The Reason Why We are Existing
121 subscribers
24 photos
96 links
ሀገራችንን ጨምሮ በአለማችን ላይ በበርካታ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይኖራሉ ቁምነገሩ ግን ምን ያህል ሰው ለምን እንደተፈጠረና ለምን እንደሚኖር ያውቃል 🤔ይህ ቻናል እንዴት የተሻልን ሰዎች እንደምንሆንና ድርጊቶቻችንን እንዴት መቆጣጠር እንደምንችል ያስተምረናል የህይወታችንን ትክክለኛ ግብና እውነተኛ ስኬት የምናውቅበት ትክክለኛ ቦታ ነው
ለምን እንደተፈጠራችሁ ማወቅትፈለጋላችሁ??
@whyamhere join
Download Telegram
በምድር ላይ አርአያ አድርገን የወሰድናቸውና ለመሆን የተመኘናቸው ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ
መች ነው እኔ እንደሱ የምሆነው ያልነው ሰው ሁሌም የምንቀናበትና የደረሰበት ለመድረስ የምናስበው ሰው ይኖራል ይሄ ምንም ችግር የለውም ግን እነሱን እያየን እራሳችንን መጥላት የለብንም አለመቻላችንን ብቻ ደጋግመን ለእራሳችን መንገር የለብንም እራሳችንን መርዛማ እና ገዳይ በሆነ ሀሳብ መሙላት የለብንም
የእኛን ዋጋና አስፈላጊነት ከሌሎች ሰዎች ጋር ማነፃፀር የለብንም
እንዳለን በቂ ነን ወደ ማንም ማየት አያስፈልግም!
የሌሎች ሰዎች መሳካት እኛን የበታች እንደሆን እንዲሰማን ካደረገ ውድቀታቸውን መመኘት እንጀምራለን ቀስ በቀስ ማንነታችንን እናጣለን
ለእኛ ከፍ ማለት የግድ የሆነ ሰው ዝቅ ማለት የለበትም
የእነሱም ከፍ ማለት እኛ ዝቅ እንድንል አያደርገንም
ህይወት በጣም በብዙ ክፍት በሮችና ዕድሎች የተሞላች ናት
የአይምሯችንን ትኩረት አንድ ነገር ላይ ብቻ አድርገን ዕድላችንን ማጥበብ የለብንም::

ደግሞ ማለት ምርጥ የምትሏቸው ሰዎች ሁሉንም ነገር ማድረግ አይችሉማ?? ይችላሉ ብለን እራሱ ብናስብ አንድ ነገር ግን በእርግጠኝነት ማድረግ አይችሉም!
የማይችሉት ነገር ምን ይመስላችኋል 😉

.
.
.
.
.
እናንተን መሆን😊
አንተን/አንቺን ማንም ነው መሆን የማይችለው
ምርጦቹ ሰዎች እራሱ ሊያገኙት የማይችሉት ነገር በእጃችሁ ላይ አለ
ማንነታችሁ ሀብታችሁ ነው ያውም ማንም የማይወስድባችሁ
አንተነትህን ተቀበል
አንቺነትሽን ተቀበይ
ከዛ በአዲስ ተስፋ ቀንን መጀመር !!

መልካሙን ሁሉ ለናንተ😊
https://t.me/Whyamhere
https://t.me/Whyamhere
ምላሾችህን ቀይር!!

በሕይወትህ ልትቆጣጠራቸው የምትችላቸው ሶስት ነገሮች ብቻ አሉ::

1- የምታስባቸውን ሃሳቦች፣ 
2- በአእምሮህ የምትስላቸውን ምስሎች፣ 
3- የምትወስዳቸውን እርምጃዎች (ባህሪህን)።

እነዚህን ሶስት ነገሮች የምትጠቀምበት ሁኔታ የምታልፍባቸውን ነገሮችና ሁኔታዎች ሁሉ ይወስናል። የምታገኘውን ውጤት ወይም ልምምድህን ካልወደድከው ምላሽህን መለወጥ ግድ ነው።

