ፍልስፍና
698 subscribers
493 photos
11 videos
478 files
39 links
"ይህ ቻናል መግቢያም ሆነ አጥር የለውም እንደ ሰው ለሚያስብ ብቻ ተከፍቷል!"
ጲላጦስ
Download Telegram
"ጠርጥር! ፣ ጠርጥር! አንዳንዴ ከገንፎም አይጠፋም ስንጥር" ይላል ያገሬ ሰው!

በ17ኛው ክፍለ ዘመን በፈረንሳይ ገኖ የወጣ አፍቃሬ−አመክንዮ ፈላስፋ ነው፤ ዴካርት። በዓለም የፍልስፍና ታሪክ ውስጥም የዘመናዊ ፍልስፍና አባት ተደርጎ ይቆጠራል። ገና በጠዋቱ እናቱ እንደወለደችው የሞተችበት ዴካርት፣ የህይወት ውጣ-ውረዱን ዘመዶቹ ቤት በማደግ መወጣት የቻለ ሲሆን አልፎ ተርፎም እውቅ የሒሳብ ልሂቅ፤ ፈላስፋ እና ሳይንቲስት እንዲሁም የዘመናዊ ፍልስፍና አባት ሊሆንም ችሏል።

ዴካርት እድሜውን የፈጀው የእውቀት መጀመሪያ ምን እንደሆነ ሲያስስ ነው፡፡ ይህ እሱ የፈለገው ቀዳማይ-እውቀት እያንዳንዱ ሰው የግሉን ህይወት ሊመሠርት የሚችልበት የማይናወጥ እውቀት ነው፡፡
ለመጠራጠር ማሰብ ያስፈልጋል፤ ከተጠራጠርን ማሰብ እንችላለን፤ ካሰብን ደግሞ ያ ያሰብነውን እንሆናለን፡፡ ጥርጣሬ መጀመሪያ ላይ ነገሮችን በሙሉ ወደ ጥያቄ ይለውጣል ኋላ ላይ ደግሞ ይገለብጥና የእርግጠኝነት ምንጭ ይሆናል፡፡
በዚህች ዓለም ላይ የማንጠረጥረው ነገር ምን አለ? ለሚለው ጥያቄ ቁጭ ብሎ ሲቆዝም ዴካርት ያገኘው መልስ ቢኖር “I think, therefore I am” የሚለውን ዓረፍተ-ነገር ነው፡፡
ሁሉን እጠራጠራለሁ፤ እኔ ራሴ በሕይወት እየኖርኩ ስለመሆኔ ግን ልጠራጠር አልችልም፤ ምክንያቱም አስባለሁ፤ ለመጠራጠር ራሱ መጀመሪያ መኖር አለብኝ፤ አሁን እያሰብኩ ነው፤ ስለዚህም እየኖርኩ ነው፡፡ (I think, therefore I am) የሚለው የዴካርት አባባል፣ ለፈላስፎች ጥልቅ የሆነ ትርጉም አለው፡፡ የጥንቱና የመካከለኛው ዘመን ሰው፣ እውቀትንና እውነትን ለማግኘት ከራሱ ውጭ ባለው ሰፊ ዓለም ውስጥ ሲባዝን ነበር፡፡ በዴካርት ፍልስፍና ውስጥ ግን የውጭውን ዓለም መዳሰሱ ቀርቶ የምርምሩ ጅማሮ ከራስ ሕልውና ሆነ፡፡
የዚህን ዓለም እውነት ለማግኘት መጀመር ያለብን “ከራሳችን” ነው የሚለው የዴካርት ፍልስፍና፤ የዕውቀትንና የእውነትን መለኪያ መስፈርትን ለማግኘት ባደረገው ጥረት ውስጥ “ተፈጥሮን” ከእውነት ምንጭነት አስወገደው! ... ለነገሩ እሱዬ መጀመሪያ መጠራጠር የጀመረው እሱ-ራሱ ነበር፡፡

እፊታችን እያየን ከምናወራቸው ተጨባጭ ነገሮች ጀምሮ የምናምናቸው ነገሮች እርግጠኞች ልንሆን አንችልም የሚለው ዴካርት ሁሉንም ነገር፤ የሚያየውን፣ የሚዳስሰውን፣ የሚያሸተውን፣ የሚቀምሰውን በአጠቃላይ በስሜት ህዋሳቱ አማካኝነት የሚያገኘውን መረጃ በሙሉ ከመቀበል ይልቅ በጥያቄና በጥርጣሬ ያዋክባቸዋል።
እርግጠኛ የሆነ እውቀትን ለማግኘት ዴካርት የተጠቀመበት ዘዴ ደግሞ፤ ከዚህ በፊት እርግጠኛ የሆንባቸውን ነገሮች ሁሉ በመጠራጠር እና ባለመቀበል ነው። እናውቀዋለን የምንለውን ነገር ሁሉ በጥያቄ ማብጠርጠር ማለት ነው።”
ዘላቂና የማይናወጥ እውቀትን መመስረት ካለብኝ፣ እስከዛሬ በሕይወት ዘመኔ የሰበሰብኩትን እውቀት ተብዬ ሁሉ ድምጥማጡን ማጥፋት እንዳለብኝ ተገንዝቤአለሁ” ይለናል፤ “ቀዳማዊ ተመስጦ” በተባለው ድርሳኑ በአካባቢያችን ያሉ ነገሮችን ሁሉ እየበረቃቀስን እና እያብጠረጠርን መፈተሽ እንዳለብን ያሳስባል፤ ዴካርት።
ይህንንም ተከትሎ ሦስት አፈንጋጭ ሙግቶችን
ያቀርባል፤ በዘልማድ የተቀበላቸውን ነገሮች ሁሉ ለማስወገድ እንዲረዱትና እርግጠኛ የሆነ እውቀት ለመመስረት እንዲችል። እያንዳንዱን እምነቱን አንድ በአንድ በመጨፍለቅ ሳይሆን መሰረታዊ የእምነቱን መርሆዎችን ማንገራገጭ እንደስልት ይጠቀማል፤ ዴካርት።
በመሰረታዊነት የተጠቀመባቸውን ሦስቱን ሙግቶች እንደሚከተለው ማየት ይቻላል።

