ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
50.8K subscribers
67 photos
67 videos
19 files
1.71K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
መደምደሚያ
አላህ መልክተኞቹን በግልጽ ማስረጃዎች ልኳል፤ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ *”መጽሐፎችን ወደ እነርሱ አውርዷል፤ ነብያችንም”ﷺ” ወደ መልክተኞቹ የተወረደውን ለሰዎች ሊገልጹ ቁርአን ወርዶላቸዋል፦
57፥25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ *”መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን”*፤ لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْمِيزَانَ لِيَقُومَ ٱلنَّاسُ بِٱلْقِسْطِ
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎች እና በመጻሕፍት ላክናቸው፡፡ ወደ አንተም ለሰዎች *”ወደ እነርሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸው”* እና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡ بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَٱلزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُون

ነብያችን”ﷺ” የመጽሐፉ ባለቤቶች ከመጽሐፉ ይሸሽጉት ከነበሩት ነገር ብዙውን ለእነርሱ የሚገልጹ ሆነው ከአላህ ተልከዋል፦
5፥15 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *”ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ”* ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ قَدْ جَآءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًۭا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَيَعْفُوا۟ عَن كَثِيرٍۢ ۚ قَدْ جَآءَكُم مِّنَ ٱللَّهِ نُورٌۭ وَكِتَٰبٌۭ مُّبِينٌۭ

“ከብዙውም የሚተው ሲኾን” ማለት የመጽሐፉ ባለቤቶች ከደበቋቸው ሁሉንም አልተናገሩም ማለት ነው፤ ግን ወደ ነብያት የወረደውን አንኳር መልእክት አምላካችን አላህ ለነብያችን”ﷺ” ተርኮታላቸዋል፦
11:120 *”ከመልክተኞቹም “ወሬዎች” ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “እንተርክልሃለን”*َ፤ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ
20:99 እንደዚሁ በእርግጥ ካለፉት “ወሬዎች” በአንተ ላይ *“እንተርካለን”* َ፤ كَذَٰلِكَ نَقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ مَا قَدْ سَبَقَ

አላህ ካለፉት ወደ መልእክተኞች የወረዱትን ጭብጥ ተርኮታል፤ “ወሬ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ነበእ” نَبَإِ ሲሆን “ነቢይ” نبي የሚለው ቃል የመጣበት ዝሪያ ሲሆን “ንግግር” ማለት ነው፤ ይህ መለኮታዊ ንግግር ወሕይ ነው፤ ቁርአን ከእርሱ በፊት ወደ ነብያት የተወረደውን የሚያረጋግጥ እና በውስጡ ያለውን የሚዘረዝር ሲሆን ከዓለማቱ ጌታ የተወረደ ነው፦
10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን *”ከእርሱ በፊት ያለውን”* የሚያረጋግጥ እና *”በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር”* በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ وَمَا كَانَ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ ٱلَّذِى بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

ከአላህ ዘንድ ወደ ነብያት የወረዱት መጽሐፍት በውስጡ የነበረውን የትምህርት ጭብጥ ቁርአን በመዘርዘር ያረጋግጣል፤ ካረጋገጠው ጭብጥ ለናሙና ያክል ወደ ነብያቱን ሲያወርድ የነበረው ወሕይ በዐቂዳህ ነጥብ፦ “እነሆ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም” ማለትን ሲሆን በፊቅህ ነጥብ ደግሞ “መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን” ነው፦
16፥2 ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል ከሓዲዎችን በቅጣት አስጠንቅቁ፤ *”እነሆ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም”* ማለትን አስታውቁ በማለት ያወርዳል፡፡ يُنَزِّلُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ بِٱلرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦٓ أَنْ أَنذِرُوٓا۟ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱتَّقُونِ
21፥73 *”ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን”*፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِمْ فِعْلَ ٱلْخَيْرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰة

ስለዚህ ከላይ የተነሳው ስሁት ሙግት ውሃ የሚቋጥር አይደለም፤ የንዑዱ የአላህ ኅሩያን እንዲህ ሳይቃጠል በቅጠል ድባቅ ያስገቡታል፤ ዐሊሞቻችን ጋር ያሉት ዒልም በስፋትና በልፋት፤ በጥልቀትና በምጥቀት ነው። ሡመ አልሀምዱ ሊልላህ!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርኣን አወራረድ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥106 *ቁርአንንም በሰዎች ላይ ሆነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፤ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው*። وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا

"ኑዙል" نُزُل ማለት "አወራረድ" ማለት ሲሆን "ተንዚል" تَنزِيل ማለት ደግሞ "የተወረደ"Revelation" ማለት ነው፤ ሁለቱም ቃላት "አንዘለ" أَنْزَلَ ወይም "ነዝዘለ" نَزَّلَ ማለትም "አወረደ" ወይም "ገለጠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጡ ናቸው። አላህ ወደ ነብያት ተንዚል የሚያወርድበት መንገድ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም፦ በራዕይ፣ ወይም ከግርዶ ወዲያ እና መልክተኛን መልአክን ልኮ በፈቃዱ የሚሻውን ያወርዳል፦
42:51 *ለሰው” አላህ “በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም*፤ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ረሱል” رَسُول የሚለው ቃል “ተላላኪ” ማለት ሲሆን “መለክ” مَلَك ማለትም “መልአክ” የሚለው ቃል ተለዋዋጭ”inter-change” ሆኖ የመጣ ነው፤ ይህም የወህይ መልአክ ጂብሪል ነው፤ አላህ ቁርኣን ለነብያችን”ﷺ” ያወረደው በሦስተኛው መንገድ ነው ፤ “መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን የሚያወርድለት ቢሆን እንጅ” የሚለው ይሰመርበት፤ ጂብሪልም መልአክ እንደመሆኑ መጠን ከአላህ ወደ ነብያችን”ﷺ” ቀልብ ቁርኣንን በአላህ ፈቃድ አውርዶታል፦
2፥97 ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ *እርሱ ቁርኣኑን ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና*፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

“በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና” የሚለው ሃይለ-ቃል እና “መልክተኛን መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን የሚያወርድለት ቢሆን እንጅ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ጅብሪል ተልኮ የመጣ መልአክ ነውና ከራሱ አመንጭቶ አይደለም ያወረደው፤ ከዛ ይልቅ አላህ ወደ ባሪያው ያወረደውን ጂብሪል አወረደው፦
53፥10 *ወደ ባሪያውም አላህ ያወረደውን አወረደ*፡፡ فَأَوْحَىٰ إِلَىٰ عَبْدِهِ مَا أَوْحَىٰ

የቁርኣን አወራረዱ ሁለት አይነት ነው፤ አንዱ በጠቅላላ አንድ ጊዜ ከለውሐል መሕፉዝ ማለትም ከተጠበቀው ሰሌዳ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ሲሆን ሁለተኛው ከቅርቢቱ ሰማይ ወደ ነብያችን"ﷺ" ልብ ቀስ በቀስ ለ 23 ዓመት ወረደ፤ ይህንን ነጥብ በነጥብ እስቲ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ጁምለተን ዋሒዳህ"
ቁርኣን በለውሐል መሕፉዝ ማለትም በተጠበቀው ሰሌዳ የተከተበ የአላህ ዕውቀት ነው፤ ይህ ዕውቀት ጊዜውን ጠብቆ ከመውረዱ በፊት ተከትቦ ነበር፤ ለዛ ነው ቁርኣን በተጠበቀ ሰሌዳ ወይም በመጽሐፉ እናት ውስጥ ነው የተባለው፦
85፥21-22 ይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡ *የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው*፡፡ بَلْ هُوَ قُرْءَانٌۭ مَّجِيدٌۭ فِي لَوْحٍ مَّحْفُوظٍ
56፥77-78 እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡ *በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥ ነው*፡፡ إِنَّهُۥ لَقُرْءَانٌۭ كَرِيمٌۭ فِى كِتَٰبٍۢ مَّكْنُونٍۢ
43፥3-4 እኛ ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው፡፡ *እርሱም በመጽሐፉ እናት ውስጥ እኛ ዘንድ በእርግጥ ከፍተኛ ጥበብ የተመላ ነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَٰهُ قُرْءَٰنًا عَرَبِيًّۭا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ وَإِنَّهُ فِي أُمِّ الْكِتَابِ لَدَيْنَا لَعَلِيٌّ حَكِيمٌ

"ጁምለተን ዋሒዳህ" جُمْلَةً وَاحِدَةً ማለት "በጠቅላላ አንድ ጊዜ" ማለት ነው፤ ይህ የአላህ ንግግር ከለውሐል መሕፉዝ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ በረመዳን ወር፣ በመወሰኛይቱ ሌሊት፣ በተባረከችው ሌሊት ወረደ፦
2፥185 እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድ እና እውነትን ከውሸት ከሚለዩም ገላጮች ሲኾን *ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው*፡፡ شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ
97፥1 *እኛ ቁርኣኑን በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ
44፥3 *እኛ ቁርኣኑን በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَة

"አወረድነው" ለሚለው ቃል የተቀመጠው "አንዘልናሁ" أَنْزَلْنَاهُ ሲሆን "አንዘለ" أَنْزَلَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ይህም ቃል በቁርኣን ቋንቋ በአንድ ጊዜ መውረድን ያመለክታል፤ በዚህ ጊዜ በአንዴ ሲወርድ ከሱረቱል ፋቲሐህ ይጀምር እና ሱረቱ አን-ናስ ላይ ይጠናቀቃል። ነገር ግን ከቅርቢቱ ሰማይ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ልብ ሲወርድ አወራረድ የሚጀምረው ከሱረቱል ዐለቅ 96፥1-5 ሲሆን የሚጠናቀቅ ደግሞ በሱረቱል በቀራህ 2፥281 ነው። ኢንሻላህ ይህንን ነጥብ በክፍል ሁለት እንዳስሳለን...

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርኣን አወራረድ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥106 *ቁርአንንም በሰዎች ላይ ሆነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፤ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው*። وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا

ነጥብ ሁለት
"ተርቲል"
በመቀጠል ቁርኣን ከቅርቢቱ ሰማይ ወደ ነብያችን"ﷺ" ልብ በጨረቃ አቆጣጠር ከ 610 ዓመተ-ልደት እስከ 632 ዓመተ-ልደት ለ 23 ዓመት ቀስ በቀስ ወረደ፤ ለ 13 ዓመት 86 ሱራዎች በመካ ሲሆን 28 ደግሞ የወረዱት ለ 10 ዓመት በመዲና ነው፣ ይህም ቀስ በቀስ በተለያየ ጊዜ አወራረዱ "ተርቲል" تَرْتِيل ይባላል፦
25፥32 እነዚያ የካዱትም *«ቁርኣን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም» አሉ፡፡ እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ ከፋፍለን አወረድነው፤ ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው*፡፡ وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْلَا نُزِّلَ عَلَيْهِ الْقُرْآنُ جُمْلَةً وَاحِدَةً ۚ كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِ فُؤَادَكَ ۖ وَرَتَّلْنَاهُ تَرْتِيلًا
17፥106 *ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፤ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው*፡፡ وَقُرْءَانًۭا فَرَقْنَٰهُ لِتَقْرَأَهُۥ عَلَى ٱلنَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍۢ وَنَزَّلْنَٰهُ تَنزِيلًۭا

"አወረድነው" ለሚለው ቃል የተቀመጠው "ነዝዘልናሁ" نَزَّلْنَاهُ ሲሆን "ነዝዘለ" نَزَّلَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ይህም ቃል በቁርኣን ዐረቢኛ ቋንቋ ቀስ በቀስ በተለያየ ጊዜ መውረድን ያመለክታል፤ እዚሁ አንቀጽ ላይ "ተንዚላ" تَنزِيلًۭا የሚለው የተንዚል አንስታይ መደብ ነው፤ "ተንዚል" تَنزِيل የሚለው ቃል 15 ጊዜ ለቁርኣን ተጠቅሷል፦
26፥192 *እርሱም ቁርኣን በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ وَإِنَّهُ لَتَنزِيلُ رَبِّ الْعَالَمِين

