Forwarded from አርምሞ🧘🏽♂ (ሞገስ ዘአምድ Gυrυ🪽)
ሶስቱ ነብያት
|
|
1. ኒቼ 2. ካርል ዩንግ 3. ዶስቶቪስኪ
|
የነብይነት ጸጋ ነበራቸው። የኦርቶዶክስ ቤ/ክ መጸሀፎቻቸውን ደፍራ ከቅዱሳት መጸሀፍቷ ብትቀላቅል ብዙ ትጠቀማለች።
|
|
1. ኒቼ
በተቋማዊው ክርስትና ላይ የበረታ ሒስ በመሰንዘር ይታወቃል። " የመጨረሻው ክርስትያን መስቀል ላይ ሞቷል" እስከማለት የደረሰ ጭፍለቃው ስነጽሁፋዊ ግነት እንጂ literall(አማናዊ) ትርጉም አይደለም። የdetail አቅሙን ያየ ሌጣውን ትርጉም አይወስድም። ኒቼ cult ተሰርቶበታል። ፈጣሪን በአኗኗራቸው ክደውት በአንደበታቸው እግዜር አለ የሚሉት ቅዘናሞች አፍ ማስቲካ ሆኗል።
|
" እግዜር ሙቷል" የምትል ሀረጉን መዘው ፍዳውን ያሳዩታል።
እስቲ ሙሉውን.....
|
" እግዜር ሙቷል። አዎ ሞቶ ይቀራል። ደሞ እኛ ነን የገደልነው። ከግድያም ታላቁን ግድያ የፈጸምን እኛ ሰዎች ሊመቸን ኖሯል? ምድሪቱ ያላትን ቅዱስ እና ታላቁን ሀይል በቢላችን ደሙ አፍስሰናል! ይሔን ደም ከእጃችን የሚያጥብልን ማነው? የቱ ፌሽታ ካሳ ሊሆን? የቱ አስደንጋጭ ጫወታ ሊያረሳሳን? እውነት? ኤግዜር ለእኛ ካደረገልን በላይ ለራሳችን ማድረግ እንችላለን? ይሔን ለራሳችን በማድረግ አማልክት መሆን ምን ሊረባን?"
|
|
ቃል በቃል አልተረጎምኩም። ፍረዱኝስቲ ይሔ ወንጌል አይደለም ወይ? ስነጽሁፋዊ ውበቱ ከጀርመንኛ ወደ እንግሊዘኛ ሲሔድ ከእንግሊዘኛም ወደ አማርኛ ስመልሰው ተዳክሟል። "በራሳችሁ ምንም ማድረግ አትችሉም፣ ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ያጠፋታል፣ ደሙ በልጅ ልጆቻችን ይሁን" የሚሉ የመጸሀፍ ቅዱስ ንግግሮች ከላይ ባለው የኒቼ ሀተታ ካልተፈቱ ግራ ናቸው። በተሰቀለው ኢየሱስ ላይ ሰው ሁሉ አንድ ነው ባይ ነው። መሲሁ የትኛውም ዘመን ላይ ቢመጣ አገዳደሉ ይለያይ እንጂ ሟች ነው።
"እኔ ይሔን አላደርግም" ያለ ምእመን እንደ ጴጥሮስ ሊክድ የተዘጋጀ ነው።
📍 የተነሳውን ኢየሱስ በማመን/በመሆን ግን ልዩነት አለ ይላል።
ኒቸ በስልጣን እንጂ በጨዋነት አያምንም። ትንሳኤ ስልጣን ነው ይላል the will to power መጸሀፉ ላይ። እንደ መጀመሪያው ሟች አቤል ትሁት ሆኖ ሞቶ መቅረት ወይስ እንደ መጨረሻዉ ሟች ኢየሱስ እውነት ተናግሮ ሞቶ መነሳት?
|
|
2. ካርል ዩንግ
|
የሲግመን ፍሮይድ ተማሪ ነበር። ከፍሩይድ ይበረታል ይሉታል። አባቱ ፓስተር ነው። በሙሉ ስሙ ካርል ጉስታቭ ጁንግ(ዩንግ) ይባላል። ይሔም እንደ ኒቼ ጀርመናዊ ሲሆን psychiatrist, psychoanalys እና ሳይንቲስት ነው። ድርሳኖቹን ያነበበ ከ 149 አመት በፊት አለም እንዲህ አይነት ደፋር ነበራት ወይ ማለቱ አይቀርም!
|
ታዋቂ መጸሀፉ the red book ይሰኛል። ከዲያቢሎስ ጋር በመንፈሱ ተገናኝቶ የጻፈው ነው። ከዚህ ገጠመኙ ተነስቶ የግል ሰይጣናችንን መገናኘት አለብን ይላል። በባህል እና ሀይማኖት የተወገዘ ድብቅ ፍላጎታች የሚፈጥረው Shadow አለ። ስንቆጣ ልጆቻችንን እስከመግደል የደረሰ ቅጣት የሚቀጣቸው በዚህ Shadow ውስጥ የሚገለጠው ሰይጣን ነው።
" ተቆጡ በቁጣችሁ ላይ ጸሀይ አይግባ" ካለ በሗላ "ለዲያቢሎስም እድል ፈንታ አትሰጡት" ይላል። አጅሬ ሹልክ ትላለች ሲለን ነው።
|
ሴጦ እየተገለጠ ልጆቻችንን ይቆጋል፣ ወዳጆች bully ያደርጋል፤ ስራችሁን ብታጡስ እያለ ያቦካል። ለኛ አይታይም! ባለቤቱ ፍሬውን እያየ የራሴ ጠላት እራሴ ነኝ ብሎ የታገለ አንድ ቀን እንደ ዩንግ ይገናኘዋል። ክስተቱ shadow encounter ይባላል።
የኛ ሰይጣን ከዋናው ሰይጣን ይለይልናል። በውጣችን ሆኖ ማስጠቃቱን ያቆማል።
" እባብም እርግብም ሁኑ የሚለው ትዕዛዝ ይፈጸማል" ነው መደምደሚያው!