አሉታዊ አስተሳሰቦችህን ወደ አወንታዊ ቀይር። የምትመኘውን ቀይር። ልማዶችህን ቀይር። የምታነበውን ቀይር። ጓደኞችህን ቀይር። የምትናገርበትን መንገድ ቀይር።

ሁልጊዜ የምትሰራውን መስራት ከቀጠልክ፣ ሁልጊዜ የምታገኘውን ማግኘትህን ትቀጥላለህ፤ በተለመደ ባህርይ በመቀጠል የተለየ ውጤት ማግኘት የማይታሰብ ነው። የአልኮል ሱሰኛ ከሆንክና መጠጣት ከቀጠልክ፣ ሕይወትህ በምንም መንገድ አይሻሻልም። ልክ እንደዚያው አሁን ባለህ ባህሪይ ከቀጠልክ፣ ሕይወትህ በምንም መንገድ አይሻሻልም። 

ምላሾችህን የቀየርክ ቀን ሕይወትህ የተሻለ ሊሆን የሚጀምርበት ቀን ነው!

ስለዚህ ዛሬውኑ ለነገሮችና ለሁኔታዎች ያሉህን የተሳሳቱ #ምላሾችህ_ቀይር!

ልክ ምላሾችህን መቀየር ስትጀምር ሕይወትህ መቀየር ይጀምራል፡፡
3
ሁሉም ሰው ሊወድክ አይችልም
ለሁሉም ሰው የተመቸሽ መሆን አትችይም
ያልወደዱህን ሺህ ትተክ ከወደዱህ ጥቂቶች ጋር ተራመድ
አንቺም የጠሉሽን በርካቶች እረስተሽ የወደዱሽ ጥቂቶች ላይ አተኩሪ

መልካሙን ሁሉ ለናንተ 😊
@whyamhere
.    ምን አይነት ዕድለኛ ነህ?!

እሳትን የሚያበርደው #ውሀ_ነው
አልጫን የሚያጣፍጠው ጨው ነው፣
ያንተን ህይወት ጣዕም የሚሰጠው ፈጣሪ ነው ።
ደስታን ለማግኘት ማንኛውንም ዋጋ ልትከፍል ትችላለህ፤ ብዙ ነገር አሳክተው ደስታን የጨበጡ የመሰላቸው ሰዎች ዘግይተውም ቢሆን ንፋስ እንደዘገኑ አውቀዋል።

እውነተኛ ደስታ ከፈለክ ፈጣሪ እስከዛሬ ባደረገልህ፣ አሁን ባለህ ነገር አመስግን፤ "ምን አይነት ዕድለኛ ነኝ?" በል፤ ገና በሚመጣው ሳይሆን አሁን ህይወትህ ላይ ያለውን እይና ተደሰት
Forwarded from አዶናይ (꧁Ermias✞︎🔥)
"ለዕባራው ሰይ" 👈 ምን ይላል ?

ፍቺ የሌለው ቃል ይመስላል አይደል ነገር ግን ፊደሎቹ ተዘበራርቀው ተፃፉ እንጂ አንድ ፍቺ ያለው ቃል መስጠት ይችሉ ነበር ፤ ህይወትም ልክ እንዲሁ ናት ብልሆች ለሰዎች የሚተርፍ አድርገው ለህይወታቸው በተግባራቸው ትርጉም ይሰጧታል ሰነፎች ግን ትርጉም እንዲኖረው የተሰጣቸውን ህይወት በገዛ ፍቃዳቹውና ስሜታቸው ለትውልድ እንዳይሆን አድርገው ያዘበራርቋታል
ከላይ ያያቿቸው እነኛ ፊደላት በስነ ስርዓት ሲቀናጁ "ባለ ራዕይ ሰው" የሚል ትርጉም ያለውን ቃል ይሰጡናል፤ ዋናው ነገር ያለው የፊደላቱ ብዛትና ውበት ላይ ሳይሆን ትርጉም ያለው ቃል መስጠቱ ላይ ነውየተወደዳቹ ትርጉም ኖሮት የተሰጣቹን ውድ ህይወት በስንፍና ብዛት ትርጉም የሌለው አታድርጉት ይልቁኑስ በትጋታቹና በጥረታቹ ለትውልድ ሁሉ የሚታይ ድንቅ ስራን ስሩበት።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
Everything is perfect when it happens in the right time
Being the same with others or the thing that the people around u doing can't prove u that u are in the right place
wait for ur perfect time, without considering the time of others !



