ከቅርብ ጊዜ ወዲህ #የቤተሰብ_ምጣኔ ማስታወቂያ በየሚዲያው መለቀቅ መጀመሩ ለፈጣኑ የህዝብ ቁጥር እድገት ምላሽ ለመስጠት አንድ ጥሩ እርምጃ ነው!
March 15, 2021
#Prisoners_Dilemma
**
1950 ሁለት የአደገኛ የወንጀል ቡድን አባሎች ተይዘው ይታሰራሉ። በተያዙበት ወቅት እያንዳንዱ እስረኛ ከሌላው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አልነበራቸውም! ዐቃቤ -ሕግ በህግ የተከሰሱበት ጥፋቶች ላይ ጥፋተኛ ለመሆናቸው በቂ #ማስረጃዎች አልነበረውም!
ነገር ግን በቂ ማስረጃ በማግኘት ከዝቅተኛ ክስ ይልቅ ከፍተኛ ክስ ለመመስረት በቂ ሃሳብ ለማግኘት አቃቤ ሕጉ በአንድ ጊዜ ለእያንዳንዱ እስረኛ በሌላኛው ላይ መመስከር/ማጋለጥ አዋጪ መሆኑን እና በዚህ መንገድ ጥፋተኛውን በምስክር ማረጋገጥ ይፈልጋል። በተመሳሳይ እያንዳንዱ እስረኛ ሁለት አማራጭ አለው ለሌላውን እስረኛ ላይ መመስከር (አድርጓል ብሎ ማጋለጥ) ወይም ከሌላኛው ጋር ተማምኖ (ሌላኛው እስረኛ ለራሱ ሲል እኔ ላይ አይመሰክርብኝም ብሎ በማመን) ድርጊቱን መካድ (ዝም ማለት) ድርድሩም…….
እያንዳንዳቸው ሌላውን አሳልፈው ከሰጡ (እሱ ነው ወንጀለኛ ከተባባሉ) እያንዳንዳቸው ለሁለት ዓመት ይታሰራሉ፤ አንዱ ክዶ (በሌላው ላይ መስክሮ) ሌላው ግን ዝም ቢል (በሌላው ላይ ባይመሰክር) ያጋለጠው ነጻ ሲሆን የተመሰከረበት ለ3 ዓመት ይታሰራል እንዲሁም ሁለቱም ዝም ቢሉ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ባይመሰክሩ ሁለቱም በአንድ ዓመት እስራት ብቻ ይቀጣሉ (አነስተኛ ቅጣት)።
ለበርካታ ጊዚያት አንዱ እስረኛ በሌላው እስረኛ ላይ በመመስከር መታሰር፤ ባለመመስከርም (ሌላው ከመሰከረ) መታሰር የተለመደ ነበር ስለዚህ እነዚህ እስረኞች የጋራ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን ነጥብ አገኙ ሁለቱም መካድ ዝቅተኛውን የእስር ጊዜ መጋራት ከዛን ጊዜ ጀምሮ የጋራ እኩል ተጠቃሚነት (#Prisoners_Dilemma) የሚባል ሀሳብ ኢኮኖሚስቶች ይዘው ብቅ አሉ።
ይሄ የጋራ ተጠቃሚነት (ተፅኖንም መጋራት!) ሃሳብ መነሻው ከእስረኞቹ ሁኔታ ቢሆንም በኢኮኖሚክስ አስተምሮት ውስጥ ዳብሮ ለብዙ ሴክተሮች አሁንም ድረስ ያገለግላል። ለዚህ ተጠቃሹ Nash Equilibrium የሚባለው Theory ነው! ማንኛውም እንቅስቃሴ እና ጥቅም የሌላኛውን እንቅስቃሴ እና ጥቅም የሚጎዳ ከሆነ ዘላቂነት የሌለው መሆኑን ያስረዳል።
#ለምሳሌ፦ አንድ ፋብሪካ በመንደር ውስጥ ሲቋቋም ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ በቀጥታ አልያም በመንግስት በኩል ድርድር መደረግ አለበት። ፋብሪካው በመከፈቱ ህብረተሰብ ምን ይጠቀማል? የትኞቹን መጪ አደጋዎች ይጋራል? ፋብሪካው እንዴት ይጠቀማል? ፋብሪካው ለሚከሰቱ ተፅዕኖዎች ምን አይነት ማካካሻ ለማህበረሰቡ ያቀርባል?
