገባንበት ሰሞን ለመጀመሪያ ጊዜ ካፌ ገባን፡፡ ሽታው እያጥወለወለን መሰለፍ ጀመርን፡፡ “አመቱን ሙሉ ይሄንን እንዴት ነው የምንለምደው” ስንል ተገረምን፡፡ በዚያው ሰሞን ላውንጅ የሚባል ማስታገሻ እንዳለ አወቅን፡፡ እዚያም ሄደን ተሰለፍን፡፡ የያዝነው ገንዘብ እና ዳቦ ቆሎ ስላለቀ ባንክቤትም ሄደን ተሰለፍን፡፡
ታናሼ ህይወት በካምፓስ እንዲህ ይጀምራል፡፡

ብዙ ሳትቆይ ክላስ ትጀምራለህ፡፡ ገና በመጀመሪያው ቀን አስደንጋጭ እንግሊዘኛ ጆሮህ ላይ እንደ መብረቅ ይወርድብሃል፡፡ “ከእነዚህ ጋ ተምሬ አንድስ ሴሚስተር እዘልቃለሁ?” ትላለህ፡፡ አትፍራ ፡፡ በሴሚስተሩ መጨረሻ አንተ አስኮራጅ እነሱ ኮራጅ በአመቱ መጨረሻ ደግሞ አንተ ሰቃይ እነሱ ወራጅ ትሆናላችሁ፡፡ ከጎንህ የብርጋዴር ጀነራል እከሌ ልጅ ይቀመጣል፡፡ ከሱ ፊት የፓስተር እከሌ ልጅ አለች፡፡ ከኋላህ ሰለሳ ግመልና መቶሃምሳ ፍየል ያለው የአርብቶ አደር ልጅ አለ፡፡ ከሱ ጎን “የጤፍ ተክል አይቼ አላውቅም” ያለችዋ ልጅ፥ “የዶሮ ብልት ስንት እንደሆነ አላውቅም” ካለችዋ ሞልቃቃ ጋ ተቀምጣ ታያለህ፡፡ እነዚህ ሁለቱ ክፍል በጊዜ ገብተው አያውቁም፡፡ ከነሱ ጎን ከሁሉም ቆንጆ ነኝ ብላ የምታስበዋ፣ አንገቷን እንኳን ስታዞር ሜካፕዋ እንዳይበላሽ የምትጠነቀቅ የምትመስለው ቄንጠኛ ልጅ ትቀመጣለች ..እኛ ግን አንወዳትም፡፡ ጥግ ላይ ከሁሉም ቆንጆ ናት ብለን የምናስባትና የምንወዳት አይናፋር ትቀመጣለች፡፡ ከሁላችንም ፊት ክረምት ክረምት በሰራው ቀን ስራ ራሱን የሚያስተዳድረው ሰቃይ ይቀመጣል፡፡ ከጎኑ እንትን ሆቴል በስሙ የተሰየመለት ልጅ አለ፡፡ ይህ ሁሉ የሚገባህ ግን ስትቆይ ነው፡፡ ስትቆይ በኢትዮ-ኤርትራ ጊዜ የዘመተ ልታከብረው የሚገባህ ሰው አብሮህ እንደሚማር ታውቃለህ፡፡ ስትቆይ በጣም ዝምተኛው ልጅ ጎበዝ ሰአሊ እንደሆነ ይገባሃል፡፡ ብረት የሚገፋው ጉልቤው ልጅ ከሁሉም ፀባየኛ እና ምስኪን ይሆንብሃል፡፡ ከሁሉም ሴቶች አስቀያሚ ናት ያልካት የሚያምር ድምፅ ያላት ዘማሪ ትሆናለች፡፡ ከዛ ደግሞ እንደኔ አይነት አንድ ሁለት “ጥበብ ጠራችኝ ወ አጠናገረችኝ ፍሪኮች” እንኖራለን፡፡ ጎበዝ ዘፋኝ፣ ጎበዝ አትሌት፣ ጎበዝ እግርኳስ ተጫዋች ና ጎበዝ ምንም ሁሉንም አይነት ተማሪዎች ታያለህ፡፡ ስምንት ሴቶች ሲጀምሩ በቡድን ይንቀሳቀሱና ሲጨርሱ ስምንት ባላንጣዎች ይሆናሉ፡፡ ሲጀምሩ ስምንት ብቸኛ የነበሩ ወንዶች ሲጨርሱ አንድ ቡድን ይፈጥራሉ፡፡
ክፍል እንደ ማቅለጫ ድስት (Melting Pot)ነው፡፡ ሁላችሁም አንድ ላይ ተቀምጣችሁ ትማራላችሁ፡፡ ፈተና ይደርሳል፡፡ ቴንሽን ያከሳሃል፡፡ ያንጨባርርሃል፡፡ እስኪነጋ ታጠናለህ፡፡ በሶ ስትበጠብጥ ታድራለህ፡፡ ታስጠናለህ ታጠናለህ፡፡ ትኮርጃለህ ታስኮርጃለህ፡፡ ውጤት ሲመጣ የተገላቢጦሽ ይሆናል፡፡ ከለፈለፉት ጥቂቶች ይሰቅላሉ፡፡ ዝም ካሉትም ጥቂቶች ይሰቅላሉ፡፡ ነጋ ጠባ ካጠኑትም ጥቂቶች ይሰቅላሉ፡፡ ትንሽ ትንሽ ያጠናህ አንተም ትሰቅልና ትገረማለህ፡፡ በተገለጠለት እንጂ በገለጠ አይደለም ትላለህ፡፡ እንኳን ሊያስኮርጁህ አሳይመንት እንኳን የሚደብቁህም አሉ፡፡ የቡድን ስራ ብቻህን ሰርተህ ትቀፍላለህ፡፡ ወራጅ እየተጫረ፣ ሰቃይ እየሰቀለ አብዛኛው በመሃል ቤት ሆኖ ጊዜው እንደዚህ ይነጉዳል፡፡ በዚህ መልኩ ስማቸውን የማይፅፉ አብረውህ ይመረቃሉ፡፡ የሶስት አመት ትምህርት ሰባት አመት የሚፈጅባቸውም ይመረቃሉ፡፡

