#ስንት_አይነት_ስራ_አጥነት_አለ?
**********
አንድ ሰው ስራ አጥ የሚባለው መስራት የሚችል (በሰሪ ኃይል የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ እና በጤንነት ብቁ የሆነ) ሆኖ ስራ ለመስራት ፍላጎት ኖሮት ስራ እየፈለገ ያለ ነገር ግን ስራ ማግኘት ያልቻለ ማለት ነው፤
1. ጊዚያዊ ስራ አጥነት (Frictional Unemployment) ከአንድ ስራ ወደ ሌላ ስራ በመቀየር ወቅት የሚፈጠር በስራ ገበታ ላይ ያለመገኘት ሁኔታ ነው፤ #ለምሳሌ በዝውውር ወደ ሌላ መስሪያ ቤት የሄደ አንድ ሰው በቅጥር ወቅት በሚኖር ፕሮሰስ የስራ ገበታው ላይ ላይቀመጥ ይችላል ስለዚህ ፕሮሰሱን እስከሚያጠናቅቅ ስራ አጥ ተብሎ ይያዛል፤
2. መዋቅራዊ ስራ አጥነት (Structural Unemployment) አዳዲስ የቴክኖሎጂ አሰራሮች በመፈጠሩ ምክንያት ሰራተኞች ሲቀነሱ የሚፈጠር ስራ አጥነት ነው፤ #ለምሳሌ BPR ሲተገበር የተፈጠረ አይነት ለውጥ፤
3. Cyclical Unemployment በምርቶች ላይ በሚፈጠር የፍላጎት ማነስ ድርጅቶች ሰራተኛ ሲቀንሱ የሚፈጠር ስራ አጥነት ነው፤ መንግስታትን የሚያስጨንቅ እና መቆጣጠር የሚቻል የስራ አጥነት አይነት ነው፤
#ጤናማ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ቢኖርም ዜሮ መምጣት የማይችሉ የስራ አጥነት ምክንያቶች (frictional and structural Unemployment) በመኖራቸው ለስራ ብቁ ከሆነው ዜጋ ውስጥ እስከ 2.5 ከመቶ ስራ አጥ ቢሆን ተፍጥሯዊ ስራ አጥነት (Natural Unemployment) ይባላል፤👍🏾👍🏾👍🏾👍🏾

#LAWS_OF_RETURNS
*******
ፋብሪካዎች የማምረት አቅማቸው እያደገ ሲሄድ ማሽነሪ ከመጨመር ይልቅ የሰው ሃይል መጨመር ይቀናቸዋል! ምን ያህል ሰራተኛ ቢቀጠር ነው ብዙ ምርት ማምረት የሚቻለው? የዚህ መልስ ባለቤት Law of Variable Proportion ይባላል! በማምረት ሂደት ውስጥ ብዙ ሰራተኛ ቀጥሮ ማሰራት አጠቃላይ የምርት መጠንን ይጨምራል ነገር ግን ከተወሰነ መጠን በላይ ሰራተኛ መጨመር አጠቃላይ የሚመረተውን ተጨማሪ መጠን (Marginal Product) እንዲቀንስ ሊያደርገው ይችላል!
Law of Variable Proportion:- ለምርት ከሚያገለግሉ ግብዓቶች መካከል አንድ ብቻ ግብዓት እንዲጨምር ሲደረግ ጠቅላለ ምርት ይጨምራል ነገር ግን ከልክ በላይ የአንድ ግብዓት ብቻ ጭማሪ ካለ ጠቅላላ ምርት ይቀንሳል የሚል አስተሳሰብ ነው፡፡
#ማብራሪያ1
የትኛውም ምርት በአንድ ግብዓት ብቻ እንደማይመረት ግልጽ ነው! #ለምሳሌ ዳቦ ለማምረት ዱቄት፤ ውሃ፤ መጋገሪያ ማሽን፤ ጋጋሪ ሰራተኛ፤ ወዘተ ያስፈልጋል፤ ነገር ግን በ Law of Variable Proportion ህግ ዱቄት፤ ውሃ፤ መጋገሪያ ማሽን ምንም ሳይለወጡ/ባሉበት ሆነው ጋጋሪ ሰራተኛ ብቻ ቢጨመር የሚመረተው ዳቦ መጠን መጨመሩ አይቀርም፤ ምክንያቱም አንድ ጋጋሪ ከሚጋግረው በላይ ሁለት ሆነው ሲጋግሩ ብዙ ስለሚሆን ነው፤ ነገር ግን የሰራተኞቹ ቁጥር ከ 2 ወደ 3 ቢያድግ ዱቄት፤ ውሃ፤ መጋገሪያ ማሽን እስካልጨመረ ድረስ አጠቃላይ የሚጋግሩት መጠን እየቀነሰ ነው የሚሄደው ለማለት ነው (Stage 3)፡፡
#ማብራሪያ2
በዳቦ ፋብሪካው ምሳሌ አማካኝነት በሰራተኛ ብዛት ምርት ይቀንሳል ሲባል ምርት የሚያድግበት ልዩነት ወይም Marginal Product ነው የሚቀንሰው፤ ምን ማለት ነው?
#ለምሳሌ አንድ ዳቦ ፋብሪካ 100 ኪሎ ዱቄት፤ 100 ሊትር ውሃ፤ አንድ መጋገሪያ ማሽን እና አንድ ጋጋሪ ሰራተኛ ተጠቅሞ በቀን 1,000 ይጋግራል ብንል (የማምረት አቅም 2,000 ዳቦ ነው ብንል) እና አጠቃላይ ወጪው 100 ኪሎ ዱቄት 2,500 ብር ቢሆን፤ 100 ሊትር ውሃ 50 ብር ቢሆን፤ የአንድ መጋገሪያ ማሽን ኪራይ በቀን 1,000 ብር ቢሆን እና አንድ ጋጋሪ ሰራተኛ ደሞዝ በቀን 200 ብር ቢሆን በድምሩ 3,750 ብር ወጪ አለበት ማለት ነው (Stage 1)፤
ነገር ግን ሌሎቹ ግብዓቶች 100 ኪሎ ዱቄት፤ 100 ሊትር ውሃ እና አንድ መጋገሪያ ማሽን ሳይለወጡ ሰራተኞቹ ሁለት ቢሆኑ እና ተረዳድተው 2,000 ዳቦ በቀን ቢጋግሩ ምርቱ በእጥፍ ጨመረ ወጪ ደግሞ በ200 ብር ጨመረ! ይሄ በጣም ጥሩ ለውጥ ነው (Stage 2) ፤ ጥያቄው ሰራተኞቹ ወደ 3 ቢያድጉ ምርት ከ 2,000 በላይ ማደግ አይችልም! ወጪ ግን በ 200 ብር ያድጋል ምክንያቱም የሰራተኛው የቀን ደሞዝ ስለሆነ በ Law of Variable Proportion ህግ ዳቦ ፋብሪካው የዱቄት፤ የውሃ እና የመጋገሪያ ማሽን እስካልጨመረ ድረስ 2 ሰራተኛ ከፍተኛ ምርት ለማምረት በቂ ነው ይላል፡፡
ምርታማነትን ለማሻሻል ሁሉንም ግብዓቶች በተመጣጠነ መልኩ መጠቀም እና የሚያመጡትን ለውጥ እየመዘኑ መሄድ ያስፈልጋል (#ለምሳሌ ሁለት ሰራተኛ አለ ብሎ ዳቦ መጋገሪያውን ሁለት ማድረግ ውጤታማ ላያደርግ ይችላል ስለዚህ የማሽኑን መጨመር ተከትሎ ጋጋሪ መጨመር ወይም ዱቄቱን መጨመር ግዴታ ነው! ይህንን የሚያመጣጥነው ዘዴ Isoquant curve እና Isocost Line እንደሚባል ከዚህ በፊት አውርተናል)

