በመንግስትም ሆነ በግል ባለሃብቱ የተገነቡ ፋብሪካዎች ባላቸው #የማምረት_አቅም ከመኩራራት ይልቅ ፋብሪካዎቹ #አሁን ላይ እያመረቱ ባሉበት አቅም መቆጨት ምክንያታዊ አይሆንም?
ለሰው ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊም ጠቃሚም መሆኑ ቢታወቅም ሁሌም እና ሁሉምን ሰው መደገፍን ጠቃሚም አስፈላጊም አድርጎ ማሰብ በኢኮኖሚክስ አስተምሮት ልክ ሊሆን አይችልም!
#መስጠት_እወዳለሁ! የሚለውን ንግግር ውስጥ ምን ያህል?፤ ለማን?፤ ለምን? የሚለውን መመለስ በተጨማሪም እርግጠኝነት ለሚጎለው ነገ ምን አቅደሃል? የሚለውንም ጥያቄ መመለስ መቻል ግድ ነው፡፡
የሚቀጥለው ወር አስቤዛ ሳያስቀምጡ፤ ልጆች ድንገት ቢታመሙ ማሳከም የሚችል ጥቂት ብር ሳይዙ፤ ከቤት ኪራይ ቢባረር እቃ ማጓጓዣ ብር ሳያስቀምጥ፤ የመብራት አንፖል ቢቃጠል መቀየራ ብር ሳይኖረው፤ ወዘተ "እጄ ላይ ብር ካለ ለሰው መስጠት ያስደስተኛል!" ቢል ምክንያታዊ ነው?
ከሃይማኖት አስተምሮት አንጻር የተለያየ ምልከታ እና መልስ ሊኖር እንደሚችል እረዳለሁ! ነገር ግን እኔ የውይይቱን ሃሳብ ያመጣሁት ከሃይማኖት አስተምሮት ውጪ እንድንወያይበት ነው!
#ለምሳሌ፡- "ገንዘቡን ለማንም ሲበትን ኖሮ ልጆቹን በቤት ኪራይ ያሰቃያል!" የሚባል አባት ቤት መስራት የሚችልበትን የወጣትነት ዘመኑን ገንዘብ ለሰዎች ምክንያታዊም ሆነ ኢ-ምክንያታዊ በሆነ ምክንያት ሲያድል ከነበረ ከነባራዊው የኑሮ ትግል ቤተሰቡንም እራሱንም መጣሉ አይቀርም! ሰው መርዳት መልካም ሆኖ ሳለ እኔ የቆረቆዝኩት ለመስጠት ቅድሚያ በመስጠቴ ነው! የሚለው አባባል ትክክለኛ ሊሆን አይችልም!
#ለምሳሌ፡- በትጉነት ዘመን እየሰሩ ትጋታቸው ወደሚታይ ሃብትነት እስካልተለወጠ ድረስ "ሃብቴ የሰው ፍቅር ነው! የኢትዮጲያ ህዝብ ነው ሃብቴ" የሚሉ አባባሎችን የሚጠቀሙ ሰዎች በአብዛኛው የሰነፍ መልሶች እንደሆኑ ይሰማኛል፡፡ ለአስቤዛም ሆነ ለህክምና አዋጡልኝ ብሎ ህዝብን ማስቸገር ሰርቶ ከመታከም እና ከመሸመት እኩል ሊሆኑ አይችሉም!
ተፈጥሯቸው ሆኖ ለሰው ሲሉ ዓለማቸውን የሰጡ ሰዎች ከዚህ በፊት ነበሩም አሁንም አሉ! ነገር ግን እነዚህ እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች የነባራዊው ዓለም የኑሮ ተዋናዮች መገለጫ ሊሆኑ አይችሉም!
ማህበረሰባችን ውስጥ "ያለኝን ለሰዎች ባላካፍል ኖሮ ዛሬ የት ነበርኩ!?" የሚሉትም "ያለውን ለሰዎች ሲበትን ኖሮ እንጂ ቢያውቅበት ኖሮ ዛሬ የት ይደርስ ነበር" የሚሉትም አሉ፡፡
በማህበራዊ ኢኮኖሚክስ አስተምሮት ውስጥ ሊኖራችሁ የሚገባው ግንኙነት ዋጋ ያለው እንዲሆን ይመከራል፡፡ በማህበራዊ የሰዎች እድገት ደረጃ ውስጥ ከሰዎች በምትክ የሚገኝ ምንም ምላሽ ሳይኖር መርዳት የመጨረሻው ደረጃ በመሆኑ ብዙዎቻችን ባለንበት ደረጃ በመደጋገፍ ውስጥ ምላሽ ተጠባቂ ነው፡፡
በየሰፈሩ ለታመመ፤ ለወለደ፤ ላዘነ እና ለተደሰተ የሚደረግ መዋጮ ስም ዝርዝር ይጻፍበትም አይጻፍበትም በሆነ ጊዜ ሰዎች በምትኩ ምንም አይጠብቁም? በገንዘብ ባይሆን እንኳ በድርጊት መልስ ይጠብቃሉ "ሃዘኔ/ደስታዬ ላይ ሳይገኝ!" የሚሉ መልሶች ትርጉም አላቸው፡፡
ከወዳጆቻችሁ ወይም ጓደኞቻችሁ መካከል ስንቶቹ ናቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ብትገቡ ዋስትና የመሆን ፍላጎትም ሆነ አቅም ያላቸው?
#ለምሳሌ፡- የ100ሺ ብር ዋስትና ብትጠየቁ ዋስ መሆን የሚችሉም የሚፈቅዱም ምን ያህል ጓደኞች ፈጥራችኋል? እንድትለወጡ የእውነት ከልባቸው የሚጥሩ ወይም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ብትገቡ በምክርም በጉልበትም ስንቶቹ በጽናት ከናንተ ጋር ይቆማሉ?