|
ኒቸ እግዜርን የገደለ ሰው እረፍት የለውም ሲል ዩንግ ተቀብሎ እግዜር በውስጡ የተነሳለትን ያሳያል። ሰው ሰይጣንን ፊት ለፊት ካገኘው በሗላ 3 stage አለው ይላል።( በቀጣይ ጽሁፍመጣበታለሁ)
|
|
3. ዶስቶቪስኪ
ሩስያዊ ነው። ከ105 አመት በፊት የተገኘ ደራሲና ጋዜጠኛ። የኒቸ literatural prophecy ደርሶበታል። ተቋማት ደግፈው ያቆሙት የስነምግባር ሰው የፈረሱበት እለት ሊሆን የሚችለውን ዶቶቪስኪ ሆኖት ጻፈው።
|
ኒቼን አምኖ በዩንግ መንገድ ያልሔደ ሰው ዶቶቪስኪን ይመስላል። የስርቻውን ሰው ይሆናል። the underground man ይለዋል።
ፍርፋሪ እና ልጆች መኖር ያስቀጥሉት የነበረው የተለመደው ሰው ከ existential (ህልውናዊ) ጥያቄዎቹ ፊት ስላልቆመ የስነ-ምግባር ሰው ይመስላል ባይ ነው።
|
ዶቶቪስኪ በስሜት ሆኖት ያሳየናል። ከ Red bookም በላይ እጅግ የምፈራው መጸሀፍ ነው። ፍርሀት እንደ አይጥ ስርቻ ለስርቻ የሚያርመጠምጠኝ ነበርኩና የሚለውን ሳነብ ያ ቦታዬ ያልዳነ ያህል ያመኛል። ልቤን ስውር እያደረገኝ ስንቴ አስቀመጥኩት?
|
በስራ እና በልጅ ላመልጣት የነበረች ክፉ ጥረት ነበረች። በሁለቱም የተሳካልኝ ሰው አይደለሁምና ህልውናዊ ጥያቄዎቼ ፈጠው አላላውስ አሉኝ። ዛሬ የተወለድኩ ያህል "ከየት መጣሁ? ወዴት ልሒድ? ማነኝ?" ምናምን አልኩ። ሰውነቴ እስር ቤት ሆኖብኝ መተንፈስ ተቸግሬአለሁ። በየአመቱ ይሔን መጸሀፍ ጀምሮ ያለመጨረስ እቅድ አለኝ። ዘንድሮም እሱ ላይ ነኝ። በጨዋታ፣ በፌ.ቡ፣ በበርጫ፣ በጨብሲ፣ በኢየሱስ፣ በወንጌል፣ በታማልዳለች አታማልድም፣ በጨላ አጫብለን የረሳነውን አማናዊ ጥያቄ እና ፍላጎታችንን ያፈጣል።
|
ሶስቱ ተባብረው የሚሉት ይሔን ነው።
" በስነ-ምግባር አታመልጡም! ለጊዜው የጸጥታ ተቋማት ከሌቦች ጋር ስላልሰሩ አትሰርቁም፤ አማኝ የመሰላችሁት የሀይማኖት ተቋማት ብሔር ስላልገባቸው ነው"
.
ባጠቃላይ
#የሰላም_ዘመን_አልፎ_የጽድቅ_ዘመን_ይመጣል እያሉን ነበር።
፦ Behailu_mulugeta
@rasnflega
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዶስቶቭስኪ እግዚአብሔር እንደሞተ ከኒቼ ሲሰማ be like..😂
ይሄ የነቢዩ ዳዊት ምስል ነው ብትባሉ ምን ያህል ታምናላችሁ?
ዘመነ ትንሳኤ የ‹‹እውናዊነት (Realism)›› ፍልስፍና ያቆጠቆጠበት ወቅት ነው፡፡ ‹‹እውናዊነት (Realism)›› ማለት ከቢሆንና ከምናብ ዓለም ወጥቶ በምድር ላይ ያለውን እውነታ እንዳለ ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡ የ‹‹እውናዊነት (Realism)›› ፍልስፍና በነሚካኤል አንጀሎ አርትና በማኪያቬሊ የፖለቲካ ፍልስፍና ውስጥ ተንፀባርቋል፡፡
በዘመነ ትንሳኤ የነበሩ ሰዓሊያንና ቀራፂያን (ሊኦናርዶ ዳቬንቺ፣ ሚካኤል አንጀሎ፣ ራፋኤልና ሌሎችም) የሥዕልና የቅርፃ ቅርፅ ሥራዎች እውነታውን በማስመሰል ማስቀመጥ ብቻ ሳይሆን በርካታ ሥራዎቻቸው ዓለማዊነትን (Secularism) የሚያንፀባርቁ ናቸው፡፡
ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የምታዩት የመፅሐፍ ቅዱሱ የዳዊት Sculpture ይገኝበታል፡፡ ይሄ Sculpture የተሰራው ከ1501–1504 በሚካኤል አንጀሎ ነው ምስሉ በብዙ ባለሙያዎች ዘንድ ‹‹a masterpiece of Renaissance and world art›› ተብሎ ይወደሳል፡፡ ምንም እንኳ የመፅሐፍ ቅዱሱ ዳዊት የምናውቀው በመንፈሳዊነቱ ቢሆንም፣ ሚካኤል አንጀሎ ግን ጡንቻማ የግሪክ አትሌት አስመስሎ ሰርቶታል፡፡ በመካከለኛው ዘመን ቢሆን ሰው እንደዚህ ራቁቱን ሆኖ (ያውም ከነ ብልቱ) አይሳልም፣ አይቀረፅም፡፡ ‹‹ርቃን አካል ያልተገራና ያልሰለጠነ ሰው-ነት›› ተደርጎ ስለሚቆጠር በአደባባይ እንዲታይ አይደረግም፤ በጣም ነውር ነው!! በዘመነ ትንሳኤ ግን ይሄ ተጀመረ፡፡ አንዳንዶች ይሄንን ምስል የ‹‹Christian Humanism›› መገለጫ ይሉታል፡፡

ሲኦራን (ክፍል 2) አንድን ካላየህ ተመለስ¡
የሲኦራን መፅሀፍ እና ሀሳቦች በጥልቁ ለተገነዘበ "ትንሽ" የሚለው ቃል ብቻ ሳይሆን ስር መሰረት ያለው ጽለመታዊ አመለካከት መውረሱ አይቀሬ ነው።ሲኦራን ተወልዶ እስካረፈበት እ.አ.አ 1995 ድረስ አለም ጥሩ መልክ ያልነበራት የክፋት እና ተንኮል ያደረሰውን ውድመት እና ስቃይ ማሰለፏ ለሲኦራን የህይወት ምልከታን አቅጣጫ ቀያሪ አድርጎለታል።አንደኛውም ሆነ ሁለተኛ የአለም ጦርነት ላይ ቆሞ ብርሀናማ ነገሮችን ለማሰብ አስቸጋሪ በነበረት ወቅት የእነ ሲኦራን ፍልስፍና የገሀዱ አለም እውነታ ከመሆን የዘለለ እንደነ አፍላጦም ሆነ አርስጣጣሊስ ስለsubjective አለም ማውራት ከቅንጦትም በላይ ንቀት ነበር ምክንያቱም ጊዜ የህላዌ ፍልስፍና (Existentialism) መድረክ ነበራ።
ትንሽ ፍላጎት ደግሞ አድሮብህ ፍልስፍናውን ዘለቅ ብለህ ስትገባ የሞትና የህይወት መለያ መስመሩ የት እንደሆን ይጠፋሀል።እስቲ በትንሽ ዳሰሳ ላሳይህ ተረጋጋ!