#ትክክለኛው_ኢኮኖሚስት!
በምዕተ ዓመቱ ከተፈጠሩ 12 ስራ ፈጣሪዎች መካከል አንዱ ነው፤ በ2008 'Top 100 Global Thinkers' ከሚባሉት ውስጥ በደረጃ 2ኛው ነው! በአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት በዓመት አንድ ቀን በስሙ መታሰቢያ "January 14 Muhammad Yunus Day" ተሰይሟል፤ ለመሆኑ ለዓለም ምን ሰርቶ ነው?
****
በዓለም ላይ ብዙ ኢኮኖሚስቶች ከድህነት እንዴት መውጣት እንደሚቻል ቢያስተምሩም ያወሩትን እራሳቸው አድርገውት አይገኙም ነገር ግን ሙሃመድ የኑስ በ100 ሀገራት የሚተገበር የአነስተኛ ብድር አቅርቦት ተቋም በማቋቋም ሚሊዮኖችን ከድህነት ለማውጣት በቅቷል፤
የኑስ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መሃል 1940 በባንጊላዲሽ ቤተሰቦቹ ከወለዷቸው 9 ልጆች መካከል 3ኛው ሆኖ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ በ20 ዓመቱ የመጀመሪያ ድግሪ፤ በ21 ዓመቱ የማስተርስ ድግሪ እንዲሁም በ31 ዓመቱ የዶክትሬት ድግሪውን በኢኮኖሚክስ ጨርሷል፡፡
"ትልልቅ ኢኮኖሚያዊ ሃሳቦችን ባስተምርም በርሃብ ለሚጠቁ ዜጎች ወዲያው ምንም ጠብ የሚል ነገር አለመኖሩ ያስቆጨኛል" የሚለው የኑስ፤ በ1976 አስተማሪ ሆኖ በሚያገለግልበት ዩኒቨርስቲ አካባቢ በሚገኝ ሰፈር ውስጥ ወክ በሚያደርግበት ወቅት በቀርከሃ ንግድ የተሰማሩ የሰፈሩ ድሃ ሴቶች ቀርከሃ ለመግዛት አራጣ እንደሚበደሩ እና ያገኙትን ገቢ በአብዛኛው ላበዳሪ እንደሚከፍሉ ይመለከታል እንዲሁም በተመሳሳይ ባንክ ቤቶች መያዣ ማቅረብ ለማይችሉ ሰዎች ብድር እንደማይሠጡም አወቀ፤ በዚያ ወቅት ለድሆች ገንዘብ ቢሰጣቸው በእምነት እንደሚመልሱ በማመን ያለውን 27ዶላር ለ42 ሴቶች በ2 ሳንቲም ወለድ ያበድራቸዋል፤ ያኔ አነስተኛ ብድር (Microcredit እና Microfinance) አገልግሎትን ሀ ብሎ ጀመረ፡፡
ከባንክ በመበደር ለድሆች ያለ ምንም ወለድ ማበደሩን ቀጥሎ በ6 ዓመት ውስጥ 28ሺ አባላትን ማፍራት የቻለው የኑስ ስራውን ወደ ድርጅት አሳድጎ የመንደር ውስጥ ባንክ ማለትም Grameen Bank አቋቁሟል፤ ማህበረሰቡ ሙስሊም በመሆኑ ብድር ያለመውሰድ እምነት ስለነበራቸው ፈተና ሆኖበት የነበር ቢሆንም በ2007 (ከተቋቋመ በ31ዓመት ውስጥ) 6.38 ቢሊዮን ዶላር ለ7.4 ሚሊዮን ሴት ድሆች ብድር አቅርቧል፤ ይሄ ሁሉ ብድር ያለምንም መያዣ እርስ በርስ በመተማመን "Solidarity Groups" ብቻ ነው፡፡ የግራሚን ፕሮጀክቱ እያደገ በግብርና፤ በአሳ ማርባት፤ በመስኖ፤ በሶፍትዌር፤ በሞባይል እና በኔትዎርክ አገልግሎቶች በመሳተፍ በባንጊላዲሽ ትልቅ የግል ኩባንያ ሆኗል፡፡
የግራሚን ስኬት ዛሬ ላይ 100 ታዳጊ ሀገራት ሌላው ቀርቶ አሜሪካንን ጨምሮ በሌሎች ያደጉ ሀገራት ጭምር ተስፋፍቶ ከ94% በላይ ደንበኞቹን ሴቶቸ በማድረግ ሚሊዮኖችን ከድህነት አላቋል፡፡ በዚህም ተግባሩ ሙሃመድ የኑስ እና ያቋቋመው ግራሚን ባንክ በጋራ የ2006 የዓለም የሰላም የኖቤል ሽልማት አግኝተዋል፡፡ የኑስ በኖቤል ሽልማት ያገኘውን 1.4 ሚሊዮን ዶላር ለድሆች ተመጣጣኝ ምግብ ለሚያቀርብ ድርጅት ማቋቋሚ እና በባንጊላዲሽ ለድሆች አገልግሎት የሚሰጥ የሃይን ሆስፒታል ለማቋቋሚያ አድርጓል::
በአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት በዓመት አንድ ቀን በስሙ መታሰቢያ ማለትም "January 14 Muhammad Yunus Day" በተጨማሪም የኑስ ከ20 ሃገራት 50 የክብር ዶክትሬት እና ከ26 ሀገራት 113 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ተበርክቶሎታል፡፡ በ2010 ዓለማችን ካፈራቻቸው 50 ተጽኖ ፈጣሪ ሰዎች መካከል 40ኛው የኑስ ነው፤ ዛሬ ላይ የኑስ ጡረታ በመውጣት አለም አቀፍ መድረኮች ላይ በመገኘት ትምህርቶችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
የዓለም የተባበሩት መንግስታት አነስተኛ ብድር (Microcredit እና Microfinance) ድርጅትን በየሀገሪቱ በመመስረት በተለይ የሴቶች ድህነትን መቀነስ እንደሚቻል በማመኑ በ100 ድሃ ሀገራት (ኢትዮጲያን ጨምሮ) እንዲስፋፋ አድርጓል፤ ብዙዎቹም ተለውጠዋል የዚህ ሁሉ ባለውለታ ደግሞ የኑስ ነው፡፡

#Macro_Economic_Imbalance!
********
ከቅርብ ግዜ ወዲህ በሚዲያዎች፤ በመንግስት ባለስልጣናት እና በኢኮኖሚስቶች አንደበት በተደጋጋሚ ስለሚነገረው እና ሀገራችን ስለገጠማት የኢኮኖሚ ሚዛን መዛባት ወይም Macro-Economic Imbalance ምንንነት ሃሳቤን በአጭሩ ልግለጽላችሁ!
ኢኮኖሚክስ የሁለት ዘርፍ ውጤት ነው፤ አንደኛው በቤተሰብ እና በግለሰብ ደረጃ ያለውን የሰዎች ፍላጎት በአላቂው ሃብት ማሟላት ላይ ያተኮረው የMicro-economy ሃሳብ ሲሆን፤ ሁለተኛው የጠቅላላ ሀገራዊ ሁኔታዎችን ስለሚዳስሰው የMacro-economy ሃሳብ ነው፡፡
በ Micro-economy:- በቤተሰብ እና በግለሰብ ደረጃ ስለሚኖረው ስለ ዋጋ፤ ስለ አቅርቦት፤ ስለ ፍላጎት፤ ስለ የሰዎች ምርጫ፤ ስለ የሸማች እና አምራቾች ውሳኔ አሰጣጥ፤ ስለ እርካታ፤ ስለ ትርፍ፤ ስለ ወጪ ወዘተ የመጨነቅ እና የማጥናት ጉዳይ ነው፡፡
በ Macro-economy:- ጠቅላላ ሀገራዊ ድምር ሀኔታዎችን ማጥናት ሲሆን፤ ማለትም ስለ የዋጋ ንረት፤ ስለ ስራ አጥነት፤ ስለ የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት እና ስርጭት፤ ስለ ብሄራዊ የእዳ ጫና፤ ስለ ወለድ መጠን ወዘተ የመጨነቅ እና የማጥናት ጉዳይ ነው፡፡
#ለምሳሌ፡- የአንድ ሀገር ጠቅላላ የስራ አጥነት ደረጃ በአማካኝ እስከ ከ4 በመቶ በታች ሲሆን ጤናማ ይባላል (ኢትዮጲያ ውስጥ በከተማ ብቻ ያለው ስራ አጥነት 17.9 ከመቶ ደርሷል)፤ ጠቅላላ የስራ አጥነት መጠን ከ10 ከመቶ በታች ሲሆን ጤናማ ይባላል (የተለያዩ መረጃዎች በኢትዮጲያ 30 ከመቶ መድረሱን ያሳያሉ)፤ የውጪ ምንዛሬ ክምችት ለዓመታት የሚያዛልቅ ሲሆን ጤናማ ይባላል (በኢትዮጲያ የ2 ወር ከ15 ቀን ብቻ ክምችት ነው ያለው)፤ ሀገራዊ የእዳ ጫና ዝቅተኛ ሲሆን ጤናማ ይባላል (የኢትዮጲያ የእዳ ጫና ከሀገራዊ ጠቅላላ ምርት አንጻር 49 ከመቶ ደርሷል)፤ የንግድ ሚዛን መመጣጠን ቢቻል ሀገራት ወደ ውጪ የሚልኩት ወደ ሀገር ውስጥ ከሚያስገቡት መብልጥ ሲችል ጤናማ ይባላል (ኢትዮጲያ ከውጪ የምታስገባው ወደ ውጪ ከምትልከው አንጻር 6 እጥፍ ይበልጣል)፤……….
የኢኮኖሚ ሚዛን መዛባት ወይም Macro-Economic Imbalance የሚፈጠረው ከላይ ከተዘረዘሩት ዝቅተኛ መነሻ ኢኮኖሚያዊ ደረጃዎች በእጅጉ ርቆ መገኘት ማለት እና ሁኔታዎችን ለማረጋጋት የሚወሰዱ እርምጃዎች ሌሎች ተጨማሪ ሀገራዊ ጉዳቶችን ሲያባብሱ ማለት ነው፡፡ #ለምሳሌ፡- በፖሊሲ አለመጣጣም ምክንያት የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የተወሰደ መፍትሄ ስራ አጥነትን ሲያባብስ ማለት ነው፡፡👍🏾👍🏾👍🏾👍🏾