ሀ) ማንኛውንም ያልተመረመረ ሀሳብ እና በስምምነት የተቀበልነውን ሁሉ በተደራጀና መመሪያዎችን በተከተለ መልኩ በጥርጣሬ መፈተሽ። ወይም ባጭሩ አፈንጋጭነት ልንለው እንችላለን። ይህ በየዋህነት የተቀበልናቸውን አስተሳሰቦች ለማጥቃት የተጠቀመበት ሙግት ነው። “ከጊዜ ወደ ጊዜ የስሜት ህዋሶቼ እያጭበረበሩኝ እንደ ሆነ ደርሸበታለሁ።” የሚለው ዴካርት፤ “ለአንዲት ጊዜ እንኳን ያታለለችኝን የስሜት ህዋሴን አለማመኔ ሁነኛ እርምጃ ነው” ይላል።

ለ) ያልጠራ፣ እራሱን ያልቻለ እና ግጭቶች/መፋለሶች ያሉበትን ሐሳብ አለመቀበል። ይሄኛው የዴካርት ሙግት "የህልም ሙግት" (The Dream Argument) እየተባለ ይጠራል።

ሐ) እራስን በማወቅ፤ ከዓለት በጠነከረ መሰረት ላይ ሐሳባችንን መስርተን፤ በማንኛውም ጥርጣሬ የማይነዋወጥ ከራስ ከውስጥ የመነጨ “እያሰብኩ ስለሆነ እኔ ኅልው ነኝ” የሚል ግለሰባዊነት ላይ መድረስ። (“Cogito, ergo sum”) “የስሜት ህዋሳት አንዳንዴ ያጭበረብሩናል።


ይቀጥላል ✍️
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም  (Peter)
እንቀጥል አ


ባለ ጠርዙን ማማ ከሩቅ ስናየው ድቡልቡል አድርገው ያሳየናል፤ ቀጥ ያለ እንጨት ውኃ ውስጥ ብንከትተው ስብርብር ያለ ሆኖ ይታዩናል፤ ስለዚህ የስሜት ህዋሳት የሚታመን ብያኔ አይሰጡንም ማለት ነው።
አንዳንዴ ደግሞ ህልምና እውኑን መለየት ይቸግራል፤ “አልጋው ላይ እንዳልተጋደመ ሰው ሁሉ ጥርት ያሉ ምስሎችን አያለሁ፤ በህልሜ መሆኑን እንኳን የምለይበት ምንም ምልክት አጣለሁ” .... ዴካርት ይህንን እያምሰለሰለ ይቀጥልና እንዲህ ይለናል። “በስሜት ህዋሳቶቼ የማገኘውን መልእክት ባልቀበልም ይኸው ደግሞ ሌላ እውነት የሚመስል ነገር የሚያሳውቀኝ ሌላ መንገድ አለ”
የህልሙን እና የስሜት ህዋሳቱን መልእክት ይበልጥ እያፍተለተለ ከፍ ወዳለ ሀሳብ ይወሰደዋል።
“የሚያታልለኝ ኃይል አለ ማለት ነው። ፈጣሪ ይህንን ሊያደርግብኝ ይችላልን? ይህንን ካደረገብኝማ “ፍጽምና” ባህሪው ሊሆን አይችልም። ስለዚህ እኔን ለማወናበድ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ የሚሰራ ሌላ አወናባጅ ዲያብሎስ አለ ማለት ነው” ይላል ዴካርት።
ስለዚህም የዚህን አወናባጅ ዲያብሎስ ምክር ለማሸነፍ ሐሳቦቸን ግልጽ፣ ልዩ (እራሱን የቻለ) እና እርስ በርሱ የማይፋለስ በማድረግ ወደ ፍጹማዊው የፈጣሪ ባህሪ ማስጠጋት አለብን ማለት ነው። ሐሳባችንን በዚህ ቀመር
ማስላት ከቻልን፣ በንጹህ ልቦናችን ፈጣሪ እውነትን ስለሚለግሰን ለምናስበው ነገር እርግጠኛ መሆን ይቻለናል ማለት ነው።
በዚህ የሀሳብ ቀመራዊ አስተሳሰብ እየተመራን የማንጠራጠረው እውቀት ካገኘንና ጥያቄዎቻችንን ሁሉ መመለስ ከቻልን የእራስ ኅልውና አገኘን ማለት ነው። በአካባቢያችን ያሉትን ሁሉንም እየተጠራጠርንና እየጠየቅን በቀላሉ ስለ ህልውናቸው እርግጠኛ መሆን አንችልም፤ ነገር ግን አንድ መካድና መጠራጠር የማልችለው እውነት አለ፤ ይኸውም በአሁኑ ሰዓት እያሰብኩ መሆኑን ልቦናዬ እየነገረኝ ነው።
“እያሰብኩ ስለሆነ ኅልው ነኝ ማለት ነው” ይለናል ዴካርት።
ሁሉንም የቀደሙ እውቀቶችን እንዲፈትሻቸው የነገረው አንድ እርግጠኛ የሆነ ሳይንሳዊ እውቀት ፍለጋ ሲሆን፤ አንድ እርግጠኛ እውነት ካገኘ ሙሉ ፍልስፍና አድርጎ ሥጋና ደም እንደሚሰጠው እርግጠኛ ነበር፤ ዴካርት። ስለሆነም አሁን ልቦናው የሚነግረው እርግጠኛ እውቀት እያሰበ መሆኑን ሆኖ አገኘው።
"እኔ ግን ምንድን ነኝ?" ይላል እንደገና... የሚያስብ ቁስ ነኝ ማለት ነው አዎን፣ እያሰብኩ መሆኔን መካድ ስለማልችል፤ እኔ የማስብ "ነገር" ነኝ ማለት ነው። የማስበው በአእምሮዬ ነው፤ አእምሮ ደግሞ ግዙፍ አካል የለውም ረቂቅ ነገር ነው፤ ስለሆነም አይበሰብስም፣ አይፈረከስም፣ አይሞትም ማለት ነው