በዚህ ምሳሌ ሁለት ተዋናዮች አሉ ህብረተሰቡ እና ፋብሪካው ስለዚህ ህብረተሰቡ ፋብሪካው በአካባቢያቸው ተከፍቶ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፋብሪካውም ስራውን ጀምሮ ተጠቃሚ እንዲሆን ከፍተኛ የሚባለውን የተጠቃሚነት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ሲረዱ ውሳኔ ይወስናሉ።
በሀገራችን በኢንቨስትመንት ዙሪያ ከማህበረሰቡ ጋር የሚኖርን የጋራ ተጠቃሚነት መሀል ሆኖ የሚያደራድረዉ መንግስት ነው። #ለምሳሌ፦ አንድ ፋብሪካ የአዋጪነት ጥናት ሲያቀርብ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ጥቅም እና ጉዳቱን ፍቃድ ከመስጠት በፊት መገምገም፤ ለማህበረሰቡ ተጨማሪ ስለሚያቀርባቸው ተጨማሪ ጥቅሞች (#ለምሳሌ፦ መንገድ፤ ውሃ፤ ጤና ጣቢያ፤ ትምህርት ቤት፤ ስልጠና፤ ወዘተ ማቅረብ) በአግባቡ መጠቀሳቸውን እና በስራ ወቅት ሊገጥሙ ለሚችሉ ተፅዕኖዎች ያዘጋጀውን መከላከያ ዘዴ በመገምገም ይወስናል።
በተመሳሳይ ህብረተሰቡ ፋብሪካው በአካባቢያቸው ሲመጣ ስለሚኖራቸው የጋራ ተጠቃሚነት እንዲያውቁ እና እንዲያምኑ ማድረግ ግዴታ ነው! ብዙ ጊዜ በሚቀመጠው ተመን መሬታችሁን አስረክቡ "ፋብሪካው ከእናንተ ይበልጣል!" አይነተ አካሄድ ስለሚከሰት ፋብሪካው ከነዋሪው ጋር ድብብቆሽ ውስጥ ሆኖ ስራውን ይቀጥልል! ግጭቶች ሲከሰቱ የሚነዱ ፋብሪካዎች ከሚስተዋሉበት ምክንያት አንዱ የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ ያለው የሶስቱም ተተዋናዮች አረዳድ ችግር ነው (መንግስት፤ ፋብሪካው እና ማህበረሰቡ ማለት ነው)።
በናሽ ሃሳብ የኢኮኖሚ ተዋናዮች ከራሳቸው ጥረት (Player's strategy) በላይ ሌሎች በሚኖራቸው የውሳኔ ድክመት የማትረፍ አልያም የመክሰር አዝማሚያን (Most optimal strategy) ሊኖራቸው እንደሚችል ያስረዳል!
የዚህ አይነቱ የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ መስማማት ከሌለ የፋብሪካው ህልውና አደጋ ላይ ሲሆን! ፋብሪካው በአካባቢው ባለመከፈቱ ማህበረሰቡም ሊገኝ ከሚችል ጥቅም (ለምሳሌ የስራ እድል!) ሊያጣ ስለሚችል ተቻችሎ መስራት ተገቢ ይሆናል።
ፕሮፌሰር ናሽ ይሀንን ድንቅ ኢኮኖሚያዊ ሃሳብ ማመንጨቱን እና Theory መፍጠሩን ተከትሎ "Beautiful Mind" የሚል ፊልም ተሰርቶለት በዓለም ላይ ተወዳጅ ነው።

March 16, 2021
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሸገር ዳቦ ፋብሪካ በየወሩ 100 ሺህ ኩንታል ስንዴ ለማቅረብ ተስማማ፡፡ ይህም ፋብሪካው በቀን የሚያመርተውን የዳቦ መጠን ከ900,000 ወደ 1.5 ሚሊዮን ያደርሰዋል፡፡ ለተነሳው የኑሮ ውድነት #ጊዚያዊ መፍትሄ ለማምጣት ጥሩ እርምጃ ነው!
March 16, 2021
በዚህ ፈጣን የዋጋ መጨመር በተከሰተበት ወቅት የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ስርጭት በያዘው ፍጥነት ቀጥሎ #የእንቅስቃሴ_ገደብ መጣል ላይ ከደረስን ኢኮኖሚያዊ ቀውሱ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ኢኮኖሚው በቀላሉ ማገገም አይችልም! ስለዚህ ጥንቃቄ ግድ ነው!
March 16, 2021
March 17, 2021
ለዓመታት ስርዓት ያልተበጀለት የንግድ ስርዓት ጊዜውን ጠብቆ ሸማቹን #የደላላ ሲሳይ አደረገው! ከሽንኩርት እስከ ሲሚንቶ የማምረቻ ወጪው እስከማይታወቅ ድረስ ዋጋ ሰሩለት!
March 18, 2021
ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ወደ ማህበራዊ ቀውስ ይቀየራል የሚባለው #ዘረፋ፤ #ግድያ፤ #ልመና፤ #ማጭበርበር፤ #በረንዳ_አዳሪነት፤ ወዘተ ሲበራከት ነው! አዲስ አበባ ደግሞ ምርጥ ምሳሌ እየሆነች ነው!
March 18, 2021
#Supply_Side_Economics
*******
የኢትዮጲያ መንግስት ለብዙ ዓመታት ፍላጎትን በሚያሳድጉ ፖሊሲዎች እና ተግባራት ላይ ብዙ ሰርቷል:: ነገር ግን በተመሳሳይ አቅርቦት ላይ ባለመሰራቱ ፍላጎት ከአቅርቦት እጅግ በጣም ከመብለጡ የተነሳ አሁን ላይ የኑሮ ውድነት ከፍተኛ ሆኗል፡፡ ስለዚህ በቀጣይ ምርጫ መንግስት የሚሆነው ፓርቲ በረጅምም ሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ አቅርቦትን የሚያሳድጉ ፖሊሲዎች ላይ በቅድሚያ ማተኮር ተገቢ ነው!