#በኢኮኖሚክስ_Long_run_ምን_ያህል_ረጅም_ነው?
Short-run ምን ያህል አጭር ነው?
***********
በተለምዶ ብዙ ኢኮኖሚስቶች Short-run አጭር ግዜ ወይም ከአንድ ዓመት በታች ያለ የምርት ወቅት ሲኖር እና ከአንድ ዓመት ሲረዝም ደግሞ Long run ይባላል ይላሉ፤ ነገር ግን Short-run እና Long run ግዜን አያመለክቱም፤
Short-run እና Long run በኢኮኖሚክስ በምርት ወቅት የሚጠቀሱ መሰረታዊ ሃሳቦች ናቸው፤ ዋናው ጽንሰ ሃሳብ በማምረት ወቅት የምንጠቀማቸው ግብዓቶች ቋሚ ግብዓቶች (ቢያንስ አንዱ) ወይም Fixed Factors (#ለምሳሌ መሬት፤ እውቀት፤ ግንባታዎች እና የመሳሰሉት) እና ተለዋዋጭ ግብዓቶች ወይም Variable Factor (#ለምሳሌ ለምርት የሚያስፈልግ ጥሬ እቃ፤ ሰራተኛ እና ሌሎች ግብዓቶች) በአንድ ላይ የምንጠቀም ሲሆን Short-run ይባላል፤
ነገር ግን በምርት ወቅት ተለዋዋጭ ግብዓቶች ወይም Variable Factor (#ለምሳሌ ለምርት የሚያስፈልግ ጥሬ እቃ፤ ሰራተኛ እና ሌሎች ግብዓቶች) ብቻ የምንጠቀም ሲሆን Long run ይባላል፤ ስለዚህ መሰረታዊ ልዩነታቸው በማምረት ሂደት ውስጥ ቋሚ ግብዓት ለምሳሌ መሬት እና ግንባታ የምንጠቀም ከሆነ በምርት ሂደት Short-run ማለት ነው!👍🏾👍🏾👍🏾👍🏾

#ኢትዮጲያ_ውስጥ_ያለው_የዋጋ_ንረት_መነሻ! ******* ኢትዮጲያ ውስጥ አሁን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው የዋጋ ንረት በአጭር ግዜ ውስጥ የተከሰተ አይደለም፤ ብዙ የተንከባለሉ ምክንያቶች አሉበት፤ በኔ እምነት የሚከተሉት ከምክንያቶቹ መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡- 1. በፍላጎት እና በአቅርቦት መካከል ያለው ልዩነት በጣም መስፋት፡- መንግስት ለብዙ ግዚያት ፍላጎትን የሚያነቃቁ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ላይ ኢንቨስት በማድረጉ ፍላጎት ዛሬ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፤ #ለምሳሌ፡- የዜጎች የአኗኗር ሁኔታ በጋራ መኖሪያ ቤት መሆን የውሃ ፍጆታ፤ የመብራት ፍጆታ፤ የትራንስፖርት ፍላጎት እንዲያድግ ያደርጋል ይሄ ደግሞ የአገልግሎት ዋጋን ያንራል፤ እንዲሁም በአንጻራዊነት ገቢያቸው እያደገ የመጣ የህብረተሰብ ክፍሎች ለቤት፤ ለመኪና፤ ለነዳጅ፤ ለመዝናኛ፤ ለትምህርት፤ የልጅ ወተት ወዘተ ያላቸው ፍላጎት ሌላው ቀርቶ የአመጋገባቸው ሁኔታ በፍጥነት እየተቀየረ ስለሆነ ፍላጎት አድጓል ነገር ግን ይህንን ፍላጎት ተከትሎ በሁሉም ዘርፍ አቅርቦት ላይ የተሰራው ስራ ዝቅተኛ በመሆኑ የዋጋ ንረት እንዲባባስ አድርጓል፡፡ 2. የህዝብ ቁጥር መጨመር፡- በሀገራችን ብዙ ግዜ በቀጥተኛ ምክንያትነት ባይነሳም በተለይ በምግብ ፍጆታ ላይ የሚፈጠረውን የዋጋ ንረትን አባባሽ የሚያደርገው የህዝብ ቁጥር መብዛት ነው፤ #ለምሳሌ፡- ዘይት፤ ስኳር፤ ሽንኩርት፤ ቲማቲም፤ እንጀራ፤ ዳቦ፤ ወዘተ ከ6ወር ህጻን ጀምሮ እስከ አዛውንቶች ድረስ ስለሚጠቀሙ በየዓመቱ 6ወር የሚሞላቸው ህጻናት በሙሉ ወደ ፍላጎት ገቢያ ይወጣሉ፤ በምትኩ መንግስት ከህዝቡ ቁጥር እድገት በላቀ መልኩ በእጥፍ የማያመርት ስለሆነ የዋጋ ንረት መባባሱ ግልጽ ነው፡፡ 3. የመንግስት ግዙፍ ፕሮጀክቶች መጓተት፡- የዋጋ ንረት በገንዘብ በብዛት ወደ ገቢያ መሰራጨት ምክንያት እንደሚባባስ ይታወቃል፤ መንግስት በቢሊዮን የሚቆጠር ብር በማውጣት ብዙ ፕሮጀክቶችን እንደገነባ ይታወቃል፤ ነገር ግን በፍጥነት ተጠናቀው ወደ ስራ ባለመግባታቸው እና ወደ ስራ የገቡትም ለታለመለት ዓላማ ውለው ወደ ትርፍ መሸጋገር ባለመቻላቸው የገንዘብ ፈሰሱን አንረው የዋጋ ንረትን አባብሰዋል፤ #ለምሳሌ፡- የህዳሴ ግድብ፤ ስኳር ፋብሪካዎች፤ ኢንዱስትሪ ፓርኮች (ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በዓመት ከመንግስት ይደጎማሉ)፡፡ 4. የላላ የገቢያ ስርዓት መኖር፡- ኢትዮጲያ ውስጥ የገቢያ ሰንሰለቱ አላስፈላጊ ተዋናዮች ስላሉበት ዋጋ ከመነሻው እስከ ተጠቃሚው ድረስ ከእጥፍ በላይ አሳድጎ ነው የሚደርሰው፤ መረጃ ለገቢያ አስፈላጊው መሳሪያ ነው፤ ነገር ግን በኢትዮጲያ ገቢያ ውስጥ የገቢያ ሁኔታ መረጃ ለሁሉም ተደራሽ ባለመሆኑ ዋጋ ተለዋዋጭ ሆኗል፤ ምርትን ያለምንም ምክንያት ወደ ፊት ሲወደድ ለመሸጥ በሚል ምክንያት ብቻ አከማችተው ዋጋ የሚያስወድዱ ነጋዴዎች መበራከት አንዱ ምክንያት ነው፡፡ 5. የፖለቲካ ሁኔታ፡- ከቅርብ ግዜ ወዲህ ሰው ሰራሽ የዋጋ ንረቶች ይስተዋላል፤ ለዚህ ማስረጃው በሳምንት ውስጥ የዋጋ መጨመር እና መቀነስ በተከታታይ መዋዠቅ ይስተዋላል፤ የዚህ አይነቱ ሁኔታ ኢኮኖሚያዊ መሰረት ሳይኖረው በሰዎች ሆን ተብሎ የሚደረግ ዋጋን የማሻቀብ ሁኔታ ተስተውሏል፤ በተጨማሪም በፖለቲካ ሁኔታ መንገድ መዘጋት እና ብጥብጥ በሚከሰትበት ወቅት ዋናው በትር የሚያርፈው ዋጋ ላይ ነው ምከንያቱም በመንገድ እጦት ምርት ወደ ገቢያ ስለማይቀርብ ባለችው ምርት ላይ ከፍተኛ ዋጋ ይጫናል፡፡ 6. የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም፡- የምንዛሬ መጠን በመጨመሩ የገንዘብ የመግዛት አቅም እንደተዳከመ ይታወቃል፤ ይሄ ወደ ውጪ መላክን ቢያበረታታም ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን ውድ ማድረጉ የማይቀር ነው፡፡ 7. የእርዳታ እና የብድር ገንዘቦችን የምንጠቀምበት ሁኔታ:- መንግስት ሸማች ነው፤ ስለዚህ የገንዘብ እጥረት ሲገጥመው ወይ ያትማል አልያም ከውጪ የተገኙ የፋይናንስ ምንጮችን ወደ ብር ቀይሮ መጠቀሙ አይቀርም፤ በተለይ በምርታማነት ላይ የማይውል ከሆነ የገንዘብ አቅርቦትን አንሮ የዋጋ ንረት እንዲባባስ ሊያደግር ይችላል፤ ስንበደር በምርት ላይ አውለን እና ወደ ውጪ በመላክ በተበደርነው የውጪ ምንዛሬ በማግኘት ለመክፈል ካልቻልን ብድሩ የዋጋ ንረት መነሻ ነው፡
#ለኢኮኖሚስቶች!
*****
በዚህ ዓመት በኢኮኖሚክስ የትምህርት ዘርፍ (ለሌሎች የማህበራዊ ሳይንስ ዘርፎችም ያገለግላል) ለመጀመሪያ ድግሪ (BA)፤ ለሁለተኛ ድግሪ (MSc) እና ለሶስተኛ ድግሪ (Ph.D.) ለመመረቂያ የሚሆን የጥናት ጽሁፍ ለምታዘጋጁ ተማሪ እና ተመራማሪዎች፤ ጥናታችሁ ትክክለኛ፤ ወቅታዊ፤ መለካት የሚችል እና የማህበረሰቡን እና የመንግስትን ችግር መፍታት የሚችል እንዲሆን በሚከተሉት ሃሳቦች ዙሪያ (Thematic Areas) ብተሰሩ መልካም አጋጣሚ እንደሚሆን ለመጠቆም እንወዳለን…..
1. የከተሞች መስፋፋት በማህበራዊ ህይወት ላይ ያለው ተጽኖ (The Impact of Urbanization on Social life)
2. ግጭት በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ የሚኖረው ተጽኖ (The Impact of Violence on Economic growth)
3. የዜጎች መፈናቀል ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽኖ (People Displacement and its Socio-Economic effect)
4. የጨለማ ኢኮኖሚ በኢትዮጲያ (The Impact of Shadow Economy in Ethiopia)
5. የስራ አጥነት እና የግጭት ግንኙነት (The Relationship of Unemployment and Violence)
6. የዋጋ ንረት አባባሽ ምክንያቶች (The Determinates of Inflation)
7. የመንግስት የልማት ተቋማት ወደ ግል ማዞር ለኢኮኖሚው የሚኖረው ተጽኖ (The strategy of Privatization on Ethiopian economy)
8. በከተሞች መካከል ያለ የኑሮ ልዩነት (Economic Comparison)
9. ከገጠር ወደ ከተማ ያለው ስደት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽኖ (Rural to Urban Migration and its Socio-Economic effect), Pulling and Pushing pressure for Rural to Urban Migration decision……..
10. አማራጭ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ (Copying Strategy for Economic Development)
አብዛኛዎቹ ርዕሶች Cross-Sectional data የሚጠቀሙ ናቸው (Time series data ለመሰብሰብ የ31 ዓመት እና ከዛ በላይ መረጃ ለማግኘት አስቸጋሪ በመሆኑ) ትክክለኛ የማህበረሰቡን ሁኔታ በመጠይቅ በመሰብሰብ ታማኝ የጥናት ውጤት ማቅረብ ስለሚያስችል ነው፤
ማንኛውም ጥናት ለመጀመሪያ ድግሪ እና ለሶስተኛ ድግሪ የሚባል የርዕስ አይነት የለውም ዋናው ልዩነት የምናጠናበት ጥልቀት ነው፤ በተጨማሪም ጥናቱ የሚዳስሰውን ቦታ አጥኚው ሊወስን ይችላል! ለምሳሌ ከተሜነት እና የማህበራዊ ህይወት ተጽኖ በአዲስ አበባ፤ በቦሌ ክ/ከተማ፤ አዋሳ፤ ጎንደር፤ መቀሌ ወዘተ ተብሎ ሊወሰን ግዴታ ነው፤
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታተም ጥናት ለመስራት የምታስቡ ካላችሁ ማተኮር ያለባችሁ በሰፈር ውስጥ የምትመለከቱትን ማህበሪያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር የሚዳስስ እና የመፍትሄ ሃሳብ የሚያሳይ ሃሳብ ላይ መሆን አለበት፤ #ለምሳሌ እኔ በቤት ኪራይ ችግር ላይ በመስራቴ Journal Of Global Economics and Research Gate በደስታ አሳትሞታል! ሰፊ ሃሳብ በመፈለግ ጊዚያችሁን እንዳታጠፉ !👍👍👍