ሆኖም አሁንም መልስ ያላገኘንለት ነገር አለ፤ እኔ ከየት መጣሁ? እናትና አባቶቼ ለእኔ መፈጠር ምክንያቶች እንጂ ፈጣሪዎቼ አይደሉምና።
የእራሳችን አስገኝዎች እኛው እራሳችን ልንሆን ደግሞ በፍጹም አንችልም። ስለሆነም ማሰብ እንድንችል አድርጎ የፈጠረን ፍጹም እና “ገባሬ ኩሉ” የሆነ ፈጣሪ መኖሩን በዚሁ እንረዳለን ማለት ነው፤ ይለናል ዴካርት
የፍጽምና ባህሪ ያለው ፈጣሪ ደግሞ ጎደሎና ሐሰት የሆነ ነገር/ሀሳብ እንድናስብ አይፈቅድም፤ ምክንያቱም ከባህሪው ጋር አይስማሙምና ማለት ነው።
እዚህ ዓለም ላይ ያሉ ቁስ አካላትም (በሰው ውስጥ ያሉትንም ጨምሮ) እውነት ናቸው ማለት ነው የተምታታ ሀሳብ እንዲኖረኝ የሚያደርገኝ ሙሉ የክፋት አቅሙን አሟጥጦ የሚጠቀም ያ “አወናባጅ ዲያብሎስ” ነው እንጂ ፈጣሪ ሊሆን አይችልም የአወናባጁን ዲያብሎስ ምክር እየለየን ማሰብ ከቻልን፣ ወደ እርግጠኛ እውቀት የምናደርገው ጉዞ የተሳካ ይሆንልናል ማለት ነው።
ልዕለ መልካምነት ባህሪው የሆነ ፈጣሪ መኖሩን ማወቅ አለብን።
እዚህ ዓለም ላይ ያለው እውነት ስለመሆኑ እርግጠኛ እንድንሆን የሚያደርገን ፈጣሪ ፍጹም እና የመልካሞች ሁሉ መልካም በመሆኑ፣ ለኛም ግልጽ የሆነና የጠራ ሀሳብን ይለግሰናል፡፡
ዴካርት፤ ግልጽነት፣ ልዩነት እና አለመፋለስን እንደ ሒሳብ ቀመር፣ የአንድን ጉዳይ እውነተኝነት/እርግጠኝነት የምንመዝንባቸው አድርጎ ስለቀመራቸው በቤተሰቡ ስያሜ “የካርቴዚያን ዲበ አካል” ተብሎ ተሰይሞለታል
የአውሮፓዊያን የፍልስፍና አስተምህሮ ለመጽሐፍ ቅዱሳዊ ሀሳቦች መልስ ለመስጠት መፍጨርጨሩ አልቀረም ... ፈላስፋው አማኝ ነኝ አሊያም ኢ-አማኒ ነኝ ቢልም፣ የቀደመው የአውሮፓ ፍልስፍና የሳይንስን እና የመጽሐፍ ቅዱስን ግጭት፤ የመጽሐፍ ቅዱስን ረቂቅነት ማስገንዘብ፤ ወይም ሳይንስ መጽሐፍ ቅዱስን ሲያፈርሳት የሚከሰተውን ባዶነት መተንተን የሚመሳስሉ ሀሳቦች ያደሉበታል የዴካርት አካሄድም ከዚሁ የተለየ አይመስልም። የስህተቶች ሁሉ ምንጭ አወናባጁ ዲያብሎስ ነው ይለናልና!
“I will suppose therefore that ... rather some evil genius of the utmost power and cunning has employed all his energies in order to deceive me.”
በመጨረሻም የበረከትን አጭሬ ልጋብዛችሁ...☺️

በር መስኮት ዘግተህ
ቀዳዳዎችን ደፍነህ
የለኮስከው ሻማ፣
"በራ" "ጠፋ" ካለ
ጠርጥር...

ቤት ያፈራው ንፋስ ከጎጆህ እንዳለ!
በብዙዎች ተወዳጅነት ያተረፈው መቀመጫውን ራሺያ ያደረገው ቴሌግራም አዲስ ህግ አስተዋውቋል !

ከአንድ ሳምንት በኃላ ቴሌግራም ተግባራዊ አደርገዋለሁ በአለው አዲሱ ህግ መሰረት ከዋናው የTelegram መተግበሪያ ውጪ የሚገኙትን የቴሌግራም ሰርቨር የሚጠቀሙ Apps እንደሚዘጋ ገልጿል።

ከአንድ ሳምንት በኃላም እንደ Plus ፣Xgram Mobogram ፣ ninja gram ፣ Hulugram የመሳሰሉትን የቴሌግራም መተግበሪያወች አዲስ አካውንት መክፈት ሲፈልጉ እና Update ማድረግ ሲፈልጉ ወደ እነዚህ መተግበሪያዎች ኮድ አይላክም።

ስለሆነም በዋናው ቴሌግራም #Official App ብቻ ነው መጠቀም የሚቻለው በ 1 ሳምንት ጊዜ ውስጥም ኦፊሻል የቴሌግራም መተግበሪያ ከ PLAY STORE ዳውንሎድ በማድረግ Login ያድርጉ ብሏል።

ከ1 ሳምንት በኃላ ከዋናው የቴሌግራም መተግበሪያ ውጪ ሁሉም የቴሌግራም ሰርቨር የሚጠቀሙት መተግበሪያዎች ይዘጋሉ ቴሌግራም እንደ አሳወቀው የሚሆን ከሆነ ነገርግን Plusን ጨምሮ Hulugram ይህንን መረጃ እያስተባበሉ ይገኛሉ ! share share
"My life was in front of me, closed, ended, like a sack, and yet, everything in it was unfinished. I tried to judge her for a moment. I would have liked to be able to tell myself: it's a beautiful life. However, it could not be judged, it was only a sketch; I was wasting my time signing policies for eternity, I hadn't understood anything. I didn't regret anything: there were many things I could have regretted [...]; death had robbed them all of their charm."

(Jean-Paul Sartre, The Wall)
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም  (MUSSIE. S)
ለዚህች ሀገር እዘኑላት

ደራሲ -ካህሊል ጂብራ
መፅሀፍ -የጠቢባን መንገድ

በአንዱ ቀን ጠዋት ደቀ - መዛሙርቱ ነብዩን ከበው ተቀመጡ፡፡ በአይኖቹ ላይ ርቀቶችና ትዝታዎች ነበሩበት። ሀፊዝ የሚባለው ደቀ - መዝሙሩም እንዲህ አለው፦ «መምህር ሆይ! ስለ ኦርፋሴስ ከተማ ንገረን፡፡ በእነዚያ አስራ ሁለት አመታት ስላረፍክበት ሀገርም ንገረን፡፡»

አልሙስጠፋ ዝም አለ። ወደ ጋራዎቹና ወደ አድማሱም ፊቱን አዙሮ ተመለከተ። በፀጥታው ውስጥ ጦርነት ነበር!!
ከዚያም አላቸው
  "ወዳጆቼ  ሆይ በእምነቶችና በባዶ ሀይማኖቶች ለተሞላች ሀገር እዘኑላት...

"በጥባጮችን እንደ ጀግና በእልልታ ለምትቀበል ገዳዮችን እንደ ለጋስ ለምታሞካሽ ሀገር እዘኑላት...

"ያልሸመነውን ጨርቅ ለሚለብስ፤ያልጋገረውን ዳቦ ለሚመገብና ያልጠመቀውን ወይን ለሚጠጣ ሰው እዘኑለት።


"ፍቅርን በህልሟ ለምትንቅ ሰትነቃ ግን ለምንትበረከክለት ሀገር እዘኑላት...

