Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም ™ (Peter)
#Objectivism
ተፈጥሮ በማንም የአዕምሮ ምኞት አይለወጥም። አይዲያሊስቶች እንደሚሉት ሳይሆን፤ አዕምሮ አካባቢውን በማስተዋል ተፈጥሯቸውን የማወቅ አቅም አለው፤ አቅሙን የመጠቀምና ያለመጠቀም ምርጫም የራሱ ብቻ ነው። ነፃ ምርጫ አለው፤ ማቴሪያሊስቶች እንደሚሉት ሮቦት አይደለም።
የሚኖረን ነገር ሁሉ (Existence) የራሱ የሆነ የማይቀየር ተፈጥሮ (dentity) ነው፡፡ ብረት ሁልጊዜ ብረት ነው - ከውሃ ጋር ሲገናኝ ይዝጋል፣ በተወሰነ መጠን ካርበንና ነሃስ ሲጨመርበት ይጠነክራል፣ 1500 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በሆነ ሙቀት ይቀልጣል፤ ኃይል ሲጫነው ወደ ቆርቆሮነት ይለወጣል። ወይም ሽቦ ይሆናል ወዘተ... ። ብረት እስካለ ድረስ ዝንተ ዓለም ተፈጥሮው ይሄው ነው። እንጨት፣ ውሃ፣ ድንጋይ፣ እስካሉ ድረስ የማይቀየሩ ተፈጥሮ ናቸው፤ በምኞት የማይቀየሩ ባህርያት።
አየን ራንድ እንዲህ ትላለች፦
To be is to be something !
በሌላ እይታ ተፈጥሮ የሌለው ተፈጥሮ የለም እንደማለት ይሆናል። መሆን ማለት፣ የሆነ ነገር መሆን ነው፡፡ የአዕምሮ ስራ ደግሞ ማወቅ ብቻ ነው። ተፈጥሮን መፍጠር፣ መቀየር ፣ መለወጥ አይችልም ይላል የኦብጀክቲቪዝም ፍልስፍና መሠረታዊ እሳቤ።

ጌታ ሆይ !<<ከዝሙት አድነኝ ነገር ግን አሁን አይደለም 😋>>
Lord!! make me chaste; but not yet..!!
[ቅዱሥ አውጊስቲን ]
Lord!! make me chaste; but not yet..!!
[ቅዱሥ አውጊስቲን ]
<<........መቼ ነው ስቃዬችህ ቆርጠው የሚጥሉህ? መቼ ነው ተስፋ የምትቆርጠው?...>>
የኒቼ ጥያቄ ነበረች የእኔም ትሁን ወደ እኛ የተሰነዘረው ጥያቄ.
የኒቼ ጥያቄ ነበረች የእኔም ትሁን ወደ እኛ የተሰነዘረው ጥያቄ.
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም ™ (Peter)
የኒሂሊዝም (Nihilism) ፍልስፍና መሰረቱ ጥቅሙስ ምንድን ነው?.
