ፍልስፍና
731 subscribers
500 photos
11 videos
478 files
39 links
"ይህ ቻናል መግቢያም ሆነ አጥር የለውም እንደ ሰው ለሚያስብ ብቻ ተከፍቷል!"
ጲላጦስ
Download Telegram
እንኳን ለአድዋ የሰው ልጅ የነፃነት ድል ቀን በሰላም አደረሳችሁ !💯💯
💥💥🤩🤩🤩🥳🥳🥳🥳🥳
Silence as presence
ከእግዜር ጋር ንግግር
(ያዕቆብ ብርሃኑ)
*
… እንደ አንዳች ሞትና መቃብር ጠርዝ ላይ ያመላልሰኛል፡፡ በጩኸታሟ አዲስ አበባ መሃልአብዛኛውን የጽሞና ሀሰሳ ሰዓቴን የማሳልፈው በፈራረሱ የመቃብር ቅጥሮች ውስጥ ነው፡፡  በየሳምንቱ የማነባቸው the economist  እና the new York times ጋዜጣና መጽሔቶች ላይ እንኳን ቀድሜ የማነበው obituary (ዜና ዕረፍት) አምዳቸውን ሆኗል፡፡
ጊዜው ትንሽ ቆይቷል፡፡ ከአራት ወራት በፊት ከDecember 22- January 4 2019 የሚሸፍነው የthe economist መጽሔት double issue ዕትም ዜና ዕረፍት አምድ ላይ Silence as presence በሚል ርዕስ ስር ስለመነኩሴው ቶማስ ኬቲንግ ሕልፈት የተጻፈውን አነበበኩ፡፡ ካፒታሊዝምና ፍትወት በሚያቅነዘንዘው ልቅ ዓለም እንደ ኢየሱስና እንደ ጋንዲ ባለ ከፍያለ ልዕለ ሰብዕና ዝምታን የሕይወት መመሪያቸው አድርገው ለ95 ዓመታት ኖረው ስላለፉት ታላቅ ሰው፤ ለ95 ዓመታት በመኖሪያ ክፍላቸው ውስጥ ከአንዲት አልጋ፣ ከመጻፊያና ማንበቢያ ጠረጼዛና ወንበር በስተቀር ምንም ስላልነበራቸው መናኝ… እንደ ጋንዲ ለንቋሳ ገጽታን የተላበሱ፣ ግን ደግሞ ትንሽ ገዘፍ ያሉ፣ ረጅም፣ ራሰ በራ፣ በሚያስተዳድሩት ገዳም የሕይወት ዜይቤያቸውን ለሚሹ ፅሞናን በጸጥታ ከማስተማሩ መልስ በገዳሙ አንድ ጥግ ተቀምጠው ሞትን በመናፈቅ (longing to death) ዘመናቸውን በሙሉ የኖሩ ግዙፍ ስብዕና…

የእኒህ ሰው የሕይወት ዘመን ፍላጎት አንድ ብቻ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር… ይህንን ማድረግ የሚቻለው በጽሞና ብቻ ነው ብለው በማመናቸው ሌሎችም ከዕለትተለት ሩጫቸው በምትተርፋቸው ጊዜ ማድረግ እንዲችሉ ሲጥሩ አሳልፈዋል፡፡

እኒህ ሰው ከበመካከለኛው ዘመን በእስፓኝ ከኖሩት st. John the cross የተዋሱትና አሻሽለው መታወቂያቸው ያደረጉት ግሩም አባባል አላቸው፡፡
‹‹God's first language was silence.››   st. John the cross
‹‹everything else is bad translation.››   Thomas Keating
‹‹Including holy manuscripts.›› እኔ
እኔም አልኩ… ስታወሩ ስሜታችሁን ዝም ስትሉ ግን ነፍሳችሁን ማንበብ እችላለሁ፡፡ ዝም ማለት የቻለ እርሱ አሁንን ብቻ ሳይሆን ዘለዓለምን ማዘዝ ይችላል፡፡ ዝም ማለት የቻለ እርሱ ከአምላኩ ጋር እንኳን ባይሆን ከራሱ ጋር በተግባቦት ማውራት ይችላል፡፡ ግጥም ምንም አይልም፡፡ ስዕል ጥሩ ነገር ነው፡፡ ድርሰት በጣም ጥሩ ነገር ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሙዚቃም እጅግ በጣም ጥሩ ነገር መሆን አለበት፡፡ እነዚህ ሁሉ ግን ስንኩል የዝምታ ገጽታዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ በላይ ዝምታ ይበልጣል፡፡ ዝም ማለት፣ ፀጥታ(የሚረብሽ ድምጽ አለመኖር) ሁሉ ዝምታ ሊሆን አይችልም፡፡ ዝምታ(ጽሞና) ረቂቅ ነገር ነው፡፡   
የሆነን ነገር፣ መውደድህንም ቢሆን እንዴትም ብትገልጸው በተናገርከው ቅጽበት ወዲያው ትርጉሙን አዛብተኸዋል፡፡ ዋጋውን ቀንሰኸዋል፡፡ ለ misunderstanding ግዙፍ በር ከፍተሃል፡፡ ከቻልክ በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ምንም አትበል፡፡ በጣም ውድ የሆነውን ነገር በዝምታና በተግባር ልትገልፀው ሞክር፡፡  እኔ እንኳን ይህችን ሹክ ልልህ ጽሁፉን ካነበብኩበት ከፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ጀምሮ ራሴን ማሳመን ተስኖኝ ይሄው ሳመነታ ነበር፡፡
በቅርቡ ከmay 4- may 10 በሸፈነው በዚሁ የthe economist ዕትም ethics and evolution በሚል ርዕስ ስር ባነበብኩት አንድ ጥናት መሰረት ባለፉት 30,000 ዓመታት ሂደት የሰው ልጅ ጭካኔ(cruelity) እና እንስሳዊ ባህሪት ከመሰሎቹ ዝንጀሮና ጎሬላዎች ተሽሎ የተገኘው እጅግ በጣም በጥቂቱ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የሰለጠነው የሰው ልጅ እስከ አውሬያዊ ባህሪያቱ ይኖራል፡፡ እኔም፣ አንተም፣ አንቺም ጭምር… ከዚህ አውሬያዊነት መሻሻልን የሻተ ዝም ይላል፡፡ በየቀኑ ቢያንስ የ40 ደቂቃ የጽሞና ጊዜ ይኖረዋል፡፡ ዝም ማለት የቻለ እርሱ ራሱን ያሸንፋል፡፡ ራሱን ማሸነፍ የቻለ፣ ሌሎችን፣ ዓለምን የማሸነፍ ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ የጠቀስኳቸውን የዘኢኮኖሚስት ጽሁፎች በጠቀስኳቸው ርዕሶች Google ላይ search ብታደርግ ማግኘት እንደምትችል አረጋግጥልሃለሁ፡፡ በል እንግዲህ ልሰናበትህ… የጽሞና ሠዓቴ ደረሰች!

