ፍልስፍና
697 subscribers
493 photos
11 videos
478 files
39 links
"ይህ ቻናል መግቢያም ሆነ አጥር የለውም እንደ ሰው ለሚያስብ ብቻ ተከፍቷል!"
ጲላጦስ
Download Telegram
ፍልስፍና
Photo
°°

-ደስተኛ መሆን የሚፈልግ ማንኛውም ሰው #ሃንዳዛኪ ማንበብ አለበት፤

-አለምን ለመበቀል የሚፈልግ #አል_ማጉትን ማንበብ አለበት፤

-መዝፈን የሚፈልግ #ዳርዊሽን ይስማ፤

-ከሕልውና ጋር የሚበጣበጥ  #ማርኬዝን ማንበብ አለበት፤

-ህልም ማየት የሚፈልግ ሰው #ኢዛቤል_አሌን ያንብብ፤

-መውደድ የሚፈልግ ሁሉ #ኔሩዳን ማንበብ አለበት።

-ለብቸኝነቱ ሰዎችን የተራበ #ዶስቶቭስኪን ማንበብ አለበት፤

-ደስ የሚል ስሜትን የፈለገ  #አዚዝ_ናሲን ያንብብ፤

-እብደትን የሚሻ #ካፍካን ማንበብ አለበት፤

-ሁሉም ነገር የስቃይ ምንጭ እንደሆነ ለማወቅ የሚፈልግ #ሾፐንሃወርን ያንብብ፤

-ራሱን ማጥፋት የሚፈልግ #ራምቦን ማንበብ አለበት፤

-ቁጥርን ማወቅ የፈለገ #ፓይታጎረስን ያንብብ፤

-አለምን ማግኘት የሚፈልግ ሰው #ጋሊኖን ያንብብ፤

-እውነተኛ ነቀፋን የፈለገ #ማርክ_ትዌንን ያንብብ፤

-መማር የሚፈልግ #ታራቢሺን ያንብብ፤

-በዱር መሄድ የሚፈልግ ሁሉ #ሄንሪ ሚለርን ማንበብ አለበት፤

-በረሃውን ለማወቅ የሚፈልግ #ሙኒፍን ማንበብ አለበት።

-በመርከብ መጓዝ የሚፈልግ ሰው #ኮንራድን ያንብብ።

-ህማዊነትህ ከዚህ ዓለም እንዲነጥለው የሚፈልግ #ሲሆራንን ግለጥ፤

-ምድርን መውደድ መማር የሚፈልግ ሰው #ጋምዛቶቭን ያንብብ፤

-የአጻጻፍን መሰሪነት ለማወቅ የሚፈልግ #መሐመድ_አል_አሊን ማንበብ አለበት።

-ስለ ቋንቋው መማር የሚፈልግ #ሳሊም_ባራካትን ማንበብ አለበት።

-ህይወትን መፈልሰፍ የሚፈልግ ሰው #ሄሚንግዌይን ያንብብ፤

-መቃወም የሚፈልግ #ቾምስኪን ያንብብ፤

-እምቢ ለማለት የሚፈልግ ሁሉ #ኒቼን ያንብብ፤

-ለህይወት ትክክለኛ ጥያቄዋን መጠየቅ የሚሻ #አልበርት_ካሙ ማንበብ አለበት፤

-ስለ ሕይወት የበለጠ ለማወቅ የሚፈልግ #ዣን_ሄቨን ያንብብ፤