"ወደ መቃብር ሲወርድ ካልሆነ በስተቀር ድምፁ ለማይሰማ፤ እንዲሁም አንገቱ በሰይፍ እና በግንዲላ መካከል ሲጋደም ካልሆነ በስተቀር  ለማያምፅ ህዝብ እዘኑለት...

"መሪው ቀበሮ ፣ፈላሰፋው ቀጣፊ  ፣ጥበቡም መኮረጅና መለጣጠፍ ለሆነ ህዝብ እዘኑለት...

"አዲስ ገዢዎቹን ጥሩምባ እየነፋ ለሚቀበልና እንደገና ጡሩምባ እየነፋ ሌላውን ለመቀበል ሲል ብቻ በንቀት ጩኸት ለሚያሰናብታቸው ህዝብ እዘኑለት....

"አዋቂዎቹዋ እድሜ በመግፋት ዲዳ ለሆኑባትና ልጆቹዋ ገና ከህፃን አልጋ ላይ ላልተነሱላት ሀገር እዘኑላት...

"ግዛቷ ለተበጣጠሰና እያንዳንዱ ብጥስጣሽ  ራሱን እንደ አንድ ሀገር ለሚቆጥርባት ሀገር እዘኑላት...
<< There is always some madness in love. But there is also always some reason in madness. >>

Thus Spoke Zarathustra

 
      ``ሁሌም በፍቅር ውስጥ ትንሽዬ እብደት ትኖራለች ፤ በእብደቷም ውስጥ ትንሽ ምክንያት አለ``

         #ኒቼ  በዛራቱስትራ በኩል
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም  (Peter)
የስርቻው መጣጥፍ.pdf
6.4 MB
የስርቻው መጣጥፍ | Notes from the underground

ይሄው ብዙ ሰው ሲጠይቅ ስላየሁ ነው የለቀቁት ! አብዛኞቻቹ ሰዎች ግን መፀሀፍ ገዝታቹ የማንበብ ልምድ ቢኖራቹ ጥሩ ነው ! የደራሲውን ልፋት እንዲው በከንቱ ባስታቀሩ መልካም ነው
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም  (Peter)
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም  (Peter)
አብዛኞቹ   ቅዱስ  መጽሀፎች  የሚባሉት የግሪክን  አፈታሪክ  በቀጥታም  ሆነ  በተዘዋዋሪ ቅድት  አርገዋታል  😊 አሁን  ለምሳሌ  የፓንዶራን  ታሪክ ቀየር  አርገው  ሄዋንን  እባብ  አታሎዋት  ምናምን  ብለው ይሰክሱሀል  አምነህ  ትቀበላለህ 🤓 ለማንኛውም  ፓንዶራን  የማታውቋት  ታሪኳን ልንገራችሁና  እናንተው  ፍረዱ በጥንታዊ  የግሪክ አፈ-ታሪክ  ፓንዶራ  በምድር  ላይ  የመጀመሪያዋ ሴት  ነበረች  የአማልክት  አምላክ  ዜዑስ የጥበብ  አምላክ  የሆነችውን  ሔፋስቱስ ፓንዶራን  ከምድር  አፈርና  ውኃ  አድቦልቡላ ትሠራት  ዘንድ  አዘዛት ሌሎች  አማልዕክትም እንደየችሎታቸው  ለፓንዶራ  ስጦታ  አበረከቱላት—አፍሮዳይት  ቁንጅናን፣  አፖሎ  ሙዚቃ፣ ሔርመስ  ደግሞ  የንግግር  ችሎታን  ሰጧት ስሟ  ፓንዶራም  ትርጉሙ  ‹‹ሁሉ-የተሰጣት›› ማለት  ነው።
The  Ancient  Greek  myth  of Pandora's  box  tells  the  story  of  how  Prometheus  gave  the  gift  of fire  to  humans,  and  as  a  result  was punished  by  Zeus.  Prometheus escaped  his  punishment  and  as  an act  of  revenge,  Zeus  created  a beautiful  woman  for  Prometheus  to marry  and  called  her  Pandora.
ፕሮሚትየስ  ከገነት  እሳትን  በሰረቀ  ግዜ፣  ዜዑስ  ተቆጣ፤  ብቀላም  ይሆን  ዘንድ  ፓንዶራን አሳልፎ  ለፕሮሚትየስ  ወንድም  ሰጠ  ፓንዶራም  በማንኛውም  ሁኔታ  ቢሆን እንድትከፍት  ያልተፈቀደላት  ትንሽ  ሳጥን ተሰጣት ይሁን  እንጂ  በተፈጥሮ  አለቅጥ የተቸራት  ጉጉቷ  በዛና  ፓንዶራ  ያንን  ሳጥን ከፈተችው።  ነገር  ግን  በሳጥኑ  ተከድኖ ተቀምጦ  የነበረው  ‹‹ክፋት››  ከሳጥኑ  አምልጦ ወጣ፤  በመላው  ምድርም  ተሰራጨ።
ፓንዶራ  ተቻኩላ  ሳጥኑን  ለመዝጋት  ሞከረች፤ ነገር  ግን  በሳጥኑ  ውስጥ  የነበረው  ሁሉ  ድሮ ወጥቶ  አልቋል— ከአንድ  ነገር  በስተቀር  ያም ‹‹ተስፋ››  ነበር ፓንዶራ  በሠራችው  ሥራ  ሁሉ አዘነች፤  ተጸጸተችም  የተጣለባትን  ኃላፊነት በአግባቡ  ባለመወጣቷ  የዜዑስን  የቁጣ ውርጅብኝ  በፍርኅት  መጠባበቅ  ጀመረች ዜዑስ  ግን  አልቆጣትም— ይህ  እንደሚሆን ያውቅ  ነበርና ከዚያ  ወዲህ  ክፋት  ዓለምን ተቆጣጠረው …....  ምን ይመስላችኋል ታዲያ ፍርዱን ለናንተ 😊
  ``በዚህ ጊዜ: ወንድ በሁለት ቡድን መካከል  በአንዱ ወድቋል በነፃነት ውስጥ አልያ በባርነት።  ማንም ሰው ሁለት-ሶስተኛው የሚሆነው ቀኑን ለራሱ ካልሆነ: እርሱ ባርያ ነው።ምናልባትም እሱ የቢዝነስ ሰው አልያ የመንግስት ሰራተኛ ወይም የአገር መሪ እንዲሁም ምሁር ሊሆን ይችላል።``

