The Ethiopian Economist View
23.9K subscribers
321 photos
2 videos
131 files
675 links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
ዛሬ ከፓርቲዎች የምርጫ ክርክር ላይ አንድ አንጋፋ ፖለቲከኛ የመሬት ፖሊሲያቸው "በገጠር ሰፋፊ መሬት ካላቸው አርሶ አደሮች ላይ መሬት #በመቀነስ ለወጣቶች #ማደል ነው" ሲሉ ሰማሁ! የዚህ አይነቱ ፖሊስ ኢኮኖሚዊ አማራጭ መሆኑ እራሱ ጥያቄ ነው!
የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሚተገበሩ ሶስት ፕሮጀክቶች የሚውል የ907 ሚሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ አድርጓል።

200 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ውስጥ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚውል ነው።

500 ሚሊዮን ዶላር በሀገሪቱ ለሚከናወን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነት እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ካፒታል ተሳትፎንና ዘላቂ የፋይናንስ አማራጮችን ለማምጣት የሚያስችል ነው ፤ ከዚህ ውስጥ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚውለው የግሉ ዘርፍ በኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ እና አቅርቦት ተሳትፎ እንዲኖረው ለማስቻል ነው፡፡

207 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ የሚያስከተለውን ጉዳት ለመቀነስ እና የበሽታው መከላከያ ክትባቶችን ውጤታማ እና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንዲዳረስ ለማድረግ የሚውል ነው።

በአንድ ወር ውስጥ ምርጫ ለምታከናውን ታዳጊ ሀገር ቢሊየን የሚጠጋ ዶላር እርዳታ መፍቀድ የሚያሳየው የእርዳታ እና የብድር መሰረት ህዝብ መሆኑን ነው! ስለዚህ ከዚህ ቀደም እንደነበረው የእርዳታ ገንዘቦችን ከማባከን ወጥተን ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የአሁኑም ሆነ በቀጣይ መንግስት የሚሆነው አካል የቤት ስራ ነው!
#መደጎም_ያለበት_ሸማች_ወይስ_አምራች?
**
በዓለም ላይ መከራከሪያ ከሆኑ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዬች መካከል፡ የሸማቾችን አቅም የተለያዩ የድጎማ አይነቶችን በማድረግ የመግዛት አቅማቸውን ማሳደግ እና በገፍ ሸምተው የምርት ስርዓትም ጠቅላላ ኢኮኖሚው እንዲያድግ ማድረግ የሚል እና በሌላ መልኩ አምራቹን ክፍል በተለያዩ የድጎማ እና ማበረታቻ መንገዶች በማገዝ ከፍተኛ ምርት እንዲያቀርብ በማድረግ የኢኮኖሚውን እንቅስቃሴ ማሳደግ ይቻላል/ይገባል የሚሉት ናቸው!

#ለምሳሌ፦ ኮቪድን ተከትሎ የሸማቾች የመግዛት አቅም ተዳክሟል(የእንቅስቃሴ ገደብን ተከትሎ ተሯሩጦ መስራት ቀላል አልሆነም!) ስለዚህ አምራቾች ምርታቸውን የሚገዛቸው ሸማች በመቀነሱ ተጨማሪ ላለማምረት እና ሰራተኛ ለመቀነስ ተገደዋል! ተጨማሪ አለማምረታቸውን ተከትሎ የምርት እጥረት እና የዋጋ ንረት ተከስቷል! አሁን ጥያቄው ሸማቹ ተደጉሞ መሸመት ይቻል ወይስ አምራቹ ተደጉሞ ተጨማሪ ምርት ማምረቱን ይቀጥል የሚለው ነው!


ሸማች ከሚደጎምባቸው መንገዶች መካከል፦ ቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፤ ከቀረጥ ነፃ ምርትን ማስገባት እና ዋጋ እንዲቀንስ ማድረግ፤ ግብር በመቀነስ የመሸጫ ዋጋን ማስቀነስ፤ ወዘተ ሲሆኑ...

አምራች ከሚደጎምባቸው መንገዶች መካከል፦ የቀረጥ እፎይታ መስጠት፤ የግብር እፎይታ መስጠት፤ ቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፤ የብድር አቅርቦት ማድረግ፤ የብድር ወለድ ማራዘም/መቀነስ፤ የቦታ/የግብዓት ድጋፍ ማድረግ፤ ወዘተ ናቸው።

#ለምሳሌ፦ በሀገራችን ኮሮና የገባ ሰሞን ተቋማትን ለመደጎም በማለት 3ቢሊዮን ብር ለሆቴሎች በብድር እንዲቀርብ(ፍታዊ አጠቃቀም አልነበረም በሚል ቅሬታ ይነሳበታል!)፤ 15ቢሊዮን ብር ለባንክ ሴክተሩ የቀረበ ሲሆን እንዲሁም ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ ለአምራቾች እና ነጋዴዎች የግብር እፎይታ/ምህረት (ቫት እና ለጡረታ የሰበሰቡትን ገንዘብ ለመንግስት የማስረከቢያ ጊዜ ተራዝሞ በብሩ እንዲጠቀሙ ተደርጎም ነበር) ቀርቦ ነበር! ይህ አምራቾች ሰራተኛ እንዳይበትኑ እና ከኪሳራ እንዲያገግሙ ሲባል የተደረገ ድጎማ ሲሆን ሸማች ውስን መሰረታዊ ሸቀጦች ማለትም ስኳር፤ ዘይት፤ ስንዴ፤ ወተት፤ ሩዝ፤ ወዘተ ለ6 ወር ያለ ቀረጥ እንዲገባ በመፍቀድ የዋጋ ድጎማ ተደርጓል!(ለሸማች የታሰበው ድጎማ ተጨማሪ ችግር ማስከተሉ የሚታወስ ነው!)።

በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የአቅርቦት እና ፍላጎት ልዩነት ሰፊ ከሆነ መጥበብ የሚችለው በዋናነት አቅርቦትን በማሳደግ እንጂ ፍላጎትን በመቀነስ አይደለም ስለዚህ አምራች የሚበረታታ ከሆነ እና በቂ ምርት ከተፈጠረ የሸማች አቅም በተጋነነ መልኩ ባያድግ እንኳን የማምረቻ ወጪ መቀነስን ተከትሎ ዋጋ ስለሚወርድ ሸማች ባለው አቅም መሸመት ይችላል።

የአምራች የማምረቻ ወጪ ከፍተኛ ከሆነ የመሸጫ ዋጋ እየጨመረ መሄዱ ግልፅ ነው! ነገር ግን የማምረቻ ወጪን በመቀነስ ፋንታ የሸማች አቅም እንዲጨምር ቢደረግ በዝቅተኛ አቅርቦት ላይ የመሸመት አቅም ማደግ #የዋጋ_ግሽበት ይቀሰቅሳል እንጂ ፋይዳ የለውም።

በእኛ ሀገር ኢኮኖሚያዊ አቅም ሸማችም አምራችም እኩል እየተደጎሙ መቀጠል አይችሉም! ስለዚህ ለጊዜያዊ የኑሮ ውድነት ማስታገሻ ሸማች ሲደጎም ሁኔታው የረገበ ይመስላል እንጂ ውጤቱ ደካማ ነው! ነገር ግን ዘላቂ የገበያ መርህን በመከተል አምራቾች የማምረት አቅማቸው አድጎ ምርት እና ምርታማነት ካደገ ገበያው የተረጋጋ ሆኖ የመቆየት እድሉ ሰፊ ነው።

ስለዚህ መንግስት ጊዚያዊ መፍትሄ ጊዚያዊ ውጤት ብቻ እንደሚያመጣ በመረዳት የማምረት ስርዓት ላይ መሰረታዊ እርብርብ በማድረግ ገበያውን መታደግ ይገባዋል እላለሁ!
ኢትዮጵያ.....


#በአክቲቪስቱ፦ ተስፋዋን አሟጣ የጨረሰች!


#በባለስልጣናቱ፦ የተስፋ እቅፍ ውስጥ ያለች!


#በህዝቡ፦ ወደ አልተለመደ ሁኔታ ውስጥ እየገባች ያለች!


#በኢኮኖሚስቱ፦ ለትንበያ ፍፁም እየራቀች ያለች!
#ብሄራዊ_ባንክ፦ አዲስ የብር ኖት ከተዋወቀ ጀምሮ 126 ቢሊየን አሮጌው ብር የተሰበሰበ ሲሆን 185 ቢሊየን አዲሱ የብር ኖት ተሰራጭቷል! እንዲሁም 7.2 ሚሊየን ህዝብ አዳዲስ አካውንት ከፍቷል! ይህም የተሳከ ነበር ብሏል!


ብር በመቀየር ሂደት ውስጥ አሮጌውን የብር ኖት መቀየር፤ አዳዲሶቹን የብር ኖቶች ማሰራጨት፤ አዳዲስ አካውንቶች እንዲከፈት ማድረግ እና የጥሬ ገንዘብ ገደብ ማስቀመጥ እንዲሳኩ ጠንካራ ስራ የሚጠይቅ መሆኑ እና መሳካታቸው ሀገራችን ከነበረችበት እና ካለችበት ሁኔታ አንፃር የሚበረታታ ነው!


ነገር ግን የብር ለውጥ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በብዙ ሀገራት እንደታየው የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ላይ ቀጥተኛ ጥቅም ስለማይታይ ጠንካራ ስራ ካሁን በኋላ ይጠበቃል!
ዛሬ የምርጫ ካርድ እንደምንም አገኘሁ! ጥሩ የኢኮኖሚ ፖሊሲን ከጥሩ የፖለቲካ አካሄድ ጋር ያጣጣመ የፖለቲካ ፓርቲ ካገኘው እሱን እመርጣለሁ! ነገር ግን ከጥሩ #የኢኮኖሚ_ፖሊሲ እና ከጥሩ #የፖለቲካ_አካሄድ እንድመርጥ ከተገደድኩ "ያለ መሰረት ቤት አይቆምም!" ስለዚህ አሻጋሪ የፖለቲካ አማራጭ ያለውን ፓርቲ አስቀድማለሁ!


