ፍልስፍና
623 subscribers
491 photos
11 videos
478 files
39 links
"ይህ ቻናል መግቢያም ሆነ አጥር የለውም እንደ ሰው ለሚያስብ ብቻ ተከፍቷል!"
ጲላጦስ
Download Telegram
ፍልስፍና
Photo
  የዴስካርት የ"ሀሳብ ምንጭ"


የሀሳብ ምንጭ የት ነው?ከየት ነው የሚፈልቀው?. ዴስካርት ይሄንን ሀሳብ "ስለማስብ አለሁ!" ከሚለው የፍልስፍናው መሰረት የተነሳ ጥያቄ ነው። ዴስካርት ሀሳቦቻችንን በ3 ይከፍላቸዋል፦

1]Innate ideas ይላቸዋል፦እነዚህ ከሰው ልጅ የምክንያት ተፈጥሮ ያለ እንዲሁም በሁሉም የሰው ልጅ ሀሳብ ምንጭ የጋራ ወይም መሰረታዊ የሆነ ነው ይለዋል። ለምሳሌ ህልውና፣ቁሳዊ ነገሮች፣ ጊዜ ፣ምክንያት.. ወዘተ ሀሳቦችን

2] factitious ideas፦ እነዚህ ደግሞ ምንጮቻቸው ልቦለዳዊ ፈጠራ ሲሆን ለምሳሌ መርሜዶች(የሰውና አሳ ውህድ ፍጡር)፣ፍፁማዊ አለም፣በራሪ ፈረሶች...ወዘተ በገሀዱ አለም የማናገኛቸው የነገሮችን በፈጠራ የተዋቀሩ ሀሳቦች ናቸው ይላቸዋል።

3]Adventitious ideas፦እነዚህ ደግሞ ከእኛ እና ከእኛ ውጪ ባለው አለም የሚፈጠሩ ሀሳብች ሲሆኑ ድምፆችን መስማት፣ፀሀይን መመልከት፣ ቀለማትን ተመልክቶ መለየት፣ማሽተት...ወዘተ የገሀዱ አለም የሀሳብ ምንጮቻችን ናቸው ይለናል-ዴስካርት።

ይሄ የinnert idea ለአምላክ ሀልዎት እንደ 11ኛው ክፍለዘመን ፈላስፋና የቲዎሎጂ መምህር ለሆነ አንሰለም የተጠቀመበት ሲሆን ፍፁም የሆነ አካል፣ሁሉን ቻይ፣ሁሉን አድራጊ አካል አእምሯችን ውስጥ መፈጠሩ በራሱ የፈጣሪ ጠቋሚ ነው የሚለን Ontological Argument ነበር። ኋላ ላይ የብሪቲሽ ዳሰሳዊው ፈላስፋ ዴቪድ ሂዩም የዴስካርትን ሆነ የአንሰለምን የፈጣሪ መኖር አስረጂ አድርገው ያቀረቡበትን ተሳልቆበት ነበር፤ በጥቅሉ እንኳን ዴቪድ ሂዩም የዲበ አካል (Metaphysics) ጥናት "ቀልድ እና የማይቻል ነው" ባይ ነው።በተመሳሳይ መልኩ ጆን ሎክ ደግሞ የዴስካርትን የinnert idea ምንጩ በራሱ የራሳችን የስሜቶች ምንጭ(our experience of impressions) እንደሆነ ይነግረናል።ዴቪድ ሂዩም ከስሜቶቻንን ልምድ የሌላቸው ሀሳቦች ትርጉም አልባ የሆኑ ናቸው ይለናል። የሀሳብ ምንጩ የት ነው??...

@Wisdom_Wisdom
<<...እግዚአብሔር ሞቷል። እግዚአብሔር ሞቶ ይቀራል።እኛ ደግሞ ገድለነዋል። የገዳዮች ሁሉ ነፍሰ-ገዳዮች ራሳችንን እንዴት እናጽናና? በዓለም ላይ ካለው ነገር ሁሉ እጅግ ቅዱሱና ኃያል የሆነው በእኛ ቢላዋ ሥር ደሙ ፈሰሰ፤ ይህን ደም ማን ያብሳል? እራሳችንን የሚያፀዳ ምን አይነት ውሃ አለ? ምን ዓይነት የስርየት በዓላት፣ምን አይነት ቅዱስ ባህሪያት ልንፈጥር ይገባል?...>>

  The Gay Science By Nietzsche 1882
He was free, free for everything, free to act like an animal or like a machine … He could do what he wanted to do, nobody had the right to advise him … He was alone in a monstrous silence, free and alone, without an excuse, condemned to decide without an excuse, condemned to decide without any possible recourse, condemned forever to be free.Man is Condemned to be free!because once thrown into the world he is responsible for everything he does. It is up to you to give[Life] Meaning.