     ፍሬድሪክ ኒቼ"Human, All Too Human"
የእስረኞቹ እንቆቅልሽ

አንተ እና ጓደኛህ በአንድ ወንጀል ተጠርጥራችሁ ታሰራችሁ፡፡ ሆኖም መርማሪ ፖሊሶቹ ምንም አይነት ማስረጃ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ እናም ሁለታችሁም በተለያየ ክፍል እንድትሆኑ ተደረገ። መርማሪዎቹም ለየብቻችሁ ያሉትን አማራጮች አቀረቡላችሁ።


አማራጭ አንድ - አንተ ከተባበርክ እና ወንጀላችሁን ከተናዘዝክ ነገር ግን ጓደኛህ ዝም ካለ አንተን በነጻ እንለቅሃለን እርሱ ግን
አስራ አምስት አመታት ይታሰራል፡፡

አማራጭ ሁለት - ጓደኛህ ወንጀላችሁን ከተናዘዘ ነገር ግን አንተ ዝም ካልክ፣ እርሱ በነጻ ይለቀቃል... አንተ አስራ አምስት አመታትን ትታሰራለህ።

አማራጭ ሶስት- ጓደኛህም አንተም ከተባበራችሁን ሁለታችሁም አምስት አመታትን ትታሰራላችሁ፡፡

አማራጭ አራት- አንተም ጓደኛህም ካልተናዘዛችሁ፤ ሁለታችሁም ቀላል የሆነ የአንድ አመት እስራት ትታሰራላችሁ።

በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ብትሆን ምን ታደርጋለህ?
መናዘዝህ የተሻለ ውጤትን የሚያስገኝ ይመስላል፤ ጓደኛህን ብትከዳውና ብትናዘዝ  የሚገጥምህ በነጻ የመለቀቅ ዕድል ነው᎓᎓በተቃራኒው ዝም ብትልና ባትናዘዝ፣ የአንድ አመት ወይም የአስራ አምስት አመት እስራት ይጠብቅሃል።

ሆኖም አንተ ነጻ ሁነህ ጓደኛህ አስራ አምስት አመታትን በእስር ቤት ሲማቅቅ ማየት ምን አይነት ስሜት ይፈጥርብሃል?

እናም ይህ እንቆቅልሽ የሚያስነሳው መሰረታዊ ጥያቄ “እንደ ማህበረሰብ ማሰብ” ወይስ “እንደ ግለሰብ ማሰብ” የሚል ይሆናል። ለሁላችንም የተሻለ አማራጭ የሚሆነው እንደ ማህበረሰብ ማሰብ ነው፤ ሆኖም ሌላኛው ሰው ምን እንደሚያስብ አናውቅምና ለራሳችን
መልካም የሚሆነውን ለማድረግ ስንል ራስ ወዳድ እንሆናለን፡፡ እኔ እንኳ ባልስርቅ ሌላው ይሰርቃል የሚል ሃሳብ ይፈጠራል። ይህ አስተሳሰብም በድሃ አገራት ላለው የሙስና እና ስርዓት አልበኝነት አንዱ ምክንያት ነው፡፡

ለምሳሌ ያህል፣ አንድ አሳ የሚሰገርበት ሃይቅ አለ ብለን እናስብ። አሳ አስጋሪዎች በዚህ ሃይቅ ውስጥ ያሉት አሳዎች በራስ ወዳድነት ያለ ልክ የሚያጠምዱ ከሆነ፣ የአሳዎቹ ቁጥር ተመናምኖ በአንድ አመት ውስጥ ሃይቁ አሳ አልባ ይሆናል። ሆኖም ግን አግባብ ባለው ሁኔታ በልክ እና በመጠን የሚያሰግሩ ከሆነ፣ የአሳዎቹ ቁጥር አይመናመንም፤ እንዲያውም ከአመት ወደ አመት የሚያገኙት የአሳ ቁጥር እየጨመረ ይመጣል።

እዚህ ላይ ዋነኛ ጥያቄው መተማመን የሚለው ነው፡፡ አሳ አስጋሪዎቹ በመጠን ሊያሰግሩ ቢስማሙም አንዳቸው ሌላኛውን እስካላመኑ ድረስ ስምምነታቸው ዋጋ አይኖረውም፡፡ ልክ በሁለት ክፍሎች ውስጥ ለብቻቸው ተቀምጠው እንዳሉ እስረኞችም ይሆናሉ፡፡

ምንጭ- ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ዝግጅት-ፍሉይ አለም
``ከልክ ያለፈ እውቀት እኮ በውኑ በሽታ ነው: ሊያምኑ ፅኑ በሽታ.. ``