-መጨናነቅ የሚፈልግ #አንቶኒዮ_ስካርሜትታን ያንብብ።

-ልጅነቱን ማየት የሚፈልግ አዳም_ረታን ያንብብ፤

-ሙሉ በሙሉ ማበድ የፈለገ #ዲዮጋንን ያንብብ፤
እንኳን ለአድዋ የሰው ልጅ የነፃነት ድል ቀን በሰላም አደረሳችሁ !💯💯
💥💥🤩🤩🤩🥳🥳🥳🥳🥳
Silence as presence
ከእግዜር ጋር ንግግር
(ያዕቆብ ብርሃኑ)
*
… እንደ አንዳች ሞትና መቃብር ጠርዝ ላይ ያመላልሰኛል፡፡ በጩኸታሟ አዲስ አበባ መሃልአብዛኛውን የጽሞና ሀሰሳ ሰዓቴን የማሳልፈው በፈራረሱ የመቃብር ቅጥሮች ውስጥ ነው፡፡  በየሳምንቱ የማነባቸው the economist  እና the new York times ጋዜጣና መጽሔቶች ላይ እንኳን ቀድሜ የማነበው obituary (ዜና ዕረፍት) አምዳቸውን ሆኗል፡፡
ጊዜው ትንሽ ቆይቷል፡፡ ከአራት ወራት በፊት ከDecember 22- January 4 2019 የሚሸፍነው የthe economist መጽሔት double issue ዕትም ዜና ዕረፍት አምድ ላይ Silence as presence በሚል ርዕስ ስር ስለመነኩሴው ቶማስ ኬቲንግ ሕልፈት የተጻፈውን አነበበኩ፡፡ ካፒታሊዝምና ፍትወት በሚያቅነዘንዘው ልቅ ዓለም እንደ ኢየሱስና እንደ ጋንዲ ባለ ከፍያለ ልዕለ ሰብዕና ዝምታን የሕይወት መመሪያቸው አድርገው ለ95 ዓመታት ኖረው ስላለፉት ታላቅ ሰው፤ ለ95 ዓመታት በመኖሪያ ክፍላቸው ውስጥ ከአንዲት አልጋ፣ ከመጻፊያና ማንበቢያ ጠረጼዛና ወንበር በስተቀር ምንም ስላልነበራቸው መናኝ… እንደ ጋንዲ ለንቋሳ ገጽታን የተላበሱ፣ ግን ደግሞ ትንሽ ገዘፍ ያሉ፣ ረጅም፣ ራሰ በራ፣ በሚያስተዳድሩት ገዳም የሕይወት ዜይቤያቸውን ለሚሹ ፅሞናን በጸጥታ ከማስተማሩ መልስ በገዳሙ አንድ ጥግ ተቀምጠው ሞትን በመናፈቅ (longing to death) ዘመናቸውን በሙሉ የኖሩ ግዙፍ ስብዕና…

የእኒህ ሰው የሕይወት ዘመን ፍላጎት አንድ ብቻ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር… ይህንን ማድረግ የሚቻለው በጽሞና ብቻ ነው ብለው በማመናቸው ሌሎችም ከዕለትተለት ሩጫቸው በምትተርፋቸው ጊዜ ማድረግ እንዲችሉ ሲጥሩ አሳልፈዋል፡፡