በMonetary Policy፡- በገበያ የሚሰራጨውን የገንዘብ መጠን በመቀነስ ወይም በመጨመር አቅርቦትን ማበረታታት ይቻላል፡፡ በRegulatory Policy፡- መንግስት በገበያ ያለውን ከፍተኛ ጣልቃ ገብነት በመቀነስ እንዲሁም በTax Policy፡- ተጨማሪ ግብርን መቀነስ እንዲሁም የገቢ ግብር መጠንን ሳይቀር መቀነስ፣ ይሄ ተጨማሪ የስራ ተነሳሽነት ይፈጥራል እንዲሁም ባለሃብቶች እና ስራ ፈጣሪዎች ሃብታቸውን ለተጨማሪ ስራ እንዲያውሉት ያግዛል፡፡ ስለዚህ……
Labor Market፡- ነጻ የሆኑ የሰራተኛ ማህበራትን በማጠናከር፤ ሰራተኛ የመቅጠር እና የማሰናበት ሁኔታን በማላላት፤ በተጨማሪ የገቢ ግብርን በመቀነስ የተሻለ ፉክክር እንዲፈጠር እና የምርታማነት አቅም እንዲያድግ ማድረግ ይቻላል፡፡
Capital Markets፡- መንግስት ለባንክ ሴክተሩ ድጋፍ በማድረግ፤ ለኢንቨስትመንት የሚሆን ካፒታል እንዲጨምር በማድረግ እና ቁጠባን በማበረታታት አቅርቦትን ማሳደግ ይቻላል፡፡
Entrepreneurship፡- መንግስት አዲስ ስራ ጀማሪዎችን የማበረታታት ሃላፊነት አለበት (#ለምሳሌ፡- አዲስ ኢንቨስትመንት ለሚጀምሩ ባለሃብቶች የገቢ ግብር እፎይታ ማድረግ) ይህም የተሻለ የስራ ተነሳሽነት ስለሚፈጥር የአቅርቦት ሁኔታ ያድጋል፡፡
Competition and Efficiency፡- ጤናማ የሆነ የንግድ ፉክክር እንዲፈጠር በማድረግ፤ የኢንቨስትመንት ህጎችን በማሻሻል፤ ንግድ የመጀመር ተግዳራቶችን በመቀነስ፤ ወዘተ አቅርቦትን ማሳደግ ይቻላል፡፡
Education፡- ጥራት ያለው እና በተግባር የተደገፈ ትምህርት ምርታማነትን የማሳደግ አቅም ስላለው በዚህ ዘርፍ ላይ ማተኮር አቅርቦትን ማሳደግ ይቻላል፡፡
ከላይ የተዘረዘሩ ፖሊሲዎች ከተሳኩ የዋጋ ንረትን መቀነስ (በተለይ በሀገራችን በብዛት ከሚስተዋለው ከማምረቻ ግብዓት ወጪ መጨመር (Cost Push Inflation) የሚነሳን የዋጋ ንረት ይቀንሳል)፤ ስራ አጥነትን መቀነስ፤ የንግድ ሚዛንን ማስተካከል (አቅርቦት ከጨመረ ወደ ውጪ የሚላክ ምርት ይጨምራል) በጠቅላላ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

March 19, 2021
የኮንስትራክሽን ግብዓት አምራቾች ይህንን ታክቲክ ተከትለው ነው ሸማቹን እና መንግስትን መቅጣት የያዙት!
አምራቾች ከአቅም በታች ያመርታሉ! እጥረት ይከሰታል! መንግስት ይደነግጣል! አምራቾቹን ለውይይት ይጠራል! ብዙ ችግር ይዘረዝራሉ! መንግስት ያዋጣል በምትሉት ዋጋ ሽጡ፣ የጠየቃችሁት በቅርቡ ይሟላል! ብሎ ማስታገሻ ይሰጣል!