Dostoyevsky የስርቻው መጣጥፍ ትርጉም በፋሲል ይትባረክ
Forwarded from አርምሞ🧘🏽‍♂ (ሞገስ ዘአምድ Gυrυ🪽)
ሶስቱ ነብያት
|
|
1. ኒቼ 2. ካርል ዩንግ 3. ዶስቶቪስኪ
|
የነብይነት ጸጋ ነበራቸው። የኦርቶዶክስ ቤ/ክ መጸሀፎቻቸውን ደፍራ ከቅዱሳት መጸሀፍቷ ብትቀላቅል ብዙ ትጠቀማለች።
|
|
1. ኒቼ
በተቋማዊው ክርስትና ላይ የበረታ ሒስ በመሰንዘር ይታወቃል። " የመጨረሻው ክርስትያን መስቀል ላይ ሞቷል" እስከማለት የደረሰ ጭፍለቃው ስነጽሁፋዊ ግነት እንጂ literall(አማናዊ) ትርጉም አይደለም። የdetail አቅሙን ያየ ሌጣውን ትርጉም አይወስድም። ኒቼ cult ተሰርቶበታል። ፈጣሪን በአኗኗራቸው ክደውት በአንደበታቸው እግዜር አለ የሚሉት ቅዘናሞች አፍ ማስቲካ ሆኗል።
|
" እግዜር ሙቷል" የምትል ሀረጉን መዘው ፍዳውን ያሳዩታል።
እስቲ ሙሉውን.....
|
" እግዜር ሙቷል። አዎ ሞቶ ይቀራል። ደሞ እኛ ነን የገደልነው። ከግድያም ታላቁን ግድያ የፈጸምን እኛ ሰዎች ሊመቸን ኖሯል? ምድሪቱ ያላትን ቅዱስ እና ታላቁን ሀይል በቢላችን ደሙ አፍስሰናል! ይሔን ደም ከእጃችን የሚያጥብልን ማነው? የቱ ፌሽታ ካሳ ሊሆን? የቱ አስደንጋጭ ጫወታ ሊያረሳሳን? እውነት? ኤግዜር ለእኛ ካደረገልን በላይ ለራሳችን ማድረግ እንችላለን? ይሔን ለራሳችን በማድረግ አማልክት መሆን ምን ሊረባን?"
|
|
ቃል በቃል አልተረጎምኩም። ፍረዱኝስቲ ይሔ ወንጌል አይደለም ወይ? ስነጽሁፋዊ ውበቱ ከጀርመንኛ ወደ እንግሊዘኛ ሲሔድ ከእንግሊዘኛም ወደ አማርኛ ስመልሰው ተዳክሟል። "በራሳችሁ ምንም ማድረግ አትችሉም፣ ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ያጠፋታል፣ ደሙ በልጅ ልጆቻችን ይሁን" የሚሉ የመጸሀፍ ቅዱስ ንግግሮች ከላይ ባለው የኒቼ ሀተታ ካልተፈቱ ግራ ናቸው። በተሰቀለው ኢየሱስ ላይ ሰው ሁሉ አንድ ነው ባይ ነው። መሲሁ የትኛውም ዘመን ላይ ቢመጣ አገዳደሉ ይለያይ እንጂ ሟች ነው።
"እኔ ይሔን አላደርግም" ያለ ምእመን እንደ ጴጥሮስ ሊክድ የተዘጋጀ ነው።
📍 የተነሳውን ኢየሱስ በማመን/በመሆን ግን ልዩነት አለ ይላል።
ኒቸ በስልጣን እንጂ በጨዋነት አያምንም። ትንሳኤ ስልጣን ነው ይላል the will to power መጸሀፉ ላይ። እንደ መጀመሪያው ሟች አቤል ትሁት ሆኖ ሞቶ መቅረት ወይስ እንደ መጨረሻዉ ሟች ኢየሱስ እውነት ተናግሮ ሞቶ መነሳት?
|
|
2. ካርል ዩንግ
|
የሲግመን ፍሮይድ ተማሪ ነበር። ከፍሩይድ ይበረታል ይሉታል። አባቱ ፓስተር ነው። በሙሉ ስሙ ካርል ጉስታቭ ጁንግ(ዩንግ) ይባላል። ይሔም እንደ ኒቼ ጀርመናዊ ሲሆን psychiatrist, psychoanalys እና ሳይንቲስት ነው። ድርሳኖቹን ያነበበ ከ 149 አመት በፊት አለም እንዲህ አይነት ደፋር ነበራት ወይ ማለቱ አይቀርም!
|
ታዋቂ መጸሀፉ the red book ይሰኛል። ከዲያቢሎስ ጋር በመንፈሱ ተገናኝቶ የጻፈው ነው። ከዚህ ገጠመኙ ተነስቶ የግል ሰይጣናችንን መገናኘት አለብን ይላል። በባህል እና ሀይማኖት የተወገዘ ድብቅ ፍላጎታች የሚፈጥረው Shadow አለ። ስንቆጣ ልጆቻችንን እስከመግደል የደረሰ ቅጣት የሚቀጣቸው በዚህ Shadow ውስጥ የሚገለጠው ሰይጣን ነው።
" ተቆጡ በቁጣችሁ ላይ ጸሀይ አይግባ" ካለ በሗላ "ለዲያቢሎስም እድል ፈንታ አትሰጡት" ይላል። አጅሬ ሹልክ ትላለች ሲለን ነው።
|
ሴጦ እየተገለጠ ልጆቻችንን ይቆጋል፣ ወዳጆች bully ያደርጋል፤ ስራችሁን ብታጡስ እያለ ያቦካል። ለኛ አይታይም! ባለቤቱ ፍሬውን እያየ የራሴ ጠላት እራሴ ነኝ ብሎ የታገለ አንድ ቀን እንደ ዩንግ ይገናኘዋል። ክስተቱ shadow encounter ይባላል።
የኛ ሰይጣን ከዋናው ሰይጣን ይለይልናል። በውጣችን ሆኖ ማስጠቃቱን ያቆማል።
" እባብም እርግብም ሁኑ የሚለው ትዕዛዝ ይፈጸማል" ነው መደምደሚያው!
|
ኒቸ እግዜርን የገደለ ሰው እረፍት የለውም ሲል ዩንግ ተቀብሎ እግዜር በውስጡ የተነሳለትን ያሳያል። ሰው ሰይጣንን ፊት ለፊት ካገኘው በሗላ 3 stage አለው ይላል።( በቀጣይ ጽሁፍመጣበታለሁ)
|
|
3. ዶስቶቪስኪ

ሩስያዊ ነው። ከ105 አመት በፊት የተገኘ ደራሲና ጋዜጠኛ። የኒቸ literatural prophecy ደርሶበታል። ተቋማት ደግፈው ያቆሙት የስነምግባር ሰው የፈረሱበት እለት ሊሆን የሚችለውን ዶቶቪስኪ ሆኖት ጻፈው።
|
ኒቼን አምኖ በዩንግ መንገድ ያልሔደ ሰው ዶቶቪስኪን ይመስላል። የስርቻውን ሰው ይሆናል። the underground man ይለዋል።
ፍርፋሪ እና ልጆች መኖር ያስቀጥሉት የነበረው የተለመደው ሰው ከ existential (ህልውናዊ) ጥያቄዎቹ ፊት ስላልቆመ የስነ-ምግባር ሰው ይመስላል ባይ ነው።
|
ዶቶቪስኪ በስሜት ሆኖት ያሳየናል። ከ Red bookም በላይ እጅግ የምፈራው መጸሀፍ ነው። ፍርሀት እንደ አይጥ ስርቻ ለስርቻ የሚያርመጠምጠኝ ነበርኩና የሚለውን ሳነብ ያ ቦታዬ ያልዳነ ያህል ያመኛል። ልቤን ስውር እያደረገኝ ስንቴ አስቀመጥኩት?
|
በስራ እና በልጅ ላመልጣት የነበረች ክፉ ጥረት ነበረች። በሁለቱም የተሳካልኝ ሰው አይደለሁምና ህልውናዊ ጥያቄዎቼ ፈጠው አላላውስ አሉኝ። ዛሬ የተወለድኩ ያህል "ከየት መጣሁ? ወዴት ልሒድ? ማነኝ?" ምናምን አልኩ። ሰውነቴ እስር ቤት ሆኖብኝ መተንፈስ ተቸግሬአለሁ። በየአመቱ ይሔን መጸሀፍ ጀምሮ ያለመጨረስ እቅድ አለኝ። ዘንድሮም እሱ ላይ ነኝ። በጨዋታ፣ በፌ.ቡ፣ በበርጫ፣ በጨብሲ፣ በኢየሱስ፣ በወንጌል፣ በታማልዳለች አታማልድም፣ በጨላ አጫብለን የረሳነውን አማናዊ ጥያቄ እና ፍላጎታችንን ያፈጣል።
|
ሶስቱ ተባብረው የሚሉት ይሔን ነው።
" በስነ-ምግባር አታመልጡም! ለጊዜው የጸጥታ ተቋማት ከሌቦች ጋር ስላልሰሩ አትሰርቁም፤ አማኝ የመሰላችሁት የሀይማኖት ተቋማት ብሔር ስላልገባቸው ነው"