𝑜𝑛 𝑡ℎ𝑒 ℎ𝑒𝑖𝑔ℎ𝑡𝑠 𝑜𝑓 𝑑𝑒𝑠𝑝𝑎𝑖𝑟
ሲኦራን የፍልስፍና ``ዋና`` መገኛ መጣጥፉ ነው ብዬ አስባለሁ።መፅሀፉ ባለፈው እንዳልኩህ በአጫጭር ርዕሶች የተሞላ ሲሆን ከራሳችን ተነስቷ ራሳችን ላይ ያልቃል።መፅሀፉ ውስጥ በተደጋጋሚ ለመነገር የተፈለጉ መልእክቶች ብዙ ቢሆኑም ``የህይወት ፍሬ ከርሲስ``ነት ዋንኛ መዳረሻው ነው። ሲኦራን በመፅሀፉ ውስጥ እንዲህ ይላል``From a grave perspective, every step in life is a step into death and memory is only the sign of nothingness...(ጽልመታዊ እይታ አንፃር እያንዳንዱ ወደ ህይወት የሚደረግ እርምጃ አብሮ ወደ ሞት የሚመስድ እንዲሁ ትውስታዎች እንደአመድ ብናኝ የሚጠፉ ናቸው)``።
በሌላኛው የመፅሀፉ ክፍል(the Double and His Art ርዕስ ስር ማለት ነው) ላይ ደግሞ ስለ የህይወትን እውነታዎች መረዳት ላይ እንዲህ ብሏል ``The more you know, the less you want to know. He who has not suffered from knowledge has never known anything...(ብዙ ባወክ እና በተረዳህ ቁጥር፤ትንሽ መረዳት ትፈልጋለህ።በእውቀት ስቃይ ስር ካልወደክ ምንም አታውቅም ማለት ነው..) የእውቀትን ጉዳይ ካነሳን በስነህላውያን ዘንድ ብዙ ማወቅ ትርፉ ወለፈንዲ የሆነችውን ህይወት የምታቀርብልህን የክብር ስጦታ የሆነውን ሞት ይበልጥ መለማመድ ነው(Memento mori ልብ ይሏል)።ነገርን ነገር ያነሳዋል ወለፈንዲ ስል የሀሳቡ ባለቤት አልበርት ካሙ ትዝ አለኝ፤ ሲኦራን በአንድ ቃለምልልሱ ላይ በአንድ ወቅት አልበርት ካሙ ጋር ተገናኝተው በካሙ ``Absurdism`` ፍልስፍና ላይ ተጨዋውተው እንደነበር አንስቷል። የካሙን የሲሲፈስ መንገድ አዋጭ አድርጓ አያየውም(ድሮስ ሁለት ፈላስፎች ተስማምተው የት ያቁና¡)።
እንዲሁ በሌላው ርዕስ ስር ስለሰው ልጅ እንቅልፍ እጦት ሲያነሳ ``The loss of hope comes with the loss of sleep. The difference between paradise and hell: you can always sleep in paradise, never in hell. God punished man by taking away sleep and giving him knowledge....(የተስፋ እጦት ከእንቅልፍ እጦትየሚመነጭ ነው፤በገነት እና በሲኦል መካከል ያለው ልዩነት በገነት ሁሌም መተኛት ይቻላል ነገርግን በሲኦል ውስጥ አይታሰብም።እግዚአብሔር የሰውን ልጅ እንቅልፍም ወስዶ እውቀት በመስጠት ቀጣው..)
1.1 𝑛𝑖ℎ𝑖𝑙𝑖𝑠𝑚 (ጽልመተኝነት)
በመፅሀፉ ውስጥ ጥግ የያዘ ጽልመተኝነት ይስተዋላል።ለህይወት የሰጠው ዋጋ አነስተኛ አድርጎ እንዲሁም "ሞት" በሚለው ቃል ውስጥ የተሸከመውን እንቅስቃሴ በስጋ ለመግለጥ የቻለ አይነት ፅሁፍ ነው።``At this moment I do not believe in anything and I have no hope. All forms and expressions that give life its charm seem to me meaningless. I have no feeling either for the future or for the past, while the present seems to me poison...(በዚህ ጊዜ በምንም ነገር አላምንም እንዲሁም ምንም አይነት ተስፋ የለኝም።ለሕይወት ውበት የሚሰጡ ቅርፆች እና አገላለፆች ለእኔ ትርጉም የላቸውም፣ ለወደፊቱም ሆነ ላለፉቱ ጊዜያት ምንም አይነት ስሜት የለኝም እንደውም አሁን ያለው ጊዜ እንደመርዝ ይመስለኛል.....) በማለት ጨለምተኛ የሆነ እይታውን ይነግረናል።
1.2 𝑘𝑛𝑜𝑤𝑙𝑒𝑑𝑔𝑒
𝑢𝑛𝑑𝑒𝑟 𝑟𝑒𝑎𝑙𝑖𝑡𝑦 𝑎𝑛𝑑 𝑐𝑜𝑛𝑐𝑠𝑖𝑜𝑢𝑠𝑛𝑒𝑠𝑠
ሌላው መፅሀፉን ስትዳስሱ(ከዚህ በፊት ዳሳችሁ ሊሆን ይችላል) በእውነታው እና በንቃተ ህሊናችን መካከል ስላለው እውቀት መፅሀፉ ይነግረናል። ሲኦራን እውቀት እንደቅጣት እንጂ እንደ ሌሎች ፈላስፎች(እንደነ ስር ፍራንሲስ ቤከን ያሉ) እውቀትን አይመለከተውም።ስለእውቀት አንድ የሚለን ነገር ቢኖር ``knowledge having irritated and stimulated our appetite for power.will lead us inexorable to our ruin...``(እውቀት እያናደደን እና ለ' ኃይል' ያለንን ፍላጎት በመቀስቀስ በማያዳግም ሁኔታ ወደ ጥፋት ይመራናል)....
ቀረ የምለው ካለ በComment section ላይ እፅፋለሁ!
ተፃፈ በይሁዳ
@Wisdom_wisdom

ፍልስፍና
``. . . . . . . . . . . ብንሄድ ይሻለናል . . ``
ዝም ብዬ አላነሳኋትም ጎበዝ!