March 20, 2021
የራሴን የራዲዮ የአየር ሰዓት ጀምሪያለሁ! በማህበራዊ ሚዲያዎች ላለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ ኢኮኖሚያዊ ሀሳቦችን ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ መልኩ ሳጋራችሁ ቆይቻለሁ። እንዲሁም በተለያዩ የሚዲያ ዘርፎች( በቴሌቭዥን ፣በሬድዮ እና በተለያዩ የህትመት ውጤቶች) ላይ መረጃ እና ትንታኔዎችን በመስጠት በኢኮኖሚው ዘርፍ የበኩሌን አስተዋፅኦ ሳበረክት እንደቆየሁ ይታወቃል።
በአሁኑ ግዜም በተለይም በሀገራችን ስለኢኮኖሚው ብዙ መወያየት እና መፃፍ ያለብን ወቅት እንደሆነ ይሰማኛል።
በመሆኑም በአጭሩ የማካፍላቸውን መረጃዎች ሰፋ በማድረግ እና አድማጮችን በመጋበዝ ሰፋ ያለ ተደራሽነት ያለው ስለኢኮኖሚያችን በደንብ የምንወያይበት "ይመለከተኛል ኢትዮጵያ! በኢኮኖሚ " የሚል በሳምንት ሁለት ቀን እሮብ እና ሀሙስ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት በአዋሽ ኤፍ ኤም 90.7 የሚቀርብ የሬድዮ ፕሮግራም ከጋዜጠኛ መሀመድ ሲራጅ ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል።
ለመንግስት፣ለሸማቾች፣ ለአምራቾች፣ ለነጋዴዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለጋዜጠኞች፣ ለመደበኛው ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊ መረጃ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ በተቻለን አቅም ወቅታዊ መረጃዎችን በማቅረብ ተመራጭ እና ለመደበ ፕሮግራም ለማቅረብ ዝግጅታችንን አጠናቀናል። በመሆኑም እንድታደምጡን እና ተሳታፊ እንድትሆኑ ብሎም ፍላጎት ያላችሁ ስፖንሰር እንድታደርጉ እንጋብዛለን።

የዛሬ 6 ወር በሀገራችን አዲስ የብር ኖት ሲተዋወቅ ስለሚኖረው ዋና ዋና ጥቅሞች ጽፌ ነበር! ዛሬ ደግሞ ያስገኘውን ውጤት ካለን መረጃ ብቻ በመነሳት ብናየው ወድጃለሁ፡፡
#የዛሬ_6_ወር፡- የገንዘብ ለውጡ በኢኮኖሚው የሚዘዋወረውን ህገ-ወጥና ከመጠን በላይ የሆነ ገንዘብ በማጥራት የዋጋ ንረትን መቆጣጠር እንዲሁም የገንዘብ አጠቃቀምን ውጤታማ ማድረግ ይቻላል፡፡ ባንኮችም ተንቀሳቃሽ ገንዘብ (Liquidity Problem) እጥረት አይገጥማቸውም፡፡
#ከ6_ወር_በኋላ፡- ከ130 ቢሊየን ብር በላይ ከባንክ ስርዓት ውጪ ይንቀሳቀስ የነበረውን በገንዘብ ለውጡ እና ከጥሬ ገንዘብ ገደብ ውሳኔው ጋር ተያይዞ ይህንን ገንዘብ ከጥቂት የአፈጻጸም ክፍተት (መዘግየት ከታየበት ትግራይ ክልል) በስተቀር አሮጌውን ብር ለመቀየር ተችሏል፡፡
አብዛኛው የግል እና የመንግስት ባንኮች የብር ለውጡን እንደመምራታቸው ከነባር ደንበኞቻቸው እና አዳዲስ ደብተር ከከፈቱ ዜጎች ከሰበሰቡት ብር የተሻለ የገንዘብ አቅርቦት እንዲኖራቸው አድርጓል በተመሳሳይ የንግድ ባንኮች ካቀረቡት የብድር መጠን 28 ከመቶ ቦንድ እንዲገዙ የሚያዘው መመሪያ በመነሳቱ ላለፉት 6 ወራት ባንኮች የገንዘብ እጥረት (Liquidity Problem) ገጥሟቸዋል ብሎ ለመናገር አይቻልም፡፡
በአብዛኛው የንግድ ባንኮች ይቆጥቡ ይሸለሙ ቅስቀሳ እና የማስቀመጥ ወለድ መጠን መሻሻላቸው ከቁጠባ ማነስ እና ከጥሬ ገንዘብ እጥረት ጋር የሚያገናኙት ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ! በዋናነት ዜጎች በመጪው ጊዜ ላይ ያላቸው መተማመን ሲቀንስ፤ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ሲፈጠር የጥሬ ገንዘብ ፍላጎታቸው ሲያድግ! ቁጠባቸው መናዱ አይቀርም! በተቃራኒው ባንኮች ከመጪዎቹ የባንክ ሴክተር ተዋናዮች (በአክሲዮን እየተቋቋሙ ካሉ ባንኮች) ጋር የሚኖርባቸውን ፉክክር በመፍራት ቁጠባን እና ደንበኞቻቸውን ለማሳደግ እንደሚሆን ይሰማኛል፡፡
#የዛሬ_6_ወር፡- የገንዘብ ለውጡ ህገ ወጥነትን እና ሙስናን በማስወገድ የመንግስትን የግብር መጠን መጨመር፤ የቁጠባ መጠንን ማሳደግ፤ በባንኮች የሚፈለገውን የገንዘብ መጠን መጨመር ብሎም ኢንቨስትመንትን ማበረታታት ይቻላል፡፡ መንግስት የሰራተኛ ደመወዝ ለመክፈል፣ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለመስጠት የበጀት እጥረት አይገጥመውም፡፡