© ያዕቆብ ብርሃኑ


Source : Philosphyloves 🔥
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም  (Alador)
ነገረ እኩይ—Problem of Evil

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
==============================

የፊታችን ቅዳሜ (ግንቦት 24) የበጋ ሌክቸሮች መርሐ ግብራችን ትኩረቱን በ<<ነገረ እኩይ—Problem of Evil>> ላይ አድርጎአል። በትምህርት ቤታችን በሃይማኖት ፍልስፍና ስር በፍሬው ማሩፍ የሚሰጥ ኮርስ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በዘርዐያዕቆባዊ "እነዚህ እንዲህ እንዲህ ይላሉ እነዚያ እንዲህ እንዲህ ይላሉ.." የፍልስፍና መንገድ በተጋባዥ እንግዳ ልንቃኘው ነው።

መምህሩ ዮናስ ዘውዴ ነው።

የ<<ነገረ እኩይ>> አንኳር ጥያቄ <<ከፍፁማዊውና ደግ አምላክ ጎን ለጎን እንዴት እኩይ አብሮት ሊኖር ቻለ?>> የሚለው ነው፡፡ የጥያቄው መነሻ ደግሞ የፈጣሪ መለያ ባህርያት ተብለው በሚታወቁት (omnipresent, omnipotent, omniscient, and omnibenevolence) ላይ ተንተርሰው የተለያዩ አሳቢዎች እና ፈላስፎች <<በዓለም ውስጥ የሚታየውን እኩይ ነገር ከነዚህ የፈጣሪ ባህርያት ጋር የሚጣረስ ነገር አለው>> ብለው የሚያነሷቸው መከራከሪያዎች ናቸው።

ለምሳሌ የጥንታዊ ግሪክ ፈላስፋ ኤፒኩረስ ከፍፁማዊው አምላክ ጎን ለጎን እንዴት እኩይ አብሮት ሊኖር እንደቻለና ማጥፋት እንዳልቻለ ለማብራራት የሚከተሉትን አማራጮች እና አማራጮቹ የሚያስከትሉት የሎጂክ ተቃርኖ አስቀምጦአል :-

— ምናልባት እግዚአብሔር እኩይን ማጥፋት እየፈለገ ነገር ግን አልቻለ ይሆን? ይሄ ከሆነ ደግሞ ከእግዚአብሔር የ"ሁሉን ቻይነት" ባህሪ ጋር የሚጣረስ ነው።

— ሁለተኛው እግዚአብሔር እኩይን ማጥፋት እየቻለ ግን ማጥፋት አልፈለገ ይሆን? ይሄ ደግሞ ከእግዚአብሔር "የደግነት" ባህሪ ጋር የሚቃረን ነው።

— ሦስተኛ እግዚአብሔር እኩይን ማጥፋት እየቻለም እየፈለገም ሆኖም ግን ሆን ብሎ እኩይ እንዲኖር ፈልጎ ይሆን? ይሄ ደግሞ የእግዚአብሔርን "ጨካኝነት" የሚያሳይ እና ከ"ፍፁም ደግነቱ" ጋር የሚጋጭ ሊሆን ነው።

— አራተኛ እግዚአብሔር እኩይን ማጥፋት የማይፈልግ እና የማይችል ሆኖ ይሆን? ይሄ ደግሞ የእግዚአብሔርን "ሁሉም ቻይነት" ብሎም ህልውነት የሚያሳጣ ሊሆን ነው።

ወደ ትምህርት ቤታችን ጎራ ብለው ይሄን ለዘመናት ሲያከራክር የቆየውን እና አሁንም እያከራከረ ያለን የሃይማኖት ፍልስፍና ጥያቄ ላይ ይወያዩ፣ ይከራከሩ፣ ይማሩ።

ዮናስ ዘውዴ አብዛኞቻችሁ (በሚድያ) የምታውቁት ሲሆን የመጀመርያ ዲግሪ የቋንቋ እና የየማህበራዊ ሳይንስ፤ ሁለተኛ ዲግሪ የቲዮሎጂ፣ እና የፍልስፍና ትምህርቶችን አጠናቅቆአል። አሁን ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ሦስተኛ ዲግሪውን በመስራት ላይ ይገኛል።

© ዘርዓያዕቆብ የፍልስፍና ትምህርት ቤት
ፍልስፍና
Photo
ሳልስተ ደረጃዎች


በቀደሞት የፍልስፍና የ❝እውቀት❞ እንዲሁም የ❝ህይወት❞ ጉዞ አንዱ ሀሳብ ገዢ ሆኖ ጊዜውን ሲገዛ ደግሞ በተራው የወደቀና የተናቀው ደግሞ ቀን ወቶለት በቀደመው ላይ ድል ተቀናጅቶ የፍልስፍናው አሳብ የልህቀት ተደርጎ ሲመለክ እና ሲታይ እዚህኛው ክፍለዘመን ደረሰን። በዘመነ ዳግም ውልደት(በምዕራባውያን) የሀይማኖተ-ፍልስፍና ነገር ራሱን ወደ ማጥፋት በፍጥነት እያመራ በነበረበት ወቅት አንዳንድ (በጣት መጥቀስ የምንችላቸው) ፈላስፎች ሀይማኖተ-ህግጋታቸው ወደ ፍልስፍናው ከማቅረብ አልፈው መሰረታቸውን አፅንተው የእናንተንም እንዲሁ ተመልከቱ ብለው ሀይማኖተ ፍልስፍና ❝ሐዋሪያ❞ዊነታቸውን ተወጥተዋል። ከእነሱ መካከል ደግሞ አንዱ ሶረን ኪርጋርድ ተጠቃሽ ነው።