ከሱረቱል ዐለቅ 96፥1-5 እስከ ሱረቱል በቀራህ 2፥281 ቀስ በቀስ በተለያየ ጊዜ ከዐለማቱ ጌታ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ልብ ሲያወርድ የነበረው ጂብሪል ነው፦
26፥193 *እርሱን ታማኙ መንፈስ ጂብሪል አወረደው*፤ نَزَلَ بِهِ الرُّوحُ الْأَمِين
16፥102 እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር *ቁርኣንን ቅዱሱ መንፈስ ጂብሪል እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው* በላቸው፡፡ قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِالْحَقِّ لِيُثَبِّتَ الَّذِينَ آمَنُوا وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُسْلِمِينَ
2፥97 *ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው*፡፡ እርሱ ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን *በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና*፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِين
ቁርኣን መጽሐፍ ሆኖ የወረደው ወደ ነብያችን”ﷺ” ልብ ነው፤ ልብ ላይ የተሰበሰበው ንባብ ደግሞ መጽሐፍ ይባላል እንጂ በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ አልወረደም፦
26፥194 ከአስስጠንቃቂዎቹ ትኾን ዘንድ *በልብህ ላይ አወረደው*፡፡ عَلَىٰ قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ الْمُنذِرِينَ
2፥97 *በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና*፡፡ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ
75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ
6፥7 *በአንተም ላይ በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ ባወረድንና በእጆቻቸው በነኩት ኖሮ እነዚያ የካዱት ሰዎች «ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም» ባሉ ነበር*፡፡ وَلَوْ نَزَّلْنَا عَلَيْكَ كِتَابًا فِي قِرْطَاسٍ فَلَمَسُوهُ بِأَيْدِيهِمْ لَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا إِنْ هَـٰذَا إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ

“ቂርጧስ” قِرْطَاس ማለት በብራና የተጻፈ “ወረቀት” ነው፤ ቁርኣን በዚህ ቁስ ተጽፎ አልወረደም፤ ስለዚህ አላህ መጽሐፍ የሚለው በብራና፣ በሰሌን፣ በስስ ድንጋይ፣ በሰሌዳ፣ በበግ አጥንት፣ በዘንባባ ቅርፊት ፣ በቴምር ቅጠል፣ በከብት ቆዳ በመሳሰሉት ላይ 48 የሚያክሉ እነ አቡበከር፣ ዑመር፣ ዑስማን፣ ዐሊይ፣ ዙበይር፣ ዑበይ፣ ሙአዊያህ፣ ዘይድ ኢብኑ ሳቢት በተፃፉ ጊዜ ሳይሆን ከዓለማቱ ጌታ ሲወርድ ነው፦
7፥2 *ይህ ወደ አንተ የተወረደ መጽሐፍ ነው፡፡ በደረትህም ውስጥ ከእርሱ ጭንቀት አይኑር*፡፡ كِتَابٌ أُنزِلَ إِلَيْكَ فَلَا يَكُن فِي صَدْرِكَ حَرَجٌ مِّنْهُ لِتُنذِرَ بِهِ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
29፥51 *እኛ መጽሐፉን በእነርሱ ላይ የሚነበብ ኾኖ በአንተ ላይ ማውረዳችን አይበቃቸውምን?* أَوَلَمْ يَكْفِهِمْ أَنَّا أَنزَلْنَا عَلَيْكَ الْكِتَابَ يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ

ቁርኣን ቀስ በቀስ በተለያየ ጊዜ የወረደበት ምክንያት የሰዎችን ጥያቄና የአስተሳሰብ ደረጃ ዋቢ ያደረገ ነው፤ በጥያቄ ሲመጡ እውነተኛውን ምላሽ በመስጠት ከመጠየቃቸው በፊት ይጠይቁሃል እንዲህ በላቸው እያለ መልስ ይሰጣል፦
25፥33 *በጥያቄም አይመጡብህም እውነተኛውን መልስ፣ መልካምን ፍች የምናመጣልህ ብንኾን እንጅ*። وَلَا يَأْتُونَكَ بِمَثَلٍ إِلَّا جِئْنَاكَ بِالْحَقِّ وَأَحْسَنَ تَفْسِيرًا
17፥85 *ስለ ሩሕም ይጠይቁሃል፤ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው፤ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው*፡፡ وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلرُّوحِ ۖ قُلِ ٱلرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّى وَمَآ أُوتِيتُم مِّنَ ٱلْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًۭا
ይህ የጊዜውን ቅድመ-ተከተል ያማከለ ተከታታይ ግህደተ-መለኮት”progressive revelation” እና ዘመነ-መግቦት”dispensation” ነው፤ ይህ ግልጠተ-መለኮት ነብያችን”ﷺ” በዕድሜ 40 ዓመት ሲሞላቸው የጀመረ ሲሆን ከ 23 ዓመት ቆይታ በኃላ ሊሞቱ 9 ቀር ሲቀራቸው በ 63 እድሚያቸው ተጠናቋል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 4
አነሥ ኢብኑ ማሊክረ.ዐ.” እንደተረከው፦ *”አላህ በመልእክተኛው ላይ ከመሞታቸው በፊት እስኪሞቱ ድረስ በተከታታይ ወሕይን አወረደ፤ ያም የወሕይ ታላቁ ክፍል ነበር፤ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ኪዚያም ሞቱ*። قَالَ أَخْبَرَنِي أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ اللَّهَ، تَعَالَى تَابَعَ عَلَى رَسُولِهِ صلى الله عليه وسلم قَبْلَ وَفَاتِهِ حَتَّى تَوَفَّاهُ أَكْثَرَ مَا كَانَ الْوَحْىُ، ثُمَّ تُوُفِّيَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم بَعْدُ‏.‏
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 46, ሐዲስ 3652
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”ነብዩ በመካ 13 ዓመት ወሕይ እየተቀበሉ ቆይተዋል፤ 63 እድሜያቸው በሆነ ጊዜ ሞተዋል*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ مَكَثَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم بِمَكَّةَ ثَلاَثَ عَشْرَةَ – يَعْنِي يُوحَى إِلَيْهِ وَتُوُفِّيَ وَهُوَ ابْنُ ثَلاَثٍ وَسِتِّينَ ‏.

እዚህ ላይ የሚያጅበት ቁርአን 114 ሱራዎች እና 6,236 አናቅጽ አሉት፣ ቁርኣን አንቀጾቹ የተሰካኩ መጽሐፍ ነው፤ አንቀጾቹ ብቻ ሳይሆን ሱራዎቹም ከአላህ የወረዱ ናቸው፦
11፥1 አሊፍ ላም ራ፤ *ይህ ቁርኣን አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው*፡፡ *ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ የተወረደ ነው*፡፡ الر ۚ كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ
47፥20 እነዚያም ያመኑት ሰዎች መታገል ያለባት *«ሱራ አትወርድም ኖሮአልን?» ይላሉ፡፡ የጠነከረችም ሱራ በተወረደች* እና በውስጧም መጋደል በተወሳ ጊዜ እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ የንፍቅና በሺታ ያለባቸውን ሰዎች ከሞት የኾነ መከራ በርሱ ላይ እንደ ወደቀበት ሰው አስተያየት ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ፡፡ ለእነሱም ወዮላቸው፡፡ وَيَقُولُ الَّذِينَ آمَنُوا لَوْلَا نُزِّلَتْ سُورَةٌ ۖ فَإِذَا أُنزِلَتْ سُورَةٌ مُّحْكَمَةٌ وَذُكِرَ فِيهَا الْقِتَالُ ۙ رَأَيْتَ الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ يَنظُرُونَ إِلَيْكَ نَظَرَ الْمَغْشِيِّ عَلَيْهِ مِنَ الْمَوْتِ ۖ فَأَوْلَىٰ لَهُمْ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርኣን አሰባሰብ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ

"ቁርኣን" قُرْءَان ማለት "በልብ ታፍዞ በምላስ የሚነበነብ መነባነብ" ማለት ሲሆን ይህም ቁርኣን አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነብያችን"ﷺ" የሚያስቀራቸው ቂራኣት ነው፦
2፥252 *እነዚህ በእውነት በአንተ ላይ የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ አንቀጾች ናቸው*፤ تِلْكَ آيَاتُ اللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِالْحَ
87፥6 *ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም*፡፡ سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰ
75:18 *ባነበብነውም ጊዜ ንባቡን ተከተል*። فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَه
75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ

"ማንበቡ" ለሚለው ቃል የገባው "ቁርኣነሁ" َقُرْآنَهُ ሲሆን የግስ መደብ ነው፤ የስም መደቡ ደግሞ "ቁርኣን" قُرْءَان ነው፤ ይህ የሚነበበው አንቀጽ የአላህ የራሱ ንግግር ስለሆነ አላህ በመጀመሪያ መደብ "አያቱና" آيَاتُنَا ማለትም "አንቀጾቻችን" በማለት ይናገራል፦
46፥7 *በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጾች ኾነው በተነበቡ ጊዜ* እነዚያ እውነቱን በመጣላቸው ጊዜ የካዱትን «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡ وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ قَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِلْحَقِّ لَمَّا جَاءَهُمْ هَـٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ

"ቃሪእ" قَارِئ‎ ማለት "በልብ አፍዞ በምላስ አነብናቢ"reciter" ማለት ነው፤ የቃሪእ ብዙ ቁጥር "ቁርራ" قُرَّاء ነው፤ አንድ ቃሪ የሆነ ሰው ቁርኣንን ሲቀራ አዳማጩ የሚያደምጠው የአላህን ንግግር ነው፦
7፥204 *ቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፤ ጸጥም በሉ፤ ይታዘንላችኋልና*፡፡ وَإِذَا قُرِئَ الْقُرْآنُ فَاسْتَمِعُوا لَهُ وَأَنصِتُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
9፥6 ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ *የአላህን ንግግር ይሰማ ዘንድ አስጠጋው*፡፡ وَإِنْ أَحَدٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَامَ اللَّهِ

አምላካችን አላህ ይህንን የእርሱን ንግግር ነብያችን"ﷺ" በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነው ያነቡት ዘንድ ቀስ በቀስ አወረደው፦
17፥106 *ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው*፤ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው፡፡ وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا

ይህ የአላህ ንግግር በሁለት መልኩ ተሰብስቧል፤ አንዱ በሰዎች ልብ ውስጥ በመታፈዝ ደረጃ ሲሆን ሁለተኛው በጽሑፍ በመጻፍ ደረጃ ነው፤ ይህንን ነጥብ በነጥብ ጥርስና ምላሱን እየነቀስን እንመልከት፦
ነጥብ አንድ
"ዚክር"
“ዚክር” ذِكْر የሚለው ቃል “ዘከረ” ذَكَرَ ማለትም “አስታወሰ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማስታወስ”memorization" ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ ቁርኣን በልብ እንዲታፈዝ አግርቶታል፦
54፥17 *ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው፡፡ አስታዋሽም አለን?* وَلَقَدْ يَسَّرْنَا ٱلْقُرْءَانَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍۢ

አላህ፦ እኔ ቁርኣንን በቃላችሁ እንድትዙት ገር አርጌዋለው፤ ሙደኪር የት አለ? ብሎ ይጠይቃል፤ "ሙደኪር" مُّدَّكِرٍۢ ማለት "አስታዋሽ"Memorizer" ማለት ነው፤ አላህ ቁርአንን በቀልባችን እንድናፍዘው ብቻ ሳይሆን ስንቀራው በምላስ እንዲቀል እና በዐረቢኛው ቋንቋ እንድንገነዘበው አግርቶታል፦
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّآ أَنزَلْنَٰهُ قُرْءَٰنًا عَرَبِيًّۭا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
44፥58 *ቁርአኑን በምላስህ ያገራነው ይገነዘቡ ዘንድ ነው*። فَإِنَّمَا يَسَّرْنَاهُ بِلِسَانِكَ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
And indeed, We have eased the Qur’an in your tongue that they might be reminded.

“ዩሥራ” يُسْرَىٰ ማለት “ገር” ወይም “ቀላል” ማለት ሲሆን በልብ ለማስታወስ፣ በምላስ ላይ ለመቅራት፣ በቋንቋው ለመረዳት አግርቶታል። “ሊሣን” لِسَان የሚለው ቃል “ምላስ” ወይም “ቋንቋ” ማለት ነው፤ አላህ ቁርአንን በልባችን እንደሚሰበስበው ቃል ገብቶልናል፦
75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ
ኢማም ሙስሊም: መጽሐፍ 4, ሐዲስ 166
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"በአላህ አዘ ወጀል ንግግር፦ "በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ" ነብዩ"ﷺ" ጂብሪል ወደ እሳቸው ሲያወርድ ምላሳቸውና ከንፈራቸውን ለማንበብ በማንበብ ያላውሱ ስለነበር ነው፤ ይህ ችግር አልፎ አልፎ ይታይ ነበርና፤ አላህ ተዓላ፦ "በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ" የሚለውን አወረደ፤ "በልብህ ውስጥ መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና" ብሎ ሰበሰበው፤ በእርግጥም በልብህ ውስጥ እንድትቀራው እንጠብቀዋለን አንተም ትቀራዋለህ" ማለት ነው፤ "ባነበብነውም ጊዜ ካለቀ በኋላ ንባቡን ተከተል፣ ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው" ማለት "በምላስህ ላይ ማስቀመጡ በእኛ ላይ ነው" ማለት ነው፤ ጂብሪል ወደ እርሳቸው በሚመጣ ጊዜ ዝም ይላሉ፤ ከእርሳቸው በተለየ ጊዜ አላህ ቃል እንደገባላቸው ይቀራሉ*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، فِي قَوْلِهِ عَزَّ وَجَلَّ ‏{‏ لاَ تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ‏}‏ قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِذَا نَزَلَ عَلَيْهِ جِبْرِيلُ بِالْوَحْىِ كَانَ مِمَّا يُحَرِّكُ بِهِ لِسَانَهُ وَشَفَتَيْهِ فَيَشْتَدُّ عَلَيْهِ فَكَانَ ذَلِكَ يُعْرَفُ مِنْهُ فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى ‏{‏ لاَ تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ لِتَعْجَلَ بِهِ‏}‏ أَخْذَهُ ‏{‏ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ‏}‏ إِنَّ عَلَيْنَا أَنْ نَجْمَعَهُ فِي صَدْرِكَ ‏.‏ وَقُرْآنَهُ فَتَقْرَأُهُ ‏{‏ فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَهُ‏}‏ قَالَ أَنْزَلْنَاهُ فَاسْتَمِعْ لَهُ ‏{‏ إِنَّ عَلَيْنَا بَيَانَهُ‏}‏ أَنْ نُبَيِّنَهُ بِلِسَانِكَ فَكَانَ إِذَا أَتَاهُ جِبْرِيلُ أَطْرَقَ فَإِذَا ذَهَبَ قَرَأَهُ كَمَا وَعَدَهُ اللَّهُ ‏
በአሰባሰቡ ጉዳይ ላይ ሚሽነሪዎች የሚያነሱት የመርሳት ጉዳይ ነው፤ አንድ ነብይ ማንኛውም ሰው እንደሚዘነጋ ይዘነጋል፤ አደም፣ ሙሳ፣ ነብያችንም"ﷺ" ቢሆኑ ይረሳሉ፦
20፥115 ወደ አደምም ከዚህ በፊት ኪዳንን በእርግጥ አወረድን፡፡ *ረሳም*፡፡ ለእርሱም ቆራጥነትን አላገኘንለትም፡፡ وَلَقَدْ عَهِدْنَا إِلَىٰ آدَمَ مِن قَبْلُ فَنَسِيَ وَلَمْ نَجِدْ لَهُ عَزْمًا
18፥73 *«በረሳሁት ነገር አትያዘኝ፡፡ ከነገሬም ችግርን አታሸክመኝ»* አለው፡፡ قَالَ لَا تُؤَاخِذْنِى بِمَا نَسِيتُ وَلَا تُرْهِقْنِى مِنْ أَمْرِى عُسْرًۭا
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 1260 
ዐብደላህ እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ሶላት ላይ ይጨምሩ ወይም ይቀንሱ ነበር፤ ኢብራሂምም፦ "ይህ መወዛገብ ከእኔ ነው" አለ፤ እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንዳንድ ጊዜ ሶላት ላይ ይጨምራሉን? እርሳቸውም፦ "እኔ ሰው ብቻ ነኝ፤ እናንተ እንደምትረሱ እኔም እረሳለው፤ ማንም ከረሳ ሁለት ረከዐት ይስገድ። ከዚያም ነብዩ"ﷺ" ተመልሰው ሁለቴ ሰገዱ*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ صَلَّى رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَزَادَ أَوْ نَقَصَ - قَالَ إِبْرَاهِيمُ وَالْوَهْمُ مِنِّي - فَقِيلَ لَهُ يَا رَسُولَ اللَّهِ أَزِيدَ فِي الصَّلاَةِ شَىْءٌ قَالَ ‏ "‏ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ أَنْسَى كَمَا تَنْسَوْنَ فَإِذَا نَسِيَ أَحَدُكُمْ فَلْيَسْجُدْ سَجْدَتَيْنِ وَهُوَ جَالِسٌ ‏"‏ ‏.‏ ثُمَّ تَحَوَّلَ النَّبِيُّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَسَجَدَ سَجْدَتَيْنِ ‏.‏

እዚህ ሐዲስ ላይ ነብያችን"ﷺ" እኔ ሰው ብቻ ነኝ፤ እናንተ እንደምትረሱት እኔም እረሳለው" ያሉት ሶላት ላይ ረከዐትን መጨመርና መቀነስ እንጂ በፍጹም ስለ ቁርኣን መርሳት ሽታው እንኳን የለም። ሌላው ሂስ ይህ ሐዲስ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 62
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አንድ ሰው በሌሊት ሱራህን ሲቀራ እና እንዲህ ሲል ሰምተውታል፦ "የአላህ ምህረት በእርሱ ላይ ይሁን! የረሳኃትን እንዲህና እንዲያ የሚሉ ከሱራህ አንቀጽ አስታወሰኝ*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ سَمِعَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم رَجُلاً يَقْرَأُ فِي سُورَةٍ بِاللَّيْلِ فَقَالَ ‏ "‏ يَرْحَمُهُ اللَّهُ لَقَدْ أَذْكَرَنِي كَذَا وَكَذَا آيَةً كُنْتُ أُنْسِيتُهَا مِنْ سُورَةِ كَذَا وَكَذَا ‏"‌‏.‏

ሐዲሱ ላይ እረሳሁት የሚለው ሰው በሌሊት ሲቀራ የነበረው ሰው እንጂ እርሳቸው አይደሉም።
ሲቀጥል የሐዲሱ አርስት ላይ፦ "የቁርኣን መርሳት እና "እንዲህና እንዲያ የሚሉ አንቀጽ እረሳሁኝ" የሚል" بَابُ نِسْيَانِ الْقُرْآنِ وَهَلْ يَقُولُ نَسِيتُ آيَةَ كَذَا وَكَذَا
ተብሎ ተቀምጧል።
ሢሰልስ በሌሎች ሐዲሶች ላይ እንዲህና እንዲያ የሚሉ አናቅጽ የሚረሳው ማን እንደሆነ በስፋት ተብራርቷል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 63
ዐብደሏህ እንደተረከው፦ *"ነብዩም"ﷺ" አሉ፦ "ለምን ከእነርሱ አንዱ፦ "እንዲህና እንዲያ የሚሉ አናቅጽ እረስቻለው ይላል? በእርግጥም እረስቶታል*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَا لأَحَدِهِمْ يَقُولُ نَسِيتُ آيَةَ كَيْتَ وَكَيْتَ‏.‏ بَلْ هُوَ نُسِّيَ ‏"‌‏.‏
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 54
ዐብደሏህ እንደተረከው፦ *"ነብዩም"ﷺ" አሉ፦ "አሳፋሪ ነገር ከእነርሱ አንዱ፦ "እንዲህና እንዲያ የሚሉ የቁርኣን አናቅጽ እረስቻለው" የሚል ነው፤ በእርግጥም እረስቶታል፤ ቁርኣንን ከግመል ፍጥነት ይልቅ ከሰው ልብ ያመልጣልና በደንብ ያዙት*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ بِئْسَ مَا لأَحَدِهِمْ أَنْ يَقُولَ نَسِيتُ آيَةَ كَيْتَ وَكَيْتَ بَلْ نُسِّيَ، وَاسْتَذْكِرُوا الْقُرْآنَ فَإِنَّهُ أَشَدُّ تَفَصِّيًا مِنْ صُدُورِ الرِّجَالِ مِنَ النَّعَمِ ‏

ሲያረብብ አምላካችን አላህ ቁርኣንን ለእርሳቸው አስቀርቶ እንደማይረሱት ቃል ገብቷል፦
87፥6 *ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም*፡፡ سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰ
87፥7 *አላህ ከሻው በስተቀር*፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡ إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ إِنَّهُ يَعْلَمُ الْجَهْرَ وَمَا يَخْفَىٰ

"አላህ ከሻው በስተቀር" ማለት አላህ አንድን አንቀጽ በማስረሳት በሌላ አንቀጽ ከመለወጥ በስተቀር ማለት ነው፤ ይህ ነሥኽ ይባላል፤ “ነሥኽ” نسخ ማለት “ሽረት”abrogation” ማለት ሲሆን ይህም ሽረት አንደኛው “ናሢኽ” الناسخ ማለትም “ሻሪ አንቀጽ”Abrogator” ሲሆን ሁለተኛው “መንሡኽ” المنسوخ ማለትም “ተሻሪ አንቀጽ”Abrogated” ነው፦
2፥106 *ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከእርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን*፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን አታውቅምን? مَا نَنسَخْ مِنْ آيَةٍ أَوْ نُنسِهَا نَأْتِ بِخَيْرٍ مِّنْهَا أَوْ مِثْلِهَا ۗ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
ነብያች"ﷺ" ሰው ናቸው ለጊዜው ቁርኣንን ይረሱ ነበር ቢባል እንኳን ጂብሪል በዓመት አንድ ጊዜ በረመዳን ወር ለዓመት ያክል ያስቀራቸውን ይደግምላቸው ነበር፤ እርሷቸውም ለዓመት የወረደውን በእርሱ ፊት ይቀሩ ነበር፤ ሊሞቱ ሲሉ ሁለቴ ደግሞላቸዋል፤ አንዱ ዓመታዊ ልማዱን ለመድገም ሲሆን ሁለተኛው አጠቃላይ ቁርኣንን ለማሳፈዝ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 20
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንዳለው፦ *“ጂብሪል ቁርኣንን በየዓመት አንዴ ለነብዩ"ﷺ" ይደግምላቸው ነበር፤ በሚሞቱበት ዓመት ግን ሁለቴ ደገመላቸው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ كَانَ يَعْرِضُ عَلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم الْقُرْآنَ كُلَّ عَامٍ مَرَّةً، فَعَرَضَ عَلَيْهِ مَرَّتَيْنِ فِي الْعَامِ الَّذِي قُبِضَ،
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 61, ሐዲስ 63
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነብዩ"ﷺ" ለሁሉም ሰው በጣም ለጋስ ነበሩ፤ የበለጠ በረመዷን ወር ጂብሪል በሚገናኛቸው ጊዜ ለጋስ ነበሩ፤ ሁልጊዜ በረመዳን ሌሊት ጂብሪል ሰላም በእርሱ ላይ ይሁን! ቁርኣንን ሊደግምላቸው ይገናኛቸው ነበር*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم أَجْوَدَ النَّاسِ، وَأَجْوَدُ مَا يَكُونُ فِي رَمَضَانَ، حِينَ يَلْقَاهُ جِبْرِيلُ، وَكَانَ جِبْرِيلُ ـ عَلَيْهِ السَّلاَمُ ـ يَلْقَاهُ فِي كُلِّ لَيْلَةٍ مِنْ رَمَضَانَ، فَيُدَارِسُهُ الْقُرْآنَ
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 19
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነብዩ"ﷺ" በጣም ለጋስ ነበሩ፤ የበለጠ በረመዷን ወር ረመዷን እስኪያልቅ ድረስ ጂብሪል በሚገናኛቸው ጊዜ ለጋስ ነበሩ፤ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ቁርኣንን ይቀሩለት ነበር። ጂብሪል በተገናኛቸው ጊዜ ከነፋስ ፍጥነት ይልቅ ለጋስ ነበሩ*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم أَجْوَدَ النَّاسِ بِالْخَيْرِ، وَأَجْوَدُ مَا يَكُونُ فِي شَهْرِ رَمَضَانَ لأَنَّ جِبْرِيلَ كَانَ يَلْقَاهُ فِي كُلِّ لَيْلَةٍ فِي شَهْرِ رَمَضَانَ حَتَّى يَنْسَلِخَ يَعْرِضُ عَلَيْهِ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْقُرْآنَ، فَإِذَا لَقِيَهُ جِبْرِيلُ كَانَ أَجْوَدَ بِالْخَيْرِ مِنَ الرِّيحِ الْمُرْسَلَةِ‏.‏

ይህ በቃል ደረጃ"oral form" የተሰበሰበው ቁርኣን በሙተዋቲር ከነብያችን"ﷺ" ወደ ሶሐባቦች፣ ከሶሐባዎች ወደ ታቢኢይዎች፣ ከታቢኢይዎች ወደ አትባኡ ታቢኢይዎች እያለ በሙተዋቲር አስራ አራት ትውልድ አሳልፎ መጥቷል፤ “ሙተዋቲር” مُتَواتِر ማለት ቁርኣን ከአንድ ኢስናድ በላይ በጀመዓ የሚደረግ ዘገባ ነው። አላህ ቁርኣንን እራሱ አውርዶ ከኋላውም ከፊቱም ውሸት እንዳይመጣበት እራሱ በአማኞች ልብ እንዲሰበሰብ ገር በማድረግ እና በምላስ እንዲቀራ ገር በማድረግ ይጠብቀዋል፦
15፥9 *እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን*፡፡ إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا ٱلذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
41፥42 *ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም*፡፡ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው፡፡ لَّا يَأْتِيهِ ٱلْبَٰطِلُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِۦ ۖ تَنزِيلٌۭ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍۢ

ኢንሻላህ በገቢር ሁለት በጽሑፍ ደረጃ የተሰበሰበውን ሙስሐፍ ጥልልና ጥንፍፍ አርገን እናያለን....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርኣን አሰባሰብ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ

ነጥብ ሁለት
"ሙስሐፍ"
አምላካችም አላህ ቁርኣንን በነብያችን"ﷺ" ልብ ላይ ያወረደው መነባነብ እንጂ በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ አላወረደም፦
26፥194 ከአስስጠንቃቂዎቹ ትኾን ዘንድ *በልብህ ላይ አወረደው*፡፡ عَلَىٰ قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ الْمُنذِرِينَ
2፥97 *በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና*፡፡ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ
6፥7 *በአንተም ላይ በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ ባወረድን እና በእጆቻቸው በነኩት ኖሮ እነዚያ የካዱት ሰዎች «ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም» ባሉ ነበር*፡፡ وَلَوْ نَزَّلْنَا عَلَيْكَ كِتَابًا فِي قِرْطَاسٍ فَلَمَسُوهُ بِأَيْدِيهِمْ لَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا إِنْ هَـٰذَا إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ

“ቂርጧስ” قِرْطَاس ማለት በብራና የተጻፈ “ወረቀት” ነው፤ ቁርኣን በዚህ ቁስ ተጽፎ አልወረደም፤ ወደ ነብያችን"ﷺ" ልብ የተወረደው መጽሐፍ ወሕይ ወይም ተንዚል ነው፦
7፥2 *ይህ ወደ አንተ የተወረደ መጽሐፍ ነው፡፡ በደረትህም ውስጥ ከእርሱ ጭንቀት አይኑር*፡፡ كِتَابٌ أُنزِلَ إِلَيْكَ فَلَا يَكُن فِي صَدْرِكَ حَرَجٌ مِّنْهُ لِتُنذِرَ بِهِ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

"ሙስሐፍ" مُصْحَف ማለት "የቁርአን ጥራዝ" ማለት ነው፤ ይህም ቁስ ብራና፣ ሰሌን፣ ስስ ድንጋይ፣ ሰሌዳ፣ የበግ አጥንት፣ የዘንባባ ቅርፊት፣ የቴምር ቅጠል፣ የከብት ቆዳ የመሳሰሉት ነው፤ ቁርኣን በነብያችን"ﷺ" የሕይወት ዘመን በተለያዩ ቁስ"Heterogeneous material" ማለትም በብራና፣ በሰሌን፣ በስስ ድንጋይ፣ በሰሌዳ፣ በበግ አጥንት፣ በዘንባባ ቅርፊት፣ በቴምር ቅጠል፣ በከብት ቆዳ በመሳሰሉት ላይ ተጻፈ። ነብያችን"ﷺ" ከስር ከስር የሚያጽፏቸው 48 የሚያክሉ ጸሐፊዎች እነ አቡበከር፣ ኡመር፣ ኡስማን፣ ዐሊይ፣ ዙበይር፣ ኡበይ፣ ሙአዊያህ፣ ዘይድ ኢብኑ ሣቢት ወዘተ ነበሯቸው። በጽሑፍ ደረጃም"graphic form" በዚህ መልኩ ተሰብስቧል፤ ዋቢ መጽሐፍ ይመልከቱ፦
ዛደል መዓድ መጽሐፍ 1 ቁጥር 117

ዋና ዋና ሰብሳቢዎቹ ኡባይ፣ ሙዐዝ ኢብኑ ጀበል፣ ዘይድ ኢብኑ ሣቢት እና አቡ ዘይድ ናቸው፦
ኢማም ቡኻሪይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 25
ቃታዳህ እንደተረከው፤ እኔ አነሥ ኢብኑ ማሊክን"ረ.ዐ"፦ *"በነብዩ"ﷺ" የሕይወት ዘመን ቁርአንን የሰበሰቡት እነማን ናቸው? ብዬ ጠየኩት፤ እርሱም፦ "ሁሉም ከአንሷር ኡባይ፣ ሙዐዝ ኢብኑ ጀበል፣ ዘይድ ኢብኑ ሣቢት እና አቡ ዘይድ ናቸው" ብሎ መለሰልኝ*። حَدَّثَنَا قَتَادَةُ، قَالَ سَأَلْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ ـ رضى الله عنه ـ مَنْ جَمَعَ الْقُرْآنَ عَلَى عَهْدِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ أَرْبَعَةٌ كُلُّهُمْ مِنَ الأَنْصَارِ أُبَىُّ بْنُ كَعْبٍ وَمُعَاذُ بْنُ جَبَلٍ، وَزَيْدُ بْنُ ثَابِتٍ، وَأَبُو زَيْدٍ‏.‏
ኢማም ቡኻሪይ: መጽሐፍ 63, ሐዲስ 36
ቃታዳህ እንደተረከው፤ አነሥ"ረ.ዐ" እንደተናገረው፦ *"ቁርኣን በነብዩ"ﷺ" የሕይወት ዘመን በአራቱ ሰዎች ተሰብስቧል፤ ሁሉም ከአንሷር ኡባይ፣ ሙዐዝ ኢብኑ ጀበል፣ አቡ ዘይድ እና ዘይድ ኢብኑ ሣቢት ናቸው*። عَنْ قَتَادَةَ، عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ جَمَعَ الْقُرْآنَ عَلَى عَهْدِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَرْبَعَةٌ، كُلُّهُمْ مِنَ الأَنْصَارِ أُبَىٌّ، وَمُعَاذُ بْنُ جَبَلٍ، وَأَبُو زَيْدٍ، وَزَيْدُ بْنُ ثَابِتٍ‏.‏
ኢማም ቡኻሪይ: መጽሐፍ 63, ሐዲስ 26
አነሥ"ረ.ዐ" እንደተረከው፦ *"ቁርኣን ነብዩ"ﷺ" በሞቱ ጊዜ በአራቱ ሰዎች እንጂ አልተሰበሰበም፤ እነርሱም፦ አቡ አድ-ደርዳ(ኡባይ)፤ ሙዐዝ ኢብኑ ጀበል፣ ዘይድ ኢብኑ ሣቢት እና አቡ ዘይድ ናቸው*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ مَاتَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم وَلَمْ يَجْمَعِ الْقُرْآنَ غَيْرُ أَرْبَعَةٍ أَبُو الدَّرْدَاءِ وَمُعَاذُ بْنُ جَبَلٍ وَزَيْدُ بْنُ ثَابِتٍ وَأَبُو زَيْد
ይህ በተለያየ ቁስ ማለትም በብራና፣ በሰሌን፣ በስስ ድንጋይ፣ በሰሌዳ፣ በበግ አጥንት፣ በዘንባባ ቅርፊት፣ በቴምር ቅጠል፣ በከብት ቆዳ በመሳሰሉት ላይ የነበረው የቁርኣን ጥራዝ በአንድ ቁስ"homogeneous material" ላይ ተቀመጠ፤ ይህ መርሃ-ግብር በየማማህ ፍልሚያ ብዙዎች ቃሪእዎች ስለሞቱ በዑመር አሳቢነትና በአቡ በከር መሪነት ዘይድ ኢብኑ ሳቢት ከተለያየ ጥራዝ በመሰብስብ በቃሪእዎች ልብ ካለው ጋር እያመሳከረ የሱራዎቹን ቅድመ-ተከለተል ጂብሪል በተናገረበት፣ ነቢያችን"ﷺ" ባስተላለፉበት፣ ሰሃባዎች ባፈዙበት ቅድመ-ተከተል ማለትም ከሱረቱል ፋቲሐህ እስከ ሱረቱ አን-ናስ በአንድ ቅጸ-ጥራዝ"one volume" ላይ ተጠርዞ እንዲቀመጥ አደረገው።
ይህ ወጥ አንድ ቅጸ-ጥራዝ"codex" አቡ በከር ዘንድ እስኪሞት ድረስ ተቀመጠ፤ ከዚያም ዑመር ዘንድ እስከ ሕይወቱ ማብቂያ ተቀመጠ፤ ከዚያም በስተመጨረሻ የዑመር ልጅ ሐፍሷህ ዘንድ ተቀመጠ፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 8
ዘይድ ኢብኑ ሳቢት እንደተረከው"ረ.ዐ."፦ *"የየማማህ ሕዝቦች በተገደሉ ጊዜ አቡ በከር ወደ እርሱ እንድመጣ ላከብኝ። ወደ እርሱ ስሄድ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ከእርሱ ጋር ተቀምጧል*፤ አቡ በከርም"ረ.ዐ." እንዲህ አለኝ፦ *ዑመር ወደ እኔ መጥቶ እንዲህ አለ፦ በየማማህ ፍልሚያ አብዛኛውን የቁርኣን ቃሪእዎች ተገለዋል፤ በሌሎች የፍልሚያ መስኮች የበለጠ ከባድ ግድያ በቃሪእዎቹ ሊፈጸሙ እንደሚችሉ እና ከቁርኣን ብዙ እንዳይጠፋ እሰጋለሁ፤ ስለዚህ ቁርኣን እንዲሰበሰብ እንድታዝ አበረታታካለው*። እኔም ለዑመር፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ያላደረጉትን ነገር እንዴት ላደርግ እችላለው? አልኩት፤ ዑመርም፦ "በአላህ ይሁንብህ! ይህ ሰናይ መርሃ-ግብር ነው" አለ። አላህም በዚህ ጉዳይ ልቤን እስከሚከፍትልኝ ድረስ ዑመር ያበረታታኝ ነበር፤ ያንን ዑመር ያጤነውን ሰናይ ሃልዮ እኔም ማጤን ጀመርኩኝ*።
ከዚያም አቡ በከር እኔን ዘይድን፦ *"አንተ ጥበበኛ ወጣት ነህ፤ ስለ አንተ ምንም አይነት ጥርጣሬ የለንም፤ አንተ ለአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ወሕይ ትጽፍላቸው ነበር፤ የቁርኣንን ጽሑፎች ፈልግና በአንድ ጥራዝ ሰብስባቸው" አለኝ። በአላህ! ቁርኣንን ለመሰብሰብ ከሚያዙኝ ይልቅ ከተራራዎች አንዱን እንድቀይር ቢያዙኝ አይከብደኝም ነበር፤ እኔም ለአቡበከር፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ያላደረጉትን ነገር እንዴት ላደርግ እችላለው? አልኩት*፤ አቡ በከርም፦ *"በአላህ ይሁንብህ! ይህ ሰናይ መርሃ-ግብር ነው" አለ። በዚህ ጉዳይ ለአቡ በከር እና ለዑመር"ረ.ዐ" ልባቸውን የከፈተው አላህም በዚህ ጉዳይ ልቤን እስከሚከፍትልኝ ድረስ አቡ በከር ያበረታታኝ ነበር። ከዚያም እኔም ቁርኣንን መፈለግ ጀመርኩኝ፤ ከዘንባባ ቅጠል፣ ከስስ ነጭ ድንጋይ ወዘተ እና ከሰዎች ልቦች ፍለጋዬን እስከ በአቢ ኹዘይመተል አንሷሪይ ጋር ሁለት የሱረቱል ተውባህ የመጨረሻ አናቅጽ እስከማገኝ ድረስ ሰበሰብኩት። እነዚህ ሁለት አናቅጽ ከማንም ጋር አላገኘሁም ከእርሱ ጋር በስተቀር*፤ እነርሱም፦ *"ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ እምነት ላይ የሚጓጓ .."9፥128-129 የሚሉ አናቅጽ ናቸው*።
*ያም የተጠረዘው ጥራዝ አቡ በከር ዘንድ እስኪሞት ድረስ ተቀመጠ፤ ከዚያም ዑመር ዘንድ እስከ ሕይወቱ ማብቂያ ተቀመጠ፤ ከዚያም በስተመጨረሻ የዑመር ልጅ ሐፍሷህ"ረ.ዐ." ዘንድ ተቀመጠ*። أَنَّ زَيْدَ بْنَ ثَابِتٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ أَرْسَلَ إِلَىَّ أَبُو بَكْرٍ مَقْتَلَ أَهْلِ الْيَمَامَةِ فَإِذَا عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ عِنْدَهُ قَالَ أَبُو بَكْرٍ ـ رضى الله عنه ـ إِنَّ عُمَرَ أَتَانِي فَقَالَ إِنَّ الْقَتْلَ قَدِ اسْتَحَرَّ يَوْمَ الْيَمَامَةِ بِقُرَّاءِ الْقُرْآنِ وَإِنِّي أَخْشَى أَنْ يَسْتَحِرَّ الْقَتْلُ بِالْقُرَّاءِ بِالْمَوَاطِنِ، فَيَذْهَبَ كَثِيرٌ مِنَ الْقُرْآنِ وَإِنِّي أَرَى أَنْ تَأْمُرَ بِجَمْعِ الْقُرْآنِ‏.‏ قُلْتُ لِعُمَرَ كَيْفَ تَفْعَلُ شَيْئًا لَمْ يَفْعَلْهُ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ عُمَرُ هَذَا وَاللَّهِ خَيْرٌ‏.‏ فَلَمْ يَزَلْ عُمَرُ يُرَاجِعُنِي حَتَّى شَرَحَ اللَّهُ صَدْرِي لِذَلِكَ، وَرَأَيْتُ فِي ذَلِكَ الَّذِي رَأَى عُمَرُ‏.‏ قَالَ زَيْدٌ قَالَ أَبُو بَكْرٍ إِنَّكَ رَجُلٌ شَابٌّ عَاقِلٌ لاَ نَتَّهِمُكَ، وَقَدْ كُنْتَ تَكْتُبُ الْوَحْىَ لِرَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَتَتَبَّعِ الْقُرْآنَ فَاجْمَعْهُ فَوَاللَّهِ لَوْ كَلَّفُونِي نَقْلَ جَبَلٍ مِنَ الْجِبَالِ مَا كَانَ أَثْقَلَ عَلَىَّ مِمَّا أَمَرَنِي مِنْ جَمْعِ الْقُرْآنِ قُلْتُ كَيْفَ تَفْعَلُونَ شَيْئًا لَمْ يَفْعَلْهُ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ هُوَ وَاللَّهِ خَيْرٌ فَلَمْ يَزَلْ أَبُو بَكْرٍ يُرَاجِعُنِي حَتَّى شَرَحَ اللَّهُ صَدْرِي لِلَّذِي شَرَحَ لَهُ صَدْرَ أَبِي بَكْرٍ وَعُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ فَتَتَبَّعْتُ الْقُرْآنَ أَجْمَعُهُ مِنَ الْعُسُبِ وَاللِّخَافِ وَصُدُورِ الرِّجَالِ حَتَّى وَجَدْتُ آخِرَ سُورَةِ التَّوْبَةِ مَعَ أَبِي خُزَيْمَةَ الأَنْصَارِيِّ لَمْ أَجِدْهَا مَعَ أَحَدٍ غَيْرَهُ ‏{‏لَقَدْ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مِنْ أَنْفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ‏}‏ حَتَّى خَاتِمَةِ بَرَاءَةَ، فَكَانَتِ الصُّحُفُ عِنْدَ أَبِي بَكْرٍ حَتَّى تَوَفَّاهُ اللَّهُ ثُمَّ عِنْدَ عُمَرَ حَيَاتَهُ ثُمَّ عِنْدَ حَفْصَةَ بِنْتِ عُمَرَ ـ رضى الله عنه ـ‏.‏
ዘይድ ሱረቱል ተውባህ 9፥128-129 ሌላ ማንም ጋር አላገኘው ማለት ሌላ ሰው ጋር አልነበረም አያሰኝም። ምክንያቱም እርሱ ነው ፈልጎ ያላገኘው እንጂ ሁሉም ሶሐባዎች አይደሉም፤ ሲቀጥል የፈለገው በጽሑፍ ደረጃ ያሉትን ስብስብ እንጂ በቃል የታፈዙትን አይደለም። ምክንያቱም ሊፈልግ የቻለው በቃል ደረጃ ስለሚያውቀው ነው። ይህንን ሱረቱል አሕዛብ 33፥23 ያለውን እንዴት እንደፈለገ በመገንዘብ መረዳት ይቻላል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 56, ሐዲስ 23
ኻሪያህ ኢብኑ ዘይድ እንደተረከው፦ *"ዘይድ ኢብኑ ሳቢትም"ረ.ዐ." አለ፦ "ቁርኣን ከተለያዩ ጽሑፎች በተሰበሰበ ጊዜ ከሱረቱል አሕዛብ አንቀጽ ላይ የተረሳች ግን እኔ ከአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ሲቀሯት የሰማኃትን ከማንም ጋር አላገኘኃትም፤ ያም ምስክርነት የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ስለ ሁለቱ ወንዶች እኩል ምስክርነት ነው፤ አንቀጹም፦ "ከአማኞቹ በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አሉ፤..."33፥23 የሚል ነው*። عَنْ خَارِجَةَ بْنِ زَيْدٍ، أَنَّ زَيْدَ بْنَ ثَابِتٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ نَسَخْتُ الصُّحُفَ فِي الْمَصَاحِفِ، فَفَقَدْتُ آيَةً مِنْ سُورَةِ الأَحْزَابِ، كُنْتُ أَسْمَعُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقْرَأُ بِهَا، فَلَمْ أَجِدْهَا إِلاَّ مَعَ خُزَيْمَةَ بْنِ ثَابِتٍ الأَنْصَارِيِّ الَّذِي جَعَلَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم شَهَادَتَهُ شَهَادَةَ رَجُلَيْنِ، وَهْوَ قَوْلُهُ ‏{‏مِنَ الْمُؤْمِنِينَ رِجَالٌ صَدَقُوا مَا عَاهَدُوا اللَّهَ عَلَيْهِ‏}‏

እነዚህ ሦስት አናቅጽ ከነብያችን"ﷺ" ሲቀሯት ባይሰማ ኖሮ ፍለጋ ባልወጣ ነበር። ምክንያቱም ቁርኣን ማለት በነጥብ አንድ እንደተመለከትነው በልብ የሚታፈዝ መነባነብ ነው። በጽሑፍ ደረጃ የተሰበሰቡት ጥራዞች ሁሉ ጠፉ ቢባል እንኳን ቁርኣን በቃሪእዎች ልብ ውስጥ አለ፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4937
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"ነብዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ያ ልክ ቁርኣንን በልቡ ሓፍዞ የሚቀራ በሰማይ ከተከበሩ ጸሐፊዎች(መላእክት) ጋር ይሆናል፤ ያ ልክ ቁርኣንን በልቡ እያወቀው በጣም እየከበደው የሚቀራ እጥፍ ምንዳ አለው*። عَنْ عَائِشَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَثَلُ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَهْوَ حَافِظٌ لَهُ مَعَ السَّفَرَةِ الْكِرَامِ الْبَرَرَةِ، وَمَثَلُ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَهْوَ يَتَعَاهَدُهُ وَهْوَ عَلَيْهِ شَدِيدٌ، فَلَهُ أَجْرَانِ ‏"‌‏.‏

ነብያችን"ﷺ" በሕይወታቸው ዘመን ማብቂያ ላይ ስለ ሙሉ ቁርኣን በልብ ውስጥ እንዴት እንደሚቀራ እንዲህ ተናግረዋል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 78
ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ *"ነብዩም"ﷺ" እኔን፦ "ሙሉ ቁርኣንን ቀርቶ ለመጨረስ ስንት ጊዜ ይወስድብሃል? ብለው ጠየቁኝ*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ لِي النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ فِي كَمْ تَقْرَأُ الْقُرْآنَ ‏"‌‏.‏
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 79
ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ "ሙሉ ቁርኣንን በአንድ ወር ጊዜ ቅራ"። እኔም፦ "ከዛ በታች ለመቅራት ችሎታው አለኝ" አልኩኝ፤ እርሳቸው፦ "በሰባት ቀናት ቅራው፤ ከዚያ በታች ሙሉውን ለመቅራት አይቻልም*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ اقْرَإِ الْقُرْآنَ فِي شَهْرٍ ‏"‌‏.‏ قُلْتُ إِنِّي أَجِدُ قُوَّةً حَتَّى قَالَ ‏"‏ فَاقْرَأْهُ فِي سَبْعٍ وَلاَ تَزِدْ عَلَى ذَلِكَ ‏"‌‏.‏

በሰባት ቀናት ከፋፍሎ መቅራት "መንዚል" منزل ይባላል፤ ሌላው ቁርኣን ሠላሳ ጁዝዕ" አለው፤ "ጁዝዕ" جُزْءْ‎ ማለት "ክፍል"part" ማለት ሲሆን በሠላሳ ቀናት ከፋፍሎ መቀራትን ያሳያል፤ በተለይ በተራዊህ ሶላት ላይ ሙሉ ሠላሳ ጁዝዕ ይቀራል፤ “ተራዊህ” تراويح‌‎ ማለትም “በረመዳን የሌሊት ሶላት” ማለት ነው። ስለዚህ ቁርኣን ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃሪእዎች ልብ ውስጥ በሙተዋቲር የሚተላለፍ ታምር ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ነሷራ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

5፥14 ከእነዚያም እኛ *ክርስቲያኖች* ነን ካሉት የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን፡፡ *በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት*፡፡ ስለዚህ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብንና ጥላቻን ጣልንባቸው፡፡ አላህም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ በእርግጥ ፡፡ وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا بِهِ فَأَغْرَيْنَا بَيْنَهُمُ ይነግራቸዋልالْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ ۚ وَسَوْفَ يُنَبِّئُهُمُ اللَّهُ بِمَا كَانُوا يَصْنَعُونَ

አምላካችን አላህ ለዒሳ ወንጌልን ሰጠው፤ በዚያ ወንጌል ውስጥ፦ “የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ” የሚል መመሪያ አለ፦
5፥46 በፈለጎቻቸውም ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲሆን፣ ፤ *ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን አስከተልንተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ሲሆን ሰጠነው*። وَقَفَّيْنَا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم بِعِيسَى ٱبْنِ مَرْيَمَ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلتَّوْرَىٰةِ ۖ وَءَاتَيْنَٰهُ ገሣጭٱلْإِنجِيلَ فِيهِ هُدًۭى وَنُورٌۭ وَمُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلتَّوْرَىٰةِ وَهُدًۭى وَمَوْعِظَةًۭ لِّلْمُتَّقِينَ
5፥47 የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ *አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ*፤ وَلْيَحْكُمْ أَهْلُ ٱلْإِنجِيلِ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فِيهِ

“ቀፈይና” قَفَّيْنَا ማለትም “አስከተልን” እና “አተይናሁ” آتَيْنَاهُ ማለትም “ሰጠነው” የሚሉት ያለቁ አላፊ ግስ ናቸው፤ “ልየሕኩም” َلْيَحْكُمْ ማለትም “ይፍረዱ” የሚለው ትዕዛዛዊ ግስ መነሻ ላይ “ወ” و ማለትም “እና” የሚል አያያዥ መስተጻምር አለ፤ ያ ማለት “ይፍረዱ” የሚለው ትዕዛዛዊ ግስ “አስከተልን” እና “ሰጠነው” ከሚሉት ግስ ጋር ተያይዞ የመጣ መሆኑ “አልን” የሚል ሙስጠጢር ማለትም ህቡዕ ግስ‘’headen verb‘’ አላፊ ሆኖ መጥቷል፣ ስለዚህ ‘’የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ አልን‘’ የሚል ፍቺ ይኖረዋል። ተፍሲሩል ጀላለይን በዚህ መልኩ ነው የፈሰረው፤ ለናሙና ያክል ሌላ ተጨማሪ ጥቅስ ብንመለከት ነገሩን የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል፦
19:12 የሕያ ሆይ! መጽሐፉን በጥብቅ *ያዝ*፣ ጥበብንም በሕጻንነቱ *ሰጠነዉ*። يَٰيَحْيَىٰ خُذِ ٱلْكِتَٰبَ بِقُوَّةٍۢ ۖ وَءَاتَيْنَٰهُ ٱلْحُكْمَ صَبِيًّۭا

“ሁዚ” خُذِ ማለትም “ያዝ” ትዕዛዛዊ ግስ ነው፤ “አተይናሁ” آتَيْنَاهُ ማለትም “ሰጠነው” የሚለው ቃል ደግሞ ያለቀ አላፊ ግስ ነዉ፣ “አተይናሁ” ከሚለው የሚለቅቃል በፊት “ወ” و ማለትም “እና” የሚል አያያዥ መስተጻምር አለ፤ ያ ማለት “ያዝ” የሚለው ግስ “ሰጠነው” ከሚለው ግስ ጋር ተያይዞ የመጣ መሆኑ “አልን” የሚል ሙስጠጢር አላፊ ሆኖ መጥቷል፣ ትዕዛዛዊስለዚህ ‘’መጽሐፉን በጥብቅ ያዝ አልነዉ‘‘’ የሚል ፍቺ እንደሚኖረው ሁሉ ከላይ ያለውንም በዚህ ሒሳብ እንረዳዋለን።

አምላካችን አላህ የኢንጅል ባለቤቶችን ከነበሩት ከዒሳ ቀዳማይ ጋር የከበደ ኪዳን አድርጓል፦
5፥14 ከእነዚያም እኛ *ክርስቲያኖች* ነን ካሉትጣልንባቸው የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን፡፡ *በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት*፡፡ ስለዚህ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብንና ጥላቻን ፡፡ አላህም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ በእርግጥ ይነግራቸዋል፡፡ وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُواተብሎ بِهِ فَأَغْرَيْنَا بَيْنَهُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ ۚ وَسَوْفَ يُنَبِّئُهُمُ اللَّهُ بِمَا كَانُوا يَصْنَعُونَ

“ክርስቲያኖች” የተቀመጠው ቃል “ነሷራ” نَصَارَىٰ ነው፤ “ነስራኒይ” نَصْرَانِيّ የሚለው ቃል በነጠላ ሲሆን በብዜት ደግሞ “ነሷራ” نَصَارَىٰ ነው፤ ይህም ቃል “ነሰረ” نَصَرَ ማለትም “ረዳ” ከሚል ግስ መደብ ወይም “ነስር” نَصْر ማለትም “እርዳታ” ከሚል ከስም መደብ የረባ ሲሆን ቋንቋዊው ፍቺው “ረዳቶች” ማለት ነው።
“ነሲር” نَصِير ወይም “ናሲር” نَاصِر ማለትም “እረዳት”፣ “መንሱር” مَنصُور ማለትም “የተረዳ”፣ “ሙንተሲር” مُّنتَصِر ማለትም “ተረጂ” የሚሉት ቃላት ልክ እንደ “ነሳራ” ቃል “ነሰረ” ከሚል ግስ መደብ ወይም “ነስር” ከሚል የስም መደብ የረቡ ናቸው፤ ይህ ስም በቁርኣን 15 ጊዜ ተውስቷል፤ እነዚህ የአላህ እና የመልእክተኛ የዒሳ እረዳቶች ሐዋርያት ናቸው፦
60፥14 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የመርየም ልጅ ዒሳ ለሐዋርያቶቹ «ወደ አላህ *ረዳቴ* ማነው?» እንዳለ ሐወርያቶቹም «እኛ የአላህ *ረዳቶች* ነን» እንዳሉትላይ የአላህ ረዳቶች ኹኑ፡፡ ከእስራኤልም ልጆች አንደኛዋ ጭፍራ አመነች፡፡ ሌላይቱም ጭፍራ ካደች፡፡ እነዚያን ያመኑትንም በጠላታቸው አበረታናቸው፤ አሸናፊዎችም ኾኑ፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُونُوٓا۟ أَنصَارَ ٱللَّهِ كَمَا قَالَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ لِلْحَوَارِيِّـۧنَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ ۖ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ ۖ فَـَٔامَنَت طَّآئِفَةٌۭ مِّنۢ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ وَكَفَرَت طَّآئِفَةٌۭ ۖ فَأَيَّدْنَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ عَلَىٰ عَدُوِّهِمْ فَأَصْبَحُوا۟ ظَٰهِرِينَ
3፥52 ዒሳ ከእነርሱ ክህደት በተሰማውም ጊዜ፡- «ወደ አላህ *ረዳቶቼ* እነማን ናቸው» አለ፤ ሐዋርያት፡- «እኛ የአላህ *ረዳቶች* ነን፤ በአላህ አምነናል፤ እኛም ትክክለኛ ታዛዦች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ فَلَمَّآ أَحَسَّ عِيسَىٰ مِنْهُمُ ٱلْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ ۖ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَٱشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

አላህ ከእነዚህ የእርሱ እና የመልእክተኛ እረዳቶች ጋር የከበደ ቃል ኪዳን አድርጓል፤ ይህምም ቃል ኪዳን “በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ» በማለት አዟል፤ አነዚህ የዒሳ ሐዋርያትም ይህንን ቃል አምነው ሙስሊሞች መሆናቸውን አስመስክረዋል፦
5፥111 ወደ *ሐዋርያትም* «በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ» *በማለት ባዘዝኩ* ጊዜ አስታውስ፡፡ *«አመንን፤ እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክር»* አሉ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى ٱلْحَوَارِيِّـۧنَ أَنْ ءَامِنُوا۟ بِى وَبِرَسُولِى قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا وَٱشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ
3:52 ዒሳ ከእነርሱ ክሕደት በተሰማዉም ጊዜ ፡-ወደ አላህ *ረዳቶቼ እነማን ናቸዉ? አለ፤ ሐዋሪያት ፡ -እኛ የአላህ ረዳቶች ነን፤ በአላህም አምነናል፤ እኛም ትክክለኛ ”ታዛዦች”* መሆናችንን፥ መስክር፥ አሉ። فَلَمَّآ أَحَسَّ عِيسَىٰትተው مِنْهُمُ ٱلْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ ۖ

ነገር ግን ከሐዋርያት ህልፈት በኃላ ያሉት ነስራኒይዎች በእርሱም ከታዘዙት ፈንታ በአላህ ላይ በመቅጠፍ “ሦስት ነው” በማለት ወሰን አልፈዋል፦
4፥171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ *በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡……. ሦስት ነው* አትበሉም፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

አላህ የኢየሱስን ቀዳማይ ተከታይ በእነዚያ ኢየሱስን በካዱት አይሁዳውያን ላይ ሲያበልጣቸው በተቃራኒው በሁለተኛው ክፍለ-ዘመን ያሉት ተከታዮቹ ግን አላህ ያልተናገረውን ምንኩስና የእርሱን ውዴታ ለመጠበቅ ፈጠሯት፦
3፥55 አላህም ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ ዒሳ ሆይ! እኔአድራጊ ወሳጂህ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፡፡ ከነዚያም ከካዱት ሰዎች አጥሪህ ነኝ *እነዚያንም የተከተሉህን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ ነኝ*፡፡ إِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَىٰٓ إِنِّى مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ إِلَىَّ وَمُطَهِّرُكَ مِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَجَاعِلُ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوكَ فَوْقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ
57፥27 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም አስከተልን፡፡ ኢንጂልንም ሰጠነው፡፡ *በእነዚያም በተከተሉት ልቦች ውሰጥ መለዘብንና እዝነትን፣ አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስና አደረግን፡፡ በእነርሱ ምንኩስናን አልጻፍናትም፡፡ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ፈጠሩዋት፡፡ ተገቢ አጠባበቋንም፤ አልጠበቋትም*፡፡ ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው፡፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡ ثُمَّ قَفَّيْنَا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم بِرُسُلِنَا وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ٱبْنِ مَرْيَمَ وَءَاتَيْنَٰهُ ٱلْإِنجِيلَ وَجَعَلْنَا فِى قُلُوبِ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُ رَأْفَةًۭ وَرَحْمَةًۭ وَرَهْبَانِيَّةً ٱبْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَٰهَا عَلَيْهِمْ إِلَّا ٱبْتِغَآءَ رِضْوَٰنِ ٱللَّهِ فَمَا رَعَوْهَا حَقَّ رِعَايَتِهَا ۖ فَـَٔاتَيْنَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنْهُمْ أَجْرَهُمْ ۖ وَكَثِيرٌۭ مِّنْهُمْ فَٰسِقُونَ

ከዒሳ ተከታዮች ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፤ ነገር ግን አላህ ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጣቸው፤ በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፤ እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን» ይላሉ፦
28፥52 እነዚያ ከእርሱ በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ *በእርሱ ያምናሉ*፡፡ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ مِن قَبْلِهِ هُم بِهِ يُؤْمِنُونَ
28፥53 በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ *እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን*» ይላሉ፡፡ وَإِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ قَالُوا آمَنَّا بِهِ إِنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّنَا إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلِهِ مُسْلِمِينَ

ልብ አድርግ “እኛ ከእርሱ ከመጽሐፉ ማለትም ከቁርአን መውረድ በፊት ሙስሊም ነበርን” ማለታቸው ምክንያታዊ ነው፤ ሙስሊም” مُسْلِم ትርጉሙ “አቢድ” عَابِدُ ማለትም “አምላኪ” አሊያም “ቃኒት” قَانِتِ ማለትም “ታዛዥ” ማለት ነው። እንደሚታወቀው የመጽሐፉ ሰዎች ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፤ አይሁዳውያን አላህ የተቆጣባቸው ሲሆኑ ክርስቲያኖች ደግሞ የተሳቱተት ናቸው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3212
ዐዲይ ኢብኑ ሓቲም እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ አይሁዳውያን የተቆጣባቸው ናቸው፤ ክርስቲያኖች የተሳቱተት ናቸው። عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْيَهُودُ مَغْضُوبٌ عَلَيْهِمْ وَالنَّصَارَى ضُلاَّلٌ ‏”‏ ‏.‏

ነገር ግን ከአይሁዳውያን ጥቂት ያልተቆጣቸው፤ እንዲሁ ከክርስቲያኖች ጥቂት ያልተሳሳቱ ነበሩ፤ እኛም ከመንገዱ እንዳንስት የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋለላቸውን መንገድ ምራን ብለን እንቀራለን፦
1፥7 የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን፣ በእነርሱ ላይ *”ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን”*፤ በሉ። صِرَٰطَ ٱلَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ ٱلْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا ٱلضَّآلِّينَ
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4475
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “ኢማሙ፦ “ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን” ባለ ጊዜ አሚን በሉ፤ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ إِذَا قَالَ الإِمَامُአላህ ‏{‏غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلاَ الضَّالِّينَ‏}‏ فَقُولُوا آمِينَ‏.

“አሚን” آمين‌‎ ማለት ተስማምቻለው “ይሁን” “ይደረግ” ማለት ነው፤ አላህ ሆይ! ” ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን፤ አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አልተበረዘምን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

መግቢያ
ሚሽነሪዎች አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ ስለራሱ በሶስተኛ መደብ “የአላህ ቃላት መለወጥ የላትም” ብሎ የሚናገረው ንግግር ለቀድሞቹ መጽሐፍት ላለመበረዝ ማስረጃ ነው ብለው መሪ ሙግት ሲያቀርቡ ለጊዜው የሚያስኬድ ቢመስልም አበሳና አሳር ውስጥ እራሳቸውን እያስገቡ መሆኑ እሙን ነው፤ ምክንያቱም የቀድሞ መጽሐፍት ለመለወጣቸው በዋዛ ፈዛዛ ሊታዩ ያማይቻሉ አንቀፆች ስላሉ፤ ለምሳሌ፦”የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ “”የሚለውጡት” ሲኾኑ” ይላልና፤ ይህንን መረጃ ሲያገኙ ደግሞ እንደ ግጭትና ተቃርኖ ለማየት ይሞክራሉ፤ እኛ የምንለው ሙሾና ፌሽታ አብረው አይሔዱም ነው፤ ግራም ነፈሰ ቀኝ ሲጀመር “መለወጥ” የሚለው ቃል ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ ሀሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፤ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፤ ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው ሐሳብ መታየት ያለበት።
ሲቀጥል የቁርአን ቅኝት የሆነው የአረብኛው ቃል “ተህሪፍ” تحريف, እና “ተብዲል” تَبْدِيل የአማርኛችን ጥበት ሁለቱንም “መለወጥ” ይበለው እንጂ ስሜቱ አንድ አይነት አይደለም፤ ይህንን ለመረዳት ጉባኤ ሆነ ሱባኤ አያስፈልግም ወደ ቁርአኑ ዘው ብሎ መግባት ብቻ ነው፦
ነጥብ አንድ
“ተህሪፍ”
“ተህሪፍ” تحريف, ማለት “ብርዘት” ማለት ሲሆን በመለወጥ የሚደረግ ብርዘት ሲሆን ይህ ጉዳይ አላህ በቃሉ ይነግረናል፦
2:75 ከነሱ የኾኑ ጭፍሮች “የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ “የሚለውጡት” يُحَرِّفُونَهُ ሲኾኑ ለናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?
4:46 ከነዚያ ይሁዳውያን ከሆኑት ሰዎች “ንግግሮችን” ከሥፍራዎቹ “የሚለውጡ” يُحَرِّفُونَ አሉ፤
5:13 ቃልኪዳናቸውንም በማፍረሳቸው ረገምናቸው፤ ልቦቻቸውንም ደረቆች አደረግን፤ “ቃላትን” ከቦታዎቻቸው “ይለውጣሉ” يُحَرِّفُونَ ።

የመጸሐፉ ሰዎች አይሁድና ክርስቲያኖች ቃሉን የለወጡት የአላህ ቃልን ከሰው ቃል ጋር በመቀላቀል መጨመርና የአላህ ቃል በመደበቅ አፖክራፋ አድርጎ መቀነስ ነው፦
3:71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! “እዉነቱን በዉሸት” ለምን *ትቀላቅላላችሁ*? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን *ትደብቃላችሁ*?

“እውነት” የተባለው ከአላህ የወረደው ኪታብ፦
34:48 ፦ጌታዬ “እውነትን” ያወርዳል፤ ሩቅ የኾኑትን ሚስጢሮች ሁሉ ዐዋቂ ነው በላቸው።

“ውሸት” የተባለው ደግሞ መጽሐፉን በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው የቀጠፉት ጭማሬ ነው፦
2:79 ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡

የነቢያችን ቅርብ ባልደረባ ኢብኑ ዓባስ”ረ.አ.” የሱረቱል በቀራ 2:79 አንቀጽ ሲፈስረው፦
ኢማም ቡሃሪ ቅጽ 3, መጽሃፍ 48, ቁጥር 850:
ኢብኑ አባስ ሲናገር፦ ሙስሊሞች ሆይ ለምን የመጽሐፉ ሰዎችን ትጠይቃላችሁ? በተመሳሳይ መጽሐፋችሁ ከአላህ ዘንድ ለነቢዩ የተወረደው ወቅታቂ ንግግርና የምትቀሩት እያለ? መጽሐፋ አልተበረዘምን? አላህ ለእናንተ የመጽሐፉ ሰዎች በእጆቻቸው በርዘው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» እንደሚሉ አውርዷል።
حَدَّثَنَا يَحْيَى بْنُ بُكَيْرٍ، حَدَّثَنَا اللَّيْثُ، عَنْ يُونُسَ، عَنِ ابْنِ شِهَابٍ، عَنْ عُبَيْدِ اللَّهِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُتْبَةَ، عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ يَا مَعْشَرَ الْمُسْلِمِينَ، كَيْفَ تَسْأَلُونَ أَهْلَ الْكِتَابِ، وَكِتَابُكُمُ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَى نَبِيِّهِ صلى الله عليه وسلم أَحْدَثُ الأَخْبَارِ بِاللَّهِ، تَقْرَءُونَهُ لَمْ يُشَبْ، وَقَدْ حَدَّثَكُمُ اللَّهُ أَنَّ أَهْلَ الْكِتَابِ بَدَّلُوا مَا كَتَبَ اللَّهُ وَغَيَّرُوا بِأَيْدِيهِمُ الْكِتَابَ، فَقَالُوا هُوَ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ، لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلاً أَفَلاَ يَنْهَاكُمْ مَا جَاءَكُمْ مِنَ الْعِلْمِ عَنْ مُسَاءَلَتِهِمْ، وَلاَ وَاللَّهِ مَا رَأَيْنَا مِنْهُمْ رَجُلاً قَطُّ يَسْأَلُكُمْ عَنِ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَيْكُمْ. 
ነጥብ ሁለት
“ተብዲል”
“ተህሪፍ” تحريف, ማለት ቃልና መልዕክትን መለወጥ መሆኑን አይተን ነበር፤ “ተብዲል” تَبْدِيل ማለት ደግሞ “ማስቀየር” ነው፤ ተብዲል የንግግርን ሃሳብ፣ የውሳኔ ቃል እና የተስፋ ቃል ማስቀየርን ያመለክታል፤ አላህ የተናገረውን የውሳኔ ቃል አሊያም የትንቢትና የተስፋ ቃል ማንም ማስቆም አሊያም ማስቀረት እንደማይችል አላህ በቃሉ ይናገራል፦
6:115 “”የጌታህም ቃላት እውነተኛና ትክክለኛ ስትኾን “ተፈጸመች”፡፡ ለቃላቱ ለዋጭ የለም” لَا مُبَدِّلَ፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡
10:64 ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም “ብስራት” አላቸው፤ “”የአላህ ቃላት “መለወጥ የላትም*لَا تَبْدِيلَ ፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
6:34 ከበፊትህም መልክተኞች በእርግጥ ተስተባበሉ፡፡ በተስተባበሉበትም ነገርና በተሰቃዩት ላይ እርዳታችን እስከመጣላቸው ድረስ ታገሱ፡፡ “”የአላህንም ንግግሮች *ለዋጭ የለም*وَلَا مُبَدَِّ፡፡

በተለይ “ተፈጸመች” እና “ብስራት” የሚሉት ቃላት የሚበሰርን እና የሚፈጸም ቃልን እንጂ በቀድሞ መጽሐፍት የተናገረውን መልእክት አያመለክትም፣ ኢማም ጦበራኒ ለሱረቱል አንአም 6፡115 የሰጡት ማብራሪያ እንዲህ ይላል፦
‹‹ለቃላቱ ለዋጭ የለም የሚለው ቃል አላህ በእርሱ መጽሀፍ ውስጥ ጉዳዩ ይከሰታል ብሎ ለመተግበሩ የሰጠው ቃል በጊዜው ከመተግበር ማንም አያግደውም እሱ እነደተናገረው ይፈጸማል ማለት ነው››
ኢማም ቁርጡቢም ተመሳሳይ ሀሳብ ያዘለ ማብራሪያቸውን እንዲህ ሲሉ ይገልጻል፦
‹‹ አልራሚኒ እንዳስተላለፉት አቡ ቀታዳ እንዲህ ይላሉ፡-ለኣላህ ፍርድ ምንም ለዋጭ የለውም የመጽሀፉ ሰዎች እንዳደረጉት ቃላቱን አንድ ሰው እንኳ ቢቀይረው የአላህ እውነተኛ ቃል ግን ከመፈጸም ወደ ኋላ አይልም የተለወጠው ቃል የሚፈጸመውን ቃል መለወጥ አይችልም፡፡››

ይህ የውሳኔ ቃል “ከሊማቱል-ከውኒያህ” ሲባል “ከሊማቱ አሽ-ሸርዒያህ” ደግሜ ወሕይ ነው፤  እንደው ሙግቱን ጠበብ ለማድረግ “ለቃላቱ ለዋጭ የለም” የሚለው ሃረግ መልእክቱን ነው ብንል እንኳን “ለቃላቱ ለዋጭ የለም” የሚለው የቀድሞ መጽሐፍትን ሳይሆን ቁርአንን ብቻና ብቻ ነው አራት ነጥብ። ምክንያት ከተባለ ማስረጀው ይኸው፦

18:27 ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፤ “ለቃላቶቹ ለዋጭ የላቸውም” لَا مُبَدِّلَ፤

“ኢለይከ” إِلَيْكَ “ወደ አንተ” የሚል ነጠላ ተውላጠ-ስም ነቢያችንን ብቻ የሚያመለክት ሲሆን ወደ እርሳቸው የተወረደው የተስፋ ቃላት ለማመልከት ደግሞ “ኢለይ” إِلَيْ “ወደ” በሚል መስተዋድድ ተጠፍንጓል፣ ወደ ነብያችን ደግሞ የወረደው ቁርአን ብቻ ነው።
ተህሪፍ እና ተብዲል በመንስኤ ሆነ በውጤት ሁለት ለየቅል የሆኑ ቃላት እና እሳቦት ናቸውና የተነሳችሁበት ስሁት የሆነ ሙግት ስህተትና ግድፈት ነው ብዬ ስል ምፀታዊ ተምኔት ሳይሆን እርምት እና ትምህርት እንድትወስዱበት ነው። አይ ሌሎችንም መጽሐፍት ያመለክታል የሚል ተሟጋች ካለ ያቀረብነውን ሙግት የሚያስተባብልበት የአውድ፣ የቋንቋ፣ የሰዋስው ሙግት ጠቅሶና አጣቅሶ ማቅረብ ይጠበቅበታል። ስለዚህ “የአላህ ቃል መለወጥ የላትም” የሚለው ሃረግ የቀድሞ መጽሐፍት ላለመለወጣቸው ማስረጃ ሊሆን አይችልም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርኣን አሻሻር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥106 *ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከእርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን*፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን አታውቅምን? مَا نَنسَخْ مِنْ آيَةٍ أَوْ نُنسِهَا نَأْتِ بِخَيْرٍ مِّنْهَا أَوْ مِثْلِهَا ۗ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

በሥነ-ጽሑፍ ጥናት "ተሕሪፍ" تَحريف ማለት "ብርዘት"corruption" ማለት ሲሆን አንድ ጽሑፍን የሚበርዘው "በራዥ" ደግሞ "ሙተሐሪፍ" تَدْعُونَ ይባላል፤ ቁርኣን የአላህ ንግግር ነው፤ በእርሱ ንግግር ላይ ጂብሪል፣ ነብያችን"ﷺ" ሶሐባዎች፣ ታቢኢይዎች፣ አትባኡ ታቢኢይዎች በእርሱ ንግግር ላይ የጨመሩት ወይም የቀነሱት አንዳችም ንግግር የለም። ቁርኣን የመጨረሻው ግህደተ-መለኮት ነው። ከነብያችን"ﷺ" በኃላ የሚመጣ ነቢይ፣ የሚወርድ ወሕይ፣ የሚላክ መልእክተኛ ስለሌለ ይህንን ቁርኣን አላህ ካወረደው በኃላ ፍጡራን እንዳይጨምሩበትና እንዳይቀንሱበት የሚጠብቀው እራሱ የዓለማቱ ጌታ አላህ ነው፦
15፥9 *እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን*፡፡ إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا ٱلذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
41፥42 *ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፤ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ لَّا يَأْتِيهِ ٱلْبَٰطِلُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِۦ ۖ تَنزِيلٌۭ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍۢ

ይህንን ከተረዳን ዘንድ በቁርኣን "ነሥኽ" የሚባል እሳቤ አለ፤ “ነሥኽ” نسخ ማለት “ሽረት”abrogation” ማለት ሲሆን ይህም ሽረት ሁለት ክፍል አለው፤ አንደኛው ክፍል “ናሢኽ” ناسخ ማለትም “ሻሪ አንቀጽ”Abrogator verse” ሲሆን ሁለተኛው “መንሡኽ” منسوخ ማለትም “ተሻሪ አንቀጽ”Abrogated verse” ነው፦
2፥106 *ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከእርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን*፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን አታውቅምን? مَا نَنسَخْ مِنْ آيَةٍ أَوْ نُنسِهَا نَأْتِ بِخَيْرٍ مِّنْهَا أَوْ مِثْلِهَا ۗ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
16፥101 *በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ዐዋቂ ነው*፡፡ «አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም» ይላሉ፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ وَإِذَا بَدَّلْنَا آيَةً مَّكَانَ آيَةٍ ۙ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يُنَزِّلُ قَالُوا إِنَّمَا أَنتَ مُفْتَرٍ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ

ይህንን እሳቤ ምሁራን "አን-ናሲኽ ወል መንሱኽ" الناسخ والمنسوخ ይሉታል፤ ይህ ሽረት በቁርኣን ሕጉን ታሳቢና ዋቢ ያረደገ ሲሆን የማህበረሰቡትን ዕድገትና የአስተሳሰብ ደረጃ፣ የጊዜውን ቅድመ-ተከተል እና ዘመነ-መግቦት”dispensation” ያማከለ ነው፣ ይህም “ተከታታይ ግህደተ-መለኮትን”progressive revelation” እሴት እና ግብአት ነው፤ አላህ የሕጉን አንቀጽ በሌላ የሕግ አንቀጽ የመሻሩ ሂደት በሁለት ይከፈላል፤ ይህንን ነጥብ በነጥብ በአጽንዖትና በአንክሮት ማየት ይቻላል፦
ነጥብ አንድ
"ነሥኹል ሑክም"
“ሑክም” حُكْم ማለት "ሕግ" ማለት ሲሆን "መትን” مَتن ማለት ደግሞ "ጥሬ-ቃል" ማለት ነው፤ "ነሥኹል ሑክም" ማለት "ሕግ" ተነሥኾ ግን "ጥሬ-ቃል" የማይነሠኽበት ማለት ነው፤ ለምሳሌ ተሻሪ አንቀጽ ይህ አንቀጽ ነው፦
2፥240 *እነዚያ ከእናንተ ውስጥ የሚሞቱ ሚስቶችንም የሚተዉ፤ ለሚስቶቻቸው ከቤታቸው የማይወጡ ሲኾኑ ዓመት ድረስ መጠቀምን ኑዛዜን ይናዘዙ፡፡ በፈቃዳቸው ቢወጡም በሕግ ከታወቀው ነገር በነፍሶቻቸው በሠሩት በእናንተ በሟቹ ዘመዶች ላይ ኃጢኣት የለባችሁም አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው*፡፡ وَالَّذِينَ يُتَوَفَّوْنَ مِنكُمْ وَيَذَرُونَ أَزْوَاجًا وَصِيَّةً لِّأَزْوَاجِهِم مَّتَاعًا إِلَى الْحَوْلِ غَيْرَ إِخْرَاجٍ ۚ فَإِنْ خَرَجْنَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ فِي مَا فَعَلْنَ فِي أَنفُسِهِنَّ مِن مَّعْرُوفٍ ۗ وَاللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4530
ኢብኑ አዝ-ዙበይር እንደተረከው፦ *"እኔም ለዑስማን ኢብኑ ዐፋል"ረ.ዐ."፦ " እነዚያ ከእናንተ ውስጥ የሚሞቱ ሚስቶችንም የሚተዉ.."2፥240 ስለዚህ ይህ አንቀጽ በሌላ አንቀጽ ተሽሯል፤ ለምንድን ነው የምትጽፈው ወይም የምትተወው? ዑስማንም፦ "የወንድሜ ልጅ ሆይ! እኔ ከቦታው ምንም ነገር አለውጥም" አለው*። قَالَ ابْنُ الزُّبَيْرِ قُلْتُ لِعُثْمَانَ بْنِ عَفَّانَ ‏{‏وَالَّذِينَ يُتَوَفَّوْنَ مِنْكُمْ وَيَذَرُونَ أَزْوَاجًا‏}‏ قَالَ قَدْ نَسَخَتْهَا الآيَةُ الأُخْرَى فَلِمَ تَكْتُبُهَا أَوْ تَدَعُهَا قَالَ يَا ابْنَ أَخِي، لاَ أُغَيِّرُ شَيْئًا مِنْهُ مِنْ مَكَانِهِ‏.‏

አላህ መትኑን ከሚነሥኸው ውጪ ሰዎች የመነሠኽ ሥልጣን እንደሌላቸው ይህ ሐዲስ ያሳያል፤ "ኢብዳል" إبـدال ማለት "ምትክ"replacement" ማለት ሲሆን የተተካበት ሻሪ አንቀጽ ደግሞ ይህ አንቀጽ ነው፦
4፥12 *ለእናንተም ሚስቶቻችሁ ከተዉት ንብረት ለእነርሱ ልጅ ባይኖራቸው ግማሹ አላችሁ፡፡ ለእነሱም ልጅ ቢኖራቸው ከተዉት ሀብት ከአራት አንድ አላችሁ፡፡ ይህም በእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው፡፡ ለናንተም ልጅ ባይኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ ለሚስቶች ከአራት አንድ አላቸው፡፡ ለእናንተም ልጅ ቢኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ ከስምንት አንድ አላቸው ይህም በርሷ ከምትናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው፡፡ ወላጅም ልጅም የሌለው በጎን ወራሾች የሚወርስ ወንድ ወይም ሴት ቢገኝ ለእርሱም ለሟቹ ወንድም ወይም እኅት (ከእናቱ በኩል ብቻ የኾነ ቢኖር ከሁለቱ ለያንዳንዳቸው ከስድስት አንድ አላቸው፡፡ ከዚህም ከአንድ የበዙ ቢኾኑ እነርሱ በሲሶው ተጋሪዎች ናቸው፡፡ ይህም ወራሾችን የማይጎዳ ኾኖ በእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው፡፡ ከአላህም የኾነን ኑዛዜ ያዛችኋል፡፡ አላህም ዐዋቂ ቻይ ነው*፡፡ وَلَكُمْ نِصْفُ مَا تَرَكَ أَزْوَاجُكُمْ إِن لَّمْ يَكُن لَّهُنَّ وَلَدٌ ۚ فَإِن كَانَ لَهُنَّ وَلَدٌ فَلَكُمُ الرُّبُعُ مِمَّا تَرَكْنَ ۚ مِن بَعْدِ وَصِيَّةٍ يُوصِينَ بِهَا أَوْ دَيْنٍ ۚ وَلَهُنَّ الرُّبُعُ مِمَّا تَرَكْتُمْ إِن لَّمْ يَكُن لَّكُمْ وَلَدٌ ۚ فَإِن كَانَ لَكُمْ وَلَدٌ فَلَهُنَّ الثُّمُنُ مِمَّا تَرَكْتُم ۚ مِّن بَعْدِ وَصِيَّةٍ تُوصُونَ بِهَا أَوْ دَيْنٍ ۗ وَإِن كَانَ رَجُلٌ يُورَثُ كَلَالَةً أَوِ امْرَأَةٌ وَلَهُ أَخٌ أَوْ أُخْتٌ فَلِكُلِّ وَاحِدٍ مِّنْهُمَا السُّدُسُ ۚ فَإِن كَانُوا أَكْثَرَ مِن ذَٰلِكَ فَهُمْ شُرَكَاءُ فِي الثُّلُثِ ۚ مِن بَعْدِ وَصِيَّةٍ يُوصَىٰ بِهَا أَوْ دَيْنٍ غَيْرَ مُضَارٍّ ۚ وَصِيَّةً مِّنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَلِيمٌ

"በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ዐዋቂ ነው" የሚለው ይህንን እሳቤ ዋቢ ያደረገ ነው፦
16፥101 *በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ዐዋቂ ነው*፡፡ «አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም» ይላሉ፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ وَإِذَا بَدَّلْنَا آيَةً مَّكَانَ آيَةٍ ۙ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يُنَزِّلُ قَالُوا إِنَّمَا أَنتَ مُفْتَرٍ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
ነጥብ ሁለት
"ነሥኹል መትን"
"ነሥኹል መትን" ማለት "ሕግ" ተነሥኾ ግን "ጥሬ-ቃል" የሚነሠኽበት ማለት ነው፤ "ኢብታል" إبـتال ማለት "ማንሳት"nullification" ማለት ሲሆን አምላካችን አላህ ጥሬ ቃሉ በማንሳት ይነሥኸዋል፦
2፥106 *ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከእርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን*፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን አታውቅምን? مَا نَنسَخْ مِنْ آيَةٍ أَوْ نُنسِهَا نَأْتِ بِخَيْرٍ مِّنْهَا أَوْ مِثْلِهَا ۗ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
87፥6 *ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም*፡፡ سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰ
87፥7 *አላህ ከሻው በስተቀር*፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡ إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ إِنَّهُ يَعْلَمُ الْجَهْرَ وَمَا يَخْفَىٰ

ነብያችን"ﷺ" ከሚወርድላቸው አንቀጽ ምንም አይረሱም አላህ ከሻው በስተቀር፤ “አላህ ከሻው በስተቀር” ማለት አላህ አንድን አንቀጽ በማስረሳት በሌላ አንቀጽ ከመለወጥ በስተቀር ማለት ነው፤ "ብናስረሳህ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ለዛ ነው የተነሰኹ አናቅጽ ሐዲስ ላይ የምናገኘው፤ ለምሳሌ አንድ ናሙና ማየት ይቻላል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 5, ሐዲስ 264:
አል-በረራዒ ኢብኑ ዓዚብ እንደተረከው፦ *“በሶላቶች እና በአስር ሶላት ላይ ተጠባበቁ” ይህ አንቀፅ ወርዶ ነበር፤ አላህ እስከሻው ድረስ እንቀራው ነበር፤ ከዚያም *አላህ ነሠኸውና፦ “በሶላቶች በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ ተጠባበቁ፡፡ ታዛዦች ኾናችሁም ለአላህ ቁሙ” የሚለውን አንቀፅ አወረደ*። عَنِ الْبَرَاءِ بْنِ عَازِبٍ، قَالَ نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ حَافِظُوا عَلَى الصَّلَوَاتِ وَصَلاَةِ الْعَصْرِ ‏.‏ فَقَرَأْنَاهَا مَا شَاءَ اللَّهُ ثُمَّ نَسَخَهَا اللَّهُ فَنَزَلَتْ ‏{‏ حَافِظُوا عَلَى الصَّلَوَاتِ وَالصَّلاَةِ الْوُسْطَى‏}‏

ሶሐባዎችም መትኑ የተነሠኸውን አንቀጾች አላህ እስከ ነሠኸው ድረስ በቂራኣታቸው ውስጥ አያካትቱም ነበር፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4481
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"ዑመር"ረ.ዐ." አለ፦ " የእኛ ምርጥ ቃሪእ ኡበይ ነው፤ የእኛ ምርጥ ዳኛ ዐሊይ ነው፤ ሆኖም ግን የዑበይን አንዳንድ ንግግር እንተወው ነበር፤ እርሱም፦ "ከአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ከምሰማው ምንም አልተውኩም፤ አላህ እንዳለው ከሚረሳው በቀር፦ "ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ عُمَرُ ـ رضى الله عنه ـ أَقْرَؤُنَا أُبَىٌّ، وَأَقْضَانَا عَلِيٌّ، وَإِنَّا لَنَدَعُ مِنْ قَوْلِ أُبَىٍّ، وَذَاكَ أَنَّ أُبَيًّا يَقُولُ لاَ أَدَعُ شَيْئًا سَمِعْتُهُ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَقَدْ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى ‏{‏مَا نَنْسَخْ مِنْ آيَةٍ أَوْ نَنْسَأْهَا‏}‏

አምላካችን አላህ አንቀጹን ሽሮ ከሚያስረሳው በቀር ሰዎች በግላቸው የቁርኣንን አንቀጽ የቀነሱበት የጨመሩበት የለም። ለነብያችን"ﷺ" የሚወርደው ቁርኣን ብቻ ሳይሆን ሐዲሱል ቁድስ እና ሐዲሱል ነበውይም ጭምር ነው፤ ነብያችን"ﷺ" በዐቂዳህ እና በፊቅህ ነጥብ ላይ የሚናገሩት ወሕይ ነው፦
53፥4 *እርሱ ንግግሩ የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም*፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