እኒህ ሰው ከበመካከለኛው ዘመን በእስፓኝ ከኖሩት st. John the cross የተዋሱትና አሻሽለው መታወቂያቸው ያደረጉት ግሩም አባባል አላቸው፡፡
‹‹God's first language was silence.››   st. John the cross
‹‹everything else is bad translation.››   Thomas Keating
‹‹Including holy manuscripts.›› እኔ
እኔም አልኩ… ስታወሩ ስሜታችሁን ዝም ስትሉ ግን ነፍሳችሁን ማንበብ እችላለሁ፡፡ ዝም ማለት የቻለ እርሱ አሁንን ብቻ ሳይሆን ዘለዓለምን ማዘዝ ይችላል፡፡ ዝም ማለት የቻለ እርሱ ከአምላኩ ጋር እንኳን ባይሆን ከራሱ ጋር በተግባቦት ማውራት ይችላል፡፡ ግጥም ምንም አይልም፡፡ ስዕል ጥሩ ነገር ነው፡፡ ድርሰት በጣም ጥሩ ነገር ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሙዚቃም እጅግ በጣም ጥሩ ነገር መሆን አለበት፡፡ እነዚህ ሁሉ ግን ስንኩል የዝምታ ገጽታዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ በላይ ዝምታ ይበልጣል፡፡ ዝም ማለት፣ ፀጥታ(የሚረብሽ ድምጽ አለመኖር) ሁሉ ዝምታ ሊሆን አይችልም፡፡ ዝምታ(ጽሞና) ረቂቅ ነገር ነው፡፡   
የሆነን ነገር፣ መውደድህንም ቢሆን እንዴትም ብትገልጸው በተናገርከው ቅጽበት ወዲያው ትርጉሙን አዛብተኸዋል፡፡ ዋጋውን ቀንሰኸዋል፡፡ ለ misunderstanding ግዙፍ በር ከፍተሃል፡፡ ከቻልክ በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ምንም አትበል፡፡ በጣም ውድ የሆነውን ነገር በዝምታና በተግባር ልትገልፀው ሞክር፡፡  እኔ እንኳን ይህችን ሹክ ልልህ ጽሁፉን ካነበብኩበት ከፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ጀምሮ ራሴን ማሳመን ተስኖኝ ይሄው ሳመነታ ነበር፡፡
በቅርቡ ከmay 4- may 10 በሸፈነው በዚሁ የthe economist ዕትም ethics and evolution በሚል ርዕስ ስር ባነበብኩት አንድ ጥናት መሰረት ባለፉት 30,000 ዓመታት ሂደት የሰው ልጅ ጭካኔ(cruelity) እና እንስሳዊ ባህሪት ከመሰሎቹ ዝንጀሮና ጎሬላዎች ተሽሎ የተገኘው እጅግ በጣም በጥቂቱ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የሰለጠነው የሰው ልጅ እስከ አውሬያዊ ባህሪያቱ ይኖራል፡፡ እኔም፣ አንተም፣ አንቺም ጭምር… ከዚህ አውሬያዊነት መሻሻልን የሻተ ዝም ይላል፡፡ በየቀኑ ቢያንስ የ40 ደቂቃ የጽሞና ጊዜ ይኖረዋል፡፡ ዝም ማለት የቻለ እርሱ ራሱን ያሸንፋል፡፡ ራሱን ማሸነፍ የቻለ፣ ሌሎችን፣ ዓለምን የማሸነፍ ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ የጠቀስኳቸውን የዘኢኮኖሚስት ጽሁፎች በጠቀስኳቸው ርዕሶች Google ላይ search ብታደርግ ማግኘት እንደምትችል አረጋግጥልሃለሁ፡፡ በል እንግዲህ ልሰናበትህ… የጽሞና ሠዓቴ ደረሰች!

© ያዕቆብ ብርሃኑ


Source : Philosphyloves 🔥
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም  (Alador)
ነገረ እኩይ—Problem of Evil

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
==============================

የፊታችን ቅዳሜ (ግንቦት 24) የበጋ ሌክቸሮች መርሐ ግብራችን ትኩረቱን በ<<ነገረ እኩይ—Problem of Evil>> ላይ አድርጎአል። በትምህርት ቤታችን በሃይማኖት ፍልስፍና ስር በፍሬው ማሩፍ የሚሰጥ ኮርስ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በዘርዐያዕቆባዊ "እነዚህ እንዲህ እንዲህ ይላሉ እነዚያ እንዲህ እንዲህ ይላሉ.." የፍልስፍና መንገድ በተጋባዥ እንግዳ ልንቃኘው ነው።

መምህሩ ዮናስ ዘውዴ ነው።

የ<<ነገረ እኩይ>> አንኳር ጥያቄ <<ከፍፁማዊውና ደግ አምላክ ጎን ለጎን እንዴት እኩይ አብሮት ሊኖር ቻለ?>> የሚለው ነው፡፡ የጥያቄው መነሻ ደግሞ የፈጣሪ መለያ ባህርያት ተብለው በሚታወቁት (omnipresent, omnipotent, omniscient, and omnibenevolence) ላይ ተንተርሰው የተለያዩ አሳቢዎች እና ፈላስፎች <<በዓለም ውስጥ የሚታየውን እኩይ ነገር ከነዚህ የፈጣሪ ባህርያት ጋር የሚጣረስ ነገር አለው>> ብለው የሚያነሷቸው መከራከሪያዎች ናቸው።