`` ብንሄድ ይሻለናል [እነ ሾፐን ሀወር፣ዶስቶቭስኪ ሲኦራን፣ኪርጋርድ ጎራ]``
እና
``ባንሄድም ይሻለናል[እነ አልበርት ካሙ፣ ኢማኑኤል ካንት፣ጆን ስታር ሚል፣``
እንዲሁም ደግሞ
``መቆየትም ሆነ መሄድ ለውጥ አያመጣም [ኒቼ. . . . .]?``
በቀደሙት ፖስቶች ስለእነዚህ ሰዎች አንስተናል።ደጋሚ የመኖርን ትርጉም መቃኘት አስፈላጊ መስሎ አይታየኝም ከተነሳን አይቀር ግን የቱን ትቀበላላችሁ¿ ¿

የሰው ልጅ እና የውጪው አለም ተግባቦት . . .
𝑐𝑜𝑚𝑚𝑢𝑛𝑖𝑐𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛 𝑏𝑒𝑡𝑤𝑒𝑒𝑛 𝑚𝑎𝑛𝑘𝑖𝑛𝑑 𝑎𝑛𝑑 𝑡ℎ𝑒 𝑜𝑢𝑡𝑠𝑖𝑑𝑒 𝑤𝑜𝑟𝑙𝑑 . . . . .
አስገርሞህ አያውቅም(¿) በሰውልጅ (በነጠላው ``አእምሮ``) እና በውጪው አለም ያለው ትስስር፣በነገሮች እና በውጤቶቻቸው እንዲሁም በስሜት እና በተግባራቶቻችን . . . .እነዚህ የጥርጣሬ በሽታዎች ናቸው ዴካርትን ለዚህ ያደረሱት ለዘመናዊው ፍልስፍና፤ በእርግጥ በዚህ ሀተታሄ ከዴካርት አልጀምርም የትንታኔው ይዘት 𝑏𝑎𝑠𝑒𝑑 𝑜𝑛 𝑚𝑎𝑡𝑒𝑟𝑖𝑎𝑙𝑖𝑠𝑡𝑖𝑐 𝑏𝑟𝑖𝑡𝑖𝑠ℎ 𝑒𝑚𝑝𝑖𝑟𝑖𝑐𝑖𝑠𝑚 𝑎𝑛𝑑 𝑟𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛𝑎𝑙𝑖𝑠𝑚 𝑣𝑖𝑒𝑤 𝑜𝑓 𝑝𝑜𝑖𝑛𝑡 አስፈላጊነቱ እየታየ አንዳንድ s𝑐𝑖𝑒𝑛𝑡𝑖𝑓𝑖𝑐 𝑟𝑒𝑠𝑒𝑎𝑟𝑐ℎ የምናይ ይሆናል።
እኛና የውጪው አለም? . . . . ¿
``ሰው`` እና የ``ውጫዊው አለም``ጥያቄ በፍልስፍናው ዘርፍ አንድ ክፍል ተሰቶት እስኪብራራ እና ትንተና እስኪያገኝ ድረስ በደረቁ ከተቀመጡ የሀሳብ ባህር ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ ነው ማለት እንችላለን።በቅድመ-ሶቅራጠስ ዘመን( 𝑝𝑟𝑒-𝑠𝑜𝑐𝑟𝑎𝑡𝑖𝑐 𝑒𝑟𝑎) በፊት እንኳን ይሄንን ጥያቄ በእነታለስ ኋላም በእነአናክሲማነስ እና አናክሲማንደር ቀጥሎም በአንድ አንድ የህንድ ፈላስፎች ዘንድ ትኩረት ተሰጥቶ እንደውም አለፍ ብሎ ፍልስፍና የሚያጠናው ይሄንኑ ዘርፍ እስኪመስል ድረስ የሙጥኝ ተብሎ ነበር።
ታድያ መቼ ተንገዳገደ(ወይም ተተወ?)?መልሱ የሚሆነ የአባ ሶቅራጠስ መወለድ ወይም ክስተት በለው ብቻ የዚህ ሰው ``ሰው ተኮር`` ፍልስፍናን ማንፀባረቅ ነው፤ለእነዚህ አይነት ህልውና ተኮር ጥያቄ መቀዛቀዝ መንስኤ የሚሆነው።ወደ ሌሎቹ ሀገራት ብትዞር ደግሞ እየተለዋወጠ ያለ የፍልስፍና አቅጣጫ ይታይሀል ወደ ራስ የዞረ ፍልስፍና፣ወደ ውስጥ ብቻ የሚታዩ አለማት፣ ውጪውን ከመጠን ያለፈ አካል የማድረግ አባዜ እየበዛ የነበረበት ወቅት ነው ልክ Enlightenment መግቢያ ሰሞን ሀይማኖትን በዋዜማው መገዳደር እና ሂስ ስር መክተት አይነት ነገር . . . .