ሴሚስተሮች ያልፋሉ፡፡ ፍሬሽነት ቀርቶ ሲኒየር ትሆናለህ፡፡ ስትቆይ ከብዙ ሰዎች ጋር ትግባባለህ፡፡ ባህሪ ትወራረሳለህ፡፡ ፀጉርህን ታንጨባርራለህ፡፡ የማታውቀውን ብሄር ቋንቋ ትማራለህ፡፡ የፅዳት ሰራተኛ እናቶች የግቢ እናት ይሆኑሃል፡፡ ካፌ ሳይገቡ የመኖር ሚስጥር ይገለጥልሃል፡፡ ትቀፍላለህ፡፡ ካልሆነልህ ትሰቅላለህ፡፡ ሰልፍ የማጭበርበር ክህሎትን ታዳብራለህ፡፡ ከብረት ገፊዎች ጋ ዶርም ከደረሰህ ብረት ገፊ ትሆናለህ፡፡ “በጌታ ነኝ” ትል የነበረች አይናፋር የበግተራ ቦዘኔዎች የጋራ ንብረት ትሆናለች፡፡ ምናልባት ሰክራ ወድቃ ተሸክመህ አስገብተሃት ይሆናል፡፡ አስካለች ...ፌቨን ነኝ ትላለች፡፡ ያምራል የሚባለው ልጅ እንኳን የሚያምር ስሙን ይቀይራል፡፡ እልል ያልክ ወመኔ ሆነህ ገብተህ ጌታ ይጠራህና “አመለጥኩ” የሚለውን መዝሙር በነጋ በጠባው እየከፈትክ ሰፈር ትረብሻለህ፡፡ ነጠላ ይዘህ የገባህ ዲያቆን አርብ እሮብ መግደፍ ትጀምራለህ፡፡ ከአጫሾች ጋር ውለህ ማጨስ ትማራለህ፡፡ መቃም ትማራለህ፡፡ ሲጠጡ እያነጉ ባጥር ዘሎ መግባት ትማራለህ፡፡ ቢጤህን ሴት ወንድ ዶርም ማስገባት ትማራለህ፡፡ ጭፈራ ትማራለህ፡፡ ቁማር ትለምዳለህ፡፡ ጭማድ ትለምዳለህ፡፡ ደህና ሰው ያልከው ይበላሻል፡፡ ተበላሸ ያልከው ደህና ሰው ይወጣዋል፡፡ የኮፒ ታጣለህ፥ የውስኪ ታገኛለህ፡፡ ሃንድአውት ትሰርቃለህ ወይ ትዋሳለህ፡፡ አጤሬራ ኮፒ ታደርጋለህ፡፡ “እግዜር የለም፥ አንተም የለህም” የሚሉህ ጀማሪ ፈላስፋዎች ታገኛለህ፡፡ በተቃራኒው በንባብና በአስተውሎት የበሰሉ ልጆች ታገኛለህ፡፡ ማታ ማታ ወክ እያደረክ ወይም ቡና እየጠጣህ የከረሩ እሳቤዎችን ትለዋወጣለህ፡፡ እመነኝ.... እናንተ በተመስጦ ያወራችሁትን ወሬ በስንተኛው ቀን የሆነው ኮርስ ላይ በሆነው ፈረንጅ ስም የሆነ አይነት ቲዎሪ ተብሎ ሲመጣልህ እንዳትገረም፡፡ በጊዜ ቀደሙህ እንጂ አልበለጡህም፡፡ በገንዘብ የበለጡህን፥ በግሬድ ትበልጣለህ፡፡ በግሬድ የበለጡህን በጠቅላላ እውቀት ትበልጣለህ፡፡