(አለማየሁ ገላጋይ ኢትዮጵያዊው ኒሂሊስት)
ኒሂሊዝም የሚባለው ፍልስፍና በአውሮፓ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተነሳ ርዕዮት ነው። ኒሂሊዝም እንደሚገለፅበት አውድ እና ዲሲፕሊን የተለያዩ መልኮች ቢኖሩትም ማጠንጠኛው ሃይማኖት፣ ዕምነት፣ ባህል፣ እውቀት፣ ሕግ፣ ሥነ ምግባር ወዘተን መካድ ነው። ኒሂሊዝም መሠረቱ ጥርጥር (skepticism) ነው። ጥርጥር ዓላማው ውሸትን ለይቶ እውነት ጋር መድረስ ነው። ጥርጥር ግን በወለደችው ኒሂሊዝም የተሰኘ ልጅ ዓላማዋንም፣ ትርጉሟንም አጥታ እየሞተች ነው። ጥርጣሬ ጫፍ ሲይዝ እና ጨለምተኛነት የሚባል ቅመም ተጨምሮበት ሲበስል ኒሂሊዝምን ይወልዳል። ኒሂሊዝም ሁሉንም ነገር ያለምህረት መካድ ነውና። በኔ በኩል ጥቅም አለው ብዬ አላስብም። የአብዘርድ አቀንቃኙ አልበርት ካሙዩ እንኩዋን፣ እውነት ነው ህይወት ትርጉም የላትም፣ ግን ትርጉም የላትም ብለን ልንተዋት አይገባም፣ ትርጉም ልንፈጥርላት ግድ ነው ይለናል። አይሁዲው ቪክተር ፍራንክል ከአልበርት ካምዩ በተቃራኒ በሕይወት ለመኖር የሚያነሳሳን ነገር ትርጉም ፍለጋችን መሆኑን ቢያስረዳም።
"""""
እሴቶች: —
* የሰው ልጅ በማህበራዊ ኑሮ ዉስጥ ህልውናውን የሚያስጠብቅባቸው፣
ባህሉን የሚያስከብርባቸውና ለትውልድ የሚያስተላልፍባቸው፣
* ዕውቀቱን የሚያሰፍርባቸው፣
* ስሜቱን የሚገልጽባቸውና ሥነ ምግባሩን የሚተረጉምባቸው. ናቸው።
"""""
የሰው ልጅ እነዚህን የህልውናው ምሰሶዎች የተከለበት እሴቶች አሉት፡፡ እነዚህ እሴቶች የሰው ልጅ የፈጠራቸው እና ለእነዚህ ዕሴቶች ተገዥ ሆኖ የሚኖርባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል አንድ ማህበረሰብ እንደ ማኅበር ራሱን የሚገልጥበትና ህላዌውን የሚያዘልቅበት ባህል አለው፡፡ ባህል ለተፈጥሮአዊ ጉዳዮች የሚሰጥ “ምላሽ” (expression) ነው፡፡ እምነት፣ ሃይማኖት፣ እውቀት፣ ሞራል፣ ልማድ፣ ህግ/መተዳደሪያ ደንብ፣ ኪነ-ጥበብ፣ ምርትና ማምረቻ መሳሪያ፣ አልባሳት፣ ወዘተ. . . የባህል ዘርፎች ናቸው፡፡
በየትኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ባህል አለ። ማህበረሰብ ለባሕል ያለው አመለካከት የተለያዬ ቢሆንም ለዕሴቶቹ እውቅናን መስጠት ብቻ ሳይሆን አስፈላጊነታቸውንም ያምናል፡፡ ነገር ግን ኒሂሊዝም እነዚህን ሰዋዊ እሴቶች ይክዳል፤ አላስፈላጊነታቸውንም ይሰብካል፡፡ መሰረት የሌላቸውና አንዳችም ጥቅም የማይሰጡ መሆናቸውን በመግለጽ በሰው ልጅ ህላዌ ውስጥ ያላቸውን ህልውና ይክዳል። ኒሂሊዝም ሕይወት ትርጉም የለሽ እንደሆነ በማመን፣ ሁሉንም ሃይማኖታዊ እና ሥነ ምግባራዊ መርሆች አለመቀበል ነው፣ ልቅ የሆነ ነፃነት ይኑርም፣ ሁሉንም ከዜሮ እንጀምረው ይላል። «ነባሩ እሴት፣ ወግ፣ ባህል፣ እምነት በአጠቃላይ ምድራዊ ህግጋትና ማህበራዊ ትብታቦች የሠውን ልጅ ነፃነት ተጋፍተዋል፤ ስለዚህ የሠው ልጂ ከእነዚህ ትብታቦችና ሠው ሠራሽ ሠንሠለቶች እስር ነፃ መውጣት አለበት» ይላል።
የሰውን ተፈጥሯዊ ምንነት ካለማወቅ የሚመነጭ የጥፋት መንገድም ይመስላል። ሰው በcognitive evolution ያገኘውና ከሌሎች እንሰሳት የለየው ነገር ቢኖር የሌለን ነገር በ association በአዕምሮው መፍጠር መቻሉ ነው። ነገር ግን ኒሂሊስቶች በዚህ መንገድ የተፈጠረው ይጥፋና በሌላ ተጨባጭ እውነት ይተካ ይላሉ። በመጀመሪያ ይህን የማይጨበጥ እውነት እንዴት ለማጥፋት ይቻለናል? ከተቻለስ፣ ሰው እራሱ መልሱ እንደማይፈጥረው ምን እርግጠኛ አደረገን? ሃይማኖት የራሱ ችግር እንዳለበት ብስማማም፣ እንደምንለው ስላሰብን የሚጠፋ አይደለም። የጠፋ ቢመስለንም ቅርጹን ቀይሮ ይቀጥላል። የተሻለው፣ ችግርንና መንስኤዎችን መለየት፣ መፍትሔን መዘየድ ነው። ችግሩ፣ ከችግሮች ከአንዱ ላይ ፊጥ ስላልን ችግር የፈታን መስሎናል።
ይቀጥላልል ✍

የቀጠለ .. ኒሂሊዝም ...
