Tutorial for highschool students
174 subscribers
24 photos
25 videos
13 files
98 links
Educational channel
You can dm me at:
t.me/Abboud1088
Download Telegram
ሰላም
(ስላረፈድኩ ይቅርታ)

ነገ ረቡዕ (10/03/2017 ዓ.ል.) ጠዋት 4:30 ከ10ኞች ጋር ክላስ #ይኖረናል።

መልዕክቱን መምጣት ለሚፈልግና ለሚመቸው አድርሱ።

Main Channel
https://t.me/Werabesps
.
Tutorial Channel
https://t.me/WSPSTutorial
.
DM
@itutor_w
👍5🤯1😭1
ሰላም

ነገ ሐሙስ (11/03/2017 ዓ.ል.) ጠዋት 4:30 ከ10ኞች ጋር ክላስ #ይኖረናል።

መልዕክቱን መምጣት ለሚፈልግና ለሚመቸው አድርሱ።

Main Channel
https://t.me/Werabesps
.
Tutorial Channel
https://t.me/WSPSTutorial
.
DM
@itutor_w
👍4🔥1
ሰላም

ነገ ረቡዕ (25/03/2017 ዓ.ል) ከጠዋቱ 4:00 የጠራችሁ መምህር በመኖሩ ከኔ ጋር ክላስ አይኖራችሁም።

.
Main Channel
https://t.me/Werabesps
.
Tutorial Channel
https://t.me/WSPSTutorial
.
DM
@itutor_w
.
😭4👍2
ለአጋማሽ ፈተና እንደደረሳችሁ ለመልካም ውጤት ያብቃችሁ።
በፈተና ወቅት
አይናችሁን መልስ ፍለጋ ስልክ ከማየት፣ አንገታችሁን መልስ ፍለጋ ወዲህ ወዲያ ከማለት፣ እጃችሁን ህጋዊ ያልሆነ መልስ ለመኮረጅ ቁራጭ ወረቀት ከመቀበል፣ እግራችሁን ለኩረጃ በማንሳት መምህር ወደማይፈቅደው ቦታ ከመሄድ፣ ወረቀታችሁን በኩረጃ ምክንያት ከቀይ ቀለም ፊርማ ይሰውራችሁ።

የፈተና ደንብ ከማያሟላ ምግባር ተቆጠቡ።


መልካም ፈተና!
👍6
የአጋማሽ ፈተናው ሁላችሁም አንብባችሁ እንደሰራችሁና አሪፍ እንደነበር አልጠራጠርም።
ባነበባችሁት ልክ ውጤታችሁ ያማረ እና እውቀታችሁ የበዛ እንዲሆን ተመኘሁላችሁ።

መልካም የቅዳሜ ምሽት!
👍3❤1
ሰላም!

ነገ ረቡዕ በህመም ምክንያት ከይቅርታ ጋር ክላስ አይኖረንም።
😢5😁1
ሰላም

ነገ ሐሙስ (10/04/2017 ዓ.ል.) ከጠዋቱ 4:30 ከ10ኞች ጋር ክላስ #ይኖረናል።

መልዕክቱን መምጣት ለሚፈልግና ለሚመቸው አድርሱ።

Main Channel
https://t.me/Werabesps
.
Tutorial Channel
https://t.me/WSPSTutorial
.
DM
@itutor_w
ሰላም ለሁላችሁም

ትምህርት ዘርፍ ላይ እንደተሰማራ ግለሰብ ይህን ሰሞን አንድ ነገር አስቤ፤ ከሐሳብም ከፍ ብዬ በተግባር ወደናንተ ብቅ ብያለሁ።

አሁን ባለሁበት ጊዜ አቅሜ በፈቀደው መጠን፤ ወደፊትም አቅሜ በሚፈቅደው መጠን ትምህርትና ተማሪዎች ላይ በሰፊው የመስራት እቅድ አለኝ። ከመምህራን ጎን በመሆን ተማሪዎችን ማገዝ ከምደሰትባቸው ስራዎች አንዱ ነው። የመምህራንን ድካም መቀነስና የተማሪዎችን እውቀትና ውጤት ለማሻሻል ካለን ጊዜ መስጠት ድካም የበዛበት፤ ነገር ግን ጥሩ ውጤትና የህሊና ደስታ የሚገኝበት መልካም ስራ ነው።