#ከ6_ወር_በኋላ፡- መንግስት ላለፉት 8 ወራት ያስገባው የገቢ መጠን 191 ቢሊየን ብር ሲሆን በአንድ ወር ውስጥ ይሰበሰብ ከነበረው በአማካኝ በ12 ከመቶ የበለጠ ነው፡፡ በጊዚያዊነት አስገዳጅ በሆነው የገንዘብ ለውጥ፤ የባንክ ደብተር መክፈት እና የጥሬ ገንዘብ ገደብ ምክንያት በባንኮች የደንበኞች ገንዘብ ከጨመረ በተዘዋዋሪ ቁጠባ አድጓል፡፡ አዲስ ከ155 ቢሊየን ብር በላይ ለኢንቨስትመንት በብድር የቀረበ ሲሆን ከ74 ከመቶ በላይ ብድር ለግል ሲክተሩ የቀረበ መሆኑን የመንግስት ሪፖርት ከተቀበልን ኢንቨስትመንት መበረታታት አሳይቷል፡፡
#የዛሬ_6_ወር፡- የገንዘብ ለውጡ የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራትን ማለትም የሰዎች መፈናቀል፣ ግድያ፣ እርስ በርስ ግጭት ያስቆማል፡፡ ሃሰተኛ ብርን ከሲስተም እንዲወጣ ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ ሰዎችን ከመሸወድ ያድናል፡፡ ኢኮኖሚውም ውጤታማ ይሆናል፡፡ በአብዛኛው መደበኛ ባልሆነው የፋይናንስ ስርአት (Informal banking system) ሲጠቀሙ የነበሩ ወደ መደበኛው ይመጣሉ፡፡ እንደ አራጣ አበዳሪዎች እና ህገ ወጥ ገንዘብ አዟሪዎች ያሉ አካላትን ወደ ሲስተም ለማምጣት ያግዛል፡፡
#ከ6_ወር_በኋላ፡- የብሩን ለውጥ ተከትሎ የዋጋ ንረት መውረድ ሳይሆን መጨመር አሳይቷል፤ ስራ አጥነት መጨመር እንጂ መቀነስ ለማሳየት አልቻለም፤ የዜጎች መፈናቀል፣ ግድያ፣ እርስ በርስ ግጭት አልቀነሰም፤ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር በመጀመሪያ ወራቶቹ ለመቀነስ ተቸግሮ ነበር፤ የጥቁር ገበያው እንቅስቃሴ አልቀነሰም፤ ወዘተ ተስተውሏል፡፡
የገንዘብ ለውጥ ውጤት ዓመታትን አስቆጥሮ የሚታይ መሆኑ ግልጽ ነው (#ለምሳሌ፡- በህንድ 2014 ላይ የተደረገው የገንዘብ ለውጥ ውስን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አዎንታዊ ለውጥ ማሳየት የጀመረው ከገንዘብ ቅየራው 4 ዓመታት በኋላ እንደነበር እናስታውሳለን)፡፡
የገንዘብ ለውጥ ኢኮኖሚያዊ ግብ መሆን አይችልም! ከገንዘብ ለውጡ ጋር መሻሻል ያለባቸው ፖሊሲዎች እና አሰራሮች መኖር አለባቸው፡፡
#ለምሳሌ፡- የዋጋ ንረት እንዲቀንስ የጥሬ ገንብ መጠንን ለመቀነስ የገንዘብ ለውጥ ቢደረግም ምርት እና ምርታማነት እድጎ አቅርቦት እንዲሻሻል ኢንቨስትመንት መበረታታት አለበት፤ ከውጪ የሚገቡ ቁሶችን መተካት ላይ ስራዎችን በመስራት የውጪ ምንዛሬን መቆጠብ እና የውጪ ምንዛሬ ግኝቶችን ማሳደግ፤ ገበያውን በትኩረት መከታተል፤ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት አድማስን ማስፋት፤ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ምህዳር መፍጠር፤ የመሰረተ ልማት እድገት እና የፕሮጀክት አፈጻጸምን ማሳደግ፤ ሙስናን መቀነስ፤ ወዘተ አብረው መለወጥ ግድ ነው፡፡
እንደአለመታደል ሆኖ የሀገራችን የብር ኖት ለውጥ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ባሉበት ወቅት ላይ የተወሰደ እርምጃ በመሆኑ ፈተናዎች በዝተውበታል! የኮሮና ወረርሺኝ፤ የአንበጣ መንጋ፤ ጦርነት፤ ግጭቶች፤ ዓለም አቀፍ ጫና፤ ወዘተ እንዲሁም የመንግስት የነዳጅ ድጎማ መላላት፤ የቀረጥ እፎይታ መለዋወጥ፤ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የወለድ ማሻሻያ፤ የምርጫ ወቅት መቃረብ፤ ገበያውን በአግባቡ ያለመምራት ችግር፤ የውጪ ምንዛሬ እጥረት፤ ወዘተ ታክለውበት የኑሮ ውድነት የተከሰተበት ወቅት በመሆኑ የገንዘብ ለውጡን ፋይዳ አደብዝዞታል፡፡
ብዙ ሰዎች የብር ለውጡ ሁኔታዎችን ያባባሰ እንደሆነ ቢያስቡም እኔ በግሌ አሁንም ድረስ ብር መለወጣችን ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑን አምናለሁ! የኢኮኖሚ ለውጥ ጊዜ እና ጠንካራ ስራዎችን የሚጠይቅ ነው።