ኪርጋርድ በተለያዩ መፅሀፎቹ "የአምላክን አስፈላጊነት ከዛም በዘለለ ደግሞ የኃይማኖትን በሰውልጅ ህይወት ላይ እጅግ የጠለቀ እና ጎልህ ሚና በብእሮቹ ከትቦ አልፏል «ሆነ» ያልውን አስፍሯል።ከዛሬ አንዱን መፅሀፉን ወስደን ትምህርታዊ ዳሰሳ እናድርግበት።


   °𝑓𝑒𝑎𝑟 𝑎𝑛𝑑 𝑡𝑟𝑒𝑚𝑏𝑙𝑖𝑛𝑔
𝑢𝑛𝑑𝑒𝑟 ˝𝑝𝑟𝑒𝑎𝑚𝑏𝑙𝑒 𝑓𝑟𝑜𝑚 𝑡ℎ𝑒 ℎ𝑒𝑎𝑟𝑡˝

በመፅሀፉ ኪርጋርድ ሦስተ የህልውና ደረጃዎች (Sphere of Existence ይላቸዋል) አሉ ይለናል።

  1)ኪነጥበባዊ(Aesthetic)
  2)ስነ-ምግባራዊ(Ethical)
  3)ኃይማኖታዊ(Religious)

እንደኪርጋርድ መልከተ ሰውልጅ ከነዚህ የህይወቱ መስመር በአንዱ ነው።ኪርጋርዱ ራሱን በኃይማኖታዊ(Religious) ይመድባል ሌሎችም ቢሆኑ በዚሁ ጎራ እንዲሆኑም ይመክራል። መፅሀፉ በውስጥ የኪነጥበብን(Aesthetic) እና ኃይማኖታዊ(Religious)መካከል ያለውን ጠብ (ጠቡ ካለም!)ለማብረድ ይመስላል።ሁለቱ ለገዛ ራሳቸው ምእሉ ናቸው ይሄም ደግሞ አንዱ ያለሌላኛው ጎዶሎ አልሆነም ባይነቱን ኪርጋርድ ይተቸዋል።በምሳሌ ሶስቱንም እንያቸው

  1)ኪነጥበባዊ[Aesthetic]
በዚህኛው መደብ ውስጥ ደስታ ተኮር ህልውናን[Hedonistic Existence] ሲመድበው ቅፅበታዊ ደስታ መሻትን ውበትን በደቂቃ መመኘትን ከጊዜያዊ ሁነት ጋር ያያይዘዋል።

  2)ስነምግባራዊ [Ethical]
የአብርሀም የእምነት ፍተሻ(leap of faith) ማመን ብቻውን በቂ አደለም በመሰረቱ በአምላክ የተቀረፀ የታመነበት ህግ(ስነምግባር) እጅጉኑ አስፈላጊ ነው።በየትኛው መሰረታዊ ሀይማኖት አስተምህሮ ስነምግባር የእምነቱ ማዕከል ነው።በስነምግባር መደብ እራሱ መንገድ ነው ከውበት ወደ ሀይማኖታዊነት ያለ ድልድይ

   3]ሀይማኖተኛ[Religious]
ይሄ በኪርጋርድ ፍልስፍናዊ ሀሳብ ከሆነ የመጨረሻው ደረጃ ሲሆን ሰው ራሱን ለፈጣሪ የሚሰጥበት በውበት አምኖ በስነምግባር ታሽቶ የሚቀርብበትን የአብርሃም እምነት በልጁ የመስዋት «ቀልድ» አልፎ የታየበትን የማረጋገጫ እና የምርቃት ደረጃ ነው።በዚህ ደረጃ አንድ ሰው ስርአታዊ ሀይማኖተኛ ነው ከስርአተ ተፈጥሮ ያለፈ[the Man Who higher than the universal] ነው። ከውበት[አካል] ወደ ስነምግባር[መንፈስ] አልፎ ሀይማኖተኛ¹ [ነፍስ] ሆኗልና።


ኪርጋርድ ሶስቱን የሰው ህልውናዎች እኺህ ናቸው ይላቸዋል።❝አንድ ሰው የመጨረሻ ግቡ ሊሆን የሚገባ ሀይማኖተኛ መሆን ነው።በቅፅበት ደስታ ወይም በረጅም ህግ ብቻ መቅረት የለበትም።መንገዶች እንጂ መዳረሻ አደሉምና! ❞ሲል ያጠናቅቃል።


___________
¹ሀይማኖተኛ ሲል የአርብ ሰጋጅ አልያ የእሁድ ተሳላሚ ለማለት እንዳልሆነ ልብ ይሏል!
ፍልስፍና
#ካርል_ጃስፕርስ
❝በራሴ ቆራጥነት በየጊዜው እና ሁኔታ ውስጥ፣ ያለፈውን ቋንቋ ይበልጥ ግልጽ በሆነ መንገድ በሰማሁ ቁጥር፣ ለህይወት ብርሃን እየተቃረብኩኝ ይሰማኛል።❞
                   ፥ካርል ጃስፕርስ

የካርል ጃስፕርስ [Karl Jaspers]
ፍልስፍናዊ ዕይታ እና የመፅሀፍ ቅኝት

ካርል ጃስፕርስ በየካቲት 23 1883(እ.አ.አ) ተወልዶ በየካቲት 26 1969(እ.አ.አ) ዓ.ም ያረፈ ታላቅ እና ወሳኝነቱ ሕልዖተ-ፍልስፍና
(Existentialism) የነበረ የጀርመን-ስዊድን ሀገር ተወላጅ የሆነ ፈላስፋ እና ሳይካትሪስት ነው። በልጅነት ጊዜው ለፍልስፍና ፍላጎት የነበረው ቢሆን በአባቱ ግፊት የህግ ትምህርትን አጥንቶ በውስጡ ወደ ሳይኮሎጂው ገብቶ ከዛም በኋላ ፍላጎቱን ፍልስፍናን ተማረ።በፍልስፍና ስራዎቹ ውስጥም የሁለት ታላላቅ ፈላስፎች ማለትም የፍሬድሪክ ኒቼ እና የሶረን ኪርጋርድ 'የግለሰብ ነፃነት(individual freedom)' አስተሳሰብ በሰፊው የተንፀባረቁበት ሲሆን¹ የህይወት ፍልስፍናውም ወደ ሕልዖተ-ፍልስፍና (Existentialism) እንዲቀይር ያደረገውም ይኽ ነበር።