ስልኮቻችሁ ውስጥ የተደረደሩ ሰዎችን ዋጋ መዝኑ እና ጊዜዎቻችሁን/ገንዘባችሁን የምታጠፉላቸው ሰዎችን ዋጋ መዝኑ! የብዙ ሰዎች ጓደኛ መሆኑ ለአስቤዛ መተማመኛ ካልሆነ በግንኙነት መካከል በብዙ መለኪያ መስፈርት ማውጣት ግድ ነው፡፡

በሁለት ዓመት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ጦርነት ውስጥ መግባታችን አይደለም ሌሎች እያደረጉ ባሉት ጦርነት (ራሽያ እና ዩክሬን) ኢኮኖሚያችን ብዙ እየተፈተነ ነው!
የምትኖሩት ኑሮ #ዋናውን ነው?
ልጅ እያለሁ እናቴ የነበረንን ጥሩ #ብርድ_ልብስ ለሙቀትም ሆነ ለምቾት እናውጣው ስላት ለክፉ ቀን ነው የተቀመጠው ትለኝ ነበር!
አንዳንድ ቤተሰቦች ቤት ጥሩ ሰሀን፤ ሲኒ፤ ብርጭቆ፤ መጥበሻ፤ ወዘተ በብፌ ውስጥ ተቆልፎበት በተጣመመ ሰሀን መመገብ፤ በተሸረፈ ሲኒ መጠጣት ልምድ ነው።
አንዳንዶች ጋር ልብስ ሳይቀር ቀን እየጠበቀ ቁም ሳጥን ውስጥ ተንጠልጥሎ በዓመት አንዴ ብቻ ሊለበስ ይችላል (በዓመት አንዴ ሲዘንጥ ለራሱም ለሌሎችም እንግዳ ይሆናል!)።
የተለያዩ የኢኮኖሚክስ አስተምሮቶች ውስጥ የሰዎች ህይወት ወደ ፊት ባሉ ቀናት እንደሚመጣ ነው የሚመስሉት!
በኢኮኖሚክስ ቁጠባ መሰረታዊ ምክር ነው! ስለዚህ ከወጪ ቀንሶ መቆጠብ ግድ ነው #ለምሳሌ፦ ከጥሩ ምግብም ሆነ መጠጥ መቀነስ፤ ጥሩ ከመልበስ መቀነስ፤ ከመዝናናት መቀነስ፤ ወዘተ ማለት ነው።
አብዛኛው ኢኮኖሚያዊ ጥናቶች ገቢ ትዳር ከመያዝ እና ከልጆች ቁጥር ጋር ያለው ግንኙነት ቀጥተኛ ነው! #ለምሳሌ፦ ለመሰረታዊ ወጪዎች ገቢ ካልበቃ ትዳር ገቢው እስኪገኝ መቆየት አለበት የሚል ስሜት አለው! የልጆች ቁጥርም በተመሳሳይ።
#ለምሳል፦ ትዳር ለመያዝ፤ ልጅ ለመውለድ፤ ልጅ ለመድገም፤ ወዘተ መጀመሪያ ማሟላት ስለሚኖርባቸው ጉዳይ የሚያስቡ ሰዎችን የምትመለከቱት እድሚያቸው የደረሰ ቢሆንም #ወደፊት የሚል ቃል አለው!
#ለምሳሌ፦ ደሞዛቸው ዝቅተኛ ሆኖ ምንም ሳይኖራቸው ከሚበሉት ከሚጠጡት ቀንሰው ከ4 ዓመት በኋላ ትምህርቱ የተሻለ ገቢ አስገኝቶኝ #ወደፊት የምፈልገውን አደርጋለሁ የሚሉም አሉ።
#ለምሳሌ፦ ብዙዎች ለጡረታ ጊዜዬ በሚል ከመዝናናቱም ከሌሎቹም ቀንሰው #ወደፊት ለሚባለው Undefined ለሆነው ጊዜ ቅድሚያ ይሰጣሉ።
የዚህ አይነቱ አስተሳሰብ ሰዎች #ወደፊት እንዳሉ ማሰባቸውን ያሳያል! የኢኮኖሚክስ አስተምሮቶችም ሰዎች እና ድርጅቶች #ዛሬ የሚያደርጉት ውሳኔ በሙሉ #ነገ እንዳለ በማመን ነው።
#ለምሳሌ፦ ገቢ ማሳደግ (Income Maximization)፤ ወጪ መቀነስ (Cost Minimization)፤ እርካታ መጨመር (Utility maximization) የሚሉ የኢኮኖሚክስ ሃሳቦች ከዛሬ በተሻለ ነገን እርግጠኝነት የጎደለው በመሆኑ ወደፊትን የሻለ ትኩረት ስለመስጠት ነው።
ይህንን አስተምሮት እየተከተሉ ከሆነ ግለሰባዊ ግብ እና ከተለመደው ማዕቀፍ የዘለለ ነገር ሊኖር እንደሚችልም ማሰብ ተገቢ ነው።
#ለምሳሌ፦ በሰፈራችሁ ወይም መስሪያቤታችሁ "ያሰኘውን ሳይበላ!፤ እንደጓደኞቹ ደህና ልብስ ሳይለብስ እና በስራ ተወጥሮ አንድ ቀን ሳይዝናና ሞተ!" የተባለ ሰው አላጋጠማችሁም?
ጥያቄው ወደፊት መቼ ነው? ደግሞ ችግሩ ይህ ወደፊት መቼ እንደሆነ አለመታወቁ ነው!