March 22, 2021
የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ግቦች፡- የብድር ጫናን መቀነስ፤ የፕሮጀክት አፈጻጸምን ማሻሻል፤ የውጪ ንግድ ግኝትን ማሳደግ፤ ብሄራዊ ገቢን ማሳደግ፤ ገበያን ማረጋጋት እንዲሁም ቀጣይነት ያለው የእድገት ስትራቴጂ መዘርጋት ነበር፡፡ የቀረበው ሪፖርት……
የውጪ ንግድ ባለፉት 6 ወራት ያስገባው ግኝት በ 21 ከመቶ እድገት አሳይቷል! ይህም ካለፉት 20 ዓመታት በአማካኝ ከፍተኛው ነው፡፡ ወርቅ ከቡና በላይ የሆነበት ዓመት ዘንድሮ ነው! በ6 ወር ውስጥ 1.54 ቢሊዮን ብር ከውጪ ንግድ ተገኝቷል፡፡
የሀገር ውስጥ ገቢ መጠን በ2010ዓ.ም የነበረው 176.9 ቢሊዮን ብር ሲሆን ይህም በዓመቱ በ20 ቢሊዮን ብር አድጎ በ2011ዓ.ም 196.5 ቢሊዮን ብር ደርሷል፤ በ2012ዓ.ም በ30 ቢሊዮን ብር አድጎ 228.9 ቢሊዮን ብር ደርሷል፤ 2013 በ8 ወር ብቻ 191 ቢሊዮን ብር ደርሷል (ይህ በ2010 ጠቅላላ ከተሰበሰበው 176.9 ቢሊዮን ብር ይበልጣል!)፡፡
የንግድ ጉድለት (ወደ ውጪ የሚላከው ከውጪ ከሚገባው ሲቀነስ ማለት ነው!) በ2010ዓ.ም ከዜሮ በታች 14.7 ከመቶ የነበረ ሲሆን በ2011ዓ.ም በ1.7 ከመቶ ቀንሶ ከዜሮ በታች 13 ከመቶ ደርሷል፤ በ2012ዓ.ም በ2.9 ከመቶ ቀንሶ ከዜሮ በታች 10.1 ከመቶ ደርሷል! ይህ የሚያሳየው በ3 ዓመት ውስጥ በ4.6 ከመቶ እንዲቀንስ ሆኗል፡፡ ይህ ውጤት የውጪ ንግድ ማደግ (Export ከ3 ቢሊዮን ዶላር አልፏል) በተጨማሪም ከውጪ የሚገቡ ቁሳቁሶች ላይ ክትትል በመደረጉ ነው፡፡
የውጪ እዳ ጫና ከጠቅላላው ሃገራዊ ምርት ያለው ልዩነት በ2010ዓ.ም የነበረው 37.6 ከመቶ የነበረ ሲሆን በ2011ዓ.ም ወደ 29.4 ከመቶ ቀንሶ በ2012ዓ.ም 26.8 ከመቶ ደርሷል፡፡ ይህ ውጤት የሚያሳየው በ3 ዓመት ውስጥ በ10 ከመቶ የውጪ እዳ ጫና ከጠቅላላው ሃገራዊ ምርት ያለው ልዩነት ቀንሷል፡፡ የዚህ ውጤት መሰረታዊ እርምጃ የብድር ስረዛ እና ሽግሽግ ድርድር፤ የመክፈል አቅምን ማሳደግ፤ ከፍተኛ ወለድ ያለው ብድርን በመቀነስ የመጣ ነው፡፡
የገንዘብ አቅርቦት በ15 ከመቶ ሲያድግ የቁጠባ መጠን በ25 ከመቶ አድጓል! ባንኮች የነበራቸው ቁጠባ በ2010ዓ.ም የነበረው 730 ቢሊዮን ብር ሲሆን ይህም በዓመቱ በ169 ቢሊዮን ብር አድጎ በ2011ዓ.ም 899 ቢሊዮን ብር ደርሷል፤ በ2012ዓ.ም በ141 ቢሊዮን ብር አድጎ 1.04 ትሪሊዮን ብር ደርሷል፤ 2013 በ6 ወር ብቻ 1.2 ቢሊዮን ብር ትሪሊዮን ብር ደርሷል (ይህ በ2012 ጠቅላላ ዓመቱን በሙሉ በ2013 ዓ.ም በግማሽ ዓመት የተሰበሰበው 160 ቢሊዮን ብር ይበልጣል!)፡፡
በተጨማሪም ገንዘብ ለውጡን ተከትሎ 6.2 ሚሊዮን ሰዎች አዳዲስ የባንክ አካውንት በመክፈታቸው ተጨማሪ 98 ቢሊዮን ብር ተቆጥቧል፡፡
የኢንቨስትመንት ብድር አቅርቦት በ2010ዓ.ም የነበረው 170 ቢሊዮን ብር ብድር የቀረበ ሲሆን (ከጠቅላላ ብድሩ ውስጥ 45 ከመቶ ብቻ ነበር ለግል ሴክተሩ ቀርቦ የነበረው) ይህም በዓመቱ በ66 ቢሊዮን ብር አድጎ በ2011ዓ.ም 236 ቢሊዮን ብር ብድር ቀርቧል (ከጠቅላላ ብድሩ ውስጥ 61 ከመቶ ነበር ለግል ሴክተሩ ቀርቧል)፤ በ2012ዓ.ም በ35 ቢሊዮን ብር አድጎ 271 ቢሊዮን ብር ብድር ቀርቧል (ከጠቅላላ ብድሩ ውስጥ 70 ከመቶ ለግል ሴክተሩ ቀርቧል)፤ በ2013 በ6 ወር ብቻ 155 ቢሊዮን ብር ብድር ቀርቧል የግል ሴክተሩ ከ74 ከመቶ በላይ ድርሻ፡፡
ይህ የሚያሳየው ቁጠባ አድጓል፤ የግል ሴክተሩ የሚያነሳው የኢንቨስትምንት አቅም በብድር አቅርቦት አድጓል፤ የካፒታል ወጪ በ3 ዓመት ውስጥ ከ97 ቢሊዮን ብር ወደ 160 ቢሊዮን ብር አድጓል፤ የሚታረስ መሬት መጠን እና በበጋ የግብርና ምርት መጠን አድጓል፡፡
አንበጣ፤ ጎርፍ፤ ኮሮና እና ተደጋጋሚ ግጭት በመኖሩ የኢኮኖሚው እድገቱ በፈታናዎች ውስጥ ነው! ዜጎች ከውጪ የሚልኩት የውጪ ምንዛሬ ቀንሷል፤ የግጭት መብዛት የምርት መጠናችንን ቀንሷል፤ ከውጪ የሚገቡ ቁሶች ዋጋ መናር፤ የሎጀስቲክ እጥረት እንዲሁም የገበያው ሁኔታው ችግር ውስጥ በመሆኑ ከዋጋ ግሽበት በሚነሳው የኑሮ ውድነት ጨምሯል፡፡