#ኢንጅነሪንግ_ኢኮኖሚክስ?
**************
ኢንጅነሪንግ ኢኮኖሚክስ የኢኮኖሚክስ አስተሳሰቦችን ከኢንጅነሪንግ ተግባራት ጋር ያስተሳስራል፤
***************
ኢንጅነሪንግ ኢኮኖሚክስ የMicro-Economics ዘርፍ ሲሆን የሚያተኩረው በኢንጅነሪንግ ተግባራቶች ወቅት የሚከናወኑ ስራዎች ላይ የቁሳቁስ አጠቃቀም ሁኔታን (የውስን ሃብትን ውጤታማ አጠቃቀም)፤ በተግባር ወቅት የፕሮጀክት ወጪን እና ጥቅም (ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጥቅሞች) እንዲሁም የኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎችን ለመስጠት የሚረዳ የኢኮኖሚክስ የጥናት ዘርፍ ነው፤
ለምሳሌ፤- አንድ የሲቪል ኢንጅነሪንግ ስራ ቢኖር (ለምሳሌ፤-የኮንዶሚኒየም ህንጻ) ኢንጂነሩ የግንባታ ስራው በአግባቡ ስለመከናወኑ ይመለከታል ነገር ግን የህንጻው መሰራት በሀገር፤ በተጠቃሚዎች እና በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ያለውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽኖ አያጠናም፤ የዚህን ክፍተት የሚደፍነው ኢንጅነሪንግ ኢኮኖሚስቱ ነው፤👷🏿♀️👷🏿♀️👷🏿♀️👷🏿♀️

Catch-Up Effect
******
ድሃ ሀገራት ከበለጸጉ ሀገራት በላይ የነፍስ ወከፍ ገቢያቸው በፍጥነት ስለሚያድግ ያደጉ ሀገራት ላይ መድረስ ይችላሉ! የሚለው Theory of Convergence ለብዙዎች ቀልድ ቢመስልም የ21ኛው ክፍለ ዘመን ግሩም ኢኮኖሚያዊ ቲዎሪ ነው!
በኢኮኖሚ ባደጉ ሀገራት ከኢንቨስትመንት የሚገኝ ተጨማሪ ገቢ በ Law of Diminishing Marginal Returns እምነት እየቀነሰ ስለሚሄድ እና ድሃ ሀገራት ለዓለም አቀፉ ገበያ ክፍት በመሆን፤ ቴክኖሎጂ በመጠቀም፤ የውጪ ባለሃብትን በመሳብ እና ማህበራዊ አቅማቸውን (Social Capabilities) በማጠናከር ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት ስለሚያድግ መቀራረብ ወይም Catch-Up ይፈጠራል ይላል፡፡
በኢኮኖሚ ባደጉ ሀገራት ከኢንቨስትመንት የሚገኝ ተጨማሪ ትርፍ ዝቅተኛ ነው፤ ነገር ግን ድሃ ሀገራት ካደጉ ሀገራት ቴክኖሎጂ እና እውቀት በቀላሉ ማስመጣት ስለሚችሉ በትንሽ ወጪ በፍጥነት የሚያድግ ትርፍ ማግኘት ይችላሉ፤ #ለምሳሌ ዱባይ፤ ሲንጋፖር እና ኳታር እንግሊዝ እና አሜሪካ ከወሰደባቸው ግዜ ባነሰ ተጠቅመው ከተማቸውን ማስዋብ ችለዋል እንደማለት ነው (በነዚህ ሀገራት ቴክኖሎጂው እና የተማረው የሰው ሃይል ካደጉት ሀገራት የመጣ ነው)፡፡ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኃላ በጃፓን እና አሜሪካ ኢኮኖሚ መካከል የዚህ አይነቱ ሁኔታ በደንብ ታይቷል!
በተቃራኒው ድሃ ሀገራት በፍጥነት ለማደግ አሁንም ድረስ የካፒታል እጥረት ያደጉ ሀገራት ላይ እንዲደርሱባቸው አላደረጋቸውም! #ለምሳሌ ዘመናዊ የሆኑትን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለመግዛት አቅም የላቸውም ስለዚህ Theory of Convergence ህልም ነው የሚሉ ብዙ ሃሳቡን የሚተቹ ኢኮኖሚስቶች አሉ፤ እናንተስ?

Harrod-Domar Model
******
ምርታማነት ሲያድግ የሰዎች ገቢ (በቂ የስራ እድል ስለሚፈጠር) ስለሚያድግ አጠቃላይ ፍላጎት ያድጋል ስለዚህ ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲመጣ ኢንቨስትመንት በመጀመሪያ ማደግ አለበት፤ እሱን ተከትሎ የሰዎችም የመሸመት ፍላጎት ተያይዞ ማደግ ይኖርበታል፤ በተመሳሳይ ኢንቨስትመንት ሲያድግ ምርታማነት ያድጋል (አቅርቦት አደገ ማለት ነው) የኢንቨስትመንት ማደግን ተከትሎ የስራ እድል ስለሚሰፋ የሰዎች የመግዛት አቅም ያድጋል (ፍላጎት አደገ ማለት ነው) ስለዚህ Equilibrium ይፈጠራል ይላል አሜሪካዊው ኢኮኖሚስት Domar::
የመንግስት ጣልቃ ገብነት እና የውጪ እርዳታ ሳይኖር (Closed-Economic) በሀገር ውስጥ በሚደረግ ቁጠባ በመታገዝ፤ በቂ የሰው ሃይል ጉልበትን (Full Employment) በመጠቀም ሀገርን ማሳደግ ይቻላል!
ምርታማነት እንዲጨምር ቴክኖሎጂ በአጠቃላይ የካፒታል አቅም (Capital Accumulation) እና የሰው ሃይል መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠና ሲሆን በተቃራኒው እንግሊዛዊው ኢኮኖሚስት Harrod (1939) አጠቃላይ የካፒታል አጠቃቀም በጠቅላላ የምርት መጠን (Output) ላይ ያለውን ግንኙነት አጥንቷል፤ በአጭሩ Domar (1946) ኢንቨስት ስለማድረግ ብቻ ሲጨነቅ Harrod ደግሞ ኢንቨስትመንትን ከሚያስገኘው የትርፍ ገቢ አንጻር መመልከት እንዳለብን ያስረዳል፤
የሁለቱ አስተሳሰብ አንድ ላይ ሲዋሃድ Harrod-Domar Model ይባላል፤ ሃሳቡም ለኢኮኖሚ እድገት መሰረታዊው ነገር ቁጠባ እና ካፒታልን በአግባቡ መጠቀም ላይ ያተኮረ ስለመሆኑ ያስረዳል (የ Keynesian ቅጂ ነው)፤ በዋናነት የ Development Economics ትምህርት አካል ነው!
Full Employment ወይም ሁሉም ለስራ ዝግጁ የሆኑ ሰዎችን ወደ ስራ መሰማራት አለባቸው የሚለው አስተሳሰብ የ Harrod-Domar Model የሚተችበት ጉዳይ ነው፡፡🙏🏿🙏🏿🙏🏿🙏🏿