በተረጋጋ ፖለቲካ ውስጥ ኢኮኖሚ በሂደት ሊዳብር ይችላል! ባልተረጋጋ ፖለቲካ ውስጥ ጥሩ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሽባ ነው የሚሆነው! ምርጥ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ኖሮት ደካማ የፖለቲካ አማራጭ ካለው መንግስት ይልቅ ጥሩ የፖለቲካ አማራጭ ኖሮት በሂደት የሚዳብር የኢኮኖሚ ፖሊሲ የያዘ መንግስት ቀላል ስጋት! አጓጊ እድል! እንደሚኖረው ይሰማኛል!
የዛሬው የብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ መግለጫ ምንም ስሜት የለውም! ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከወራት በፊት በምክር ቤት ቆይታቸው በድምፅ ያሰሙትን የኢኮኖሚ ጥረት እና ስጋት በፅሁፍ ቀጥታ ሳይጨምር ሳይቀነስ ብቻ ነው የቀረበበት!
ስራ አጥነት ከፍተኛ ሆኖም ስራ ፈላጊ ቀንሷል!
ታዋቂው "The Economist" መፅሔት በትናንትናው ዕለት አንድ ጥናት ይዞ ወጥቷል! በጥናቱ እንደሚያሳየው በአሜሪካ ኮሮናን ተከትሎ ስራ አጥነት ከፍ ባለበት ባሁኑ ወቅት ድርጅቶች የሚቀጥሩት ሰራተኛ ማጣታቸውን የሚገልፅ ነው።

ተፈጥሯዊው የሆነው የኮቪድ ወረርሽኝ መሰረታዊ የሚባለውን እና የሚታወቀውን የኢኮኖሚክስ አስተምህሮት የሰራተኛ ፍላጎት እና አቅርቦት ያላቸውን ግንኙነት ቀይሯል! ምክንያቱም ስራ አጥነት ከፍተኛ ከሆነ የሰራተኛ ክፍያ (wage rate) ሊጨምር አይችልም! ነገር ግን አሁን ላይ ስራ ተትረፍርፎም ሆነ በሰዓት የሚከፈለው ክፍያ ጨምሮም የሚቀጠር ሰራተኛ ጠፍቷል (The pandemic has led to all sorts of weird economic outcomes!)።

#ለምሳሌ፦ በBloomberg ዘገባ መሰረት በያዝነው ወር ብቻ በሰራተኛ እጥረት የዴልታ አየርመንገድ (Delta Air Lines) 100 በረራዎችን ሰርዟል። በተመሳሳይ በሰራተኛ እጥረት ምክንያት ሮቦቶችን መጠቀም የጀመሩ ካፌዎች ከመኖራቸው ጀምሮ እንደ McDonald አይነት ድርጅት የክፍያ መጠኑን በ50% አሳድጎም ሰራተኛ ማግኘት ቀላል አልሆነም።

ከታች በምትመለከቱት የማክዶናልድ ክፍት የስራ ማስታወቂያ በሰዓት የሚከፈልን ደሞዝ አሳድጎም፣ ለሰራተኛ ነፃ የምግብ አቅርቦት አለን ብሎም ሰራተኛ ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን ጥናቱ ያሳያል።

ለተፈጠረው የሰራተኛ እጥረት 3 ምክንያቶች የተጠቀሱ ሲሆን እነሱም.....

#አንደኛ፦ የአሜሪካ መንግስት ኮሮናን ተከትሎ ለዜጎች ያደለው የድጎማ ገንዘብ ከፍተኛ መሆን (over-generous benefits) ዜጋውን ስራ ጠል አድርጎታል ይላል (አንዳንዶች በስራ ዓለም እያሉ ከሚያገኙት ደሞዝ በላይ በድጎማ ማግኘት ጀምረዋል!) ኮቪዱ ተከስቶ የስራ አጥነት ድጎማው የጀመረ አካባቢ ይቀርብ የነበረው ድጎማ በወር 600 ዶላር ብቻ ስለነበር የስራ ገበያውን የዚህን ያህል አልጎዳውም ነበር፣ ነገር ግን በዚህ ወቅት በሳምንት ስራ አጥ ለሆነ አሜሪካዊ 300ዶላር (በወር 1200 ዶላር) ይሰጣል! ይህ ደግሞ ለስራ ያላቸው ተነሳሽነት ቀንሶታል።

#ሁለተኛ፦ የኮሮና ቫይረስን ፍራቻ (fearful workers) ብዙዎች በስራ ቦታዎቻቸው ላይ መገኘት አይፈልጉም (በዚህ ወቅት 4 ሚሊየን አሜሪካ በሽታውን ፈርቶ ስራ ከመስራት ተቆጥበዋል) ይላል።

#ሶስተኛ፦ ኮሮና ያጠፋቸው ብዙ ስራዎች ከመኖራቸው ጋር ተያይዞ ሰዎች ቅድሚያ ይሰሩት የነበረውን ስራ ቢያጡም (a reallocation of labour between industries) ሌላ አይነት የስራ ዘርፍ ፈልጎ ለማግኘት መቸገር እና ፍላጎት ማጣት አለ ይላል! #ለምሳሌ፦ ኮሮና ከመምጣቱ በፊት የካፌ አስተናጋጅ የነበረ ሰው በአሁኑ ወቅት ከማስተናገድ ውጪ ያለ ስራ ለመስራት ፍላጎትም ሌላውን የስራ ዘርፍ በቀላሉ ማግኘት አለመቻል ክፍተቱን ፈጥሯል ይላል።
መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁንላችሁ!
#Blue_Economy
*
የዓለም ባንክ "የባህር እና የውቅያኖስ አካላትን በዘላቂነት ለሃብት ምንጭነት፤ ለስራ እድል እና የኑሮ ዋስትና አድርጎ የሚደረግ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሙሉ ሰማያዊ ኢኮኖሚ (Blue Economy) ይባላል" ይላል! ሰማያዊ የተባለበት ምክንያት የውቅያኖሶች መልክ የሰማይ ነጸብራቅ የሆነው ሰማያዊ ስለሆነ ነው ፡፡