የመኖሪያ እድሜ ጣሪያን ያለፈ ጎልማሳ ወደፊትን ማስቀደሙ አይቀርም! አዛውንቶችን ጠጋ ብላችሁ አውሯቸው ለወደፊት ሲሉ ዛሬ የሚተውት ብዙ ነገር አላቸው።
አንዳንድ ሰዎች በሰራሁት ገንዘብ የተሻለ ካልተመገብኩ፤ የተሻለ ቤት ውስጥ ካልኖርኩ፤ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ሰውነቴን እና አዕምሮዬ ዘና እንዲል ካላደረኩ፤ ጥሩ ስሜት የሚፈጥርልኝን ንፁህ እና አዲስ ልብስ ካለበስኩ፤ ወዘተ ህይወቴን መቼ እኖራለሁ ይላሉ።
አንዳንዶች እኔን ጨምሮ እየኖርኩ ያለሁት እና ይበልጥ ዋጋ የምሰጠው #ለዛሬ ነው ነገር ግን የዛሬ ምቾቴ በቀጣይ ጊዚያትም እንዳላጣው ስለወደፊት ማሰብም መዘጋጀትም ያስፈልጋል በሚል የሚኖሩ አሉ።
ዋናው ጉዳያቸው ወደፊት እንደሆነ በአመለካከትም ሆነ በተግባር የሚያምኑ ሰዎች ዛሬ እየኖሩ ያሉት ለመጪው ዋና ህይወታቸው ዝግጅት እንደሆነ ያስባሉ።
ወደፊት የሚለው ጊዜ ግብ ወይም መስፈርት ከሌለው ግልፅ ስለማይሆን ሰውየውን ህይወቱን ሙሉ እንደደካማ እየቆጠረ እንዲኖር ሊያደርግ ይችላል።
#ለምሳሌ፦ ትዳር የምመሰርተው ቤት እና መኪና ሲኖረኝ ነው ያለ ሰው በ40 ዓመቱ ቤትም መኪናም አግኝቶ በ45 ዓመቱ ቢያገባ እና ቢወልድ ልጁ 18 ዓመት ሲሞላው Already አዛውንት ሆኗል (63 ዓመት)!
በ30 ዓመቱ አባት ሆኖ ቢሆን የ48 ዓመት ጎልማሳ እና የ18 ዓመት ወጣት መዝናኛ ቦታ ቢሄዱ ጨዋታቸው ተቀራራቢ ይሆን ነበር! ዛሬውን እየኖረ ወደፊቱን ማሰቡን ባያቆም እንደማለት ነው!

የጦርነት ተፅዕኖ በሚወስደው ጊዜ እና በሚሸፍነው የቦታ ስፋት የሚወሰን ቢሆንም #ተደጋጋሚ_ጦርነት ኢኮኖሚ ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ ይህንን https://youtu.be/oCxzWm9J0wY ቪዲዮ አዘጋጅቻለሁ ተመልከቱት!
YouTube
ጦርነት እና ኢኮኖሚ| War and Economy
የጦርነት ተፅዕኖ በሚወስደው ጊዜ እና በሚሸፍነው የቦታ ስፋት የሚወሰን ቢሆንም #ተደጋጋሚ_ጦርነት ኢኮኖሚ ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ ይህንን ቪዲዮ አዘጋጅቻለሁ ተመልከቱት!
የመስከረም ወር ለቤተሰቦች ከፍተኛ የወጪ ዝርዝር ያለበት አስጨናቂ ወር ነው! መስከረም ወር መግቢያ ላይ የወጪ ዝርዝሩ የሚዛነፍ ቤተሰብ ለተከታታይ ወራት ወደ ጤነኛ የወጪ መስመር ለመምጣት ስለሚቸገር ምን ያድርግ?
https://youtu.be/y_OmiG_fUYg
https://youtu.be/y_OmiG_fUYg
YouTube
የመስከረም ወር ለቤተሰቦች አስጨናቂ ወር ነው! Household expenditure in Ethiopia!
አንድ ሰው ሲመክረኝ "የቤተሰቦቼ ጊቢ ውስጥ አንድ ክፍል ቤት ሰርቻለሁ፤ ኮንደሚኒየም ቤት ደርሶኝ እዳውን ለመክፈል ብዙ ቢቀረኝም ለማደስ የሚስቴ ወንድም እያገዘኝ ነው!" አለኝ "እና ለልጆች አንድ ቋሚ ነገር ለማድረግ መጣር ግድ ነው ሲል ሊመክረኝ ሞከረ!
እድልን ተሞርኩዞ እንደ ውጤታማ ትጉ ሰው ሌሎችን ለመምከር መሞከር ሙሉ አይደለም!
የቤተሰቡ ግቢ ያለው ቤት ካኮረፉት የሚያባርሩት! በእድል እጁ የገባው ኮንደሚኒየም ቤት እዳውን ከፍሎ መጨረስ ካለመቻሉ በተጨማሪ ለዓመታት ለማደስ እንኳን የሚስቱን ወንድም ችሮታ እየጠበቀ ነው።
ውጤታማነት መለኪያው የተዛባ መሆን የለበትም! እድል አንድ ጥሩ ነገር ነው (ግን እሴት ካልተጨመረበት ለሌሎች እንደ ብቃት ሊቆጠር አይችልም) በተመሳሳይ ካደረጉት ባልተናነስ ያደርጉት የነበረን ክፍተት ማየትም ተገቢ ነው!
ባጠራቀመው 300ሺ ብር Ph.D የሰራ ሰው እና ባጠራቀመው 300ሺ ብር ገጠር ላይ መሬት የገዛ ሰው ለተሞክሮ ቢቀመጡ ስለሆነ ጥረት ስለተጨመረ እድል ሊለዋወጡ ይችላሉ።
በርግጥ በኢኮኖሚክስ አስተምሮት ውስጥ ይዞ መገኘት እንጂ ይዘው የተገኙበት መንገድ ዋጋ የለውም! ብዙ አትርፍ እንጂ ህጋዊ መንገድ ተከትለህ ተገቢውን ብቻ መጠን አትርፍ የሚል ግልፅ መርህ የለም!