Why_Nations_Fail? ******* በ2012 በምርጥ ኢኮኖሚስቶች የተጻፈው Why Nations Fail መጽሃፍ ሀገራት ድሃ የሚሆኑበትን ምክንያት ሲያስረዳ፤ ዋናው ምክንያት በሰዎች በሚፈጠር የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተቷማት ሁኔታ ነው ድህነት የሚመጣውም የሚባባሰውም ብሏል! መጽሃፉ በ14 ክፍሎች የተከፋፈለ ቢሆንም ክፍል 13 ላይ ብቻ ያለውን ሃሳብ አጠር አድርጌ ላቅርብላቹ፤ ለብዙ ዘመናት በዓለም ላይ ያሉ ሀገራት (ኢትዮጲያንም ጨምሮ!) በኢኮኖሚ ላለማደጋቸው እና በከፋ ድህነት ውስጥ ለመኖራቸው በርካታ ምክንያቶችን ሲደረድሩ ይሰማል #ለምሳሌ፤ በተፈጥሮ ሃብት አለመበልጸግ፤ ምቹ የሆነ ጆግራፊካል አቀማመጥ አለመኖር፤ በቀደመ ታሪክ ምክንያት፤ ለስራ ምቹ ያልሆነ ባህል መኖር፤ የህዝብ ቁጥር መጨመር ወይም መቀነስ፤ የባህር በር የመኖር ያለመኖር ጉዳይ፤ ወዘተ ሲነሱ ቆይተዋል ነገር ግን ድሃ ሀገራት በኢኮኖሚ ላለማደጋቸው የቱም ምክንያት አሳማኝ መሆን አይችልም! 👉#ምሳሌ1 በተመሳሳይ የመነሻ ሁኔታ ውስጥ፤ ተቀራራቢ ታሪክ፤ ተቀራራቢ የነጻነት ዘመን፤ በአንድ አህጉር ውስጥ ሆነው የቦትስዋናን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እና የዝምባቤ፤ ኮንጎ እና ሴራሊዮን ድህነት እና ብጥብጥን በአብነት ማንሳት ይቻላል ይላል፤ ዋናው ችግር በሰዎች ምክንያት የሚፈጠሩት የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተቷማት ሁኔታ ነው ድህነትን የሚያመጣውም የሚያባብሰውም በተመሳሳይ ኢኮኖሚያዊ ለውጥን የሚያመጡትም የሚያስቀጥሉትም! 👉#ምሳሌ2 አንድ ህዝብ እና መሬት የሆኑት ኮርያዊያን ዛሬ ላይ ሰሜኑ በከፋ ድህነት ደቡቡ ደግሞ በዓለም ባለጸጋነት ምሳሌ ናቸው፤ የደቡብ ኮርያ አስተዳደር ማንኛውም ዜጋ ኢኮኖሚው ላይ ተሳታፊ እንዲሆን በማድረግ፤ ፈጠራን በማበረታታ እና ግልጽ እና ተጠያቂነትን ያሰፈነ መንግስት በመመስረት በኢኮኖሚ ሲያድጉ ሰሜኑ በድርቅ፤ የፖለቲካ ግለኝነት እና በደካማ የኢኮኖሚ ተቋማት ምክንያት ድሆች ናቸው፤ በሁለቱ እህት እና ወንድም ህዝቦች መካከል ያለው ልዩነት ፖለቲካው የፈጠረው የኢኮኖሚ ተቋማት ሁኔታ ብቻ ነው፤ ከ 15 ዓመት በላይ በወሰደ ጥልቅ ጥናት Acemoglu እና Robinson እንዳረጋገጡት በዓለም ላይ ባላደጉ ሀገራት ላይ ያለው ደካማ ፖለቲካዊ ተቋማት ሁኔታ፤ ደካማ ኢኮኖሚያዊ ተቋማት ሁኔታ ማለትም….. 👉1. የመንግስት በገቢያ ላይ ትልቅ ጣልቃ ገብነት መኖር፤ 👉2. የግል ሴክተርን ያለማሳተፍ፤ አለምአቀፍ የፋይናንስ ስርዓትን ያለመከተል ፤ 👉3. ለፖለቲካ ሹመኞች ብቻ ኢኮኖሚያዊ አቅም የመፍጠር ልምድ፤ ወዘተ ችግሮችን በመፍጠር እንጂ ሌላ ምንም አይነት ሰው ሰራሽ ያልሆነ ጠንካራ እና አሳማኝ ምክንያት ላለማደጋቸው ተጠቃሽ እንደማይሆን አረጋግጠዋል፤ በመጽሃፉ የኢትዮጲያም ሁኔታ በሰፊው የተገለጸ ስለሆነ ኢኮኖሚስቶች በዚህ አጋጣሚ ለማንበብ ከፈለጋችሁ ሙሉ መጽሃፉን በ Telegram ገጼ ላይ ስላስቀመጥኩት ይህንን መጽሃፍ ብታነቡት ጥሩ ትምህርት ታገኙበታላችሁ፤
#Labor_Market
ለገቢያ የሚቀርበው ምንድን ነው? ሻጭ እና ገዢስ እነማን ናቸው?
👆👆👆👆
ኢኮኖሚክስ ውስጥ በዋናነት 3 ዓይነት የገቢያ አይነቶች አሉ፤ እነሱም 👉 አንደኛው የቁሳቁስ (የሙዝ፤ የዳቦ፤ የልብስ፤ የቤት፤ የመኪና ወዘተ መገበያያ) እና የአገልግሎት (ሲኒማ፤ ትምህርት፤ ህክምና፤ ምክር ወዘተ መገበያያ) ገቢያ፤ 👉ሁለተኛ የገንዘብ ገቢያ (ምንዛሬ መገበያያ) (Money Market) 👉ሶስተኛው የሰው ሃይል ገቢያ (Labor Market) ናቸው፤
Labor Market ወይም የሰው ሃይል ገቢያ ማለት ምርት ለማምረትም ሆነ አገልግሎት ወደ ገቢያ እና ወደ ተጠቃሚው ለማቅረብ አምራቾችም ሆኑ አገልግሎት ሰጪዎች የሚያስፈልጋቸውን ሰራተኛ የሚያገኙበት (ቀጣሪዎች) እንዲሁም የሚያቀርቡበት (ተቀጣሪዎች) የመገናኛ ቦታ ማለት ነው፤ #ለምሳሌ አንድ ድርጅት ኢኮኖሚስት ለመቅጠር ቢፈልግ ወደ ገቢያ በመውጣት የፈለገውን ኢኮኖሚስት (ልምድ ያለውንም ልምድ የሌለውንም) አማርጦ ይገዛል (ይቀጥራል) ማለት ነው፤ በተመሳሳይ አንድ ኢኮኖሚስት ከተመረቀ በኃላ ስራ ለመቀጠር የተለያዩ ዘዴዎችን ተጠቅሞ እራሱን ለገቢያ ያቀርባል ማለት ነው፤
ሰራተኛ አገናኝ ድርጅቶች፤ ኢንተርኔት፤ የማስታወቂያ ቦርድ፤ ጋዜጣ እንዲሁም በመተዋወቅ ወይም በዘመድ ተገበያይዎች ሊገናኙ ይችላሉ፤ ሻጮች ለገቢያ የሚመጥን እውቀት (የቴክኒክ ስራ ከሆነ)፤ ጉልበት (የጉልበት ስራ ከሆነ)፤ መልክ (ትወና እና ሞዴሊንግ ከሆነ) እንዲሁም የተለያዩ ክህሎቶች እና ልምዶችን ይዘው ሲቀርቡ፤ ገዢዎች የተሻለ ደሞዝ፤ ጥቅማጥቅም፤ የኮንትራት ሁኔታ፤ የስራ ቦታ፤ የሃላፊነት ደረጃ በማቅረብ ሁለቱም በገቢያው የፈለጉትን ለማግኘት ተወዳዳሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል፤
Labor Market ውስጥ የሚገቡት ማንኛውም እድሚያቸው ለስራ ምቹ የሆነ እና የመስራት ፍላጎት ያላቸው ሰዎች በሙሉ ናቸው፤ #ለምሳሌ የቤት ሰራተኛ፤ የግንባታ ሰራተኛ፤ ቡና አፊይ፤ ሹሩባ ሰሪ፤ ኢንጂነር፤ ሃኪም፤ ከንቲባ፤ ፓይለት፤ ፖሊስ፤ ዳንሰኛ፤ ጋዜጠኛ ወዘተ ያጠቃለለ ነው፤
አሁን አሁን በሰራተኛ ገቢያ ውስጥ ተመራጭ ሆኖ ለመገኘት ከፍተኛ የትምህር ደረጃ፤ በተግባር የተደገፈ እውቀት፤ ተጨማሪ ክህሎቶች፤ የመግባባት ችሎታ፤ የመረጃ ተደራሽነት መኖር፤ ጉልበት፤ ከፍተኛ የስራ ተነሳሽነት ወዘተ አስፈላጊ ናቸው፤ #ለምሳሌ በቅርቡ የተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ኢንጅነሪንግ ላይ ብዙ ተመራቂ በመኖሩ በትምህርት ውጤት ብቻ በመወዳደር ማሸነፍ በጣም አስቸጋሪ እየሆነ ነው፤