Jean-Paul Sartre Existentialism is a Humanism1946
ከሰማያዊው ማስታወሻ ደብተር ('ቀይ ፀጉር ያለው ሰው')

ዓይንና ጆሮ የሌለው ቀይ ፀጉር ያለው ሰው ነበር። እሱ ምንም አይነት ፀጉር ስላልነበረው በንድፈ ሀሳብ ቀይ ፀጉር ተብሎ ይጠራ ነበር.

አፍ ስለሌለው መናገር አልቻለም። ሁለቱም አፍንጫ አልነበረውም።እጅና እግር እንኳን አልነበረውም። ሆድ አልነበረውም፤ ጀርባም አልነበረውም፤ የጀርባ አጥንት አልነበረውም፤ ምንም አይነት የሆድ ዕቃም አልነበረውም። እሱ ምንም አልነበረውም! ስለዚህ ስለማን እንደምንናገር እንኳን የሚታወቅ ነገር የለም።እንዲያውም ስለ እሱ ምንም ባንናገር ይሻላል።

ከዳንኤል ካርማስ incidence መፅሀፍ ተወሰደ


@Wisdom_Wisdom
በእርግጥ እጅግ አንገብጋቢ የፍልስፍና ችግር አለ፤እርሱም ራስን ማጥፋት ነው። ሕይወትን መኖር ዋጋ እንደሌለው ወይም እንዳለው መተንተን የፍልስፍና መሠረታዊ ጥያቄን ከመመለስ ጋር ይመሳሰላል።አለም ሦስት ስፍረታዊ ሆነች አእምሮ ዘጠኝ ወይም አስራ ሁለት ምድቦች ኖሩትም አልኖሩት፡ ለመኖር ከወሰንኩ በኋላ የማስተናግዳቸው ጥያቄዎች ናቸው።

Albert Camus The Myths of Sisyphus 1942
አንዳንድ ሰዎች ግርምታን በመፍጠር አፍን ያሲዛሉ ። እንደመምህር ኢያሱ በሬንቶ ያሉ ሰዎች ፍልስፍና ን እንደተረዱት በሚገባ ያሳብቅባቸዋል ። አድምጠን ለመጠቀም ያብቃን !


Watch "ሰው ምንድን ነው? | ከመ/ር እያሱ በሬንቶ ጋር | ክፍል 1 | መልክ ሕይወት | ሀገሬ ቴቪ" on YouTube
https://youtu.be/IV8eDmXqaLk
" The business of philosophy is to teach man to live in uncertainty... not to reassure him, but to upset him. "

" የፍልስፍና ዋና ዓላማው ሰው ያለ እርግጠኝነት ይኖር ዘንድ ማስተማር ነው ። እርግጠኛ እንዲሆን ሳይሆን እረፍት አጥቶ እንዲበሳጭ ነው ። "

(Leo Shestov) , Russian Existentialist and Religious Philosopher)]
" The most thought - provoking thing in our thought - provoking time is we still don't think. "

" በዚህ ሀሳብ በሚያነሳሳ ዘመን ዋናው ሀሳብ አነሳሹ ነገር አሁንም አለማሰባችን ነው ። "

[(Martin Heidegger) : German Philosopher]
" A man can be himself only so long as he is alone ; and if he doesn't love solitude, he willnot love freedom ; for it is only when he is alone that he is really free. "

" ሰው ራሱ በራሱ መሆን የሚችለው ብቻውን ሲሆን ነው ። ስለዚህም ብቸኝነትን የማይወድ ሰው ነጻነትን ሊወዳት አይችልም ፤ ምክንያቱም ሰው እውነተኛ ነጻነትን የሚያገኘው ብቻውን ሲሆን ብቻ ስለሆነ ነው ። "

[(Arthur Schopenhauer) : German Philosopher]
<<የሰው ልጅ ምናልባት ራሱን ለመከላከል ሲል ራሱን ሊያጠፋ ይችላል!>>

ጅብራን ካህሊል

‌♡        ⎙ㅤ   ‌  ⌲
ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢʰᵃʳᵉ
" If there is anything worth fearing in the world, It is living in such a way that gives one cause for regret in the end. "

" በዓለም ላይ እንደው መፈራት የሚገባው ነገር ቢኖር አንድ ሰው ከኖረው ኑሮ የተነሳ በመጨረሻ ላይ ውጤቱ ጸጸት የሆነ እንደሆን ነው ።"

[(A.C. Grayling) : British Philosopher]
<<....ወጣት እያለ ያልሞተ ሁሉ ሞት ይገባዋል...!>>

ኤሚል ሲኦራን
<<......
እራሴን የማጥፋት ሀሳብ ባይኖረኝ ኖሮ እራሴን አጠፋ ነበር!.....>>

ሮማዊው ፈላስፋ ኤሚል ሲኦራን
" Life is not a problem to be solved but a reality to be experienced. "

" ሕይወት የሚፈታ ችግር ሳይሆን የምንለምደው እውነታ ነው ። "

[(Søren Kierkegaard) : Danish Theologian and Philosopher]
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም  (Peter)