በሎተሪ እድል 10 ሚሊየን ብር ያገኘ ሰው እድለኛ ነው! ነገር ግን ውጤታማ የሚሆነው ገንዘቡን ማባዛት ሲችል ነው! ስለዚህ ሌሎችን መምከር መጀመር ያለበት ያገኘሁትን ብር እዚህ ደረጃ ላይ አደረስኩት እያለ መሆን አለበት።
ስኬት ዘርፈ ብዙ ነው! ሰዎች ህይወትን የሚጀምሩት እኩል ላይሆን ይችላል (የሃብታም ልጅ ከውርስ ቢነሳ እና የድሃ ልጅ ታናናሽ ወንድሞችን ከማሳደግ ቢጀምር እንደማለት ነው) ስለዚህ ውጤታማነት አሳማኝ እንዲሆን በየአጋጣሚው የሚያገኙት እድል ላይ የጨመሩትን ውስን ጥረት ማሳየት አለበት ባይ ነኝ።

ዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የባንክ ዘርፍን #ለውጭ_ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል።
የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ የዘርፉን አገልግሎቶች በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፣ የአገራችን ኢኮኖሚ ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ያለውን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪነት፣ ውጤታማነትና ቀልጣፋነት በመጨመር በቂ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር የሚያስችል ረቂቅ ፖሊሲ በዛሬው ዕለት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱ በፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በሥራ ላይ እንዲውል ተወስኗል።
የውጪ ባንኮች መግባት በባንኮች እና በኢኮኖሚው ላይ ሊኖረው የሚችለው እድል እና ስጋት ምንድን ነው? የኢትዮጵያ የፋይናንስ ገበያ እስካሁን ለውጪ ገበያው ክፍት አይደለም! ነገር ግን የውጪ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የማድረግ አዝማሚያ አለ! ስለዚህ የውጪ ባንኮች መግባትን ተከትሎ በሀገር በቀል ባንኮች እና በኢኮኖሚው ላይ ሊኖር ስለሚችለው እድል እና ስጋት ይህንን https://youtu.be/eQbkKnQOawI ቪዲዮ አዘጋጅቻለሁ ተከታተሉት።

የውጪ ባንኮች መግባት በኢኮኖሚው ላይ ሊኖረው የሚችለው እድል እና ስጋት! What to expect from foreign banks coming to Ethiopia?
የኢትዮጵያ የፋይናንስ ገበያ እስካሁን ለውጪ ገበያው ክፍት አይደለም! ነገር ግን የውጪ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የማድረግ አዝማሚያ አለ! ስለዚህ የውጪ ባንኮች መግባትን ተከትሎ በሀገር በቀል ባንኮች እና በኢኮኖሚው ላይ ሊኖር ስለሚችለው እድል እና ስጋት ይህንን ቪዲዮ አዘጋጅቻለሁ ተከታተሉት።
#መረጃ
ኢትዮጵያ በ2014 ከሁሉም ዘርፎች 22 ቢሊዮን ዶላር አግኝታለች፡፡
7.89 ቢሊየን ዶላር በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም አለም አቀፍ ተቋማት በኩል የመጣ።
4.12 ቢሊየን ዶላር ከሸቀጦች ወጪ ንግድ የተገኘ፤ 3.31 ቢሊየን ዶላር ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የተገኘ እና 6.3 ቢሊየን ዶላር ከአገልግሎት ዘርፍ የተገኘ ሲሆን የተቀረው ከሌሎች ምንጮች የተገኘ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በ2014 ከውጪ ሀገር ምርቶችን ሸምቶ ለማስገባት 18.1 ቢሊየን ዶላር አውጥታለች በተጨማሪም ከውጪ ለተሸመተ አገልግሎት 4.9 ቢሊየን ዶላር አውጥታለች።
#መረጃው፦ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር፤ የፋይናንስ ሚኒስትር እና የብሄራዊ ባንክ ነው!
#ለማስታወስ፦
Balance of payment፦ ኢትዮጵያ እንደመንግስት፤ እንደግለሰብ እና እንደተቋም የተወሰደ ብድር እና የተደረገ ክፍያን፤ ከውጪ ንግድ የተገኘ እና ከውጪ ለተሸመተ የሚደረግ ክፍያ፤ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ግኝት እና ክፍያ፤ ወዘተ ያጠቃልላል!
Trade balance፦ ከኢትዮጵያ ወደ ውጪ የተላከ (Export) ከውጪ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ (Import) ሲቀነስ ያለ ልዩነት ነው።
ስለዚህ ገቢ ከወጪ አነሰ ማለት በሀገር ውስጥ ከነበረ የውጪ ምንዛሬ ክምችት ወይም በብድር የተደረገ ግዢ/ክፍያ አለ ማለት ነው።

የኢትዮጲያ የወጪ ንግድ አፈጻጸም!
በ2014 ኢትዮጲያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያገኘችው እንዴት ነው?
የኢትዮጲያ ጠቅላላ ወደ ውጪ የተላኩ ምርቶች መጠን እና የዓለም አቀፉ ገበያ ዋጋ ሁኔታ የኢትዮጲያ Export ገቢ እና Import ወጪ መጠንን እንዴት እንደወሰኑት የብሄራዊ ባንክ፤ የገንዘብ ሚኒስትር እና የሲቨስ ሪፖርት ዳሰሳን ትንታኔ https://youtu.be/xZ8OVyvhGdM አቅርቤላችኋለሁ እስከመጨረሻ ተከታተሉት፡፡

የኢትዮጲያ የወጪ ንግድ አፈጻጸም! Ethiopian Foreign Trade Performance 2022!