በDie Grossen Philosophen(The Great Philosophers)² መፅሀፍ ስራው
የፍልስፍናን የሀሳብ ምልከታ ጉዞ ለአራት ሲከፍለው ፦
1] The foundations[ምስረታ]: የግለሰብ ንቅናቄ ያስጀመሩትን ሶቅራጠስ፡ቡድሀ:ኮንፊውሺየስ፡ ኢየሱስን ሲያስቀምጥ ምስረታውን ያጠነከሩት ደግሞ ፕሌቶን፡ኦውገስቲን:ካንት እና ሌሎችን አካቶ መድቦታል።

2] The original thinkers[ቀንደኛ ሀሳቢያን]: አናክሲማንደር፡ሄራክሊተስ፡ፓራሜንደስ፡ባሩች ስፒኖዛ፡ፕሎቶኒየስ፡ላ-ቱዙ.  .  .

3]ተንታኝና ለዋጭ ሀሳቢያን: አርስቶትል፡ ዲሞክራተስ፡ቡሩኖ፡ኢፒከረስ፡ሌብኔዝ:ሂግል፡ዚኖፋነስ  ሌሎችንም አካቶበታል።

[4] The disturbers[አብዮተኛ ሀሳቢያን]:
ዴካርት፡ፓስካል፡ኒቼ፡ኪርጋርድ፡ማርክስ እንዲሁም በሳይንሱ መስክ አንስታይን፡ዌብነር ማክስ. . . በማድረግ በዚህ መልክ ይከፍላቸዋል።


   Philosophy³ (ፍልስፍና) በተሰኘው ስራው ውስጥ በቅፅ 3 በ1932 በታተመው የፍልስፍናውን ጉዞ በዘመናዊው ሳይንስ በሆነው ዳሰሳዊያን (Empiricism) በማንሳት ከሚታየው ሀሳብ ተሻጋሪ (transcend) እንደማያደርግ እና መጋፈጥ እንደማይችል በማስረዳት ሰዎች እውነታን(Reality) በጠየቁ ጊዜ የግለሰብ ምርጫ ውስጥ ይወድቃሉ።በዚህም ጊዜ ምርጫ የሚሆነው በተስፋ ማጣት እና በእምነት ማለፍ (sink between despair and resignation, or take a leap of faith)መካከል እንደደሆነ እና፤ይሄንን ጃስፕርስ «መሻገር (Transcendence)» እያለ ይጠራዋል። እምነትን[Leap of Faith] በመምረጥ ግለሰቡ እውነተኛ ገደብ አልባ ነፃነቱን ሲያገኝ ይሄንን ጃስፕርስ «EXISTENZ» ይለዋል።“ይሄ ነፃነት ትክክለኛውን ሕልውና ያሳየናልና”በሚል ያስቀምጣል።


Philosophy Is for Everyman
የካርል ጃስፕርስ የፍልስፍና ትምህርቶች በመፅሀፍ መልክ ተሰንዶ የተቀመጠበት ቢሆን በመፅሀፉ ውስጥ «ሰውና ተፈጥሮ»፡ «ጥንተ-ታሪክና የአሁኑ ጊዜ»፡«ፖለቲካዊ እና ነፃነት»፡«ሶሺዎሎጂ እስከ ሳይኮሎጂ»፡«ከሲሲፈስ አፈታሪክ እስከ ሜታፊዚክስ»፡ «ከፍቅር እስከ መቃብር». . . በአጠቃላይ ፍልስፍናዊ ዳራን ያስቃኘትበት ሕልውና በሰፊው የተዳሰሰበት በይዘት አነስ ያለ መፅሀፍ ነው።


General Psychopathology⁵
በተሰኘው መፅሀፉ ውስጥ Psychopathology (ነገረ-አእምሮ ቀውስ)ን በሀስለሪያን (Husserlian) በተመሰረተ Phenomenological⁶(ክስተታዊነት) ጋር በማቆራኘት እጅግ ታላቅ የሆነ ሀሳብን በማሳየት ታላቅነቱ ያስመሰከረበት ስራው ሲሆን የሰው እና የአለም ግንኙነትን በፅንሰ-ሃሳቡ ለማንፀባረቅ የስሜት ምላሽን[Respond]  በማሸነፍ እንዲሁም በእሱ አብዮታዊ ጽንሰ-ሀሳብ  በመተካት እና በመጨረሻም በሳይኮፓቶሎጂ እና በስነ-አእምሮ ውስጥ የዲያሌክቲክ አስተሳሰብን ያስተዋወቀበት ስራው ነው።
    

እነዚህን እና ሌሎች ብዙ መፅሀፍትን በመፃፍ ፍልስፍናዊ ሀሳቦቹ እስከ ዘመናችን ድረስ ተፅእኖ ፈጥረው ተቀምጠዋል።ጃስፕርስ በሕልዎተ ፍልስፍና መስክ ቢመደብም በፍልስፍና ስራዎች እንደነአልበት ካሙ፣ጃን ፖል ሳርተር፣ሲሞን ዴ ቢዮቮር እንዲሁም ሌሎች ቀንደኛ ፈላስፎች እኩል የሚጠቀስ "መድቡት ቢባል" በራሱ የምደባ ስልት The disturbers[አብዮተኛ ሀሳቢያን] ስር ሊመድ የሚችል ታላቅ ሀሳቢ ነው።


_


ዋቢ መፅሀፍት
¹In Philosophy ላይ በፃፈው
²The Great Philosophers (Die großen Philosophen)ላይ በፃፈው
³Philosophy,By Karl Jasper
⁴Philosophy Is for Everyman by Karl Jasper
⁵General Psychopathology by Karl Jasper
⁶ነገሮች በክስተት የተፈጠሩ እና ያልተፈጠሩትን የሚያጠና የፍልስፍና የሀሳብ ጎራ ነው።