ለምሳሌ የጥንታዊ ግሪክ ፈላስፋ ኤፒኩረስ ከፍፁማዊው አምላክ ጎን ለጎን እንዴት እኩይ አብሮት ሊኖር እንደቻለና ማጥፋት እንዳልቻለ ለማብራራት የሚከተሉትን አማራጮች እና አማራጮቹ የሚያስከትሉት የሎጂክ ተቃርኖ አስቀምጦአል :-

— ምናልባት እግዚአብሔር እኩይን ማጥፋት እየፈለገ ነገር ግን አልቻለ ይሆን? ይሄ ከሆነ ደግሞ ከእግዚአብሔር የ"ሁሉን ቻይነት" ባህሪ ጋር የሚጣረስ ነው።

— ሁለተኛው እግዚአብሔር እኩይን ማጥፋት እየቻለ ግን ማጥፋት አልፈለገ ይሆን? ይሄ ደግሞ ከእግዚአብሔር "የደግነት" ባህሪ ጋር የሚቃረን ነው።

— ሦስተኛ እግዚአብሔር እኩይን ማጥፋት እየቻለም እየፈለገም ሆኖም ግን ሆን ብሎ እኩይ እንዲኖር ፈልጎ ይሆን? ይሄ ደግሞ የእግዚአብሔርን "ጨካኝነት" የሚያሳይ እና ከ"ፍፁም ደግነቱ" ጋር የሚጋጭ ሊሆን ነው።

— አራተኛ እግዚአብሔር እኩይን ማጥፋት የማይፈልግ እና የማይችል ሆኖ ይሆን? ይሄ ደግሞ የእግዚአብሔርን "ሁሉም ቻይነት" ብሎም ህልውነት የሚያሳጣ ሊሆን ነው።

ወደ ትምህርት ቤታችን ጎራ ብለው ይሄን ለዘመናት ሲያከራክር የቆየውን እና አሁንም እያከራከረ ያለን የሃይማኖት ፍልስፍና ጥያቄ ላይ ይወያዩ፣ ይከራከሩ፣ ይማሩ።

ዮናስ ዘውዴ አብዛኞቻችሁ (በሚድያ) የምታውቁት ሲሆን የመጀመርያ ዲግሪ የቋንቋ እና የየማህበራዊ ሳይንስ፤ ሁለተኛ ዲግሪ የቲዮሎጂ፣ እና የፍልስፍና ትምህርቶችን አጠናቅቆአል። አሁን ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ሦስተኛ ዲግሪውን በመስራት ላይ ይገኛል።

© ዘርዓያዕቆብ የፍልስፍና ትምህርት ቤት
ፍልስፍና
Photo
ሳልስተ ደረጃዎች


በቀደሞት የፍልስፍና የ❝እውቀት❞ እንዲሁም የ❝ህይወት❞ ጉዞ አንዱ ሀሳብ ገዢ ሆኖ ጊዜውን ሲገዛ ደግሞ በተራው የወደቀና የተናቀው ደግሞ ቀን ወቶለት በቀደመው ላይ ድል ተቀናጅቶ የፍልስፍናው አሳብ የልህቀት ተደርጎ ሲመለክ እና ሲታይ እዚህኛው ክፍለዘመን ደረሰን። በዘመነ ዳግም ውልደት(በምዕራባውያን) የሀይማኖተ-ፍልስፍና ነገር ራሱን ወደ ማጥፋት በፍጥነት እያመራ በነበረበት ወቅት አንዳንድ (በጣት መጥቀስ የምንችላቸው) ፈላስፎች ሀይማኖተ-ህግጋታቸው ወደ ፍልስፍናው ከማቅረብ አልፈው መሰረታቸውን አፅንተው የእናንተንም እንዲሁ ተመልከቱ ብለው ሀይማኖተ ፍልስፍና ❝ሐዋሪያ❞ዊነታቸውን ተወጥተዋል። ከእነሱ መካከል ደግሞ አንዱ ሶረን ኪርጋርድ ተጠቃሽ ነው።