የኢትዮጲያ ጠቅላላ ወደ ውጪ የተላኩ ምርቶች መጠን እና የዓለም አቀፉ ገበያ ዋጋ ሁኔታ የኢትዮጲያ Export ገቢ እና Import ወጪ መጠንን እንዴት እንደወሰኑት የብሄራዊ ባንክ፤ የገንዘብ ሚኒስትር እና የሲቨስ ሪፖርት ዳሰሳን ትንታኔ አቅርቤላችኋለሁ እስከመጨረሻ ተከታተሉት፡፡
አጠቃላይ ሰነዱን ለማንበብ:- Telegram:- https://t.me/wasealpha

በ2014 ጠቅላላ የውጪ ንግድ (Export and Import) ሪፖርት
የውጪ ንግድ (Export)፡- የኢትዮጲያ የውጪ ንግድ 4.1 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን ከባለፈው አመት የ600 ሚሊየን ዶላር ጭማሪ አለው፡፡ የውጪ ንግድ ግኝት 20 % ያድጋል ተብሎ የታቀደ ቢሆንም በ14 % ጭማሪ ያለው ግኝት ተገኝቷል፡፡
ወደ ውጪ የተላኩ ቁሳቁሶች የደረሱበት ሀገር ድርሻ ሲታይ ሲዊዘርላንድ 13%፤ ኔዘርላንድ 9%፤ አሜሪካ 9% ድርሻ፤ ሶማሊያ 8%፤ ሳውዲ አረቢያ 7% እና ጀርመን 7% በመሸመት ቀዳሚ ሲሆኑ በጠቅላላ ኢትዮጲያ ከ30 በላይ ለሆኑ የዓለም ሀገራት ምርቶቿን ልካለች፡፡
ከ2013 የውጪ ንግድ አንጻር በ2014 የተገኘው የ600 ሚሊየን ዶላር ጭማሪ ምክንያት የጎረቤት ሀገር ሶማሊያ የጫት ፍላጎት ማደግ (27%)፤ ጀርመን ለቡና ያላት ፍላት ማደግ (24%) እና ኔዘርላንድ ለአበባ የነበራት ፍላጎት ማደግ (19%) የፈጠረው ነው (እነዚህ ሶስት ሀገራት ያላቸው ፍላጎት ማደግ 70% የኢትዮጲያ የውጪ ንግድ እንዲያድግ አግዟል)፡፡
ወደ ውጪ የተላኩ ምርቶች ዝርዝር ሲታይ ቡና (1.4 ቢሊየን ዶላር)፤ ወርቅ (546 ሚሊየን ዶላር) እና አበባ (544 ሚሊየን ዶላር) ድርሻ አላቸው በድምሩ ሶስቱ ምርቶች ብቻ ከጠቅላላው ግኝት የ60% ድርሻ አላቸው፡፡
ወደ ውጪ የተላኩ ምርቶች መጠን ሲታይ ወደ ውጪ ከተላኩት መካከል ቡና በ57%፤ ስጋ በ45% ፤ ፍራፍሬ በ27% እና ጨርቃጨርቅ በ19% ወደ ውጪ የተላከው ከ2013 አንጻር እድገት ሲኖራቸው በተቃራኒው የቅባት እህል እና ጥራጥሬ በ26%፤ ወርቅ በ16% እና የቆዳ ውጤቶች በ9% ከ2013 አንጻር የቀነሰ ምርት ወደ ውጪ ተልኳል፡፡ ለውጪ ገበያ ከሚቀርቡ 18 ምርቶች መካከል 10 የሚሆኑ ምርቶች ጠቅላላ አቅርቦት በ2014 ዝቅተኛ ሆኗል፡፡
ይህ የሚያሳየው የውጪ ምንዛሬ ግኝት እድገቱ የተገኘው ከፍተኛ መጠን ያለው ምርት በመላክ ሳይሆን በዓለም ገበያ የመሸጫ ዋጋዎች በመጨመራቸው ነው፡፡ #ለምሳሌ፡- የቡና መሸጫ ዋጋ በዓለም ገበያ በ30% አድጓል፡፡ የውጪ ንግድ አፈጻጸም መለኪያ ዋነኛው በየዓመቱ ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች መጠን እየጨመረ መሄዱ ቢሆብም ወደ ውጪ የሚላከው መጠን ቀንሶ የዓለም ገበያ ዋጋ በመጨመር የሚገኝ የትርፍ እድገት ውስን ድክመት አለበት፡፡
ቡና በከፍተኛ ሁኔታ በዓለም ገበያ ዋጋው በመጨመሩ የውጪ ግኝቱ ሲያድግ ጨርቃጨርቅ፤ አበባ እና ስጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጠናቸው በመጨመሩ የውጪ ምንዛሬ ግኝቱ እንዲያድግ ሆኗል፡፡
#ለምሳሌ፡- የAGOA ክልከላ የጨርቃጨርቅ ምርትን ለጥቂት ወር የቀነሰው ቢሆንም ቀድሞ የነበሩ ትዛዞችን በመሸጥ፤ ከነታሪፉ በአሜሪካ ገበያ ማቅረብ የቻሉ አምራቾች መኖር እንዲሁም የጨርቃጨርቅ አምራቾች በአማራጭ የቻይና፤ የካናዳ እና የቱርክ ገበያዎች ላይ ሽያጭ መጀመራቸው መጠኑ እንዲያንሰራራ አድርጓል)፡፡
#ለምሳሌ፡- የአበባ ምርቶች ላይ አዳዲስ ማሳዎች መዘጋጀት እና ነባር የአበባ አምራቾች የማስፋፊያ ቦታ ማዘጋጀት (የአበባ ማሳዎች ስፋት በ12% ጨምሯል)፤ የማጓጓዣ ስርዓት መስተካከል እና የቀጠለ የአውሮፓ ሀገራት የአበባ ፍላጎት መኖር፤ ከአውሮፓ ውጪ ያሉ ሀገራት እንደ መካከለኛው ምስራቅ፤ እስያ እና አፍሪካዊያን የኢትዮጲያን አበባ ለመግዛት ያላቸው ፍላጎት በ19 % ማደጉ የአበባ ምርት መጠን በ2014 እንዲጨምር አድርጓል፡፡
#ለምሳሌ፡- የስጋ ምርት በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራ ያለው ፍላጎት ካለፈው ሁለት ዓመታት ወዲህ በማደጉ 67 ሚሊየን ዶላር ይገኝበት የነበረው መጠን በ2014 ወደ 100 ሚሊየን ዶላር ግኝቱ አድጓል፡፡