ተፃፈ . . .
ፍልስፍና
#ዳዳይዝም
❝ለእኛ ጥበብ በራሱ ፍጻሜ አይደለም...ነገር ግን የምንኖርበትን ጊዜ ለእውነተኛ ግንዛቤ እና ትችት የሚጋብዝ እድል እንጂ።❞
 
                    ሁጎ ቤል[የዳዳ ፍልስፍና አቀንቃኝ]




Dadaism[ዳዳይዝም]
በኪነጥበብ ላይ የተቀሰቀሰ አብዮት

“ዳዳ” የሚለው ቃል ምንነቱ ግልፅ ባይሆንም[ምንአልባት እንደእንቅስቃሴው ትርጉም አልባ ሊሆን ይችላል!] ❝ዳዳ[Dada]❞ በሮማዊዎቹ አርቲስቶች ትርስቲን ቲዛር እና ማርሲል ጃንኮ "Dada" የሚለው እንደ «እሺ፡አዎ፡ ይሁን» በሮማንኛ እንደሆነ በተደጋጋሚ አሰምተው ገልፀዋል።ከ1915[እ.አ.አ] በኋላ ጥበብ ላይ[ኪነጥበብ በዋናነት] የተዘነዘረ ዱላ ሲሆን ከበርሊን አቅንቶ ወደ ኒውዮርክ ሄዶ መላው አውሮፓን አዳርሶ እስያ ድረስ የዘመተ ፀረ-ጥበባዊ እንቅስቃሴ ነው።ዋንኛ ግቤ ነው የሚለውም «ዘመናዊ ነኝ ያለው አለም በማፈራረስና አዲስ ቅርፅ» መስጠት የነበረ ሲሆን የሰው ልጅ መለስ ብሎ ራሱን እንዲመረምር በጥበብ በኩል ለመቀስቀስ የሞከረም ነበር። ማንኛውም ዳዳይዝምን እከተላለሁ የሚል በጊዜው በሎጂክ፡ ስነግጥም፡በአስተሳሰብ ጎራ እና በዘመናዊ ካፒታሊዝም[Modern Capitalism] ላይ ጦርነቱን በሥዕል እና በኪነጥበብ በኩል አድርጎ መክፈት ይኖርበታል።በማሕበረሰቡ ውስጥ «አይነኬ[Taboo]» የሚባሉት ትላልቅ እምነትና የአስተሳሰብ ሁነቶችን ይተቻል። ይሄንን እንቅስቃሴ በዋናንት ያስጀመረው እና የመራው ጀርመናዊው ገጣሚና ደራሲ ሁጎ ቤል[Hugo Ball] ቢሆንም ኋላ ላይ ከፍተኛ መልኩ በምሁራን፡ፈላስፎች እና የኪነጥበብ ባለሙያዎች ድጋፍ አሰኝቷል አለም በጥበብ በኩል ቀስቅሷል።

አመፃቸውንም ለማሳየት ምንም አይነት ትርጉም የማይሰጡ[Nonsense] እና ምክንያት አልባ እንዲሁ ስግብግቦችን¹ የሚቃወሙ ሥዕል እና የኪነጥበብ ዘውጎችን በሰፊው የተጠቀሙ ሲሆን መጀመሪያ አካባቢ የነባር ኪነ ጥበባዊ ሂደትን[Normalistical Art] መቃወም ላይ ቢያተኩርም እየቆየ ሲሄድ በስነጹሁፉም፣ በሙዚቃውም፣በትምህርቱ፣በፖለቲካውም፣ኢኮኖሚም በመግባት «ለውጥ እንፈልጋለን!» የሚል የተቃውሞ ድምፅ አሰምቷል።

በገዢው ጨቋኝ መደብ እና ብሔርተኝነት ላይ የጥበብ በትርን በማንሳት ለኪነጥበብ ትግል ያደረገ ሲሆን «የስግብግብ ካቲታሊስቶች ምክኑይ እና አስተሳሰብ ማሕበረሰቡን ወደ ጦርነት አምርቷታል፤ለዚህም ኪነጥበብን እንደ መሳሪያት በመጠቀም በምክንያታቸው እና የአስተሳሰብ ፅንፋቸውን በተቃርኖሽ ማሳየት አለብን!» የሚል ቋሚ ፍልስፍና ሲኖረው ጆርጅ ግሮዝ[George Grosz] እንደውም ገፋ አድርጎት “የዳዳ እንቅሰቃሴ የዚህችን የጥፋት አለም መንገድ መቃወም[against this world of destruction] መሆን” አለበት በማለት በስራዎቹ ገልፆ አሳይቷል።እንደሀንስ ሪቸተር [Hans Richter] ገለፃ ‟ዳዳ ኪነጥበብ ሳይሆን ፀረ-ኪነጥበባዊ ነው፤ኪነጥበብ ላይ ኪነጥበብን በመጠቀም የሚያምፅ”እንደሆነ በተደጋጋሚ አስቀምጧል።ዳዳይዝም ባህላዊ[ተለምዷዊ] የሆነው የኪነጥበብ ሂደት ማሕበረሰቡን እዚህ ካደረሰ የኪነጥበብ የተቃርኖ ሂደት የተሻለ ነገርን ሊያስከትል የሚችል እንደሆነ በዋናነት አንፀባርቋል።


ኢትዮጵያ እና ዳዳይዝም[ግለሰባዊ ዕይታ]