𝑒𝑝𝑖𝑠𝑡𝑒𝑚𝑜𝑙𝑜𝑔𝑦
እነዚህ ጥያቄዎች ስናነሳ በዋናነት ጥያቄው ትኩረቱን የሚያደርገው እውቀት ``𝑘𝑛𝑜𝑤𝑙𝑒𝑑𝑒𝑔𝑒`` እንዲሁም በስሜት ህዋሳት መገንዘብ ``𝑝𝑒𝑟𝑐𝑒𝑝𝑡𝑖𝑜𝑛`` ላይ ይወድቃሉ ለዚህም ነው ነገሩ 𝑒𝑝𝑖𝑠𝑡𝑒𝑚𝑜𝑙𝑜𝑔𝑖𝑐𝑎𝑙 የሆነው ማለትም በመጀመሪያ ውጫዊውን አለም ለማወቅ ወይም ለመረዳት በእጃችን ላይ ያለውን መሳሪያ እውቀት የተባለው ነገር መፍተሽ እንዲሁም መተያት ይገባዋል ማለት ነው።
𝑏𝑟𝑖𝑡𝑖𝑠ℎ 𝑒𝑚𝑝𝑖𝑟𝑖𝑐𝑖𝑠𝑚
እነኚ ጎራዎች እንደሚፈርዱ እና ፍልስፍናዊ አመለካከታችው ለማስረዳት የሚሞክሩት ``𝑝𝑒𝑟𝑐𝑒𝑝𝑡𝑖𝑜𝑛`` ላይ ተንተርሰው ነው። ምን ማለት መሰለህ! ``በመጀመሪያ እውቀት የምንለውን ነገር የምንገነባው በ
𝑟𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛𝑎𝑙𝑖𝑠𝑚
እነዚህኛዎቹ ደግሞ የ𝑒𝑚𝑝𝑖𝑟𝑖𝑐𝑖𝑠𝑚 ተቃራኒዎች ሲሆን ``እውቀት የምንለው ነገር የምናገኘው በምርምር እንዲሁም በምክንያታዊ ሀሳቦች ብቻ ሲሆን እነዚህን በሎጂካዊ መንገድ በመገንባት ስለውጫዊው አለም መመልከቻ መነፅር ማድረግ እንችላለን`` በሚለው ሀሳብ ላይ መሰረታቸው ይጥላሉ።
𝑚𝑎𝑡𝑒𝑟𝑖𝑎𝑙𝑖𝑠𝑚
በዚህ የሀሳብ ቤት በፍቅር የወደቁት ደግሞ ከ ``ቁስ ወይም 𝑚𝑎𝑡𝑡𝑒𝑟``ሲሆን ``እውቀት እንዲሁም የተለያዩ ሀሳቦች በተጨማሪም ደግሞ የማሰብ መንገዶች የሚመነጩት በውጫዊው አካል ነው ማለትም ከሰዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት ውስጥ ሰዎች ከ
𝑚𝑒𝑡𝑎𝑝ℎ𝑦𝑠𝑖𝑐𝑠
ይሄንን ጥያቄ ከ``እውቀት`` ተነስተን ወደ ሜታፊዚክካል ጥያቄ ሊሄድ የሚችል ነው ነገርግን ልብ ልንል የሚገባው ነገር ቀደም ብለን ባነሳናቸው የእውቀት ፍቺ አወቃቀሮች ላይ ጥገኛ እንደሚሆን ነው።
𝑒𝑥𝑖𝑠𝑡𝑒𝑛𝑐𝑒 (ህልውና) የምንለው እውነታ ወይም ደግሞ ያለ ነገርን ነው።
𝑐𝑜𝑛𝑠𝑐𝑖𝑜𝑢𝑠𝑛𝑒𝑠𝑠 (ንቃተ-ህሊና) ደግሞ ያሉትን ነገሮች የሚረዳ ወይም የሚያውቅ አካል ነው። ``I think therefore I am`` የሚትለው የዴካርት አባባል የተነሳችው ከዚህ ነው ምክንያቱም አእምሮህን እየተጠቀምክ አእምሮ እንደሌለህ ሎጂካሊ ልታረጋግጥ ስለማትችል።
𝑒𝑥𝑖𝑠𝑡𝑒𝑛𝑐𝑒 & 𝑐𝑜𝑛𝑠𝑐𝑖𝑜𝑢𝑠𝑛𝑒𝑠𝑠
ነገሮች ያለ አእምሮ የሚኖሩ ከሆነ ማለትም ``𝑏𝑒𝑖𝑛𝑔 𝑖𝑛 𝑖𝑡𝑠𝑒𝑙𝑓 ``ከሆኑ እና ንቃተ ህሊናችንን ያንን ሊረዳ የሚቻለው አካል ከሆነ ነገሮች በ ``መረዳት`` መስመር ላይ ይቀራሉ ማለት ነው።ይሄ ከሆነ ደግሞ 𝑐𝑜𝑛𝑠𝑐𝑖𝑜𝑢𝑠𝑛𝑒𝑠𝑠 በራሱ እውነታን ሊፈጥር አይችልም ማለት ነው!። ዴካርት ራሱ ይሄንን ነገር ጥርት አላደረገውም (ለምን እንደሆነ እንጃ!)።ንቃተ ህሊና እውነታን እፈጠረ የራሳችንን ሀሳብ እና አመለካከቶች እንዲሁም ህልሞች በቀድሞ ልምድ ላይ በመመርኮዝ የራሱን እውነታ እንደሚፈጥር የሳይንስ የምርምር ውጤቶች ** ያሳያሉ።
𝑎𝑏𝑠𝑡𝑟𝑎𝑐𝑡 𝑜𝑏𝑗𝑒𝑐𝑡𝑠 &𝑚𝑎𝑡ℎ𝑒𝑚𝑎𝑡𝑖𝑐𝑠
አንዳንድ ፈላስፎች ረቂቅ የሆነ አካላት(ለምሳሌ እንደ ቁጥሮች፣ሒሳባዊ መፍትሄዎች እንዲሁም ልቦለዳዊ አካል) እና ዩለንተናዊ(ለብዙሃኑ መገለፃነት የሚውሉ ለምሳሌ እንደ ሰው-ነት ወይም ፈረስ-ነት የመሳሰሉ . . . .) አሉ ብለው ያስባሉ።
°𝑟𝑒𝑎𝑙𝑖𝑠𝑚
በአፍላጦ እንዲሁም በስራዎቹ ውስጥ የተነፀባረቀች ሀሳብ ስትሆን ``የሚታየው እና የማይታየው`` ወይም ደግሞ ``የሚዳሰሰው እና የማይዳሰሰው አለም`` በማለት ይከፍለዋል። ይሄንን አለም(የሚታየውን አለም ማለት ነው) እንደ ጥላ ሲሆን "እውነተኛ" የሚለው አለም ደግሞ የማይታየው(የማይዳሰሰው) አለም ነው። ይሄንን ለማብራራት ነው እንግዲህ ታዋቂው ፅንሰሀሳቡን የሚያመጣት The theory of Form።
__
*https://www.news-medical.net/health/How-is-Reality-Constructed-in-the-Brain.aspx#:~:text=In%20A%20Nutshell%2C%20Our%20Brain%20Models%20The%20World%20for%20Us&text=Through%20something%20as%20simple%20as,reality%20as%20we%20know%20it
. . . . . . . . .. . ይቀጥላል . . . . . . .