#ለምሳሌ፡- ውሃን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት እና መጠቀም፤ የትራንስፖርት አገልግሎት (80 ከመቶ የሚሆነው ዓለም አቀፍ ቁሳቁስ የሚጓጓዘው በባህር ነው! #ለምሳሌ፡- መርከብን መጥቀስ ይቻላል)፤ የምግብ አቅርቦትን ማግኘት (በዓለም ላይ አሳ ብቻ በየዓመቱ ለጠቅላላው የዓለም ምርት ወይም GDP ከ270 ቢሊየን ዶላር በላይ ያዋጣል)፤ የመዝናኛ ቦታ አቅርቦት (በዓመት ከ41 ሚሊየን በላይ ቱሪስቶች የውሃ አካላትን መሰረት ያደረገ ጉብኝት ያደርጋሉ)፤ ውሃ የዓለምን የካርቦን ልቀት የማመጣጠን እና የምድርን ቁሻሻ የማጣራት ሚናቸው፤ ወዘተ ከፍተኛ ነው፡፡

#ለምሳሌ፡- በቅርቡ Ever Given በምትባለዋ ግዙፍ መርከብ ተዘግቶ የነበረው የግብጹ ሲዊዝ ካናል መተላለፊያ በቀናት ውስጥ ዓለምን ከ6 እስከ 10 ቢሊየን ዶላር በላይ ሃብት ሲያሳጣ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ዓለም አቀፍ ተቋማት የውሃ አካላትን ሃብት አውቆ መጠቀም ብቻ ሳይሆን ይህ አላቂ ሃብት እንዴት በዘላቂነት (Sustainability) መጠቀም እንደሚቻል ስትራቴጂ አውጥቶ መምራት እንደሚገባ የአውሮፓ ህብረት በ2020 የፖሊሲ አማራጭ አቅርቧል፡፡

ኢኮኖሚን ካላቸው ሚና አንጻር ስያሜ መስጠት የተለመደ ነው! #ለምሳሌ፡- የአካባቢን ጥበቃ መሰረት ያደረገ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን አረንጓዴ ኢኮኖሚ ወይም Green Economy ይሉታል፡፡
#ተበዳሪ_መንግስት_ከፋይ_ደግሞ_ህዝብ_ነው!
ምርጫ ለማድረግ ቀናት የቀረው መንግስት የውጪ ብድር መቀበሉ አዝማሚያው ምንድን ነው? ሲል አንድ ተከታይ ጠየቀኝ! ለጋሽም ሆኑ አበዳሪ የዓለም ሀገራት ለኢትዮጵያ ብድር ሲሰጡ ዋስትናቸው ህዝቡ ነው!(መንግስት ለመበደር በማስያዣነት "Collateral" የሚያቀርበው ደግሞ የሚያስተዳድረውን ህዝብ ነው!)። ምክንያቱም ስልጣን እና ባለስልጣናት ተለዋዋጭ ሲሆኑ ህዝቡ እየተተካካ እና ሀገር እንደነ #ሶሪያ እና #ሊቢያ በቀላሉ ሲጠፉ ስለማይታይ ጠንካራ ዋስትና ሆነው ለዘመናት የብድር ጫናን ተቀብለው ይቆያሉ!

#ለምሳሌ፦ ሀገራችንን እስከ አሁን ከ50 በላይ ሀገራት ሲያበድሯት ከንጉሳዊ ስርዓት እስከ ወታደራዊ አገዛዝ፣ ከወታደራዊ የርዕዮተ ዓለም ለውጥ እስከ ዛሬው አስተዳደር ድረስ ብዙ አስተዳዳሪዎች ቢለዋወጡም ህዝቡ እየተተካካ ኢትዮጵያ በሚለው ግዛት ስር ስላላ የብድር ዋስትና አጥታ አታውቅም።

ፈጣን የኢኮኖሚ አቅም ለመገንባት በተለይ የውጪ ትበብር በሚጠብቅ የእድገት እቅድ (Exogenous growth model) ውስጥ ላለች ሀገር የፋይናንስ ድጋፍን ከበለፀጉ ሀገራት በብድር እና እርዳታ አማካኝነት ማፈላለግ የውዴታ ግዴታ ነው። ነገር ግን ሀገራችን ትጉ ተበዳሪ እና ትጉ አባካኝ በመሆኗ ብድሯን በወቅቱ መክፈል እና በሚገባው ልክ ማቃለል አልቻለችም።