ይሄንን መሰል የኪነጥበብ አመፃ እንቅስቃሴ ሀገራዊ ሂደትን በተላበሰ መንገድ መፈጠር መቻል አለበት።ሀገራችን በማሕበራዊ፣ፖለቲካው እና ኢኮኖሚያዊ መፈራረስ ውስጥ የከተታት ምንአልባትም እስከአሁን የመጣንበት የአስተሳሰብ ዘውግ ሊሆን ይችላል!ልክ በርሊንን የ"ለውጥ" ስሜት መፋፋም እና ከተጫነ ፍርሀት አልፎ በስግብግብነት እና ፍቅረ-ዝሙት በላይ እንደሄደች ሁሉ አዲስአበባ የዚህ በረከት ተቆዳሽ ልትሆን ይገባል።የማሕበራዊ፡ፖለቲካዊ፡የኢኮኖሚ እና የግለሰብ ማንነትን አብርሆት በኪነጥበባዊ አመፃ መፍጠር መቻል አለባት።የከተማ ብቻ ሳይሆን የመንፈስ አዲስነትን አም'ጣ ልትወልድ ይገባል።በግጥም፡በስዕል፡በስነፅሁፍ፡በሙዚቃ እና ፊልሞች የጭቆና ቀንበር በኪነጥበዊ ዱላ መገረፍ ይገባዋል።በትምህርት ስርአቱ እና ኢኮ-ፖለቲካል [Eco-oltical] ምህዳሩ በአብርሆት እንዲሁ በእውቀት ሊመራ ይገባዋል። ኪነጥበብም ሆነ ፍልስፍና በአብስትራክ ያለ ውበትን ከመግለፅ በመቆጠብ ቁሳዊ ትርምሶችን ሊተቹ እና ሊያንፀባርቁ ይገባል።የግለሰብ ልዕልናን በማሕበረሰብ ውስጥ እስኪሰርፅ ድረስ እና ማንኛውም የተቃርኖ ሀሳብ ቦታ እስኪሰጠው ድረስ አይነኬ ዘርፎችን መግለጡ የተሻለም ሊሆን ይችላል።



_______
¹Capitalism by itself


ተፃፈ በይሁዳ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ፍልስፍና
❝ለእኛ ጥበብ በራሱ ፍጻሜ አይደለም...ነገር ግን የምንኖርበትን ጊዜ ለእውነተኛ ግንዛቤ እና ትችት የሚጋብዝ እድል እንጂ።❞                       ሁጎ ቤል[የዳዳ ፍልስፍና አቀንቃኝ] Dadaism[ዳዳይዝም] በኪነጥበብ ላይ የተቀሰቀሰ አብዮት “ዳዳ” የሚለው ቃል ምንነቱ ግልፅ ባይሆንም[ምንአልባት እንደእንቅስቃሴው ትርጉም አልባ ሊሆን ይችላል!] ❝ዳዳ[Dada]❞ በሮማዊዎቹ አርቲስቶች…
የዳዳን ኪነጥበባዊ አመፅ እንቅስቃሴ ካነሳው አይቀር ፍልስምና ላይ ቃለመጠይቁ ከተሳተፉት የሀገራችን ታላላቅ ሰአሊያን አንዱ የሆነው ሰአሊ ዳንኤል ታዬ አለምን እንደ'ገማች [አስቸጋሪ ሽታ እንደያዘች] ሲያንፀባርቅ በተመሳሳይ መልኩ ቀንደኛ የዳዳ ፍልስፍና አቀንቃኝ የነበረው ጆርጅ ግሮዝ «የጥፋት መንገድ ላይ ያለችውን አለም[ግም ውስጥ የተዘፈቀች አለም]  የኪነጥበብን አመፃ ያስፈልጋታል»ል የሚል ጽኑ እምነት ሲኖረው ዳንኤል ይሄንን ሀሳቡን እንዲህ ሲል አንፀባርቋል፥

❝ .    .   .    .     .    .  .
ቴድሮስ:-ዳንኤል 'አለም ተገምቷል' ይላል ይሉሃል።ዓለምና ሕይወትን እንዴት ታየቸዋለህ?

ዳንኤል፦ገምቷል ማለት. . . አንተ ዓለም ያልገማ ይመስልኃል?

ቴዎድሮስ፦አዎን ያልገማ ነው የሚመስለኝ

ዳንኤል፦እ . . .እንዴት ላስረዳህ?. .  . በጣም የሚሸት ሽንትቤት ውስጥ ገብተህ ታውቃለህ?

ቴዎድሮስ፦አዎን

ዳንኤል፦ገና እንደገባህ በጣም ይሸትሃል አይደል?

ቴዎድሮስ፦አዎን

ዳንኤል፦አንድ ሰአት ብትቀመጥ'ስ?

ቴዎድሮስ፦አፍንጫዬ ሽታውን እየለመደው የሚሄድ ይመስለኛል።

ዳንኤል፦ሃያ አራት ሰአት ብትቀመጥ'ስ?

ቴዎድሮስ፦ይበልጥ ሽታውን የምለምደው ይመስለኛል።

ዳንኤል፦ አሥር . .መቶ . . .ሺህ አመት ስትኖር 'ሽታው የለም' የምትልበት ደረጃ ላይ ትደርሳለህ።እዚህ ውስጥ ልጅ ብትወልድ ልጆችህ ስለግማቱ ፈጽሞ እውቀት ይኖራቸዋል?

ቴዎድሮስ፦አይኖራቸውም።

ዳንኤል፦ልክ እንደዚህ ነው የእኛም ነገር።ስለአፈጣጠራችንና ስለምንኖርባት ዓለም ለዚህ ነው ማሽተትና ማሰብ ያቃተን።  .   .   .   .   .❞

[ፍልስምና ፩+፪+፫ በቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ከገፅ 17 የተወሰደ]



በዳንኤል ውስጥም ሆነ ሌሎች እውቅ ኢትዮጵያዊያን ሰአሊ እና ገጣሚያን ውስጥም የምትገኝ የአመፃ መንፈስ ናት።በእርግጥ «የዳዳ እንቅስቃሴ ደጋፊ ነኝ» የሚል በግልፅ ባይገጥመኝም ሀሳቡ ልቦናቸው ውስጥ ስለመኖር እምነት አለኝ[ከሀሳባቸው ለመረዳት እንደሞከርኩት!]።
ሶቅራጠስ የአቴን ፍልስፍናዊ ሙግት ሲያይ፦

❝የደካሞች አእምሮ ስለሌሎች ያስባል፤ የመካከለኛ አሳቢያን አእምሮ ስለ ተፈጥሮ ሲያስብ የጠንካሮች ደግሞ ስለ'ሀሳብ ያስባል!❞



ሶቅራጠስ የኢትዮጵያ የፍልስፍና ቻናል የሃሳብ ሙግት ካየ በኋላ፦

❝የደካሞች አእምሮ ስለ ማህበረሰቡ የባህል እስራት ያስባል፤መካከለኛ አእምሮ ያላቸው ስለሴት እና ፈጣሪ አለመኖር ቀኑን ሙሉ ይጨቃጨቃሉ፤ጠንካራ አሳቢያን በዜን ተጠምቀው የአርምሞ ዋሻ ገብተዋል !❞