በ2014 ጠቅላላ 22.7 ቢሊየን ዶላር ከተለያዩ ምንጮች የውጪ ምንዛሬ የተገኘ ሲሆን የቁሳቁስ ሽያጭ 4.1 ቢሊየን ዶላር፤ የአገልግሎት ሽያጭ 6.2 ቢሊየን ዶላር፤ ሬሚታንስ 5.3 ቢሊየን ዶላር፤ FDI 3.2 ቢሊየን ዶላር፤ ብድር 1.1 ቢሊየን ዶላር (ብድሩ በመንግስት እና በመንግስት የልማት ድርጅቶች በጋራ የተወሰደ ነው) እና እርዳታ 1 ቢሊየን ዶላር ነው፡፡
ከ2013 አንጻር ለውጪ ምንዛሬ ግኝቱ መጨመር የቁሳቁስ ሽያጭ በ13% የአገልግሎት ሽያጭ በ21% እና ሬሚታንስ በ2% እድገት የነበራቸው ቢሆንም የመንግስት ብድር በ100 ሚሊየን፤ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ብድር በ900 ሚሊየን ዶላር እና እርዳታ በ300 ሚሊየን ዶላር ከ2013 አንጻር በ2014 ቀንሷል፡፡
በ2014 ጠቅላላ የተገኘ የውጪ ምንዛሬ 22 ቢሊየን ዶላር ቢሆንም ከውጪ የተሸመተው የ18 ቢሊየን ዶላር ወጪ ልዩነት 4 ቢሊየን ዶላር ያለፈ ሲሆን የ Balance of Payment ልዩነቱ በ2014ዓ.ም 2 ቢሊየን ዶላር ደርሷል፡፡ በ2013 ከነበረው የ2.9 ቢሊየን ዶላር ልዩነት አንጻር መሻሻል ያለው ሲሆን ክፍተቱን ለመሙላት የብሄራዊ ባንክ እና ከባንኮች ከነበረው ከጠቅላላ የውጪ ምንዛሬ ክምችት ተሸፍኗል፡፡
2014 ዓ.ም ሲጀምር የመንግስት የውጪ ምንዛሬ ግኝት እቅድ 5.4 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ ቢሆንም የተሳካው 4.1 ቢሊየን ዶላር ነው፡፡ ይህም ግኝት የተገኘው የቡና እና የወርቅ ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ በከፍተኛ ሁኔታ ስለጨመረ (#ለምሳሌ፡- የኢትዮጲያ ቡና ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ ከ2013 አንጻር በ25% ጨምሯል) አንዲሁም የአበባ እና የፍራፍሬ ምርት መጠን መጨመር ለግኝቱ አስተዋጾ አድርጓል፡፡ #ለምሳሌ፡- የጫት አቅርቦት በ21% ቢቀንስም በዓለም አቀፍ ገበያ (ጅቡቲ) ያለው የጫት ዋጋ በ23% በመጨመሩ የመቻቻል አይነት አዝማሚያ አለው ማለት ነው፡፡
የውጪ ንግድ (Import)፡- በ2014 ኢትዮጲያ ከፍተኛ ሸቀጦች ከውጪ ሀገራት ሸምታለች፡፡ በ2013 ከነበረው 14.2 ቢሊየን ዶላር በ2014 ወደ 18.1 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሸመታ አድርጋለች ይህም ላለፉት 10 ዓመታት ከነበረው የእድገት ትሬንድ አንጻር በ27% ጨምሯል፡፡
ኢትዮጲያ የሸመተችባቸው ሀገራት ስብጥር ስንመለከት፡ ቻይና 18% ድርሻ እና ህንድ 15% ድርሻ ይዘው ቀዳሚዎች ላኪ ሀገራት ሲሆኑ የተባበሩት አረብ ኢምሬት፤ ሳውዲ፤ ኪዌት፤ ቱርክ እና አሜሪካ እያንዳንዳቸው ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ ቁሳቁስ ወደ ኢትዮጲያ ልከዋል፡፡
ኢትዮጰያ ከውጪ ላስገባቻቸው ቁሳቁሶች ወጪ መጨመር አንዱ ምክንያት ከፍተኛ የዓለም አቀፍ ዋጋ መናር ነው፡፡ #ለምሳሌ፡- የነዳጅ ዋጋ በ83%፤ የእህል ዋጋ በ63% እና የአፈር ማዳበሪያ ዋጋ በ98% ዋጋቸው ንሯል፡፡ ዋና ዋና ወጪዎች ሲታዩ ነዳጅ 3.3 ቢሊየን ዶላር ወጪ፤ እህል 2.2 ቢሊየን ዶላር ወጪ እና የአፈር ማዳበሪያ 1.4 ቢሊየን ዶላር ግዢ ተከናውኗል፡፡ እነዚህ ግዢዎች በሙሉ የተከናወኑት በመንግስት ነው፡፡
የግል ሴክተሩ ሸመታዎች በአብዛኛው በ2014 ቀንሰዋል፡፡ #ለምሳሌ፡- የማምረቻ ግብዓት ግዢ በ22%፤ መኪኖች በ17% እና የግል መጠቀሚያዎች በ1% ከ2013 አንጻር ቀንሰዋል፡፡ ይህ የሚያሳየው ሸመታዎች ምርት እና ምርታማነት ማሳደግ ያለባቸው የ Capital goods ላይ ሳይሆን ወደ ሌሎች ቁሶች ላይ ያዘነበለ ነው፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ ምክንያቶች ለግል ሴክተሩ የቀረበው የውጪ ምንዛሬ አናሳ በመሆኑ በግል ሴክተሩ የተደረገ ሸመታ ድርሻ ቀንሷል፡፡ #ለምሳሌ፡- የግብርና እና የማኒፋክቸር ተቋማት የማምረቻ ግብዓቶች (Capital goods) ሸመታ ከ2013 አንጻር በ1 ቢሊየን ዶላር ያህል ቅናሽ አላቸው፡፡ በርግጥ የውጪ ሸመታ መጠን ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት አንጻር ሲታይ ከነበረበት 13% ወደ 16% አድጓል፡፡

Ethiopia Trade Review--2021-22.pdf
2.7 MB
መረጃው ከብሄራዊ ባንክ፤ ከፋይናንስ ሚኒስትር ተሰብስቦ በሲቨስ የጥናት ተቋም የተጠቃለለ ነው፡፡ ሰነዱን ለማንበብ ለምትፈልጉ ሰዎች ከታች አስቀምጫለሁ፡፡
ለአዲስ ዓመት ስታቅዱ! #የሚለካ እና #ያልተጋነነ አድርጉት!