𝑠𝑒𝑛𝑠𝑒 𝑜𝑓 𝑒𝑥𝑝𝑒𝑟𝑖𝑒𝑛𝑐𝑒
ወይም ስሜቶቻንን ባገኙት ልምድ
ላይ ተመስርተን ነው፤ በመሆኑም የሰው ልጅ በመጀመሪያ የሚያገኘው እውቀት በራሱ የተገኘው በምክንያታዊ ፈተና እና ስር መሰረት ባለ ምርምር ሳይሆን ልምድ ተኮር በሆነ ስሜት ውስጥ ነው`` የሚለውን አጥብቀው ይደግፋሉ።𝑟𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛𝑎𝑙𝑖𝑠𝑚
እነዚህኛዎቹ ደግሞ የ𝑒𝑚𝑝𝑖𝑟𝑖𝑐𝑖𝑠𝑚 ተቃራኒዎች ሲሆን ``እውቀት የምንለው ነገር የምናገኘው በምርምር እንዲሁም በምክንያታዊ ሀሳቦች ብቻ ሲሆን እነዚህን በሎጂካዊ መንገድ በመገንባት ስለውጫዊው አለም መመልከቻ መነፅር ማድረግ እንችላለን`` በሚለው ሀሳብ ላይ መሰረታቸው ይጥላሉ።
𝑚𝑎𝑡𝑒𝑟𝑖𝑎𝑙𝑖𝑠𝑚
በዚህ የሀሳብ ቤት በፍቅር የወደቁት ደግሞ ከ ``ቁስ ወይም 𝑚𝑎𝑡𝑡𝑒𝑟``ሲሆን ``እውቀት እንዲሁም የተለያዩ ሀሳቦች በተጨማሪም ደግሞ የማሰብ መንገዶች የሚመነጩት በውጫዊው አካል ነው ማለትም ከሰዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት ውስጥ ሰዎች ከ
ቁሶች
ጋር በሚኖረው ግንኙት ውስጥ ነው`` በማለት ሀሳባቸውን ይገልፃሉ።𝑚𝑒𝑡𝑎𝑝ℎ𝑦𝑠𝑖𝑐𝑠
ይሄንን ጥያቄ ከ``እውቀት`` ተነስተን ወደ ሜታፊዚክካል ጥያቄ ሊሄድ የሚችል ነው ነገርግን ልብ ልንል የሚገባው ነገር ቀደም ብለን ባነሳናቸው የእውቀት ፍቺ አወቃቀሮች ላይ ጥገኛ እንደሚሆን ነው።
𝑒𝑥𝑖𝑠𝑡𝑒𝑛𝑐𝑒 (ህልውና) የምንለው እውነታ ወይም ደግሞ ያለ ነገርን ነው።
𝑐𝑜𝑛𝑠𝑐𝑖𝑜𝑢𝑠𝑛𝑒𝑠𝑠 (ንቃተ-ህሊና) ደግሞ ያሉትን ነገሮች የሚረዳ ወይም የሚያውቅ አካል ነው። ``I think therefore I am`` የሚትለው የዴካርት አባባል የተነሳችው ከዚህ ነው ምክንያቱም አእምሮህን እየተጠቀምክ አእምሮ እንደሌለህ ሎጂካሊ ልታረጋግጥ ስለማትችል።
𝑒𝑥𝑖𝑠𝑡𝑒𝑛𝑐𝑒 & 𝑐𝑜𝑛𝑠𝑐𝑖𝑜𝑢𝑠𝑛𝑒𝑠𝑠
ነገሮች ያለ አእምሮ የሚኖሩ ከሆነ ማለትም ``𝑏𝑒𝑖𝑛𝑔 𝑖𝑛 𝑖𝑡𝑠𝑒𝑙𝑓 ``ከሆኑ እና ንቃተ ህሊናችንን ያንን ሊረዳ የሚቻለው አካል ከሆነ ነገሮች በ ``መረዳት`` መስመር ላይ ይቀራሉ ማለት ነው።ይሄ ከሆነ ደግሞ 𝑐𝑜𝑛𝑠𝑐𝑖𝑜𝑢𝑠𝑛𝑒𝑠𝑠 በራሱ እውነታን ሊፈጥር አይችልም ማለት ነው!። ዴካርት ራሱ ይሄንን ነገር ጥርት አላደረገውም (ለምን እንደሆነ እንጃ!)።ንቃተ ህሊና እውነታን እፈጠረ የራሳችንን ሀሳብ እና አመለካከቶች እንዲሁም ህልሞች በቀድሞ ልምድ ላይ በመመርኮዝ የራሱን እውነታ እንደሚፈጥር የሳይንስ የምርምር ውጤቶች ** ያሳያሉ።
𝑎𝑏𝑠𝑡𝑟𝑎𝑐𝑡 𝑜𝑏𝑗𝑒𝑐𝑡𝑠 &𝑚𝑎𝑡ℎ𝑒𝑚𝑎𝑡𝑖𝑐𝑠
አንዳንድ ፈላስፎች ረቂቅ የሆነ አካላት(ለምሳሌ እንደ ቁጥሮች፣ሒሳባዊ መፍትሄዎች እንዲሁም ልቦለዳዊ አካል) እና ዩለንተናዊ(ለብዙሃኑ መገለፃነት የሚውሉ ለምሳሌ እንደ ሰው-ነት ወይም ፈረስ-ነት የመሳሰሉ . . . .) አሉ ብለው ያስባሉ።
°𝑟𝑒𝑎𝑙𝑖𝑠𝑚
በአፍላጦ እንዲሁም በስራዎቹ ውስጥ የተነፀባረቀች ሀሳብ ስትሆን ``የሚታየው እና የማይታየው`` ወይም ደግሞ ``የሚዳሰሰው እና የማይዳሰሰው አለም`` በማለት ይከፍለዋል። ይሄንን አለም(የሚታየውን አለም ማለት ነው) እንደ ጥላ ሲሆን "እውነተኛ" የሚለው አለም ደግሞ የማይታየው(የማይዳሰሰው) አለም ነው። ይሄንን ለማብራራት ነው እንግዲህ ታዋቂው ፅንሰሀሳቡን የሚያመጣት The theory of Form።
__
*https://www.news-medical.net/health/How-is-Reality-Constructed-in-the-Brain.aspx#:~:text=In%20A%20Nutshell%2C%20Our%20Brain%20Models%20The%20World%20for%20Us&text=Through%20something%20as%20simple%20as,reality%20as%20we%20know%20it
. . . . . . . . .. . ይቀጥላል . . . . . . .
ተፃፈ በይሁዳ
@Wisdom_wisdom
News-Medical.net
How is Reality Constructed in the Brain?
How the brain allows us to see an animal, know what the animal is, where it is in relation to us, and what it looks like in comparison to other things in our world is a phenomenon that is confusing to many.