ኪርጋርድ በተለያዩ መፅሀፎቹ "የአምላክን አስፈላጊነት ከዛም በዘለለ ደግሞ የኃይማኖትን በሰውልጅ ህይወት ላይ እጅግ የጠለቀ እና ጎልህ ሚና በብእሮቹ ከትቦ አልፏል «ሆነ» ያልውን አስፍሯል።ከዛሬ አንዱን መፅሀፉን ወስደን ትምህርታዊ ዳሰሳ እናድርግበት።


   °𝑓𝑒𝑎𝑟 𝑎𝑛𝑑 𝑡𝑟𝑒𝑚𝑏𝑙𝑖𝑛𝑔
𝑢𝑛𝑑𝑒𝑟 ˝𝑝𝑟𝑒𝑎𝑚𝑏𝑙𝑒 𝑓𝑟𝑜𝑚 𝑡ℎ𝑒 ℎ𝑒𝑎𝑟𝑡˝

በመፅሀፉ ኪርጋርድ ሦስተ የህልውና ደረጃዎች (Sphere of Existence ይላቸዋል) አሉ ይለናል።

  1)ኪነጥበባዊ(Aesthetic)
  2)ስነ-ምግባራዊ(Ethical)
  3)ኃይማኖታዊ(Religious)

እንደኪርጋርድ መልከተ ሰውልጅ ከነዚህ የህይወቱ መስመር በአንዱ ነው።ኪርጋርዱ ራሱን በኃይማኖታዊ(Religious) ይመድባል ሌሎችም ቢሆኑ በዚሁ ጎራ እንዲሆኑም ይመክራል። መፅሀፉ በውስጥ የኪነጥበብን(Aesthetic) እና ኃይማኖታዊ(Religious)መካከል ያለውን ጠብ (ጠቡ ካለም!)ለማብረድ ይመስላል።ሁለቱ ለገዛ ራሳቸው ምእሉ ናቸው ይሄም ደግሞ አንዱ ያለሌላኛው ጎዶሎ አልሆነም ባይነቱን ኪርጋርድ ይተቸዋል።በምሳሌ ሶስቱንም እንያቸው

  1)ኪነጥበባዊ[Aesthetic]
በዚህኛው መደብ ውስጥ ደስታ ተኮር ህልውናን[Hedonistic Existence] ሲመድበው ቅፅበታዊ ደስታ መሻትን ውበትን በደቂቃ መመኘትን ከጊዜያዊ ሁነት ጋር ያያይዘዋል።

  2)ስነምግባራዊ [Ethical]
የአብርሀም የእምነት ፍተሻ(leap of faith) ማመን ብቻውን በቂ አደለም በመሰረቱ በአምላክ የተቀረፀ የታመነበት ህግ(ስነምግባር) እጅጉኑ አስፈላጊ ነው።በየትኛው መሰረታዊ ሀይማኖት አስተምህሮ ስነምግባር የእምነቱ ማዕከል ነው።በስነምግባር መደብ እራሱ መንገድ ነው ከውበት ወደ ሀይማኖታዊነት ያለ ድልድይ

   3]ሀይማኖተኛ[Religious]
ይሄ በኪርጋርድ ፍልስፍናዊ ሀሳብ ከሆነ የመጨረሻው ደረጃ ሲሆን ሰው ራሱን ለፈጣሪ የሚሰጥበት በውበት አምኖ በስነምግባር ታሽቶ የሚቀርብበትን የአብርሃም እምነት በልጁ የመስዋት «ቀልድ» አልፎ የታየበትን የማረጋገጫ እና የምርቃት ደረጃ ነው።በዚህ ደረጃ አንድ ሰው ስርአታዊ ሀይማኖተኛ ነው ከስርአተ ተፈጥሮ ያለፈ[the Man Who higher than the universal] ነው። ከውበት[አካል] ወደ ስነምግባር[መንፈስ] አልፎ ሀይማኖተኛ¹ [ነፍስ] ሆኗልና።


ኪርጋርድ ሶስቱን የሰው ህልውናዎች እኺህ ናቸው ይላቸዋል።❝አንድ ሰው የመጨረሻ ግቡ ሊሆን የሚገባ ሀይማኖተኛ መሆን ነው።በቅፅበት ደስታ ወይም በረጅም ህግ ብቻ መቅረት የለበትም።መንገዶች እንጂ መዳረሻ አደሉምና! ❞ሲል ያጠናቅቃል።