በ2014 ዓ.ም የነበራችሁን ኑሮ ላለመድገም ወጥራችሁ ለመስራት፤ ድፍረት የተሞላባቸው የለውጥ ውሳኔዎችን ለማድረግ (ሱስ መቀነስ፤ ስራ መቀየር፤ የስራ መነሻ ብድር መውሰድ፤ ጓደኞች መለወጥ፤ ወዘተ ሊሆን ይችላል)፤ ማህበራዊ ግንኙነታችሁን ለማሳደግ (ከነበራችሁ ውሎ ከፍ ማለት፤ ከሰዎች ጋር ያላችሁን የግንኙነት ዋጋዎችን/ምክንያታዊነት መለየት፤ ለአዳዲስ የቢዝነስ ሃሳቦች ጆሮ መስጠት፤ ወዘተ ሊሆን ይችላል) እና ገቢያችሁን እጥፍ ለማድረግ (የመጨረሻ የጉልበት፤ የማህበራዊ እና የእውቀት አቅማችሁን መጠቀም፤ ትንንሽ ብሮችን ማክበር፤ ገንዘብ እስካስገኘ ምንም መስራት፤ ወጪን ምክንያታዊ ማድረግ፤ ወደ ገቢ መቅረብ፤ የቢዝነስ መረጃ መሰብሰብ፤ ወዘተ ሊሆን ይችላል)፡፡
ስለዚህ ወስኑ! ጻፉት! እና ዓመቱን ጀምሩ! ከነበራችሁበት ጥቂትም ቢሆን ከፍ ለማለት ካቀዳችሁ #የሚለካ አድርጉት! ለተለምዶ ሲባል የውሸት አታቅዱ (ማቀድ ጥሩ ልምድ ነው! ለተነሳሽነት ምክንያት መሆን ይችላል!)።
እኔ ውስብስብ እና የማይለካ እቅድ ኖሮኝ አያውቅም! ከላይ የጻፍኩት በየዓመቱ ማስታወሻዬ ላይ እጽፈው የነበረውን ነው፡፡ #ለምሳሌ፡- የዚህን ያህል ብር በዓመት ለማግኘት ብዮ አቅዳለሁ ለሱ አቅሜን አሟጥጬ መስራት ነው፡፡ የጻፍኩትን እቅድ በመጨረሻ ደምሬ ቀንሼ ውጤቱን የመለካት ልምድ አለኝ (ሁሉም ነገር ባይለካም ነገር ግን ከነበረበት መለወጡን አረጋግጣለሁ!)፡፡
ምን አልባት ከተሳካልኝ ስራ መቀየር፤ ምን አልባት ከተሳካልኝ ማግባት፤ ምን አልባት ከተሳካልኝ ልጅ መውለድ፤ ምን አልባት ከተሳካልኝ ቤት/መኪና መግዛት፤ ምን አልባት ከተሳካልኝ አዲስ ስራ መጀመር፤ ምን አልባት ከተሳካልኝ ውጪ ሃገር መሄድ፤ ወዘተ እቅድ መሆን አይችልም፡፡ እቅዱ በራሱ ለመሳካት የሌሎችን ሃይል የሚፈልግ ይመስላል፡፡
ምኞት ያላችሁን እና መፍጠር የምትችሉትን አቅም መነሻ በማድረግ ካልታቀደ ተስፋ እንድትቆርጡ ያደርጋል። ስለዚህ አሁን ባለኝ አቅም ምን ማድረግ እችላለሁ? እና የመጨረሻ በዙሪያዬ የሚኖርን የመጨረሻ አቅም አሰባስቤ ብጠቀም ምን ልሰራ እችላለሁ? የሚለውን በደንብ ለዩ!
#ለምሳሌ፡- አንድ ሰው እቅዴ በ2015 ዓ/ም የተሻለ ኑሮ ለመኖር የሚል በደፈናው ቢያቅድ ልክ ሊሆን አይችልም! የተሻለ ኑሮ፤ የተሻለ ስራ፤ የተሻለ ህይወት የሚል መለኪያ የለም፡፡ ካቀዳችሁ #የሚለካ እና #ያልተጋነነ አድርጉት!

የአዲስ ዓመት እቅድ!