ፍልስፍና
Photo
°°
-ህይወትን መፈልሰፍ የሚፈልግ ሰው
-
-ደስተኛ መሆን የሚፈልግ ማንኛውም ሰው #ሃንዳዛኪ ማንበብ አለበት፤
-አለምን ለመበቀል የሚፈልግ #አል_ማጉትን ማንበብ አለበት፤
-
መዝፈን የሚፈልግ #ዳርዊሽን ይስማ፤
-ከሕልውና ጋር የሚበጣበጥ #ማርኬዝን ማንበብ አለበት፤
-ህልም ማየት የሚፈልግ ሰው #ኢዛቤል_አሌን ያንብብ፤
-መውደድ የሚፈልግ ሁሉ #ኔሩዳን ማንበብ አለበት።
-ለብቸኝነቱ ሰዎችን የተራበ #ዶስቶቭስኪን ማንበብ አለበት፤
-ደስ የሚል ስሜትን የፈለገ #አዚዝ_ናሲን ያንብብ፤
-እብደትን የሚሻ #ካፍካን ማንበብ አለበት፤
-ሁሉም ነገር የስቃይ ምንጭ እንደሆነ ለማወቅ የሚፈልግ #ሾፐንሃወርን ያንብብ፤
-ራሱን ማጥፋት የሚፈልግ #ራምቦን ማንበብ አለበት፤
-ቁጥርን ማወቅ የፈለገ #ፓይታጎረስን ያንብብ፤
-አለምን ማግኘት የሚፈልግ ሰው #ጋሊኖን ያንብብ፤
-እውነተኛ ነቀፋን የፈለገ #ማርክ_ትዌንን ያንብብ፤
-መማር የሚፈልግ #ታራቢሺን ያንብብ፤
-በዱር መሄድ የሚፈልግ ሁሉ #ሄንሪ ሚለርን ማንበብ አለበት፤
-በረሃውን ለማወቅ የሚፈልግ #ሙኒፍን ማንበብ አለበት።
-በመርከብ መጓዝ የሚፈልግ ሰው #ኮንራድን ያንብብ።
-ህማዊነትህ ከዚህ ዓለም እንዲነጥለው የሚፈልግ #ሲሆራንን ግለጥ፤
-ምድርን መውደድ መማር የሚፈልግ ሰው #ጋምዛቶቭን ያንብብ፤
-የአጻጻፍን መሰሪነት ለማወቅ የሚፈልግ #መሐመድ_አል_አሊን ማንበብ አለበት።
-ስለ ቋንቋው መማር የሚፈልግ #ሳሊም_ባራካትን ማንበብ አለበት።
-ህይወትን መፈልሰፍ የሚፈልግ ሰው
#ሄሚንግዌይን ያንብብ፤
-መቃወም የሚፈልግ #ቾምስኪን ያንብብ፤
-እምቢ ለማለት የሚፈልግ ሁሉ #ኒቼን ያንብብ፤
-ለህይወት ትክክለኛ ጥያቄዋን መጠየቅ የሚሻ #አልበርት_ካሙ ማንበብ አለበት፤
-
ስለ ሕይወት የበለጠ ለማወቅ የሚፈልግ #ዣን_ሄቨን ያንብብ፤
-መጨናነቅ የሚፈልግ #አንቶኒዮ_ስካርሜትታን ያንብብ።
-ልጅነቱን ማየት የሚፈልግ አዳም_ረታን ያንብብ፤
-ሙሉ በሙሉ ማበድ የፈለገ #ዲዮጋንን ያንብብ፤
Silence as presence
ከእግዜር ጋር ንግግር
(ያዕቆብ ብርሃኑ)
*
… እንደ አንዳች ሞትና መቃብር ጠርዝ ላይ ያመላልሰኛል፡፡ በጩኸታሟ አዲስ አበባ መሃልአብዛኛውን የጽሞና ሀሰሳ ሰዓቴን የማሳልፈው በፈራረሱ የመቃብር ቅጥሮች ውስጥ ነው፡፡ በየሳምንቱ የማነባቸው the economist እና the new York times ጋዜጣና መጽሔቶች ላይ እንኳን ቀድሜ የማነበው obituary (ዜና ዕረፍት) አምዳቸውን ሆኗል፡፡
ጊዜው ትንሽ ቆይቷል፡፡ ከአራት ወራት በፊት ከDecember 22- January 4 2019 የሚሸፍነው የthe economist መጽሔት double issue ዕትም ዜና ዕረፍት አምድ ላይ Silence as presence በሚል ርዕስ ስር ስለመነኩሴው ቶማስ ኬቲንግ ሕልፈት የተጻፈውን አነበበኩ፡፡ ካፒታሊዝምና ፍትወት በሚያቅነዘንዘው ልቅ ዓለም እንደ ኢየሱስና እንደ ጋንዲ ባለ ከፍያለ ልዕለ ሰብዕና ዝምታን የሕይወት መመሪያቸው አድርገው ለ95 ዓመታት ኖረው ስላለፉት ታላቅ ሰው፤ ለ95 ዓመታት በመኖሪያ ክፍላቸው ውስጥ ከአንዲት አልጋ፣ ከመጻፊያና ማንበቢያ ጠረጼዛና ወንበር በስተቀር ምንም ስላልነበራቸው መናኝ… እንደ ጋንዲ ለንቋሳ ገጽታን የተላበሱ፣ ግን ደግሞ ትንሽ ገዘፍ ያሉ፣ ረጅም፣ ራሰ በራ፣ በሚያስተዳድሩት ገዳም የሕይወት ዜይቤያቸውን ለሚሹ ፅሞናን በጸጥታ ከማስተማሩ መልስ በገዳሙ አንድ ጥግ ተቀምጠው ሞትን በመናፈቅ (longing to death) ዘመናቸውን በሙሉ የኖሩ ግዙፍ ስብዕና…
የእኒህ ሰው የሕይወት ዘመን ፍላጎት አንድ ብቻ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር… ይህንን ማድረግ የሚቻለው በጽሞና ብቻ ነው ብለው በማመናቸው ሌሎችም ከዕለትተለት ሩጫቸው በምትተርፋቸው ጊዜ ማድረግ እንዲችሉ ሲጥሩ አሳልፈዋል፡፡
እኒህ ሰው ከበመካከለኛው ዘመን በእስፓኝ ከኖሩት st. John the cross የተዋሱትና አሻሽለው መታወቂያቸው ያደረጉት ግሩም አባባል አላቸው፡፡
‹‹God's first language was silence.›› st. John the cross
‹‹everything else is bad translation.›› Thomas Keating
‹‹Including holy manuscripts.›› እኔ
እኔም አልኩ… ስታወሩ ስሜታችሁን ዝም ስትሉ ግን ነፍሳችሁን ማንበብ እችላለሁ፡፡ ዝም ማለት የቻለ እርሱ አሁንን ብቻ ሳይሆን ዘለዓለምን ማዘዝ ይችላል፡፡ ዝም ማለት የቻለ እርሱ ከአምላኩ ጋር እንኳን ባይሆን ከራሱ ጋር በተግባቦት ማውራት ይችላል፡፡ ግጥም ምንም አይልም፡፡ ስዕል ጥሩ ነገር ነው፡፡ ድርሰት በጣም ጥሩ ነገር ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሙዚቃም እጅግ በጣም ጥሩ ነገር መሆን አለበት፡፡ እነዚህ ሁሉ ግን ስንኩል የዝምታ ገጽታዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ በላይ ዝምታ ይበልጣል፡፡ ዝም ማለት፣ ፀጥታ(የሚረብሽ ድምጽ አለመኖር) ሁሉ ዝምታ ሊሆን አይችልም፡፡ ዝምታ(ጽሞና) ረቂቅ ነገር ነው፡፡