#Liberalization
******
Economic liberalization ማለት በጥቅሉ የሀገርን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ለተቀረው ዓለም ክፍት ማድረግ ማለት ሲሆን ይህም የሚሆነው በንግድ ግንኙነት ዘርፍ፤ በቁጥጥር ስራዎች፤ በግብር ስርዓት እና ሌሎች የኢኮኖሚ ተግባራትን በሚዳስሱ እንቅስቃሴዎች ላይ ማለት ነው፤
ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ለተቀረው ዓለም ክፍት ማድረግ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለባለሃብቶች በማስፋት የገበያ አማራጭን መፍጠር እና የተሻለ ትርፍ ማግኘት ነው ብለው ይጠሩታል፤
የ Liberalization መሰረታዊው መስፈርት ሀገራት በምን ያህል ጥልቀት ሀገራዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለተቀረው ዓለም ክፍት እንደሚያደርጉ እና ኢንቨስትመንት እንዲሁም ሌሎች የንግድ እንቅስቃሴዎች በቀላሉ መከናወን እንደሚችሉ ማረጋገጥ ላይ ነው፤ ሁሉም በኢኮኖሚ የበለጸጉ ሀገራት በዚህ አይነቱ መንገድ አልፈዋል፤
ስለዚህ በኢኮኖሚ ለማደግ ጉጉት ያላቸው ታዳጊ ሀገራት በወደዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዲመጡ ይፈልጋሉ ለዚህም ይረዳ ዘንድ የሚከተሉትን ሁኔታዎች እንዲያሟሉ ይፈለጋል፤
1. ለዓለም አቀፉ ገበያ ከፍት መሆን
ክፍት ባልሆኑ ሀገራት የውጪ ባለሃብቶች ኢንቨስት ለማድረግ ያለው ውጣ ውረድ ከፍተኛ ነው ለምሳሌ በግብር ስርዓት፤ የውጪ ባለሃብቶች ላይ ባለ ገደብ፤ የህግ ጉዳዮች መብዛት፤ የንግድ ቁጥጥር መጥበቅ፤ ወዘተ ሀገራት የተሻለ ጥቅም እንዳያገኙ ሲያደርግ ቆይቷል፤ ስለዚህ Economic liberalization ከላይ የተጠቀሱ ማነቆዎች እንዲፈቱ በማድረግ ይጀምራሉ በተጨማሪም በኢኮኖሚያዊ መእንቅስቃሴ ውስጥ የግል ሴክተሩ ከፍተኛ ሚና እንዲወስድ ይፈልጋሉ (የመንግስት ጣልቃ ገብነት እንዲቀንስ ይፈለጋል)
የ Economic liberalization ዋናው ዓላማ ገደብ የሌለበት የካፒታል ልውውጥ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ እንዲኖር በማድረግ ኢኮኖሚያዊ እድገት እና ውጤታማነት (Efficiency) እንዲመጣ ማስቻል ነው፤ ሁሉም እንደሚስማማው ጀማሪ ሀገራት በመጀመሪያዎቹ ወቅታቶች ሊቸገሩ እንሚችሉ ያነሳሉ፤
2. ነጻ የሆነ የካፒታል እንቅስቃሴ መፍቀድ
ሀገራት የታሪፍ መጠንን በመቀነስ፤ የንግድ ህጎችን በማላላት እና ሌሎች የንግድ ስርዓትን የሚጎዱ አሰራሮችን በመቀነስ የተሻለ አቅም (Competitive Advantages) ካላቸው ሀገራት በመግዛት የተሻለ አቅም ለሌላቸው ሀገራት በመሸመት (ያልተገደበ የንግድ ልውውጥ በማድረግ) ነጻ የሆነ የካፒታል እንቅስቃሴ መፍጠር ነው፤
3. Stock Market ማሳደግ/መፍቀድ
ሀገራት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለተቀረው ዓለም ክፍት በሚያደርጉበት ወቅት በቀላሉ የድርጅቶችን አክሲዎኖች ግዢ እና ሽያጭ ያድጋል፤ ይሄ ካፒታል ማሳደግ ለሚፈልጉ እና ለባለሃብቶ አዳዲስ እድሎችን እንዲመለከቱ እና ትርፋማ እንዲሆኑ ያግዛል ተብሎ ስለሚታሰብ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤
4. የፖለቲካ ስጋቶችን መቀነስ
Liberalization ሀገራት ብዙ የውጪ ባለሃብቶችን ወደ ሀገራቸው ለመሳብ የፖለቲካ አለመረጋጋቶችን በመቀነስ የባለሃብቶችን ፍላጎት እንዲያድግ ማድረግ #ለምሳሌ የህግ መዋቅሮችን ማጠናከር፤ ጠንካራ የኮንትራት ህግ መፍጠር፤ የባለመብትነት መብትን ማስጠበቅ እና ሌሎች የንግድ እና ኢንቨስትመንት ህጎች ማሻሻል ይገባል ይላሉ፤
5. የኢንቨስትመንት አማራጮችን ማስፋት
ባለሃብቶች የተሸለ ትርፍ ለማግኘት የተለያዩ ዘርፎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉ ይታወቃል ስለዚህ ሀገራት የጋራ ኢኮኖሚያዊ ትብብር የሚፈጥሩ ከሆነ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲደጋገ ያግዛል ብለው ያስባል ለዚህ ምሳሌ የምትሆነው ግሪክ የዛሬ 10 ዓመት ከገባችበት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በአውሮፓ ሀገራት ድጋፍ ለመቋቋም መቻላ ይነሳል፤
Liberalization ለድሃ ሀገራት የሚያመጣው ጉዳት ምንድን ነው?
1. ከውጪው ዓለም ጋር በሚኖር የንግድ ፉክክር የሀገር ውስጥ አምራቾች ሊዳከሙ ይችላሉ ምክንያቱም በኢኮኖሚ የበለጸጉ ሀገራት የተሻለ የማምረት አቅም ቀድመው ስለፈጠሩ ማለት ነው ይሄ ደግሞ ሀገር በቀል ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን መጉዳቱ የማይቀር ነው፤
2. ድሃ ሀገራት ሲገቡ ታሪፍ እንዲቀንሱ ይገደዳሉ ነገር ግን ያላደጉ ሀገራት መንግስታት ጠቅላላ ከሚያገኙት ገቢ ከ10-20% የሚሆነው የሚገኘው ከታሪፍ ነው ስለዚህ ይህንን እንዲቀንሱ የሚገደዱ ከሆነ ሌሎች የገቢ አማራጮች ላይ መጨመራቸው አይቀርም (#ለምሳሌ ሌሎች የግብር አይነቶች ላይ) ምክንያቱም የበጀት መጠናቸውን ማመጣጠን ስለሚኖርባቸው ነገር ግን ይሄ አካሄድ ሌሎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን መጉዳቱ አይቀርም፤
3. #ለምሳሌ በግብርና ምርቶች ላይ ያለው ገደብ የሚነሳ ከሆነ በርካታ የሰው ሃይል የሚሰማራበት እና ለታዳጊ ሀገራት የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነው ግብርና መጎዳቱ አይቀርም ይሄ ደግሞ ስራ አጥነትን በማስፋፋት ከገጠር ወደ ከተማ የሚኖርን ፍልሰት በማፋጠን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ መፍጠሩ አይቀርም፤
አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ለኢትዮጲያ ሊሰጥ ያሰበው 2.9 ቢሊዮን ዶላር 5 መሰረታዊ ጉዳዮችን ያማከለ ነው እነሱም…
1. ሀገሪቷ ያለባትን የውጪ ምንዛሬ ክምችል ለመደገፍ እና በገበያ የሚመራ የምንዛሬ አሰራርን እንድትከተል ለማገዝ (በነገራችን ላይ ኢትዮጲያ Pure fixed exchange rate ስትጠቀም አልነበረም ሁለቱንም አቀላቅላ በመጠቀም ላይ ነበረች (Fixed exchange rate + Floating exchange rate))፤
2. የመንግስት የልማት ተቋማት ካለባቸው እዳ አንዲላቀቁ ለማገዝ፤
3. መሰረተ ልማትን በማገዝ ድህነትን ለመቀነስ የሚሰሩ ስራዎችን ለማገዝ፤
4. የፋይናንስ ዘርፉ ላይ ያለውን ሪፎርም ለማገዝ እና የግል ባለሃብቶችን እንቅስቃሴ ለማገዝ፤
5. የ Safety nets እንቅስቃሴን ለማጠናከር የሚሉ ናቸው፤
#ማሳሰቢያ
IMF ኢኮኖሚያዊ liberalization እንድናደርግ እየጠየቀን ነው! ታዲያ የኢትዮጲያ መንግስት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዝግ ኢኮኖሚን ይዞ መራመድ ይችላል? አይችልም! ሞላ ጎደለም ለተቀረው ዓለም ክፍት መሆን ግዴታ ነው! ነገር ግን ሁሉንም እንቅስቃሴዎች መንግስት በመጠኑ መመልከት አለበት ብዬ አስባለሁ!