ሁሉም ነገር ምርጥ የሚሆነው በትክክለኛው ሰዓት ሲሆን ነው
ከሌሎች ጋር መመሳሰል ወይም በአጠገባችሁ ያሉ ሰዎች የሚያደርጉት ነገር የናንተን ልክ መሆን አያረጋግጥላቹም
የራሳችሁን ምርጥ ሰዓት ጠብቁ ፤የሌሎችን ጊዜ ከግምት ውስጥ ሳታስገቡ

መልካሙን ሁሉ ለናንተ 😊

https://t.me/Whyamhere
👍1
👉👉#ምክር_ለወጣት_ሴቶች👈👈

ሁለት ወጣት ሴቶች የሰውነታቸውን ክፍል አጋልጦ የሚያሳይ ልብስ ለብሰው ወደ አንድ ስብሰባ ደረሱ፡፡
የስብሰባው መሪ በደንብ ካያቸው በኋላ እንዲቀመጡ አደረገ፡፡ ከዛ በኋላ የተናገራቸው ንግግር ምናልባት በህይወት ዘመናቸው ሙሉ የማይረሱትን ንግግር ነው፡፡
አይን አይናቸውን እያየ እንዲህ አላቸው
"እናንተ ሴቶች እግዚአብሄር በምድር ላይ የፈጠራቸው ውድ ነገሮች በሙሉ በደንብ የተሸፈኑና ለማየትም ሆነ ለማግኘት የሚከብዱና ዋጋ የሚያስከፍሉ ናቸው፡፡

👉አልማዝ የት ነው ምታገኙት? በመሬት ጥልቅ ውስጥ! ተሸፍኖና ተጠብቆ

👉ዕንቁ የት ነው ምታገኙት በውቅያኖስ የታችኛው ጥልቅ ክፍል ውስጥ!

👉ወርቅንስ ከየት ነው ምታገኙት? ወደታች ብዙ ቆፍራችሁ፣ በአለቶች ተሸፍኖ ነው! እሱን ለማግኘት ብዙ መልፋት አለባችሁ"

ኮስተር ብሎ አያቸውና ንግግሩን ቀጠለ
"ሰውነታችሁ ውድና እና ልዩ ነው፡፡
ከወርቅ ከአልማዝና ከዕንቁ ሁሉ ይልቅ እጅግ ውድ ነው፡፡ ስለዚህ እናንተም መሸፈን አለባችሁ፡፡

የከበረውን ማዕድናችሁን እንደ ወርቅና አልማዝ በደንብ ከደበቃችሁት የማዕድን አውጪ ድርጅቶች ከአስፈላጊ ማሽኖች ጋር #በጨረታ ተወዳድረው የአመታት ፍለጋ ለመድረግ ይሰለፋሉ፡፡

በመጀመሪያ መንግስታችሁን (#ቤተሰባችሁን) ይጠይቃሉ፡፡ ከዛም ሙያዊ ኮንትራት ይፈርማሉ(#ሰርግ) በመቀጠል በሙያቸው መሠረት ማዕድን የማውጣቱን ስራ ይቀጥላሉ(ህጋዊ #ትዳር)

ነገርግን ውዱን ማዕድናችሁን ካልሸፈናችሁትና በግልጥ ካስቀመጣችሁት ማንም ህገወጥ ማዕድን አውጪ መጥቶ በማይረባ መሳሪያ ነካክቶ እንደ ጠጠር በቀላሉ ይወስድበችኋል፡፡