እንግዲህ ይህ ሃሳብ ነው የኢትዮጵያ ችግር መፈቻ ቁልፍ ሆኖ በአለማያሁ ገላገይ «የተጠላው እንዳልተጠላ» መጽሐፍ ዘንድ የቀረበው መጽሐፉ ሙሉውን አጥፍተን ከዜሮ እንጀምር አይነት አቀራረብ ያለው አለምን በጠባብ መነጸር ያየ ነው። ስራን (ባርነትን) የድህነት መውጫ መንገድ አድርጎ ገልጾ ግን ያለውን መንፈሳዊ እውቀት ይጥፋ ይለናል፣ የሚተካውን የእውቀት መንገድ ግን አላሳየንም የችግሩን መንስኤዎች በሙሉው የሚያሳይም አይደለም እናም መፍትሔ ጠቋሚ አይደለም። ጥሩ ጥያቄ፣ የመፍትሔው መንገድ ግን የጎደለና በሾርኔ አይቶ ወይም ሳያይ ያለፈ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ችግርን በቃላት ድርድራ አንፈታውም። ትክክለኛውን የሃሳብ መንገድ አላገኘውም እያልኩ ነው። ችግራችን የምንፈታው፣ በዚህ አይነት የመንስኤ-ውጤት ግንኙነትን በሚያጣርስ፣ ሁሉ ይጥፋ ከዜሮ እንጀምር በሚል ሃሳብ አይደለም።
የችግራችን መንስኤዎች ብዙ መሆናቸውን መለየት፣ መፍትሔም ከዚህ አንፃር መፈለግን ይጠይቃል። እናም ስንጽፍ ብቻ ሳይሆን አስተያየት ስንረጥም ይህን ያገናዘበ መሆን አለበት። ከመጽሐፉም፣ ከውይይቱም ግን ይህን አላየሁም። ከዜሮ መጀመር መፍትሄ አይደለም መፍትሄው ያለንን ጥሩ፣ ከመጥፎው መለየት። የጎደለውን ከአለም ዘንድ መፈለግና ለእኛ ችግር መፍቻ በሚሆን መንገድ መቅረጽ፣ ሁለቱን ለንቅጦና የእኛ አድርጎ መጠቀም ነው። ይጥፋ አብዮት ወይም ኒሂልስም ነው፣ ጥፋት። ከጥፋትም ልማት አይገኝም።
""""
አሌክሶ የኢትዮጵያን ችግር ሃይማኖት ላይ አንጠልጥሎ፣ cause-effect relation እንዳንፈልግ መንገዱን ዘግቶብናል። ሃይማኖት የችግራችን አንዱ መንስኤ ነው፣ ብቸኛው መንስኤ ግን አይደለም። የተለመደው ሃይማኖትን በኒህሊዝም ይጥፋ አይነት አካሄድ ግን መፍትሄ አይሆንም። እንደምሳሌም፣ የአውሮፓው የ500 አመታት፣ የጃፓን ቢያንስ 170 ተሰርቶበት የመጣ ነው። የመንፈሳዊ እውቀት ለሌላው secular እውቀት ቦታ እንዲለቅ (አውሮፓ) ወይም አጋዥ መሆን የሚችለውን አጋዥ በማድረግ (ጃፓን) የተሰራ ነው። አሌክስ እንደሚለው በማጥፋት አይደለም። ቱርክን ስንወስደ ደግሞ ኢምፓየር ሆኖ ከአረቢያን ኢምፓየር መውደቅ ቀጥሎ የመጣ፣ እስከ አንደኛው አለም ጦርነት ድረስ በጣም ሰፊ ግዛት የነበረው ነው። ይህም ከኢምፓየሮች ታሪክ ጋር መመርመር ያለበት ነው። ነገር ግን ሃይማኖታቸውንና የምዕራቡን ሳይንስ ይዘው፣ የምዕራቡን የፖለቲካ ተጽዕኖ ከምስራቁም ጋር እየሰሩ ቀንሰው፣ ከአንደኛው የአለም ጦርነት ሽንፈታቸው በኋላ ቱርኮች እድገት ላይ ናቸው። ይህም ሃይማኖትን የችግራችን ዋናው መንስኤ አድርጎ መቁጠር ውሃ የማይቋጥር መሆኑን ያሳያል።

<<.....