#ከውጪ_የሚገባ_የዋጋ_ንረት_Imported_Inflation?
**************
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ለተወካዮች ምክር ቤት ስለዋጋ ንረት ሲያስረዱ "በኢትዮጲያ ያለው አሁናዊ የዋጋ ንረት ከውጪ የገባ (Imported Inflation) አለመሆኑ ጥሩ ጎን ነው" ብለው ነበር፤ ለመሆኑ የዋጋ ንረት እንዴት ነው ከአንድ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር የሚዘዋወረው? አስቲ በምሳሌ እንመልከተው!
የዋጋ ንረት ማለት በተከታታይ የአገልግሎት ወይም የሸቀጦች ዋጋ መጨመር ማለት ነው፤ ዋጋ እንዲንር የሚያደርጉ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም በዋናነት ለአገልግሎትም ሆነ ለሸቀጦች በፍላጎት እና በአቅርቦት መካከል ሲፊ ክፍተት ሲፈጠር (ፍላጎት ከአቅርቦት ሲበልጥ)፤ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን በኢኮኖሚው ላይ ሲረጭ (ገንዘብ ማተም፤ የክፍያ መብዛት፤ አዋጪ ያልሆኑ ፕሮጅክቶች ላይ ብዙ ገንዘብ ፈሰስ ማድረግ ወዘተ) እንዲሁም የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከምም ሲከሰት ወዘተ ነው፤
ሀገራት በሀጋራቸው ወጪን በቀነሰ መልኩ ማምረት ያልቻሉትን ወይም በሀገራቸው ጭራሽ የማይመረቱ አገልግሎት እና ሸቀጦችን ከሌላ ሀገር እንደሚያስመጡ ይታወቃል፤ ነገር ግን በሀገር ውስጥ ከላይ የጠቀስኳቸው የዋጋ ንረት አባባሽ ምክንያቶች ምንም ሳይለወጡ ከውጪ ሀገር የሚገዙበት ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት ምርቶቹ በሀገር ውስጥ ከመጡ በኃላ ውድ በመሆን የዋጋ ንረት ሊያስከትሉ ይችላሉ፤ የዚህ አይነቱ የዋጋ መጨመር ከውጪ የገባ የዋጋ ንረት ወይም Imported Inflation ይባላል፤
ለምሳሌ ኢትዮጲያ የሱፍ ዘይት ከቻይና የምታስገባ ቢሆን እና የአንድ ሊትር ዘይት ዋጋ በ50ብር ከቻይና ተገዝቶ በኢትዮጲያ ገቢያ በ60ብር ሲሸጥ የነበረ ቢሆን እና በቻይና ሀገር ያለው ዘይት አምራች ካምፓኒ ለምርት የሚያስፈልገውን ሱፍ ከሚገዛበት ሀገር (ለምሳሌ ህንድ) ዋጋው በተከታታይ ቢጨምር ወደ ኢትዮጲያ የሚልከው የአንድ ሊትር ዘይት ዋጋ መጨመሩ አይቀርም (ለምሳሌ ወደ 80ብር ከፍ ብሎ ኢትዮጲያ ውስጥ 100ብር ሊደርስ ይችላል) ምክንያቱም የማምረቻ ወጪው ስለጨመረበት ማለት ነው፤ በዚህ ምክንያት ኢትዮጲያ ውስጥ ያለው የዋጋ ንረትን የሚያባብሰው ምክንያት ምንም ሳይለወጥ ሌላ ሀገር በተፈጠረ የማምረቻ ዋጋ መጨመርን ተከትሎ የዋጋ ንረት ይከሰታል ማለት፤ የዚህን ግዜ የዋጋ ንርት Imported ሆነ እንላለን፤👍🏾👍🏾👍🏾👍🏾

#የመንግስት_ኤክሳይስ_ታክስ_እያሰጋኝ_ነው!
*********
የመንግስት ፖሊሲ የመተቸት ልምድ የለኝም ነገር ግን አሁን መንግስት እያሰበ ያለው ኤክሳይስ ታክስ እጅግ አስፈርቶኛል ስለዚህ ዛሬ ስጋቴን ለመግለጽ እፈልጋለሁ!
መንግስት የሀገር ውስጥ ገቢ ከሚያገኝበት ምንጭ ዋነኛው ከተለያዩ የታክስ አይነቶች እንደሆነ ይታወቃል፤ ስለዚህ ታክስ መሰብሰብ ግዴታ ነው (ምንም ታክስ ከዜጎቻቸው የማይሰበስቡ ሀብታም እና አነስተኛ ደሴት ሀገራት እንዳሉም ከዚህ ቀደም አቅርቢያለሁ) በተጨማሪም ታክስ አጠቃላይ የ Macro Economy እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የሚያገለግል የ Fiscal Policy አካል እንደሆነም ይታወቃል፤
መንግስታት በሁለት መንገድ ታክስን ሊጨምሩ ይችላሉ፤ አንደኛው የገቢ መጠናቸውን በመጨመር ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ለማዋል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የገንዘብ አቅርቦትን እና ፍላጎትን ለመቆጣጠር በሚያስቡበት ወቅት ነው፤ #ለምሳሌ የገንዘብ አቅርቦት በሰዎች እጅ ሲበዛ በታክስ ሰበብ መሰብሰብ የተለመደ አሰራር ነው፤ የገንዘብ አቅርቦትን ለመጨመር ታክስ መቀነስ ሌላው አሰራር ነው (ታክስ ተቀነሰ ማለት ሰዎች ለመንግስት ይከፍሉት የነበረው ገንዘብ እጃቸው ላይ ይቆያል ማለት ነው)፤
በተጨማሪም ከውጪ በሚገቡ ቁሳቁሶች ላይ የሚጣል ታክስ የውጪ ምንዛሬን አቅርቦት መሰረት ያደረገ መሆን ስለሚኖርበት ሀገራት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ እጥረት ሲገጥማቸው ከውጪ በሚገቡ እና መሰረታዊ በማይባሉ ቁሶች ላይ ተጨማሪ ታክስ ይጥላሉ::
የኢትዮጲያ መንግስት ከ30% እስከ 430% የሚደርስ ታክስ (#ለምሳሌ 100 ብር ለመንግስት ይከፈልበት የነበረ እቃ ከ130 እስከ 530 ብር እንዲከፈልበት ማድረግ ማለት ነው) በተለያዩ የቅንጦትም (#ለምሳሌ ሰው ሰራሽ ቅንድብ እና ሂውማን ሄር) የቅንጦት ባልሆኑ ቁሳቁሶች (#ለምሳሌ የታሸገ ውሃ) ላይ ሊጥል ማሰቡን ሰምተናል፤ በአሁን ግዜ መንግስት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ እጥረት እንዳለበት እናውቃለን፤ ስለዚህ……
1. ከውጪ የሚገቡ የቅንጦች እቃዎች ላይ ከፍተኛ ግብር ጥሎ ገቢውን ቢያሳድግ (በቅርቡ የ500 ሚሊዮን ብር የግምጃ ቤት ሰነድ ለሽያጭ እንደሚቀርብ የተገለጸው የገንዘብ አቅርቦትን ለመሸፈን መሆኑ ይታወቃል)፤
2. አካባቢን እና ሰው ሰራሽ አደጋን ቢከላከል (#ለምሳሌ ከ10 ዓመት በላይ ያገለገሉ መኪኖች ላይ የቀረበው ምክንያት)፤
3. የውጪ ምንዛሬን አጠቃቀም ለመቆጣጠር ቢሞክር (#ለምሳሌ ሀገሪቷ ዛሬ ላይ ከሰው ሰራሽ ቅንድብ እና ሂውማን ሄር ይልቅ ስንዴ፤ ነዳጅ እና ዘይት ከውጪ ለማስገባት የውጪ ምንዛሬ ስለሚያስፈልጋት)፤
4. የገንዘብ አቅርቦትን (Money Supply) ለመቆጣጠር ቢሞክር፤ ወዘተ
መንግስት ከላይ የተጠቀሱትን ምክንያቶች እሳቦ ታክስ ለመጨመር ማሰቡ መጥፎ አይደለም ነገር ግን የኔ ስጋት…..
1. በትንሹ የሚበረግግ ኢንቨስትመንት ባለበት ሀገር ይሄ ሁኔታ በማምረት ሆነ በንግድ ስርዓት ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገበያ እንዲሸሹ ሊያደርጋቸው ይችላል፤ እሱን ተከትሎ ስራ አጥነት እንዳይጨምር ስጋት አለኝ፤
2. ብዙ የማታመርት ነገር ግን ብዙ ከውጪ በመግዛት የምትኖር ሀገር በመሆኗ ተያያዥ የዋጋ መጨመር (Multiple effects) የተለመደ ነው (#ለምሳሌ የነዳጅ ዋጋ መጨመር የዕንቁላል ዋጋን በቀጥታ የሚነካባት አስገራሚ ሀገር ነች) ስለዚህ ከፍተኛ የዋጋ ንረት መፈጠሩ አይቀርም፤
3. የህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ማለትም ከመንግስት እይታ የተሰወረ ንግድ ወይም Shadow Economy አካሄድ በከፍተኛ ሁኔታ ሊባባስ መቻሉ የማይቀር ነው፤
4. የመጨረሻው ሸማች (እኔ!) ሁሌም በዋጋ ምክንያት ተጎጂ እንደምሆን ግልጽ ነው፤ ምክንያቱም ነጋዴ ከስሮ ሸጦ አያውቅም ስለዚህ ከትርፍ ላለመውረድ በሸማቹ ላይ ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ በሆኑ ቁሳቁሶች እና አገልግሎቶች ላይ ዋጋ መጨመሩ አይቀርም፤
#ለምሳሌ ኢትዮጲያ ውስጥ አንድ ሚሊየን ነጋዴ (ከውጪ አስመጪዎችንም ጨምሮ) እና አምራች አለ ብለን ብናስብ፤ ተጨማሪ ታክስ መጨመር መቶ ሚሊየኑን ህዝብ በአንድ ሚሊየኑ ነጋዴ እና አምራች Cost ለመለወጥ ማሰብ ይመስላል ነገር ግን ተጎጂው ይባስ ብሎ የሚመስለኝ መቶ ሚሊየኑ ህዝብ ነው! ስለዚህ ሌሎች ምርታማነትን የሚያሻሽሉ ስራዎች ላይ በመረባረብ እና ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በተቻለ መጠን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት በመስራት ሁኔታዎችን ለመቆጣጠር መሞከር ሳይሻል አይቀርም፤
ስለዚህ መንግስት አንደኛ የታክስ መጠኑን (ከ30% እስከ 430%) ደጋግሞ ቢያስብበት መልካም ነው! በተጨማሪም ለመጨረሻው ሸማች የሚሆን መላ ከወዲሁ ቢያስብ የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ ምክንያቱም ከ 20% በዘለለ የዋጋ ንረት ላይ ተጨማሪ ታክስ መጨመር ወዴት እንደሚወስደን ሳስበው እኔ ስጋት ተሰምቶኛል! እናንተስ?