#ሰውነታችሁ_እንቁ_ነውና_ደብቁት

ወንድሞች እህቶቻችሁን ፣ ባሎች ሚስቶቻችሁን ፣ እናም ወላጆችም ሴት ልጆቻችሁን መልካም አለባበስ እንዲለብሱ እበረታቷቸው

ለሚመለከተው ሁሉ #ሼር ይደረግ


#shady
የሆነ ምድረበዳ ቦታ ብትሄዱ ምን ዓይነት ስሜት ነው የሚሰማቹ ?
ከእናንተ ውጪ ሰው የሚባል ፍጥረት በዛ ቦታ ባይኖር ምን ነበር የምታደርጉት 🤔


ከዛ ቦታ ለመውጣት የቻላቹትን ሁሉ ታደርጋላቹ አይደል ?
አዎ በትክክል ሁሉም ሰው እንደዛ ነው የሚያደርገው
በቻላቹት ፍጥነት ከዛ መራቅ ስለምትፈልጉ አይምሯቹ ውስጥ የሚመጣውን ነገር በሙሉ ወደ ተግባር ትቀይራላቹ ያውም ምንም አይነት አጋዥ ሳይኖራቹ
ታዲያ በዚህ ሰዓት ተስፋ መቁረጥ የማይታሰብ ነገረ ነው
አስቡት በረሃ ነው ፀሀይ በሀይል ታቃጥላለች
ውሃ በጣም ይጠማቹሀል
በድካም ትዝላላቹ
መራብም አለ ያውም በሀይለኛው
ግን እነዚህ ሁሉ ከማድረግ አያስቆማቹም
ታማራላቹ
ታለቅሳላቹ
መፈጠራቹንም ልጠሉ ትችላላችሁ
በመሀል ተስፋ ቆርጣቹ ልታቆሙም ትችላላችሁ
ሆኖም በጭራሽ አትተዉትም አሁንም ትታገላላቹ
ካልሆነ እዛው መቅረታቹ ነው ከዛ የመውጣት ዕድላቹ እናንተ ና እናንተ ብቻ ናችሁ !!



ህይወትንም እንደዚሁ አስቡ አጠገባቹ የሚያግዛቹ ሰው ይኖራል ግን እናንተ በምትሮጡት ሩጫ ውስጥ ነው
እናንተ በምትኖሩት ህይወት
ማንም የናንተን ህይወት መገንባት አይችልም
የህይወታቹን መስመር የምታሰምሩት እራሳቹ ናችሁ !

ማንም ስለማየደርግላቹ ለእራሳችሁ እራሳችሁ አድርጉ
መንገዳገድ ያለ ነው መልሶ "balance" ማድረግ ብልሃት ነው 😁

ጠንክራችሁ ታገሉ ፍፃሜው ላይ ገና አልደረሳቹም
ዛሬም ጊዜ አላቹ

የምትኮሩበትን ነገ መፍጠር እንድችሉ ተመኘን

መልካሙን ሁሉ ለናንተ 😊


https://t.me/Whyamhere
A journey of a thousand miles begins with a single step
ሁሉም ትላልቅ ጉዙዎች የሚጀመሩት በትናንሽ እርምጃዎች ነው
ወደ ግባችሁ ለመድረስ ሁሌም የመጀመሪያውን እርምጃ መውሰድ ወሳኝ ነው
መልካሙን ሁሉ ለናንተ😊
@whyamhere
@whyamhere
@whyamhere
@whyamhere
🔥1
The Reason Why We are Existing pinned «Love covers all ፍቅር የበደልን ብዛት ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል ላወራርድ ቢባል እራሱ የተሰማን ህመም በምንም አይድንም😞 ከባዱን በደል የሚሽረው በፍቅር የታገዘ ይቅርታ ነው😍 ፍቅር ሁሉን ይለውጣል ከባዱን ያቀላል🥰 ደስተኛ ሆነን እንድንኖር ተፈጥሮን እንድናጣጥም ና ከራሳችን ጋር ሰላም እንድንሆን ያደርገናል ያለፍቅር ምንም ነገር ሙሉ አይደለም!! ያለፍቅር ማንንም ማስደሰት አይቻልም፤ፈጣሪንም…»
The Reason Why We are Existing pinned «Đon't expect perfection from anyone, as u are not perfect @whyamhere»
Check this out