የሚለካ እና ያልተጋነነ እቅድ እንዴት ማቀድ ይቻላል? 2014 የነበራችሁበትን ደረጃ ካላወቃችሁ በ2015 ስለ መሻሻላችሁ ማረጋገጥ እንዴት ትችላላችሁ? ይህንን በተመለከተ የተዘጋጀውን ቪዲዮ ይመልከቱ!
https://youtu.be/7O_facc23N8

የአዲስ ዓመት እቅድ! New Year Plan
የሚለካ እና ያልተጋነነ እቅድ እንዴት ማቀድ ይቻላል? 2014 የነበራችሁበትን ደረጃ ካላወቃችሁ በ2015 ስለ መሻሻላችሁ ማረጋገጥ እንዴት ትችላላችሁ? ይህንን በተመለከተ የተዘጋጀውን ቪዲዮ ይመልከቱ!
በኑሮ ውድነት ወቅት ወጪያችንን እንዴት ማስተካከል እንደምንችል ያቀረብኩላችሁን https://www.youtube.com/watch?v=_S2pGFeLZrkeLZrk ተመልከቱ!
YouTube
በዚህ የኑሮ ውድነት ወጪን መቆጠቢያ መንገዶች
#Wasyhunbelay
አዲስ አበባ ውስጥ #ባስ በመጠበቅ ከሚጠፋው ጊዜ በላይ #ባስ_ውስጥ ሆኖ በመንገድ መዘጋጋት የሚጠፋው ጊዜ እየበለጠ ነው!
የትራንስፖርት ሁኔታ የሰዎች መጓጓዝ ማለት ብቻ ሳይሆን የገንዘብ እና ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ፍጥነትን ይወስናል። ሰዎች በመንገድ መጨናነቅ መንገድ ላይ ዋሉ ማለት ከምርት ስርዓት ተቀነሱ ማለት ነው።
#ለምሳሌ፦ በአንድ ከተማ ውስጥ የመንገድ እንቅስቃሴን ለማስተካከል የትራንስፖርት አማራጮችን መጨመር፤ የመንገድ አማራጮችን ማስፋት ወይም የመንገድ እና የትራንስፖርት አጠቃቀም እና ስምሪትን ማስተካከል በተናጥል ወይም በአንድ ላይ ሊተገበሩ ይችላሉ።
ሁሉም አማራጮች ተገቢ ቢሆኑም በጣም የሚያዋጣውን መምረጥ ደግሞ ግድ ነው (Mitigate opportunity Cost)!
#ለምሳሌ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 110 አዳዲስ የአንበሳ አውቶቢሶችን 16.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ በማድረግ ሥራ አስጀመረ እንዲሁም በሚቀጥሉት ሦስት ወራት 250 አዳዲስ አውቶቢሶች ወደ አገልግሎት የሚገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል (ወጪው የአስተዳደሩ በጀት እና የዓለም ባንክ ድጋፍ ነው)።
በርግጥ ከአገልግሎት እየወጡ ያሉ በርካታ አሮጌ ባሶች ያሉበት ከተማ በመሆኑ አዳዲስ ባሶች ግዢ መደረጉ መጥፎ አይደለም! ለጉዳዩ ትኩረት ለመስጠት እና ለመወያየት ያህል የሚከተለው ጥያቄ ቢነሳ....
#ጥያቄው! ለአዲስ አበባ ከተማ ለትራንስፖርት ሁኔታው ተቀዳሚ መፍትሄው ተጨማሪ 360 ባስ ነው? ወይስ የተለዋጭ መንገድ ማስፋፋት እና የመንገድ አጠቃቀም ስርዓት ማበጀት? የሚለው ነው።
360ዎቹ ባሶች የመንገድ መስፋፋት ሳይኖር እና የመንገድ እና የትራንስፖርት አጠቃቀም እና ስምሪት ላይ ሳይሰራ ወደ ስምሪት ሲገቡ ተጨማሪ Opportunity Cost አለመፍጠራቸውን ማረጋገጥ ተገቢ ነው።
የበጀት እና የውጪ ምንዛሬ እጥረት ባለበት ኢኮኖሚ ውስጥ ወሳኙ ነጥብ የሚከናወኑ ስራዎች የሚኖራቸው ፋይዳ በጣም አሳማኝ እና ተቀዳሚ (Significant) መሆናቸውን ማረጋገጥ ነው።

"ለግል መገልገያ እንዲውሉ ወደ ሀገር የሚገቡ/የሚወጡ ዕቃዎች ሁኔታን የሚወስነው በሥራ ላይ ያለው መመሪያ (መመሪያ ቁጥር 51/2010) ለሕገ ወጥ ንግድ በር የከፈተ እና አገልግሎት አሰጣጡ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ በመሆኑ ዓለምአቀፍ አሠራሮችን በተከተለ አኳኋን መመሪያውን አሻሽል ማውጣት በማስፈለጉ" በሚል ምክንያት ለግል መገልገያ እንዲውሉ ወደ አገር የሚገቡ ወይም ከአገር የሚወጡ ዕቃዎችን ለመወሰን መመሪያ ቁጥር 923/2014 ከነሀሴ 12/2014 ጀምሮ ተፈፃሚ እንዲሆን በገንዘብ ሚኒስቴር የተሻሻለው መመሪያ ይፋ ወጥቷል፡፡
በቀደመው መመሪያ በርካታ የቁሳቁስ አይነቶች ወደ ሀገር ውስጥ ከቀረጥ ነጻ ለማስገባት የሚፈቅደው መመሪያ በተሻሻለው አዲሱ መመሪያ መጠኑን ወደሚከተለው ሰንጠረዥ አሳጥሯል፡፡ ሙሉ መመሪያውን ማንበብ ለምትፈልጉ ከታች አስቀምጫለሁ!