ይህን የደስታ ምንጬን ከናንተው ጋር በመጣመር ሰፋ አድርገነው እንድንቀጥል ስላሰብኩ ወራቤ እና አካባቢዋ (ወደፊት በሰፊው አገር አቀፍ የምናደርገው ይሆናል) ላይ ያሉ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የመማር ማስተማር ሂደትን የሚያሳልጡ አካላትን በቴሌግራም ሰብሰብ እያደረግን ነው። የቴሌግራም ቻነልና ግሩፕ የከፈትኩ በመሆኔ ስልጤ ዞን ውስጥ ያሉ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የመማር ማስተማር ሂደትን የምታሳልጡ አካላት እንድትቀላቀሉኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

በቻነሉ ከላይ ወደታች መረጃዎች ይተላለፋሉ። ከተለያዩ ትምህርት መምሪያ አካላት (ፌዴራል፣ ክልል፣ ዞን፣ ከተማ አስተዳደር) የሚተላለፉ መልዕክቶች፣ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚተላለፉ መልዕክቶች፣ አጠቃላይ ክፍለ ጊዜያት፣ አጠቃላይ የፈተና ፕሮግራሞች፣ ለመምህራንና ተያያዥ ስራዎች የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎች፣ የተማሪ እና የመምህራን መጻሕፍት፣ አጋዥ መጻሕፍት፣ የተለያዩ አጋዥ ቪድዮዎች... በአጠቃላይ ከተማሪ እና ትምህርት ጋር ተያያዥ የሆኑ መረጃዎች የሚተላለፉበት ይሆናል።

በግሩፑ ደግሞ መረጃዎች ከታች ወደ ላይ የሚደርሱ ይሆናል። ተማሪዎች ሐሳቦቻቸውን የሚገልጹበት፣ መምህራን ግለ-ምልከታቸውን የሚያጋሩበት፣ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ያሉ መረጃዎች የሚሰበሰቡበት... በአጠቃላይ  ከተማሪ እና ትምህርት ተያያዥ የሆኑ መረጃዎች ወደሚመለከተው አካል የሚደርሱበት፣ በተጨማሪም ዳጎስ ያሉ ሽልማቶች የተካተቱበት የጥያቄና መልስ ውድድር ይኖረናል።

እነዚህን ቻነልና ግሩፕ #እንድትቀላቀሉ፣ #የሂደቱ_አካል_እንድትሆኑ እና #ለሌሎችም_እንድታጋሩ በአክብሮት እጠይቃለሁ። ለትብብራችሁም ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው።

ቻነል
https://t.me/WerabeStudents

ግሩፕ
https://t.me/WorabeStudents
👍1
ሰላም

ከይቅርታ ጋር ነገ ረቡዕ (16/04/2017 ዓ.ል) ከኔ ጋር ክላስ አይኖራችሁም።

.
Main Channel
https://t.me/Werabesps
.
Tutorial Channel
https://t.me/WSPSTutorial
.
DM
@itutor_w
.
👍4🤷‍♀1🎉1
ሰላም

ከይቅርታ ጋር ነገ ሐሙስ (17/04/2017 ዓ.ል) ከኔ ጋር ክላስ አይኖራችሁም።

.
Main Channel
https://t.me/Werabesps
.
Tutorial Channel
https://t.me/WSPSTutorial
.
DM
@itutor_w
.
🤷‍♂2🎉1
ሰላም

ከይቅርታ ጋር በግል ጉዳይ በዚህ ሳምንት ከኔ ጋር ክላስ አይኖራችሁም።

.
Main Channel
https://t.me/Werabesps
.
Tutorial Channel
https://t.me/WSPSTutorial
.
DM
@itutor_w
.
👍2
እንኳን ለአንደኛው መንፈቀ-ዓመት ማጠቃለያ ፈተና በሰላም አደረሳችሁ።