.
ባጠቃላይ
#የሰላም_ዘመን_አልፎ_የጽድቅ_ዘመን_ይመጣል እያሉን ነበር።



፦ Behailu_mulugeta


@rasnflega
`` እናንተ ወደ እግዚአብሔር ስትናገሩ እየፀለያችሁ ነው፤ እግዚአብሔር መልሶ እናንተን ሲያናግር ግን የአእምሮ ታማሚ (𝑠𝑐ℎ𝑖𝑧𝑜𝑝ℎ𝑟𝑒𝑛𝑖𝑎) ናችሁ። ሞታን እናንተን ሲያናግሩ እናንተ መንፈሳዊ ናችሁ፤ ግን እናንተ ሞታንን ስታናግሩ የአእምሮ ህመም ተጠቂ ናችሁ! ``

𝑡ℎ𝑜𝑚𝑎𝑠 𝑠𝑧𝑎𝑠𝑧 𝑓𝑟𝑜𝑚 ℎ𝑖𝑠 𝑏𝑜𝑜𝑘 "𝑡ℎ𝑒 𝑚𝑦𝑡ℎ𝑠 𝑜𝑓 𝑚𝑒𝑛𝑡𝑎𝑙 𝑖𝑙𝑙𝑛𝑒𝑠𝑠"
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዶስቶቭስኪ እግዚአብሔር እንደሞተ ከኒቼ ሲሰማ be like..😂
ይሄ የነቢዩ ዳዊት ምስል ነው ብትባሉ ምን ያህል ታምናላችሁ?

ዘመነ ትንሳኤ የ‹‹እውናዊነት (Realism)›› ፍልስፍና ያቆጠቆጠበት ወቅት ነው፡፡ ‹‹እውናዊነት (Realism)›› ማለት ከቢሆንና ከምናብ ዓለም ወጥቶ በምድር ላይ ያለውን እውነታ እንዳለ ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡ የ‹‹እውናዊነት (Realism)›› ፍልስፍና በነሚካኤል አንጀሎ አርትና በማኪያቬሊ የፖለቲካ ፍልስፍና ውስጥ ተንፀባርቋል፡፡

በዘመነ ትንሳኤ የነበሩ ሰዓሊያንና ቀራፂያን (ሊኦናርዶ ዳቬንቺ፣ ሚካኤል አንጀሎ፣ ራፋኤልና ሌሎችም) የሥዕልና የቅርፃ ቅርፅ ሥራዎች እውነታውን በማስመሰል ማስቀመጥ ብቻ ሳይሆን በርካታ ሥራዎቻቸው ዓለማዊነትን (Secularism) የሚያንፀባርቁ ናቸው፡፡
ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የምታዩት የመፅሐፍ ቅዱሱ የዳዊት Sculpture ይገኝበታል፡፡ ይሄ Sculpture የተሰራው ከ1501–1504 በሚካኤል አንጀሎ ነው ምስሉ በብዙ ባለሙያዎች ዘንድ ‹‹a masterpiece of Renaissance and world art›› ተብሎ ይወደሳል፡፡ ምንም እንኳ የመፅሐፍ ቅዱሱ ዳዊት የምናውቀው በመንፈሳዊነቱ ቢሆንም፣ ሚካኤል አንጀሎ ግን ጡንቻማ የግሪክ አትሌት አስመስሎ ሰርቶታል፡፡ በመካከለኛው ዘመን ቢሆን ሰው እንደዚህ ራቁቱን ሆኖ (ያውም ከነ ብልቱ) አይሳልም፣ አይቀረፅም፡፡ ‹‹ርቃን አካል ያልተገራና ያልሰለጠነ ሰው-ነት›› ተደርጎ ስለሚቆጠር በአደባባይ እንዲታይ አይደረግም፤ በጣም ነውር ነው!! በዘመነ ትንሳኤ ግን ይሄ ተጀመረ፡፡ አንዳንዶች ይሄንን ምስል የ‹‹Christian Humanism›› መገለጫ ይሉታል፡፡
ሲኦራን (ክፍል 2)  አንድን ካላየህ ተመለስ¡

የሲኦራን መፅሀፍ እና ሀሳቦች በጥልቁ ለተገነዘበ "ትንሽ" የሚለው ቃል ብቻ ሳይሆን ስር መሰረት ያለው ጽለመታዊ አመለካከት መውረሱ አይቀሬ ነው።ሲኦራን ተወልዶ እስካረፈበት እ.አ.አ 1995 ድረስ አለም ጥሩ መልክ ያልነበራት የክፋት እና ተንኮል ያደረሰውን ውድመት እና ስቃይ ማሰለፏ ለሲኦራን የህይወት ምልከታን አቅጣጫ ቀያሪ አድርጎለታል።አንደኛውም ሆነ ሁለተኛ የአለም ጦርነት ላይ ቆሞ ብርሀናማ ነገሮችን ለማሰብ አስቸጋሪ በነበረት ወቅት የእነ ሲኦራን ፍልስፍና የገሀዱ አለም እውነታ ከመሆን የዘለለ እንደነ አፍላጦም ሆነ አርስጣጣሊስ ስለsubjective አለም ማውራት ከቅንጦትም በላይ ንቀት ነበር ምክንያቱም ጊዜ የህላዌ ፍልስፍና (Existentialism) መድረክ ነበራ።

ትንሽ ፍላጎት ደግሞ አድሮብህ ፍልስፍናውን ዘለቅ ብለህ ስትገባ የሞትና የህይወት መለያ መስመሩ የት እንደሆን ይጠፋሀል።እስቲ በትንሽ ዳሰሳ ላሳይህ ተረጋጋ!