ከክላሳችሁ ብዙዎች ተግባብተው ታያለህ፡፡ ስታየው ያስጠላህ የነበረው ልጅ ምርጥ ጓደኛህ ይሆናል፡፡ ረጅሙ ጺማሙ ሙስሊም አክራሪዋን ነጠላ ለባሽ ኦርቶዶክስ ይጠብሳል፡፡ በግቢው የሚያስቀኑ ጥንዶች ይወጣቸዋል፡፡ አንተም ከማን አንሼ ብለህ በግተራ ቆመህ ትለክፋለህ፡፡ ፉንቃ ይገባልሃል፡፡ ትጀናጀናለህ፡፡ በለስ ይቀናህና ትጠብሳለህ፡፡ ኪሲንግፑል ስትሳሳም ታመሻለህ፡፡ ቤተመፅሃፍት አብረህ ታድራለህ፡፡ ኳስ ሜዳ ሄደህ በኩለሌሊት ትዳራለህ፡፡ ትፋታለህ ሌላ ትጠብሳለህ፡፡ እውነቱ ምንድነው ከግቢ ፍቅር በጣም ጥቂቱ ብቻ ዘላቂ ይሆናል፡፡ አንዳንዶቹ ከመጡበት ቦታ ትዳራቸውን አስቀምጠውት እንደመጡ ሳትዘነጋ፡፡ ጊዜው እየሄደ አመት ትጨምራለህ፡፡ አመት ሲጨምር የሴቶች ተፈላጊነት ይቀንሳል፥ አዳዲስ ሴቶች ስለሚመጡ፡፡ አመት ሲጨምር የወንዶች ተፈላጊነት ይጨምራል፥ በልምድ፣ በብልሃትና በድፍረት ከፍሬሹ ወንድ ስለሚሻሉ፡፡ አመት ሲጨምር ገበያውን እና ችግራቸውን ያወቁ ሲኒየር ሴቶች ሹገር ይጠብሳሉ፡፡ ካጣበስካቸው ደግሞ አንተም ከጥቅሙ ትካፈላለህ፡፡ ቢያንስ ማታ ማታ የማዘር ቤት ፍርፍር ትበላለህ፡፡

ከእለታት ባንዱ ቀን የአንዱ ብሄር ልጆች የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድ እንደጀመሩ ከየት መጣ የማትለው ፌደራል ፖሊስ ዶርም ድረስ ገብቶ በካልቾ እያለ ያስነ
ሳሃል፡፡ ሲመሽ የሌሎች ብሄር ልጆች ተቧድነው ለድብድብ ሲጠራሩ ትሰማለህ፡፡ ደህና ጓደኛ ካለህ አስቀድሞ ይነገርህና ሳትመታ ትወጣለህ፡፡ ሳትወድ በግድ ቡድን ትለያለህ፡፡ በዲፓርትመንት እና በከተማ እየተደራጀህ ኳስ ትጫወታለህ፡፡ የሃዋሳ ቡድን እና የአዲሳባ ቡድን ሁሌም ቢደባደቡ አይግረምህ፥ ኮምፕሌክስ ነው፡፡ የሽሬና የመቀሌ ቡድኖችም ይደባደባሉ፥ይህም ኮምሌክስ ነው፡፡ እንደኔ የስምንት ከተሞች ውጤት ስትሆን ግን ወገን ታጣለህ፡፡ የውጪውን ካልሆነ ኳስ ማየት ታቆማለህ፡፡