ለማጠቃለያ ፈተና እንደደረሳችሁ ፈተናውን በሰላም አስጨርሶ ለመልካም ውጤት ያብቃችሁ።
በፈተና ወቅት የፈተና ደንብ ከማያሟላ ተግባር ተቆጥባችሁ ፈተናችሁን እንድትጨርሱ እመኛለሁ።

ለሁላችሁም መልካም ፈተና!
Forwarded from English For Ethiopia - በቀላሉ (S A M I)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from English For Ethiopia - በቀላሉ (S A M I)
🇺🇸 American English Vs British English 🇬🇧

🇺🇸 Diaper 💬 Nappy 🇬🇧
🇺🇸 Sidewalk 💬 Pavement 🇬🇧
🇺🇸 Sweater 💬 Jumper 🇬🇧
🇺🇸 Soccer 💬 Football 🇬🇧
🇺🇸 Cookie 💬 Biscuit 🇬🇧
🇺🇸 Closet 💬 Wardrobe 🇬🇧
🇺🇸 Pants 💬 Trousers 🇬🇧
🇺🇸 Sneakers 💬 Trainers 🇬🇧
🇺🇸 Yard 💬 Garden 🇬🇧

❤️ @English_Ethiopian ✅
🌐 Follow Us
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ክብር ለመምህሮቻችን!
ለኛ ማለፍ ወድቀው ለቀሩ
ለኛ መፍካት የኮሰመኑ
ለኛ ማደግ ለወደቁ

ከክብርና ምስጋና ውጭ ምንም ላላደረግንላቸው መምህራን ክብር ለነርሱ ይሁን።
Forwarded from English For Ethiopia - በቀላሉ (Sam G)
Mr. Mister ሚስተር
አቶ

Ms. ሚዝ
ላላገቡ ወጣት ሴቶች

Miss ሚስ
ላላገቡ ልጃገረዶች

Mrs. Misuss ሚስስ
ላገቡ ሴቶች

አዲስ ነገር ካወቃቹ React አድርጉ ካላወቃችሁም አድርጉ 😉

❤️ @English_Ethiopian ✅
🌐 Follow Us
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የሳቀ ሁሉ ደስተኛ አይደለም !!

(ዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)

ሁሌም ስታገኙት ደስተኛና ሳቂታ የነበረ ሰው በድንገት ራሱን አጥፍቶ ሞተ ሲባል ሰምታችሁ ታዉቃላቹ ?

ብዙ ሰዉ የድብርት ህመም ደስተኛ አለመሆን ፣ የሀዘን ስሜት ፣ ተስፋ መቁረጥ እና የመሳሰሉት ብቻ ይመስለዋል። አንዳዴ እየሳቁ እና እየተጫወቱ በከባድ የድብርት ህመም የሚሰቃዩ ሰዎች አሉ። በህክምናዉ (atypical depression) ይባላል።

- አብዛኛዉን ጊዜ ደስ የሚያሰኝ ነገር ሲያገኙ ለተወሰነ ጊዜ መደሰት ከዛም መልሶ የሀዘን እና የባዶነት ስሜት ዉስጥ መግባት፣
- ምግብ ፍላጎት እና ክብደት መጨመር፣
- ከሳምንታት በላይ ቀኑን ሙሉ መድከም እና እንቅልፍ ማብዛት፣
- በትንንሽ አስተያየቶች እና ትችቶች መሰበር፣
- የዘወትር ተግባራትን ለመከወን መቸገር የድብርት በሽታ ሌላኛዉ መልክ ሊሆን ይችላል።

ስለዚህ የሳቀ ሁሉ ደስተኛ አይደለም፤ ምናልባት ከሳቁ ጀርባ የተደበቀ የባዶነት እና የሀዘን ስሜት ይኖራልና እርስ በእርስ እንጠያየቅ።

(ይህ የግንቦት ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ የአዕምሮ ጤና ግንዛቤ ወር ነው)