𝑜𝑛 𝑡ℎ𝑒 ℎ𝑒𝑖𝑔ℎ𝑡𝑠 𝑜𝑓 𝑑𝑒𝑠𝑝𝑎𝑖𝑟

ሲኦራን የፍልስፍና ``ዋና`` መገኛ መጣጥፉ ነው ብዬ አስባለሁ።መፅሀፉ ባለፈው እንዳልኩህ በአጫጭር ርዕሶች የተሞላ ሲሆን ከራሳችን ተነስቷ ራሳችን ላይ ያልቃል።መፅሀፉ ውስጥ በተደጋጋሚ ለመነገር የተፈለጉ መልእክቶች ብዙ ቢሆኑም ``የህይወት ፍሬ ከርሲስ``ነት ዋንኛ መዳረሻው ነው። ሲኦራን በመፅሀፉ ውስጥ እንዲህ ይላል``From a grave perspective, every step in life is a step into death and memory is only the sign of nothingness...(ጽልመታዊ እይታ አንፃር እያንዳንዱ ወደ ህይወት የሚደረግ እርምጃ አብሮ ወደ ሞት የሚመስድ እንዲሁ ትውስታዎች እንደአመድ ብናኝ የሚጠፉ ናቸው)``።

በሌላኛው የመፅሀፉ ክፍል(the Double and His Art ርዕስ ስር ማለት ነው) ላይ ደግሞ ስለ የህይወትን እውነታዎች መረዳት ላይ እንዲህ ብሏል ``The more you know, the less you want to know. He who has not suffered from knowledge has never known anything...(ብዙ ባወክ እና በተረዳህ ቁጥር፤ትንሽ መረዳት ትፈልጋለህ።በእውቀት ስቃይ ስር ካልወደክ ምንም አታውቅም ማለት ነው..) የእውቀትን ጉዳይ ካነሳን በስነህላውያን ዘንድ ብዙ ማወቅ ትርፉ ወለፈንዲ የሆነችውን ህይወት የምታቀርብልህን የክብር ስጦታ የሆነውን ሞት ይበልጥ መለማመድ ነው(Memento mori ልብ ይሏል)።ነገርን ነገር ያነሳዋል ወለፈንዲ ስል የሀሳቡ ባለቤት አልበርት ካሙ ትዝ አለኝ፤ ሲኦራን በአንድ ቃለምልልሱ ላይ በአንድ ወቅት አልበርት ካሙ ጋር ተገናኝተው በካሙ ``Absurdism`` ፍልስፍና ላይ ተጨዋውተው እንደነበር አንስቷል። የካሙን የሲሲፈስ መንገድ አዋጭ አድርጓ አያየውም(ድሮስ ሁለት ፈላስፎች ተስማምተው የት ያቁና¡)።

እንዲሁ በሌላው ርዕስ ስር ስለሰው ልጅ እንቅልፍ እጦት ሲያነሳ ``The loss of hope comes with the loss of sleep. The difference between paradise and hell: you can always sleep in paradise, never in hell. God punished man by taking away sleep and giving him knowledge....(የተስፋ እጦት ከእንቅልፍ እጦትየሚመነጭ ነው፤በገነት እና በሲኦል መካከል ያለው ልዩነት በገነት ሁሌም መተኛት  ይቻላል ነገርግን በሲኦል ውስጥ አይታሰብም።እግዚአብሔር የሰውን ልጅ እንቅልፍም ወስዶ እውቀት በመስጠት ቀጣው..)



      1.1 𝑛𝑖ℎ𝑖𝑙𝑖𝑠𝑚 (ጽልመተኝነት)

በመፅሀፉ ውስጥ ጥግ የያዘ ጽልመተኝነት ይስተዋላል።ለህይወት የሰጠው ዋጋ አነስተኛ አድርጎ እንዲሁም "ሞት" በሚለው ቃል ውስጥ የተሸከመውን እንቅስቃሴ በስጋ ለመግለጥ የቻለ አይነት ፅሁፍ ነው።``At this moment I do not believe in anything and I have no hope. All forms and expressions that give life its charm seem to me meaningless. I have no feeling either for the future or for the past, while the present seems to me poison...(በዚህ ጊዜ በምንም ነገር አላምንም እንዲሁም ምንም አይነት ተስፋ የለኝም።ለሕይወት ውበት የሚሰጡ ቅርፆች እና አገላለፆች ለእኔ ትርጉም የላቸውም፣ ለወደፊቱም ሆነ ላለፉቱ ጊዜያት ምንም አይነት ስሜት የለኝም እንደውም አሁን ያለው ጊዜ እንደመርዝ ይመስለኛል.....) በማለት ጨለምተኛ የሆነ እይታውን ይነግረናል።


      1.2 𝑘𝑛𝑜𝑤𝑙𝑒𝑑𝑔𝑒
𝑢𝑛𝑑𝑒𝑟 𝑟𝑒𝑎𝑙𝑖𝑡𝑦 𝑎𝑛𝑑 𝑐𝑜𝑛𝑐𝑠𝑖𝑜𝑢𝑠𝑛𝑒𝑠𝑠

ሌላው መፅሀፉን ስትዳስሱ(ከዚህ በፊት ዳሳችሁ ሊሆን ይችላል) በእውነታው እና በንቃተ ህሊናችን መካከል ስላለው እውቀት መፅሀፉ ይነግረናል። ሲኦራን እውቀት እንደቅጣት እንጂ እንደ ሌሎች ፈላስፎች(እንደነ ስር ፍራንሲስ ቤከን ያሉ) እውቀትን አይመለከተውም።ስለእውቀት አንድ የሚለን ነገር ቢኖር ``knowledge having irritated and stimulated our appetite for power.will lead us inexorable to our ruin...``(እውቀት እያናደደን እና ለ' ኃይል' ያለንን ፍላጎት በመቀስቀስ በማያዳግም ሁኔታ ወደ ጥፋት ይመራናል)....

ቀረ የምለው ካለ በComment section ላይ እፅፋለሁ!



ተፃፈ በይሁዳ


@Wisdom_wisdom
@Wisdom_wisdom
``ታስታውሳለህ...?

   አለም ማን መሆን እንዳለብህ  ሳትነግርህ በፊት ማን እንደነበርክ ታስታውሳለህ?.....``


  ``𝑐𝑎𝑛 𝑦𝑜𝑢 𝑟𝑒𝑚𝑒𝑚𝑏𝑒𝑟 𝑤ℎ𝑜 𝑦𝑜𝑢 𝑤ℎ𝑒𝑟𝑒 𝑏𝑒𝑓𝑜𝑟𝑒 𝑡ℎ𝑒 𝑤𝑜𝑟𝑙𝑑 𝑡𝑜𝑙𝑑 𝑦𝑜𝑢 𝑤ℎ𝑜 𝑦𝑜𝑢 𝑠ℎ𝑜𝑢𝑙𝑑 𝑏𝑒......?``


           -ቡኮቩስኪ /𝑏𝑢𝑘𝑜𝑤𝑠𝑘𝑖/