___________
¹ሀይማኖተኛ ሲል የአርብ ሰጋጅ አልያ የእሁድ ተሳላሚ ለማለት እንዳልሆነ ልብ ይሏል!
ፍልስፍና
#ካርል_ጃስፕርስ
❝በራሴ ቆራጥነት በየጊዜው እና ሁኔታ ውስጥ፣ ያለፈውን ቋንቋ ይበልጥ ግልጽ በሆነ መንገድ በሰማሁ ቁጥር፣ ለህይወት ብርሃን እየተቃረብኩኝ ይሰማኛል።❞
                   ፥ካርል ጃስፕርስ

የካርል ጃስፕርስ [Karl Jaspers]
ፍልስፍናዊ ዕይታ እና የመፅሀፍ ቅኝት

ካርል ጃስፕርስ በየካቲት 23 1883(እ.አ.አ) ተወልዶ በየካቲት 26 1969(እ.አ.አ) ዓ.ም ያረፈ ታላቅ እና ወሳኝነቱ ሕልዖተ-ፍልስፍና
(Existentialism) የነበረ የጀርመን-ስዊድን ሀገር ተወላጅ የሆነ ፈላስፋ እና ሳይካትሪስት ነው። በልጅነት ጊዜው ለፍልስፍና ፍላጎት የነበረው ቢሆን በአባቱ ግፊት የህግ ትምህርትን አጥንቶ በውስጡ ወደ ሳይኮሎጂው ገብቶ ከዛም በኋላ ፍላጎቱን ፍልስፍናን ተማረ።በፍልስፍና ስራዎቹ ውስጥም የሁለት ታላላቅ ፈላስፎች ማለትም የፍሬድሪክ ኒቼ እና የሶረን ኪርጋርድ 'የግለሰብ ነፃነት(individual freedom)' አስተሳሰብ በሰፊው የተንፀባረቁበት ሲሆን¹ የህይወት ፍልስፍናውም ወደ ሕልዖተ-ፍልስፍና (Existentialism) እንዲቀይር ያደረገውም ይኽ ነበር።

በDie Grossen Philosophen(The Great Philosophers)² መፅሀፍ ስራው
የፍልስፍናን የሀሳብ ምልከታ ጉዞ ለአራት ሲከፍለው ፦
1] The foundations[ምስረታ]: የግለሰብ ንቅናቄ ያስጀመሩትን ሶቅራጠስ፡ቡድሀ:ኮንፊውሺየስ፡ ኢየሱስን ሲያስቀምጥ ምስረታውን ያጠነከሩት ደግሞ ፕሌቶን፡ኦውገስቲን:ካንት እና ሌሎችን አካቶ መድቦታል።

2] The original thinkers[ቀንደኛ ሀሳቢያን]: አናክሲማንደር፡ሄራክሊተስ፡ፓራሜንደስ፡ባሩች ስፒኖዛ፡ፕሎቶኒየስ፡ላ-ቱዙ.  .  .

3]ተንታኝና ለዋጭ ሀሳቢያን: አርስቶትል፡ ዲሞክራተስ፡ቡሩኖ፡ኢፒከረስ፡ሌብኔዝ:ሂግል፡ዚኖፋነስ  ሌሎችንም አካቶበታል።

[4] The disturbers[አብዮተኛ ሀሳቢያን]:
ዴካርት፡ፓስካል፡ኒቼ፡ኪርጋርድ፡ማርክስ እንዲሁም በሳይንሱ መስክ አንስታይን፡ዌብነር ማክስ. . . በማድረግ በዚህ መልክ ይከፍላቸዋል።