#A_Public_Private_Partnership(PPP, 3P or P3)?
*********************
በ 21ኛው ክፍለ ዘመን ከመጡ አዳዲስ ሃሳቦች መካከል ሲሆን በጣም የሚገርም Mediator አሰራር ነው፤ ሃሳቡ ሁለት እና ከዚያም በላይ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማትን በማቀናጀት የረጅም ግዜ ለውጥ ለማምጣት ስራ መስራት ማለት ነው፤ መንግስት ሁሉንም አካላት በማቀናጀት ተግባራትን ያከናውናል፤
በምሳሌ እንመልከተው መንግስት ትምህርት ቤት ለማስገንባት ቢያስብ እና የአዋጪነት ጥናቱን ከአንዱ የግል ድርጅት ቢዋዋል፤ የእቃ አቅርቦት ከሌላ የግል ድርጅት ቢዋዋል፤ ግንባታውን መንግስት ቢይዝ እንዲሁም የሰው ሃይል ቀጠራን ሌላኛው የግል ተቋም ቢጨርስ ፍጥነት፤ እኩል ተጠቃሚነት እና ጥራትን አሟልቶ ማጠናቀቅ ይችላል ማለት ነው፤
ለምሳሌ አሁን አሁን ለመንግስት ዪኒቨርስቲዎች የሚውል እንጀራ፤ ዳቦ አንዲሁም ስጋ እና አትክልት የግል ተቋማት እንዲያቀርቡ የሚደረገው በ Public–Private Partnership ጽንሰ ሃሳብ ነው፤

#የኢኮኖሚስቶች_ክርክር!
********
ኢኮኖሚስቶች የአንድ ሀገር የኢኮኖሚክ ፖሊሲ መመራት ያለበት በህግ ተደንግጎ (Economic policy should be conducted by RULE) ወይም ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ በነጻነት ተለዋዋጭ በሆነ መልኩ (Economic policy should be conducted by DISCRETION) መሆን አለበት በሚሉ ሃሳቦች ላለፉት 60 ዓመታት ሲከራከሩበት ኖረዋል፤ አሁንም ከፍተኛ ክርክሮች አሉ፤
በህግ ተደንግጎ (በመንግስት ውሳኔ) የኢኮኖሚክ ፖሊሲዎች ሲቀመጡ ‘በየግዜው የሚፈጠርን ጣልቃ ገብነትን’ ለመከላከል በማሰብ ነው…..
1. የሀገሪቷን ምንዛሬን መጠን ቀድሞ መወሰን (#ለምሳሌ አንድ ዶላር በ28 ብር እንዲመነዘር ብሎ ውሳኔ ማስተላለፍ)፤
2. የገንዘብ አቅርቦት መጠንን ቀድሞ መወሰን (በየዓመቱ 3% ብቻ መጨመር አለበት ብሎ ውሳኔ ማስተላለፍ)፤
3. የወለድ መጠንን ቀድሞ መወሰን (7% ወለድ እንዲሆን ውሳኔ ማስተላለፍ)፤
4. የግብር መጠንን ቀድሞ መወሰን እና ወዘተ የመሳሰሉት ሲሆኑ፤
ሁለተኛው የሀገሪቷን ኢኮኖሚክ ሁኔታዎችን በመመርመር ‘በቀላሉ የማይገመቱ አካሄዶችን’ ለመከተል ካለ ፍላጎት በመነሳት የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግ ነው፤
ብዙ ግዜ የFiscal እና የMonetary ፖሊሲ ውሳኔዎች ላይ ሁለቱንም አካሄዶች አቀላቅሎ መሄድ የተለመደ ነው ነገር ግን ረጅም ዓመታት አብዛኛዎቹ ሀገራት ኢኮኖሚያቸውን የመሩት በ Rules-Based Policymaking ነው፤ ኢትዮጲያም የኢኮኖሚክ ፖሊሲ መመራት ያለበት በህግ ተደንግጎ መሆን አለበት የሚለውን አካሄድ የምትከተል ሀገር ነች፤

#Duty_Drawback_Scheme
👆👆👆👆
የተለያዩ እቃዎች ወደ አንድ ሀገር ከውጪ የሚገቡ ሲሆን ተገቢው የማስገባት የግዴታ ወጪዎች (import duty fee) እንደሚከፈል ይታወቃል (ውስን መሰረታዊ ቁሳቁሶች duty free ሊገቡ ይችላሉ)፤ ነገር ግን የተገዙት እቃዎች የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎባቸው (ወደ ውጪ ተመልሰው እስከሚላኩ ድረስ ለሀገር ውስጥ አገልግሎት ላይ አይውሉም) ወደ ሌላ ሀገር በexport መልክ የሚላኩ ሲሆን ለማስገባት የተከፈለ ክፍያ (import duty fee) እንዲመለስ ይደረጋል፤ ይሄ አሰራር Duty Drawback Scheme ይባላል፤ ለማስገባት የተከፈሉት ወጪ እንዲመለስላቸው ባለሃብቶች ናቸው የሚጠይቁት፤ ነገር ግን ከውጪ የገባው እቃ ሀገር ውስጥ አገልግሎት ላይ ከዋለ Duty Drawback መጠየቅ አይቻልም፤ የዚህ አይነቱ አሰራር ያልተገባ ምርትን ላለመጠቀም፤የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታት፤ የስራ እድል በሀገር ውስጥ ለመፍጠር እና የውጪ ንግድን ለማበረታታ ሲባል የሚካሄድ የፖሊሲ አማራጭ ነው፤

#የGDP_እና_GNP_ልዩነት!
***********
የአንድ ሀገር ሀገራዊ ጠቅላላ ገቢ በዋናነት በሁለት መንገዶች ይለካል፤ እነሱም ጠቅላላ በሀገር ውስጥ ያለ የምርት መጠን (GDP) እና ጠቅላላ የሀገሪቷ ዜጎች የፈጠሩት የገቢ መጠን (GNP) ነው፤ እስቲ መሰረታዊ ልዩነታቸውን በምሳሌ እንመልከት፤
GDP፤- በአንድ ሀገር ድንበር ክልል ውስጥ በአንድ ዓመት ውስጥ ከኢንቨስትመንት፤ ከመንግስት ጠቅላላ ወጪ፤ ከጠቅላላ ፍጆታ ወጪ እንዲሁም ወደ ውጪ ከሚላክ ጠቅላላ አገልግሎት እና ቁሳቁስ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን አገልግሎት እና ቁሳቁስ በመቀነስ የሚገኝ ልዩነትን የሚያሰላ ሲሆን በሀገር ውስጥ የውጪ ዜጎችም ሆኑ የሀገር ውስጥ ዜጎች ያመረቱትን እና የሸጡትን ጠቅላላ ምርት ያጠቃልላል፤
GDP= Consumption + Investment + Government Expenditure + (Export-Import)
GNP፤- በሀገር ውስጥ እና በተለያየ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ የአንድ ሀገር ዜጎች ብቻ በማምረት እና አገልግሎት በመስጠት የሚገኝን ገቢ አጠቃሎ የሚያሰላ ነው፤ ነገር ግን በውጪ ሀገር ዜጎች የሚመረት ቅሳቁስ እና አገልግሎት ገቢ አይጠቃለልም (ምክንያቱም ወደ ውጪ የሚላክ ገቢ ተብሎ ስለሚታሰብ ነው)፤ ለምሳሌ አንድ ህንዳዊ በኢትዮጲያ አፓርታማ ገንብቶ ቢያከራይ (ለደሞዝ የተከፈለው፤ ለኪራይ የተከፈለው እና ትርፉ) በኢትዮጲያ GDP ላይ ሲመዘገብ (ምክንያቱም ገቢው የተገኘው በኢትዮጲያ መሬት ላይ ስለሆነ) ነገር ግን ባለቤቱ ወደ ህንድ የሚልከው ገቢ በኢትዮጲያ GNP ላይ ሳይሆን በህንድ GNP ላይ ነው የሚመዘገበው፤
GNP= GDP + Factor payments from abroad - Factor payments to abroad
ያደጉ ሀገራት የGDP እና GNP ልዩነት እያሰሉ የኢኮኖሚ የእድገት ሁኔታቸውን ይመዝናሉ ነገር ግን እንደ ኢትዮጲያ ላሉ ሀገራት GNP በሁሉም የዓለም ሀገራት በዜጎቿ በማምረት እና አገልግሎት በመስጠት የሚገኝን ገቢ አጠቃሎ ማስላት አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፤ ለምሳሌ ኢትዮጲያዊያን የሚያገኙትን ገቢ በሚኖሩበት ሀገር ባንክ በማስቀመጠ ወደ ሀገር ቤት የማይልኩ ከሆነ (ሀገርን ከመውደድ እና ከመደገፍ ጋር ሊያያዝ ይችላል) ማስላት አስቸጋሪ ነው፤👍🏾👍🏾👍🏾👍🏾