ደህና ደህና መምህራኖችህ መፅሃፍ ይሰጡሃል፡፡ ይረዱሃል፡፡ መጥፎዎቹ ደግሞ ያንቋሽሹሃል፡፡ ሚስትህን በግሬድ ያባልጉብሃል፡፡

እንዲህ እንዲህ እያለ መጨረሻህ ይደርሳል፡፡ ጂሲ ነኝ ብለህ ሁሉንም አይነት ቡዘናዎች ትቦዝናለህ፡፡ ጠጥቶ ማያውቅ ልጅ ታጠጣና የፌሚኒስት ነኝ ባይ እንስት ጡት ነክቶ በክስ ስትጉላላ ትከርማለህ፡፡ ዘበኛ ወይ ፕሮክተር መታወቂያ ይቀማህና ትጉላላህ፡፡ ላይብረሪ መሃል ትጨፍራለህ፡፡ አራት አመት የኖርከውን ሁሉ ደጋግመህ ትኖረዋለህ፡፡ አራት አመት ያልኖርከውን ሁሉ ፈልገህ ትኖረዋለህ፡፡ በስተመጨረሻም ተመርቀህ በገባህበት በር ሻንጣህን እየጎተትክ ትወጣለህ፡፡ ብዙ ሰው ግን በፌስታል ነው የሚወጣው ለምን? ሻንጣውን ሸጦታል፡፡
ምን ይተርፍሃል?
ጨጓራ በሽታ፥ ዲግሪ እና ብዙ ትዝታ፡፡

ከወጣህ በኋላ ማንንም አታገኝም፡፡ ብትንትንህ ይወጣል፡፡ የኔን ልንገርህ ፡፡ ከሰባው ተማሪ አስሩ የክፍለሃገር ዩንቨርስቲ መምህራን ሆኑ፡፡ አስሩን መንግስት ቀጠራቸው፡፡ አስሩን መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ወሰዷቸው፡፡ አምስቱ ማስተርስ ቀጠሉ፡፡ በጣም ጥቂቶች ከቤተሰብ ጋ ቢዝነስ ጀመሩ፡፡ ሁለት ልጆች አለማቀፍ ተቋማት ውስጥ ገቡ፡፡ ቆንጆ ነኝ ብላ የምታስበዋ ሆስተስ ሆነች፡፡ እኔ ደሞ እዚህ ጋ ነኝ፡፡

ታናሼ አደራ ስለተቀሩት እንዳትጠይቀኝ፡፡

ስትወጣ ትደርስበታለህ፡፡
ወልዲያ! ከላፉት 3 ቀናት በተሻለ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየታየ ነው። ይህም ቢሆን ተማሪዎች ወደ ውጪ እንዲወጡ አልተፈቀደላቸውም። ዩኒቨርሲቲው የተፈጠሩ ችግሮችን በንግግር ፈቶ ተማሪዎችን ወደ መደበኛ ትምህርታቸው ለመመለስ ጥረት እያደረገ ነው። በግቢው ሰላም እንዲሰፍን ከፀጥታ አካላት በተጨማሪ የሀይማኖት አባቶች አስተዋፆኦ ከፍተኛ እንደሆነ በግቢው ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ተግረዋል።

ምንጭ፦ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
Channel photo updated
https://t.me/chinapoland
🔱Scholarship offer🔱
🍴Tibs, Menchet, Ketfo
💵 250B with two beers🍺
📌 Cevery restaurant
📍Piassa, next to fasika hotel
@Woldiauniversity
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ...

"በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የውሃ አቅርቦት ከተቋረጠ ከሳምንት በላይ ሆኖናል የመጠጥ እንዲሁም የግል ነፅህናችንን የምንጠይቅበት ውሃ አጥተናል እባካችሁ መልክታችንን አድርሱልን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🍴Assa dulet, Beyaynet
💵 100B
🏠Tensae restaurant
📍Piassa
@Woldiauniversity
🍴Shekla tebs 1/2 Kilo
💵 140B
🏠Hormat restaurant
📍On the way to bus station
@Woldiauniversity
🍴#1 Key’wet
💵 40B
📌 Cevery restaurant
📍Piassa, next to fasika hotel
@Woldiauniversity
Best View of the #Birds_nest🦅 around #block_49
🥪 Club Sandwich👌
💵 35B
📌 Liya Fast Foods
📍Adago, in front of Mazza juice
@Woldiauniversity
🍴1/2 Agelgel⭐️⭐️⭐️⭐️
💵 100B
📌 Cevery restaurant
📍Piassa, next to fasika hotel
@Woldiauniversity
🍖Shekla Tebs⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
💵 130B
🏠Tensae restaurant
📍Piassa
@Woldiauniversity
Greetings everyone, & thank you for being part of our channel. Your inputs & comments have been a very important part of our journey. So i would like to get your opinions regarding everything related to our channel, anything you feel is important or needs to be improved.
@VJ_Sura
Thank you. 🎩
🍴Kuanta’ferfer⭐️⭐️⭐️
💵 60B
📌 Cevery restaurant
📍Piassa, next to fasika hotel
@Woldiauniversity