#የአዕምሮ_ጤና_ግንዛቤ_ወር
#ዶክተር_ኃይለልዑል_መኮንን
#MentalHealthAwarenessMonth

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሳቀ ሁሉ ደስተኛ አይደለም !! (ዶክተር ኃይለልዑል መኮንን) ሁሌም ስታገኙት ደስተኛና ሳቂታ የነበረ ሰው በድንገት ራሱን አጥፍቶ ሞተ ሲባል ሰምታችሁ ታዉቃላቹ ? ብዙ ሰዉ የድብርት ህመም ደስተኛ አለመሆን ፣ የሀዘን ስሜት ፣ ተስፋ መቁረጥ እና የመሳሰሉት ብቻ ይመስለዋል። አንዳዴ እየሳቁ እና እየተጫወቱ በከባድ የድብርት ህመም የሚሰቃዩ ሰዎች አሉ። በህክምናዉ (atypical depression)…
<< የሳቀ ሁሉ ደስተኛ አይደለም! >>

ብንተዋወቅም ባንተዋወቅም ይህ መልዕክት ለሁላችሁም ነው።

ልባችሁ ውስጥ ታፍኖ የተቀመጠ፣ ለማን ብነግር ያዳምጠኛል፣ ማን የመፍትሔ ሐሳብ ይሰጠኛል፣ እንደው ሐሳብ ባይሰጠኝ እንኳ የልቤን ተናግሬ የምተነፍስበትን ሰው ከየት ላግኝ፣ ጭንቀትና ድባቴ ሊጨርሰኝ ነው...... ብላችሁ ያሰባችሁ ሰዎች በዱዐ ለአላህ ከመንገር ባሻገር ልታማክሩት የፈለጋችሁት ሰው ካለ እኔን ማናገር ትችላላችሁ። ፈራጅም ወቃሽም ሳልሆን ለመፍትሔ እስከመጨረሻው ከጎናችሁ ነኝ።

ችግራችሁ ችግሬ ነው። ጭንቀታችሁ ጭንቀቴ ነው። የፈለጋችሁትን ነገር ልታወያዩኝ ትችላላችሁ። መፍትሔ ባናገኝ እንኳ ሐሳብ በመለዋወጣችን ብቻ እረፍት እናገኝበታለን።

ነቢዩላህ ዩሱፍ (ዐለይሂ ሰላም) ጉድጓድ ውስጥ የተወረወረው፣ ባሪያ ሆኖ ተሽጦ በባርነት ያደገው ከአመታት በኋላ የገዢዎቹ ንጉስ ሊሆን ነውና የታገሰ የትዕግስቱን ጣፋጭ ፍሬ ይቀምሳል። አንተም አብሽር። አንቺም አብሽሪ።

ሐሳብ ለመለዋወጥ፦ @Abboud1088
Forwarded from Tikvah-University
ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይዘጋጁ!

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡

ለሀገር አቀፍ ፈተናው እየተዘጋጁ ነው?
ተፈታኝ ተማሪ ከሆኑ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ለፈተናው በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችሉ ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ።

በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ የቲቶርያል ቪዲዮዎችን ለማግኘት 👇
https://examinfo.moe.gov.et/guides

@tikvahuniversity
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam

በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 608 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ/ም የሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ላይ 608 ሺህ ተማሪዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ፈተናው በወረቀት እና በበየነ መረብ ይሰጣል።

ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች እንደ ቀደሙት ዓመታት ሁሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ይወስዳሉ።

ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ ፦
- በዩኒቨርሲቲዎች፣
- በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች፣
- በጤና እና መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች
- በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ባሉ ኮምፒዩተሮች ይፈተናሉ። ተማሪዎቹ ግቢ ማደር ሳይጠበቅባቸው ከቤታቸው እየተመላለሱ ነው ፈተናውን የሚወስዱት።

በበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና በሁለት ዙር ሲሆን ይህም የሆነው በበይነ መረብ የመፈተን አቅምን እና የተፈታኝ ተማሪዎችን ቁጥር ለመጨመር እንዲሁም ያለውን የመሰረተ ልማት አቅም ለማሳደግ እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኤፍ ኤም ሲ በሰጠው ቃል አስረድቷል።

#Ethiopia #NationalExam #Grade12 #ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia