The Ethiopian Economist View
29.3K subscribers
723 photos
4 videos
197 files
1.33K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
IMF ኢትዮጵያ የምንዛሬ ተመኗን በገበያ በመወሰኗ (Floating Exchange Rate በመከተሏ) በምትኩ የሚያገኘው ምንድን ነው?

IMF ለኢትዮጵያ ባዘጋጀው የሪፎርም ሰነድ ላይ....

የኢትዮጵያ የዋጋ ንረት በ2017 ወደ (30.1%) ያድጋል ከዚያ በ2018 (16.2%)፤ በ2019 (12.2%)፤ በ2020 (10.4%) እና በ2021 (9.6%) ይሆናል የሚል የትንበያ ቀመር አለው።

ይህ IMF የኢትዮጵያ መንግስት ካዘጋጀው የኢኮኖሚ ሪፎርም (የምንዛሬ ተመንን በገበያ መወሰንን ጨምሮ) ጋር የተያያዘ እና ለዚህ ፕሮግራም ከሰጠው እና ከሚሰጠው ድጋፍ እና ብድር ጋር የተያያዘ ነው....

ታዲያ IMF ሀገራት እንዲያድጉ ከፈለገ ለምን በሪፎርሞቹ (Privatization፤ Liberalization፤ Exchange rate reform፤ ወዘተ) ላይ ክርክር እና አመፅ ይነሳል?

ይህንን ትንታኔ ለመመልከት https://youtu.be/8bclfQ06UzI

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በነገው ዕለት  የአሜሪካ ዶላር ለሚፈልጉ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊያካሄድ ነው!

የውጪ ምንዛሬ (የአሜሪካ ዶላር) ለመግዛት ፍላጎትት ያላቸው ባንኮች እንዲያመለክቱ ጥሪ ቀርቧል (አንድ ባንክ ለጨረታ ከሚቀርበው ዶላር ውስጥ ከፍተኛ መግዛት የሚችለው 20% ነው)።
ጨረታው በሚቀጥለው ሳምንትም እንደሁኔታው ሊኖር ይችላል ይላል!

ጨረታው የባንኮች የምንዛሬ ተመን ፍጥነት እና መጠን ላይ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል የብሄራዊ ባንክ መሳሪያ ነው!
አንዳንድ ኢኮኖሚስቶች የምንዛሬ ተመኑ በገበያ መወሰኑ የዘገየ እና #በረከት ይዞ የመጣ ነው ሲሉ ሌሎች የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ደግሞ ቅድመ ዝግጅት የሌለው እና #አደጋ ሊፈጥር ይችላል ይላሉ!

የመንግስት ኢኮኖሚስቶችን አመክንዮ ጨምሮ የሃገራችን ታዋቂ ኢኮኖሚስቶች (ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት አማካሪ) ፅሁፍ እና ኢንተርቪው ስመለከት የገባኝን ነገር ልንገራችሁ!https://youtu.be/Rm4ccpU1CXo
አንዳንድ ኢኮኖሚስቶች የምንዛሬ ተመኑ በገበያ መወሰኑ የዘገየ እና #በረከት ይዞ የመጣ ነው ሲሉ ሌሎች የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ደግሞ ቅድመ ዝግጅት የሌለው እና #አደጋ ሊፈጥር ይችላል ይላሉ!

የመንግስት ኢኮኖሚስቶችን አመክንዮ ጨምሮ የሃገራችን ታዋቂ ኢኮኖሚስቶች (ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት አማካሪ) ፅሁፍ እና ኢንተርቪው ስመለከት የመለያየታቸው ነጥብ.....!https://youtu.be/Rm4ccpU1CXo
በብሄራዊ ባንክ የተካሄደው የዶላር ምንዛሬ የጨረታ አማካይ ዋጋ 107.90 ብር ሆኗል (በጨረታው 27 ባንኮች ተሳትፈዋል)!
ብሄራዊ ባንክ ያጫረተው የአንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ 107.90 ብር ሆኗል! የውጪ ምንዛሬ ጨረታ ምን ማለት ነው? የውጪ ምንዛሬ ጨረታ እንዴት ይከናወናል? የዕለቱ የውጪ ምንዛሬ ጨረታ ዋጋ እንዴት ይወጣል?

የመጀመሪያው ልዩ የብሄራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሬ ጨረታ ለውጪ ምንዛሬ ፈላጊዎች እና ለንግድ ባንኮች ምን አይነት እድል አለው?

ይህንን ለመመልከት....https://youtu.be/ZE208Q3UFck
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችን (Forex Bureau) ለመክፈት የሥራ ፈቃድ ማመልከቻዎችን መቀበል ጀመረ! Forex Bureau in Ethiopia!

የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችን (Forex Bureau) ምን ማለት ነው? ፍቃድ ለማውጣት መስፈርቱ ምንድን ነው? ቢሮዎቹ እንዴት ይሰራሉ? ቢሮዎቹ ከጥቁር ገበያ እና ከንግድ ባንኮች ምን ይለያቸዋል? የኢትዮጵያ የፍቃድ መስፈርት ከጎረቤት ሀገራት በምን ይለያል? ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን መረጃ አዘጋጅቻለሁ....https://youtu.be/9TmBUDGcwug
*የኢትዮጲያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የአመራር ለውጥ ማድረጉን ገለጸ።*

ላለፉት ሁለት አመታት የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ብሩክ ታዬ ከስልጣን በመልቀቅ (የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዉ መሾማቸው  ተሰምቷል) በሃና ተኀልኩ መተካታቸውን ባለስልጣኑ በማህበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል።

ወ/ሮ ሃና ከመቀሌ እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ምሩቅ መሆናቸው እና በዘርፉ ሰፊ ልምድ እንዳላቸው ተገልጿል!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችን (Forex Bureau) ለመክፈት የሥራ ፈቃድ ማመልከቻዎችን መቀበል ጀመረ! Forex Bureau in Ethiopia!

የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችን (Forex Bureau) ምን ማለት ነው? ፍቃድ ለማውጣት መስፈርቱ ምንድን ነው? ቢሮዎቹ እንዴት ይሰራሉ? ቢሮዎቹ ከጥቁር ገበያ እና ከንግድ ባንኮች ምን ይለያቸዋል? የኢትዮጵያ የፍቃድ መስፈርት ከጎረቤት ሀገራት በምን ይለያል? ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን መረጃ አዘጋጅቻለሁ....https://youtu.be/9TmBUDGcwug
የ Forex ቢሮ ፍቃድ ለማውጣት መስፈርቶች!

ነፃ የውጭ ምንዛሪ ቢሮ (Independent Forex Bureau) የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ ኖቶችን #በመግዛትና #በመሸጥ ላይ ብቻ የሚሰማራ እንጂ በሌላ የባንክ ሥራ ላይ መሰማራት የለበትም።

1. በማንኛውም ህጋዊ መንገድ የተቋቋመ፣ በኢትዮጵያዊ ዜጋ፣ ነዋሪ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ እና/ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ የሆነ የተቋቋመ የንግድ ድርጅት፤

2. ዝቅተኛውን የብር 15 ሚሊዮን ካፒታል አሟልቷል እናም 30 ሚሊዮን ብር የደህንነት ማስያዣ በተዘጋ አካውንት (ወለድ ሊያስገኝ ይችላል) በማንኛውም ባንክ ማቅረብ የሚችል፤

3. የሴኪዩሪቲ ተቀማጭ ገንዘብ ፊት ዋጋ በገለልተኛ Forex ቢሮ ለሁለት ዓመታት ከቀጠለ አገልግሎት ይለቀቃል፤

4. የፎርክስ ቢሮን ንግድ ለመፈፀም በሁሉም ረገድ ተስማሚ የሆነ እና NBE ለባንክ ላሉ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ያስቀመጠውን የደህንነት እና የደህንነት መስፈርቶችን የሚያሟላ፤

5. የፎርክስ ቢሮ አድራሻን የሚያመለክት የስም ሰሌዳ፤

6. የውሸት ማስታወሻዎችን ለመለየት አስፈላጊ መሳሪያ መያዝ፤

7. የ forex ቢሮ ሰራተኞችን ስም ዝርዝር እና ስያሜ መስጠት፤

8. የፎርክስ ቢሮ ሰራተኞች የማጭበርበር ፣የማታለል እና የሙስና መዝገብ የሌላቸው ታማኝ ፣ታማኝነት እና ብቃት ያላቸው ሰዎች መሆናቸውን ማረጋገጥ፤

9. በማንኛውም የፎርክስ ቢሮ ሳይት የሚገኘውን ከፍተኛውን የገንዘብ መጠን ለመሸፈን በቂ ኢንሹራንስ መግዛቱን ያረጋገጡ።
የባንኮች የዕለቱ የምንዛሪ ዋጋ ላይ #የመሸጫ እና #የመግዣ ዋጋ ልዩነት!

የመግዣ ዋጋ (Buying Rate):- ንግድ ባንኮች ማንኛውም የውጪ ምንዛሬ ያለውን ግለሰብ እና ድርጅት (ከውጪ በሃዋላ የተላከለት፤ ምርት ወደ ውጪ ሸጦ የውጪ ምንዛሬ ያገኘ (Exporter)፤ በተለያየ ምክንያት በእጁ የውጪ ምንዛሬ ያለው (Cash ያለው)፤ እዚህ ሀገር ቱሪስት ወይም የስብሰባ ተሳታፊ ሆኖ የውጪ ምንዛሬ ያለው ወደ ባንክ ሄዶ ሲዘረዝር ባንኩ የውጪ ምንዛሬ #ገዛ ይባላል፡፡

#ለምሳሌ፡- አንድ ዶላር ያለው ሰው በባንክ ሄዶ በ101.8 ብር ቢዘረዝር (የመግዣ ዋጋው 101.8 ብር ነው ማለት ነው)!

የመሸጫ ዋጋ (Selling Rate)፡- ንግድ ባንኮች ማንኛውም የውጪ ምንዛሬ የሚፈልግ ሰው ወይም ድርጅት ቀርቦ ሲጠይቃቸው (ከውጪ ምርት ለማስገባት የሚፈልግ (Importer)፤ ወደ ውጪ ሃገር ለትምህርት፤ ለመዝናናት፤ ለህክምና፤ ወዘተ የሚሄድ ሰው ወይም ድርጅት የኢትዮጲያ ብር ይዞ ቀርቦ በዶላር ተመንዝሮ የሚሰጠው ዋጋ የመሸጫ ዋጋ ይባላል! በዚህ ወቅት ባንኩ የውጪ ምንዛሬ #ሸጠ ይባላል፡፡

#ለምሳሌ፡- አንድ ዶላር የሚፈልግ ሰው ከባንክ ሄዶ በ111.9 ብር አንዱን ዶላር ቢገዛ (የመሸጫ ዋጋው 111.9 ብር ነው ማለት ነው)!

ከላይኛው ምሳሌ ብንነሳ በምሳሌ የቀረበው ንግድ ባንክ የዕለቱ የውጪ ምንዛሬ ተመን የመግዣ ዋጋ 101.8 እና የመሸጫ ዋጋ 111.9 ብር ነው ማለት ነው፡፡

ባንኩ አንድን ዶላር 101.8 ገዝቶ 111.9ብር ይሸጠዋል (111.9-101.8 = 10.1 ብር ከአንድ ዶላር ማለት ነው)።
የምንዛሬ ተመን እና የጉምሩክ ቀረጥ በዕለታዊ ምንዛሬ በመሰላቱ እየተፈጠረ ያለው የዋጋ ንረት....

በኢትዮጲያ በጥቂት ቀናት ውስጥ ምንዛሬም ከውጪ የሚገቡ ምርቶች ቀረጥም በእጥፍ ጨምሯል (የገበያ ዕለታዊ የምንዛሬ ተመን መከተል በመጀመሩ)! ይህ ጉዳይ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን ዋጋ ከምገምቱት በላይ ለውጦታል!

ለመሆኑ አንድ የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ እቃ ከውጪ ተገዝቶ ጉምሩክ ሲደርስ የሚጣልበት ነባር ቀረጥ ተደምሮ ማዕከል ገበያ ላይ እቃው ሊኖረው የሚችለው ዋጋ አንድ ዶላር 58 ብር ከነበረበት (ከ15 ቀን በፊት) እና አሁን ላይ አንድ ዶላር 110 ብር በደረሰበት ስሌት እናስላው!
https://youtu.be/ErnGEqG6oxU

🙏1
Official and Parallel Exchange Rates—Recognizing Reality.pdf
2 MB
IMF በ2021 ስለ መደበኛ እና የጥቁር ገበያ ምንዛሬን ስለማቀራረብ (Recognizing Reality፡ Unification of Official and Parallel Exchange Rates) ሪፎርም የሰሩ ሀገራትን ሁኔታ የተነተነበት የጥናት ሰነድ ነው! ምንዛሬን በገበያ የመወሰን ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ለምትፈልጉ ሰዎች!
#በኢትዮጵያ የባንክ እና የጥቁር ገበያ ምንዛሬ እኩል የሚሆኑበት መጠን (Real Exchange Rate Point) ስንት ሊሆን ይችላል?

በኢትዮጵያ የባንክ ምንዛሬ ከጥቁር ገበያው ምንዛሬ #እኩል ከሆነ በኋላ ለምን ያህል ጊዜ ሊቆይ ይችላል? (አሁን ከ15-20 ብር ልዩነት ላይ ነው!) ተመኑ እኩል ከሆኑ በኋላ የጥቁር ገበያው ምንዛሬ በምን ምክንያት ድጋሚ ሊነሳ ይችላል?

የተለያዩ ሀገራትን ከሪፎርም በኋላ የምንዛሬ ሁኔታ ያጠናው IMF የሚያስቀምጠው ግምት እና ማስጠንቀቂያ ምንድን ነው?

የሚከተለውን ትንታኔ እና መረጃ እንመልከት.....https://youtu.be/9ifADzgFR78

በናይጄሪያ ምንዛሬን በገበያ መወሰን (Floating Exchange Rate) አልተሳካም!

በIMF ምክር ናይጄሪያ ምንዛሬን በገበያ እንዲወሰን ስታደርግ አንድ ዶላር በ400 ናይራ ከሚመነዘርበት በአንድ ሳምንቱ ወደ 750 ናይራ አደገ! በአንድ ዓመት ውስጥ አንድ ዶላር ወደ 1,600 ናይራ መመንዘር አድጓል! ለምን?

ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ ውሳኔ ዓመት ዘግይታ የምንዛሬ ገበያ ነፃ አድርጋለች! ምንዛሬው እያደገ ነው! ስለዚህ ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ ውድቀት ምን መማር እና ማስተካከል አለባት?

ይህንን ምርጥ ትንታኔ ተመልከቱ ለሌሎችም እንዲማሩበት አጋሩት....https://youtu.be/NqhgvjUXD_s