<Quality Assurance, Outcome-Based Education, Academic Program Audit and Accreditation> በሚል ርእስ የተዘጋጀ ስልጠና ለዳይሬክተሮች፣ ለኮሌጅ ዲኖች እና ለት/ት ጥራት አስተባባሪዎች ተሰጠ፡፡

ጥቅምት 26/2017ዓ.ም (የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)
የትምህርት ፕሮግራም ኦዲት እና እዉቅና አሰጣጥ ስርአት ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ስልጠና በትናንትናዉ እለት ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በመጣ ባለሙያ ለሚመለከታቸዉ የስራ ክፍሎች ስልጠና ተሰጠ፡፡
በስልጠና መክፈቻ መርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት የአካዳሚክና ምርምር ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ማርየ በለጠ - የት/ት ፕሮግራሞች በተቀመጠላቸዉ መመዘኛ ደረጃ ኦዲት ለማድረግና እዉቅና አሰጣጥ ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲፈጠር በማሰብ ስልጠናዉ መዘጋጀቱን አሳዉቀዋል፡፡
የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን (Education & Training Authority, ETA) በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጡ ያሉ የትምህርትና የስልጠና መርሀ-ግብሮችን ፈቃድ መስጠት፣ ጥራቱን ኦዲት ማድረግ፣ ማረጃገጫ መስጠት፣ መቆጣጠር፣ ህጋዊነትን ማጣራትና አቻ- ግመታ መስጠት ስራዎችን እንደሚሰራ ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የመጡት እና ስልጠናዉን በሰጡት አቶ ተረፈ በላይ ተገልጧል፡፡
ስልጠናዉ የትምርት ፕሮግራም ኦዲትና እዉቅና አሰጣጥ ስርአት ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር አላማ ያደረገ እንደሆነ የዩኒቨርሲቲዉ የት/ት ጥራት ማሻሻያ ዳይሬክቶት ዳይሬክተር ወ/ሮ ዙፋን አበበ ገልጸዋል፡፡
የፕሮግራምና የተቋማዊ ጥራት ማረጋገጫ መኖሩ፡- ስራዎችን ለመቆጣጠር፣ በተማሪ ፍላጎት ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞችን ለማዎቅና ቅቡልነትን ለመጨመር፣ ተጠያቂነት ለማስፈን፣ የተማሪዎችን ዝዉዉር ሊገድብ የማይችል ስርአተ-ት/ት እንዲኖር፣ አለማቀፋዊ እዉቅና ለመፍጠር፣ የተማሪዎች በስራላይ ተፈላጊ መሆን፣ የት/ትና ስልጠና ተቋማት ባለሙያዎች ከደረጃ በታች ሆነዉ እንዳይመረቁና ማህበረሰቡ ከደረጃ በታች በሆኑ ባለሙያዎች አገልግሎት እንዳያገኝ መከላከል እና ዉጤታማ፣ ቀጣይነት ያለዉ የት/ት ጥራንት ለማረጋገጥ እንደሚረዳ በስልጠናዉ ተመላክቷል፡፡
መርሀ-ግብሩ በአካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክቶሬት እና በት/ት ጥራት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሲሆን፤ በዚህ አመት የተመረጡ የት/ት ፕሮግራሞች ኦዲት ይደረጋሉ፡፡ ደረጃዉን ለሚያሟሉ ፕሮግራች ደግሞ እዉቅና እንዲያገኙ ስራዎች እንደሚሰሩና ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የቤት ስራ በመዉሰድ አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉ አስተባባሪዎቹ ጠቁመዋል፡፡
----------------------------------------------------------------------------------------------
አእምሮ ሲከፈት አይኖች ማየት ይችላሉ / Open Mind. Open Eyes!
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://www.wldu.edu.et/
Facebook = https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel = https://t.me/Woldia_University
YouTube = https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.

Woldia University
Homepage - Woldia University
Woldia University is one of the public universities established by the Government of Ethiopia following its plan to expand higher education institutions in the country’ to increase access and shore up its economic development and social transformation.