በቀጣይ የሃይል አቅርቦትን በማሻሻል፤ የምርታማነት ሁኔታን በማሻሻል፤ የውጪ ምንዛሬ ግኝትን በማሻሻል፤ የገበያ ቁጥጥር በማድረግ፤ የፖለቲካ ሁኔታን በማሻሻል፤ ከውጪ የሚገቡ ቁሳቁሶችን በመተካት፤ ሙስናን በመቀነስ፤ ወዘተ ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲኖር ማድረግ ይገባል እላለሁ፡፡

March 23, 2021
የመጀመሪያ ቀን የራዲዮ ፕሮግራማችንን በትናንትናው እለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡትን ኢኮኖሚያዊ ሪፖርት መሰረት በማድረግ ያቀረብነውን ትንታኔ ዛሬ ከምሽቱ 3 ጀምሮ በአዋሽ ኤፍ ኤም 90.7 ላይ መከታተል ትችላላችሁ!
March 24, 2021
#የነፍስ_ወከፍ_ገቢያችን_ያጠራጥራል!
***
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገራችን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) 100 ቢሊየን ዶላር ደርሷል በተመሳሳይ የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ 1,000 ዶላር ደርሷል ብለዋል፡፡
ጠቅላላ ሀገራዊ ምርቱ (GDP) 100 ቢሊየን ዶላር መድረሱ ላይ ከተማመንን የህዝቡ ቁጥር 100 ሚሊየን ብቻ ከሆነ ነው የነፍስ ወከፍ ገቢ 1,000 ዶላር የሚሆነው! በተቃራኒው የህዝብ ቁጥራችን 110 ሚሊየን ደርሷል በሚለው ከተማመንን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርቱ (GDP) 110 ቢሊየን ዶላር ከሆነ ነው የነፍስ ወከፍ ገቢ 1,000 ዶላር የሚሆነው! ስለዚህ የትኛው ቁጥር ላይ ነው ስህተቱ?
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጠቅላላ ሀገራዊ ምርቱ (GDP) 100 ቢሊየን ዶላር ከደረሰ በብር ሲለወጥ ወደ 4 ትርሊየን ብር ይደርሳል ማለት ነው (አንድ ዶላር በ40 ብር ይመነዘራል)፡፡ በተመሳሳይ የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ በዓመት 1,000 ዶላር ደርሷል ማለት በብር ሲለወጥ በዓመት 40ሺ ብር ወይም በወር 3,333 ያገኛሉ ማለት ነው፡፡
የነፍስ ወከፍ ገቢን ለማስላት የጠቅላላ ሀገራዊ ምርቱ 4 ትርሊን ብር ሲካፈል ህዝባችን 110 ሚሊየን ቢሆን እያንዳንዱ ግለሰብ በዓመት 36,363 ብር ያገኛል ማለት ሲሆን ይህም ወደ ዶላር ሲቀየር 909 ዶላር ይሆናል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት የነፍስ ወከፍ ገቢ 1,000 ዶላር ደርሷል የሚሉት ቁጥር ልክ እንዲሆን ጠቅላላ የምርት መጠኑ (GDP) 100 ቢሊየን ዶላር በላይ መሆን አለበት አልያም የሀገራችን ህዝብ ቁጥር ግምት ከ110 ሚሊየን በታች መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ የትኛውን ቁጥር እንቀበል?

March 26, 2021
Forwarded from FBC (Fana Broadcasting Corporate)
March 26, 2021
March 27, 2021
የጋራ መኖሪያ ቤት በማህበር ተደራጅቶ መስራት ለሚችሉ የ20/80 እና የ40/60 ተመዝጋቢዎች አዲስ Modality ቀርቧል። በማህበር የተደራጁ የመርሀ ግብሩ ተጠቃሚዎች እጣ ከወጣላቸው የቤት ግንባታ ወጪውን 70% በባንክ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
#ለምሳሌ፦ አንድ መኝታ 20/80 ቤት ሙሉ ወጪው 882,087 ብር የሚፈጅ ሲሆን ተመዝጋቢው ቅድሚያ መክፈል ያለበት 617,000 ብር ነው! ከባንክ ጋር የሚተሳሰረው 30% ክፍያ 265,087 ብር ይሆናል! ይላል በመመሪያው ላይ ያለው መግለጫ።
የተለመደው 30% ሴት ተመዝጋቢዎች እና 20% የመንግስት ሰራተኞች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ይላል። #ለምሳሌ፦ ለአንድ መኝታ ቤት ቅድሚያ 617,000 ብር መክፈል ለሚችሉ #የመንግስት_ሰራተኞች 20% ኮታ ተሰጥቷል ማለት ነው! በአዲስ አበባ ኑሮ መንግስት ሰራተኛ ሆኖ 617ሺ ብር ቅድሚያ ክፍያ የሚታለም ነው?