በዓለም ላይ በብዙ ተበዳሪ ሀገራት ውስጥ በተደረገ "ብድር ለኢኮኖሚ እድገት ያለውን ጥቅም" ለማወቅ በተደረጉ የጥናት ስራዎች መረዳት እንደተቻለው ብድር ለኢኮኖሚ እድገት የጠቀመበትም ሀገር አለ! በተቃራኒው ብድር ለኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ የሚባል ለውጥ ያላመጣበትም ሀገር አለ! በጥቅሉ የሚያመዝነው ግኝት ብድር #ለአጭር ጊዜ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ሲያመጣ #ለረጅም ጊዜ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ጠንካራ ማስረጃ አልተገኘም።

ሀገራችን ያሏት 110ሚሊየን ዜጎች ካበዳሪ ሀገራት ጋር ተደራድረው ሊበደሩ ስለማይችሉ! ሀገሪቷን እንዲያስተዳድሩ እድል ያገኙ መሪዎች ህዝቡን ወክለው ይበደራሉ! ስለዚህ በአጠቃቀም ወቅት ለሚከሰቱ ዘረፋዎች እና ውጤት አልባ ስራ የወቅቱ መሪዎች የጎላውን ሃላፊነት መውሰድ አለባቸው።

በዚህ ወቅት ሀገራችን ያለባትን የውጪ ምንዛሬ እጥረት ተከትሎ የኑሮ ውድነት ሰፊ በመሆኑ ይህንን ሸማች የሆነ ኢኮኖሚ ለመደገፍ የብድር አቅርቦት ማፈላለግ ተገቢ ቢሆንም በዚህ ወቅት የሚያስተዳድረው ፓርቲ የብድር ገንዘብን አጠቃቀም ብሄራዊ ተጠቃሚነትን ከግምት ከተው እንዲሆን ማሳሰብ ግን ግዴታ ነው።

በቅርቡ ቃል ሲገቡ በየሚዲያው የሚሰሙት ብድር እና እርዳታዎች ዜናው በተለቀቀ ቅስፈት ወደ ኢትዮጵያ ካዝና የሚገቡ ሳይሆኑ የፕሮጀክት አፈፃፀምን እየገመገሙ በሂደት የሚለቀቁ በመሆኑ አስተዳዳሪዎች በተቀያየሩ ቁጥር ፕሮግራሞችን ለማጠናቀቅ በመሞከር የቀጣይ የመበደር ዋስትናችንን ማስጠበቅ አለባቸው።

#ለምሳሌ፦ የአንድ ሀገር ብድር ያለመክፈል ቅጣት በቀጣይ ካበዳሪ ሀገራት ተጨማሪ መሰረታዊ ችግሮቿን ለመሸፈን የሚሆን ብድር እንዳታገኝ ክልከላ ማድረግ ነው! ይህ ደግሞ ለትምህርት፤ ለህክምና፤ ለሰብዓዊ የምግብ ድጋፍ፤ ለግብርና፤ ለነዳጅ፤ ወዘተ ያለ ወጪን መሸፈን መከራ ያደርገዋል።

#ለማስታወስ_ያህል፦ ሀገራችን የ50 ሀገራት እዳ (IMF፤ World Bank፤ EU፤ ወዘተ ሳይጨመሩ)፤ የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት(GDP) 55 ከመቶ የደረሰ እዳ (ግማሹን የተበደሩት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ማለትም ቴሌ፤ መብራት ሃይል፤ አየር መንገድ፤ ወዘተ ናቸው)፤ የሀገራችን GDP የ100 ቢሊየን ዶላር አቅም ካለው እዳችን 55 ቢሊየን ዶላር ነው ማለት ነው!.........የሀገራችን የውጪ እዳ ጫና አስጊ ደረጃ ላይ አልደረሰም ከሚሉት መካከል ነኝ!

እኔ ብድር በጥናት አዋጪ ለሆኑ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ሲወሰድ መልካም እንደሆነ ከሚያምኑት መካከል ነኝ! ምክንያቱም ግብርና ላይ መሰረቱን ለጣለ ኢኮኖሚ እና ፈጣን የህዝብ ቁጥር ባለበት ሁኔታ የCapital goods በማስገባት የኢንዱስትሪ ሽግግር ለማከናወን ብድር ከጠንካራ የፕሮጀክት አፈፃፀም ጋር ቢወሰድ መጥፎ አይደለም! ችግሩ የውጪ ብድር ለስራ ማስኪያጃ ወጪነት (#ለምሳሌ፦ ለባለስልጣናት V8 መኪና ለመግዣ ከዋለ) ግን ችግር ነው።
እየተከተልነው ባለነው የካፒታሊስት ስርዓት ውስጥ ላመረቱት ምርት ገበያ ማፈላለግ የአምራች ክፍሉ ብቻ የቤት ስራ አይደለም!

በ100 ኪ.ሜ ራድየስ እራሱን በ100% የሚጨምር የሽንኩርት ምርት የተቀናጀ የገበያ ትስስር በማጣቱ በምትመለከቱት መልኩ በገበያ በቅሎ ተበላሽቷል!