ድብብቆሽ እንጫወት?!እኔ ልብ ውስጥ ከተደበቅሽ አንቺን ማግኘት አይከብድም። ከራስሽ ቅርፊት ጀርባ ከተደበቅሽ ግን ማንም አንቺን በመፈለግ አይጠቀምም።
:( .........>>
#ጂብራን_Khalil

Pessimism....ጨለምተኝነት
እንደው በፍልስፍናው የዘመን ሀሳብ ጉዞ አርተር ሾፐንሀወር የሚያክል ጽልመታዊ አመለካከት ለህይወት፣ለሰው ልጅ አስተሳሰብ፣ለውበት የሰጠ አሳቢ ከእርሱ በኋላ እንጂ በፊት ማግኘት ከባድ ነው።እሱ ያሳረፈውን ተፅእኖ ደግሞ ከእርሱ በኋላ በተነሱ አሳቢያን ፍልስፍና ማዕከል ጀርባ መገኘቱ ፍልስፍናዎቹን በጥልቀት እንዲዳሰሱ ጉጉት ውስጥ ይጨምራል።ከሾፐንሀወር ኋላ ኒቼ፣ካሙ፣ ሳርቴር፣ኪርጋርድ፣ቤኬት፣ሲኦራን...የፍልስፍናቸውን መጠንጠኛ እንዲቀይሩ አስችሏቸዋል፤በእርግጥ ሬኒ ዴስካርት በደረጃ አንድ ብናስቀምጠውም የሾፐንሀወርን የቀጠለ ጉልህ ሚና መዘንጋት የሚቻል አይመስለኝም። ኒቼ በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት እና የጊዜ ክሽፈት ሲነግረን.. ኪርጋረደን ደግሞ የግለሰብ ልእልናን የኃይማኖት በፁኑ አስፈላጊነት ሲሰብከን... ካሙ እና ሳርቴር የህይወት ወለፈንዲነት እና የእኛን የነፃነት እንዲሁም ፈጠራዊ መንገድ አሳዩን።
ከሾፐንሀወር ኋላ እንደሰው የሆነ ህይወት አስፈሪነትን እና የህይወት ስቃይና መከራ እንደግለሰብ አውርዶ ያስመለከተን-ሮማዊው ፈላስፋ ኢሜል ሲኦራን ነበር።ሲኦራን ህይወታችን ላይ ያጠላውን ጥቁር ጨለማ በብእሩ ከነደፈው 𝑜𝑛 𝑡ℎ𝑒 ℎ𝑒𝑖𝑔ℎ𝑡𝑠 𝑜𝑓 𝑑𝑒𝑠𝑝𝑎𝑖𝑟 በተሰኘው መፅሀፉ ያሳየናል።መፅሀፉ በብዙ ቁርጥራጭ ሀሳቦች የተሞላ ሆኖ የሚያሳየን ግን ስለአንድ ነገር ብቻ ይሆናል -ስለአስፈሪዋ ህይወታችን።የሾፐንሀወርን ውለታ ላለመዘንጋት ያህል እናንሳው እንጂ የሲኦራን ፍልስፍና መለስ ብለን እንቃኛለን።
ተፃፈ በይሁዳ