የሆነን ነገር፣ መውደድህንም ቢሆን እንዴትም ብትገልጸው በተናገርከው ቅጽበት ወዲያው ትርጉሙን አዛብተኸዋል፡፡ ዋጋውን ቀንሰኸዋል፡፡ ለ misunderstanding ግዙፍ በር ከፍተሃል፡፡ ከቻልክ በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ምንም አትበል፡፡ በጣም ውድ የሆነውን ነገር በዝምታና በተግባር ልትገልፀው ሞክር፡፡ እኔ እንኳን ይህችን ሹክ ልልህ ጽሁፉን ካነበብኩበት ከፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ጀምሮ ራሴን ማሳመን ተስኖኝ ይሄው ሳመነታ ነበር፡፡
በቅርቡ ከmay 4- may 10 በሸፈነው በዚሁ የthe economist ዕትም ethics and evolution በሚል ርዕስ ስር ባነበብኩት አንድ ጥናት መሰረት ባለፉት 30,000 ዓመታት ሂደት የሰው ልጅ ጭካኔ(cruelity) እና እንስሳዊ ባህሪት ከመሰሎቹ ዝንጀሮና ጎሬላዎች ተሽሎ የተገኘው እጅግ በጣም በጥቂቱ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የሰለጠነው የሰው ልጅ እስከ አውሬያዊ ባህሪያቱ ይኖራል፡፡ እኔም፣ አንተም፣ አንቺም ጭምር… ከዚህ አውሬያዊነት መሻሻልን የሻተ ዝም ይላል፡፡ በየቀኑ ቢያንስ የ40 ደቂቃ የጽሞና ጊዜ ይኖረዋል፡፡ ዝም ማለት የቻለ እርሱ ራሱን ያሸንፋል፡፡ ራሱን ማሸነፍ የቻለ፣ ሌሎችን፣ ዓለምን የማሸነፍ ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ የጠቀስኳቸውን የዘኢኮኖሚስት ጽሁፎች በጠቀስኳቸው ርዕሶች Google ላይ search ብታደርግ ማግኘት እንደምትችል አረጋግጥልሃለሁ፡፡ በል እንግዲህ ልሰናበትህ… የጽሞና ሠዓቴ ደረሰች!
© ያዕቆብ ብርሃኑ
Source : Philosphyloves 🔥

Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም ™ (Alador)
ነገረ እኩይ—Problem of Evil
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
==============================
የፊታችን ቅዳሜ (ግንቦት 24) የበጋ ሌክቸሮች መርሐ ግብራችን ትኩረቱን በ<<ነገረ እኩይ—Problem of Evil>> ላይ አድርጎአል። በትምህርት ቤታችን በሃይማኖት ፍልስፍና ስር በፍሬው ማሩፍ የሚሰጥ ኮርስ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በዘርዐያዕቆባዊ "እነዚህ እንዲህ እንዲህ ይላሉ እነዚያ እንዲህ እንዲህ ይላሉ.." የፍልስፍና መንገድ በተጋባዥ እንግዳ ልንቃኘው ነው።
መምህሩ ዮናስ ዘውዴ ነው።
የ<<ነገረ እኩይ>> አንኳር ጥያቄ <<ከፍፁማዊውና ደግ አምላክ ጎን ለጎን እንዴት እኩይ አብሮት ሊኖር ቻለ?>> የሚለው ነው፡፡ የጥያቄው መነሻ ደግሞ የፈጣሪ መለያ ባህርያት ተብለው በሚታወቁት (omnipresent, omnipotent, omniscient, and omnibenevolence) ላይ ተንተርሰው የተለያዩ አሳቢዎች እና ፈላስፎች <<በዓለም ውስጥ የሚታየውን እኩይ ነገር ከነዚህ የፈጣሪ ባህርያት ጋር የሚጣረስ ነገር አለው>> ብለው የሚያነሷቸው መከራከሪያዎች ናቸው።
ለምሳሌ የጥንታዊ ግሪክ ፈላስፋ ኤፒኩረስ ከፍፁማዊው አምላክ ጎን ለጎን እንዴት እኩይ አብሮት ሊኖር እንደቻለና ማጥፋት እንዳልቻለ ለማብራራት የሚከተሉትን አማራጮች እና አማራጮቹ የሚያስከትሉት የሎጂክ ተቃርኖ አስቀምጦአል :-
— ምናልባት እግዚአብሔር እኩይን ማጥፋት እየፈለገ ነገር ግን አልቻለ ይሆን? ይሄ ከሆነ ደግሞ ከእግዚአብሔር የ"ሁሉን ቻይነት" ባህሪ ጋር የሚጣረስ ነው።
— ሁለተኛው እግዚአብሔር እኩይን ማጥፋት እየቻለ ግን ማጥፋት አልፈለገ ይሆን? ይሄ ደግሞ ከእግዚአብሔር "የደግነት" ባህሪ ጋር የሚቃረን ነው።
— ሦስተኛ እግዚአብሔር እኩይን ማጥፋት እየቻለም እየፈለገም ሆኖም ግን ሆን ብሎ እኩይ እንዲኖር ፈልጎ ይሆን? ይሄ ደግሞ የእግዚአብሔርን "ጨካኝነት" የሚያሳይ እና ከ"ፍፁም ደግነቱ" ጋር የሚጋጭ ሊሆን ነው።
— አራተኛ እግዚአብሔር እኩይን ማጥፋት የማይፈልግ እና የማይችል ሆኖ ይሆን? ይሄ ደግሞ የእግዚአብሔርን "ሁሉም ቻይነት" ብሎም ህልውነት የሚያሳጣ ሊሆን ነው።
ወደ ትምህርት ቤታችን ጎራ ብለው ይሄን ለዘመናት ሲያከራክር የቆየውን እና አሁንም እያከራከረ ያለን የሃይማኖት ፍልስፍና ጥያቄ ላይ ይወያዩ፣ ይከራከሩ፣ ይማሩ።
ዮናስ ዘውዴ አብዛኞቻችሁ (በሚድያ) የምታውቁት ሲሆን የመጀመርያ ዲግሪ የቋንቋ እና የየማህበራዊ ሳይንስ፤ ሁለተኛ ዲግሪ የቲዮሎጂ፣ እና የፍልስፍና ትምህርቶችን አጠናቅቆአል። አሁን ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ሦስተኛ ዲግሪውን በመስራት ላይ ይገኛል።
© ዘርዓያዕቆብ የፍልስፍና ትምህርት ቤት