ይህ ሽንኩርት ማቀነባበሪ ቀርቶበት ራቅ ላለ ገበያ ቢጓጓዝ እንኳ ትርፉ ብዙ ነበር (የዘንድሮ ሽንኩርት ገበያን ዋጋ የተመለከተ አርሶ አደር ለቀጣይ ዓመት መተማመኛው ምንድን ነው?)።

ከ20 ቀን በፊት ከጎንደር እስከ ባህር ዳር ባሉ ማሳዎች አርሶ አደሩ በማሳው የደረሰ ሽንኩርት እየነቀለ ተመለከትን! ኪሎ 5 ብር በመሆኑ ተገርሜ ነበር! 100 ኪ.ሜ ሳይርቅ ባህር ዳር ስንደርስ ኪ.ሎው 3 ብር ነበር! በዛው ወቅት 500ኪ.ሜ በምትርቀው አዲስ አበባ በኪ.ሎ 15 ብር (500% ልዩነት) ይሸጥ ነበር።

ለባዕል መዳረሻ ይህንን ፎቶ ያጋራው ወዳጄ ዶ/ር ለጤናህ እጅጉ አንድ ኪሎ ቀይ ሽንኩርት 2.50 ደርሶ እንደነበር አጋርቶን ነበር! አሁን ደግሞ በአማራ ክልል አቡነሀራ ገበያ ገዢ ያጣው እና ዋጋው የወደቀው ቀይ ሽንኩርት በዚህ መልኩ ተደፍቶ አሳይቷል። የሽንኩርት ዋጋ ከኢኮኖሚያዊ አቅሙ በላይ መቀነስ በሌሎችም ክልሎች የነበረ ክስተት ነው!

ችግሩ መንግስት የቀይ ሽንኩርት ዘር አቅርቦትን ችግርን ፈታ! እሱን ተከትሎ በአርሶ አደሩ ማሳ የሽንኩርት ምርት ተትረፈረፈ! ነገር ግን ገበያ ማፈላለግ ላይ በቂ እገዛ ባለመደረጉ ሽንኩርት ተገቢውን ዋጋ አጣ!

የጓሮ አትክልት ምርት Seasonal በመሆኑ ወቅቱን የጠበቀ የዋጋ ማረጋጊያ ዘዴዎችን ማሰብ እና መጠቀም ይገባል።
በ9 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው የቡልቡላ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ዛሬ ተመርቋል!

ፓርኩ ለፈጣን መንገድ፤ ለሞጆ ደረቅ ወደብ እንዲሁም ለአዋሽ ወንዝ ያለው ተደራሽነት ጥሩ በመሆኑ ጠንክሮ ከተሰራ ለውጤታማነት የቀረበ ግዙፍ እና መሰረታዊ ችግራችንን እና ያለንን የግብርና ጥገኝነት የተገነዘበ ፓርክ በመሆኑ የሚያመጣልን እድል ሰፊ ነው!

ሀገራችን ያላት Comparative Advantage ግብርና መሆኑን ካመንን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ትኩረት ወደ ግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ እንዲያዘነብሉ ማቀድ ትክክለኛ ውሳኔ ነው።

ፓርኩ ከሌሎች መሰል የቀደሙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ያረመው ነገር ቢኖር በፓርኩ ዙሪያ የመኖሪያ ቤቶችን ማዘጋጀቱ በመሆኑ የሰራተኛ ፍልሰትን የመቋቋም እድሉ ሰፊ ነው!

አሁን ባለበት ሁኔታ 18ሺ ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ተገንብቶ ወደ ስራ ሲገባ 100ሺዎችን ይቀጥራል ተብሏል!

በሀገራችን #በሙሉ_አቅም ወደ ስራ መግባት እና በሙሉ አቅም ማምረት የሚሉት ጉዳዬች የማይታለፉ ፈተናዎች በመሆናቸው ይህ ቁጥር እንዲሳካ ጠንክሮ መስራት ግድ ነው!
ይህ ቀን መታሰቢያነቱ እዚህ ላደረሱን እናቶች በሙሉ ይሁን! እማዬ! መልካም የእናቶች ቀን!
ሀገራችን ከእንቅልፏ ነቃች! ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ባንኪንግ ስራ "ቴሌብር" በሚል መተግበሪያ ከዛሬ ጀምሮ ጀምሯል!


ድንቅ እርምጃ! በኢኮኖሚው የገንዘብ ዝውውርን ፍጥነት ስለሚጨምር ተንቀሳቃሽ 53 ሚሊየን አካውንት የከፈተ ደንበኛ እንዳለው አዲስ ባንክ ልንቆጥረው እንችላለን!


በአጠቃቀም ቀላል የሆነ እና በማንኛውም አይነት ሞባይል ምዝገባ በማከናወን ገንዘብ ተቀብለው በሚያስገቡ ኤጀንቶች (1500 ስራ የጀመሩ) በመገኘት ጥሬ ገንዘብ ወደ አዲሱ የስልክ አካውንት በማስገባት፤ ለሌሎች ማስተላለፍ እና ለተፈቀዱ አገልግሎትቶች ክፍያ መፈፀም ያስችላል።


ከሌሎች ቴሌብር ካላቸው ደንበኞች የተላከን ብር ከኤጀንቶች ኮዱን በማሳየት መውሰድ ይቻላል።


ሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ጅማሮ ላይ የነበሩ ባንኮች ኢትዮ ቴሌኮም ግዙፍ ተፎካካሪ ሆኖ የመጣ ስለሆነ አገልግሎት ዝምና ላይ ለማሰብ መገደድ አለባቸው!