[😑]
❝የሰው ልጅ የማሰብ ችሎታ የሚያዳብረው በሶስት የአስተሳሰብ ደረጃዎች ነው።  የመጀመሪያው እና ዝቅተኛው የአስተሳሰብ ደረጃ ነገረ-መለኮታዊ[Theology] ነው፤  ሁለተኛው ሜታፊዚካል[Metaphysical] የአስተሳሰብ ደረጃ ሲሆን ሦስተኛው እና ከፍተኛው የአስተሳሰብ ደረጃ አዎንታዊነት[Positivism] ነው። ሥነ-መለኮት እና ሜታፊዚክስ የሰው ልጅ ልጅ-አእምሮ ደካማ ምሁራዊ ጥረቶች ሲሆኑ አዎንታዊነት[Positivism] የአዋቂ የማሰብ አእምሮአዊ መግለጫ ነው።❞


___________________
de Philosophie positive, ላይ ኦገስት ኮሜት እንዳሰፈረው፥
ፍልስፍና
Photo
ጥንቆላ፡አምልኮት እና ስርአት
Based on Philosophical Point of views


በሰውልጅ ቀደመት ታሪክ ውስጥ  ከፍተኛ ድርሻ ይዘው የሚገኙ ሦስት ኃይላተ ሰብ ናቸው ጥንቆላ ፡አምልኮ እና ስርአት[ስርየት]።ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሰው ልጅ ከነበረው አጠቃላይ  የመረዳት ንቃት ማነስ እንዲሁም ለማይታዩ አካላት[መለኮታዊ ለሚላቸው(Superstition)] ከፍተኛ ቦታን ሰጥቷ ሲራቀቅበት እንዲሁም ሲያመልክበት እዚህ ያለንበት ደረጃ ደርሷል።

ብዙ ሰዎች  በትረ ኃይሉን ኃይማኖት የጨበጠ ጊዜ¹ እነዚህ ነገሮች እንደጀመሩ ያስባሉ።እውነታው ግን ይሄ ነው! የሰውልጅ ታሪክ «ሀ» ብሎ የጀመረ ሰአት የጀመሩ ናቸው።እንደውም በተቃራኒው በዘመነ ጽልመት እየተዳከሙ የመጡትንም እንዲሁም የሮማን ካቶሊክ ቸርች አብዛኞቹን በፀረ ክርስትናዊ ምልከታ ግድያ የፈረደችባቸው ጊዜያት ናቸው።

በመጀመሪያ ሀሳቤን ለማስረዳት በእነዚህ ሶስት ተመሳሳይ የሚመስሉን ነገርግን የተለያዩ ቃላት ውቅርን በመፍታት ልጀምር፥

ጥንቆላ[Witch]: ጥቁር አስማት[Black Magic] እና መናፍስት መጥራት[Summoning spirits] ላይ ያተኮረ በሰውልጅ የህይወት ዳራ ውስጥ ጣልቃ ገብነት በመፍጠር ለውጥ ለማምጣት የሚደረግ ነገር።

አምልኮ[occult]: ስለመናፍስት፡የሰውልጅ እውነተኛ መንፈሳዊ ማንነት እንዲሁም ስለተለያዩ ኃይላተ ተፈጥሮ[ነጭ አስማት እና ጥቁር አስማት] የሚያጠና ሳይንስ ነው።ከሜታፊዚክሱ እና ፓራሳይኮሎጂ ጋር ከፍተኛ ተመሳስሎ አለው[በዚህ አጋጣሚ! ዘመናዊው ሳይንስ በራሱ በዚህ ስር የሚመደብ ነው]

ስርአት[Ritual]:ማንኛውም የታቀደ ተግባር ለማንኛውም ነገር ሊደረግ የሚችል በሰዎች መሰባሰብ የሚከውን ነጭ አስማታዊ ስርአት። ባህላዊ፡ ሊሆን አልያ ፖለቲካዊ[የምርጫ ሂደት Ritual ነው!]ወይም ኃይማኖታዊ ሊሆኑ ይችላል በዚህ ይካተታሉ።
እዚህ ላይ እርቅ ከፈጠረን ፍልስፍና በእነዚህ ሶስት ኃይላተ ንቃት ላይ የነበሯት ጉልህ ሚና እንመልከት።



Philosophy And Witch Teaching

በየትኛውም ሰይጣናዊ አምልኮ[Black Magic] ውስጥ ወይም አስተሳሰብ ውስጥ የምናገኘው ነገር እጅግ የተዳከመ የፍልስፍ እንቅስቃሴ ሲሆን አምልኮቱ ካረቀቁት በቀር ተከታዮች ስራቸው በሙሉ ድምፅ ልምምዱን ማፅደቅ ብቻ ነው።በርግጥ ከቀደምት አባቶቻቸው የተማሩን ነገር ነበር እነሱ የሚተገብሩት አንዳንዶቹ ግን ፍልስፍናን እንደመራቀቂያ መሳሪያ በመጠቀም ሌላ ታሪክ ውስጥ ገብተው ነበር።ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ነገር  የእነቶማስ ሆብስ እና አርስቶትል ፍልስፍና ሀሳብ እና  አንድምታ ከጥንቆላ አስተምህሮ ጋር ንክኪ የነበረው መሆኑ ነው።የፕሌቶን ፍልስፍና[በተለይ Existence of the two worlds] አጥብቀው ይወዱታል።አንዴ ከተነሳ ላይቀር በአለም ላይ እጅግ ተፈላጊ ስለነበረው የሰለሞን ቀለበት(✡️) ማንሳቱ እጅግ አስፈላጊ ይሆናል። ሰለሞን ከእግዚአብሔር ከተቀበለው ጥበብ መብዛት የተነሳ ሰባ ሁለት[72] ዋና ዋና የመናፍስት ገዢ መሪዎች ላይ ስልጣን  በቀለበቱ በኩል ያገኘ እና ቀለበቱ የመናፍስቱን መሳቢያ ጠልሰም[በእኛ አጠራር መርብበተ-ሰለሞን]  በምልክትነት እንደያዘ ይታመናል።ይሄን ቀለበት ማግኘት ዋንኛ የጥንቆላ Objective Goal ነበር።