#ለምሳሌ፦ 2005ዓ.ም አንድ መኝታ 20/80 ቤት ተመዝግቦ የነበረ ሰው በየወሩ መቆጠብ ያለበት 198ብር ነው! ስለዚህ ሳያቋርጥ ቢቆጥብ ዛሬ ላይ ከ8 ዓመት በኋላ መድረስ የሚችለው 19ሺ ብር ብቻ ነው! እስካሁን ሳያቋርጥ በቆጠበው 19ሺ ብር ላይ 598ሺ ብር መሙላት ከሚችሉት መካከል የመንግስት ሰራተኛ ከየት ነው የሚገኘው?
#ለምሳሌ፦ እኔ 2005ዓ.ም በ20/80 የአንድ መኝታ ቤት ለማግኘት ተመዝግቤ በወር 198 ብር መክፈል እየተጠበቀብኝ ያገኘሁትን በመቆጠብ ከስምንት ዓመት በኋላ ዛሬ ላይ 46ሺ ብር ብቻ ነው መድረስ የቻልኩት! በአዲሱ ማህበር ለመደራጀት መንግስትን አልጠብቅም ብል ተጨማሪ 517ሺ ብር ጨምሬ 617ሺ ብር እንዲሞላልኝ ማድረግ አለብኝ ማለት ነው። የእውነት ይህ ህልም ነው!
የጋራ መኖሪያ ቤት ፕሮግራሙ #የደሃ እና #የመካከለኛ ገቢ ባለቤት የሆኑ የከተማዋን ነዋሪዎች የሚጠቅም ነው የሚለው አስተሳሰብ ተጠምዝዞ #መካከለኛ እና #ከፍተኛ ገቢ ወዳላቸው ዜጎች እየሸሸ ይመስላል (የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ከደረሳቸው ዜጎች መካከል ከ75% በላዬቹ በቤቱ ውስጥ አይኖሩም የሚል መረጃ ከተማ መስተዳደሩ በቅርቡ አቅርቦ ነበር፣ ሸጠውታል ወይም አከራይተውታል ማለት ነው በአጭሩ!)።
በማህበሩ መደራጀት ግዴታ ሳይሆን የመንግስት ግንባታ አልጠብቅም የመክፈል አቅሙ አለኝ ለሚሉ የ20/80 እና 40/60 ተመዝጋቢዎች የቀረበ እድል መሆኑ ግልፅ ቢሆንም በችግር ውስጥ ያለው እና ስምንት ዓመት ከዝቅተኛው ደሞዙ የቆጠበው የመንግስት ሰራተኛ ኮታውን ያለመጠቀም እድሉ ሰፊ መሆኑ ያሳዝናል!
መንግስት ቤትን በተመለከተ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው እና ለመንግስት ሰራተኛው ልዩ #የዋስትና_ስርዓት ካላዘጋጀ አቅሙ በማይፈቅዳቸው የቤት ልማት Modality ውስጥ መታቀፍ መቸገሩ አይቀርም!
የጋራ መኖሪያ ቤት እየገነቡ ለዜጎች ማዳረስ የሚለው ስትራቴጂ በቀጣዩ ምርጫ የሚያሸንፈው ፓርቲ የእድገት ፕላን ውስጥ ከሌለ ውጤቱ ምንድን ነው የሚሆነው? ስለዚህ በምረጡኝ ቅስቀሳ ወቅት ሰፊ መከራከሪያ ከሚሆኑ አጀንዳዎች መካከል በአዲስ አበባ የቤት ልማት ጉዳይ ቁልፍ መሆኑ ነው።

March 28, 2021
ዛሬ TV እያየሁ አንድ የዩኒቨርስቲ ተማሪ በሀገራችን በቀጣይ ምን አይነት ስርዓት እንዲኖር እንደሚመኝ ሲጠየቅ "ለመመረቅ አንድ ዓመት ሲቀረኝ ስለምቀጠርበት ተቋም የማውቅበት ስርዓት እንዲኖር እፈልጋለሁ!" ሲል ሰማሁ። ተማሪው ኢኮኖሚስት ቢሆን ይህንን ምኞት Edit ያደርግ ነበር!
March 28, 2021
ኦሮሚያ ክልል በ2012ዓ.ም በበጋ እንዲለማ ያረሰው መሬት 7ሺ ሄክታር ብቻ የነበረ ሲሆን በ2013ዓ.ም በመጀመሪያ ዙር ብቻ 160ሺ ሄክታር (2285% እድገት) የበጋ ስንዴ በማምረት በቅርቡ ለፌዴራል መንግስት 3ሚሊዮን ኩንታል በሽያጭ ሊያቀርብ ነው! የሚበረታታ ጥረት፤ ውጤታማነት እና ደስ የሚል ዜና ነው!
March 28, 2021
March 29, 2021