ማህበረሰባችንን ከሞባይል እና ከፋይናንስ አገልግሎት ጋር የማስተዋወቅ ስራ በደንብ ከተሰራ ፋይናንስ ሴክተሩ ላይ ከተደረጉ ለውጥቶች መካከል ዋነኛው እና ውጤታማው እርምጃ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም!


በዓለም ላይ 69% የሚሆነው ህዝብ የፋይናንስ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ነው፣ ማለትም መቆጠብ የሚያውቅ፤ መበደር የሚያውቅ እና የኢንሹራንስ አገልግሎቶች የሚጠቀም ማለት ይህ ቁጥር በሀገራችን ከ35% አይበልጥም። በአለም ላይ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በ2001 የተጀመረ ሲሆን፣ በጠቅላላ አገልግሎቱን በሚሰጡ 310 ኤጀንሲዎች በቀን 2.1 ቢሊየን ዶላር፤ በወር 70 ቢሊየን ዶላር እንዲሁም በዓመት የ767 ቢሊየን ዶላር በላይ ዝውውር ይካሄድበታል (2020 መረጃ ነው!)። ሞባይል ባንኪንግ በአፍሪካ ከ2007 ጀምሮ አገልግሎቱ የጀመረ ሲሆን! በ2020 ከተደረገው 767 ቢሊየን ዶላር ዝውውር 60 ከመቶው በአፍሪካ ሲሆን ከዚህ ውስጥ በምስራቅ አፍሪካ ብቻ የ273 ቢሊየን ዶላር የዝውውር መጠን ነበረው።

ኢትዮ ቴሌኮም ይህንን አገልግሎት ካልጀመሩ 3 ብቸኛ የአፍሪካ ሀገራት አንዱ ነበር! ምክንያቱም የኢትዮጵያ የፋይናንስ ፖሊሲ ሞባል ባንኪንግን ለቴሌኮም ሴክተር የማይፈቅድ ስለነበረ ነው። ነገር ግን የቴሌኮም ሴክተሩ ለሁለት ዓለም አቀፍ ተቋማት በጨረታ ክፍት መሆኑን ተከትሎ ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ባንኪንግ/የፋይናንስ አገልግሎት እንዲሰጥ ተፈቅዷል!

ነገር ግን ከሌሎች የቴሌኮም ተጋባዥ ድርጅቶች ጋር ያለው ልምድ እና ተፎካካሪነት እስኪሻሻል አገልግሎቱ ለቀጣይ አንድ ዓመት ለኢትዮ ቴሌኮም ብቻ በመሰጠት (አዲስ የሚገቡት የቴሌኮም ድርጅቶች ገንዘብ ማዘዋወርን እንዲሰሩ አይፈቀድም! በመንግስት መረጃ ይህ ክልከላ ከ500 ሚሊየን ዶላር በላይ በጨረታ ወቅት ያሳጣን ነው!) ከዓመት በኋላ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት አዲስ ከሚመጡት የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ጋር ተደምሮ በሀገራችን 3 ድርጅት የሚያቀርበው ይሆናል።

ኢትዮ ቴሌኮም 53 ሚሊየን ሲም ካርድ የያዙ ደንበኞች በመላ ሀገሪቱ አለው! ከዚህ ውስጥ 23 ሚሊየኖቹ ኢንተርኔትን የሚጠቀሙ ሲሆን (44 ከመቶ የሚሆኑት ስማርት ፎን የያዙ ናቸው) ስለዚህ በቀጣይ አንድ ዓመት 21 ሚሊየን ደንበኞች ለቴሌብር አገልግሎት ቢመዘገቡ እና ከዛ ውስጥ 12.7 ሚሊየኑ አገልግሎቱን ቢጠቀሙ በዓመት ውስጥ ከ710 ሚሊየን ብር በላይ ማንቀሳቀስ ያስችላል። የድርጅቱ እቅድ በቀጣይ 5 ዓመት ውስጥ ከትርሊን ብር የዘለለ የገንዘብ እንቅስቃሴ ለማከናወን ነው።

#ለምሳሌ ፦ ኢትዮ ቴሌኮም የአየር ሰዓት የብድር አገልግሎት በመስጠት ብቻ በቀን 2 ሚሊየን ደንበኞች ሲበደሩ የነበረ ሲሆን 37 ሚሊየን ብር በቀን የሞባይል ካርድ ከቴሌ በመበደር እና በመሙላት ብቻ ሲያዘዋውር ነበር። ሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቱ በተለያዩ ቋንቋዎች በመጀመሩ እና ለአጠቃቀም ቀላል በመሆኑ ተደራሽ ለመሆን ፈጣን ይሆናል የሚል እምነት አለኝ! "*127#" በመደወል እና ስማርት ስልክ ላላቸው ደግሞ "Telebirr" በሚል መተግበሪያ መጠቀም ያስችላል።

በዓለም ላይ የቴሌኮም አገልግሎቶች ውስጥ 2/3ኛ የሚሆነው ትርፋቸው የሚገኘው ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በመሆኑ በትርፍ ደረጃ ቴሌኮሙ ተጠቃሚ ነው። ነገር ግን በሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚያስከፍለው ገንዘብ መጠን በጣም ወሳኝ ነው!