Philosophy Science & Occult

እመኑኝ! ሳይንስ የሚመስጣቹ ሰዎች ይሄኛውን ዘርፍ ትወዱታላቹ።በአይሁድ እምነት ውስጥ በነበረው ሚስጥራዊ ትምርህት ካባላ[Kabbalah]፤በግሪክ:በግብፅ እንዲሁ ሀገራችንን ጨምሮ  አጠቃላይ የአለም እምነቶች ውስጥ የገባው ሄርሜቲዝም [ኢትዮጵያዊው ሄኖክ] እና በስነ-ቅመማው ወይም አልኬሚ [Alchemy] ሚስጥራዊ አስተምሮች በሙሉ በከፍተኛ መልኩ ፍልስፍና የተጠቀሙ ሲሆን በአልኬሚው እንደነዚሞስ በሄርሜቲዝ ሙሉ በሙሉ Philosophical Aspect of Natural Existence  ስለነበረ በሙሉ።
በካባላው ውስጥ የአይሁድ ጠቢባን ፍልስፍና የአፍ መቻቸው ነበረ።ከእነ ዲሞክራተስ:ፕሌቶ:ታለስ:አንክሲማንደር አናክሲማነሳ:ፓራሜንደስ ወደኢል ደግሞ ዜኖ[Zeno of Elie] ከመሳሰሉትን ጋር ከፍተኛ ተመሳሳይ ነጥቦች ነበሯቸው። ዘመናዊ ሳይንስ አብዛኛው ምርምር እና ጥናት የወሰደው ከካባላ ትምህርቶች ነው።
አንደሰ ሁለቱን ለመጥቀስ ያህል፥
   1]Concept of Atom[የአተም ምንነት]
   2]የተፈጥሮ ህግ እና የሰው ልጅ ምንነት[ከሳይንስ አንፃር]
   3]የአንስታይን አንፃራዊ ህግ[Relativity Theory]
   4]የኳንተም ፊዚክስ ምርምሮች

ካባላ[Kabbalah] ወደእኛ ሀገር አስተምህሮቱን ስናመጣው ከ«ባህረ ሀሳብ» ጋር አንድ ነው[ማን ከማን ወሰደ ነጥቤ አይደለም!]


Philosophy Under  Alchemy

ይሄ ዘርፍ ላይ ደግሞ የኬሚካል ቅመማ፣ብረትን ወደ ወርቅ የመቀየር ሂደት ሌሎች የእፀዋት እና የከበሩ ዲንጋዮች ምርምር በዋናነት መርሁ ያደረ ሲሆን በግብፅ መነሻውን አድርጎ  በግሪክ በኩል ቻይና፡ህንድ እና አረብ እንዲሁም ሌሎች ጋር የደረሰ አለምአቀፋዊ ሚስጥራዊ አስተምህሮ ነው።አልኬሚ ብረትን ወደ ወርቅ የመቀየሩ ነገር በቀጥታ የሚፈታ አደለም።ፍልስፍና በሙስሊም ኡለማዎች[Golden Age of Islamic] ዘንድ እና በህንድ መንፈሳዊ እምነቶች[Hinduism,Zen Buddhism]በኩል ሞገስ ያገኘች ሰሞን ነበር አልሜኬ ከፈጣሪ የተበረከተላቸው። አልኬሜ እንደፍልስፍና የተፈጥሮ ንጥረ አካላት እና ሰው እንዴት እንደሚተሳሰሩ ስራዬ ብሎ ያጠናል።ሰው የንቃቱ እና የመረዳቱ ደረጃው ከዴካርት በላይ ያስጨንቀዋል።
በዘመነ ዳግም ውልደት ታዋቂ የነበሩ አልኬሚስቶች ኒውተን እና ተከታዮቹ[Calculase Based Universe] ፣ከአረብ ሒሳብ እና አስትሮኖሚ ምሁራን አቬሴናን እና ጅላል አል-ሩሚ እንዲሁም አቡ ሙሳ፣ ወደ ህንድ በዋናነት ኒታይኒታ
ሲድሀ እና ዮጊ ቬማናን  ፣ወደ ቻይና ሰን ፑ-ሂ[Sun Pu-Eh] እና ኮ-ሆንግ[Ko Hong]  ወደ ግብፅ ፈላስፎቹ በሙሉ በዚህ ተጠምደው ነበር ፤ወደ ግሪክ በዋናነት ዞሲሞስ እና አርስቶትል ወደእኛም ሀገር ደግሞ ሙሉበሙሉ በሚባል ደረጃ የነበረ ነገርግን ብረትን ወደ ወርቅ ከመቀየሩ በላይ ዋና ማእከሉ የእፀዋት መሰል ቅመማ ላይ ትኩረቱ ያደረገ ሆነ።



የአብርሃም ኃይማኖቶችን ጨምሮ ሌሎች ጥንታዊው ሆነ ዘመናዊ ኃይማኖት  ነገረ መለኮታ ከእነዚ በመነጨ አስተምህሮ የተቀረፀ ነው።ኒቺ በOn the Genealogy of Morality² መፅሀፉ በኩል አጠቃላይ እነዚህ ዳራ ለመጥቀስ ሞግሯል።የአምልኮ እና  የፍካሬ ከዋክብ ተመራማሪ የሆነው  ማንሊ ፒ.ሆል «The Secret Teaching of All Religion³» መፅሀፉን እንድታነቡ እየጋበዝኩ ሀተታዬን እቋጫለሁ።




___
ዋቢ

¹Dark Age[When Christianity of Thinking Mainly Dominants]
²On the Genealogy of Morality
Book by Friedrich Nietzsche
³The secret Teaching of All Religion By Manly P.Hall




ተፃፈ በበርፎሪኮን
❝መንግስት የሚናገረው ሁሉ ውሸት ነው፣ ያለውን ሁሉ ሰርቋል።❞

- Thus Spoke Zarathustra(ኒቼ)