   Philosophy³ (ፍልስፍና) በተሰኘው ስራው ውስጥ በቅፅ 3 በ1932 በታተመው የፍልስፍናውን ጉዞ በዘመናዊው ሳይንስ በሆነው ዳሰሳዊያን (Empiricism) በማንሳት ከሚታየው ሀሳብ ተሻጋሪ (transcend) እንደማያደርግ እና መጋፈጥ እንደማይችል በማስረዳት ሰዎች እውነታን(Reality) በጠየቁ ጊዜ የግለሰብ ምርጫ ውስጥ ይወድቃሉ።በዚህም ጊዜ ምርጫ የሚሆነው በተስፋ ማጣት እና በእምነት ማለፍ (sink between despair and resignation, or take a leap of faith)መካከል እንደደሆነ እና፤ይሄንን ጃስፕርስ «መሻገር (Transcendence)» እያለ ይጠራዋል። እምነትን[Leap of Faith] በመምረጥ ግለሰቡ እውነተኛ ገደብ አልባ ነፃነቱን ሲያገኝ ይሄንን ጃስፕርስ «EXISTENZ» ይለዋል።“ይሄ ነፃነት ትክክለኛውን ሕልውና ያሳየናልና”በሚል ያስቀምጣል።


Philosophy Is for Everyman
የካርል ጃስፕርስ የፍልስፍና ትምህርቶች በመፅሀፍ መልክ ተሰንዶ የተቀመጠበት ቢሆን በመፅሀፉ ውስጥ «ሰውና ተፈጥሮ»፡ «ጥንተ-ታሪክና የአሁኑ ጊዜ»፡«ፖለቲካዊ እና ነፃነት»፡«ሶሺዎሎጂ እስከ ሳይኮሎጂ»፡«ከሲሲፈስ አፈታሪክ እስከ ሜታፊዚክስ»፡ «ከፍቅር እስከ መቃብር». . . በአጠቃላይ ፍልስፍናዊ ዳራን ያስቃኘትበት ሕልውና በሰፊው የተዳሰሰበት በይዘት አነስ ያለ መፅሀፍ ነው።


General Psychopathology⁵
በተሰኘው መፅሀፉ ውስጥ Psychopathology (ነገረ-አእምሮ ቀውስ)ን በሀስለሪያን (Husserlian) በተመሰረተ Phenomenological⁶(ክስተታዊነት) ጋር በማቆራኘት እጅግ ታላቅ የሆነ ሀሳብን በማሳየት ታላቅነቱ ያስመሰከረበት ስራው ሲሆን የሰው እና የአለም ግንኙነትን በፅንሰ-ሃሳቡ ለማንፀባረቅ የስሜት ምላሽን[Respond]  በማሸነፍ እንዲሁም በእሱ አብዮታዊ ጽንሰ-ሀሳብ  በመተካት እና በመጨረሻም በሳይኮፓቶሎጂ እና በስነ-አእምሮ ውስጥ የዲያሌክቲክ አስተሳሰብን ያስተዋወቀበት ስራው ነው።
    

እነዚህን እና ሌሎች ብዙ መፅሀፍትን በመፃፍ ፍልስፍናዊ ሀሳቦቹ እስከ ዘመናችን ድረስ ተፅእኖ ፈጥረው ተቀምጠዋል።ጃስፕርስ በሕልዎተ ፍልስፍና መስክ ቢመደብም በፍልስፍና ስራዎች እንደነአልበት ካሙ፣ጃን ፖል ሳርተር፣ሲሞን ዴ ቢዮቮር እንዲሁም ሌሎች ቀንደኛ ፈላስፎች እኩል የሚጠቀስ "መድቡት ቢባል" በራሱ የምደባ ስልት The disturbers[አብዮተኛ ሀሳቢያን] ስር ሊመድ የሚችል ታላቅ ሀሳቢ ነው።


_


ዋቢ መፅሀፍት
¹In Philosophy ላይ በፃፈው
²The Great Philosophers (Die großen Philosophen)ላይ በፃፈው
³Philosophy,By Karl Jasper
⁴Philosophy Is for Everyman by Karl Jasper
⁵General Psychopathology by Karl Jasper
⁶ነገሮች በክስተት የተፈጠሩ እና ያልተፈጠሩትን የሚያጠና የፍልስፍና የሀሳብ ጎራ ነው።




ተፃፈ . . .