#ምን_አዲስ_ያደርገዋል? ባንኮች የሞባይል ባንኪንግ ስራ ጀምረው እየሰሩ አይደለ! ለሚለው የብዙዎች ጥያቄ፦ በሀገራችን መደበኛ የባንክ አካውንት ያለው ሰው ቁጥር ከ7.2 ሚሊየን አይበልጥም! ስለዚህ ባንኮች እስከዛሬ ካላቸው ደንበኞች በመነሳት የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ያቀርቡ የነበረው አነስተኛ ቁጥር ላለው ተገልጋይ ነው! የኢትዮ ቴሌኮምን ለየት የሚያደርገው ምንም አይነት የባንክ አካውንት የሌለውን የማህበረሰብ ክፍል በሲም ካርዳቸው ብቻ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ነው።

በተለያየ ምክንያት የባንክ አገልግሎት አይጠቀሙ የነበሩ ሰዎችን ወደ ፋይናንስ ስርዓት በማምጣት፤ በኤጀንትነት አማካኝነት የስራ እድል በመፍጠር፤ የገንዘብ ዝውውር በማፋጠር፤ የባንክ ቅርንጫፍ በሌለባቸው ነገር ግን ስልክ በደረሰባቸው የሀገራችን ገጠራማ ቦታዎች የገንዘብ ዝውውርን በማስፋት፤ የወረቀት ገንዘብ ዝውውርን ድርሻ በመቀነስ፤ የፋይናንስ ገበያውን ፉክክር በማፋጠን፤ ከውጪ ዜጎች በቀላሉ ገንዘብ እንዲልኩ በማገዝ፤ ወዘተ ሀገራችን ከdigital economy ተጠቃሚ እንድትሆን ያግዛል።


#ለምሳሌ፦ በጎረቤታችን ኬንያ የሚንቀሳቀሰው M-pesa የተባለው የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ዛሬ ላይ ከ 22 ሚሊየን ህዝብ (የጠቅላላ ህዝቡን ግማሽ የሚጠጋ) ግብይት ለማከናወን፤ ገንዘብ ለመበደር እና ገንዘብ ለማስተላለፍ በደሳሳ ሱቆች እና የገጠር አካባቢዎች ሳይቀር ይጠቀሙበታል።


ለሌሎች ባንኮች ስጋት አይሆንም? ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ ዘርፍ ሁለት ጥቅም ነው የያዘው፣ አንደኛው ለሌሎች ባንኮች የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እንዲሰጡ ኢንተርኔት እና መሰረተ ልማት ማቅረብ እና ሁለተኛው የራሱን ደንበኞች የፋይናንስ አገልግሎት በመጀመር ማስጠቀም ናቸው! በመጀመሪያው አንድ አመት ልዩ ተጠቃሚ ስለሚሆን በሌሎች ባንኮች ላይ የቴሌኮም አገልግሎት ዋጋን የመወሰን አቅም ይኖረዋል! ነገር ግን ከዓመት በኋላ የውጪ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች በሞባይል ባንኪንግ መሳተፍ ሲጀምሩ በዋጋ ፉክክር፤ በአገልግሎት ጥራት እና በኤጀንቶች ተደራሽነት ምክንያት ልዩ ተጠቃሚነቱ ሊቀንስ ይችላል።


ኢትዮ ቴሌኮም በመንግስት ደረጃ ልዩ ተጠቃሚ ተደርጓል! አንደኛው የፖሊሲ ማዕቀፍ ያልነበረው አገልግሎት ተሻሽሎለታል በተጨማሪም ከውጪ ከሚመጡ ተመሳሳይ ካምፓኒዎች ጋር ያለው ልምድ ዝቅተኛ በመሆኑ እንዳይጎዳ የአንድ አመት የብቸኝነት አገልግሎት የማቅረብ መብት ተሰጥቶታል።
እንኳን ለ1442ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ!
በፋና ቴሌቪዥን የተደረገውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢኮኖሚ ጉዳዬች ክርክር ማስታወሻ ደብተር ይዤ ለመከታተል አስቤ እጄን አፌ ላይ ጭኜ እየሳኩ ነው!
#ፓርቲ1፦ "የምንከተለው የኢኮኖሚ ርዕዮተ ዓለም አካታች፤ ተራማጅ፤ ፋይዳ ያለው ይሰኛል......"

#ፓርቲ2፦ "በሀገራችን ያሉ ባንኮች ተዋህደው በአንድ ላይ በትብብር እንዲሰሩ እናደርጋለን!፤ #በመጠኑ የውጪ ብድር እንወስዳለን፤ አሜሪካ አንድ እቃ አንድ ዶላር ሆኖ እኛ ሀገር አርባ ብር የደረሰበት ምክንያት አልገባንም፤ አየር መንገዱ መፀዳጃ ቤት ስለሌለው እናሻሽላለን....."

#ፓርቲ3፦ "ምርጫ ብናሸንፍ የውጪ እዳ፤ የበጀት ጉድለት፤ የዋጋ ንረት፤ የሀገር ውስጥ የገቢ መጠን ስንት እንደምናደርሰው የያዝነው የቁጥር እቅድ የለም!....."